እናቴ በልጅነታችን በተኛንበትእየመጣች በዘይት እየቀባችን ጌታ ሆይ ልጆቼን አገልጋይ አድርግልኝ እያለች የምታለቅሰው የለቅሶ ድምፅ ድንገት እዛው መድረክ ላይ አቃጨለብኝ።
የመጀመርያውን አልበሜን "ኪዳን አለኝ" የሚለውን አልበም ስሰራ ማንም ሰው አያውቀኝም ነበር ምክንያቱም ሰው ሙዚቃ በመጫወት እንጂ ስዘምር ማንም ሰምቶኝ ስለማያውቅ ካሴት ላወጣ ነው ብዬ ለቅርብ ወዳጆቼ እንኳን ስነግራቸው አርፈህ ሙዚቃህን ተጫወት አትዳፈር አሉኝ፡ ለካ ነገሩ ፡ የመዳፈር ጉዳይ ሳይሆን የጥሪ ነበር። መጀመርያ መዝሙሬን ያሰማሁት ለእናቴ ነበር አልረሳውም፡ ልጄ አገልጋይ ሆነ ብላ በሆዷ ተኝታ እያለቀሰች ጌታን ያመሰገነችው። እግዚአብሔር ፀሎትን ይሰማል።
እግዚአብሔር ሲጠራ ማን ከልካይ አለው? እግዚአብሔር ሰው እንደሚያየኝ ወይም እኔ ራሴ እንኳን ራሴን እንደማየው አያየኝም እርሱ እንደሚያየኝ እንደርሱ ይሆናል።
ፓስተርነት ማዕረግ ሳይሆን ኃላፊነት፡ ሸክም፡ጥሪ እንጂ የምንቆላመጥበት ስም አይደለምና ስሙን የሚመጥን ህይወት እንድኖር ፀጋውም እንዲረዳኝ ቅዱሳን ፀሎታችሁ አይለየኝ። የካናዳ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፓስተሮች እና አገልጋዮች የኦታዋ ምዕመናን በዚህ ፕሮግራም የተገኛችሁ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። እናቴም እንኳን ደስ አለሽ።
…✍ ዮሴፍ ካሳ
Show more ...