cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

Show more
Advertising posts
429Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
እግዚአብሔር ከጠላት ቤት ወዳጅ ያዘጋጃል!! ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቀጠሮ ይዟል። ሁሉም ሰው ከንጉሡ ጋር ለመስማማት ማሰብ አይጠበቅበትም። ዳዊትን መግደል ያሸልማል እንጂ አያስወቅስም። በዚህ ሁኔታ የዳዊት ወዳጅ መሆን አይታሰብም። እግዚአብሔር ግን የሳኦልን ልጅ የዳዊት ወዳጅ አደረገው። የጠላትህን ልጅ #ለአንተ #እንዲሠራ ማድረግ ይችላል። ዮናታን ከአባቱ ጋር ተስማምቶ ዳዊትን በመግደል ቀጣዩ የእስራኤል ንጉሥ ለመሆን አላሰበም። የራሱን ጥቅም ለማስከበር አልሮጠም። ለሥጋዬ (ለአባቴ) ላድላ አላለም። እንደ ነፍሱ ከወደደው ከዳዊት ጋር ላቆመው ኪዳን ተሸነፈ። እግዚአብሔር በዳዊት ሊያደርግ ካለው አላማ ጋር ተስማማ።  አምላካችን እጅግ ኃያል ነው። ሊያጠፉን ካቀዱት ጋር ተስማምቶ አያውቅም። እንዲያውም ከገዛ ቤታቸው ወዳጅ ያስነሳልናል። ሳኦል ሰይፉን ሲስል በቤተ-መንግስቱ ጋሻ ጃግሬዎቹም አብረው ሲዶልቱ (፪x) ትልቁም ትንሹም ዳዊትን ሲያወግዝ ማን ይሆን ዮናታን ምስኪኑን የሚያግዝ ....... አለኝ ወዳጅ የማይከዳ ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን https://t.me/tetelestaye
Show all...
ሕይወት፣ የማይደበዝዝ ተስፋ፣ ሙሉ ሠላምና ደስታ፣ የሕይወት ዘመን ጽናት ያለው በወንጌል ውስጥ ብቻ ነው! https://t.me/tetelestaye
Show all...
If the assurance of my salvation depends on my faithfulness to Christ rather than Christ's faithful and saving work, how then that could be a Gospel? God already knows that I'm depraved, wicked, and the most miserable person among a sinner. In other words, the assurance of my salvation depends on my faithfulness to the Gospel means that the work of Christ is not enough to preserve me to the end. This kind of understanding is heresy. ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አዳኛችን መልካም ነው። መስቀል ላይ የተሰራው አስደናቂ ሥራ፤ የእርሱ የሆኑትን እስከመጨረሻው ያፀናቸዋል። የወንጌሉ ተስፋ ይኽ ነው። በክርስቶስ ወንጌል ውስጥ አለመጥፋት እንጂ መጥፋት የለም!! @https://t.me/tetelestaye
Show all...
ከመንፈሱ ጋር ካልሠራህ ነገሩን እግዚአብሔር እንደሚፈልገው አትሠራውም!! ❝መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።❞ —ዘካርያስ 4፥6። እግዚአብሔርን ማገልገል ከሆነ ጥሪህ ያለ መንፈስ ቅዱስ አትችልም!! እግዚአብሔር #በመንፈሴ ካለ አንተም በመንፈሱ ብለህ ቀጥል፤ አትላላጥ!! ከመንፈሱ ጋር ካልሠራህ ነገሩን እግዚአብሔር እንደሚፈልገው አትሠራውም!! በሰው ኃይል እና ብርታት ሊደፈሩ የማይችሉ ነገሮች አሉ። በመንፈሱ ግን ሳያልብህ ትሠራዋለህ!! በቀላሉ ሊሠሩ የሚችሉ ነገሮች እንኳን ብዙ ያታግሉናል። በመንፈሱ ሲሆን ግን ከባድ የሚባል ነገር የለም፤ አይቻልም የሚባል ነገር አይኖርም!! ጴጥሮስ ያለ መንፈሱ ለሚወደው ጌታ መታመን አልቻለም፤ እንደ ቃሉ መገኘት አልቻለም!! መንፈስ ቅዱስ ከወረደ በኋላ ግን እንዴት ባለ ድፍረት እና ኃይል እንደተመላለሰ ግልጽ ነው!! ክርስቶስን እንደተረዳነው መታዘዝ የምንችለው ከመንፈሱ የተነሳ ነው!! የኢየሱስ ሆነን ለመቀጠል ዋስትናችን መንፈሱ ነው!! ❝መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ።❞ —2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥14። የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን አለ፤ በእርሱ ወይም በራሳችን ማስተዋል መደገፍ ምርጫው የእኛ ነው!! ከእኛ ምክንያት ይልቅ የእርሱ ምሪት ይበልጣል!! በእርሱ ብንታመን በታየልን ልክ መራመድ እንችላለን!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
#የሚሳካልህ ብዙ #ስለደከምክ አይደለም!! ❝ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።❞ —ዘፍጥረት 39፥3። ዮሴፍ የሚሠራው ሁሉ በእጁ ይከናወንለት ነበር፤ እርሱ ያለበት ነገር ሁሉ ውበቱ ጎልቶ ይወጣል። የስኬቱ ምስጢር ብዙ ስለደከመ አልነበረም፤ ብዙ በመድከም ቢሆን ከእርሱ በላይ የሚደክሙ ሌሎች ባሮች ነበሩ። የዮሴፍ መከናወን ምስጢር የያሕዌ አብሮነት ነው!! እስኪጎብጡ ድረስ ብዙ የሚደክሙ ሰዎች አሉ፦ እነዚህ ሰዎች ሲማረሩ እንጂ ነገር ሲሰምርላቸው አይታይም። የእግዚአብሔርን አብሮነት መረዳት ግን ብዙ ነገሮችን ይለውጣል። የዮሴፍ ስኬት በሚሰራው ሁሉ እንደነበር አስታውሱ፦ የብዙዎች ስኬት እንደዚህ አይደለም!! ለምሳሌ፦ ብዙ ሀብት ይኖራቸዋል፤ ዲስፕሊን የላቸውም፤ የአንዳንዶቹ ቤተሰብ ፈርሷል፤ የሌሎቹ ጤናቸው ተጎድቷል፥ ከዚህ እንኳን ተረፉ ስትሉ የበጎ ነገር ባለጸጋ አይደሉም። የእግዚአብሔር አብሮነት የሚሰጥህ ስኬት ግን እንደዚህ አይደለም!! ያገሬ ልጆች ስለስኬት እንደገና ማሰብ አለብን!? #እግዚአብሔርን #ተሳታፊ ስላደረገ ስኬት እናስብ!! እግዚአብሔር በክርስቶስ አብሯችሁ ነው፤ የምትሠሩትን ሁሉ በእጃችሁ ሊያከናውንላችሁ ይችላል!! ወደ ሥራችሁ ጋብዙት!! ወደ ትዳራችሁ ጋብዙት!! ❝እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ❞ —ዘፍጥረት 39: 2 https://t.me/tetelestaye
Show all...
#በመንፈሱ #መመራት ❝በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።❞ —ሮሜ 8፥14። ሕይወታችን እና አገልግሎታችን በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲመራ ከመረጥን ወደ ብስለት (Maturity) መጥተናል ማለት ነው!! በጠቀስነው ክፍል ... ልጆች በሚል የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ሁዮስ (Huios) የሚል ነው። ሁዮስ የሚያመለክተው ... በብስለት ያደጉ፣ ስሜታቸውን የሚገዙ፣ አእምሯቸውን በቃል እውቀት ያበለጸጉ፣ መረዳት የሚችሉ እና የበሰለ ውሳኔ ለመወሰን የበቁ ልጆችን ነው!! በመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ስር መተዳደር ትልቁ የብስለት ምልክት ነው!! በመንፈሳዊ ነገር ካልበሰልን ... ከእምነት ይልቅ ለስሜታችን እንታዘዛለን!! ከምሪት ይልቅ ምክንያትን እንከተላለን!! ከአላማ ይልቅ ተድላን እንመርጣለን!! በመንፈሱ መመራት ማለት #እኛ #የምንፈልገውን ሳይሆን #እርሱ #የሚፈልገውን መታዘዝ ማለት ነው!! ይህ ምርጫ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ሕይወትን ግን ቀላል ያደርጋል!! ስለዚህ በስሜት ሕዋሶች ከተቀበልነው መረጃ ተነስተን ከመወሰን መላቀቅ እና የእረኛችንን ድምፅ መከተል ይኖርብናል!! በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ የተለዩ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ከውጭ ሆኖ መርቷቸዋል። በዚህኛው ኪዳን ግን በውስጣችን ሁኖ ይመራናል፤ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል። ለእነርሱ ፈቃዱን ገልጦላቸው ይሄድ ነበር፤ ለእኛ ፈቃዱን ብቻ ገልጦ አይሄድም፤ አብሮን ይኖራል። ወደ እነርሱ ይመላለስ ነበር፤ በእኛ ውስጥ ግን እየኖረ ነው። በብሉይ ኪዳን በነበሩ መንፈሳዊ ሰዎች ይሠራል እንጂ አይኖርም። ለእነርሱ እንዳደረገው አሳብ ሰጥቶ ትቶን አልሄደም፤ በውስጣችን ሁኖ ያስብልናል!! አሳቡ ብቻ ሳይሆን አሳቢው በውስጣችን አለ!! በዚህ መንፈስ መመራት ሕይወታችን ሁልጊዜ ወደ ዕረፍት ውኃ እንዲመራ መምረጥ ነው!! በመንፈስ ቅዱስ መመራት ያለ ድካም ትክክሉን ብቻ የማድረግ ውሳኔን መከተል ነው!! በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ሕይወት ሲኖረን ያለውን ብቻ መታዘዝ እንመርጣለን። ማድረግ ቢሆን አለማድረግ፣ መናገር ቢሆን አለመናገር፣ መሄድ ቢሆን አለመሄድ፣ ....ሁሉም እንደሚፈልገው እንዲሆን መምረጥ ይሻለናል!! ለምሳሌ፦ እነጳውሎስ በእስያ ሳሉ ቃሉን እንዳይናገሩ ከለከላቸው፤ አልፈው ሄዱ። ❝በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤❞ —ሐዋርያት 16፥6። ደግሞ ዝም አትበል፤ ተናገር ሲለው ተናገረ። ❝ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው።❞ —ሐዋርያት 18፥9-10። የአገልግሎት መሳካት ያለው እንደዚህ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በመከተል ነው!! መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ እርምጃችን እንዲቀድም እንፍቀድ!! ሕይወታችን ሙሉ በሙሉ በእርሱ አመራር ወደሚተዳደርበት ከፍታ ይውጣ!! የእግዚአብሔር ልጆች የብስለት ልኬት እና የሕይወት ስኬት በመንፈሱ በመመራት ይገለጣል!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ፍቅር እና ፍቅር ያልሆነው (Love vs Lust) (ይህ መልእክት በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ላሉ እና መግባት ለሚያስቡ ይሁን!!) ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ሰባትን እና ኤፌሶን ምዕራፍ አምስትን የጻፈበት መንገድ እጅግ ያስደንቃል!! አገልጋይ ምንንም ነገር ከክርስቶስ አንጻር የሚተረጉምበት ብርሃን ካገኘው እንዲህ ይሆናል!! የፍቅር ግንኙነት ከእኛ ዓለም እውቀት ተነስቶ አይተረጎምም!! የፍቅር ንድፈ አሳቡ (Blueprint) ያለው ምንጩ (Source) ጋር ነው፤ እርሱም፦ እግዚአብሔር!! ከተሳኩ ወይም ከተሰነካከሉ የፍቅር ታሪኮች ተነስቶ ፍቅርን መተርጎም ልክ አይደለም!! የፍቅር ግንኙነት መብራራት ያለበት ከእግዚአብሔር አሳብ አንጻር ነው!! የፍቅር አሳብ በልባችን ከተጸነሰ ...ሮጠን ማውራት ያለብን ለጓደኞቻችን ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው!! ሕይወቱ እንዴት እንደሚተረጎም መናገር የሚችለው፤ እንዴት እንደሚመራ መርህ የሰጠው እርሱ ነው!! የፍቅር ግንኙነት የሚለካበት የሕይወት ብቃት (Standard) አለው፤ እርሱም፦ በክርስቶስ እና በእኛ መካከል ያለው ኅብረት ነው። በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ያለው ፍቅር ንፁህ እና ውብ መሆን ያለበት ለዚህ ነው። #ጋብቻን ሰው #እንዳቀለለው ሳይሆን #እግዚአብሔር እንዳቀደለት ማየት አስፈላጊ ነው!! ተወዳጆች እኛ ባለቤት አለን፤ በደም የገዛን ላቀደው ሕይወት ሰውነታችን መታዘዝ አለበት። (1ኛ ቆሮንቶስ 6 እና 7 ይመልከቱ) ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ሲጽፍ... ያጻፈው #የቅድስና #መንፈስ ዛሬም ሕያው ነው!! እግዚአብሔር ...ልጆቹ ለሰይጣን ደጅ እንድንከፍት እና እንድንሰነካከል አይፈልግም!! እርሱ ከብሮ የሚታይበት ምልልስ እንዲኖረን ይፈልጋል!! በእርግጥ በዚህም ዘመን ... ንጹሕ ፍቅር አለ፤ ፍቅርን የሚቀበል ንጹሕ ልብ አለ፤ እግዚአብሔር የሚፈራበት ትዳር አለ፤ በተቀበሉት ራስን የመግዛት መንፈስ ታዘዉ የሚኖሩ የጸጋ ቅሬታዎች አሉ። በተቃራኒው መረን የሆነ ሕይወትን የለመዱ ሰዎች መኖራቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ...እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም በአምላካችን መንፈስ #ተቀድሰናል፤ ለቀዳሹ በሚሆን መጠን ስለተቀደስን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን እየኖረ ነው!! ይህ እጅግ አስደናቂ እውነት ነው!! ስለዚህ ነው ለሕይወታችን የምንጠነቀቅለት!! ለእኛም ጥቅም፥ በእኛም ለሚኖረው ክብር እንድንኖር የሚረዳን ጸጋ ተሰጥቶናል!! በልባችን እንዳይፀነስ በቃሉና በመንፈሱ የምንወጋው አሳብ አለ፤ ከተፀነሰ ደግሞ ግቡን እንዳይመታ ምሽጉን ማፍረስ አለብን!! "ፍቅርን" እና "በፍቅር ስም ያሉ" ድለላዎችን መለየት ይኖርብናል!! ልባችን በስሜት ቁጥጥር ስር ከመሆኑ በፊት ፍቅር የሆነውን እና ፍቅር ያልሆነውን ቆም ብለን መመዘን ይኖርብናል!? • ፍቅር የሆነው አይቸኩልም፤ በጥልቀት ለመተዋወቅ ጊዜ ይወስዳል!! ፍቅር ያልሆነው (Lust) የተቆጣጠረው ...ከግንኙነቱ የሚያተርፈውን ነገር እንጂ ስለእርሷ ማወቅ አይገደውም!! • ፍቅር የሆነው ክብር፣ ውሳኔ እና ነገን አብሮ ማለም ይንጸባረቅበታል!! ሕይወቱ ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲታነጽ ይተጋል!! ፍቅር ያልሆነው ልብን በስሜት መንዳትና ለዝሙት ማዘጋጀት እንጂ ነገ አይታየውም!! • ፍቅር የሆነው ከመቀበል ይልቅ መስጠት ላይ ያተኩራል!! ፍቅር ያልሆነው እንኳን ሊሰጥ በሚቀበለው አይረካም!! • ፍቅር የሆነው የሚያስከፍለውን ሁሉ ዋጋ ከፍሎ ፍቅሩን አካል ያስይዛል!! ፍቅር ያልሆነው ግንኙነቱን በአሳብ ከማለም አልፎ ወደ መሬት አያወርደውም!! • ፍቅር የሆነው የፍቅር ጓደኛውን ጥንካሬና ድካም አብጠርጥሮ ያውቃል፤ ጥንካሬን ያበረታታል፤ ድካምን ለማስወገድ አብሮ ይሠራል!! ፍቅር ያልሆነው የፍቅር ጓደኛውን እንከን መቀበልም ማገዝም አይፈልግም!! • ፍቅር የሆነው እምነትን (Trust) እና ወዳጅነትን ይገነባል!! ፍቅር ያልሆነው የጊዜው ደስታ ላይ ያተኩራል!! ነገን 'ሚያይበት ዓይን የለውም!! • ፍቅር የሆነው እውነትን ማዕከል ያደርጋል፤ በአቋም ጸንቶ ይቀጥላል!! ፍቅር ያልሆነው ስሜትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ሲነጋ ተወርቶለት ሲመሽ አይገኝም!! ጠቢቡ ሰሎሞን ፍቅር የሆነውን እና ያልሆነውን ለይቶ ተረድቷል፤ ፍቅር ያልሆነውን ማለትም ዝሙትን ተቃውሟል። እርሱ ከገለፀበት አረዳድ ፍቅር የሆነውን እና ያልሆነውን የሚያሳዩ መገለጫ ጠባዮችን (Character) እንመለከታለን!! ፍቅር ያልሆነው፦ 1) ለዝሙት የሚያነሳሳ አቀራረብ (Sexual attraction)፦ በአለባበስ ይማርካል፤ በንግግር ያሳምናል!! "ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነውና፤" ምሳሌ 5፥3። ❝ከጋለሞታ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃልዋን ከምታለዝብ ከሌላዪቱም ሴት፤❞ —ምሳሌ 2፥16። "ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥ ከሌላይቱም ሴት ምላስ ጥፍጥነት።" ምሳሌ 6፥24። 2) እውነት እና እርጋታ የለውም!! ግንኙነቱ የት እንደሚደርስ አይታወቅም!! "የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፤ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።" ምሳሌ 5፥6። 3) ግንኙነቱ ላንተ ምላሽ የለውም!! አንተ ለእርሷ ትደክማለህ፤ እርሷ ለሌላ ትኖራለች!! "ሌሎች ከሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ ድካምህም በባዕድ ሰው ቤት እንዳይሆን።" ምሳሌ 5፥10። 4) አጭር ነው፤ በዚያ ላይ ወጥመድ ነው!! "የጋለሞታ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች።" ምሳሌ 6፥26። 5) የዚህ ነገር መጨረሻው ፀፀት ነው!! "በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ" ምሳሌ 5፥11። *** እንደዚህ ካለው ... የእግዚአብሔር ቃል #ሽሽ ይላል!! መተሻሸት አይደለም፤ #መሸሽ!! ❝ከክፉ የጎልማሳነት #ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።❞ —2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22። ❝Flee also youthful lusts: but follow righteousness, faith, charity, peace, with them that call on the Lord out of a pure heart.❞ —2 Timothy 2:22 (KJV) የጎልማሳነትን #ምኞቱን መሸሽ እንጂ ማሰላሰል አያስፈልግም!! ፍቅር ያልሆነውን ፍቅር ለመቀበል ሰበብ ማብዛት ሳይሆን መሸሽ ያስፈልጋል!! አጥብቀን የምንከተለው ሕይወት አለ፤ እርሱም፦ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን እና ሰላምን!! በሰሎሞን ምሳሌዎች ...የእውነተኛውም ፍቅር ባሕርይ ተገልጿል፦ "ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤ ከጕብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ። እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።" ምሳሌ 5፥18-19። #የእውነተኛው #ፍቅር #ግብ ጋብቻ እና አብሮ ማርጀት ነው!! ውጤቱም ከላይ እንደተገለጸው፦ 1) ምንጩ የተባረከ፣ 2) ደስታው ፀፀት የሌለበት፣ 3) ናፍቆቱ 'ማይቋረጥ 4) እርካታ ቀጣይነት ያለው እና 5) ፍቅሩ የሚያጠግብ ነው!! "#ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር #በቅድስና ጠርቶናልና።" 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥4-8። በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
"ትቶ ይሄዳል" ተብሎ አያሰጋም!! "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም" መዝሙር 23፥¹ ይህ ማለት ዳዊት ከእግዚአብሔር ፈልጎ ያጣው ነገር አጥቷል። ይገርማል!! ለእኛም እግዚአብሔር ታማኝ እረኛችን ነው፤ ስለዚህ #የሚያስፈልገን ሁሉ አለን፤ አንዳችም አያጎድልብንም!! ዳዊት "በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን #አልፈራም" አለ። በእረኛችን ምን ያህል እንተማመናለን!? በአስቸጋሪ መንገዶች እንኳን ስናልፍ ለራሳችን ትቶን አይሄድም!! ተወዳጆች እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አብሮን ይራመዳል!! አብሮነቱ ደግሞ የሚታመን ነው፤ "ትቶ ይሄዳል" ተብሎ አያሰጋም!! ዓለሙ ሁሉ እንኳን ቢቃወምህ ከአንተ ጎን ይቆማል!! በቃሉ ልብህን እያፀናና ደኅንነት እንዲሰማህ ያደርጋል!! ዛሬ ለእናንተ ምርጥ ግብዣ አለኝ፦ መዝሙር 23፥1-6 እባካችሁ ተጋበዙልኝ!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
የኢየሱስ ቃል #ሳትክድ ትዝ ይበልህ!? ❝ጴጥሮስም፦ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።❞ —ማቴዎስ 26፥75። ጴጥሮስ "ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም" አለ። ኢየሱስ፦ "እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" አለው። ጴጥሮስ፦ "ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን፥ ከቶ አልክድህም" አለው። ከዚህ ቃለ መሀላ በኋላ ጴጥሮስ የወሰነው ሳይሆን ኢየሱስ ያለው ሆነ። "ሰውየውን አላውቀውም" ብሎ ሦስት ጊዜ ካደው። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ። 3 ጊዜ #ከካደ በኋላ ... "ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" ያለው #የኢየሱስ ቃል #ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ። (ማቴዎስ 26፥58-75)። ጴጥሮስ የኢየሱስ ቃል ትዝ ያለው ከካደ በኋላ ነው፤ ከዚያ አምርሮ አለቀሰ። የብዙዎቻችን የህይወት ዘይቤ እንደዚህ ነው። የኢየሱስ #ቃል ሳንወድቅ ትዝ ይበለን። አጥፍተን በፀፀት ከመሰቃየት #ሳናጠፋ የነገረን ቃል ትዝ ይበለን። ኃጢአት ከመሥራታችን በፊት #መቀደሳችን እና #መጽደቃችን ትዝ ካለን በማንነታችን ልክ ልቀን እንኖራለን። ጴጥሮስ ለምን ተሰናከለ? በራሱ ስለተማመነ፤ በራሳችን ሳይሆን በጌታ እና በኃይሉ ችሎት እንተማመን። ላለመውደቅ ዋስትናችን የእርሱ ጸጋ ነው። በእርሱ የሚታመኑ ሳይክዱ ቃሉ ትዝ ይላቸዋል!! የኢየሱስ ቃል ተጠላልፈን ከመውደቃችን በፊት ትዝ ይበለን!! ቦታዉ ላይ፤ ሰአቱ ላይ ቃሉ ትዝ ሲለን ደግሞ ለቃሉ ስንታዘዝ እንዴት ደስ ይላል!! በርናባስ ዘመነ
Show all...
"አንኳኩ" ያለው እያንኳኳ ነው፤ ለከፋቹ ክፈቱ!! ጌታ ኢየሱስ የተራራውን ስብከት ሲያስተምር፦ "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።" ብሏል። ማቴዎስ 7፥7-8። ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የተጻፈውን ደብዳቤ ስናይ ደግሞ፦ ❝እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።❞ አለ። —ራእይ 3፥20። አንኳኩ ያለው ራሱ በደጅ ቆሞ እያንኳኳ ነው። ልቡን ለከፋቹ የሚከፍት "...በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ... ነጭ ልብስን፥ ... የሚኳለውን ኵል" ከእርሱ በነፃ ይገዛል። #መልሱ መልስ ልሁናችሁ እያለ ነው። #ሰጭው ስጦታ ሆኖ መጥቷል። ተፈላጊው ፈልጎን እያንኳኳ ነው። ሰጭው እጁን ዘርግቶ ተቀበሉኝ እያለ ነው። ያላንኳኳነው በር #ተከፍቶ ግቡ እያለን ነው። ውኃ ዝቅ ብሎ ያገኘውን ዝቅታ ወይም ባዶ ስፍራ እንደሚሞላ ሁሉ ኢየሱስም እንዲሁ የሰውን ጉድለት ሊሞላ ይፈልጋል። ባዶነት ሙላትን እየፈለገ ሳይሆን ሙላት ባዶውን እየፈለገ ነው። ነገሩ ተገላብጧል። አሁን የተራበ ሰው ምግብ እየፈለገ ሳይሆን ምግብ ራሱ (ኢየሱስ) የተራበውን ሰው እየፈለገው ነው። ያዘነ ሰው ደስታ እየፈለገ ሳይሆን ደስታ ራሱ (ኢየሱስ) ያዘነውን ሰው እየፈለገ ነው። ዕረፍት ተንከራታቹን ሰው እየፈለገው ነው። ኢየሱስ ሁሉንም ነገራችንን መልክ ማስያዝ ይፈልጋል!! ኢየሱስ ለሁሉም ነገር መፍትሔ መሆን ይችላል!! በረከት እየፈለጋችሁ ነው!! እባካችሁ ወደ ሕይወታችሁ ጋብዙት!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ጠባቂያችን እና መሸሸጊያችን - ኢየሱስ ******** እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና። (መዝሙር 91፡3) ✍️ ዛሬ፣ በምንኖርበት ዓለም ከትውልድ እና ከዓመታት በፊት ያልተሰሙ አዳዲስ የቫይረሶች ዓይነት እንሰማለን። ዓለም ለብዙ ቫይረሶች ፈውስ አላገኘችም ከዚህ የተነሳ ብዙ ሰዎች በእነዚህ ቫይረሶች ለመያዝ ይፈራሉ። ✍️ ግን እንደ አማኝ እና የእግዚአብሔር ልጆች በዓለም ውስጥ ብንሆንም ከዚህ ዓለም አይደለንም። (ዮሐ. 17: 15–16) ስለዚህ ጥበቃችን ከዚህ ዓለም ሳይሆን ከጌታ ነው ማለት ነው። ከጌታ ነው ስል መጠጊያዬና ምሽጌ የሆነ ነው። እርሱም “ምናልባት” አይደለም፣ ግን በእርግጠኝነት ከአዳኝ ወጥመድ እና ከሚያስደነግጥ ቸነፈር ያድነናል ማለት ነው። (መዝሙር 91: 2) ✍️ በተለያየ ጊዜ እና ዓለም የተለያዩ ቫይረሶች ተከስተዋል ወደፊትም ይከሰታሉ። የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን ግን ልባችንን በሚፈራረቁ ችግሮች ላይ ሳይሆ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው በሆነው እና በማይለዋወጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ልናሳርፍ ይገባል። (ዕብራውያን 13፡8) ✍️ ወዳጄ፡- የሌሎችን ሕይወት የገደሉ ገዳይ በሽታዎችን መፍራት አያስፈልግህም። እኔ ወይም ልጆቼ የቫይረስ ተጠቂ ሊሆኑ ይችላሉ ብለህ መፍራት የለብህም። ምክንያቱም ጌታ መጠጊያችን እና መሸሸጊያችን ሲሆን አንተም ሆንክ ቤተሰብህ አደገኛ ከሆኑ ቸነፈር ሁሉ ያድንሃል። ✍️ ምናልባት፣ አሁንም ይህንን ጽሁፍ እያነበብክ በሆነ ቫይረስ ተይዘህ ቢሆን እንኳ ከምታመልከው አምላክ የሚበልጥ ኃይል እንዳለው ማሰብህን ተው እና በክንፎቹ ፈውስን የተሸቀመውን የጽድቅ ጸሐይ (ኢየሱስ)፤ ከሙታን የተነሳውን ከዳዊት ዘር የሆነውን በቀን እና በለሊት ማሰብ እና ማሰላሰል ቀጥል! ፈውስህ ፈጥኖ በሰውነትህ አካል ይለብሳል! ሀሌሉያ ጌታ ለልጆቹ ሁል ጊዜ መልካም ነው!!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
የፍቅር እረፍት መውሰድ አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ። ዩሐንስ 15፡9 ✍️ በሥራ ቦታ ምናልባት የቡና፣ የምሳ፣ የሻይ  ዕረፍት እና በርግጠኝነት የሽንት ቤት  ዕረፍት ትወስዳለህ። በመንፈሳዊ ሕይወትህም ውስጥ እንዲሁ ለምን አታደርግም - ለእረፍት ጊዜ ውሰድ፣ በተለይም የፍቅር ረፍት? ✍️ የፍቅር ዕረፍት ምንድን ነው? በኢየሱስ ፍቅር ለመደሰት እና ለመመገብ የምትወስደው ጊዜ ነው። በየትኛውም ቀን፣ የትም ብትሆን ጸጥ ያለ ቦታ ፈልግ እና የኢየሱስን ፍቅር ተመገብ። ዝም ብለህ ቁጭ በልና ከእርሱ ጋር ተነጋገር። “ጌታ ሆይ፣ ስለወደድከኝ አመሰግናለሁ። አንተ አስቀድመህ የማያውቀው ምንም ነገር በሕይወቴ አይከሰትም። ኢየሱስ፣ እኔ እራሴን ማዳን በማልችልበት ጊዜ ለእኔ ሞተህ አዳንከኝ። ሕይወትህን ለእኔ ሰጠኸኝ። ሌላ ምንም የቀረ ነገር የለም የምታደርግልኝ!” በለው። ✍️ እንደዚህ ዓይነቱ የፍቅር ዕረፍቶች በብሉይ ኪዳን በአሮን ሊቀ ካህኑ እና ወንዶች ልጆቹ የመሥዋዕቱን እንስሳ ደረት ሲበሉ የታየ ነው። (ዘሌዋውያን 7፡31) የእንስሳው ደረት ስለ ኢየሱስ ፍቅር ይናገራል። ዛሬ የእግዚአብሔር ካህን ነህ። (ራእይ 1: 6) ስለዚህ የኢየሱስን ፍቅር በመመገብ ጊዜን ውሰድ እንዲሁም እራሱ በፍቅሩ ሲመግብህ፣ ሲያጠነክርህ እና ሲደግፍህ ተመልከት። ኢየሱስ ዛሬ ሊቀ ካህናችን ነው። ይህ ማለት የእሱ ምግብ እኛን መውደድ ነው ማለት ነው። እሱ እኛን መውደድ ያስደስተዋል እንዲሁም ለእኛ ባለው ፍቅር “የሚመግብ” ነው። ✍️ ግን ደረቱ በእሳት የተቃጠለ መሆኑን አትዘንጋ (ዘሌዋውያን 7፡35)፣ እርሱም ኃጢአታችንን ተሸክሞ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ስለነበረው የእግዚአብሔር ፍርድ በኢየሱስ ላይ መዋሉን ይናገራል። ስለዚህ ኢየሱስ ለአንተ ባለው ፍቅር በምትመገብበት ጊዜ በመስቀል ላይ የዋለውን ፍቅር ትመለከታለህ። በአካባቢህ ያሉት ነገሮች ጥሩ ካልሆኑ ዲያቢሎስ “እግዚአብሔር የሚወድህ ከሆነ እነዚህ ነገሮች እንዴት ይሆኑብሃል?” እንዲልልህ አትፍቀድለት። ወዳጄ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ወይም በሚታየው ጊዚያዊ ነገር ላይ አትመሥረት ነገር ግን በመስቀል ላይ በመመሥረት የእግዚአብሔር ፍቅር ለአንተ  መተርጎም ጀምር። ✍️ በሥራ ላይ ጠንክረህ ሲሠሩ፣ ቅናት ሲገባ፣ ችግሮች ሲሰባሰቡ ወይም ተስፋ መቁረጥ ሲመጣ፣ ሁሉንም ነገር አቁምና ከኢየሱስ ጋር ፍቅርን አድስ! ኢየሱስ ይወድሃል። በእርሱ በመወደድህ ተደሰት። በእቅፉ ላይ ዘንበል በል፣ በፍቅር ደረቱ ውስጥ ቆይ እና ለአንተ ባለው ፍቅር እደግ! ፓስተር ዳዊት ጥላሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
#ሙሽራው #ሙሽሪት   ሙሽሪት የሰርጓ ቀን ደርሶ "…ወዮ! …ወዮ! አለቀልኝ፣ ምነው ይህ ቀን በዘገየ፣ ሙሽራዬ በቶሎ ባይመጣ…" ብላ ብታለቅስ! ይህን ለቅሶ ምን ይሉታል❓ ሙሽራይቱስ ጤነኛ ነች ትባል ይሁን❓ #መጣልኝ ማለት ሲገባት #መጣብኝ❓ ነው ወይስ አትወደውም እንዴ?🤔 🔹ሙሽራው ኢየሱስ "ሊመጣ በደጅ ነኝ ተዘጋጂ" ይላታል 🔹ሙሽሪት ቤተ-ክርስቲያን በአፏ "ማራናታ" በልቧ ግን "…ትንሽ ብትቆይ አይሻልም! ገና ያልያዝኩት፡ ያልለቀኩት፡ ያልጨረስኩት ነገር አለ…" ትለዋለች❗ በግድ የታጨች ይመስል "እየመጣ ነው" ሲባል ባር ባር ይላታል ፤ ፍርሃት ፍርሃት ይላታል። 🔵እኔ እንደሚመስለኝ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ስለ እጮኛዋና ስላዘጋጀላት ስፍራ ያላት አመለካከት ጤናማ ካለመሆኑ የተነሳ ነው። "…ያላዩት ሀገር አይናፍቅም…" እንደሚሉት ሆነባት መሰል። ያላየችውስ በምድር ትርምስ ተጠምዳ #የመንፈስ_አይኗን መክፈት ስለተሳናት ነው እንጂ የከለከላት አልነበረም። 💠ብታየውማ ያቁነጠንጣት ነበር። "አሁን ካልሄድኩ! …ካልሄድኩ!" እያለች ታብድ ነበር❕ ⭕የሰላሙን አለም ስላላያች በረብሻው አለም መቆየት አማራት ⭕የቤቷን ውበት ስላላወቀች የእንግድነት ሀገሯን አካበደች ⭕ህንፃዋን ስላላየች ድንኳኗ በለጠባት ⭕ዘላለማዊውን ስላልተረዳች ጊዜያዊው ገነነባት ⭕የማይበሰብሰውን ስላላየች አፈር ለብሳ ካልበሰበስኩ አለች ⭕ፈጣሪ ያዘጋጀውን ከተማ ስላላየች ፍጡር በገነባው ፈራሽ ህንፃ ማረከች። 🔵ሰማይን እንድናስተውል እግዚአብሔር #አይኖቻችንን ይክፈትልን🙏 አሜን🙏    #ተፈፀመ #ተፈፀመ #ተፈፀመ #ተፈፀመ #ተፈፀመ        🙏 #ኢየሱስ ይመጣል ፣ #ሙሽራው በደጅ ነው🙏                         🔥🔥🔥🔥#ሰናይ #ቀን🔥🔥🔥🔥 https://t.me/tetelestaye
Show all...
መንፈስ ቅዱስ በግል ሕይወታችን መሪያችን ነው! እግዚአብሔር አያታችን ሳይሆን አባታችን ነው! አባት ደግሞ የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስን ነው። "እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?" (ሉቃስ 11፥13) እግዚአብሔር ነቢያትን የሰጠው ለቤተክርስቲያን ሲሆን የሚገኙትም በቤተክርስቲያን ነው። ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን የተሰጠን ግን ነብይ ሳይሆን መኖሪያውን በእኛ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ  ነው። ስለዚህ በግል ሕይወታችሁ መንፈስ ቅዱስን እንጂ ነብያትን መሪዎች አታድርጉ። "እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።" (1ኛ ቆሮንቶስ 12፥28) "ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤" (ዮሐንስ 14፥15-16) "ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።" (ዮሐንስ 16፥13) "በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።" (ሮሜ 8፥14) የግል ሕይወታችሁን ለመምራት ያላችሁ የግል ነብያት ወይስ የግል መንፈስ ቅዱስ? አስቸጋሪ የሆነ ነገር ሲገጥማችሁ መፍትሔን ከመንፈስ ቅዱስ ትጠይቃላችሁ ወይስ ነብይ ጋ ትደውላላችሁ? ሐዋርያ ሊሆን የተጠራው ጳውሎስ ነብያት የተሰጡበትን ዓላማ በግልጽ ይነግረናል። "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥" (ኤፌሶን 4:11-14) Pastor Alex's https://t.me/tetelestaye
Show all...
ዘመቻ Helina Dawit || New Music sʜᴀʜᴀʀᴇ sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
Show all...
Hallelujah Praise the Lord 🙏🙏🙏 5 Reasons to praise the Lord 1 He is your provider እርሱም፣ “እጅህን በብላቴናው ላይ አታሳርፍ፤ ምንም ጒዳት አታድርስበት፤ እነሆ፤ እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፤ ልጅህን፣ ያውም አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና” አለው። ዘፍጥረት 22:12 2 He is your defender ምሳ 22፥23 እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤ የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል። ምሳሌ 22:23 3 He is your healer ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ #ተፈወስን። ኢሳይያስ 53:5 4 He is your saviour በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16 5 he heals the broken hearted ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል። መዝሙር 147፡3 👉 እግዚአብሔር ለማመስገን እልፍ ምክንያቶች አሉን ፣ከብዙ ሽህ ምክንያት በላይ አለን ለዛሬ እነዝህ አምስት ምክንያቶች እንኩ ብያችኃለሁ!!!ድንቅ የምስጋና ቀን ይሁንላችሁ !! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ፍቅራችን ሳይሆን ፍቅሩ የሕጉ አጠቃላይ መልዕክት “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል። የሚል ነው!”  (ማቴዎስ 22 37-40)። ነገር ግን ይህንን ልጠይቅህ አንድ ሰው እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ እና ሐሳቡ መውደድ ይችላል? ✍️ መልሱ ግልፅ ነው። አንድም ይህን ማድረግ የቻለ የለም። በሕጉ መሠረት ማንም ሰው ያንን ፍጹም ፍቅር ሊለውጠው እንደማይችል እግዚአብሔር ሁሉን ያውቅ ነበር። ስለዚህ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? ልጁን ኢየሱስን ላከ። ይህን ሲያደርግ እርሱ በትክክል ይህንን እያለን ነበር፣ “ሙሉ በሙሉ ልትወደኝ እንደማትችል አውቃለሁ፣ አሁን እኔን ተመልከት። በሙሉ ልቤ፣ በሙሉ ነፍሴ፣ አዕምሮዬ እና ኃይሌ ሁሉ እወድሃለሁ።” ይንንም ብሎ እጆቹን በስፋት ዘርግቶ ለእኛ ሞተ! ✍️ ወዳጄ ሆይ፣ ዛሬ ይህንን ልብህ ውስጥ ለማስገባት ጊዜ ውሰድ -ምክንያቱም የክርስቶስ መስቀል ሰው ፍጹም ፍቅር መገለጥ እና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር መገለጫ አይደለም። መስቀሉ የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅሩ መገለጫ እና የእርሱ ፍጹም ጸጋ (ለእኛ የማይገባ ሞገስ) መገለጫ ነው። ✍️ ይህንን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ለአንተ የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር ፍቺን ልንገርህ “በዚህ ፍቅር ፍቅር እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደን እና ስለ ኃጢአታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ልኮታል።” የአዲሱ የጸጋ ቃል ኪዳን አፅንኦት (ያልተገባ ሞገስ) - እሱ ለእኛ ያለው ፍቅር እንጂ ለእሱ ያለን ፍቅር አይደለም። እናም ለእኛ ባለው ፍቅር ላይ ስናተኩር ለእርሱ እና ሌሎችን ያለ ምንም ጥረት በመውደድ ኃላፊነታችንን እንፈፅማለን! ፓስተር ዳዊት ጥላሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
✍️ ለጥምቀት ያልሆነ ስብከት ** ✍️ በራልኝ ያለ ሰው በጨለማ ውስጥ ናቸው ለሚላቸው ያዝናል እንጂ እንዴት ሙድ ይይዛል?....እንዴትስ ያፌዛል?.....እንዴትስ ይሳደባል? 📌 የኢየሱስ ፍቅር ያለ ኢየሱስ ልብ አይሰበክም!! ✍️ ሙሉው ወንጌል በጎደለ ማስተዋል አይሰበክም!! 📌 የክርስቶስ ፍቅር ከሸመደድነው 3 ጥቅስ ያለፈ ነው። ስንሰብክ ከፍቅር በፍቅር እውነትን በመግለጥ ይሁን እንጂ የወንጌል እንቅፋት በመሆን አይሁን!! ✍️ አንዳንዶቻችሁ ወንጌሉን የምትናገሩበት የፍቅር ልብ ደስ ይላል ልብ ያሳርፋል በርቱ!!.....አንዳንዶቻችሁ ደሞ በስድብ የተተበተበ ጽሑፋችሁ ያሳፍራል!! ቆም በሉና አስተውሉ!! 📌 ሁሌም ወንጌልን ሳታመቻምቹ በፍቅር ስበኩ!! #በወንድም_ሄኖክ_አሸብር
Show all...
ተፈጸመ ✍️ በሚያምር መልኩ ውብ ተደርጎ የተሠራን ቤት ድጋሜ ቀለም ለመቀባት ብሩሽ እንደማታነሳ ግልጽ ነው። በጭራሽ! የተከናወነው በአንድ ባለሙያ ነውና፣ ታዲያ ቤቱን ተሠርቶ ካለቀ በኃላ ለማሻሻል ምን ማከል ትችላለህ? ✍️ በተመሳሳይም መንገድ፣ በመስቀል ላይ የኢየሱስን ሥራ ሥንመልከት። ተፈጸመ አለ። የተጠናቀቀ ሥራ ማጠናቀቅ አትችልም። የጨረሰን ሥራ መጨረስ አትችልም። ድነታችንን አሸነፈ። ኃጢአታችን ሁሉ ይቅር ተብሏል። እኛ በደሙ ለዘላለም ጻድቅ ሆነናል። ለኃጢአት ይቅርታ፣ ለጽድቅ እና ለሁሉም በረከቶች ክርስቶስ ሙሉ እና ሙሉ በሙሉ የከፈለ በቂያችን ነው! ✍️ በእርግጥ፣ “ተፈጸመ” የሚለው ቃል የመጣው ከአንድ የግሪክ ቃል ቴሊኦ teleo ከሚል ነው። በኢየሱስ ዘመን አንድ አገልጋይ ለጌታው “የተሰጠኝን ሥራ አጠናቅቄአለሁ” ብሎ በሚናገርበት ጊዜ ይጠቀሙበት ነበር (ዮሐንስ 17፡4)። ቃሉ ማለት “ተፈጸመ፣ ተጠናቅቋል፣ ሁል ጊዜም ይጠናቀቃል!” ማለት ነው። ምናልባትም የቴሊኦ teleo ትርጉም በጣም አስፈላጊ ትርጉም ነጋዴዎች የሚጠቀሙበት መንገድ “ዕዳው ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል!” ማለት ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ራሱን ሲሰጥ የሕጉን የጽድቅ ፍላጎቶች ሙሉ በሙሉ አሟልቷል። እዳችንን ሙሉ በሙሉ ከፍሎልናል! ✍️ ዛሬ በረከቶችን የሚያመጣ የእኛ ሥራ አይደለም። የተጠናቀቀው የክርስቶስ ሥራ ነው። የክርስትና ኑሮ ስለ መሥራት አይደለም፣ ነገር ግን በተጠናቀቀው ሥራው ማመን ነው። በሕጉ መሠረት ማድረግ እና መሥራት አለብን። ከጸጋ በታች ስንሆን ግን፣ ተሠርቷል፣ ተፈጽሟል፣ ተጠናቅቋል! ✍️ ምናልባት ዛሬ ብዙ ችግሮች አጋጥሞህ ይሆናል። ኢየሱስ “ተፈጸመ!” በማለት ቃል ገብቷል። ከየትኛውም ችግር ነፃ ለመውጣት እየጣርክ አይደለም፤ አስቀድመህ ነጣ የወጣ ነህና! ከ 2,000 ዓመታት በፊት እግዚአብሔር ፈውሶናል! ኢሳይያስ 53: 5 እንዲህ ይላል: - "በርሱ ቁስል ተፈወሳችሁ!" ቀድሞውንም የተፈወስን ነን። በተፈጸመው ሥራ ማረፍን ቀጥል እርሱ ይገለጣል! ✍️ ወዳጄ፣ ሥራው ተጠናቅቋል። ድሉን አሸንፏል። ጠላቶቹ የእግሩ መረገጫ ሆነዋል። በረከታችን በደሙ ተገዝቷል! አንተ የምታደርገው ምንም ነገር እንደሌለ በማወቅ የእረፍት ሕይወት — በማመን ብቻ ቀጥል! ተፈጽሟል! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ርቀትን ያራቀ ደም!! ❝አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ #በክርስቶስ #ደም ቀርባችኋል።❞ —ኤፌሶን 2፥13። እኛ በፍጥረት አይሁድ አይደለንም፤ አሕዛብ ነበርን!! እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል እንግዶች ነበርን!! ``በፊት ርቀን የነበርነው`` በክርስቶስ ሆነን በክርስቶስ ደም ቀርበናል!! የኢየሱስ ደም ርቀትን አርቆ አቅርቦናል!! #የኢየሱስ #መስዋዕታዊ #ሞት አንዱ ያመጣው ድል፦ እግዚአብሔር እና ሰው የአባት እና የልጅ ኅብረት እንዲኖራቸው ማድረጉ ነው!!
Show all...
ጸጋ ከኃጢአት ይፈታል እንጂ ለኃጢአት አይፈታም!! "ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፦ አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።" _ ዮሐንስ 8፥10-11። ይህ የጸጋ ፍርድ ነው!! "እኔም አልፈርድብሽም" አመንዝራ እንደሆነች የተጋለጠች፤ ከአሁን አሁን በድንጋይ ወገሩኝ እያለች በድንጋጤ ትንፋሿ እየተቆራረጠ ያለች፤ አሰቃቂ ሞት ይፈረድብኛል ብላ የጠበቀች ነፍስ ይህን ስትሰማ ምን የሚሰማት ይመስላችኋል? ከሳሾቿ እርሷን በከሰሱበት ኃጢአት ተከሰዉ ትተዋት ሄደዋል። አጠገቧ ያለውም ዳኛ "እኔም አልፈርድብሽም" አላት። ምሕረት አገኛት። ምሕረት ማለት የሚገባትን ቅጣት አልተቀበለችም!! ያልተገባትን ሞገስ አገኘች!! በጸጋዉ ቆማ ምሕረቱን እያደነቀች ሳለ፦ ጸጋ መናገር ቀጠለ "ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ" አለ። ጸጋ እንዲህ ከኃጢአት ይፈታል እንጂ ለኃጢአት አይፈታም!! ጸጋ ሄደን ኃጢአት እንድንሰራ ሳይሆን ከኃጢአት አስተሳሰብ ነፃ ወጥተን እንድንኖር ያደርጋል!! ፍቅሩን አስቤው አቤት ስል ምሕረቱ አለ ለካ ... አለ ለካ እረ እንዴት አመስግኜዉ ልርካ!! እረ እንዴት አመስግኜዉ ልርካ!! እረ እንዴት አመስግኜዉ ልርካ!! በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
             #የእግዚአብሔርን_ፍቅር_ማወቅ_ያበረታሃል!             ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✍️ እግዚአብሔር ለአንተ ያለውን ፍቅር ማወቅ ጠንካራና ድል አድራጊ ያደርግሃል። ለዚህም፣ የዳንኤል መጽሐፍ "ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትንም በማታለል ያስታል፤ ነገር ግን አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም።" ዳን 11፡32 ብሎ ይነግረናል። ✍️ ዳንኤል የባቢሎንና የሜዶንና ፐርሺያን ነገስታት እንዲያገለግል ከኢየሩሳሌም የተወሰደ ታዳጊ ምርኮኛ ሆኖ ሳለ ከእድሜ ከአቻዎቹ በላይ ሆኖ በመቆም ዕድሜውን ሙሉ በእግዚአብሔር ጥበብ ህልም ሲፈታና በዙሪያው ላሉ ሰዎች መልካም መንፈስን ሲያሳይ ኖሯል። (ዳን 6፡3 ተመልከት) ✍️ ይህንንም ማድረግ የቻለው አምላኩ ያለውን ኃይልና ለእርሱ ያለውን የፍቅር ልብ ስለሚያውቅ ነበር። ሁልጊዜ በሚያገለግላቸው በነገስታቶች ፊት ሞገስን እንዲኖረው ያስቻለውና መውጫ የሌለው ከሚመስለው የአንበሶች ጉድጓድ ውስጥም አንዳች ጉዳት ሳይደርስበት መውጣት የቻለውም በሚያውቀው የእግዚአብሔር ፍቅር በመተማመኑ ነበር። ✍️ ወዳጄ፣ ዛሬ በሚታይና መቋቋም በማይችሉት ጥንካሬ፣ ጥበብና ሞገስ መራመድ ትፈልጋለህ? የእግዚአብሔርን ተዓምር ለማየትና በሕይወትህ ጥሶ መውጣት ትፈልጋለህ? እንደዚያ ከሆነ እግዚአብሔር ላንተ ያለውን ጸጋና ምህረት መስማትህን እንድትቀጥልና በውስጥህ ያለውን እውቀት እንድታሳድግ አበረታታሃለሁ። ✍️ ሰበዳንኤል ታሪክ ውስጥ ጌታ መልአኩን ልኮ "እጅግ የተወደደ" እንደሆነ ነግሮታል። (ዳን 10፡11) አንተንም የሚወድህ በመሆኑም ይበልጥ ስለእርሱ በሰማህና ላንተ ባለው ፍቅር በተማመንክ ቁጥር፣ ይበልጥ በደፋርነትና በልዩነት መኖር እንድትችል የሚያደርግህ መልካም መንፈስ ባንተ ሕይወት ውስጥ ይኖራል። ፓስተር ዳዊት ጥላሁን https://t.me/tetelestaye
Show all...
ጸጋ [ያልተገባን ሞገስ] ... የእግዚአብሔርን ገደብ የሌለው ችሮታ እና ጫፍ የሌለው ብልጥግና ማሳያ ነው!! ይህ ጸጋ በሕይወታችን እንዲሠራ (ላልቶ ይነበብ) ስፍራ ስንለቅ የሆነ ነገር ችለን የሆነ ነገር አያቅተንም፤ የቻይነቱን ተአምራት ዓይኖቻችን ያያሉ!! ❝ ... እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።❞ —2ኛ ቆሮ 9፥8-9። የእግዚአብሔር ጸጋ [ያልተገባን ሞገስ]  በምንም አይወሰንም!! ይህን ይችላል፥ ያ ያቅተዋል አይባልም!! ጸጋ [ያልተሸለምነው ስጦታ] የማይሠራው ጉዳይ እና አሁን የማይሠራበት ጊዜ የለም!! እግዚአብሔር ... #በየትኛውም ጊዜ፥ #ለየትኛውም ጉዳይ የሚሠራ፥ የተትረፈረፈ ጸጋ (ሞገስ) ይሰጣል!! በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
         #የዘላለም #ህይወት “ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።” — ቲቶ 3፥6-7 የዘላለም ህይወት ምንድን ነው ብለህ ራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ? ስለ ዘላለም ህይወት ስናስብ ብዙ ጊዜ የምናስበው የህይወቱ ጅማሬ ከሞት በኋላ የህይወቱ አይነት ደግሞ ዘላለማዊ ብለን ነው? ይህ አይነቱ አመለካከት በአብዛኛው የተለመደ ነው። ነገር ግን 🚨 የሕይወቱ አይነት ሳይሆን ርዝማኔው ነው ዘላለም፣ 🚨 ጅማሬውም ከሞት በኋላ ነው፤ ግን ከስጋ ሞት ሳይሆን ከአሮጌው አዳም ሞት በኋላ (በ ክርስቶስ ከሆንን በኋላ) ነው። 📍ሕይወቱን ለማብራራት የተገኘበትን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ሁሉም ሰው ሰይጣንን ጨምሮ ዘላለም ይኖራሉ፤ ስለዚህ "ዘላለም መኖር" የሚለው ብቻ ህይወቱን ሊያብራራው አይችልም። ከላይ ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ሕይወት እንዴት እንደሚገኝ ሲናገር "በጸጋው ጸድቀን የዘላለም ሕይወት ወራሽ እንድንሆን" ይለናል ስለዚህ የዚህ ሕይወት መገኛ ቅደም ተከተል እደሚከተለው ነው።                   ጸጋ➜ጽድቅ➜ሕይወት የሕይወቱ መገኛ ሕይወቱን ያብራራዋል!! መገኛው ጽድቅ ነው። ጽድቅ ደግሞ ሀጢአት ሰርቶ እንደማያውቅ ያለፍርሀት እና በልበ ሙሉነት በእግዚአብሔር ፊት የመቅረብ እና ኅብረት የማድረግ መብት ነው። “በእርሱና በእርሱ ላይ ባለን እምነት አማካይነት፣ በነጻነትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን።” — ኤፌሶን 3፥12 (አዲሱ መ.ት) ሕይወት ማለት ይህ ነው!! 📍አዳም ጋር ምን እንደሆነ ስናይ አዳም የሞተው አፈር ሲገባ አልነበረም፤ ጽድቁን ሲያጣ ነበር።  "በበላህ ቀን ትሞታለህ" የተባለው እና የእግዚአብሔርን ድምጽ ሲሰማ የተሸሸገው ጽድቁን ስላጣ ነው። የአዳምን ሞት ቅደም ተከተል ስናይ፦               ኃጢአት➜ኩነኔ➜ሞት “እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ” — ሮሜ 5፥18 መርሳት የሌለብን ግን አዳም የሞተው ለእግዚአብሔር ይሁን እንጂ ለሀጢአት እና ለሰይጣን ግን ህያው ሆኖ ነበር። 📍የእርሱ ሞት መገኛው ኩነኔ መነሻው ደግሞ ሀጢአት ነበር። 📍ለእርሱ ሞት የተባለለት መጥፋት ሳይሆን ከመገኛው መለየት ነው። ካልጠፋ ደግሞ ከመገኛው ተለይቶ ለሌላ ተገኝቶአል። እነሱም ለሀጢያት፣ ለኩነኔ እና ለሰይጣን ነው። 🚨እንዲሁ የኛ ሕይወት መገኛ ደግሞ ጽድቅ ነው። ጽድቅ ደግሞ ለሀጢአት ገድሎ ለእግዚአብሔር ህያው አድር ጎናል። “ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።” — ሮሜ 8፥10 ለሀጢአት የሞትነው ጽድቁ የተገኘው ከጸጋ ስለሆነ ነው። ጸጋ ደግሞ የተገኘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል በሰራልን ስራ ነው። #ጌታብቻ #ተስፋዬ እንደጻፈው        https://t.me/tetelestaye
Show all...
  ስኬታማ የሚያደርግህ በሕይወትህ ውስጥ የጌታ መገኘት ነው! ✍️ እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ። ዘፍጥረት 39፡2 ✍️ ስኬት ምን አለህ? ስለማለት ሳይሆን ማን አለህ? ስለማለት እንደሆነ ግልጽ አድርጎታል። ✍️ ዮሴፍ ምንም ቁሳዊ ነገር አልነበረውም፣ ነገር ግን ጌታ ከእርሱ ጋር ስለሆነ ሁሉንም ነገር ነበረው። ✍️ ስኬታማ የሚያደርግህ በሕይወትህ ውስጥ ያለው የጌታ መገኘት እንጁ፣ ያጠራቀምከው ቁሳዊ ነገር ወይም በጉጉት ልታከማቸው እየሞከርክ ያለኸው ነገር አይደለም። https://t.me/tetelestaye
Show all...
ከዓይነት አንጻር በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የገለጠው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (አጋፔ) በመባል ይታወቃል። ይህ ፍቅር ከሌሎች በተለየ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን በመስጠት የሰው ልጆችን እንደሚወድድ ያሳየበት ጥልቅ የፍቅር አይነት ነው። አጋፔ ከሰው ልጆች ምላሽን ሳይጠብቅ ራስን ለሞት አሳልፎ በመስጠት እውን የሆነ ድንቅ የፍቅር አይነት። ይገርማችኃል እናታችን እንኳን እኛ የሚትወደን ስለ ወለደችን ነው፣ባትወልድ አትወደንም ነበር ማለት እናታችን ጋር ራሱ መወደዳችን ምክንያት አለው ያም መወልድ ይባላል።እግዚአብሔር ጋር ግን #እንዲሁ ነው። ሌላኛው የእግዚአብሔር ፍቅር ትምህርት ለአዳድስ ክርስትያኖች የሚያስፈልግ ትምህርት ነው ተብሎ ብዙዎች ጋር ይታሰባል ጉዳዩ ግን እንዲያ አይደለም አዳድስ ክርስቲያኖች እንኳን ደስተኛ ከምንም በላይ ፈገግ ያሉ ናቸው በጸጋ እንደ ዳኑ ፣በክርስቶስ እንደሆኑ ስሰሙ ደስታ ብቻ ሳይሆን ሀሴት ይሞላቸዋል ግን የቆዩ ክርስትያኖች ከእግዚአብሔር ከመታመን ወደ ራስ ፣በእግዚአብሔር ከመደገፍ በራሱ ላይ ትኩረት ባደረገ ሕይወት ወደ ጭንቀት ይመራሉ ስለዝህ የእግዚአብሔር መረዳት እጅጉን ያስፈልጋቸዋል። የእግዚአብሔር ፍቅር ስንረዳ እናርፋለን፣እንረጋጋለን። የእግዚአብሔርን ፍቅር መረዳት ከሚለው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ 📚 የእግዚአብሔርን ፍቅር መረዳት 💎 በሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ ለበለጠ መረጃ : 📞 +251 902 77 0000 Share 👉 @AgapeGLCZ
Show all...
ከምናየው ይልቅ #አተያያችን ! ሙሴ ከነአንን የሚሰልሉ አስራ ሁለት ሰዎችን ከፋራን ምድረ በዳ ላከ። እነርሱም ምድሪቱን ለአርባ ቀናት ሰልለው ተመለሱ። ሪፓርታቸው ግን የተለያዬ ነበር። ስለከተማዋ አስሩ የደረሱበት ድምዳሜ፦ ❝ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች እያወሩ፦ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፤ በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው።❞ የሚል ነበር። —ዘኍልቁ 13፥32። የሁለቱ (የኢያሱ እና የካሌብ) ድምዳሜ በተቃራኒው ነበር። ❝ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት።❞ —ዘኍልቁ 14፥7። ሁለቱም ለአርባ ቀናት የሰለሉት አንዲትን አገር ነው፤ ከነአንን። ታዲያ እንዴት ሪፓርታቸው ተለያዬ? #አተያይ!! ከምናየው በላይ #የምናይበት መነፅር ዋጋ አለው!! አስሩ የሚታያቸው የጠላቶቻቸው ግዝፈት፤ ሁለቱ የታያቸው የእግዚአብሔር አብሮነት። ❝ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።❞ —ዘኍልቁ 14፥9። አስሩ የሚታያቸው ሲሞቱ፤ ሁለቱ የሚያዩት ሲወርሱ። በመጨረሻ ከአዲሱ ትውልድ ጋር ወደ ከተማዋ የገቡት ኢያሱ እና ካሌብ ብቻ ናቸው። ወደ ትክክለኛ ውሳኔ የሚያመጣን ያዬነው ሳይሆን ያዬንበት መንገድ ነው!! አንድ አይነት መሬት እያዩ የተለያየ ነገር ገባቸው!! ይህ እይታ ፍጻሜያቸውን ወሰነው!! ያዬኸው ሳይሆን አተያይህ ፍጻሜህን ሊወስነው ይችላል!! ማየት የፈለከውን ሳይሆን እንድታይ የተፈለገውን ተመልከት!! #የተሰቀለውን!! በኢየሱስ ስም የነፍሳችን ዓይን ይከፈት፥ የታየልንን ማየት ይሁንልን!! አሜን! ! https://t.me/tetelestaye
Show all...
I am convinced the greatest act of love we can ever perform for people is to tell them about God's love for them in Christ. Evangelist Dr.Billy Graham ለሰዎች ልንፈጽማቸው የምንችላቸው ትልቁ የፍቅር ተግባር እግዚአብሔር በክርስቶስ ስላለው ፍቅር መንገር እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። ወንጌላዊው ዶክተር ቢሊ ግራሃም
Show all...
በህልውናህ በህልውናህ በመገኘትህ በመገኘትህ የማይሆንልኝ ነገር የለም ሁሉነው ቀላል ×4 ___ በህልውናህ እንዳለ / Tsihon https://t.me/tetelestaye
Show all...
#መከናወን እግዚአብሔር በነገር ሁሉ #እንዲሳካላችሁ ይፈልጋል፥ መከናወን እንድትችሉ #ይረዳችኋል!! ❝ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።❞ —3ኛ ዮሐንስ 1፥2። እግዚአብሔር በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ባርኮናል!! (ኤፌሶን 1፥3) ዘራችን ቡሩክ ነው!! ሃሌ ሉያ!! ስለዚህ እግዚአብሔር ሕይወታችን በክንውን እንዲሞላ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው!! በነገር ሁሉ እንዲከናወንልን እግዚአብሔር ይፈልጋል!! ለዚህ ነገር እግዚአብሔር ይተባበረናል!! በስኬትህ ደስ የማይለየው እና ለስኬትህ የማይተባበርህ ሰይጣን ብቻ ነው!! ሽማግሌው ዮሐንስ ለጋይዮስ እንዴት እንደጸለየለት ተመልከቱ፦ ❝ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።❞ —3ኛ ዮሐንስ 1፥2። አመጽ የሌለበት ስኬት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው!! ባይሆን ኖሮ ሐዋርያው #እንዲህ አይጸልይም ነበር!! ይህ ሐዋርያ እግዚአብሔርን በክርስቶስ በመረዳት የጎለመሰ እና እንደ ፈቃዱ በመጸለይ የሚያምን አማኝ ነው!! ያ ማለት የጸለየው እንደ ቃሉ በትክክል ነው!! ወዳጆቼ በነገር ሁሉ #እንዲሳካላችሁ እግዚአብሔር ይፈልጋል!! መከናወን እንድትችሉ #ይረዳችኋል!! እግዚአብሔር ተጨምድዳችሁ እንድትኖሩ አይፈልግም!! እግዚአብሔር እንድትጨነግፉ ፈቃዱ አይደለም!! ለስኬት #ከመሳካት ጉዞ ጀምራችኋል!! እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ፥ ለእናንተ ነው!! ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ሁሉ በነገር ሁሉ እንዲሳካላችሁ ጸልያለሁ!! በኢየሱስ ስም ነገሮቻችሁ መልክ ይያዙ!! በኢየሱስ ስም የከበዱ አሠራሮች ቀላል ይሁኑላችሁ!! በኢየሱስ ስም ነገሮች ይሰካኩላችሁ!! በኢየሱስ ስም በእጆቻችሁ የተጀመሩ ሥራዎች በፍሬ ይሞሉ!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
#መከናወን #የሚሳካልህ ብዙ #ስለደከምክ አይደለም!! ❝ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።❞ —ዘፍጥረት 39፥3። ዮሴፍ የሚሠራው ሁሉ በእጁ ይከናወንለት ነበር፤ እርሱ ያለበት ነገር ሁሉ ውበቱ ጎልቶ ይወጣል። የስኬቱ ምስጢር ብዙ ስለደከመ አልነበረም፤ ብዙ በመድከም ቢሆን ከእርሱ በላይ የሚደክሙ ሌሎች ባሮች ነበሩ። የዮሴፍ መከናወን ምስጢር የያሕዌ አብሮነት ነው!! እስኪጎብጡ ድረስ ብዙ የሚደክሙ ሰዎች አሉ፦ እነዚህ ሰዎች ሲማረሩ እንጂ ነገር ሲሰምርላቸው አይታይም። የእግዚአብሔርን አብሮነት መረዳት ግን ብዙ ነገሮችን ይለውጣል። የዮሴፍ ስኬት በሚሰራው ሁሉ እንደነበር አስታውሱ፦ የብዙዎች ስኬት እንደዚህ አይደለም!! ለምሳሌ፦ ብዙ ሀብት ይኖራቸዋል፤ ዲስፕሊን የላቸውም፤ የአንዳንዶቹ ቤተሰብ ፈርሷል፤ የሌሎቹ ጤናቸው ተጎድቷል፥ ከዚህ እንኳን ተረፉ ስትሉ የበጎ ነገር ባለጸጋ አይደሉም። የእግዚአብሔር አብሮነት የሚሰጥህ ስኬት ግን እንደዚህ አይደለም!! ያገሬ ልጆች ስለስኬት እንደገና ማሰብ አለብን!? #እግዚአብሔርን #ተሳታፊ ስላደረገ ስኬት እናስብ!! እግዚአብሔር በክርስቶስ አብሯችሁ ነው፤ የምትሠሩትን ሁሉ በእጃችሁ ሊያከናውንላችሁ ይችላል!! ወደ ሥራችሁ ጋብዙት!! ወደ ትዳራችሁ ጋብዙት!! ❝እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ❞ —ዘፍጥረት 39: 2 https://t.me/tetelestaye
Show all...
በኢየሱስ ላይ የተነሱ መካከለኞች ❗ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 👉መካከለኛ ማለት በሁለት ወገን መካከል ለማስታረቅ የሚቆም ማለት ነው።(የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ፤የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገብ ቃላት ገጽ 41፤ 1992 ዓ.ም 6ኛ ዕትም ፤ባናዊ ማተምያ ቤት ፤አድስ አበባ) 👉ነብያትና ካህናት በእግዚአብሔር ፈቃድ በመካለኛነት ያገለግሉ ነበር ።በሙሴና በአሮን መካከለኛነት በመቃወም በራሳቸው ለራሳቸው መካከለኛ ለመሆን ትዕብተኞች ተነሱ።በእግዚአብሔር ላይም አመጹ፤ክህነት በመፈለግ። “..፤ ክህነትንም ደግሞ ትፈልጋላችሁን?” — ዘኍልቁ 16፥10። ስለዚህም ነገር እግዚአብሔር በቁጣው ቀሰፋቸው "ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው " ዘኁ 16፥33 ። 👉 እግዚአብሔር በቁጣ ከቀሰፋቸው በኃላ የሚመጣው ትውልድ #ክህነት_እፈልጋለሁ ብሎ እንዳይነሳ አስጠነቀቀ ዘኁ 16፥38። በእስራኤል ታርክ መካከለኛ ለመሆን የተነሳ አልነበረም ።ተምረዋል ። 👉 የአድስ ክዳን ብቻኛው #መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻና ብቻ ነው መጽሐፍ እንደምል ።“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ #አንድ_አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5። 👉 ስለዚህ በዚህ እውነት ላይ የተነሱ መናፍቃን እኔ ማናቸው ብትሉ "ሰዎችንና መላእክትን መካከለኛ ያደረጉ" ሁሉ ናቸው ።ማሳያ "ያን ጊዜም ከስዕሉ ቃል ወጥቶ ስልጣኑ ከሰማይ ከፍታ ከፍ የሚል ንፅህናውም ከሚካኤል ከገብርኤል የሚተካከል ክህነቱ #እንደመልከጸዴቅ..የሆነ ልጅ አንቺ ተቀበይ አላት።"(ም.15 ገደለ ገብረመንፈስ ቅዱስ)፥ደግሞም ያለ ማርያም አማላጅነት አይድንም የሚሉ፣ ገብረመንፈስ ቅዱስ የዘላለም ልቀ ካህን ነህ የሚሉ ....ማሳያዎች ናቸው ። 👉የቆሮንና ልጆቹን ያጠፋው እግዚአብሔር ፥በዚህ ዘመን ለዓመቴ ምህረት (ለክርስቶስ ደም) ስል እንደሚታገሰ ሃቅ ነው። ፨በእግዚአብሔር የተሰጠን ፣ ፨በሐዋሪያት የተመሰከረው ፣ ፨አባቶች የተቀበሉት ፣ ፨አንድ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻና ብቻ ነው። ...... https://t.me/tetelestaye
Show all...
መልካም ነህ Fenan Befkadu ʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ መልካም ምሽት ♥️ https://t.me/tetelestaye
Show all...
እግዚአብሔር የመጠረጠን አስቀድሞ ነው፣ይህም ማለት እኛ ሳንኖር ነው።የመርምጠን አወዳድኖር አይደለም ደሞም የመረጠንም በእኛ ምን/ስራ፣ድርግት፣እምነት፣መንፈሳዊነት/ ተመስርቶ ሳይሆን በማን /በማንነት ማለትም ፡-ክርስቶስ እየሱስ በሚባል ማንነት /ላይ ተመስርቶ ነው ። እግዚአብሔር ጋር ምርጫ #በማን ነው #በምን አይደለም በማን ራሱ ልዩነት አለው!! 👉 በማርያም❓ አይደለም!!!! 👉በሰማዕታት❓ አይደለም!!!! 👉በአባቶች ❓አይደለም !!!! እና በማን ❓ " ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ #በክርስቶስ መረጠን።" (ኤፌ 1: 4) በክርስቶስ ነዋ !!!! በውድ ልጁ ነዋ !!! መልካም ምሽት ♥️ https://t.me/tetelestaye
Show all...
#አያጠፋም!! ❝ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው።❞ —ዮሐንስ 6፥39። እግዚአብሔር እኛን ለኢየሱስ፥ ኢየሱስን ለእኛ ሰጥቷል!! ጌታ ኢየሱስ አብ የሰጠውን ሁሉ ተቀብሏል!! የተሰጠውን ሁሉ በሕይወት ይጠብቃል፤ አንድን ስንኳ አያጠፋም!! በዚህ ምድር ላለው ኑሯችን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ ላለው ሕይወት ዋስትናችን ነው!! ከሙታን እንኳን ሊያስነሳን ስልጣን አለው፤ የእርሱ ሆኖ በመቃብር የሚቀር የለም!! ላለመጥፋታችን ማረጋገጫው የእኛ ሁኔታ ሳይሆን የኢየሱስ ማንነት ነው!! የእርሱ እጅ የያዘዉን አይለቅም!! እርሱን ሕይወት ያደረገ አይጠፋም!! ❝እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።❞ —ዮሐንስ 10፥28። ተወዳጆች በያዛችሁ እጅ ተማመኑ!! በክርስቶስ በመዳናችሁ እርግጠኛ ሁኑ!! የእርሱ የሆናችሁ አትጠፉም!! በወንጌላችን የወጣው የዘላለም ሕይወት ብቻ ሳይሆን #አለመጥፋትም ነው!! ❝ ... በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።❞ —2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥10-11። #አንጠፋም የምላችሁ በታማኙ እረኛችን ተማምኜ ነው፤ እርሱ አያጠፋም!! ሁኔታችንን ሳይሆን መልካሙን እረኛችንን አይተን ያለመጥፋት ድምዳሜ ላይ መድረስ እንችላለን!! እርሱ እንዲሁ ብሏልና፦ ''... ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው" #በእርሱ ላለን ሕይወት እንጂ ጥፋት አልተጻፈልንም!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
እምነታችሁን ክርስቶስ ላይ ብቻ ያደረጋቹ ጓደኞቼ ፦ እስከመጨረሻው ምትጸኑት እናንተ ጌታን አጥብቃቹ ስለያዛችሁት ሳይሆን እንዳውም በተቃራኒ እሱ ዘላለማዊ በሆነው ጥብቅ እጁ ስለያዝዛቹ ነው። መልካም ምሽት https://t.me/tetelestaye
Show all...
ይህን መጽሐፍ ለመረዳት፦ ✦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲተረጉም መፍቀድ!! ✦ ትርጉሙን ከጥቅሱ ውስጥ ማንበብ እንጂ ወደ ጥቅሱ ውስጥ ትርጉም አለማምጣት፡፡ ቃሉ ራሱ እንዲያወራን መታዘዝ እንጂ የራሳችንን ወይም የሰውን አሳብ ወደ ቃሉ ማምጣት የለብንም!! ✦ ከስፍረ ዘመኑ (Dispensation) አንጻር እንዴት ይታያል? (ባለፈው ያጠናነውን Critical Study #6 ይመልከቱ) ✦ ጊዜውን (Tense) ማየት፦ ለምሳሌ ለአማኞች የተጻፈውን ይህን ክፍል እንይ፦ ❝ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።❞ —1ኛ ቆሮንቶስ 6፥11። "ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል" የሚለው ኃላፊ ጊዜ ነው!! ትጸድቃላችሁ አላላቸውም የጸደቁ አማኞች ናቸው!! ✦ አውድ (Context)፦ 1) ሙሉ የመጽሐፉ ርእሰ ጉዳይ ምንድነው? ለምሳሌ፦ የሮሜን መልእክት ቢሆን እያጠናን ያለነው፦ ዋና ጭብጡ "በእምነት መጽደቅ" የሚል ነው፤ የሚያነሳቸው አሳቦች ሁሉ ይህን ለማብራራት ነው። 2) ሙሉ ምዕራፉ ምንድነው እየነገረን ያለው? 3) ክፉሉ (አንቀጹ) ከአጠቃላይ የመጽሐፉ ወይም የምዕራፉ አሳብ አንጻር ምን ይመስላል? ✦የምናጠናው የመጽሐፍ ክፍል ከተፈጸመው የኢየሱስ የመስቀል ሥራ ( Finished Work of Jesus Christ) አንጻር እንዴት ይታያል? መጽሐፎቹ የሚናገሩት ስለክርስቶስ፤ የመጽሐፉም መተርጎሚያ ክርስቶስ ነው!! የኢየሱስ የተፈጸመ ሥራ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ማስተዋል አለብን፡፡ ✦ ክፍሉ ከሰው ሁለንተና አንጻር ስለ ምንድን ነው የሚያወራው? ስለ ሰው መንፈስ የተነገረውን ስለነፍስ ወይም ስለሥጋ መረዳት የለብንም!! ለምሳሌ፦ ከላይ ያዬነው 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥11 ስለ መንፈሳችን መዳን ነው የሚናገረው፤ ነፍሳችን እየዳነች ነው፤ ሥጋችን ደግሞ አዳኙን እየጠበቀ ነው!! ✦ መጽሐፉ የተጻፈላቸው (ተደራሲያን) ወቅታዊ ሁኔታና ባሕል (Background & Culture) ምን ነበር? ለምሳሌ፦ ❝ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።❞ ለምን አላቸው? —1ኛ ቆሮንቶስ 11፥6 በዚህ ጥናት ላይ በይበልጥ እንዲረዳን መጽሐፍ ቅዱስን በምንተረጉምበት ጊዜ ልንጠይቅ የሚገቡ አስፈላጊ የሆኑ አራት ጥያቄዎችን በጥልቀት እንመለከታለን፡- ⓵ ተናጋሪው ማነው? ⓶ የተነገረው ለማን ነው? (ሰሚው) ⓷ የተነገረው ስለ ምንድነው? (ርእሰ ጉዳዩ) ⓸ ጥቅሱን ከክርስቶስ የመስቀል ሥራ አንጻር እንዴት እንረዳዋለን?  
Show all...
.     ገረመኝ || ሐዋሪያው ዮሐንስ ግርማ         sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ           https://t.me/tetelestaye
Show all...
.         እንደ ሰው || ሀና ተክሌ         sʜᴀʀᴇ ◈ Join ◈ sʜᴀʀᴇ                     ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው                https://t.me/tetelestaye
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!