cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

Show more
Advertising posts
429Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እግዚአብሔር ከጠላት ቤት ወዳጅ ያዘጋጃል!! ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቀጠሮ ይዟል። ሁሉም ሰው ከንጉሡ ጋር ለመስማማት ማሰብ አይጠበቅበትም። ዳዊትን መግደል ያሸልማል እንጂ አያስወቅስም። በዚህ ሁኔታ የዳዊት ወዳጅ መሆን አይታሰብም። እግዚአብሔር ግን የሳኦልን ልጅ የዳዊት ወዳጅ አደረገው። የጠላትህን ልጅ #ለአንተ #እንዲሠራ ማድረግ ይችላል። ዮናታን ከአባቱ ጋር ተስማምቶ ዳዊትን በመግደል ቀጣዩ የእስራኤል ንጉሥ ለመሆን አላሰበም። የራሱን ጥቅም ለማስከበር አልሮጠም። ለሥጋዬ (ለአባቴ) ላድላ አላለም። እንደ ነፍሱ ከወደደው ከዳዊት ጋር ላቆመው ኪዳን ተሸነፈ። እግዚአብሔር በዳዊት ሊያደርግ ካለው አላማ ጋር ተስማማ።  አምላካችን እጅግ ኃያል ነው። ሊያጠፉን ካቀዱት ጋር ተስማምቶ አያውቅም። እንዲያውም ከገዛ ቤታቸው ወዳጅ ያስነሳልናል። ሳኦል ሰይፉን ሲስል በቤተ-መንግስቱ ጋሻ ጃግሬዎቹም አብረው ሲዶልቱ (፪x) ትልቁም ትንሹም ዳዊትን ሲያወግዝ ማን ይሆን ዮናታን ምስኪኑን የሚያግዝ ....... አለኝ ወዳጅ የማይከዳ ኑሮ ቢሆን ምድረ በዳ የቀረበ ሲርቅ ያጀበ ሲበተን ዞር ቀና ብዬ ሳይህ አላጣሁም አንተን https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

ሕይወት፣ የማይደበዝዝ ተስፋ፣ ሙሉ ሠላምና ደስታ፣ የሕይወት ዘመን ጽናት ያለው በወንጌል ውስጥ ብቻ ነው! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

If the assurance of my salvation depends on my faithfulness to Christ rather than Christ's faithful and saving work, how then that could be a Gospel? God already knows that I'm depraved, wicked, and the most miserable person among a sinner. In other words, the assurance of my salvation depends on my faithfulness to the Gospel means that the work of Christ is not enough to preserve me to the end. This kind of understanding is heresy. ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አዳኛችን መልካም ነው። መስቀል ላይ የተሰራው አስደናቂ ሥራ፤ የእርሱ የሆኑትን እስከመጨረሻው ያፀናቸዋል። የወንጌሉ ተስፋ ይኽ ነው። በክርስቶስ ወንጌል ውስጥ አለመጥፋት እንጂ መጥፋት የለም!! @https://t.me/tetelestaye
Show all...
ከመንፈሱ ጋር ካልሠራህ ነገሩን እግዚአብሔር እንደሚፈልገው አትሠራውም!! ❝መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።❞ —ዘካርያስ 4፥6። እግዚአብሔርን ማገልገል ከሆነ ጥሪህ ያለ መንፈስ ቅዱስ አትችልም!! እግዚአብሔር #በመንፈሴ ካለ አንተም በመንፈሱ ብለህ ቀጥል፤ አትላላጥ!! ከመንፈሱ ጋር ካልሠራህ ነገሩን እግዚአብሔር እንደሚፈልገው አትሠራውም!! በሰው ኃይል እና ብርታት ሊደፈሩ የማይችሉ ነገሮች አሉ። በመንፈሱ ግን ሳያልብህ ትሠራዋለህ!! በቀላሉ ሊሠሩ የሚችሉ ነገሮች እንኳን ብዙ ያታግሉናል። በመንፈሱ ሲሆን ግን ከባድ የሚባል ነገር የለም፤ አይቻልም የሚባል ነገር አይኖርም!! ጴጥሮስ ያለ መንፈሱ ለሚወደው ጌታ መታመን አልቻለም፤ እንደ ቃሉ መገኘት አልቻለም!! መንፈስ ቅዱስ ከወረደ በኋላ ግን እንዴት ባለ ድፍረት እና ኃይል እንደተመላለሰ ግልጽ ነው!! ክርስቶስን እንደተረዳነው መታዘዝ የምንችለው ከመንፈሱ የተነሳ ነው!! የኢየሱስ ሆነን ለመቀጠል ዋስትናችን መንፈሱ ነው!! ❝መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ።❞ —2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥14። የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን አለ፤ በእርሱ ወይም በራሳችን ማስተዋል መደገፍ ምርጫው የእኛ ነው!! ከእኛ ምክንያት ይልቅ የእርሱ ምሪት ይበልጣል!! በእርሱ ብንታመን በታየልን ልክ መራመድ እንችላለን!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

#የሚሳካልህ ብዙ #ስለደከምክ አይደለም!! ❝ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።❞ —ዘፍጥረት 39፥3። ዮሴፍ የሚሠራው ሁሉ በእጁ ይከናወንለት ነበር፤ እርሱ ያለበት ነገር ሁሉ ውበቱ ጎልቶ ይወጣል። የስኬቱ ምስጢር ብዙ ስለደከመ አልነበረም፤ ብዙ በመድከም ቢሆን ከእርሱ በላይ የሚደክሙ ሌሎች ባሮች ነበሩ። የዮሴፍ መከናወን ምስጢር የያሕዌ አብሮነት ነው!! እስኪጎብጡ ድረስ ብዙ የሚደክሙ ሰዎች አሉ፦ እነዚህ ሰዎች ሲማረሩ እንጂ ነገር ሲሰምርላቸው አይታይም። የእግዚአብሔርን አብሮነት መረዳት ግን ብዙ ነገሮችን ይለውጣል። የዮሴፍ ስኬት በሚሰራው ሁሉ እንደነበር አስታውሱ፦ የብዙዎች ስኬት እንደዚህ አይደለም!! ለምሳሌ፦ ብዙ ሀብት ይኖራቸዋል፤ ዲስፕሊን የላቸውም፤ የአንዳንዶቹ ቤተሰብ ፈርሷል፤ የሌሎቹ ጤናቸው ተጎድቷል፥ ከዚህ እንኳን ተረፉ ስትሉ የበጎ ነገር ባለጸጋ አይደሉም። የእግዚአብሔር አብሮነት የሚሰጥህ ስኬት ግን እንደዚህ አይደለም!! ያገሬ ልጆች ስለስኬት እንደገና ማሰብ አለብን!? #እግዚአብሔርን #ተሳታፊ ስላደረገ ስኬት እናስብ!! እግዚአብሔር በክርስቶስ አብሯችሁ ነው፤ የምትሠሩትን ሁሉ በእጃችሁ ሊያከናውንላችሁ ይችላል!! ወደ ሥራችሁ ጋብዙት!! ወደ ትዳራችሁ ጋብዙት!! ❝እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ❞ —ዘፍጥረት 39: 2 https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

#በመንፈሱ #መመራት ❝በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።❞ —ሮሜ 8፥14። ሕይወታችን እና አገልግሎታችን በእግዚአብሔር መንፈስ እንዲመራ ከመረጥን ወደ ብስለት (Maturity) መጥተናል ማለት ነው!! በጠቀስነው ክፍል ... ልጆች በሚል የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ሁዮስ (Huios) የሚል ነው። ሁዮስ የሚያመለክተው ... በብስለት ያደጉ፣ ስሜታቸውን የሚገዙ፣ አእምሯቸውን በቃል እውቀት ያበለጸጉ፣ መረዳት የሚችሉ እና የበሰለ ውሳኔ ለመወሰን የበቁ ልጆችን ነው!! በመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ስር መተዳደር ትልቁ የብስለት ምልክት ነው!! በመንፈሳዊ ነገር ካልበሰልን ... ከእምነት ይልቅ ለስሜታችን እንታዘዛለን!! ከምሪት ይልቅ ምክንያትን እንከተላለን!! ከአላማ ይልቅ ተድላን እንመርጣለን!! በመንፈሱ መመራት ማለት #እኛ #የምንፈልገውን ሳይሆን #እርሱ #የሚፈልገውን መታዘዝ ማለት ነው!! ይህ ምርጫ ቀላል ላይሆን ይችላል፤ ሕይወትን ግን ቀላል ያደርጋል!! ስለዚህ በስሜት ሕዋሶች ከተቀበልነው መረጃ ተነስተን ከመወሰን መላቀቅ እና የእረኛችንን ድምፅ መከተል ይኖርብናል!! በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ የተለዩ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ከውጭ ሆኖ መርቷቸዋል። በዚህኛው ኪዳን ግን በውስጣችን ሁኖ ይመራናል፤ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል። ለእነርሱ ፈቃዱን ገልጦላቸው ይሄድ ነበር፤ ለእኛ ፈቃዱን ብቻ ገልጦ አይሄድም፤ አብሮን ይኖራል። ወደ እነርሱ ይመላለስ ነበር፤ በእኛ ውስጥ ግን እየኖረ ነው። በብሉይ ኪዳን በነበሩ መንፈሳዊ ሰዎች ይሠራል እንጂ አይኖርም። ለእነርሱ እንዳደረገው አሳብ ሰጥቶ ትቶን አልሄደም፤ በውስጣችን ሁኖ ያስብልናል!! አሳቡ ብቻ ሳይሆን አሳቢው በውስጣችን አለ!! በዚህ መንፈስ መመራት ሕይወታችን ሁልጊዜ ወደ ዕረፍት ውኃ እንዲመራ መምረጥ ነው!! በመንፈስ ቅዱስ መመራት ያለ ድካም ትክክሉን ብቻ የማድረግ ውሳኔን መከተል ነው!! በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ሕይወት ሲኖረን ያለውን ብቻ መታዘዝ እንመርጣለን። ማድረግ ቢሆን አለማድረግ፣ መናገር ቢሆን አለመናገር፣ መሄድ ቢሆን አለመሄድ፣ ....ሁሉም እንደሚፈልገው እንዲሆን መምረጥ ይሻለናል!! ለምሳሌ፦ እነጳውሎስ በእስያ ሳሉ ቃሉን እንዳይናገሩ ከለከላቸው፤ አልፈው ሄዱ። ❝በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤❞ —ሐዋርያት 16፥6። ደግሞ ዝም አትበል፤ ተናገር ሲለው ተናገረ። ❝ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን፦ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሣብህ የለምና አትፍራ፥ ነገር ግን ተናገር ዝምም አትበል፤ በዚህ ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉኝና አለው።❞ —ሐዋርያት 18፥9-10። የአገልግሎት መሳካት ያለው እንደዚህ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት በመከተል ነው!! መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ እርምጃችን እንዲቀድም እንፍቀድ!! ሕይወታችን ሙሉ በሙሉ በእርሱ አመራር ወደሚተዳደርበት ከፍታ ይውጣ!! የእግዚአብሔር ልጆች የብስለት ልኬት እና የሕይወት ስኬት በመንፈሱ በመመራት ይገለጣል!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

ፍቅር እና ፍቅር ያልሆነው (Love vs Lust) (ይህ መልእክት በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ላሉ እና መግባት ለሚያስቡ ይሁን!!) ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ ሰባትን እና ኤፌሶን ምዕራፍ አምስትን የጻፈበት መንገድ እጅግ ያስደንቃል!! አገልጋይ ምንንም ነገር ከክርስቶስ አንጻር የሚተረጉምበት ብርሃን ካገኘው እንዲህ ይሆናል!! የፍቅር ግንኙነት ከእኛ ዓለም እውቀት ተነስቶ አይተረጎምም!! የፍቅር ንድፈ አሳቡ (Blueprint) ያለው ምንጩ (Source) ጋር ነው፤ እርሱም፦ እግዚአብሔር!! ከተሳኩ ወይም ከተሰነካከሉ የፍቅር ታሪኮች ተነስቶ ፍቅርን መተርጎም ልክ አይደለም!! የፍቅር ግንኙነት መብራራት ያለበት ከእግዚአብሔር አሳብ አንጻር ነው!! የፍቅር አሳብ በልባችን ከተጸነሰ ...ሮጠን ማውራት ያለብን ለጓደኞቻችን ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው!! ሕይወቱ እንዴት እንደሚተረጎም መናገር የሚችለው፤ እንዴት እንደሚመራ መርህ የሰጠው እርሱ ነው!! የፍቅር ግንኙነት የሚለካበት የሕይወት ብቃት (Standard) አለው፤ እርሱም፦ በክርስቶስ እና በእኛ መካከል ያለው ኅብረት ነው። በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ያለው ፍቅር ንፁህ እና ውብ መሆን ያለበት ለዚህ ነው። #ጋብቻን ሰው #እንዳቀለለው ሳይሆን #እግዚአብሔር እንዳቀደለት ማየት አስፈላጊ ነው!! ተወዳጆች እኛ ባለቤት አለን፤ በደም የገዛን ላቀደው ሕይወት ሰውነታችን መታዘዝ አለበት። (1ኛ ቆሮንቶስ 6 እና 7 ይመልከቱ) ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ሲጽፍ... ያጻፈው #የቅድስና #መንፈስ ዛሬም ሕያው ነው!! እግዚአብሔር ...ልጆቹ ለሰይጣን ደጅ እንድንከፍት እና እንድንሰነካከል አይፈልግም!! እርሱ ከብሮ የሚታይበት ምልልስ እንዲኖረን ይፈልጋል!! በእርግጥ በዚህም ዘመን ... ንጹሕ ፍቅር አለ፤ ፍቅርን የሚቀበል ንጹሕ ልብ አለ፤ እግዚአብሔር የሚፈራበት ትዳር አለ፤ በተቀበሉት ራስን የመግዛት መንፈስ ታዘዉ የሚኖሩ የጸጋ ቅሬታዎች አሉ። በተቃራኒው መረን የሆነ ሕይወትን የለመዱ ሰዎች መኖራቸው እጅግ አሳዛኝ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ...እኛ በክርስቶስ ኢየሱስ ስም በአምላካችን መንፈስ #ተቀድሰናል፤ ለቀዳሹ በሚሆን መጠን ስለተቀደስን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን እየኖረ ነው!! ይህ እጅግ አስደናቂ እውነት ነው!! ስለዚህ ነው ለሕይወታችን የምንጠነቀቅለት!! ለእኛም ጥቅም፥ በእኛም ለሚኖረው ክብር እንድንኖር የሚረዳን ጸጋ ተሰጥቶናል!! በልባችን እንዳይፀነስ በቃሉና በመንፈሱ የምንወጋው አሳብ አለ፤ ከተፀነሰ ደግሞ ግቡን እንዳይመታ ምሽጉን ማፍረስ አለብን!! "ፍቅርን" እና "በፍቅር ስም ያሉ" ድለላዎችን መለየት ይኖርብናል!! ልባችን በስሜት ቁጥጥር ስር ከመሆኑ በፊት ፍቅር የሆነውን እና ፍቅር ያልሆነውን ቆም ብለን መመዘን ይኖርብናል!? • ፍቅር የሆነው አይቸኩልም፤ በጥልቀት ለመተዋወቅ ጊዜ ይወስዳል!! ፍቅር ያልሆነው (Lust) የተቆጣጠረው ...ከግንኙነቱ የሚያተርፈውን ነገር እንጂ ስለእርሷ ማወቅ አይገደውም!! • ፍቅር የሆነው ክብር፣ ውሳኔ እና ነገን አብሮ ማለም ይንጸባረቅበታል!! ሕይወቱ ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲታነጽ ይተጋል!! ፍቅር ያልሆነው ልብን በስሜት መንዳትና ለዝሙት ማዘጋጀት እንጂ ነገ አይታየውም!! • ፍቅር የሆነው ከመቀበል ይልቅ መስጠት ላይ ያተኩራል!! ፍቅር ያልሆነው እንኳን ሊሰጥ በሚቀበለው አይረካም!! • ፍቅር የሆነው የሚያስከፍለውን ሁሉ ዋጋ ከፍሎ ፍቅሩን አካል ያስይዛል!! ፍቅር ያልሆነው ግንኙነቱን በአሳብ ከማለም አልፎ ወደ መሬት አያወርደውም!! • ፍቅር የሆነው የፍቅር ጓደኛውን ጥንካሬና ድካም አብጠርጥሮ ያውቃል፤ ጥንካሬን ያበረታታል፤ ድካምን ለማስወገድ አብሮ ይሠራል!! ፍቅር ያልሆነው የፍቅር ጓደኛውን እንከን መቀበልም ማገዝም አይፈልግም!! • ፍቅር የሆነው እምነትን (Trust) እና ወዳጅነትን ይገነባል!! ፍቅር ያልሆነው የጊዜው ደስታ ላይ ያተኩራል!! ነገን 'ሚያይበት ዓይን የለውም!! • ፍቅር የሆነው እውነትን ማዕከል ያደርጋል፤ በአቋም ጸንቶ ይቀጥላል!! ፍቅር ያልሆነው ስሜትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ሲነጋ ተወርቶለት ሲመሽ አይገኝም!! ጠቢቡ ሰሎሞን ፍቅር የሆነውን እና ያልሆነውን ለይቶ ተረድቷል፤ ፍቅር ያልሆነውን ማለትም ዝሙትን ተቃውሟል። እርሱ ከገለፀበት አረዳድ ፍቅር የሆነውን እና ያልሆነውን የሚያሳዩ መገለጫ ጠባዮችን (Character) እንመለከታለን!! ፍቅር ያልሆነው፦ 1) ለዝሙት የሚያነሳሳ አቀራረብ (Sexual attraction)፦ በአለባበስ ይማርካል፤ በንግግር ያሳምናል!! "ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነውና፤" ምሳሌ 5፥3። ❝ከጋለሞታ ሴት አንተን ለመታደግ፥ ቃልዋን ከምታለዝብ ከሌላዪቱም ሴት፤❞ —ምሳሌ 2፥16። "ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥ ከሌላይቱም ሴት ምላስ ጥፍጥነት።" ምሳሌ 6፥24። 2) እውነት እና እርጋታ የለውም!! ግንኙነቱ የት እንደሚደርስ አይታወቅም!! "የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፤ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።" ምሳሌ 5፥6። 3) ግንኙነቱ ላንተ ምላሽ የለውም!! አንተ ለእርሷ ትደክማለህ፤ እርሷ ለሌላ ትኖራለች!! "ሌሎች ከሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ ድካምህም በባዕድ ሰው ቤት እንዳይሆን።" ምሳሌ 5፥10። 4) አጭር ነው፤ በዚያ ላይ ወጥመድ ነው!! "የጋለሞታ ዋጋ እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራም ሴት የሰውን ሕይወት ታጠምዳለች።" ምሳሌ 6፥26። 5) የዚህ ነገር መጨረሻው ፀፀት ነው!! "በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፋ ጊዜ ታለቅሳለህ" ምሳሌ 5፥11። *** እንደዚህ ካለው ... የእግዚአብሔር ቃል #ሽሽ ይላል!! መተሻሸት አይደለም፤ #መሸሽ!! ❝ከክፉ የጎልማሳነት #ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።❞ —2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22። ❝Flee also youthful lusts: but follow righteousness, faith, charity, peace, with them that call on the Lord out of a pure heart.❞ —2 Timothy 2:22 (KJV) የጎልማሳነትን #ምኞቱን መሸሽ እንጂ ማሰላሰል አያስፈልግም!! ፍቅር ያልሆነውን ፍቅር ለመቀበል ሰበብ ማብዛት ሳይሆን መሸሽ ያስፈልጋል!! አጥብቀን የምንከተለው ሕይወት አለ፤ እርሱም፦ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን እና ሰላምን!! በሰሎሞን ምሳሌዎች ...የእውነተኛውም ፍቅር ባሕርይ ተገልጿል፦ "ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤ ከጕብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ። እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።" ምሳሌ 5፥18-19። #የእውነተኛው #ፍቅር #ግብ ጋብቻ እና አብሮ ማርጀት ነው!! ውጤቱም ከላይ እንደተገለጸው፦ 1) ምንጩ የተባረከ፣ 2) ደስታው ፀፀት የሌለበት፣ 3) ናፍቆቱ 'ማይቋረጥ 4) እርካታ ቀጣይነት ያለው እና 5) ፍቅሩ የሚያጠግብ ነው!! "#ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር #በቅድስና ጠርቶናልና።" 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥4-8። በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

"ትቶ ይሄዳል" ተብሎ አያሰጋም!! "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም" መዝሙር 23፥¹ ይህ ማለት ዳዊት ከእግዚአብሔር ፈልጎ ያጣው ነገር አጥቷል። ይገርማል!! ለእኛም እግዚአብሔር ታማኝ እረኛችን ነው፤ ስለዚህ #የሚያስፈልገን ሁሉ አለን፤ አንዳችም አያጎድልብንም!! ዳዊት "በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን #አልፈራም" አለ። በእረኛችን ምን ያህል እንተማመናለን!? በአስቸጋሪ መንገዶች እንኳን ስናልፍ ለራሳችን ትቶን አይሄድም!! ተወዳጆች እግዚአብሔር ከእኛ ጋር አብሮን ይራመዳል!! አብሮነቱ ደግሞ የሚታመን ነው፤ "ትቶ ይሄዳል" ተብሎ አያሰጋም!! ዓለሙ ሁሉ እንኳን ቢቃወምህ ከአንተ ጎን ይቆማል!! በቃሉ ልብህን እያፀናና ደኅንነት እንዲሰማህ ያደርጋል!! ዛሬ ለእናንተ ምርጥ ግብዣ አለኝ፦ መዝሙር 23፥1-6 እባካችሁ ተጋበዙልኝ!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

የኢየሱስ ቃል #ሳትክድ ትዝ ይበልህ!? ❝ጴጥሮስም፦ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።❞ —ማቴዎስ 26፥75። ጴጥሮስ "ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም" አለ። ኢየሱስ፦ "እውነት እልሃለሁ፥ በዚች ሌሊት ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" አለው። ጴጥሮስ፦ "ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን፥ ከቶ አልክድህም" አለው። ከዚህ ቃለ መሀላ በኋላ ጴጥሮስ የወሰነው ሳይሆን ኢየሱስ ያለው ሆነ። "ሰውየውን አላውቀውም" ብሎ ሦስት ጊዜ ካደው። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ። 3 ጊዜ #ከካደ በኋላ ... "ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" ያለው #የኢየሱስ ቃል #ትዝ አለው፤ ወደ ውጭም ወጥቶ መራራ ልቅሶ አለቀሰ። (ማቴዎስ 26፥58-75)። ጴጥሮስ የኢየሱስ ቃል ትዝ ያለው ከካደ በኋላ ነው፤ ከዚያ አምርሮ አለቀሰ። የብዙዎቻችን የህይወት ዘይቤ እንደዚህ ነው። የኢየሱስ #ቃል ሳንወድቅ ትዝ ይበለን። አጥፍተን በፀፀት ከመሰቃየት #ሳናጠፋ የነገረን ቃል ትዝ ይበለን። ኃጢአት ከመሥራታችን በፊት #መቀደሳችን እና #መጽደቃችን ትዝ ካለን በማንነታችን ልክ ልቀን እንኖራለን። ጴጥሮስ ለምን ተሰናከለ? በራሱ ስለተማመነ፤ በራሳችን ሳይሆን በጌታ እና በኃይሉ ችሎት እንተማመን። ላለመውደቅ ዋስትናችን የእርሱ ጸጋ ነው። በእርሱ የሚታመኑ ሳይክዱ ቃሉ ትዝ ይላቸዋል!! የኢየሱስ ቃል ተጠላልፈን ከመውደቃችን በፊት ትዝ ይበለን!! ቦታዉ ላይ፤ ሰአቱ ላይ ቃሉ ትዝ ሲለን ደግሞ ለቃሉ ስንታዘዝ እንዴት ደስ ይላል!! በርናባስ ዘመነ
Show all...
"አንኳኩ" ያለው እያንኳኳ ነው፤ ለከፋቹ ክፈቱ!! ጌታ ኢየሱስ የተራራውን ስብከት ሲያስተምር፦ "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።" ብሏል። ማቴዎስ 7፥7-8። ለሎዶቅያ ቤተክርስቲያን የተጻፈውን ደብዳቤ ስናይ ደግሞ፦ ❝እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።❞ አለ። —ራእይ 3፥20። አንኳኩ ያለው ራሱ በደጅ ቆሞ እያንኳኳ ነው። ልቡን ለከፋቹ የሚከፍት "...በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ... ነጭ ልብስን፥ ... የሚኳለውን ኵል" ከእርሱ በነፃ ይገዛል። #መልሱ መልስ ልሁናችሁ እያለ ነው። #ሰጭው ስጦታ ሆኖ መጥቷል። ተፈላጊው ፈልጎን እያንኳኳ ነው። ሰጭው እጁን ዘርግቶ ተቀበሉኝ እያለ ነው። ያላንኳኳነው በር #ተከፍቶ ግቡ እያለን ነው። ውኃ ዝቅ ብሎ ያገኘውን ዝቅታ ወይም ባዶ ስፍራ እንደሚሞላ ሁሉ ኢየሱስም እንዲሁ የሰውን ጉድለት ሊሞላ ይፈልጋል። ባዶነት ሙላትን እየፈለገ ሳይሆን ሙላት ባዶውን እየፈለገ ነው። ነገሩ ተገላብጧል። አሁን የተራበ ሰው ምግብ እየፈለገ ሳይሆን ምግብ ራሱ (ኢየሱስ) የተራበውን ሰው እየፈለገው ነው። ያዘነ ሰው ደስታ እየፈለገ ሳይሆን ደስታ ራሱ (ኢየሱስ) ያዘነውን ሰው እየፈለገ ነው። ዕረፍት ተንከራታቹን ሰው እየፈለገው ነው። ኢየሱስ ሁሉንም ነገራችንን መልክ ማስያዝ ይፈልጋል!! ኢየሱስ ለሁሉም ነገር መፍትሔ መሆን ይችላል!! በረከት እየፈለጋችሁ ነው!! እባካችሁ ወደ ሕይወታችሁ ጋብዙት!! በወንድም በርናባስ ዘመነ https://t.me/tetelestaye
Show all...
ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!