cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tena ጤና

ይህ ቻናል የተከፈተው በሀገራችን በስፋት የሚገኙ የጤና ዕክሎችን ምንነት፣መንስኤ፣መከላከያ መንገዶች እንዲሁም የህክምና አማራጮች ለመዳሰስና እና ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው።በተጨማሪም ለህክምና ተማሪዎች አጋዥ የሚሆኑ ቪዲዮዎች የሚቀርብበት ይሆናል። እዚህ ቻናል ላይ የሚለቀቁ ቪዲዮዎች በሃኪሞች እየተዘጋጁ የሚቀርቡ ሲሆን፤ሳይንቲፊክ ይዘቱን እንዳይስት በጥንቃቄ የታረሙ ናቸው።

Show more
The country is not specifiedAmharic1 635The category is not specified
Advertising posts
6 325Subscribers
No data24 hours
-327 days
-20130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
✈️️️Ethiopian Airlines 76th Anniversary National Government Shipping Subsidy

🎁️️️ Everyone has only one chance to claim it, and the event will end at the end of this month ️️️

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች  ማህበር የጤና ባለሙያዎችን አስቸኳይ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች  ለከፍተኛ የሀገሪቱ ተቋማትና መሪዎች አቀረበ። በጥያቄዉ የዘመናት የጤና ባለሙያዎች የመብት ጥያቄዎች ተካተዉበታል። የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች፦ 1) የደሞዝ ማሸሻያ ጥያቄ 2) የቤት ጥያቄ 3) የተጋላጭነት /Risk/ጥያቄ/ 4) የትምህርት ዕድል 5)የነፃ ህክምና ጥያቄ 6) የስራ እድል ጥያቄ 7) የትርፍ ስዓት ክፍያ ጥያቄ 8) በጤና ተቋማት የሚታየዉ የግብዓት አጥረትና አስተዳድራዊ ችግሮች ቀጣይ አቅጣጫዎች፦ ከላይ ያቀረብናቸው ህጋዊ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች  ጤና ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የጤና ባለሙያውን ክብር በሚመጥን መልኩ በአግባቡ ይመልሳሉ ብለን እናመናለን ። ነገር ግን እነዚህን ህጋዊና እና ተገቢ  የመብት  ጥያቄዎች መልስ የማይሰጣቸዉ ከሆነ ጤና ባለሙያዎች የሚወስዱት የትኛዉንም አይነት በህጋዊ  መንገድ ተከትለዉ ጥያቄችዉን  የማሰማት ህገመንግስታዊ መብት አላቸዉ ። እንዲሁም ለሚፈጠረው የትኛውም አይነት ችግር ጤና ሚኒስቴርና  የሚመለከታቸው የመግስት ተቋማት ሃላፊነት የሚወስዱ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን ።    የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር!!                   የካቲት 30/06/2015 ዓ/ም                                       አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የጥያቄዉ ሙሉ ዝርዝር ከላይ በደብዳቤዉ ተገልጿል።
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት በሐመር ወረዳ በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተ የዝናብ እጥረት የተነሳ ድርቅ በሰው እና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል። በደቡብ ኦሞ ዞን ስር በምትገኘው ሐመር ወረዳ እንደ ሶማሌ እና እንደ ቦረና ሁሉ ለወረዳው ለአርብቶ አደሮች ጊዜው ከፍቷል ተብሏል። በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተዉ የዝናብ እጥረት የአርብቶ አደሩ የኑሮ መሠረት የሆኑት የቀንድ ከብቶቹ በየጫካና ጥሻዎቹ ውስጥ በተኙበት እየሞቱ ይገኛሉ። አሁን ላይ በሐመር ድርቁ ዕለት በዕለት የአርብቶ አደሩ መተዳደሪያ የሆኑ የቁም እንስሳትን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨረሰ ነው። ውኃ የለም፤ ሣር የለም። አርብቶ አደሩ የእንስሳት ተዋጽዖ በመመገብ ነው የሚኖረው። ዝናብ የለም በዚህ ምክንያት ብዙ ከብቶች እየሞቱ ነው። ሰውም በጣም በከፍተኛ ሁኔታ በረሐብ እየተሰቃየ መሆኑን ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በወረዳው ለተከታታይ አራት ዓመት እና በላይ በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ነው ድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ የተፈጠረው ተብሏል። የእንስሳት መኖ አለመኖሩ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረ ሲሆን በየትኛውም አማራጭ ውኃ ማግኘት ወደማይቻልበት ሁኔታ ተደርሷል። ለ4 አመታትና በላይ በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ እንስሳቱ የሚግጡት ሳር ጠፍቷል። ወንዞች በመድረቃቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው የቀንድ ከብቶች ለሰው ልጅ የመጠጥ ውሃ የተቆፈሩ የጉድጓድ ውሃዎችን ፖምፕ እየተደረጉ ለማጠጣት ቢሞከርም ከአቅም በላይ ሆኗል። የከርሰምድር ውሃ እየሸሸ መሄዱና የፓምፖች ብልሽት እየተከሰተ በመሆኑ በሰው ላይ ከዚህ የከፋ ችግር ከመከሰቱ በፊት መንግስትና አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። #ሐመር_ወረዳ @tikvahethiopia
Show all...
Giant Adrenal Cyst: A Case Report To report a rare case of giant adrenal cyst and also emphasize the option of adrenal-sparing cyst excision im.the management of benign giant adrenal cysts. Abraham Ariaya, Yisihak Suga, Berhanetsehay Teklewold, Ibsa Kedir Hassen, Befikadu Lemu, Engida Abebe
Show all...
ረሃብ እንዴት ይለካል? ባለሙያዎች አምስት የምግብ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመለየት የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ደረጃ ምደባ የሚባል ዓለም አቀፍ መለኪያ ይጠቀማሉ። ደረጃ አንድ፡ ቤተሰቦች በቂ ምግብ እና መሰረታዊ ምግብ ለማግኘት የሚያስፈልጉ እቃዎች አሏቸው። ደረጃ ሁለት፡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን አነስተኛ መጠን ያለው ምግብ ያገኛሉ፣ ነገር ግን ምግብ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ለማግኘት ችግር አለባቸው። ደረጃ ሶስት፡ ቤተሰቦች በቂ ምግብ የላቸውም ወይም ምግብ ለማግኘት ሌሎች ፍላጎቶችን መስዋዕት ማድረግ አለባቸው። ደረጃ አራት፡ ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ወይም በረሃብ እየሞቱ ነው፣ ወይም ረሃብን ለማስወገድ ከባድ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው። ደረጃ አምስት፡ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ ለድህነት እና ለሞት ይዳርጋል። በዚህ ወቅት ነው አንድ አካባቢ በረሃብ ውስጥ እንዳለ የሚታወጀው። ረሃብ ተከሠተ የምንለው በሚከተሉት ጊዜያት ነው፡- 1. በአካባቢው ከ30% በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቂ ምግብ የላቸውም። 2. በአንድ አካባቢ ከሚገኙት ከአምስቱ አባወራዎች አንዱ ከፍተኛ የምግብ እጥረት አለበት። 3. ከ10,000 ሰዎች ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ በየቀኑ በርሃብ ይሞታሉ።
Show all...
#ቦረና በ #ቦረና በታሪክ እጅግ አስከፊ በተባለው ድርቅ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመርዳት የምትፈልጉ በ " #ALCHIISOO_PASTORALIST_UP " በኩል መርዳት ትችላላሁ። የዚህ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (NGO) የባንክ አካውንቶች ፦ 👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000522499823 (Swift Code: CBETETAA) 👉 የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ -  1011800084313 (Swift code: CBO RETAA) 👉 አዋሽ ባንክ - 013081084782900 (Swift code:  AWINETAA) 👉 ኦሮሚያ ባንክ - 1548414100001 (Swift code: ORIRETAA) ቁጥሮች ስለ ቦረና ምን ይናግሩናል ? - በቦረና ዞን 807 ሺህ ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ከነዚህ ውስጥ 167 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አስቸኳይና ተከታታይ ድጋፍ የሚፈልጉ ናቸው። - በዞኑ ካሉት የቀንድ ከብቶች ውስጥ 10 በመቶውን ለመታደግ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ያስፈልጋል። - በድርቁ ምክንያት በዞኑ ከ3 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 % የቀንድ ከብቶች ናቸው። - በዞኑ የቀሩት 230 ሺህ የቀንድ ከብቶች ሲሆኑ፤ ለ3 ወር የቀንድ ከብቶቹን ለመታደግ ቢያንስ 4 ነጥብ 4 ሚሊየን እስር ሳር ማቅረብ ያስፈልጋል። በተጨማሪ 135 ሺህ ኩንታል መኖ የሚያስፈልግ ሲሆን በዞኑ ማቅረብ የተቻለው አንድ በመቶ ብቻ ነው። - የተከሰተው ድርቅ በዞኑ 13 ወረዳዎች አጥቅቷል ፤ በዞኑ ከሚገኘው 60 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ ድጋፍ ይፈልጋል። Via: Tikvah Ethiopia
Show all...
ብዙ ሰዎች ፍራፍሬዎች ብዙውን ጊዜ በስኳር የበለፀጉ በመሆናቸው የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች መመገብ የለባቸውም ብለው ያምናሉ። ነገር ግን ፍራፍሬ ውስጥ ያለው ስኳር አይነት በአንድ ሰው የደም ስኳር ወይም የኢንሱሊን መጠን ላይ ብዙ ተጽእኖ የማይኖረው Fructose ነው። ስለዚህም The National Institute of Diabetes and Digestive and Kidney Diseases የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች በምግባቸው ላይ ፍራፍሬዎችን እንዲያካትቱ ይመክራል። በአጠቃላይ አንድ ሰው ፍራፍሬን ከአመጋገብ ውስጥ ማስወጣት የለበትም። እንዲያውም አንድ የ 2017 ጥናት እንደሚጠቁመው ፍራፍሬ መመገብ የስኳር በሽታን ለመከላከል ይረዳል። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን እንደ (በጣም የበሰለ ሙዝ እና ሃባብ) ያሉ ፍራፍሬዎችን መጥኖ መመገብ ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።
Show all...
Orthognathic Surgery መንገጭላ ቀዶ ጥገና (orthognathic Surgery) ፣ የመንገጭላ አጥንቶችን ብልሽቶች ያስተካክላል እና መንገጭላን እና ጥርሶችን በማስተካከል የስራቸውን መንገድ ያሻሽላል። ይህን ሰርጀሪ ማድረግ የፊት ገጽታዎን ለማስተካከልም ይረዳል።
Show all...
ሰዎች ለምን 32 ጥርሶች ኖረን? የጄኔቲክስ ሊቃውንት ቅድመ አያቶቻችን በመጀመሪያ እያንዳንዳቸው 44 ጥርሶች ነበሯቸው ይሉናል። ምክንያቱ ለብዙ ሚልዮን አመታት ለማኘክ አስቸጋሪ የሆኑ ምግቦችን በጥርሳቸው እየሰበሩ በመመገባቸው ነው። በመቀጠልም የሰው ልጅ አመጋገብ ወደ ለስላሳ ምግቦች በመተካቱ የታችኛው መንገጭላ መጠን ቀንሷል እናም ለመንጋጋ ጥርሶች በቂ ቦታ አልነበረም። ይህም የጥርሳችንን ብዛት ወደ 32 ሊያወርደው ችሏል። በአሁኑ ጊዜ ያን ያህል የደረቀ ምግብ አንመገብም እናም ከ20-22 ጥርስ ለመመገብ ከበቂ በላይ ነው።
Show all...
ቀረፋ የማስታዎስ ችሎታን ይጨምራል! በቅርቡ ተመራማሪዎች የቀረፋን በእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባር ያለውን ተጽእኖ የሚመረምሩ 40 ጥናቶችን ሜታ-ትንተና አድርገው ቀረፋን መመገብ የመማር እና የማስታወስ ችሎታን እንደሚያሻሽል ደርሰውበታል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀረፋ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ጥቅሞችን ከመስጠት ባለፈ የፀረ-ብግነት ፣ የፀረ-ካንሰር እና በሽታ መከላከልን የማጎልበት ባህሪያቶች አሉት። መደምደሚያ ከመደረጉ በፊት ግን ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።
Show all...