cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ድንግል ዘ Orthodox > 👑

ሰላም የዚህ ቻናል / Channel / አባላት ፦ የእግዚአብሄር ሰላም የ እናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅረ እረድኤት ከሁላችን ጋ ይሁን ! ዕያልን ፦ ለዚህ ቻናል አባላት ለሆናችሁ እና መሆን ለምትፈልጉ ሁልጊዜም ቢሆን በራችን ክፍት ነው ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
186Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እንጦጦ ማርያም ከዋና ከተማዋ አዲሰ አበባ በስተ ሰሜን ምስራቅ ፯.፰(7.8) ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የተቆረቆረችው ፲፰፻፸፯(1877) ዓ.ም በዳግማዊ ምኒልክ ነው፡፡ አፄ ምኒልክ በ ፲፰፻፸፯(1877) መቃኞውን አስመርቀው ከሶስት ዓመት በኃላ ደግሞ በ ፲፰፻፸፱(1879) ሁለተኛውን ቤተክርስቲያን አስመረቁ፡፡ ይህ አሁን የምናየው ግሩም ህንፃ ቤተክርስቲያን የታነጸው ግን በንግስት ዘውዲቱ በ ፲፱፻፲፫(1913) ዓ.ም የተመረቀ ነው፡፡ የሕንፃዎቹ ግንባታ ከአዲስ አበባ ከተማ አመሰራረትና በአጠቃላይም ከዘመናዊ የከተማ ባህል ዕድገት ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ አፄ ምኒልክ ከአንኮበር ወደ እንጦጦ ተጉዘው ዋና ከተማውን ከቆረቆሩ በኃላ ለተወሰኑ ዓመታት ስፍራው የባህል የኢኮኖሚ፣የፖለቲካና የሃይማኖት ማዕከል ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የእንጦጦ ማርያም ጽላት ንጉስ ተክለሐይማኖት በአምባበ ጦርነት ሲሸነፉ ከጎጃም በምርኮ የመጣች መሆኗ ይነገራል፡፡ በምርኮ የተገኘችው ይህች ጽላት በመቃኞ ለአመታት ቆይታለች፡፡ መቃኞዋም ክብ የጣሪያ ቅርጽ ያላት አነስተኛ ቆርቆሮ ቤት ሆና ከደውል ቤቱ ፊት ለፊት ትገኛለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ለዐቃቢቶች መኖሪያ ቤት በመሆን ታገለግላለች፡፡ እቴጌ ጣይቱ ከጎንደር በመጡ ዘጠኝ አናጢዎች የቤተክርስቲያኑን ግንባታ ያስጀምሩታል፡፡ ሥራውም በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ በ ፭፼፫፻፺፭(5395) የቀንድ ከብቶች ታርደው በታላቅ ድግስ ታቦትዋ "እንጦጦ ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ማርያም " በመባል በ ፲፰፻፸፱(1879) ዓ.ም ነግሳለች፡፡ በ ፲፰፻፹፪(1982) ዓ.ም አፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ለመባል የበቁትም በዚችው በእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ነበር፡፡ በ ፲፰፻፺፩(1891) ዓ.ም እቴጌ ጣይቱ ዘመናዊ የሕንጻ ሠራተኞችን ከአውሮፓ አስመጥተው ቤተክርስቲያኗን ያሳደሷት ሲሆን በ ፲፱፻፲፫(1913) ዓ.ም የሕንጻውን ግድግዳ በግንብና ጣርያውን በቆርቆሮ የቀየሩት ግን ንግሥት ዘውዲቱ ናቸው፡፡ ከአፄ ምኒልክ ሕልፈት በኃላ በተነሳው የፖለቲካ ውዝግብ ምክንያት እቴጌ ጣይቱ በዝችው ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በቁም እስር ቆይተው በ ፲፱፻፲(1910) ዓ.ም አርፈዋል፡፡ የቤተክርስቲያኗ የውስጥ ግድግዳ በዘመኑ የኢትዮጵያ የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች በአለቃ ሕሩይና በዕምዓዕላፍ ድንቅ ሥዕሎች የተዋቡ ናቸው፡፡ እንዲሁም የሕንፃው ጣራ ዲዛይንና ውቅር በጣም ማራኪ ነው፡፡በ ፲፱፻፳፰(1928) ዓ.ም አገራችንን ጠላት በወረረበት ወቅት ሕንፃው ምንም ዓይነት አደጋ አልገጠመውም፡፡ ጽላቱም በቀሳውስቱ በመሠወሩ በወራሪው ኃይል እጅ አልወደቀም፡፡ ከቤተክርስቲያኗ በስተጀርባ በመቶ ሜትር ርቀት ላይ የአፄ ምኒልክ የግብር አዳራሽ ይገኛል፡፡ የአዳራሹ የውስጥ ክፍል ለግብር የተዘጋጀ ምግብ መቆያ የነበረና ለየት ያለ ሲሆን የተለያዩ የማዕድ ቤት ዕቃዎችን ለማንጠልጠል እንዲያስችሉ በግድግዳው ላይ የተቸነከሩ ቀንዶች ይታያሉ፡፡ ለንጉሡ ማረፊያ ለየት ያለ ክፍልም አለው፡፡ ሕንጻው በጭቃና በድንጋይ የተገነባና ውፍረቱ እጅግ ቢያንስ ፹ ሳ.ሜ እንደሆነ ይገመታል፡፡ በአቅራቢያው በግምት ከሰባ ካሬ ስኩየር ሜትር ስፋት ላይ በእንቁላል ቅርጽ በጭቃና በድንጋይ የተገነባና ምድር ቤት ያለው የአፄ ምኒልክ እልፍኝ ይገኛል፡፡ የእልፍኙ ጣሪያ በጥርብ የጥድ እንጨት የተዋቀረና እንደ አዳራሹ ሁሉ በጠፍር የተማገረ ሲሆን ተመልካችን የሚማርክ ውበት አለው፡፡ ወደ እልፍኙ የሚያስገባ እና ከሕንጻው ውጫዊ ግድግዳ ጋር የተያያዘ ደረጃም ተዘጋጅቶለታል፡፡ በሰሜንና በደቡብ በኩልም ተካፋች መስኮቶች አሉት፡፡ በሁለቱም አቅጣጫ ማራኪ የመልክአ ምድር አቀማመጥንና ከፊል የአዲስ አበባን ከተማ ለመቃኘት ይቻላል፡፡ በዚሁ አከባቢ ንጉሡ ከቤተክርስቲያን መልስም ዛቲ ይቀምሱበት የነበረና ሸራ ቤት በመባል ይታወቅ የነበረው ቤት ይገኛል፡፡ ሸራ ቤት የተባለውም ጣራው በሸራ ተሸፍኖ የነበረ በመሆኑ እንደነበር ይገመታል፡፡እቴጌ ጣይቱ በ ፲፱፻፲(1910) ዓ.ም እንዳረፉ አስክሬናቸው በዚሁ በሸራው ቤት ውስጥ ቆይቶ በንግስት ዘውዲቱ አማካኝነት ወደ ባዕታ ቤተክርስቲያን ምድር ቤት ተዛውሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ታሪካዊ ቤቶች በቤተክርስቲያኑ አገልግሎት ለተሰማሩ መነኮሳት በመኖሪያነት ያገለግላሉ፡፡ በእንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን መግቢያ በር አጠገብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሙዝየም አለ፡፡ ሙዝየሙ በወቅቱ የነበሩ ነገስታት የተገለገሉባቸው የንግሥ ልብሶችና፣ዘውዶችን፣ባለወርቅ ፈርጥ ዣንጥላ፣ኮርቻ አፄ ምኒልክ ከአንኮበር ጀምረው ይገለገሉበት የነበረ የጠፍር አልጋና ከንጉሡና ከንግሥቲቱ ለቤተክርስቲያኑ የተበረከቱትን በርካታ ዕቃዎች ያካትታል፡፡ አፄ ምኒልክ በ ፲፱፻፸(1970)ዓ.ም አስደጉሰው የሰጡት ያሬዳዊ መጽሐፍ የንግሥቲቱ ደንገጡሮች ከአክርማ ያዘጋጁት ውበት የተላበሰ ባለፈርጥ መሶበ ወርቅ፣፻፳፩ ዓመት እድሜ ያስቆጠረ ከአንድ ወጥ እንጨት የተሰራ መስቀል፣ ፻፰(108) ዓመት ያለው የእመቤታችን ስዕል፣ በ ፲፰፻፹፫(1883) ዓ.ም በኢጣሊያ መንግስት የተበረከተ የድንግል ማርያም ቅርጽ፣ለቀሳውስት ጥምጣም ማስተካከያ በእቴጌ ጣይቱ የተበረከተ ያማረ መስታወት፣በጀርመን አገር የተሰራ እንዚራ(አኮርድዮን) የንግስቲቱ ካባ ከሶሪያና ከፋርስ የመጡ የሐር ምንጣፎች የንጉሡ ጋሻና ጦር በወርቅ የተጠስፈ ሆኖ ንጉሡ ወደ አድዋ ሲዘምቱ የያዙትና ከራስጌ የእመቤታችን ከግርጌ ግራና ቀኝ የጣይቱና የምኒልክ እንዲሁም በመሐል የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስል የሚታይበት አርማ በአድዋ ጦርነት ለዘመቻ ጥሪ የተገለገሉበት ነጋሪት እና ሌሎችም ማራኪ ዕቃዎች በሙዝየሙ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በ ፲፫፻፰፭ ዓ.ም በአፄ ዳዊት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የመጣውና ዛሬ በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በክብር ተቀምጦ ያለው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ እጁ ያረፈበት ግማደ መስቀል ከመናገሻ ቀጥሎ በእንጦጦ ተራራ ላይ ማረፉንም አንዳንድ ጽሑፋዊ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሌላው ደግሞ በእንጦጦ መንበር ፀሐይ ጥንትም የነበረ ነገር ግን ግዜውን ጠብቆ ሕሙማንን በመፈወስ ላይ የሚገኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ጸበልም ይገኛል፡፡ ጸበሉ ከቤተክርስቲያኒቷ ራቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በእግር ከ ፲፭-፳ ደቂቃ ያህል ይወስዳል፡፡ የእንጦጦ መንበረ ፀሐይን ጉብኝጣችንን አበቃን፡፡ የምክር ስንቅ ህይወትህ ትርጉም እንዲኖራት ዓላማ ይኑርህ፡፡ የአንተነትህ ትልቁ ምእራፍ ደግሞ ከዕውቀትህ በላይ ስራህ መሆኑን አትርሳ፡፡ የያዝከው ነገር በቂ መስሎ ካልታየህ ድፍን ዓለምን ብትጨብጥ እንኳን ሃዘንተኛ እንጂ ደስተኛ አይደለህም እናም ባለህ ነገር ፈጣሪህን እግዚአብሔርን አመስግነው፡፡ የውድቀት መጀመሪያ እራስን ዐዋቂና ብቸኛ አድርጎ ማሰብ ነው ፍጻሜ እንዲኖርህ እራስህን አታመጻድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመታረም ፈቃደኛ ሁን ጥፋትህን አሜን ብሎ መቀበል ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሰልህ ጠቢብ ሰው እንኳን ከራሱ ስህተት ከሰው ስህተት ተምሮ ራሱን ይጠብቃል፡፡ በክርስትና ህይወት ውስጥ አንዱ ሲታወር አንዱ መሪ መሆን አለበት ህይወት በመደጋገፍ የተሞላች ናትና ወንድምህን ለመርዳት ወደኃላ አትበል የአንተ እጅ ለቸገረው ሲዘረጋ የአምላክ ደግሞ ወደ አንተ ይሆናል፡፡ አንተ እግዚአብሄር ግን
Show all...
የማይቻል ነው ትላለህ ............... አንተ ብታምን በእኔ ዘንድ የማይቻል ነገር የለም ይልሀል ሉቃ 18፤27 ደክሜያለሁ ትላለህ .................... ዕረፍት እሰጥሀለሁ ይልሃል ማቴ 11፤28-30 ማንም የሚወደኝ የለም ትላለህ .... እኔ እወድሃለሁ ይልሀል ዮሐ 3፤11 መቀጠል አልችልም ትላለህ .......... እርምጃዎችህን ሁሉ እኔ መራሃለሁ ይልሀል ምሳ 3፤5-6 ፈሪ ነኝ ትላለህ ............................ የፍርሃትን መንፈስ አልሰጠሁህም ይልሀል 2ኛ ጢሞ 1፤7 ሁል ጊዜ እጨነቃለሁ ትላለህ ....... ጭንቀትህን ሁሉ በእኔ ጣለው ይልሀል 1ኛ ጴጥ 5፤7
Show all...
​​​​ቅድስት ሥላሴ ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው? ◉ አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም። ◉ አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ። ◉ አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ። ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል። ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን። ◉ አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ። ◎ አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም። ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ። ◎ ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት እንላቸዋለን። ◉ አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ ። ወስብሀት........
Show all...
ማየት ፡ ማወቅ እና መውደድ ኢትዮጵያ የመድኀኒ አለምን የማዳን ሰራ ሰለ ሰው ሲል የደረሰበትን መከራ፡ በጃንደረባው መልክተኛዋ አማካኝነት ገና መጽሀፍ ቅዱስ ተጽፎ ሳይጠናቀቅ ማንበብ የጀመረችና መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጭ ብላ መጽሀፍ ቅዱስን ስታነብ የተገኘች ሀገር ናት፡፡ የእቴጌ ህንደኬ አዛዥ ጃንደረባው ባኮስ"ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ "የተባለውን መድኀኒ አለምን ያወቀው ኢየሩሳሌም ተጉዞ ነበር፡፡በመንገዱም ላይ እያነበበ የነበረው የነብዩ ኢሳይያስን ትንቢት "እንደበግ ወደ መታረድ ተነዳ፡............"የሚለውን ሰለ ክርስቶስ የዕለተ አርብ ስቃይ የተነገረ ትንቢት ነበረ፡፡ከዚህም የምንረዳው ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ነገረ ሕማማቱን ሲያነቡ፡የክርስቶስን መከራ ሲያሰላስሉ የኖሩ መሆናቸውን ነወ፡፡ ዐቢይ ጾሙን ሙሉ በቅዱስ ያሬድ አማካኝነት ለየሳምታቱ ስም የሰጠችውና የጾሙን ወራት በስብሀተ ነግህ፡በቅዳሴና በተመስጦ ስርአተ አምልኮ የምታሳልፈው ቤ/ክ ናችን ከሆሳዕና ሳምታት በኋላ ግን ሕማሙን የምታስተምርበት መንገድ ከፍ ይላል፡፡ ሳምንቱን በጥልቅ ሀዘንና ተመስጦ ሆና ታሳልፋለች፡፡ልጆቿን ሰብስባ ከጾም ጋር እየሰገደች በቤተ መቅደስ የምታነበው ንባብ ፡የምታዜመው ዜማ ፡የምትፈፅመው ስርዓት ከሚሊየኖች የሚበልጥ ስብከት ነው፡፡ይህንን መረዳት ያልቻለ ሰው ቤ/ክ "ጌታን አታውቅም "ብሎ ይነቅፋል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ብሏል፡"ሃሌ ሉያ ወደ ሮም በወረድሁ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን አየኋት ፡አወቅኀት፡ወደድኳት "ብሏል፡፡ አንድ ሰው ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚኖረው ግንኙነት ሊቁ በሶስት ከፍሎታል፡፡ ማየት ፡ ማወቅና ፡ መውደድ፡፡ ብዙዎች የኦ/ተ/ቤ/ክንን አይተናታል ይላሉ፡፡ ግን አያውቋትም፡፡ወሳኙ ሂደት ግን ቤተ ክርስቲያንን ማወቅ ነው; የትርጓሜዋን ስልት፡የዜማዋን ውበት፡የተመስጦዋን ጥልቀት፡የቅዱሳኗን ህይወት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለሚያውቃት ግን እንኳንስ ቤ/ክያኗ መገልገያዎቿ (የጌታ ግርፋቱን በከበሮዋ፡መስቀል መሸከሙን በመቋሚያዋ፡የሾህ አክሊል መድፋቱን በካህናቶቿ ጥምጣም) ትሰብካለች፡፡ ምንጭ፡-ሕማማት ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ
Show all...
♥ ዳግመኛም ከሰሌን ዝንጣፊ ጋር ተመሳሳይ ተምር ይዘዋል ይኽም ተምር ልዑል ነው አንተም ልዑለ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ፍሬው አንድ እንደኾነ አንተም ዋሕደ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፡፡ በእሾኽ የተከበበ ነው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡ ♥ የዘይት ዛፍ ነው ቢሉ ዘይት ጽኑዕ እንደኾነ ጽኑዐ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ብሩህ ነው ብሩሀ ባሕርይ ነኽ በትምህርትኽም የሰውን ልቡናን ታበራለኽ ሲሉ፤ ዘይት መሥዋዕት እንደሚኾን መሥዋዕት ትኾናለኽ ሲሉ ነበር፡፡ ♥ “የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር” በማለት በአርያም መድኀኒት እንደኾነና እግዚአብሔር አብ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ መስክሮለት የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል መኾኑን ኹሉም መሰከሩለት፡፡ ♥ በእጅጉ የሚደንቀው የ40 ቀን የ80 ቀን ሕጻናት የፈጠራቸው ጌታ በአህያና በውርንጫ ተቀምጦ ባዩት ጊዜ በንጹሕ አንደበታቸው አንደታቸው ረቶላቸው ጌታን ዘንባባ በመያዝ ሲያመሰግኑ በእጅጉ ይደንቅ ነበር፤ ነገር ግን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት፤ ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? በማለት በሕጻናት እንደሚመሰገን የነርሱም ጌታ መኾኑን ከዳዊት መዝሙር በመጥቀስ ነገራቸው፡፡ ♥ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰለዚኽ ምስጢር ሲገልጸው ፡- “ፍቅርኽ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደኽ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደደክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠኽ ክብርኽን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጫላይቱ ላይ ተቀምጠኽ ወደ ሰማይ ሰራዊት መኼድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ያመሰግኑኻል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልኻል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድኽን ያነጥፉልኻል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትኽ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድኽን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲኾን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ ርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከ መኾን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” በማለት አስተምሯል፡፡ ♥ የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ሕፃናትን ጨምሮ ዘንባባ ሰሌን በያዙት ኹሉ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትን ታላቁን በዓል ከኹሉም ዓለም አስበልጣ በታላቅ ክብር የምታከብርና የምታስተምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ♥ ይኸውም ታላቁ የምስጋና ዕለት ሊደርስ ሲቃረብ ስንዱዋ እመቤት አስቀድማ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቊርባን ምስጋና፦ ✍ “ቦአ ኀቤሃ እግዚአ አጋዕዝት ወመናፍስት እንዘ ይጼዐን ዕዋለ አድግ ትሑት…” (የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ ርሷ ገባ፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነኽ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ኹሉ ጌትነቱን አሳየ፤ የሆሳዕናን ዑደት ለነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፤ ቡርክ ርሱ በታላቅ ቃል እየጮኻችኊ ሆሣዕና በአርያም በሉ አላቸው፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ከዚኽ አስቀድሞ ያልተደረገ ከዚኽም በኋላ የማይደረግ ተአምራትንና መንክራትን አሳየ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም... ) በማለት መድኀኒትነቱን ስትሰብክ፤ ካህናትና ምእመናንም በአንድ ድምፅ በዚያ ዘመን የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሰገነበት በዚኽ ልዩ ምስጋና “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ በመዘመር፤ ፈጣሪያቸው ክርስቶስን ያመሰግናሉ። 💥 ከዚያም በዋዜማው፦ ✍ “በዕምርት ዕለት በዓልነ ንፉሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ሆሣዕና በአርያም ቡሩክ አንተ ንጉሠ እስራኤል” 👉 (በታወቀች በበዓላችን ዕለት በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በመቅደሴ ተራራም ስበኩ ይኽቺ ዕለት የእግዚአብሔር በዓል ናት፤ በአርያም መድኀኒት የተባልኽ የእስራኤል ንጉሥ አንተ ቡሩክ (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የምታርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታድል) ነኽ) በማለት ልዩ ምስጋናዋን ጀምራ እስከ ሌሊቱ ድረስ በልዩ ምስጋና እየሰበከችው በኋላም ቤተ መቅደሱን በውርጫዋ ተቀምጦ እንደዞረ በአራቱ መኣዝን የጌትነቱ ወንጌል እየተነበበ፤ ካህናቱን ምእመናንም በእጃቸው የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘው “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ያመሰግኑታል፡፡ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ☘🍀መልካም በዓል ☘☘
Show all...
በዓለ ሆሣዕና በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ♥ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ክንፋቸው ትእምርተ መስቀል የሚሠራው ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸከሙት ጌታ በትሕትና ኾኖ ጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ባለባት በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ ♥ ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡ ♥ ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡ ♥ በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡ ❤ በልደቱ ማንም ያልገባባት የማይገባባት የሕዝቅኤል የታተመች መቅደስ የተባለች ዘላለማዊት ድንግል እመቤታችንን እንደመረጠ ዛሬም በሆሣዕና ማንም ሰው ያልተቀመጠባት አህያን ከውርንጫዋ ጋር እንዲያመጡ አዘዘ። ♦ ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና። ♥ ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡” ይላል። ♥ ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑን ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል። ♥ አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ። ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ በማለት መተርጉማን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም ልብስ በልጅነት ይመሰላልና የተገፈፍነውን የጸጋ ልብሳችን (ልጅነትን) ትመልስልናለህ ሲሉ ነው፨ ♥ ቅዱስ ኤፍሬም ይኽነን ሲተረጉም "ልብሳቸውን አውልቀው ያነጠፉለት ሰዎች አሮጌውን ማንነታቸውን ትተው ዐዲሱን ልብስ ክርስቶስን መልበሳቸውን ያስረዳል። ሐዋርያ ጳውሎስ “አሮጌውን ሰውነት አስወግዳችሁ አዲሱን ሰው ልበሱት” እንዳለው (ኤፌ.4፣23) ይኸውም ጥምቀት ነው" ይላል። ♥ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡ ♥ ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ። በተጨማሪም መተርጉማን እንዳመሰጠሩት በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡ ♥ በተጨማሪም አህያ ሲፈጥራት በጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ያላት ናትና ትእምርተ መስቀል ያለባት እእርሷ እንድትፈታ ማዘዙ ከ5 ቀን በኋላ በመስቀል ተሰቅሎ በሲኦል የታሠሩትን የሰው ልጆችን ነጻ ሊያወጣ መጥቷልና አህያን መርጧታል፨ ♥ ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት አመስጥሯል፡፡ ♥ ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው (መዝ.49፡12)፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደ አህያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጿል፡፡ ♥ ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነበር። እንስሳዋ እንኳን ጌታ ቢቀመጥባት እንዲህ ክብር ያገኘች ከሆነ ያደረባቸው ቅዱሳንማ የሚገባቸው ክብር ምን ያህል ይሆን? ይልቁኑ 9 ወር ከ5 ቀናት በማሕፀኗ የተሸከመችው ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የሆነውን አምላክ የወለደችው የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርማ እጅጉን ታላቅ ነው። ❤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
Show all...
♦♦ ዓይን♦ ዓይን የሰውነት ሕዋሳት ሁሉ መሪያቸው ከአሰቡት የሚያደርሳቸው ከመከራ የሚሠውራቸው ከውድቀት የሚጠብቃቸው ነውራቸውን የሚያነጻላቸው ተድላ ደስታን የሚመግባቸው ከኃጢአት የሚነጹበት እሾሁን አሜከላውን የሚያልፋበት ወግቷቸውም እንደሆነ ነቅለው የሚጥሉበት ገደሉን እንቅፋቱን የሚያልፉበት በቀና መንገድ የሚመላለሱበት ውበትን የሚያደንቁበት ምሥጢረ ሰማይ ወምድርን የሚማሩበት የሰውነት ፋታውራሪ አበጋዝ ነው።ጌታም ለዚህ ነው" ማኅቶቱ ለሥጋከ ዓይንከ ውእቱ= የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ነው" ማለቱ። ለመሆኑ ዓይን በመጽሐፍ መንፈሳዊ ትርጉሙ ምንድን ነው? ሀ. እግዚአብሔር ዓይናችን ነው። በዓይን ሁሉን ማየት ይቻላል። በራስ ዓይን ግን መልሶ የራስን ዓይን ማየት ግን አይቻልም። በእግዚአብሔር ሁሉን እንመረምር ዘንድ ተሰጥቶናል። እርሱን መመርመር ግን አንችልም። አባቶቻችን በማክሰኞ የማለዳ ጸሎታቸው ላይ" ትሬኢ ወኢታስተርኢ =ታያለህ ግን አትታይም" እያሉ የሚዘምሩለት ለዚህ ነው። እግዚአብሔር የምናይበት እንጅ የማናየው ስለሆነ ራሱ እንዲታየን ካልሆነ እርሱን ማየት አይሆንልንም። ለዚህ ነው በቅዱስ መጽሐፍ አብርሃም እግዚአብሔርን አየው ከማለት ይልቅ " የክብር ባለቤት እግዚአብሔር ለአብርሃም ታየ" ተብሎ የተጻው።ሐሥ፯፥፪ አብርሃም መሻት ነበረው።እግዚአብሔርን ለመሻቱ የሚያበቃውን ሁሉንም ያደረገ ቆራጥ የሃይማኖት ንሥር ነው። እግዚአብሔርም ወደ ሰማያት አብርሃምን አላወጣውም እርሱ ወደ ድንኳኑ ወረደ እንጅ። አብርሃም የራሱ በሆነች በለመዳት ማየት በሚችልባት ድንኳኑ እግዚአብሔር ለአብርሃም ወደ መታየት መጣ። ይህ ምሥጢር ምንድን ነው? ፍጡር እግዚአብሔርን ማየት አልቻለም። ባሕርይውን ማየት አይችልምና። ፈጣሪ ወደመታየት ካልመጣ ፍጡር ፈጣሪውን ሊያይ አይችልምና። ስለሆነም እግዚአብሔር በመላእክት ባሕርይ ሳይገለጥ ወይም ባሕርያችን ወደ መላእክት ሳይለውጥ ማየት በሚቻለን በእኛው ሥጋ በእውነተኛይቱ የአብርሃም ድንኳን በድንግል ማርያም ተገለጠ። ከእርስዋም ይወለድ ዘንድ እናቱን ወደ ሰማያት ወስዶ በመንበረ ክብሩ እንድትወልደው አላደረገም ይላል አባ ጊዮርጊስ። አንደዚያ ቢሆን ኖሮ ለእርሱ ወይም ለእናቱ ብቻ ተድላ ደስታ በሆነ ነበር እንጅ ለሁላችን ባልሆነ ነበር። እኛም የራበንን አምላክ ማየት ባልተቻለን ነበር። ሰብአ ሰገልስ የት ሄደው አምኃ ያቀርቡ ነበር? እረኞችስ የት ይዘምሩ ነበር? የእግዚአብሔር ክብርስ የት ይገለጥ ነበር? ከመላእክት ጋርስ የት አንድ እንሆን ነበር? ልማዱ ቸርነት የሆነ እርሱ ግን እናቱን ወደ ሰማይ ወስዶ ሳይወለድ ምድሩን ሰማይ ያደርግልን ዘንድ ወደ ምድር ወርዶ ተወለደ። በእኛው ሜዳ ተወልዷልና ተጉዘው ደርሰው አገኙት። በእኛው ሥጋ ተወልዷልና በእኛው ዓይን አየነው። በእኛው ሥጋ ተገልጧልና በምድራዊ እጅ ተዳሠሠ። የሚበረድ ሥጋንለብሷልና በጨርቅ ተጠቀለለ። ምድራዊ ሥጋን ለብሶ መገለጥን ወዷልና ሊያዩት የመጡትን በመብረቀ ክብሩ አላስደነገጣቸውም። በአቅማችን እናየው ዘንድ በአቅመ ሰብእ ተወልዷልና በዚያ ንውጽውጽታን ነጎድጓድን መባርቅትን አላደረገም። ፍጥረት ሁሉ አይታ አትጠግበውምና ወደ ፍጥረት ባሕርይ ዝቅ ብሎ ታየ። ቃለ አብ በሰው መጠን ሲታይ የእኛ ሥጋ ደግሞ ሥዋሬ መለኮትን ገንዘብ አድርጎ በቃል ገንዘብ መብረቀ ስብሐት ሆነ። የቤተክርስቲያን መብራት እስጢፋኖስ " የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ቀሞ አየሁት" ማለቱ ቀኝ ሥልጣን ነው። ቃል በሥጋ መታየቱን እና ሥጋ የግሞ በሥልጣነ አብ ጸንቶ አየሁት ማለቱ ነው።የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ርትዕት ናት የምንለው የእኛ ስለሆነች አይደለም። እግዚአብሔር ራሱ ካልሆነ በቀር ፍጥረት እርሱን ማየት የሚችል የለምና ራሱ ተገልጦ አምልኩኝ እንዳለ የምታምን ስለሆነ ነው። ዓይን እስከጠፈር ደርሶ ሲያይ ከቅንድብ ወጥቶ ወደ ጠፈር አይወረወርም ። ይልቁንም ያለበትን ሳይለቅ ከጠፈር ሁሉ በላይ ይመጥቃል እንጅ ይላሉ አበው በመቅድመ ወንጌል። ኢሳይያስ እግዚአብሔርን በረጅም ዙፋን አይቶታል። ሕዝቅኤል በፈለገ ኮቦር እግዚአብሔርን በደመናና በአውሎ መሀል አይቶታል። ዳንኤል በሽማግሌ አምሳል አይቶታል። አቡቀለምሲስም በመንበረ ኪሩቤል አይቶታል። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ዓይናቸው ወልቆ ወደ ሰማይ አልሄደም። ባሉበት ሆነው ወደ ሰማያት መጠቀ እንጅ። ይህ ግሩም የክርስቶስ ሥጋዌ ምሥጢር ነው። ዓይን ከቅንድብ ወጥቶ ሳይወድቅ ካሰበው ድረስ እንዲመለከት አካላዊ ቃል እግዚአብሔርም ከዘባነ ኪሩብ ከየማነ አብ ሳይነጠል ሳይጎድል በታች ሰው ሆኗልና። አንተ ሞኝ ለሰው ዓይን ሳይነጠል ወደ ሰማያት መውጣትከተቻለው ዓይንን ለፈጠረው ጌታ ከመንበረ ክብሩ ሳይጎድል ሰው ቢሆን ከባድ ነውን? መላእክትም የደነቃቸው ይህ ነው። በሰማይ ከአባቱ ጋር ያዩታልና ስብሐት ለእግዚአብሄር በሰማያት አሉ። በምድር አርያማዊት መቅደሱ በእናቱ እጅ ያዩታልና ወሰላም በምድር አሉ። ለ. ዓይናችን ድንግል ማርያም! ከዓይን በላይ ራስ ብቻ ነው ያለው። ከድንግል ማርያም በላይ እግዚአብሔር ብቻ ነው የለው። ዓይን ጉድፋችን እንድናይበት መርገማችን የተወገደባት ድንግል ማርያም ናት።ዓይን የሕዋሳት ሁሉ መብራት እንደሆነ እግዚአብሔር ራስ ነው። ቤተክርስቲያን አካሉ ናት። ቅዱሳን ሁሉ ሕዋሳቱ ናቸው። ስለዚህ አምለክን ወልዳ ለመላእክትም ለሰው ልጆችም ያሳየቻቸው ድንግል ማርያም ናትና። ብርሃን ከዓይን ሲዋሐድ ሁሉ እንዲታይ ለዓለሙሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ከእርሷ ሥጋን ነሥቶ በመዋሐዱ ፍጥረት ሁሉ ሊያየው ቻለ። ከአካል ተቆሮጦ ካልወደቀ በቀር ዓይን የማታስፈልገው ሕዋስ የለም። ተቀርጦ ከክርስቶስ ከተለየው ከሰየጣን በቀር ድንግል ማርያም አታስፈልገኝም የሚል የለም። እሾሁን በዓይን አይቶ እንዲያልፉት ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን እሾህና አሜከላ ታብቅልብህ ተብሎ የወደቀብንን የመርገም እሾህ ያለፍንባት መዝገበ በረከት ድንግል ማርያም ናት። ዓይንን እንዲማሩበት የትንቢተ ነቢያት ፍጻሜ የስብከተ ሐዋርያት መሠረት የምሥጢረ ሥላሴ መስታወት ወንጌልን የወለደች ፊደል እግዚአብሔር የሰጠን የሃይማኖታችን ምልክት ድንግል ማርያም! ዓይን ሳይሰበር ሳይፈስ የሰው ፊት በውስጡ ይታያል። ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ድንግልናዋ ሳይለወጥ አብን በመልክ የሚመስለው ባሕርይ የሚተካከለው የአብ ክብሩ ጸዳል አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከእርሷ በድንግልና ተወልዷልና። ዓይን ጠባብ ስትሆን የውቅያኖስ ስፋት የጠፈር ምጥቀት የተራሮች ግዝፈት በእርሷ ይወሰናል። ድንግል ማርያምም ታናሽ ብላቴና ስትሆን ሰማይና ምድር የማያወስኑትን ወስነዋለች። የመላእክትም ሆነ የሁላችን ዓይን ወላዲተ አምላክ ማርያም ሆይ እንዲህ ስልሽ ደስ ይለኛል! "የመላእክት ደስታቸው የሆነ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሸ! የነቢያት ዚና ትንቢታቸው ንጽሕት ሆይደስ ይበልሽ! እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነሥቶ ከአንቺ ሰው ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ! የዓለሙን ሁሉ ደስታ የመልአኩን ቃል ተቀብለሻልና ደስይበልሽ! ዓለሙን ሁሉ የፈጠረ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ! በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ! የሔዋን መድኀኒት ሆይ ደስ ይበልሽ! ፍጥረትን ሁሉ የሚመግበውን እርሱን ጡትሽን አጥብተሽዋልና ደስ ይበልሽ! የሕያዋን ሁሉ እናታቸው ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ" አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም። ሰናይ ቀን
Show all...
መጽሐፍ ቅዱስ የሙስሊሞች መመሪያ .........___´´´´´ እንዲሆን ቁርአኑ ያዝዛቸዋል __________´´´´´´´´´´´´
```
__ በቁርአኑ ላይ እንደምናነበው ያመኑ ሙስሊሞች ከቁርአን በተጨማሪ ከበፊቱ የወረደውን የመጀመሪያውን መጽሐፍ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያምኑና እንዲቀበሉ ያዝዛል፤ ይህ ሆኖ እያለ አብዛኛው ሙስሊም መጽሐፍ ቅዱስን አልቀበልም በማለት ሲከራከር ይታያል ይህ ግን ፈጽሞ ስህተት ነው ምክንያቱም ቁርዐኑ በግልጽ እንዲህ በማለት ያስተምራልና፡- >> “ቁርአኑን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፤ ተውራትና ኢንጅልንም (ኦሪትና ወንጌልንም) አውርዶአል” ይላል አልኢምራን 3÷3-4 ከላይ ወንጌል (ኢንጅል) ቀጥተኛ ብርሃን ያለባት ናት ማለቱን በአል ማኢዳህ ም.5 ቁ 46. ተመልክተናል፡ >> “እናንተ ያመናችሁ ሆይ (ሙስሊሞች ሆይ) በመልዕክተኛው ላይ (በመሐመድ ላይ) ባወረደው ከዚያም ከበፊቱ በወረደው (በኦሪትና በወንጌል) መጽሐፍ እመኑ” ይላል አል-ኒሳእ 4÷136. ስለዚህ ማንኛውንም ሙስሊም መጽሐፍ ቅዱስን የህይዎት መመሪያው አድርጎ ሊያምነውና ሊቀበለው ይገባል፡፡
Show all...
የምኞት አይነቶች .............,___`` ፩. የስጋ ምኞት- ለዝሙት፣ ለመብላት፣ ለመስማት የሚደረገውን ጉጉት ያጠቃልላል፡፡ ዘፍ. 25፣29-34 ኤሳው ብኩርናውን የሸጠው በመብል ምኞቱ ነው፡፡ እስራኤላውያንም የምንበላውን ስጋ ማን ይሰጠናል በማለት በልቅሶ የተመኙት በመቅሰፍት ተመተው በዚያ ተቀብረዋል፡፡ ዘኁ. 11፤34 የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ ሲል አታመንዝር ብሎዋል እና ያንተ ለማድረግ አትመኝ ለማለት ነው፡፡ ፪. የገንዘብ ምኞት - ንጉስ አክዓብ የናቡቴን መሬት ለመውሰድ የበቃበት ምክንያት የገንዘብ(ሀብት) ምኞት በመሆኑ ነው፡፡ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ ሎሌውንም ገረዱንም አህያውን በሬውን ሁሉ ያንተ ለማድረግ አትመኝ ፫. የክብር፣ የታዋቂነት፣ የስልጣን፣ የማዕረግ ምኞቶች - ዲያቢሎስ "ወደ ሰማይ አርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ክዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ… በልዑልም እመሰላለሁ" በማለት በመመኘቱ ነው ለታላቅ ውርደት የበቃው፡፡ ኢሳ. 14፤13 አዳምና ሔዋን ክፉንና ደጉን ለማወቅ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ካላቸው ጉጉት እና ምኞት የተነሳ ለታላቅ ውድቀት በቁ፡፡ ዘፍ. 3፤5 ከክፉ ምኞት ለመራቅ መፍትሔው የሚመኝ ለዚህ ዓለም እንግዳ መሆናችንን እና ከንቱ የሆውን የምኞት ምንጭ መናቅ መተው እና መሸሽ ሲቻለን ነው፡፡"ዓለሙም ምኞቱም ያልፍልና" መክ. 1፤10, ዩሐ. 2፤1
Show all...
ኒቆዲሞስ የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ማታ ማታ ጌታ ዘንድ እየተገኘ ይማር ነበር ይህ ይታሰብበታል፡፡ ዮሐ. 3፥1-15 ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን ሲሆን በኢየሩሳሌም በሀብት ቢሉ በእውቀት እንዲሁም በሥልጣን የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ‹‹መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህ ተአምራቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለንና አለው›› ዮሐ. 3÷2 በሌሊት ይመጣ ነበር ለምን አለ? አይሁድ ‹‹ማንም ከእኛ ወገን ከሆነ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ከሆነ ሀብትና ንብረቱ ይወሰድ፣ በቤተመቅደስ አይግባ፣ መሥዋዕት አይሰዋ›› ብለው ነበርና አይሁድን ፈርቶ ሀብት ንብረቱን ወዶ እንዳይታወቅበት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ በሌላ በኩል የቀን ልብ ባካኝ ነው፡፡ ዓይን ብዙ ያያል ሐሳብ ይበታተናል፡፡ በተሰበሰበ ልብ ለመማር፣ በተጨማሪ ሊቅ ነኝ እያለ እስከ ዛሬ ትምህርት አልጨረሰም እንዳይሉት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን ለመማር የመጣውን እሱን ይቅርና ጌታችን እየሄደ ያስተምር ነበርና ኒቆዲሞስ ምንም በሌሊት ቢመጣም ማወቅን ፈልጎ ነውና ስለ ዳግም መወለድ፣ ስለ ጥምቀት፣ በእግዚአብሔር ልጅ ስለማመንና ስለ ጽድቅ ሥራ በዝርዝር አስተምሮታል፡፡ ኒቆዲሞስ በመጨረሻው ቀን በዕለተ ዓርብ በስቅለቱ ጊዜ ከመስቀል ላይ ሥጋውን ለማውረድና ገንዞ ለመቅበር ቀድሞ ተገኝቷል፡፡ ዮሐ. 19፥38 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፡- የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!