cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 🇪🇹ኢትዮጵያ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 @Daily_News_Ethiopian አስተያየትና መልክት ካሎት @Natty19 ምርትና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Natty19

Show more
Advertising posts
8 815Subscribers
-624 hours
-317 days
-11130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጋምቤላ ከተማ ከምሽቱ 12:40 ጀምሮ ለጊዜው ምክንያቱ ባይታወቅም ነዋሪዎች ይህ ፖስት እስከተደረገበት 2:14 ድረስ ያልተቋረጠ የተኩስ ድምፅ እየሰሙ እንደሆነ ነግረውኛል።
Show all...
"መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችንና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆም ከደሙ ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል።" እናት ፓርቲ
Show all...
ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳወቀ::
Show all...
ከባህር ዳር ውጪ ሌላ ቦታ መብራት የለም
Show all...
ሰበር ዜና መብራት በመላ ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ ዛሬ ከቀኑ 9 ሠዓት 46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ ሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ  መሆኑም ተመላክቷል፡፡ እስከዛ ድረስም ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ  ተቋሙ ጠይቋል፡፡
Show all...
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ኢሉ ወረዳ የአስጎሪ ርጳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ************* ታጣቂዎች የካቲት 17 ቀን  2016 ዓ.ም እሁድ ንጋት ላይ ካህናቱ ጸሎተ ኪዳን አድርሰው ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ኦርቶዶክሳውያንን አግተው የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 5ቱ ካህናት ሲሆኑ ቀሪዎቹ 8ቱ ደግሞ ምእመናን ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ስምንቱን ምእመናን እና አስተዳዳሪውን የጠየቁት ገንዘብ ተከፍሎዋቸው የለቀቋዋቸው ሲሆን የተቀሩትን አገልጋይ ካህናት ገንዘብ ቢከፈልም ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸዋል። በታጣቂዎች የተገደሉት አገልጋዮች ስም:- 1.ቀሲስ ቸርነት ብዙወርቅ ቄሰ ገበዝ 2.ቀሲስ ሳሙኤል ወደጆ ቀዳሽ ካህን 3.መሪጌታ  ያሬድ የደብሩ መሪጌታ እንዲሁም 4.ዲ/ን ቤዛ ባዬ የደብሩ ጠቅላላ አገልግሎት ናቸው። በተለይም የደብሩን መሪጌታ መጀመሪያ እጃቸውን ቆርጠው ለውሻ በመስጠት ከዚያ በኋም እያንዳንዱን አካላቸውን በገጀራ በመቆራረጥ እንደገደሏቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል። ሌሎችም አገልጋዮች በተመሳሳይ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም በቾ ወረዳ ሶየማ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ቀሲስ መልአኩ የተባሉ አንድ ካህን መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ታግተው ተወስደዋል። ቶሌ ወረዳ ላይ እንዲሁ አንድ ዲያቆን በመውሰድ ለመልቀቅ አንድ ሚልዮን  ብር እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል።  በመላው ሃገሪቱ ባለው ጦርነትምም ይሁን በታጣቂዎች በሚደረጉ ጥቃቶች አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በተለየ መልኩ ጥቃት እየደረሰባቸው ሲሆን ችግሩን ለማስቆምም ይሁን ታግተው ያሉ ካህናትና ምእመናንን ለማስለቀቅ የሚደረግ መንግስታዊ ጥረት አለመኖሩ መንግስት ራሱ ከአጥቂዎች ወገን መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው። ስለሆነም ምእመናን የተከበረችና የታፈረች ቤተ ክስርቲያንን ለትውልድ ለማሻገር ይቻል ዘንድ  ለሰማዕነት ልንዘጋጅና ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ልንነሣ ይገባል። ©ስምዕ ተዋህዶ
Show all...
😱 3👍 2
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ ታላቁ የጎዳና ላይ #ኢፍጧር ስነስርዓት ከፍተኛ የምዕመናን ቁጥር በተገኘበት ተከናውኗል። ፎቶዎቹ ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኙ ናቸው። #ኢፍጧር #ረመዷን
Show all...
በአዲስ አበባ አፈሳ እንዳለ ምንጮች አድርሰውናል::
Show all...
" ግጭቱ ከ20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም፤ በግጭቱ የሞተ ሰውም የለም  " - በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ግደይ ካልኣዩ " የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  እንዲያስቆመው ተደርጓል " - የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባናል ጥያቄ በሚያነሱበት የራያ አላማጣ አካባቢ ግጭት መነሳቱን አንድ የራያ አላማጣ እና አካባቢው አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለፃቸው ይታወሳል። አመራሩ ፥ " ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በመጣስ ጦርነት ከፍቷል፤ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ የተኩሱ መነሻ በራያ እና ወልቃይት በትምህርት ስርዓቱ ካርታ ላይ ተካተዋል የሚል ነው " ብለው ነበር። በትግራይ በኩል ምን ምላሽ ተሰጠ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የራያ ጨርጨር አስተዳዳሪ አቶ ካልኣዩ ግደይና የክልሉን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም ጠይቋል።   አቶ ካልኣዩ ግደይ በፅሁፍ በሰጡት ምላሽ ፥ " ግጭቱ የተከሰተው መጋቢት 17 /2016 ዓ.ም ቀን ነው። በር ተኽላይና ዶዶታ በተባለ አከባቢ ነው። ቶክሱን የጀመሩት የአማራ ታጣቃዎች ሲሆኑ በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ላይ ቶክስ የከፈቱት በአለማጣ ከንቲባ አቶ አበራ ሃይሉ ጥሪ የተደረገላቸው የአማራ ክልል ታጣቂዎች ናቸው " ብለዋል። ግጭቱ 20 ደቂቃ በላይ አልፈጀም ያሉት አስተዳዳሪው በግጭቱ የሞተ ሰው የለም ብለዋል። " ግጭቱ ሆን ተብሎ  ፦ - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ - የትግራይ ማህበረሰብ ተወካዮች ከጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ያደረጉት ውይይትና የአማራና የትግራይ  ፕሬዚዳንቶች በፕሪቶሪያ ውል አተገባበር ዙሪያ የፈጠሩት መድረክን ተከትሎ 'ውሉ ተግባራዊ ይሆናል' የሚል ስጋት  ስለፈጠረባቸው ነው " ብለዋል። አቶ ካልኣዩ አክለው " የአማራ ክልል ታጣቂዎች ለቀጣይ ትንኮሳ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ደርሰንበታል " ብለዋል። የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የራያ ጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ በፅሁፍ የሰጡት መረጃ እንዲያረጋግጡለት ፤ የትግራይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም አግኝቶዋቸዋል።  አቶ ረዳኢ ሓለፎም ፥ የራያ ጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ መረጃ ' ልክ ነው ' ብለዋል። ከዚህ ባሻገር ፤ " የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ግዛት ውስጥ የፈፀሙት ትንኮሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲያስቆመው ተደርጓል " ሲሉ ተናግረዋል። " የፌደራል መንግስት በትግራይ ግዛት ውስጥ በመግባት ተደጋጋሚ ግጭት በመፍጠር ላይ የሚገኙ የአማራ ክልል ታጣቃዊች በዘላቂነት እንዲያስታግስ እና በሃይል ከያዙት ግዛት ለቀው እንዲወጡ የሚያስገደደው የፕሪቶሪያ የሰላም ውል እንዲተገብር ደግመን ደጋግመን እንጠይቃለን " ብለዋል።  መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።                                              
Show all...
👍 4
ትራምፕ መጽሃፍ ቅዱስ በ60 ዶላር መሸጥ ጀመሩ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ለደጋፊዎቻቸው “አሜሪካን ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
Show all...
ትራምፕ መጽሃፍ ቅዱስ በ60 ዶላር መሸጥ ጀመሩ

አወዛጋቢው ሰው አዲሱን ዘመቻ የከፈቱት በቀጣዩ ምርጫ የክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ቁጥር ለማበራከት ነው ተብሏል

Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!