cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Christ for All Nation

@Andulahulu በአንዱ አለመታዘዝ ብዙዎች ኅጡአትኞች እንደ ሆኑ እንዱህ ደግም በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻደቃን ይሆናል::(ወደ ሮም ስዎች 5:19) Share በማድረግ ወዳጆቻችሁን ጋብዙልኝ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
376Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰው ከልቡ መኖር ባቆመበት ዘመን ከልቡ የሚወድ ሰው መፈለግ ሞኝነት ነው ። የእውነት ወዳጅ ኢየሱስ👈ብቻ ነው ብቻ ነው። ((✍ስለ ህይወት✍)) ይ🀄️ላ🀄️ሉን👉✅Andulahulu✅ 👉✅@Andulahulu✅ 👉✅@Andulahulu✅ ሼር ይደረግ 👆👆👆👆👆
Show all...
ቤት ሲፀዳ እቃዎች የት እንደተቀመጡ እንኳን ይጠፋሉ።ሰላም የነበረው ቤት ትርምስምሱ ይወጣል🤔ተፀድቶ ሲያልቅ ግን ሁሉም ቦታ ቦታውን ይይዛል የጠፋው ይገኛል😃 የማያስፈልገው ይጣላል።በህይወታችንም እንዲሁ ነው ።እግዚአብሔር ቤቱን ሊያስተካክል ሲፈልግ ነገሮች የተተራመሱ ይመስላሉ ።ስራው ሲያልቅ ግን ሁሉሞ ነገር ውብ ይሆናል 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 እግዚአብሔር መልካም ነው ❤️ 😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍 ይ🀄️ላ🀄️ሉን👉✅@Andulahulu✅ 👉✅@Andulahulu✅ 👉✅@Andulahulu✅ ሼር ይደረግ 👆👆👆👆👆
Show all...
💢መልስ አለው ⛔️ድመትና አንበሳን ለፍልሚያ አቅርቦ ማን ያሸንፍ ይሆን እያለ ሀሳብ የሚገባውና የፍልሚያውን ፍፃሜ በጉጉት የሚጠባበቅ የለም ምክንያቱም ማን እንደሚያሸንፍ የታወቀ ነው ። አንበሳው በፈለገው ሰአትና በፈለገው አይነት መልኩ በቀላሉ ሳይቸገር ድመቷን እንደሚበላት እርግጥ ነው። ከፈለገ ያቆያታል ከፈለገም ወዲያው አንስቶ ይበላታል። የሚጠበቀው ድመቷን ወደ አንበሳው ማቅረብ ነው። : 〽️የእኛም የሰዎች ጭንቀትና የእግዚአብሔር ሀይል ልክ እንዲሁ ነው እኛን ግራ አጋብቶ ያቅበዘበዘን፣ መልስ አትጠንለት የተቸገርንበት፣ ከሰው በታች የሆንንበት ፣ያስናቀንና ስልችት ምርር ያለን ያ ጉዳይ ለሱ ቀላሉ ነው ። : 〽️ከኛ የሚጠበቀው ጉዳያችንን ለባለሀይሉ ኢየሱስ መስጠት ነው እንጂ ጥያቄዬ እንዴት ይመለስ ይሆን ፣ይሄን ቀን እንዴት ነው የማልፈው ፣ ማን አለኝና በማን ልመካ አይባልም። እርሱ እንዴት እንዲያድን መላ ጠፍቶበት አያውቅም ይመልስልኝ ይሆን ወይ ያግዘኛል ወይ ብሎ መጨነቅም ከንቱ ድካም ነው። እግዚአብሔር እንደሰው አይደለም ሁሉን ቻይ ነው። : 〽️ማንነታችንን እንስጠው ችግር የምንለውን ችግር ጠቅልለን ለባለመልሱ ኢየሱስ እንስጥ። : ⭕️ ከችግራችንና ከኢየሱስ ማን ያሸንፋል ብለን መጨነቅ ድመት አንበሳን ያሸንፋል ወይ?ብሎ እንደማለት ነውና ከፍልሚያው እኛ እንውጣ ። አንበሳው ኢየሱስ በራሱ ጊዜ በራሱ መንገድ በራሱ ሀሳብ 👉 ለችግራችን መፍትሄ 👉ለጥያቄአችን መልስ 👉ለጭንቀታችን እረፍትን ይሰጠናል ። ✅ከኛ ሚጠበቀው በችግራችንና በእግዚአብሔር መካከል በሚደረገው ፍልሚያ ውስጥ አለመግባት ብቻ ነው ። መልስ አለው ኢየሱስ💯!!!!!!!! Share it👇👇👇👇👇 ✅@Andulahulu✅ ✅@Andulahulu✅ ✅@Andulahulu✅ ሼር ይደረግ👆👆👆👆👆
Show all...
ንግግር ያለ አድማጭ ትርፉ ራስ ምታት ብች ነው። የትኛውም የህይወታችን እርምጃ ያለ ኢየሱስ ቅዠት ነው @Andulahulu @Andulahulu
Show all...
📔Title:-Jesus Among Secular Gods 👤Author:-Ravi Zacharias, and Vince Vitale Published © January 3rd 2017 📑Page:- 236 @Andulahulu
Show all...
📔Title፦ Has Christianity Failed You? 👤Author፦ Ravi Zacharias Year © July 10th 2010 📑Page፦ 305 @Andulahulu
Show all...
📔Title:-Jesus Among Secular Gods 👤Author:-Ravi Zacharias, and Vince Vitale Published © January 3rd 2017 📑Page:- 236 @Andulahulu
Show all...
📔Title፦ Has Christianity Failed You? 👤Author፦ Ravi Zacharias Year © July 10th 2010 📑Page፦ 305 @Andulahulu
Show all...
አሁንድ ደግሞ በእጄ ያሉ የራቪ ዘካርያስ መጽሐፎችን ልጋብዛችሁ! መጽሐፎች ጠንካራ እንደሚያደርጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ቢያንስ ስለእምነቱ በደንብ የሚሞግት ፣ ለተቋዋሚዎች ጥሩ መልስን የሚሰጥ አንድ አቅብተ እምነት(Apologist) እንደሚሰራ እጠብቃለሁ። (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:15) ይለቀቅ?
Show all...
👍 5
👎 2
ራቪ ዘካርያስ ይባላል። ከክርስቲያን ወላጆች ማድራስ(Madras) በምትባል የህንድ ግዛት እ.አ.አ 1994 የተወለደ ካናዳዊ-አሜርካዊ ዜግነት ያለው ተወዳጅና የክርስቶስን ወንጌል ለብዙዎች ያደረሰ አዕቅብተ-እምነት(Apologist) ነው። "Let My People Think and Just Thinking" የተሰኘ ሬዲዮ አዘጋጅና ተናገሪ ነው። "ክርስቲያኖች ለሚያምኑት የክርስቶስ ተስፋ መልስን ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ እንዲሆኑና ስለእምነታቸውን ርዕቱ ሙግቶችን በመጠቀም ያላቸውን እውነት እንዲገልጡ በስፋት ያስተምራል። በብዙ ዪንቨርስቲዎች ፣ ኮሌጆች ፣ የተለያዩ ክርስቲያናዊ ስብስቦች በመታደም ወጣቶችን ያስተምራል። በግብረ-ገብነት ፣ ስነምግባር ፣ በሞራላዊ ጉዳዮች ፣ ስለእግዚአብሔር መኖር ፣ ስለመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኝነት ፣ "ስለስቃይ ፣ ሰይጣንና የእግዚአብሔር ምላሽ" ፣ አይነኬ ፣ አይዳሰሴና በብዙ ሰባኪዎች የማይዳሰሱ ርዕሶች በመዳሰስ የወጣቶችን የነፍስ ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመመለስ ለክርስቶስ ይማርካል። ክርስቲያን ባልሆኑ ሰዎች የሚሰነዘሩ ትችቶችን ፣ ጥያቄዎችን ርዕቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊና አመክኗዊ መልሶችን በመስጠት የክርስቶስ ምስክር መሆኑን አስመስክሯል። ሳም ሐሪስ(Sam Harris) የተባለ ታዋቂ ኢ-አማኝ(Atheist) ክርስትናን ላጥላላበት "The End of Faith" እና "Letter to a Christian Nation" ለተሰኘው መጽሐፉ ራቪ ዘካርያስ "The End of Reason: A Response to the New Atheists" በሚል በ2008 የጻፋት የመልስ ምት አንዱ ማሳያ ነው። በ1984(እ.እ.አ) Ravi Zacharias International Ministries(RZIM) በቶሮንቶ በመመስረትና መጀመር ስለክርስትና መልስ ለሚፈልግና ጥያቄ ላላቸው ሁሉ ተደራሽ የሚሆኑበትን አድማስ አሰፋ። በዚህ ብቻ አላበቃም ተቀማጭነቱን ወደ ካናዳ ፣ ሆንግ ኮንግ ፣ ህንድ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቱርክ ፣ እስፔን ፣ ሲንጋ ፖር ፣ ዩናይትድ ኪንግደም.....ወዘተ ፡ ማስፋት ችሏል። በውስጡም ከሁለት አመት በፊት ወደ ጌታ የሄደውን ነቢል ቁረሺ(Nabeel Qureshi) ፣ አብዱ ሙረይ(Abdu Murray) ጨምር ብዙ ትላልቅ ሊቃውንቶች የያዘ ግዙፍ አግልግሎት ለመሆን በቅቷል። ሌላው ራቪ የሚታወቅበት አንዱ ብዙ መጽሐፍትን በመጻፍ ነው። ብዙ ተወዳጅነትን ፣ ተነባቢነትን ያተረፉና ብዙ ሽልማቶችን ያስገኙ መጽሐፍት ደርሷል። በግሉና ከሌሎች ጸሐፊዎች ጋር በመተባበር ከ25 በላይ መጽሐፍቶችን ለአንባቢያን አድርሰዋል። ለአብነት ያህል A Shattered Visage: The Real Face of Atheism(1994, 2004) ፣ Is Your Church Ready?: Motivating Leaders to Live an Apologetic Life (2003) (Editor, with Norman Geisler) ፣ Who Made God? And Answers to Over 100 Other Tough Questions of Faith (2003) (General Editor, with Norman Geisler) ፣ The Logic of God: 52 Christian Essentials for the Heart and Mind (2019)። "Can Man Live Without God?" የተሰኘው መጽሐፍ 1995 "በስነመለኮትና ዶክትሪን" ዘርፍ ከEvangelical Christian Publishers Association የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነበር። ወንጌላዊያን ጸሐፊዎች ተጽፈው ፡ ብዙ ተነባቢነት ያገኙ መጽሐፍቶች ዝርዝር የሚያወጣው Christian Booksellers Association ማኅበር "Light in the Shadow of Jihad" የተሰኘውን በ2002 ፣ "The Grand Weaver" የተሰኘውን በ2007 "በብዙዎች" ተነበዋል ሲል እውቅናን ሰጥቶ ነበር። ራቪ ዘካርያስ የቅድመ-ክርስትና ሕይወቱ ምን ይመስላል? እንዴት ወደ ክርስትና መጣ? ምንም እንኳ ፈርሃ-እግዚአብሔር ካላቸው ክርስቲያን ወላጆች ቢወለድም ቅሉ ፣ "የእሳት ልጅ አመድ" እንዲሉ ራቪ ሕይወቱን ወደ ኢየሱስ ብርሃን የሚጠራ አጋጣሚ እስከሚፈጠርበት ድረስ በእግዚአብሔር መኖር የማያምን(Atheist) ነበር። እድሜው 17 ሲደርስ ዓለም የጨለበት ራቪ ይህቺን አስቀያሚና ትርጉም አልባ ዓለም በሞት ሊሰናበታት በማሰብ መርዝ በመጠጣት ፡ እራሱን በመሳቱ ሆስፒታል ይወሰዳል። ይህን ጊዜ ነበር በሆስፒታሉ የምትሰራ አንዲት ክርስቲያን ሴት ፣ ለራቪ እናት ለራቪ ዮሐንስ ወንጌል 14 እንድታነብለት በማሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠቻት። በፕሪንስተን ዩንቨርሲትዪ(Princeton University) "ለምን ኢ-አማኝ አልሆንኹም(Why I'm Not an Atheist)" በሚል ርዕስ ባስተማረበት ወቅት ስለዚህ አስደናቂ ትዕይት ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር[1]። በዮሐ 14:19 የሚገኘው " .... እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።" ይህ ቃል ሞት ያጠላበትን የልቡን ጨለማ በማጥፋት የኢየሱስ ብርሃን ጮራ እንዳፈነጠቀ ከመናገር አልቦዘነም። "This may be my only hope: A new way of living. Life as defined by the Author of Life." በአልጋው እንደተጋደመ ኢየሱስ ከሆስፒታሉ በሰላም እንዲያወጣው በመለመን ፣ እንድሜ ዘመኑን የእርሱን እውነት እንደሚሰብክ ቃል በመግባት ጸለየ፦ "Jesus if You are the one who gives life as it is meant to be, I want it. Please get me out of this hospital bed well, and I promise I will leave no stone unturned in my pursuit of truth." ራቪ አዲስ ሕይወት ፣ ከኢየሱስ ጋር ጀመረ። ከህንድ ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ካናዳ በመምጣት ኑሮአቸውን መሰረቱ(1866)። ራቪ ካናዳን ከመጡ በ6 ዓመቱ በ1972 የስነ መለኮት ድግሪው በTyndale University College & Seminary እና በስነመለኮት ማስተርሱን(Master of Divinity [MDiv]) ከTrinity International University ተቀበለ። ከዚህ በኋላ ራቪ በብዙ ቦታዎች እየተጋበዘ ስለክርስቶስ መስበክን ቀጠለ። ተስፋ በሌለበት በሞት መካከል ያለፈው የጌታ ባርያ ፣ ቃል የገባለትን እርሱን(ኢየሱስን) ሲያገለግል ይኸው ድፍን 48 አመታት ሞሉት። ብዙ ያልተወሱ ፣ ያልተነሱ ጉዳዮች እንዳሉ አውቃለህ። ለዚህ ገጽ ይህንን ያህል ካልኩ ይበቃል። ____ የግርጌ ማስታወሻ፦ [[1]"Ravi at princeton university 'Why I'm not Atheist"](https://m.youtube.com/watch?v=d6aDoOzYN-U) ምንጭ፦ [*RZIM](https://www.rzim.org/speakers/ravi-zacharias) [**Christianity today በስፋት ተጽፏል ፣ ጠቅ ያድርጉ](https://ai.christianitytoday.com/cti/adclick/FCID=69231/viewid=39276326/random=2812679276/site=ctmag/area=article/position=mobile_1/size=320x50/category=/keyword=YouthforChrist(YFC),TheologyandSpirituality/platform=android/status=guest/visit_source=)
Show all...