cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቅዱሳንን እናስተዋውቃችሁ

"እኔ ግን እላለሁ.! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም ፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ በቻናልችን ላይ ያልችሁን አስየያየት ጥቆማ በ ቀጥታ @zeeaman ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
176Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የ ኦርቶዶክስ ተዋእዶ መዝሙር ᝪℛᝨᝪⅅᝪᝣ ᝨℰℰᗅℍⅅᝪ ℳℰℤℳႮℛ ℬℂℍᗅᗅ!  💒✍ᗅⅅⅅⅈՏ ᗅⅅⅅⅈՏ ℳℰℤℳႮℛ   💒✍ℽℰℰ ᗅℽⅈℳᗅℕᝪᝨᗅᗯⅈ ℙℂ.               ★ ℒⅈℽႮ ℒⅈℽႮ ℕℰℊℰℛᝪℂℍ.  💒 ℽⅈℊᝪℬℕℊႮℕ.                                               ℱᝪℛ ᗅℕℽ ℂᝪℳℳℰℕᝨՏ    👇👇👇👇👇👇       @Yee_maryam 👆👆👆👆👆👆👆👆 https://telegram.me/ort_mezmur
Show all...
የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ✞

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን። በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። መራግብራችን :-👇👇 ✅የበገና መዝሙሮች ✅ የንስሐ መዝሙሮች ✅ ያሬዳዊ ዜማ ✅ ስብከቶች ✅ የማርያም ውዳሴዎች ✅ መፅሐፍ ሀይማኖት........ ወዘተ @Orthodox_tewahdo_mezmurbot

#ጥር_21 በዓለ ዕረፍታ ለቅድስት ድንግል ማርያም "ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው፡፡ከድካማቸውም ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል፡፡ ራእ14፡13 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአባትና ከእናቷ ጋር 3 ዓመት በቤተ መቅደስ 12 ዓመት ከልጃ ጋር 33 ዓመት ከ 3 ወር ጌታ ከዐረገ በኋላ 15 ዓመት ከዮሐንስ ጋር በድምሩ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት በዕለተ እሁድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው እሱም በሲኦል ወስዶ የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳያት እሷም እነዚህን በሲኦል የሚሰቃዩትን ነፍሳት ከማርክልኝ በእነርሱ ፋንታ ይሁን አለችው፡፡ ጌታም ሊምርላት ቃል ኪዳን ገብቶ ቅዱስ ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ በሲኦል የሚሰቃዩ ነፍሳትም ከሞት ጉድጓድ ወተዋል፤የእናታችን የድንግል ማርያም ዕረፍቷ መድኃኒት ሆኗቿል፡፡ሐዋርያትን ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሷቸው እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ የእመቤታችንን ቅዱስ ሥጋዋን በክብር አድርገው ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አዩ ከዚህ በፊት ልጃን ተነሣ፣ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሣች፣ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? "ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም፤ኑ የማርያምን ሥጋዋን እናቃጥላት" ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸውም ታውፋንያ የተባለ በድፍረት ዘልሎ የአልጋዋን ሸንኮር ያዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው በድያለው ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት አዛኝ ናትና ቀና ብላ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት አለችው እሱም ቢመልሰው እንደነበረ ሆኖለታል፡፡ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀምጧታል፡፡ እግዚአብሔርን አምኖ መሞት ለክብር ያበቃል፡፡የእመቤታችን ዕረፍት እንጂ ሞት አይደለም፡፡ እንዳመንን ኖረን ብንሞት እንከብራለን እናም እርሱን በማምለክ እንጽና፡፡ እስከ መጨረሻውም እርሱን በማምለክ እንድንጸና እርሱ በቸርነቱ ይጠብቀን
Show all...
ነህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ያን ጊዜም በሬው አፍ አውጥቶ ‹‹እኔ አምላክ አይደለሁም፣ ሰይጣን በእኔ ላይ አድሮ ሰዎችን እንዳስት አደረገኝ እንጂ›› ብሎ ከተናገረ በኋላ በሬው ተነሥቶ የቅዱስ ፊላታዎስን ወላጆች በቀንዶቹ ወግቶ ገደላቸው፡፡ ቅዱስ ፊላታዎስም በሬውን አመድ እስከሚሆን ድረስ በእሳት አቃጥሎ በነፋስ አስበተነው፡፡ በወላጆቹም በድን ላይ ከጸለየ በኋላ ነፍሳቸው ተመልሳ ከሞት ተነሡ፡፡ በሲዖልም ያዩትን ሥቃይ ለልጃቸው ነገሩት፡፡ ቅዱስ ፊላታዎስም ወላጆቹን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲጠመቁ አደረጋቸው፣ እርሱም ተጠመቀ፡፡ ቅዱስ ፊላታዎስም ሀብተ ፈውስ ተሰጥቶት ሕሙማንን የሚፈውስ ሆነ፡፡ ወሬውም በከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ መልእክተኞቹንም ልኮ ወደ እርሱ አስመጣውና ለአጵሎን ዕጣን ያሳርግ ዘንድ አዘዘው፡፡ ማባበያም ብዙ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ቅዱስ ፊላታዎስም በፍጹም ልቡ በክርስቶስ እንደሚያምን ሲነግረው ልዩ ልዩ የሆኑ ጽኑ ሥቃዮችን አደረሰበት፡፡ ነገር ግን በጌታችን ኃይል ዳነ፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ይረግማቸው ጀመር፡፡ ንጉሡም ጥርሶቹን ሰብሮ ምላሱን አስቆረጠው፡፡ አሁንም ጌታችን ያለ ጥፋት ጤነኛ አደረገው፡፡ ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ፊላታዎስን በድጋሚ ሊሸነግለው በሞከረ ጊዜ ቅዱስ ፊላታዎስ ሊዘባበትበት ፈልጎ የውሸቱን እሺ አለው፡፡ ንጉሡም በከተማው አዋጅ ነጋሪ በማዞር ‹‹ሁላችሁ አሕዛብ ኑ ፊላታዎስ ለአማልክት ሲሠዋ ታዩ ዘንድ ሁላችሁ ተሰብሰቡ›› ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ጣዖታቱንም በጎዳናዎች ላይ ሲያመጡአቸው ባየ ጊዜ ቅዱስ ፊላታዎስ ጣዖታቱንና አገልጋዮቻቸውን ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያውም ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ያዩ ብዙዎች በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አመኑ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ የንጉሡ መኰንኖች አሉበት፡፡ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ ራስ ራሶቻቸውን አስቆረጣቸውና የሰማዕትነት ክብርን ተቀበሉ፡፡ ቁጥራቸውም ዐሥር ሺህ አምስት መቶ ሦስት ነበር፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ቅዱስ ፊላታዎስን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ጥር 16 ቀን አንገቱን በሰይፍ አስቆረጠውና ሰማዕትነቱን ፈጸመ፡፡ የቅዱስ ፊላታዎስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን! + + + ዳግመኛም በዚህች ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ እናት ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕትነቷን በጥር 16 ቀን ፈጽማ የክብር አክሊልን ተቀዳጅታለች፡፡ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ ዓሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎችም የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ያረፉት በዚህች ዕለት ነው፡፡ የቅድስት ኢየሉጣና የሰማዕታቱ ዜና ገድላቸው ከአባታቸው ከሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ገድል ጋር በጥር 15 ላይ ተጽፏል፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን! +++ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ታላቁ አባት አባ ጽሕማ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ነገር ግን በዚኽች ካረፉ በኃላ ከሞት ተነሥተው ከ3 ቀን በኃላ ድጋሚ አርፈዋል፡፡ ገድላቸውን ጥር 19 እናየዋለን፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
Show all...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም አሜን ጥር 16-በላም ላይ አድሮ ይመለክ የነበረውን መረግድ የሚባለውን ሰይጣንና አምኮተ ጣዖትን ሰባብሮ ያጠፋው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፊላታዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ማኅበርተኞቹ የሆኑ ዓሥር ሺህ አምስት መቶ ሦስት መኳንንቶችም በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ + ከዋሻ ሳይወጣና የሴቶችን ፊት ሳያይ 50 ዓመት የኖረው የከበረ አባት አባ ጰላድዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ + የሞተውን ሰው አስነሥተው ያስመሰከሩት የሶርያው አባ ዳንኤል ዕረፍታቸው ነው፡፡ + ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ታላቁ አባት አባ ጽሕማ ዕረፍታቸው ነው፡፡ + ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ እናት ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕትነቷን በድል ፈጸመች፡፡ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ ዓሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎችም የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ያረፉት በዚሁ ዕለት ነው፡፡ አባ ዳንኤል ዘሶርያ፡- ዓምድ ከሚባል ሀገር የተገኘ የሶርያ ሊቅ ነው፡፡ አባታቸው በወርቅና በብር እጅግ ባለጸጋ ነበሩ፡፡ አባታቸውም በሞቱ ጊዜ የሀገረ ዓአምድ ሊቀ ጳጳስ በሚገባ አሳደጓቸው፡፡ መጀመሪያ ድቁና ቀጥሎም ቅስና ከሾሟቸው በኋላ አመነኮሷቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ዳንኤል ከሰንበት እስከ ሰንበት በመጾም በመጸለይ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ ሀብተ ፈውስም ተሰጣቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የሴቶችን ፊት እንዳያዩ ከጌታችን ጋር ጽኑ መሐላ አደረጉ፡፡ ወላጅ እናታቸውም ስለ እርሳቸው ወሬያቸውን በሰማች ጊዜ ልትጠይቃቸው መጣች፡፡ እንድታያቸውም መልዕክት ላከችባቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹የሴቶችን ፊት እንዳላይ በጌታችን ፊት ምያለሁ›› አሏት፡፡ እርሷም ‹‹እኔ እናትህ አይደለሁምን? እንዴት እንደ ሌሎቹ ሴቶች ታስመስለኛለህ?›› አለቻቸው፡፡ እምቢ ባሏትም ጊዜ ‹‹ሁለት ሴቶች አንድ ልብስ ለብሰው እያዩህ ሲጠቃቀሱብህ እግዚአብሔር ያሳየኝ›› ብላ ረገመቻቸውና ተልሳ ሄደች፡፡ ከጥቂት ቀን በኋላ አንድ ምእመን ሰው ለሊቁ ዳንኤል 300 የወርቅ ዲናር ወሰደላቸው፡፡ በማታም ከሊቁ ዳንኤል ደጃፍ ሲደርስ አብሮት የነበረ ወዳጁ ስለ ወርቁ ብሎ ገደለው፡፡ ስለሟቹም ጉዳይ የዓምድ ሀገር ንጉሥ በሰማ ጊዜ አባ ዳንኤልን ካሉበት አስጠራቸው፡፡ በውሽባ ቤት ያሉ ሁለት ሴቶች የአባ ዳንኤልን መምጣት ወሬውን በሰሙ ጊዜ ከችኮላቸው ብዛት የተነሣ ያዩአቸው ዘንድ አንድ ልብስ ለብሰው ወጡ፡፡ አባ ዳንኤልም እናታቸው የተናገሯቸው መርገም ስለደረሰባቸው በአግራሞት ፈገግ ብለው ሳቁ፡፡ ንጉሡም ስለሞተው ሰው አባ ዳንኤልን በመረመራቸው ጊዜ ‹‹እኔ አልገደልኩትም ነገር ግን የገደለውን ራሱ የሞተው ሰው ይናገር›› አሉት፡፡ በዚያም ጊዜ ሟቹ በአባ ዳንኤል ጸሎት ከሞት ተነሥቶ ገዳዩን ተናገረ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በአባ ዳንኤል ፊት ሰገዱ፡፡ ንጉሡም እጅ መንሻ ብዙ ወርቅ ሲሰጣቸው አልቀበልም ብለው ወደ በዓታቸው ተመለሱ፡፡ ንጉሡም ትልቅ ገዳም ሠራላቸውና ገዳሙ የብዙ መነኮሳት መሰባሰቢያ ሆነ፡፡ አባ ዳንኤልም ከሸመገሉ በኋላ ጥር 16 ቀን በሰላም ዐረፉ፡፡ + + + አባ ጰላድዮን፡- ይኽም ቅዱስ አባት ከዋሻ ሳይወጣና የሴቶችን ፊት ሳያይ 50 ዓመት የኖረ ነው፡፡ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን የማድረግና ትንቢትን የመናገር ሀብት ተሰጠው፡፡ ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ፡፡ በምስር አገር አንድ ነጋዴ ነበር፡፡ እርሱም ይነግድ ዘንድ በመርከብ ተጭኖ ሄዶ ሳለ ማዕበል ተነሥቶበት ለመስጠም ደረሰ፡፡ በዚህም አስጨናቂ ጊዜ ያ ነጋዴ ‹‹በአባ ጰላድዮን ጸሎት ተማጽኛለሁ፣ ከሞት ከዳንኩ መቶ የወርቅ ዲናር ለእርሱ እሰጣለሁ›› ብሎ ጨኸ፡፡ እንዲህም ብሎ በተናገረ ጊዜ ወዲያው መርከቡን በመስቀሉ ሲቀዝፍ አባ ጰላድዮንን አየው፤ ከመስጠምም አድኖት ወደ ወደብ በሰላም አደረሰው፡፡ ነጋዴውም የተሳለውን መቶ ወርቅ ዲናሩን ይዞ ወደ አባ ጰላድዮን ሄደ፡፡ በመንገድም ሳለ መሽቶበት በእንግዶች ማደሪያ አደረ፡፡ በዚያም ሞሪት የሚባል አንድ ሰው አገኘና በልቡ ያሰበውን ምሥጢሩን ነገረው፡፡ ሞሪትም ‹‹እኔ ቦታውን ዐውቀዋለሁና አድርስሃለሁ›› ብሎት በማግሥቱ ሁለቱም ተያይዘው ወደ አባ ጰላድዮን ዘንድ ሄዱ፡፡ ነጋዴውም ይዞ የመጣውን መቶ የወርቅ ዲናር ለአባ ጰላድዮን ሰጠው፣ ነገር ግን አባ ጰላድዮን ባረከውና ወርቁን እንደማይስድ ነገረው ይልቁንም ወስዶ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች እንዲበትነው ነገረው፡፡ ነጋዴውም ከአባ ጰላድዮን እግር ሥር ወድቆ በለመነው ጊዜ ለበረከት ይሆንለት ዘንድ ጥቂት ወሰደለትና ለድኆች ወስዶ እንዲሰጥ ነገረውና ባርኮ አሰናበተው፡፡ ነጋዴውም ወርቁን ይዞ በተመለሰ ጊዜ ከተራራው ወርዶ ከወንዝ እንደደረሰ ሰይጣን በሞሪት ልብ አደረና ወርቁን ሊወስድ ወደደ፡፡ ነጋዴውንም ገደለውና ወርቁን ወሰደ፡፡ በሌሊትም የነጋዴውን አስክሬን ተሸክሞ ወስዶ በአባ ጰላድዮን ደጅ ጣለው፡፡ በማግስቱም ወደ አገረ ገዥው ሄዶ ነጋዴውን አባ ጰላድዮን እንደገለደው አስመስሎ አወራ፡፡ አገረ ገዥው መኮንንም ሄዶ አባ ጰላድዮንን አሠረውና ስለ ነጋዴው ግድያ መረመረው፡፡ አባ ጰላድዮንም ‹‹እኔ አልገደልኩትም›› ቢለው አላምን አለው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጰላድዮን ወደ አስክሬኑ ቀርቦ ቃሬዛውን ይዞ ከጸለየ በኋላ ‹‹አንተ በድን ሆይ ማን እንደገደለህ ተነሥተህ ትናገር ዘንድ በእግዚአብሔር ስም አዝሃለሁ›› አለ፡፡ ወዲያውም ያ የሞተው ነጋዴ ከሞት አፈፍ ብሎ ተነሣና ስለ ወርቁ ብሎ ሞሪት በወንዙ ዳር እንደገደለው ተናገረ፡፡ መኮንኑም ይህንን ተአምር ባየ ጊዜ ደንግጦ ለአባ ጰላድዮን ሰገደለት፡፡ በላዩም ክፉ ስላደረገ ተጸጽቶ ሞሪትን ሊገድለው ወደደ ነገር ግን አባ ጰላድዮን አስተወው፡፡ አባ ጰላድዮንም ከብዙ ተጋድሎ በኋላ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሰኝ ኖሮ በሽምግልናው ወቅት በዚሀች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን! + + + ሰማዕቱ ቅዱስ ፊላታዎስ፡- ቅዱስ ፊላታዎስ ከአንጾኪያ ሰዎች ወገን ነው፡፡ ወላጆቹም መረግድ የሚባል ሰይጣን ያደረበትን ላም ያመልኩ ነበር፡፡ የተፈተገና የበሰለ በሰሊጥ ቅባትና በማር የተለወሰ ስንዴ ይመግቡታል፡፡ ሁልጊዜም የተወደደ የሽቱ ቅባት ይቀቡታል፡፡ የወይን ጠጅም ያጠጡታል፡፡ በአንገቱም የወርቅ ዛምጅርና ድሪ አለ፡፡ ይህ መልኩ እጅግ የሚያምረው ቅዱስ ፊላታዎስም ዓሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለዚያ በሬ ይሰግድ ዘንድ ወላጆቹ አዘዙት፡፡ ሕፃን ፊላታዎስ ግን ቃላቸውን አልተቀበላቸውም፡፡ በዚህም ጊዜ ገና የክብርን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አያውቀውም ነበር፡፡ ፀሐይም አምላክ ይመስለው ነበር፡፡ በፀሐይም ፊት ቆሞ ‹‹አንተ ፀሐይ አምላክ ከሆንክ ታስረዳኝ ዘንድ እለምንሃለሁ›› አለው፡፡ በዚህም ጊዜ ከፀሐይ ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ፡- ‹‹እኔ አንተ ልታውቀውና ስለ ከበረ ስሙ ደምህ ይፈስ ዘንድ ያለህ አምላክ አይደለሁም›› የሚል ድምፅ መጣለት፡፡ ሕፃን ፊላታዎስም ይህን በሰማ ጊዜ ልቡ ጸና፡፡ በዚያችም ሰዓት አንድ መልአክ ተላከለትና የአምላክን ምሥጢር አስረዳው፡፡ የሚነግረውንም ያስተውል ዘንድ ልቡን ከፈተለት፡፡ መልአኩም ከዓለም መፈጠር ጀምሮ ጌታችን ሰው እስከሆነበት ዘመን ድረስ ያለውን የሃይማኖት ምሥጢር ሁሉ አስተማረው፡፡ ከዚህም ጊዜ ጀመሮ የሚጾምና የሚጸልይ ምጽዋትንም የሚሰጥ ሆነ፡፡ ከዓመትም በኋላ ወላጆቹ ለልጃቸው ባልንጀሮች ሁሉ ምሳ አዘጋጁና ከምግብና ከመጠቱ በፊት ቅዱስ ፊላታዎስን ለዚያ በሬ ዕጣን እንዲያሳርግ ወላጆቹ ጠየቁት፡፡ ፊላታዎስም በሬውን ‹‹ሰዎች ሁሉ የሚያመልኩህ በእውነት አንተ አምላክ
Show all...
††† እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: ††† ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? ††† ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል አፈ ወርቅ ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ) በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: "ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ - የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: "ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: 'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: በዚህ ቀን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጉዋል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኩዋል:: ††† ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- *ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ *አፈ በረከት *አፈ መዐር (ማር) *አፈ ሶከር (ስኩዋር) *አፈ አፈው (ሽቱ) *ልሳነ ወርቅ *የዓለም ሁሉ መምሕር *ርዕሰ ሊቃውንት *ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) *ሐዲስ ዳንኤል *ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) *መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ *ጥዑመ ቃል
Show all...
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ "ይህን ባሰብኩ ቁጥር"
Show all...
ዲ/ን ዘአማኑኤል "የምናመሰግንበት ምክኒያት ብዙ ነው"
Show all...