cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍቅርና ተስፋ

ተስፋ ማለት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብርሃን አለ ብሎ ማመን ነው። ተስፋ ማለት ወደ ባህር እየተወረወሩ በሆነ ተአምር እንደ ሚድኑ ማመን ነው ፍቅር ማለት ፍፃሜው የሚያምር ቅርብ ማንነትንና ግልፅነትን የሚያስተምር...ርህራሄና ለሰው ማዘንን በልብ የሚያኖር ከፈጣሪ የሚገኝ ፀጋ ነው። ፍቅር ያለ እምነት ነፋስ ላይ እንደ ተቀመጠ ሻማ ነው።

Show more
Advertising posts
247Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከደን የሚኖር አንድ ቁራ በሕይወቱ ተደሳች ነበር። ግን አንድ ቀን ዳክዬ ሲመለከት "ይህች ዳክዬ በጣም ነጭ ነች። እኔ ደግሞ ጥቁር ነኝ። ይህቺ ዳክዬ በእውነት ከአዕዋፋት የምድራችን ተደሳች መሆን አለባት" ሲል አሰበ። እናም ሀሳቡን ለወ/ሪት  ዳክዬ ገለጠላት። "በእርግጥ ሁለት ቀለማትን የታደለው በቀቀንን አስካየሁት ጊዜ ድረስ ተደሳች ወፍ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር። ቢሆንም አሁን በቀቀን ከአዕዋፋቶች ተደሳች እንደሆነ አስባለሁ" ስትል መለሰችለት። ቁራም አቶ በቀቀንን ቀርቦ ቢያናግረው "ፒኮክን ማየት እስከምችል ወቅት ድረስ በጣም ደስተኛ ሕይወት እኖር ነበር። እኔ ሁለት ቀለሞች ሲኖሩኝ ፒኮክ ግን አዕላፍ ቀለማት ታድላለች" ሲል አብራራለት። አሁንም ቁራ ከመካነ-አራዊት (zoo) ወ/ሪት ፒኮክን ሲጎበኝ በብዙ ሰዎች እንደምትጎበኝ ተመለከተ። ጎብኚዎቹ ከሄዱ በኋላ ወደ ፒኮኳ ቀርቦ "ውዷ ፒኮክ ሆይ! በጣም ታምሪያለሽ። ሰርክ ሺ ሰዎች መጥተው ይጎበኙሻል። ነገር ግን እኔን ሲያዩኝ (ሲያገኙኝ) በቶሎ እሽ ብለው ወዲያ ያበሩኛል። ይመስለኛ ከየብስ ተደሳች ወፍ አንቺ ነሽ" አላት። "ሁሌም በጣም ቆንጆ እና ደስተኛ ወፍ አድርጌ ራሴን አስብ ነበር። ዳሩ ግን በቁንጅናዬ ምክንያት በዚህ በመካነ-አራዊት ውስጥ ታሰርኩኝ። እናም በጥንቃቄ መካነ-አራዊቱን ሳጠና ከአዕዋፋት ውስጥ ቁራ ብቻ በወፍ ጎጆ ውስጥ እንዳልተያዘ ተረዳሁኝ። ያለፉትን ቀናት ቁራን ብሆን ኖሮ በደስታ የትም መብረር እችል ነበር ብዬ አስባለሁ" ስትል መለሰችለት። ፧ "የታደልነውን ብንገነዘብ ኖሮ ሁላችንም ስኬታማ ሰዎች መሆን ይቻለን ነበር" @tloveandhope
Show all...
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹 የራሳችን ፊደል የራሳችን ቁጥር፣ የራሳችን ቋንቋ የቃላት ድርድር። አቦጊዳ ብለን ሀ.ሁ.ን ስንጀምረው ፣a.b.c.d ገባን ገና ሳንጨርሰው። ከማያልቅ ጎተራ የሚያልቀውን መረጥን፣ ከሚያመራምረው እርቀን ሄደናል፣ የአባቶቻችንን ሚስጥራት ትተናል። ነጭ ነጭ እያልን ሌላ ፈልገናል፣ ብራናውን ትተን ወረቀት አይተናል  ። ይሄኛውን ትተን ያኛውን መረግን፣ የሰው ቤት አንኳክተን ቆመን ለመለመን። ይሄው ትተነዋል የኛን በሰመመን፣ ተውት ይሄንማ ይሄንማ ተውት፣የሰው ከበለጠ የራስን ትተውት።ሳያዩት ነው እንጂ ይሄስ መች አነሰ፣የተለቀ መስሎት ነው እንጂ እያነሰ፣የረቀቀ መስሎት ነው እየኮሰሰ።ያተረፈ መስሎት ነው እየከሰረ፣የራስ አስቀምጦ የሰው የዘወረ።a.b.c.d ብሎ የመጠቀ መስሎት፣ቋንቋውን ተናግሮ የተማረ መስሎት።የኛኑ ኖሩአላ አ.ቦ.ጊ.ዳን እረስቶት፣የኛኑ ኖሩአላ ሀ.ሁ.ንም እረስቶት፣ቅኔ ነበር እንጂ እንቢ አለ ተሰቶት።በእጅ እንደያዙ ት ነገሩስ ሆኖብን፣ወዲያ ማዶ እያየን የኛ እንዳይጠፋብን።መቸስ ሰው አያየው አይኑ ስር ያለውን፣በበረከት ፀጋ በቅኔ የተሞላውን፣በሰማይ የታየው በምድር ያለውን።ምንድነው የያዘን ከቶ የጎተተን፣የኛኑ እንዳናይ አርጎ ያራቆተን፣እስኪ ማነው ማነው እረ የወተወተን።በእጅ እንደያዙት ሆኖብን ነገሩ፣መዳብ ነው እያልነው ሲኖር በሃገሩ። ስልጣኔ መሠል እንዲ ያደረገን፣ማወቁም መሠለኝ ወደታች ያረገን።እግር እያለን ኖሮ በዳዴ ሚያስኬደን፣እጅ እያለን ኖሮ መጉረስ ያስጠበቀን፣አፍ እያለን ኖሮ ማውራት ያስጠበቀን።ጤነኛ ሁነን ሳለ ድክም ድክም የሚያረገን፣ሳንፈልግ ቀርተን ነው ወንዝ ያላሻገረን።#ብንፈልገውማ ብንፈልገውማ።ወንዙ ትንሽ ነበር ውቅያኖስ ቢሠፋ፣ሃገር ትንሽ ነበር ብሔር ነው የሠፋ።ከቶ አለማወቅ ነው ታሪክ የሚያስጠፋው፣የኋላው ሲኖር ነው የፊቱ ሚኖረው።ሀ--ግዕ ዝ እያልን ያኔ እንዳልበራን፣a.b.c.d ብለን ታዲያ ለምን ጠፋን።ጠፋን አሉ ጠፋን ልክ እንደ ጨለማ፣የሚያደርሰን መስሎን ሄድን በጠማማ፣#ብንፈልገውማ ብንፈልገውማ።የሚያደርሰን ነበር ከከፍታው ማማ፣የምናየውማ ብርሃን ነበረ ጠፍቶልን ጨለማ፣የራስ ንቆ የሰው መመኘት፣ ባህር ወርዶ ወድቆ መገኘት።ሻማ እያበሩልን መሠለን ብርሃን፣ሌላ እንፈልጋለን በእጃችን ይዘን።ፊደሉ በጥበብ ቁጥር በቀመር፣ሚስጥሩ ማይገኝ የማይመረመር።       @tloveandhope
Show all...
ብቃትን ፍለጋ! አንድ ጊዜ ፈጣሪ ሰውን ያላካተተ ስብሰባን ጠራና ፍጥረትን ሁሉ ሰብስቦ አንድን ጥያቄ ጠየቃቸው፣ ይላል አንድ ምንጩ ያልታወቀ አፈ-ታሪክ፡፡ ጥያቄው እንዲህ የሚል ነበር፡- “ለነገሩ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ አንድን ነገር ከሰው ልጆች ልሰውርባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ስለሆነም ያንን ከሰዎች ለመሰወር የምፈልገውን ነገር የት ባስቀምጠው ሰዎች ላያገኙት የሚችሉ ይመስላችኋል?” አላቸው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ብዙም የደፈረ እንስሳ ማግኘት ከባድ የነበረ ቢሆንም አራት እንስሶች የየግል ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡ ንስር እንዲህ አለ፡- “ከሰዎች ለመሰወር የፈለከውን ነገር ለእኔ ስጠኝና ከፍ ብዬ መብረር ስለምችል ጨረቃ ድረስ ይዤው እወጣና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ “አንድ ቀን የሰው ዘር ጨረቃ ላይ የመውጣት ብቃት ስለሚኖረው ማግኘታቸው አይቀርም” አለው፡፡ አሳ እንዲህ አለ፡- “እንደ ውቂያኖስ ጥልቅ ነገር እንደሌለለና ሰዎች እዚያ ጥልቀት ድረስ እንደማይሄዱ አውቃለሁና እኔ በዋና እዚያ ድረስ መጥለቅ ስለምችል ይዤው ልግባና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ የሰው ልጅ ወደጠለቀው ባህር የመግባት አቅም ለማዳበር ብዙ ጊዜ ስከማይፈጅበት ማግኘቱ አይቀርም” ብሎ መለሰ፡፡ አንበሳ በተራው እንዲህ አለ፡- “እንኳን ሰው አብዛኛዎቹ የዱር እንስሶች እንኳ የሚፈሩት ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ የምደፍር እኔ ነኝ፡፡ እዚያ ወስጄ ባስቀምጠው ስለማያገኙት ለእኔ ስጠኝ”፡፡ ፈጣሪም፣ “ሰዎች ጫካን መመንጠር ብዙም ስለማይከብዳቸው ቀስ በቀስ ይደርሱበታል” አለ፡፡ ጦጣ በመጨረሻ እንዲህ አለች፡- “ፈጣሪ ሆይ፣ ከእነዚህ ሁሉ ሃሳብ ሰጪዎች በበለጠ ሁኔታ ከሰው ጋር ቀረብ ብዬ የምኖረው እኔ ስለሆንኩኝ ባህሪያቸው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ሰዎች አብዛኛውን ነገር ፍለጋ ውጪ ውጪውን ነው የሚሉት፡፡ ውስጣቸው ያለው ነገር ትዝም አይላቸው፡፡ ስለዚህ ውስጣቸው ብታስቀምጠው በቀላሉ አያገኙትም” አለችው፡፡ የጦጣ መልስ ተቀባይነት ስላገኘ ፈጣሪ ለመደበቅ ያሰበውን ነገር በሰው ውስጥ አስቀመጠው ይባላል፡፡ ይህ የተደበቀው ነገር የራሳቸው የሰዎቹ እምቅ ብቃት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በውስጣቸው ፈጣሪ ያስቀመጠው አስገራሚና የታመቀ ብቃት እያላቸው ምንም እንደሌላቸው በከንቱ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡ በውስጣችሁ ተዝቆ የማያልቅ እምቅ ብቃት እንዳለ ታውቃላችሁ? ፈልጋችሁ አግኙት! አውጡት! አዳብሩት! ተጠቀሙበት! ዶ/ር እዮብ ማሞ @tloveandhope
Show all...
አንደበት የአይምሮ መስታወት ነው። 👉በአይምሮህ ውስጥያለውን ሀሳብ እና ፍላጎት አንደበትህ መስታወት ሆኖ ያሳይሀል። ሰው በአይምሮው ውስጥ ምንድነው ያለው የሚለውን ለማወቅ ከፈለክ አንደበቱን ተከታተለው። ወይም ደግሞ እንዲያወራ አድርገው ያኔ አይምሮ ውስጥ ምን እንዳለ ታያለህ። ምክንያቱም ሰው በአይምሮ ሞልቶ የተረፈውን ነው በአንደበቱ የሚናገረው። ስለዚህ አንደበትህን መደበቅ ከቻልክ ሰዎች በአይምሮህ ውስጥ ያለውን እቅድ አያውቁትም። እራስህን መጠበቅ ከፈለክ አንደበትህን ጠብቀው። @tloveandhope
Show all...
አይገርምም!! 🔹የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው። 🔹ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው። 🔹የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው። 🔹«ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው። 🔹ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው።ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው። 🔹ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል። 🔹እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው። 🔹 በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱ የበሉት ሌሎች ሰዎች፤ ሰንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው። ⚠️ይህ ሁሉ እውነታ እያለ "ነኝ "እና "አልኝ"  በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም። እስቲ ያወሰብናትን ሕይወትን ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር!! @tloveandhope
Show all...
አክብር ! ሁሉም ሰው የተለያየ ነው በመልክ ፣ በቁመና ፣ በትምህርት ደረጃ ፣ ባለው የሀብት መጠን በመሳሰሉት ሁላችንም የየራሳችን ልዩነት አለን ነገር ግን አንድ የሚያደርገን ትልቅ ነገር አለ " ሰውነት ! " ፈጣሪ ከፍጡሩ ሁሉ የበላይ አዛዥ አድርጎ ሰርቶናል ! በሀብት መጠናችን ወይ በዝናችን አልለየንም ለሁላችን እኩል ክብር ሰጥቶን እኩል ፀሀይ ና ጨረቃን ያበራልናል ! " ታድያ የፈጠረው ፈጣሪ ባለው ነገር ያልናቀውን ሰው እኛ ምን ብለን ነው የምንንቀው እኩል ያከበረን ፈጣሪ ነውና ሁሌም መከባበር እንልመድ " መልካም ቀን ተመኘን 🙏 @tloveandhope የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊
Show all...
ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታውን ልንገራችሁ ተፃፋ  በሥነልቦና ባለሞያ Bini Girmachew 1. ዝምተኛ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ  ፤ አንዳንድ ጊዜም ብቻቸውን ያወራሉ። 2. አንድ ጊዜ ከአናንተ ጋር ምቾት ከተሰማቸው። እብድ እና ልዩ ነው የሚሆኑት። 3. የሚናገሩት በሀሳባቸው እና በልባቸው ነው። 4. አይናፋሮች ናቸው ፤ የአይን ለአይን ግንኙነት ብዙ ጊዜ መጠበቅ አይችሉም። 5. በጣም ብዙ ንዴት አለባቸው እንዲናደዱ አታድርጓቸው። እናም  ንዴታቸውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚችሉ ያውቃሉ። 6. ጠንካራ እና ብልህ ናቸው። 7.  በጣም እብድ ናቸው በማህበራዊ ሚዲያ (አንዳንድ ጊዜ) 8. የተረጋጋ ስብእና አላቸው እና ከእነሱ ጋር መሆንም አስደሳች ነው። 9. የእነሱ አእምሮ ሁልጊም እያሰላ ነው ፣ ከመጠን በላይ ይብሰለሰላሉ። ጥሩ ነገሮችን እና መጥፎ ነገሮችን። እንደዛ ነው የተገነዘብኩት። 10.  ታማኝ እና በፍቅር ግንኙነት በጣም የሚወዱ ናቸው። ዝምተኛ ሰዎች በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሲሆኑ በሙሉ ልባቸው ይወዳሉ።  በጥልቀት ይወዳሉ። ግን እነሱ የማይወዱህ ከሆነ ፤ ሙሉ በሙሉ ይተዋሉ ምክንያቱም ፍቅራቸው በጣም ጠንካራ ስለሆነ ነው። 11. የእነሱን ህመም አያሳዩም እና በጣም ስሜታዊ ሰዎች ናቸው። 12. አንዳንዶቹ ድብርት ውስጥ ናቸው ብቸኛ ናቸው ግን ያስመስላሉ ፣ ውስጥ ውስጡን ብቻቸውን ቢሆኑ ይፈልጋሉ ፤ እነሱ ከሰው የማይቀላቀሉ ሰዎች ናቸው። 13. በጣም የሚወደድ ፈገግታ አላቸው እና ግራ የሚያጋባ ሳቅ። 14. አብዛኞቹ እውነትን ይወዳሉ እና ትክክለኛ ናቸው። 15. ዝምተኛ ሰዎች ሚስጢረኞች ናቸው ፣ በተጨማሪ ብዙ ነገሮችን ይደብቃሉ ፣ ግን ምቾት እንዳይሰማቸው እና እንዲያዝኑ ካደረካቸው እውነቱን ይነግሩሀል ያለምንም ፍርሃት። 16. ዝምተኛ ሰዎች ከሰዎች የማይቀላቀሉ (introverts) ናቸው እንደእውነቱ ከሆነ በጣም ደስተኛ ሚሆኑት ብቻቸውን ሲሆኑ ነው። በሚወዷቸው ነገሮች እራሳቸውን እስከጠመዱ ድረስ። ይሄ ጥሩ ነው። 17. ዝምተኛ ሰዎች እና የማይቀላቀሉ ሰዎች ማንበብ ይወዳሉ። የሚነበቡ መጽሐፎች , በተለይ ሁለቱንም ልቦለድ እና ልቦለድ ያልሆኑትን። አንዳንድ ጊዜ የሚነቃቁ መጽሐፎችን (የራስ አጋዥ መጽሐፎችን) ያስማማል ?  እናንተ ደሞ የራሳችን ጨምሩ ✍️Bini Girmachew   
Show all...
አቤቱ በስቅለት ፡ ግርፋትህ ታውሶት ፡ በችንካር ተነክቶ፣ እንባውን ይዘራል     ልጅነት ያገኘ         የአይኖቹ ማድጋ በፈሳሽ ተሞልቶ እኔ ግን አምላኬ አንዲት ስንዝር እንኳ ካንተ ሳልጠጋ ስለሾህ አክሊለህ ፡         ስለ ግርፋትህ ፡       ስለ ስቅለትህ ቀን ፥ ስላልሰጠው ዋጋ ልጅነት ናፍቄ፡     በደሌ እንዲሻር ፡       ከጥግጋቱ ላይ ሆኜ እሰግዳለው፡ ማረኝን ነው እንጂ፡         ስለኔ ተገረፍክ፡            አቤቱ ሰቀሉህ ፥ መች ብዬ አውቃለው? ፡ መቼ ነው ፈጣሪ ፡ ልቤ የሚመለስ ከይሁዳ ድንኳን፡              ሕብረቴን የማፈርስ፡ መቼ ነው አምላኬ፡         እንደ ቀራጩ ሰው ራሴን ማጠራ ከጌትነት ውጪ             በክብር ምጠራ ይኽ ነበር ቃላቴ፡          ከስግደቴ ጋር በጥፍ የሚወጣ አቤቱ አምላኬ   በስቅላትህ ስም            ራሱን የሚያስምር ምን ይሆን ሚቀጣ?      አቡ (አላዛር ቴዎድሮስ)
Show all...
የተጠማሁ ቃልህ      ካንተ አንደበት ላይ ለሰማይ ሲወጣ እፈራ ነበረ የሰማይ መስኮቶች እንዳይለቁ ቁጣ    አሁን ግን           አሁን ግን ተረዳው የፍጹም መውደድህ የሰው ልጅ ኑፋጌ ያጣኸው ፍቅር ነው     ከፍጥረቶችህ መሐል ተጥሎ ከግርጌ አዎን እውነቴን ነው        ስለ ፍጹም መውደድ           ተገኝተህ ከኔ ደጅ ከክብርህ ዝቅታ ፍቅርን ብታጣብኝ      ነፍሲታህ ቃል አለች ተጠማሁኝ ጌታ        ተጠማሁ ፤ ተጠማሁ ፤ ተጠማሁ!       አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)
Show all...