cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ልብ አንጠልጣይ ታሪኮች

Show more
Ethiopia343Amharic331The category is not specified
Advertising posts
32 861Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰላም ሰላም ውድ የልብ አንጠልጣይ ቻናል ቤተሰቦች @Eyobad ነኝ ትልቁ ቻናል ላይ ታሪኮች ማቅረብ ካቁምን ብዙ ግዜ ሆነን እና ለምን አቆማች እያላችሁ ብዙ ጥያቄዎች ደርሰውናል:: አቁመን ሳይሆን የቻናል ለውጥ አርገን ነው አዲስ በከፈትነው ቻናል በአይነቶ ልዬ በሆነ አቀራረብ ስራችንን እየሰራን ነው እና የቻናላችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ ቤተሰቦች ከታች ያለውን Link በመጫን Join ብላችሁ ቤተሰባችን ይሁኑ ለወዳጅ ዘመዶም share ማረግ እንዳይረሳ https://t.me/joinchat/AAAAAEhEwt6ztCunzhyfig
Show all...
ሰላም ሰላም ውድ የልብ አንጠልጣይ ቻናል ቤተሰቦች @Eyobad ነኝ ትልቁ ቻናል ላይ ታሪኮች ማቅረብ ካቁምን ብዙ ግዜ ሆነን እና ለምን አቆማች እያላችሁ ብዙ ጥያቄዎች ደርሰውናል:: አቁመን ሳይሆን የቻናል ለውጥ አርገን ነው አዲስ በከፈትነው ቻናል በአይነቶ ልዬ በሆነ አቀራረብ ስራችንን እየሰራን ነው እና የቻናላችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ ቤተሰቦች ከታች ያለውን Link በመጫን Join ብላችሁ ቤተሰባችን ይሁኑ ለወዳጅ ዘመዶም share ማረግ እንዳይረሳ https://t.me/joinchat/AAAAAEhEwt6ztCunzhyfig
Show all...
Show all...
ፀጉረ ልውጡ
⚰ የጠፋው ሬሳ ⚰
ከቤቱ ስር ያለው ድብቅ መቃብር ቤት
ሞሮ
ገማህልያ
ይቀላቀሉን አብዝተው ያተርፉበታል
Show all...
Everyday Addis

This is the official channel for Everyday Addis Podcast. We have a different kind of insight and perspective. DO NOT take us seriously.

Show all...
Sunlight

If you don't like the posts you can leave! 👋🏼 chaw Remember to ማይንድ ዩር ኦውን ቢዝነስ @sunlight_qbot .

መቀራረብ ጀመርን ጓደኝነታችን እየጠበቀ መጣ ብዙ ምክሮችን ትመክረኝ ነበር እያለ ናዲ ታሪኩን በሰፊው አጫወተኝ እንዴት ሰሙ እሱን እየመከረች እንዳስተካከላችው ምናምን ሁሉንም ታሪክ አንድም ሳይቀር አጫወተኝ ለሰአታትት ሳይደክመው አወራኝ እኔም በጣም ተመስጬ ሳልሰለች እየሰማሁት ነበር። እንዴት የተበላሸ ማንነቱን አስተካክሎ ከቀድሞ የበላጠ ጠንካራ እንደሆነ እንዴት በሁለት ዲግሪ ትምህርቱን በማእረግ እንደጨረሰና ከነሰሙና ኤቤጊያ ጋር አንድላይ እንደተመረቁ እንዴት ቤተክርስቲያ ቀለብት እንዳሰረላት እና እንደተጋቡ በቅርቡ እፁዬን እንደወለዱ በሰፊው አጫወተኝ በጣም ደስ አለኝ ታሪኩ ከጠበቅኩት በላይ አስተምሮኛል ናዲ እውነት ፍቅርን፣ የራስ ማንነት ጥንካሬን፣ ከምንም በላይ ደግሞ ይቅርታንና መልካምነት አስተማርከኝ አልኩት። ደስ ብሎኛል ስላስተማረክ ህይወት እንዲህ ናት እንግዲ ብዙ ውጣ ውረድ ቢኖራትም ፈተናዋን ስታልፍ ሽልማቷ ብዙ ነው አለኝ ከውጪ በር ተንኳኳ.... ናዲ እጁ ላይ ያለውን ሰአት አየት አደረገና ኦ.... ምሳ ሰአት ደርሷል ሰሙ ናት መሰለኝ አለና ከመቀመጫው ተነስቶ በር ሊከፍት ሄደ። የሳሎኑ መጋረጃ ስስ ስለነበር ውጪ ያለውን ክዋኔ በደምብ ያሳያል ናኦል በሩን ሲከፍተው አንዲት ዝንጥ ያለች ሴት ወደውስጥ ገብታ ጥምጥም አለችበት ፍቅር.... ብላ ከንፈሩን ሳመችው ሰምሃል እንደሆነች አልተጠራጠርኩም ነበር ከውስጥ ሆኜ ሁኔታቸውን አይቼ ፈገግ አልኩና ወደኮርኒሱ አንጋጥጬ አምላክ አንድ ቀን እንዲህ ለኔም..... አልኩና ተመለስኩ ሰምሃልና ናኦድ እንደተቃቀፉ ወደ ቤት ገቡ ልክ ሳሎኑ ጋር ጫማዋን አውልቃ ስትገባ ከሰሙ ጋር አይን ለአይን ተገጣጠምን ረሙ ያገሬ... ልጅ አለችኝ ሰሙዬ ብዬ ተነሳውና ተቃቀፍን። ሰምሃል ማለት ናዝሬት ሃይስኩል እማቃት በእድሜና በክፍል ትንሽ እምትበልጠኝ ጓደኛዬ ናት ቤተሰቦቿ ወደ አዲስ አበባ ጠቅልለው እስኪገቡ ድረስ የቅርብ ጒደኛሞች ነበርን እዚ ከገቡ በኃላ ግን ለረጅም ግዜ ተራረቀን በናኦድ ምክንያት ዳግም ተገናኘን የአጋጣሚ ነገር ይገርማል። እንዴት ነሽ ባክሽ ሰሙ ወፍረሻል ይሄ ትዳር ተመችቶሻል አይደል አልኳት እየሳቀች ኣው ባክህ ምን እናድርግ ብለህ ነው አላችኝ። እፁ ከእንቅልፏ ተነሳች መሰለኝ ማልቀስ ጀመረች ሰሙ የእናት አንጀት ሆኖባት እኔን ልጄ እኔን ልጄ መጥቼልሻለው መጥቼልሻለው እያለች በፍጥነት ወደመኝታ ክፍል ገባች። ኤቤጊያም የእፁን ድምፅ ሰምታ ነው መሰል እየሮጠች መጥታ መኝታ ክፍል ገባች። ሰሙና አቢጊ ለሁለት እፁን እያባበሏት ይዘዋት ወደሳሎን መጡ ሰሙ አቢጊን እያየቻት እጡዬ ኔኔ ማል አክትሽ አቢጊ በደም ተንተባተበትሻ አለቻት ጥፍጥ ባለ በኮልታፋ የህፃን አንደበት። አቢጊ እኔ የክርስትና እናቷ እያለውማ ምን ትሆናለች በደምብ አድርጌ ነው የምይዛት አለች የእፁን እጅ እየሳመች። ሁኔታቸውን ሳይ አስቀናኝ ያንን ሁሉ ግዜ አልፈው አሁን ላይ ለዚ በቅተዋል ደስ ይላል። ናዲ ከሰሙ እጅ ላይ እፁን ተቀበላትና ፍቅር ታጣጥበሽ ነይና ምሳ እንብላ አላትና ወደ አቢጊ ዞሮ አክስት ተብዬዋ ምሳ ደርሷል አይደል አላት አው ላቀራርብ እንደውም ብላ ሄደች። ናዲ እኔን ፍፁም እረስቶኝ ከእፁ ጋር ጨዋታ ጀመረ.... አይ የልጅ ፍቅር! አልኩ በልቤ። ምሳ ቀራርቦ ከበላን በኃላ ሰሙ ቡና አፍልታ መጨዋወት ጀመርን በመሃል ናዲ ስልኩላይ ያለውን ሰአት አየና እንዴ ኪያር አይመጣም እንዴ ቆየ አለና ደወለለት ስልኩን ስፒከር ላይ አድርጎት ነበር። ምናባክ ነው ምትጨቀጭቀኝ በር ላይ ደርሻለው ክፈት አለው ናኦድ እየሳቀ ሄዶ ከፈተለት ተያይዘው ገቡ ኪያር መጥቶ በአንዴ ቤቱን ሞቅ አደረገው! ከሰአቱን ከነሰሙና ናዲ ጋር ስጫወት አመሸው አራቱም በእድሜም ሆነ በሌላም ነገር ከኔ ይበልጣሉ ታላላቆቼ ናቸው በዛች እለት ናዲ በነገረኝ ታሪክ እና እኔም ባየሁት እውነታ ብዙ ነገር ተማርኩ! ሁሉም ያላቸው ወዳጅነትና ፍቅር በጣም ያስቀናል እኔም እንደነሱ ብሆን ብዬ ተመኘው። ግዜው እየመሸ ደንገዝገዝ ብሎ ለአይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር እኔ ለመሄድ ተነሳው ሰሙ ቅር እያላት ልትሄድ ነው አታድርም አለችኝ አይ መሄድ አለብኝ ይቅርታ ሰሙ ባይሆን ሌላ ግዜ አድራለው አልኳት እሺ በቃ ካልክ ምን ይደረጋል አለችኝና ተሰናበትኳት ኪያርና ኤቤጊያንም ተሰናበትኳቸው እነሱ ትንሽ ይቆዩ ነበር። ከናኦድ ጋር ትንሽ ሊሸኘኝ አብረን ወጣን ከቤት እንደወጣን ወደ ታክሲ መያዣው ቦታ እየሸኘኝ እያለ ናኦድ ዛሬ ቤትህ ስለጠራኀኝ በጣም ደስ ብሎኛል ብዙ ነገር ነው ያስተማራችሁኝ አልኩ። አው ቅድም እኮ ያው በደምብ ሳልመክርህ ሁሉም ተሰባሰበ ደስ ስላለህ እኔም ደስ ብሎኛል አየህ አይደል ፈተናህን ታግለህ ስታሸንፍ ደስታህን ትሰጥሃለች ሁሌም ጠንካራ ማንነት እና ቅን ልቦና ይኑርህ ሁሉን ታሸንፋለህ የሚበድሉህን ይቅር በላቸው ባለማወቅ በድለውህ ሊሆን ይችላል ግን ሰው ይቀየራል ሁሌም አንድ ቦታ ላይ አታገኘውም መልካምነትና ይቅርታን በልብህ ሁሌም አኑራቸው ጥለው ኣይጥሉህም እህቴ ናሆሚ ስላንተ ብዙ ነገር ነግራኛላች ለሷ ያደረክላትን ነገር በሙሉ አውቃለው ለዛም አመሰግንሃለው አስተዋይ ልጅ ነህ ብዙ ምክር አላብዛብህ አለኝ እየሳቅኩ አረ ናዲ እንደውም ብትጨምርልኝ ደስ ይለኛል እንዲ ስለህይወር እሚያስተምረኝና እሚመክረኝ ሰው ነው እምፈልገው አልኩት እሺ ብዙ እምናውራቸው ነገሮች ይኖራሉ ወደፊት አለኝ። ቦሌ... ቦሌ ቦሌ ቦሌ አለ አንድ ወያላ የታክሲውን በር እየከፈተ። ከናዲ ጋር መሰነባባት ጀመርን ስለመከረኝና ስላስተማረኝ ነገር ሁሉ ከልብ ኣመስግኜው እና ሌላም ግዜ እንዲጨምርልኝ ነግሬው ቻው ተባብለን ታክሲው ውስጥ ገባው። ጋቢናው ውስጥ ከሹፌሩ ጋር ብቻዬን ስለነበርኩ በሃሳብ ማእበል እየተናጥኩ ናኦድ የነገረኝን ታሪክ አሰብኩና ተገረምኩ ይገርማል የሰው ልጅ እንደመፅሃፍ ገልጠው እስካላነበቡት ድረስ ማወቅ አይቻልም ምን ቀን ከናኦድ ጋር እንደተዋወቅን ለማስታወስ ሞከርኩ...። ናኦድ ግቢ እያለው ከአርክ ውጪ ሌላ ትምህርትም እድማር መንፈሳዊ ቅናት ያሳደረብኝ ልጅ ነው እኔም እሱ በአንዴ ሁለት ዲግሪ ስይዝ አቀናኝ እኔም በሱ ፈለግ ተከተልኩ። ይሄ ታሪክ መፃፍ አለበት እኔ እንደተማርኩበት ብዙ ሰው ይማርበታል አልኩ በልቤ እፅፈዋለው! ስልኬን ኣወጣው አዲስ ኖት ከፈትኩና ትንሽ ማሰላሰል ጀመርኩ ...መጣልኝ!!!! ከላይ ርእሱን "ሞሮ" አልኩት ክፍል አንድ ......ታክሲው እየሄደ መፃፌን ቀጠልኩ። እነሆ አንድ ብልህ አስተዋይ ወዳጄ የነገረኝ የግል ታሪኩን እኔ እንደተማርኩበት እናንተም ትማሩበት ዘንድ ፃፍኩላችው ሞሮ ተፈፀመ ፍቅር ከበቀልና ጥላቻ በላይ ናት የፅድቅ ሁሉ ፍፃሜም ፍቅር ናት ፍቅር ለዘልአለም ትኑር በመፅሃፍ መልክ ታትሞ በሰፊው ተስተካክሎና ሌሎች ያልተፃፉ ታሪኮችም ተፅፈውበት ዳግም በመፅሃፉ እንገናኝ ┈•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•˚•✿•┈ ✥┈┈┈┈┈••◉ተፈፀመ◉●••┈┈┈┈┈✥ እንግዲ ሞሮ እዚ ላይ ቢያልቅም በመፅሃፍነት ታትሞ ሲወጣ ብዙ ያልተፃፉ ታሪኮች ተጨምረውበት ይመለሳል። @Lbe_Anteltay @Lbe_Anteltay
Show all...
💓💓💓💓💓 💓 💓💓💓💓💓 💓💓💓💓💓ሞሮ 💓💓💓💓💓 💓💓💓💓 ፍፃሜ 💓💓💓💓 💓💓💓💓💓 💓 💓💓💓💓💓 ፀሃፊ ረምሃይ ፀሃፊው ነኝ .... ከጥቂት ወራት በፊት በአንደኛው እለተሰንበት በእድሜ የሚበልጠኝ አንድ ጓደኛዬ ሲአምሲ አከባቢ ከሚገኘው ቤቱ እንደመጣ ጋበዘኝ እናንተ "ናኦድ" በሚለው ለፅሁፍ እንዲያመች በተቀየረው ስሙ ታውቁታላችው። እናም ግብዣውን ተቀብዬ ቤቱ ሄድኩ ወደቤቱ እየገባን እያለ አዲሱ ትዳር እንዴት ይዞሃል አልኩት በፈገግታ እሱም እየሳቀ አሪፍ ነው በልጄም በሚስቴም ደስተኛ ነኝ አለኝ አሪፍ ነው አልኩት። እንደለመደብኝ አዲስ ቦታ ስሄድ እንደማደርገው በአርክቴክት አይኔ ቤቱን ቃኘሁት ደስ ይላል ቀለል ያለ ኮተታኮተት ያልበዛበት የባለትዳር ቤት ይመስላል። ልክ ሳሎን ውስጥ እንደተቀመጥን ከመኝታ ቤት አንዲት ሴት ወጣች እንዴ... አቢጊ ብዬ አቀፍኳት ረጅም ግዜ ሆኖኝ ነበር ካገኘኃት ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠኃት ናኦድን ሰላም ልትለው ስትል ከመኝታ ቤት የህፃን ልጅ ለቅሶ ሰማን ኤቤጊያ ውይ እፁዬ አለቀሰች ብላ እየሮጠች ወደመኝታቤት ተመለሰች ናኦድም ተከትሏት ሄደ። ትንሽ ከቆየ በኃላ ትንሿ በጣም እምታምረው ልጁን ይዟት ወጣ ብዙ ግዜ እኔ ህፃናት ብዙም አይመቹኝም ግን እፁብን እንዳየኃት ውድድድ አደረኳት እንዴት እንደምታምር ቀይ ድንቡሽቡሽ ልጅ ሉጫ ፀጉር ትልልቅ አይን ያላት ቆንጅዬ ልእልት ናት እፁብ። ከሶፋው ላይ ተነሳውና ወደናኦድ ተጠጋው ናዲ እምታምር ልጅ አለህ በጣም ነው ምታምረው አልኩና ግንባሯን በስሱ ሳምኳት አው ባክህ ቆንጅዬ ልእልት ናት ትንሽ እንቅልፏ ሲመጣ ለቅሶዋ መከራ ነው እንጂ አለኝ ህፃኗን እፁብ እሹሩሩ እያለ እንግዲ እኔ ስለህፃናት እማውቀው ነገር የለም አልኩት እየሳቀ ባክህ አንተም አግብተህ ስትወልድ ታየዋለህ አለኝ እኔም እየሳቅኩ ኡ.... ገና አልኩት። እፁብ ማልቀስ ስትጀምር እያባበላት ወደመኝታ ቤት ይዟት ሄደና ለአቢጊ ሰጥቷት ተመለሰ። እሺ እስራኤል እና ደህና ነህ ተጠፋፋን አይደል ያው ታውቀዋለህ ትዳር ስራ ምናምን ሲደራረብ አሁን ደግሞ እፁዬ መጥታለች ተጠፋፋን አለኝ አው ተጠፋፋን አልኩትና ከመቀመጫዬ ዳግም ተነሳውና ፊትለፊቴ ወዳለው ግርግዳ ሄድኩ የናዲ እና የሚስቱ የሰርግ ፎቶ በትልቁ በፍሬም ታሰቅሏል ባዶ ቦታዎቻቸው ላይ በወርቃማ እስክርቢቶ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መልካም ምኞት አውቶግራፍ ተሞልቷል አይኔን አጥብቤ የተወሰኑትን ለማንበብ ሞከርኩ ደስ ይላሉ። ወደ ናኦድ እየዞርኩ ሳቅ ብዬ ለሰርጋቹ ግን ሳትጠሩኝ በጣም ታዝቢያቹሃለው አልኩት ናዲም እየሳቀ እኛማ ጠርተንህ ነበር አንተ አልመጣም አልክ እንጂ አለኝ። እና መቀሌ ነበርኳ ግቢ የእህቴን ሰርግ እራሱ አንድ ቀን ቆይቼ ነው የተመለስኩት ምናለ ለእረፍት እስከምንመለስ ብትጠብቁኝ እንኳን አንድ ብሬ ብጨርስ ነው አልኩት እየሳቅኩ ናዲም እየሳቀ አይ ረም ዘንድሮም ትኮምካለህ አ አለኝ እየሳቅኩ የቴሌቭዥኑ ስታንድ ጋር ሄጄ እዛ ላይ በፍሬም የተቀመጡትን ፎቶዎች እያነሳው ማየት ጀመርኩ ካሉት ውስጥ የምርቃታቸውን ፎቶ በእጄ አንስቼ አየሁት ናዲ መሃል ሆኖ ሰምሃል እና ኤቤጊያ በጎና በጎን ሆነው የተነሱት ፎቶ ነበር ወደናዲ እየዞርኩ ይሄ ፎቶዋቹ ደስ ይላል አልኩት። አውው... ባክህ ጥሩ ትውስታ ነው ግዜው ይሮጣል አይደል ከተመረቅን እንኳን አራት አመት ሆነን አይ ግዜዜዜ.... አለና ትንሽ በሃሳብ ሰመመን ሄደ። እኔ ፎቶዎቹን እያነሳው አይቼ ስጨርስ አስቀምጥና ሌላ አንስቼ ማየት ጀምራለው። ናዲ እንዳጎነበሰ ሲያስብ ከቆየ በኃላ ረምሃይ ብሎ ጠራኝ እእእ ናዲ አልኩት። እስኪ ና ቁጭ በል ስለ ግቢ አንድ ታሪክ ልንገርህ አንተ አስተዋይ እንደሆንክ አውቃለው ናሆሚም ነግራኛላች ግን ምናልባት እምትማርበት ነገር ይኖራል አለኝ እኔም ሄጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ። ትንሽ አጎንብሶ ግንባሩን እያሸ ካሰላሰለ በኃላ ታውቃለህ ግቢ እያለው ብዙ ትዝታ ነበረኝ ብዙዎቹ መጥፎና አሳዛኝ ቢሆኑም በዛው ልክ ደግሞ ክፉውን ግዜ የሚያስረሱ ጥሩ ትዝታዎችና ምርጥ ጓደኞች ነበሩኝ። ግቢ ፍሬሽማን እና ሁለተኛ አመት ላይ በጣም ጎበዝ ተማሪ ቀለሜ ነበርኩ ብዙ ደሳስ እሚሉ ጓደኞች ነበሩኝ። ደስ የሚል ጊዜ እናሳልፍ ነበር በአስተማሪዎቼም ተወዳጅ ተማሪ ነበርኩ ግን ህይወት ልታስተምርህ ስትፈልግ ከፊትህ ፈተና ማስቀመጥ ትጀምራለች ልክ 2004 ሶስተኛ አመት እንደገባን አንዲት ሴት በፍቅር አንባረከከችኝ ሲለኝ በዚያው ቅፅበት ኤቤጊያ ከመኝታ ክፍሉ ቀስ ብላ እያተራመደች ወደኛ ጠጋ ብላ እፁ ተኝታለች ቀስ ብላችው ተጫወቱ እኔ ሰሙ ሳትመጣ ምሳ ልሰራራ ብላን በእግሮቿ ጣት ብቻ ቀስ ብላ እየተራመደች ከሳሎን ሄደች። ናዲ ወደኔ እያየ በእጁ አቢጊ ወደወጣችበት በር እየጠቆመ ያቺ በፍቅር ያንበረከከችኝ ሴት አቢጊ ነበረች አለኝ በአግራሞት ምን!? አልኩት አው አቢጊ በጣም ቆንጅዬ ቀበጥባጣ ልጅ ነበረች ያኔ አሁን እንደምታያየት የተረጋጋች አልነበረችም እና ስለሷ ሳስብ ስለሷ ሳልም ትምህርቴን እረሳው ያኔ ፍቅሯ ልቤን አውሮት በጣም እፈራት ነበር ገና ከርቀት ሳያት መንገዴን እቀይራለ ጓደኞቼ ሁኔታዬን እያዩ ይስቁብኝ ነበር ግዜያት እየተቆጠሩ ሲሄዱ እኔም ፍቅሯ በጣም እየባሰብኝ ሄደ.... ከውስጥ ኤቤጊያ ሽንኩርት ስትከትፍ የመክተፊያው ድምፅ ይሰማናል ተመስጬ እየሰማሁት ስለነበር ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር ናዲ ብድግ አለና መኝታ ቤቱን ከፍቶ እፁ አለመነሳቷን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ መጣና ፈገግ እያለ እና.... ራሴን መጣል ጀመርኩ እሷ እኔን አትመጥነኝም እል ነበር ፍቅሬን ድፍረት ኖሮኝ ብገልፅላት እንኳን ምሏሿ ተቀራኒ እንዳይሆን እልና እፈራለው እተወዋለው ስለሌላ ነገር ማሰብ ተሳነኝ ስልቹና ቸልተኛ ለምንም ነገር ግድ የማይሰጠኝ ሰው ሆንኩ ጓደኜቼ ለኔ ያላቸው ከበሬታ ቀስበቀስ እየቀነሰ ሄደ ይባስ ብለው ይስቁብኝና ይሳለቁብኝ ጀመር ታውቃላሃ "ሞሮ" ይሉኝ እንደነበር አለኝ አው አውቃለው ሰሙም ናሆሚም ነግረውኛል አልኩት። አው ሞሮ ማለት ምንም የማይገባው ደደብ ማለት ነበር የሚገርምህ ይህንን ስም ያወጡልኝ የገዛ ጓደኞቼ ናቸው የልብ ጓደኞቼ እምላቸው ነበሩ ሁሉም ከዱኝ ከአንድ በስተቀር ኪያር! ኪያር አሁንም ድረስ በጣም እምወደው እና እማከብረው የልብ ጓደኛዬና የስራ ባልደረባዬ ነው ከዛም በላይ ደግሞ የእህቴ ናሆሚ እጮኛም ነው። ሶስተኛ አመት ሙሉ ስለኤቤጊያ ሳስብና ሳልም ኖርኩ ጓደኞቼ ሸሹኝ እኔም ከትምህርት ራቅኩ መማር አስጠላኝ ቀን ከቀን ተኝቼ እውላለው የጓደኞቼ ስድብና ኤቤጊያን መቼም እንደማላገኛት ሳስብ መጠጣት ጀመርኩ ሱስ ውስጥ ተዘፈቅኩ ዶርም ተኝቼ ካልሆነ በጠርሙስ ተደብቂያለው ወይ በሲጋራ ጭስ ራሴን ደብቂያለው ደህና የነበርኵት ልጅ በግዜ ሂደት መውጣት እማልችለው አዘቅት ውስጥ ተዘፈቅኩ ብዙ ግዜ ራሴን ላስተካክል ጣርኩ ግን አልሆነልኝም እንዲው እንደሆንኩ አራተኛ አመት ገባን የግቢው ቁጥር አንድ ጀዝባ እና ሞሮ ሆንኩ ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም። አንድ ቀን ኤቤጊያን ከአንድ ራስታ ልጅ ጋር ስትሳሳም አየኃት በጣም ተናደድኩ በማግስቱ ልጁን ሺሻ ቤት አጊንቼ ተጣላን ጓደኞቹ ማታ ላይ ጠብቀው በጩቤ ወጉኝ ያኔ... ያኔ... ነበር ህይወቴን በሙሉ የምትቀይረዋን ሴት ያገኘሁት ሰምሃል! ኣለኝ ከሰሙ ጋር የተዋወቃቹት ያኔ ነው አልኩ በመገረም። አው ያኔ በሞትና በህይወት መካከል ሆኜ ያተረፈችኝ እሷ ነች ሆስፒታል ወስዳኝ ለመዳኔ ምክንያት ሆነች ከዛን ግዜ በኃላ ከሰምሃል ጋር
Show all...
💓💓💓💓💓ሞሮ💓💓💓💓💓 💓💓💓💓 ክፍል 43 💓💓💓💓 ፀሃፊ ረምሃይ ወደ ሰምሃል እየሮጥኩ ስሄድ ሊዲያ ትንሽ ወደኃላ ቀረት ብላ አስቆመችኝ ናኦድ አንተ በጣም መጥፎ ሰው ነህ እንዲ አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር አለችኝና ጥላኝ ሄደች እዛው ቆሜ ቀረው ኤቤጊያ ከኃላዬ መጥታ ቀስ ብላ ትከሻዬን ነካ አድርጋኝ አይዞህ ናዲ ሁሉም ነገር ግዜውን ጠብቆ ይስተካከላል አለችኝ። እዛው መሬት ላይ ቁጭ ብዬ አላቀስኩ እኔ ቆይ ለምድነው ሁሉም ነገር እሚጠምብኝ!!! ኤቤጊያ አፅናናችኝ በቃ ወደ ዶርም ሂድና እረፍት አድርግ አለችኝ ው ተባብለም ተለያየን። ዶርም አከባቢ ስደርስ የዶርሜ ልጆች ሳለቅስ እንደነበር ቢያውቁ.... ደበረኝና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ተኛው እዛው ተጋድሜ እንዳለ ለራሴ አንድ ነገር ቃል ገባው ማንንም ሴት ከዚህ በኃላ ላልቀርብ! ሴትን በማሰብ ያቃጠልኩትን ግዜ ጠንክሬ ተምሬ ላካክስ ወስንኩ። በማግስቱ ከኤቤጊያ ጋር ስንገናኝ ዶርም ሰምሃልን ለማናገር ስትሄድ እንደተጣላቻትና ከዶርሟ እንዳሶጣቻት ነገረችኝ ሰምሃልና ኤቤጊያም ተጣሉ። ሁለት ሳምንት ሙሉ ሰምሃልን ሳላገኛት አለፈ ትምህር... ተጀመረ... ሙሉ ሃሳቤን ወደ ትምህርቴ አድረጌ መማር ጀመርኩ ቢከብደኝም ራሴን አልጥልም አልሰላችም በራሴ ተስፋ አልቆርጥም እንደቀድሞዬ ጠንካራ እና ሰቃይ ሆንኩ። ከሰምሃል ጋር ከተጣላን በወራችን ላይብረሪ ስገባ እሷ ደግሞ ስትወጣ በር ላይ ተገናኘን ደንገጥ ብላ ቆማ አየችኝ እኔን ትንሽ ቆሜ አየኃትና ፈጠን ብዬ ወደላይብረሪ ገባው ሰምሃልም ሄደች ግዜውም ሄደ.... የፋይናል ፈተና ደረሰ ላይብረሪ ውስጥ ሁሌ አያታለው አንነጋገርም ሌላው ቀርቶ ሰላምታም የለንም ድንገት እንኳን መንገድ ላይ ብንገጣጠም እንዳልተያየ ሆነን እንተላለፋለን። 2006 የአንደኛ ሴሚስተር ግዜ አልቆ ሁለተኛ ሴሚስተር ገባ ከሰምሃል ጋር ከተጣላን ከአምስት ወር በላይ ሆነን ሁልግዜ ስልኬን አነሳና ልደውልላት አስቤ እተወው ነበር አሁን ግን በሰምሃል ተስፋ ቆረጥኩ ስልኳን ከስልኬ ላይ አጠፋሁት። የአንደኛ ሴሚስተር ውጤት ሲለቀቅ ከክላሴ ከፍተኛውን ነጥብ አስቆጠርኩ 3.98 በሚቀጥለው 4 ነጥብ ለማምጣት ወሰንኩ ሰምሃልን ረሳኃት ... ሁለተኛውም ሴሚስተር ማንንም ሳይጠብቅ ገሰገሰ እኔም ግቢ መኖር ስላስጠላኝ ከግቢያችን ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ቤት ተከራይቼ መኖርና መማሬን ቀጠልኩ ብዙ ግዜ ሲደብረኝ ወይም ብቸኝነት ሲሰማኝ ኪያር ወይም ኤቤጊያ መጥተው ያዳብሩኛል። ሁለተኛ ሴሚስተር ሲጀምር የማታ ሌላ ትምህር ጀምሬ ስለነበር በጣም እጨናነቃለው ግዜውም ሳይታወቀኝ በትምህርት ራሴን እንደወጠርኩ ገሰገሰ የሚድተርም ፈተና ከተፈተንን በኃላ አንድ ቀን ኤቤጊያና ኪያር ቤት እንድጠብቃቸውና አስቸኳይ እሚነግሩኝ ነገር እንዳለ ነገሩኝ ምን እንደሆነ ለናወቅ ጓጓው ከአንድ ሰአት በኃላ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ መፅሃፍ እያነበብኩ ኪያር እና አቢጊ ዘው ብለው ገቡ። አቢጊ እንኳን ደስ ያለ...ህህክ ብላ እዛው አልጋው ላይ እንደተቀመጥኩ መጥታ ተጠመጠመችብኝ እየሳቅኩ ምን ተገኘ አልኳቸው ሁለቱንም እያየኃቸው። ምን ሆነ መሰለህ ብሎ ኪያር ሲጀምር እኔ አይደል እንዴ ሰምቼ የነገርኩ እኔ እራሴው ነው እምነግረው ብላ ኤቤጊያ እየሳቀች አቋረጠችው የውልህ ናዲ ቅድም እነሰምሃል ስፔስ ቁጭ ብዬ እያጠናው እያለ ሰሙ ሊዱ እና ራኪ ሆነው ሊያጠኑ መጡ እኔ ከኃላ ያጥቁሩን ባለሁዲ ጃኬት ከነኮፍያው አድርጌው ስለነበር አላወቁኝም ነበር ብዙም አላዩኝም እናም እያጠኑ እያለ በመሃል ሰምሃል ማልቀስ ጀመረች እና እነ ራኪ ምነው አሏት ናዲ ናፈቀኝ ፍቅሩ አሁንም አልወጣልሽ አለኝ ይባስ ብሎ ተጣልተን ስንራራቅ ፍቅሩ ባሰብኝ ኣረሳው አልቻልኩም አለቻቸው። ኤቤጊያ ይህንን ስትነግረኝ ደነገጥኩ እስከዛሬ እሷ ስታፈቅረው የነበረው ሌላ ወንድ አልነበረም እኔኑ ነው!? እኔኮ ፍቅሬን ያልነገርኳት እሷ ሌላ እምታፈቅር ስለመሰለኝ ነው አልኳት አቢጊም እየሳቀች አው አይገርምም አንተን ነበር እንጂ ሌላ ሰው አልነበረም አለችኝ። ሁለታችሁም አሁን ትዋደዳላችው አይደል አሁን ወደ ቤተክርስቲያን እየወጡ ነው ሂድና አግኛት አለኝ ኪያር አይ አይሆንም አሁን ግዜው ረፍዷል ወደ ስምንት ወር ምናምን ሆነን ከተጣላን አሁን ላይ ምን ብለን ነው እምንታረቀው በዛ ላይ እኔ በፍቅር ተስፋ ቆርጫለው ዳግም ሴት ቀርቤ መጎዳት አልፈልግም በሰምሃል ተስፋ ከቆረጥኩ ቆየው አልኩት ኪያር ተናዶ ምን? አለኝ እኔ ከዚ በላይ ልታገስህ አልችልም ናኦድ ቻው ብሎኝ ወጥቶ ሄደ አልጋዬ ላይ ተመልሼ ዘፍ አልኩ። ኤቤጊያ ባዘነ አንደበት ለምን አለችኝ ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ አቢጊ እኔ በዚ አለም ላይ ለፍቅር ያልተፈጠርኩ ሰው ነኝ ምንም ነገር አይሳካልኝ አልኳት አቢጊ እንደዛ አትበል ናዲ አንተ ጥሩ ሰው ነህ እኔ እንኳን ብዙ ነገር አድርጌህ ይቅር ብለኀኛል ይኀው አሁን ላይ ካንተና ከኪዩ ውጪ ምንም ጓደኛ የለኝም እባክህ በፍቅር ተስፋ አትቁረጥ እኔንም ፍቅርና ይቅርታን ያስተማርከኝ አንተ ነህ አንተ ተስፋ ስትቆርጥ አይቼ እኔም ተስፋ መቁረጥ አልገልግም ብላ አቀፈችኝ። አቀፍኳት!
Show all...
💓💓💓💓💓ሞሮ💓💓💓💓💓 💓💓💓💓 ክፍል 42 💓💓💓💓 ፀሃፊ ረምሃይ በውስጤ ለማንም ሳልናገር ሳብሰለስለው የነበረ የኔም ጥያቄ ነበር አቢጊ እንደዚ ስትለኝ ለምን ደነገጥኩ? እውነት ስለሆነ ነው? ፊቴ በአንዴ ተቀያየረ ። አይ አቢጊ ተሳስተሻል ሰሙ ጥሩ ጓደኛዬ ናት እሷ እኔን በጓደኝነት እንጂ በፍቅር ምናምን አይን አይታኝ አታውቅም ስለፍቅር እንኳን አንድም ቀን አውርተን አናውቅም አንዴ ብቻ እምትወደው ሰው እንዳለ ነግራኛለች አልኳት። ................................................ ሰምሃል ትንሽ ከተረጋጋች በኃላ ሊዲያ ወደሷ አልጋ እየተጠጋች ሰሙዬ ወክ እናድርግ ላንቺም ጥሩ ነው ትንሽ ቀለል ይልሻል አለቻት ራኬብም ቀበል አድርጋ አው ለምን ወክ እናደርግም እንደውም አንፊ አከባቢ እንቀመጥ አየሩ ደስ ይላል እዛ አከባቢ አለቻት እሷም እየተደረበች። አረ... እኔ አልሄድም መተኛት ነው እምፈልገው አለቻቸው ሊዲያ ተናደደች ኤጭጭ.... አሁንስ አበዛሽው ብላ የለበሰችውን ብርድልብስ ገፈፈቻትና እግሯን ትጎትታት ጀመር ሰምሃል እንደመሳቅ እያለች ምን እያደረግሽ ነው አለቻት። ራኬብም ስትስቅ ስታያት እሷም ተደርባ እግሯን ለሁለት እየጎተቱ በግድ ከአልጋው አውርደው መሬት ተቀመጠች በሁኔታው ሶስቱም ተሳሳቁ እሺ በቃ ወጣለው ፊቴን ልተጣጠብና እንሄዳለን አለቻቸው እንሱም እሺታዋን ሲሰሙ ጉትጎታቸውን ትተው ልብስ መደራረብ ጀመሩ። ራኬብ ቡኒ ባለኮፍያ ጃኬቷን እያደረገች በናታችው አምፊ ደረጃዎቹ አከባቢ ሄደን እንቀመጥ እሱ ቦታ እንቀመጥ አለቻቸው ሊዲያ ወደሷ ዞራ ከዶርም እምንወጣው እኮ አምፊ ሄደን ልንዘፈዘፍ አይደለም ወክ ልናደርግ እንጂ አለቻት እሺ በቃ በሜይን ካፌ አከባቢ ወክ እናድርግና ሲደክመን አምፊ እንሂድ አለቻታ። ሶስቱም ጨራርሰው ነበር በይ ነው ውጪ ባክሽ ሰሙ ነይ እንጂ ብላ ራኬብን ሳትሰማት ሶስቱም ተነስተው ወጡ። ............................................... ስለሷ ሳይሆን ስላንተ ነው የጠየቅኩህ እሷ ሌላ ሰው ታፍቅር አታፍቅር ሌላ ጉዳይ ነው አንተ ግን ሰምሃልን ታፈቅራታለህ አይደል? ብላ ድጋሚ ስትጠይቀኝ ልቤ ብፍጥነት ይመታ ጀመር እኔንጃ አላውቅም አልኳት እንዴት ነው እማታውቀው ትወዳትለህ..ብላ አስጨነቀችኝ ሳላውቀው ለወራት አምቄ የያዝኩት ስሜት ገነፈለ... አው እወዳታለው አፈቅራታለውው!!... ደግነቷ የዋህነቷ ቀልቤን ይገዛዋል ሁሌም ስለሷ አስባለው ሁሌም እሷን ማግኘት ለኔ ትልቅ እድል እንደሆነ አስባለው እስከዛሬ እንደሷ አይነት ሴት በህይወቴ አይቼ አላውቅም አንቺን ሳላውቅሽ ነበር እማፈቅርሽ እሷን ግን በግዜ ሂደት ስብእናዋን ሳውቅ ነበር ያፈቀርኳት ላንቺ የነበረኝን ፍቅር አስወጥታ በምትኩ የሷን ንፀህ ፍቅር በልቤ አኖረች ሁሌም ምን አይነት ሴት እንደሆነች እያሰብኩ እደነቃለው እፁብ ግሩም የሆነች ሴት!! እንደሌሎቹ ብልጭልጭ አለም እማያታልላት ሴት! አስተዋይ ሴት። አንቺን ያፈቀርኩሽ መልክሽን አይቼ ነበር እሷን ግን ስብእናዋን አይቼ ነው የወደድኳት። ውበትና ደምግባት ቁንጅና ሁሉም ፈራሽ ናቸው መልክን አይቶ ያፈቀረ ያ.. ያፈቀረው መልክንል ግፕላ ሲያረጅ ሲጠፋ ፍቅሩም አብሮ ይጠፋል ስብእና ግን አያረጅም አይጠፋም ዘላለማዊ ፍቅርን ይሰጣል... ግን.. ግን ምን ያደርጋል ብዬ በረጅሙ ተነፈስኩ በእጄ የደረጃው ላይ መሞነጫጨር ጀመርኩ ግን ምን ያደርጋል ኡፍፍፍ... እሷ ሌላ እምታፈቅረው ሰው አላት አፍቅሮ ማጣትን በደምብ አውቃለው ያፈቀሩት ሰው ሌላ ሰው ሲያፈቅር ማየት ትልቅ ስብራት ነው ባንቺ የተጎዳሁትን ዳግም በሷ መጎዳት አልገልግም ፍቅሬን ቀብሬው ብኖር ይሻላል አልኳትና አገቴን አቀረቀርኩ ኤቤጊያ አይኗ ዳግም በእንባ ተሞላ ወደኔ ተጠግታ አቀፈችኝ ናዲ ለሷ እንዲ የጠለቀ ፍቅር እንደነበረህ አላውቅም ነበር አይዞህ እኔም እንዳንተ ያፈቀሩት ሰው ሌላ ሰው ሲያፈቅር ማየት ምንያህል ቅስም እንደሚሰብር አውቃለው ስሜትህ ይገባኛል አይዞህ ሰምሃል እኔ ባላዋቂነት እንደጎዳሁህ እምትጎዳህ አይነት ሴት አይደለችም አለችኝ አይኖቼ በእንባ ተሞሉ አቢጊ እኔ ግን ለፍቅር ያልታደልኩ ሰው ነኝ ጥሩ ፍቅር መስጠት የሚችል ልብ አለኝ ግን.... ግን.... ማውራት አቃተኝ ይበልጥ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት። ኤቤጊያን ጥብቅ አድርጌ እንዳቀፍኳት ከጀርባዬ ሶስት ሴቶች ሲመጡ ታየኝ ጨለማ ስለነበር አይኔም በእንባ ተሞልቶ ስለነበር ማንነታቸው በውል ለመለየት አልቻልኩም ምንም ሃሳብ አልሰጠኃቸውም ቀልቤን ወደ አቢጊ መለስኩ በቃ አታልቅስ ናዲ በእናትህ አታልቅስ በቃ አለችኝ የራሷንም እንባ ለመቆጣጠር እየጣረች እንባዬን ጠራረግኩ እና እንነሳና እንሂድ በቃ ከዚ በላይ አንቆይ አልኳት እሺ አለችና ተነስታ እጄን ጎተት አድርጋኝ እኔም ተነሳው እዛው እንደቆምን ድጋሚ አቀፈችኝ እኔም አቀፍኳት በጆሮዬ አይዞህ ናዲ አምላክ ላንተ ያላት ከሆነ የትም አትሄድም አንድ ላይ ትሆናላችው አለችኝ። ሶስቱ ሴቶች ከአቢጊ ጀርባ ብርሃን ያለበት ቦታ ላይ ደርሰው ቆመው እኛን እያዩን ነበር ልብ ብዬ አይቻቸው ማንነታቸውን ሳውቅ በድንጋጤ ደርቄ ቀረው ሰምሃል? አልኩ ኤቤጊያ ከጀርባዋ ስላሉ እንዳቀፈችኝ ሳታያቸው አው ሰምሃል አለችኝ። ሰምሃል እየሮጠች ወደኃላ ተመለሰች ሊዲያና ራኬብም ተከተሏት ሰምሃል ብዬ ጮህኩና ኤቤጊያን አስለቅቂያት ወደሷ ሮጥኩ። ይቀጥላል @Lbe_Anteltay @Lbe_Anteltay
Show all...