cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች Facebook : bit.ly/42rUuKj WhatsApp : bit.ly/Huleadis_whatsapp YouTube : bit.ly/3p7kj3N Twitter : bit.ly/3NVMRrB Telegram: bit.ly/Huleadis_tele ለጥቆማ ና አስተያየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ ተከታዮን አድራሻ ይጠቀሙ bit.ly/3VMy7x7 ወይም +251939758767

Show more
Advertising posts
3 208Subscribers
No data24 hours
-127 days
-2630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከታጣቂዎች ጋር ለመነጋገር “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች ገለጸ ከመንግሥት ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ ታጣቂ ቡድኖች “ነፍጣቸውን ወደ ጎን አድርገው” ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲነጋገሩ “የሰላም መንገድ” እንደሚያመቻች የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ። የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን “ሁሉም አሸናፊ ይሆንበታል” ለሚለው ምክክር ከታጣቂ ኃይሎች ጋር የመነጋጋገር ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ቢገልጽም፤ ለዚህ ውይይት ግን ታጣቂዎች ‘ነፍጥን ማስቀመጥ’ አለባቸው ብሏል። ታጣቂዎች ነፍጣቸውን አውርደው ለመነጋገር ከመንግሥት ስጋት እንዳለባቸው ያነሳሉ ሲሉ የገለጹት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፤  እስካሁን የኮሚሽኑን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ታጣቂ ኃይሎች እንደሌሉ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ከታጣቂዎች ጋር ተገናኝቶ ለመነጋገርና ስጋቱን ለመቅረፍ “የሰላም መንገድ” (ደኅንነት ዋስትና) እንደሚያመቻች ፕ/ር መሥፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል።      
Show all...
ዛሬ በሚጠናቀቀው የአክሲዎን ሽያጭ አማራ ባንክ በሰነደ መዋእለ ንዋይ  ገበያ (Securities Exchange) ላይ ከግል ኢንቨስተሮች ከፍተኛ ባለድርሻ የሚያረገውን አክሲዎን ገዛ። አማራ ባንክ ከፍተኛውን መዋዕለ ነዋይ በመመደብ የ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ መግዛቱን ገልጿል። ባንኩ የሰነደ መዋዕለ ገበያን ላይ በ 90.6 ሚሊዮን ብር ከፍተኛዉን ድርሻ የገዛ የግል ኩባንያ መሆን ችሏል። ይህን ተከትሎ የአክሲዮን ግዢን  የመፈፀመ አምስተኛዉ ባንክ ሆኗል። ካፒታል ገበያን በኢትዮጵያ ለማቋቋም ድርሻ ከገዙት ባንኮች ዉስጥ እስካሁን 308.1 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል Capital
Show all...
ትርጉም ያሻዋል
Show all...
የሆቴሎች የኮከብ ደረጃ ይፋ ተደረገ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ያስቀመጣቸውን አስገዳጅ መስፈርቶች ላሟሉ 31 ሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ ውጤታቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል:: በ2014 እና 2015 ዓ.ም ምዘና ከተደረገላቸው 64 ሆቴሎች መካከል ሰባቱ ባለ 4 ኮኮብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን፤ ዘጠኝ ሆቴሎች ደግሞ የ3 ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል:: አምስት ሆቴሎች የ 2 ኮከብ እና ስምንት ሆቴሎች ባለ 1 ኮኮብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን፤ ሁለት ሆቴሎች ደግሞ ከደረጃ በታች ሆነዋል። እነዚህ ሆቴሎች በአዲስ አበባ፣ ኦሮምያ ክልል ቢሾፍቱ እና አዳማ ከተሞች የሚገኙ ናቸው:: የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የደረጃ ምደባው ሆቴሎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ብቃት እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ፣ በቅርበት ካሉ ተፎካካሪ ሀገራት ጋር ያላቸውን አቅም በማሳየት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ገልፀዋል::
Show all...
አሌ ማለያው በክብር ተሰቅሏል🥹 ባህርዳር ከነማዎች ወንድማቸውን አለልኝ አዘነን ሽኝት በዛሬው እለት በትውልድ ቦታው የተገኙ ሲሆን እጅግ አስደንጋጭ በሆነው የቡድን አጋራቸው ፣ ጓደኛቸው እና ወንድማቸውም ጭምር ማጣት ምክንያት ከባድ ጊዜን እያሳለፉ ይገኛሉ። የባህርዳር ከነማ እግርኳስ ክለብም ለዚሁ ኮከባቸው ክብር በማሰብ ይለብሰው የነበረውን የ23 ቁጥር ማለያ በክለቡ እንዳይለበስ እና በክለቡም ታሪክ በክብር እንዲቀመጥ በመወሰን ለወንድማቸው ያላቸውን ክብር አሳይተዋል። Yonas Amare
Show all...
የኃይል መቋረጥ የተፈጠረው ከኃይል ማመንጫዎች የሚመነጨውን ኃይል ወደ ግሪድ የሚያስገባበት ሥርዓት ላይ ባጋጠመ ችግር ነው! የተቋሙ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሞገስ መኮንን ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ችግሩ በምን ምክንያት እንደመጣ እስካሁን አለመታወቁን ገልጸዋል። አሁን ባለው ሁኔታ አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ኃይል መልሶ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል ነው ያሉት። በባህርዳር እና አካባቢ ላይ ከበለስ ኃይል ማመንጫ ኃይል ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ በመፈጠሩ እዛ አካባቢ የኃይል መቋረጥ አለመከሰቱን የገለጹት ኃላፊው በሌላው የሀገሪቱ ክፍል የኃይል መቋረጥ ሲያጋጥም ደግሞ መልሶ ኃይል ለማገናኘት ጊዜ ይወስዳል ብለዋል። ይሁን እንጂ በተደረገው ርብርብ ሁለት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ መልሶ ማገናኘት መቻሉን አመልክተዋል። እንደዚህ ዓይነት የኃይል መቆራረጥ ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥም አስታውሰው አሁን ላይ ግን በዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ የሚያጋጥምበት ሁኔታ እንዳለ ገልጸዋል። አሁን ላይ በብዙ አካባቢዎች ማገናኘት ስለተቻለ የቀሩት አካባቢዎች ላይ መልሶ ለማገናኘት ብዙም ጊዜ እንደማይወስድ ጠቁመዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ከቀኑ 9:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ እንደነበር ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወቃል።
Show all...
👍 1
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድጋሚ የሚያገረሽበት ዕድል ዝግ ነው በማለት ትናንት ከቻይናው ሲጂቲኤን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ያለፈው ጦርነት የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት አልነበረም ያሉት ጌታቸው ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርና የትግራይ ሕዝብ ድጋሚ ጦርነት እንዳያገረሽ የተቻላቸውን ጥረት ኹሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ጌታቸው ይህን ያሉት ፣ በአላማጣ አቅራቢያ በትግራይ ኃይሎች እና ባካባቢው ሚሊሻዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በተደረገ ማግስት ነው መባሉን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል። አቶ ጌታቸዉ ይህንን ይበሉ እንጂ አብን፣ ሕወሃት ለአዲስ ዙር ጦርነት ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት የሕወሃት ተዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ሳይፈቱና መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጸጥታ ለማስከበር ሳይሠማራ ሕወሃት ለሌላ ዙር ጦርነት ፕሮፓጋንዳ በመለፈፍ ተጠምዷል ብሏል። የፌደራሉና የአማራ ክልል መንግሥታት የሕወሃትን የጠባጫሪነት ቅስቀሳ በትኩረት እንዲከታተሉና በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት "በንግግር" እና "ድርድር" እንዲፈታም አብን ጠይቋል። የአማራ ሕዝብ ሕወሃት ሊያደርስበት የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት እንዲቆም የጠየቀው ፓርቲው፣ የትግራይ ሕዝብም ራሱን ከሕወሃት ቀንበር እንዲያላቅቅ ጥሪ አድርጓል።
Show all...
👍 1
በቅርቡ ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኃላፊነት በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን የለቀቁት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአለም አቀፉን ተቋም በዋና ዳይሬክተርነት ተቀላቀሉ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ትኩረቱን በቀርከሃ ምርት፣ የተራቆተ መሬት ወደ ነበረበት በመመለስ፣ በአቅም ግንባታ ስራዎች እና በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ላይ ያደረገዉን አለምአቀፍ ድርጅት ‘International Bamboo and Rattan Organization (INBAR)’ ዋና ዳይሬክተር በመሆን መቀላቀላቸውን ተቋሙ አስታዉቋል። የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ላለፉት ከአንድ አመት በላይ በሃላፊነት የነመሩት አምባሳደሩ ዋና መስሪያ ቤቱን በቻይና አድርጎ ኢትዮዮጵያን ጨምሮ ከ50 በላይ ሀገራት ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ዘላቂ ልማትን በማበረታታት እየሰራ በሚገኘው አለምአቀፉ ተቋም መቀላቀላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በተለያዩ ሀገራት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ኢትዮጵያን ማገልገላቸዉ የሚነገረዉ አምባሳደር ተሾመ በቀድሞው መንግስት አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡ አምባሳደር ተሾመ የ INBAR ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አሊ ምቹሞ የአምስት አመት የስራ ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከቀጣዩ ሰኞ መጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሏል ። ካፒታል ጋዜጣ
Show all...
በ #ቀይ_ባሕር የሚፈጸሙ ጥቃቶች በ #ኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ አንቅስቃሴ ላይ ችግር መፍጠራቸው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ፤ በቀይ ባሕር የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ትልልቅ የመርከብ ኩባንያዎች ወደ #ጅቡቲ ወደብ ሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በማቆማቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና የሚወጡ ጭነቶች እንዳይገቡና እንዳይወጡ ችግር ሆኗል ሲል ገልጿል፡፡ አጓጓዥ መርከብ ድርጅቶች በአሁኑ ሰዓት ወደ ጅቡቲ መምጣት ቀንሰዋል ብሎም አቁመዋል ያለው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘም በተለይ የኢትዮጵያን #ቡናን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት የአገልግሎት ክፍተት እንዳይፈጠር የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ፤ የራሱን መርከቦች በማሰማራት እና ምልልሳቸውን በመጨመር ጭነቶች ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቋል፡፡ ድርጅቱ የተለያዩ የወጪ ንግድ ጭነቶችን ወደ #ቻይና ቲያንጂ እና ሻንጋይ /ታይካንግ/ ወደቦች ወደ #ህንድ ሙንድራ እና ናሃቫሼቫ ወደቦች እንዲሁም ወደ ተባበሩት #አረብ ኤምሬት ጀበል አሊ እና ሻርጃ ወደቦች በመደበኛነት በማጓጓዝ ላይ መሆኑን በመግለጽ፤ ላኪዎች፤ ቡና እና ሌሎች የወጪ ንግድ ጭነቶችን የድርጅቱ መርከቦች በሄዱባቸው ወደቦች ማጓጓዝ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡ ከቅርብ ግዚ ጀምሮ የየመን ሁቲዎች በቀይ ባሕር በሚተላለፍ መርከብ ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየፈጸሙ ይገኛል። የንግድ መርከብ ላይ በሚፈጽሙት የሚሳዔል ጥቃቶች የሰዎች ህይወት ማለፉና በርካታ ንብረቶች መውደማቸው ይታወቃል።
Show all...
👍 2
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!