cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

muaz jemal

@Muazjemal

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
498Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጠፉ ተማሪዎች ጉዳይ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፡፡ ልጆቹ የት ናቸው?
Show all...
የጠፉት ተማሪዎች ጉዳይ (ሙአዝ ጀማል) 1 "እነ ኧከሌ ጩሁ እንጂ" ሳንል ድምፃችንን ማሰማት እንችላለን፡፡ በተፈጠሩ ጉዳዮች ሁሉ የሆነን ጎራ ማጥቃት ማንንም አይጠቅምም፡፡ ፌሚኒስቶችን መዝለፍ ልጆቹን አይመልሳቸውም፡፡ 2 የልጆቹ ጉዳይ (ሴቶችም ወንዶችም አሉበት ስለተባለ) የት እንዳሉ ማወቅ አልተቻለም፡፡ መንግስት አስመልሻለሁ ያላቸውን ሰዎች ሳይረከብ መግለጫ ሰጥቶ ከሆነ (በርግጠኝነት ወደዛ ድምዳሜ እየመጣን ነው) ተዓማኒነቱን ያሳጣዋል፡፡ እዚህ አስቀያሚ ጨዋታ ውስጥ ግን እነማን ሊኖሩ ይችላሉ? : ➊ የጃልመሮ ሰራዊት(?) በአከባቢው ያሉ አማፂያን እነሱ ስለሆኑ.... ሰውዬው የፖለቲካ ብስለቱ እምብዛም ስለሆነ መደራደሪያ ሊያደርጋቸው አስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ➋ መንግስት ፦ የጃል መሮን ሰራዊት ለማስመታት ልጆቹን ራሱ ጋር አድርጎ (አግቶ) ውግያ ለመግጠም፡፡ (ይሄ ብዙ አያሳምንም፡፡ ቢያንስ አስፈትቻለሁ ካለ በኋላ ሊለቃቸው ፡፡ ይችል ነበር፡፡) ➌ ይሄ በጣም የደከመ ጥርጣሬ ነው፡፡ ቢሆንም አለመገመት ከባድ ነው፡፡ ከአጋቾች በኩል ምንም መግለጫ ሳይሰጥ ፤ ምንም አይነት ቪድዮና ፎቶ ሳይወጣ (እኔ በበኩሌ ያየሁት የለም) እንዴት ስማቸው ታወቀ ፣ ቤተሰባቸው ተገኘ ፣ ፎቷቸው ተለቀቀ? አመለጠች የተባለችው ልጅ ለBBC ቃሏን ሰጥታለች፡፡ እንዴት አገኟት? እንዴት አገኘቻቸው? የተናገረችው ዲፓርትመንት ግቢ ውስጥ የማይሰጥ መሆኑ ይሄንን ጨዋታ ሌላ ግሩፕ በማይገመት መልኩ እየተጫወቱት ነው ያስብላል፡፡ ------------ የሆነው ሆኖ ልጆቹ መለቀቅ አለባቸው፡፡ ከዚህ ጉዳይ ለማትረፍ እየተሯሯጡ ያሉ ወገኖችም ከዚህ ርካሽ ጉዳያቸው ቢታቀቡ ጥሩ ነው፡፡ በሚዲያ የደረሰንን መረጃ አንለቅም ሀገር ያፈርሳል ብሎ ለቤተሰብና ይሄንን ጉዳይ ለሚከታተል ሰው እያለቀሱ ማርዳት (ያላቸው መረጃ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ) ሀገር አያድንም፡፡መንግስትም ጥርት ያለ መግለጫ (ከይቅርታ ጋር ጨምሮ) መስጠት አለበት፡፡ ----- #ልጆቹ_የትናቸው? #Bring_back_our_student
Show all...
አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዛሬ ቅዳሜ 16/2012 ይህንን መስላ ወጥታለች፡፡
Show all...
ፍትህ ነገ ቅዳሜ ጥር 16/2012 ይህንን መስላ ትመጣለች፡፡
Show all...
ይሄንን ፋራ ህዝብ ምን አድርጌ ላሰልጥነው ቆይ?😪 - ገና የኖቬል ሽልማት ሲታወጅና አብያችን መመረጡን ስሰማ እንዲህ ብዬ ነበር፡፡ትራምፕ ሲነግርህ ባረቀብህ እንጂ🤷‍♂️ "ከዓለም አንፃር ስትታይ ከጥፍር ቆሻሻ በላይ ተፅዕኖ ማትፈጥረው ሀገር መሪ የኖቬል ሽልማትን መቀበሉ እንዲሁ ይከነክነኛል" ሙሉውን ኮሜንት ላይ ሊንኩ አለ፡፡ ፡ በደንብ ላብራራልህ? : - እኛ እንደ ሀገር የምንኖረው አሜሪካና ሌሎች ሀያሎች ስለፈቀዱልን ነው፡፡ - ፖለቲካችንን እኛ አንመራውም ፤ መሪዎቹም ለመምራት አስበው አያውቁም፡፡ በነጮቹ እጅ ነው፡፡ - ምርጫውን ከፈለጉት ይከናወናል ፤ ካልፈለጉት ያራዝሙታል፡፡ አብጠህ ብትፈነዳ ምንም አታመጣም፡፡ - ዲሞክራሲህን አፈርፍረህ ብላው፡፡ ቅድሚያ ጥቅማቸውን ነው ሚያሰሉት፡፡ አንተ የኔ ፉዞ መጠቀሚያ ነህ፡፡ የሚተነፍስ ሮቦታቸው ነህ፡፡ ህይወቴን ለብሔሬ ገብራለሁ በል፡፡ ካልፈለጉት ራስህን እንኳን ማጥፋት እንዳትችል ያደረጉሀል፡፡ መጥፋትህ ካማራቸው ፤ ሊቢያን ተመልከታት፡፡ - ከሶሪያ በላይ ታሪክ አለን አትለኝም መቼስ፡፡ - በማታውቀው ፖለቲካ ጦስ ከምትሆን ፤ ጦሴን ጥንቡሳሴን ብለህ ስራህን ወጥር፡፡ - ስራ ፍጠር ፤ ተማር ፤ አንብብ ፤ ነቃ በል፡፡ ጃዋር እንጀራ አይገዛልህም፡፡ አብን ግራ እንደገባት አይተሀል መቼስ፡፡ ህውሀትዬ አመዷ ቡን ብሏል፡፡ ብሔርህ እከካም ነው፡፡ ሀገሪቷ ራሱ እከክ ነች፡፡ ችጋራም ሀገር ላይ ወጥሮ መስራት እንጂ ከረቫት እያነቁ በየመድረኩ የተሰለቸ ዲስኩር ማቅረብ ለታዬ ቦጋለ መፅሀፍ ማተሚያ ብቻ ነው የተረፈው፡፡ ፡ አሪፍ አርብ አመሻሽ♥
Show all...
Re እኔ ፣ እኔ የምወደው ሰው ና የማይመቸኝ ባህሪ ------ አራዳ ሲባል ትዝ የሚለኝ ፈገግታዬ ነው፡፡ ዘናጭ ፈገግታ ነው ያለኝ፡፡ (እንደዛ ይመስለኛል) አራዳ ነኝ፡፡ ተንኮል አላሳብብህም፡፡ ከተጋጨኸኝ ግን አልሰማህም...ጥፋትህ እስኪገባህ ድረስ ፍዳህን አበላሀለው፡፡ ሼም ከያዘህ በይቅርታ እፋታለሁ፡፡ ፀዴ ከሆንክ አንጋጭም፡፡ ካነበብክ አለቃዬ ነህ...ፊልም ትወደዳለህ...ሻለቃ ብዬሀለው...ግጥም ከፃፍክ ነግሰሀል,..ይሄ ሁሉ ባይሆንም ቀልድ ከገባህ ጀለስ ነን፡፡ ይመችህ ካካበድክ እፋታሀለው፡፡ ሾካካ ነህ?...ትቀፈኛለህ፡፡ በኔ ፊት ማንንም እንዳታማ,,,ሰንፍ ከሆንክ አለቀልህ...ታዛቢ ከሆንክ ከነትዝብትህ ገደል ግባ...ፈሪ አይመቸኝም...አጉል ደፋር ያስጠላኛል...ጉረኛ ሳቄን ነው ሚያመጣው...አንተ ራስህን ስትሆን ደስ ትለኛለህ፡፡ ያኔ እልልል ያልን ወዳጆች እንሆናለን፡፡ እኔ ደስ የሚለኝ እንዲህ አይነቱ ሰው ነው፡፡ እናንተስ እንዴት ያለ ሰው ይደብራቹሀል? እንዴት ያለ ሰው ይመቻቹሀል? አውሩኝ እስኪ...
Show all...
Muaz: welcome 👍 የታባህ ጠፍተህ መጣህ?😡 ማን ልበል?😂 👍😂😡
Show all...
👍 9
😂 10
😡 10
ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት እስከ ዝምታ (እኔ ሙአዝ ነኝ!) ፡ ይሄ ዘመን እውነት የመባል አንድ ነገር የለም ብሎ ያምናል፡፡ እውነትህን አንተ ነው ምትሰራው፡፡ ስለሌሎች ግድ የለም፡፡ ብቻ እኔ ያመንኩት ነው ሀቅ፡፡ የናንተው የበሬ ወለደ ታሪክ ነው የማለት መብትን ያጎናፅፋል፡፡ ምክንያቱስ? ሁላችንም የየግላችን ሚዲያ አለን፡፡ ፡ ታዲያ በዚህ ጊዜ ፤ የትኛው እውነት እንደሆነ በማይታወቅበት ዘመን አንድ ርዕስ ላይ የሙጥኝ ብለን ፤ ጅማታችን እስኪበጠስ የምንከራከርለት ጉዳይ ይኑር አይኑር ፤ ይፈፀም አይፈጸም ፤ ልክ ይሁን ስህተት ማረጋገጥ አንችልም፡፡ ምክንያቱም አንድ እውነት የለም! : መረጃ ማዛባትና የሀሰት ዜናዎች ለዚህ እውነታ ጥሩ ግብአቶች ሲሆኑ ፤ የጥላቻ ንግግርና አግላይ ገለፃዎች ደግሞ እሳቱ ላይ ቤንዚን አርከፍካፊዎች ናቸው፡፡ ለዚህ መፍትሄው ምንድነ ነው የሚለው ላይ እናንተ አዋቂዎች ናችሁና የምትሉትን በሉ፡፡ እኔ ግን ጊዜያዊ መፍትሄ አለኝ፡፡ ፡ የዝምታ መብት! ፡ ይሄ በብዙዎቻችን የተዘነጋ ፤ "በበላዮቻችን" የተነጠቅነው መብት ነው፡፡ ያለመናገር መብት እንዳለን የረሳን ብዙ ሰዎች አለን፡፡ በተለይ የኛ ዝምታ እየተንበለበለ ያለውን እሳት ፤ የሚንቀለቀለውን ጥፋት የማብረድ ሀይል እንዳለው ሲገባን፡ከመብቶቻችን ሁሉ ትሉቁን መብት እንደተነጠቅን ይገባናል፡፡ (ያው አነጣጠቃቸው systematic ነዋ ፤ መቼስ "ዝም አትበል ብሎ የከለከለኝ የለም" የሚል ተሟጋች አይጠፋምና) ፡ ሁላችንም ሀሳብ የመግለፅ ነፃነት አለን፡፡ ይሄ ሰብአዊ መብት ላይ የሰፈረ የመብት አካል ነው፡፡ እንደው መብት ተገኘ ተብሎ ግን ያንንም ይሄንንም ማንቦራጨቅ ምንጩን ማደፍረስ ነው፡፡ ነገ ጠዋት ሁላችንም ውሀ የምናገኝባትን ምንጭ አንቦራጭቀን ካደፈረስናት ተጠምተን በድርቅ ማለቃችን ነው፡፡ ለአንዳንዶች መፍትሄው መጮህ ነው፡፡ ለእኔ ደግሞ መፍትሄው ዝምታ ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ዘመን የትኛው ነው እውነት ብሎ መልስ የሚያገኝ አካል የለም፡፡ ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት እስከ ዝምታ!!!
Show all...
ደግሞ መጥተናል😜
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!