cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሐመረ ኖህ በገና ክረር መስንቆ መገኛ💒

በገና ክራር መሰንቆ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኙበት አዳዲስ እና ቆየት ያሉ የበገና መዝሙሮችን የሚገኙበት channel ነው

Show more
Advertising posts
21 543Subscribers
-1024 hours
-767 days
-33930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

☘️ሰላም ለልደትከ✨ ኦ አማኑኤል፤ ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ✨ብሉየ መዋዕል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ✨ ዘአብ ቃል፤ እፎ እፎ✨ አግመረተከ ድንግል፤ ወእፎ እንዘ አምላክ ✨ሰከብከ በጎል።         እንኳን 🍁ለአምላከ አማልክት✨ ወእግዚአ አጋእዝት✨ ወንጉሠ ነገሥት ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ ማርያም ሥግው ✨ኢየሱስ ክርስቶስ✨ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ✨ ከሁለት አካል አንድ አካል✨ከሁለት ባሕርይ ✨አንድ ባሕርይ✨አድርጎ ያለመከፈል ያለመለወጥ ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን✨✨ ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም✨ ነፍስን ነስቶ ያለ ዘርዓ ብእሲ✨ በፍጹም ተዋሕዶ✨ በዓለም ✨ለዓለም✨ ለታየባት✨ለቅድስት ልደቱ✨ በሰላም አደረሳችሁ።🌱መልካም በዓል H𝑖𝑤𝑜𝑡 G𝑒𝑧𝑎ℎ𝑒𝑔𝑛
Show all...
🙏 12👍 3 2
ኦ! ለዝንቱ መንክር ልዑል ላዕለ ኩሉ ሕሊናት:: ✝️ 🍀ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለእግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ:: ✝️🌱 ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ:: ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ . . . ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል! ✝️🌿ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ወለደችው:: ✝️🍀 ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው:: ✝️☘️ እርሱም እናቱን ፈጠረ:: ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ:: 🌿 ተዋርዶ በእኛ ባሕርይ ተወለደ:: እርሱም እኛን ስለ መውደዱ ፈጠረን:: (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍ ሶርያዊ ቁ. 2) ኦ ማርያም! በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ። እስመ ወለድኪ ለነ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን። ወስቴ ሕይወት ዘበአማን። "ማርያም (እመቤታችን) ሆይ! ስለዚህ ነገር እንወድሻለን። ከፍ ከፍ እናደርግሻለን። የጽድቅ መብልን የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና።" (አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ) ከበረከተ ልደቱ ይክፈለን) 👉 @hameranohh
Show all...
👍 4
​​እንኳን #አቡነ_ገብረመንፈስ_ቅዱስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን! አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው። አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ። ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል። አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ " የሚል ድምጽ ሰማች። በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ። አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል። አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል። በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል። በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው። በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ። ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው። ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ። ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ። ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር። በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው። መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት። 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል። ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው። ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል። ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር። 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው። እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል። ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል። ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል። ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው። 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል። ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው። በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው። አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው። ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል። ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ። #ምንጭ - ገድለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ተአምር 14  @hameranohh
Show all...
👍 8
Hiwot በገና ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ 🔵በገና ክራር እና መሰንቆ በሚያምር ዲዛይን እና በተመጣጣኝ ዋጋ ተሰርተው  ይደርሶታል። 🔵ከእርሶ እሚጠበቀው  ማዘዝ ብቻ ነው።በሚፈልጉት ቅርጽ አይነት እና ብዛት እንደ ፍላጎቶ በጥራት እንሰራለን። 👉ለማከፋፈል ብዛት ለሚገዙ ታላቅ ቅናሽ እናደርጋለን። ውጭ ሀገር ለምትኖሩ ወገኖቻችንም እንልካን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዉጭ ላላቸው በ 24ሰዓት ውስጥ እናደርሳለን። በገና 5000 10000 እና 12000 ክራር 3500እና 4000 መሰንቆ 2500እና3500              በጥራት አንደራደርም!!!!! ✍️+251934841025 ይደውሉ @hameranohh💚 @hameranohh💛 @hameranohh❤️
Show all...
መሰንቆ ሃይማኖት ምሳሌ ነው በመሰንቆ ጫፍ ላይ የንፃነታችን ዓርማ የደኅንነታን ምልክት የሆነውን መስቀል እናገናለንስለዚህም በመሰንቆ መዝሙር በዘመርን ቁጥር በቀራን ተፈጸመልንን ውለታ ተከፈለልንን ካሳ በማሰብ ፈጣሪያችንን በፍጹም ልባችን እናመሰግነዋለን፡፡ ፍቅሩንም እያሰብን ዘወትር በኃጢአታችን እንፀፀጻለን፡፡ የመሰንቆ መምቻው የኪዳነ ኖኅ ምሳሌ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ለኖኅ ምድርን ዳግመኛ በንፍር ውኃ ላያጠፋት ቃል የገባለት ምሳሌ ነው፡፡ዘፍ 9፡11-20 ይህም የመሰንቆ መምቻ ቀስተ ደመና ይመስላል፡፡ አባታችን ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነበት መርከብ ደግሞ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ነው፡፡ “ኖኅ ከጥፋት ውኃ የዳነብሽ መርከብ አንቺ ነሽ” በማለት አባ ሕርያቆስ በቀረዳሴ ማርያም ቁ 31 እንደተናገረው፡፡ ስለዚህ በመሰንቆ ስንዘምር ለአባታችን ለኖኅ በገባህለት ቃል ኪዳን መሠረት ኃጢአታችንን ተመልክተህ አታትፋን ማረን ብለን መለመናችን ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አባታችን ኖኅን ከጥፋት ውኃ ያዳንሽ አማናዊቷ ሐመር /መርከብ/ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የኃ ጢአት ማዕበል ጎልብቶ የፈተናውም ማዕበል በርትቶ በክህደት በጥርጥር ማዕበል እንዳንሰጥም ዛሬም ለእኛ ፈጥነሽ ድረሽልን በማለት እመቤታችንን መለመናችን ነው፡፡ ዋሽንት፡- ከቀርከሃ፣ ከሸንበቆ ፣ከብረት የሚሠራ የመዝሙር መሣሪያ ሲሆን በመጽሀፍ ቅዱስ ትን.ዳን 3፡5፤10 1ኛ ቆሮ 14፡7 ላይ ተጠቅሶ እናገናለን፡፡ ዋሽንት የወንጌል ምሳሌ ነው ፡፡ ከዋሽንት የሚወጣው ድምጽ መልካም እንደሆነ ልቡናን እንደሚመስጥ ደስ እንደሚያሰኝ ሁሉ ወንጌልም እግዚአብሔር ንጉሥ ነው ዲያቢሎሽ ተሻረ የሚለውን ደስ ሚያሰኝ የምሥራች ድምፅ ታሰማለች፡፡ መለከት፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ ለመዝሙር አገልግሎት ይጠቀምባቸው ከነበሩት የመዝሙር መሣሪያዎች አንዱ እንደነበር ከሊቀ ነቢያት ሙሴ የአገልግሎት ዘመን በፊት አገልግሎት ላይ መዋሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጻል ዘፍ 4፡21 በተጨማሪም በብዙ ሥፍራዎች በብዛት ተተቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ኢያሰ 6፡20፤ 2ኛ ዜና 15፡28፤መዝ80፡3 መለከት በትንሣኤ ዘጉባኤ ጌታን መምጣት ያበስራል፡፡ ማቴ 24፡31 1ኛ ተሰ 4፡16 መለከት ሰዎችን ለግዳጅ ያዘጋጃል፡፡ በጥንት ጊዜ ሰዎችን ለጦርነት ሲጠሩ ነጋሪት ይጎሰማል መለከት ይነፋል፡፡ በአጠቃላ መለከት ሰዎችን ለግዳጅ ዝግጁ እንድንሆን ያስጠነቅቃል፡፡ ሕዝ 33፡1-6 መዝሙር ስንዘምር በመለከት መዘመራችን በጌታ ዳግም ምፅአት በትንሣኤ ዘጉባኤ የምናገኘውን አዲስ ህወት በማሰብ ራሳችንን ከወዲሁ በንሥሐ እንድናዘጋጅ ሲረዳን በዕለተ ምጽአት ዕጣ ተርታችን ጽዋ ፈንጻችን ከቶ ከየትናው ወገን ይሆን ? በማለት ራሳችንን ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድንዘጋጅ ያሳስበናል፡፡ እንዚራ፡- በመጽሐፍ ቅዱስ በት ኢሣ 5፡12 ላይ የተጠቀሰ የመዝሙር መሣሪያ ሲሆን አሁን ግን ስለጠፋ በአገልግሎት ላይ ሲውል ባይታይም ቅዱስ ሲኖዶስ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበላቸው የዜማ መሣሪያዎች ውስጥ አንዱ እንዲገልግል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር @hameranohh
Show all...
5👍 2
ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4 : 1-2 አዲሱ አመት የሰማዪንም የምድሩንም የምናቀናበት ይሁንልን  እንኳን አደረሳችሁ
Show all...
👍 6🙏 4🕊 3 1
Show all...
D&H ሕንፃ መሣሪያ Dejene Construction Materials Supplier 0960009363

ማንኛውም ክፍለ ሀገር ያላቹ የሕንፃ መሣሪያ ነጋዴዎች መርካቶ ድረስ ምጣት ሳይጠበቅባቹ ማንኛውም የሕንፃ መሣሪያ እቃ በተመጣጣኝ ዋጋ ምንም ተጨማሪ ክፍያ ሳትከፍሉ ያላቹበት ድረስ እንልካለን ማኛውም የሕንፆ መሣሪያ እቃ ከኛ ዘንድ ለምን ይገዛሉ? 1እኛ መርካቶ ስለ ሆነ ስራችን እና ማከፋፈያ ስለሆንን 2ማንኛውም ሰው ክፍለ ሀገር ወደ መርካቶ ሲመጣ ብዙ ወጪ አውጥቶ ነው 3 እኛ ሱቃቹ ዘግታቹ ከመምጣት

👍 1
"አልጠቅምም አትበል" ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡ ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት ዲናሯ ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡ "ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቲዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡ ✝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...
24👍 6
፳፩❤ ዘማሪት መራሽ። ክራር ዲያቆን ታረቀኝ (ኩሽ)።
Show all...
👍 4 2🙏 2
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!