cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ስንክሳር ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ-The Ethiopian Synaxarium

ስንክሳር ማለት ስብስብ ማለት ነው ስብስብ የተባለበት ምክንያት የብዙ ቅዱሳን ገድልና ዜና ሕይወት በአንድ ላይ የያዘ መጽሐፍ ስለሆነ ነው።ስንክሳር በእያንዳንዱ ቀን የሚዘከረው የቅዱሳን ታሪክ ጠቅለል ባለ መልኩ የያዘ ነው። Contact us👇 @The_Ethiopian_Synaxarium_bot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
685Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የfacebook እንዲሁም የtelegram profile picture ዎን በዚህ መልዕክት በመቀየር ይሳተፉ። @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
Show all...
#ኅዳር_23 ኅዳር ሃያ ሦስት በዚች ቀን የመቶ አለቃ የነበረ #ጻድቁ_ቆርኔሌዎስ አረፈ፣ #የነቢይ_አብድዩም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ጻድቁ_ቆርኔሌዎስ (የመቶ አለቃው) ኅዳር ሃያ ሦስት በዚች ቀን የመቶ አለቃ የነበረ ጻድቁ ቆርኔሌዎስ አረፈ። ይህም ቅዱስ የፍልስጥዔም ክፍል በሆነች በቂሣርያ የመቶ አለቃ ሁኖ የተሾመ ነው። እርሱም ከዋክብትን ሲያመልክ ነበር እንደርሱ ማንም ሊአደርግ የማይቻለውን የሚያመልካቸው አማልክቶቹም ቢሆኑ በሐዋርያት እጅ የሚደረገውን የተአምራታቸውንና የስብከታቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወዲያውኑ ለአማልክት መስገድን ተወ። ከዚህም በኋላ የሚጾም የሚጸልይ ለድኆችና ለችግረኞች የሚመጸውት ሆነ በጸሎቱም ጊዜ እንዲህ ይል ነበር አቤቱ አምላክ ሆይ እኔ አንተን ከማወቅ ጎደሎነኝና አንተ ግን የቀና መንገድህን ምራኝ። ቸር ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ይቅር ብሎት መልአኩን ላከለት ወደርሱም አይቶ ቆርኔሌዎስ ፈራ አቤቱ ምን ትላለህ አለ ጸሎትህ ምጽዋትህ መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል አሁንም በጫማ ሰፊው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ስምዖን ጴጥሮስን ይጠሩልህ ዘንድ ሰዎችን በባሕር አቅራቢያ ወደአለች ኢዮጴ ከተማ ላክ አለው። በዚያንም ጊዜ መልአኩ እንደነገረው ሰዎችን ላከ ጴጥሮስም በመጣ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተቀብሎ ከእግሩ በታች ሰገደለት ጴጥሮስም አነሣውና ተነሥ እኔም እንዳንተ ሰው ነኝ አለው። ከእርሱም ጋር እየተነጋገረ ገባ ወደርሱም የመጡ ብዙ ሰዎችን አገኘ። ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው ለአይሁዳዊ ሰው ሒዶ ከባዕድ ወገን ጋር መቀላቀል እንደማይገባው ታውቃላችሁ እኔን ግን ማንንም ማን ቢሆን እንዳልጸየፍ እግዚአብሔር አሳየኝ። አሁንም እንደላካችሁብኝ ሳልጠራጠር ወደ እናንተ መጣሁ የጠራችሁኝ ለምን እንደሆነ እስቲ ንገሩኝ። ቆርኔሌዎስም ዛሬ አራተኛ ቀን ነው አለ በቤቴ ውስጥ በዘጠኝ ሰዓት ስጸልይ አንድ ሰው ብርሃን ለብሶ ታየኝ። እንዲህም አለኝ ቆርኔሌዎስ ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም በእግዚአብሔር ፊት ታሰበልህ ። አሁንም ከባሕር አቅራቢያ ወዳለችው ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በጫማ ሰፊው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ጴጥሮስ የተባለ ስምዖንን ይጥሩልህ እርሱ አንተ የምትድንበትን ወገኖችህም ሁሉ የሚድኑበትን ይነግርሃል። ያን ጊዜም ስለዚህ ወዳንተ ላክሁ ወደእኛ መምጣትህም መልካም አደረግህ አሁንም እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ ልንሰማ እነሆ ሁላችን በፊትህ አለን። ጴጥሮስም አንደበቱን ገልጦ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለሙ ሁሉ ድኅነት ሰው መሆኑን መከራ ተቀብሎም ተሰቅሎ ስለ መሞቱ ስለ መነሣቱና ወደ ሰማይ ስለማረጉ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ ስለ መምጣቱ አስተማራቸው። የከበረ ቆርኔሌዎስም ከቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ ከዚያ የነበሩ ብዙዎች አሕዛብም አመኑ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም እንደተጻፈ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠመቁ። ከዚህም በኋላ ቆርኔሌዎስ ይህን ዓለም ለመግዛት የተሾመውን ሹመት ተወ ቅዱስ ጴጥሮስ ለክርስቶስ ጭፍራ የመሆንን ሹመት በመስጠት ለእስክንድርያ አገር ኤጲስቆጶስነት ሹሞታልና ወደ ርሷም ሒዶ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ጣዖታትንም ለሚያመልኩ ስሕተት መሆኑን ገለጠላቸው ልባቸውንም እግዚአብሔርን በማወቅ ብሩህ አደረገላቸው በፊታቸውም ተአምራትን አደረገ ብዙዎችም አምነው ተጠመቁ ከእነርሱም በኋላ መኰንኑን ድሜጥሮስን አጠመቀው። እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ነቢዩ_ቅዱስ_አብድዩ በዚችም ዕለት ዳግመኛ የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ የነቢይ አብድዩ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ ነገ. 18፥3 ላይ "አብደዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር" ተብሎ የተነገረለት እውነትም "የእግዚአብሔር አገልጋይ" የሆነ የነቢዩ ኤልያስ ደቀመዝሙር የነበረ ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ ነቢዩ አብድዩ ነገዱ ከነገደ ኤፍሬም ሲኾን አባቱ አኪላ እናቱም ሳፍጣ እንደሚባሉ የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ያስረዳል፡፡ ይህም ቅዱስ ነቢይ ከጠረፍ በረሃ አቅራቢያ ካለች ሱሳም በምትባል አገር ካሉ ሰዎች ወገን ነው፡፡ ለነቢዩ ኤልያስ ደቀ መዝሙሩ ሆኖ በንጉሡ በአክዓብምና በንግሥቲቱ በኤልዛቤል ምክንያት በእርሱ ላይ የመጣውን መከራ ሁሉ ታግሷል፡፡ ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ከእነ ኤልዛቤል ሸሽቶ ወደ ተራራ ላይ ወጥቶ በዋሻ ተሸሽጎ ምግቡን አሞራ እያመጣለት በኖረበት ጊዜ እንኳን አብድዩ ግን ብቻውን የእግዚአብሔርን ነቢያት ይንከባከብ ነበር፡፡ አብድዩ የንጉሥ አክዓብ የቤቱን አዛዥ የነበረ ቢሆንም ንግሥት ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው የነበረ ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪኩ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- "ከብዙ ቀንም በኋላ በሦስተኛው ዓመት "ሂድ ለአክዓብ ተገለጥ፥ በምድር ላይም ዝናብ እሰጣለሁ" የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ፡፡ ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፤ በሰማርያም ራብ ጸንቶ ነበር፡፡ አክዓብም የቤቱን አዛዥ አብድዩን ጠራ፤ አብድዩ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ ነበር፡፡ ኤልዛቤልም የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ እርሱ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር፡፡ አክዓብም አብድዩን "በአገሩ መካከል ወደ ውኃው ምንጭ ሁሉና ወደ ወንዝ ሁሉ ሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኛለን" አለው፡፡ ሁለቱም የሚመለሱበትን አገር ተካፈሉ፤ አክዓብም ለብቻው በአንድ መንገድ አብድዩም ለብቻው በሌላ መንገድ ሄዱ፡፡ አብድዩም በመንገድ ሲሄድ እነሆ ኤልያስ ተገናኘው፤ አብድዩም አወቀው፣ በግምባሩም ተደፍቶ "ጌታዬ ሆይ! ኤልያስ አንተ ነህን?" አለ፡፡ ኤልያስም "እኔ ነኝ ሄደህ ለጌታህ ‹ኤልያስ ተገኝቶአል› በል አለው፡፡ አብድዩም "እኔን ባሪያህን እንዲገድል በአክዓብ እጅ አሳልፈህ ትሰጠኝ ዘንድ ምን ኃጢአት አድርጌአለሁ? አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም 'በዚህ የለም' ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር፡፡ አሁንም እነሆ 'ሂድ ኤልያስ ተገኘ ብለህ ለጌታህ ንገር' ትለኛለህ፡፡ እኔም ከአንተ ጥቂት ራቅ ስል የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደማላውቀው ስፍራ ይወስድሃል፤ እኔም ገብቼ ለአክዓብ ስናገር ባያገኝህ ይገድለኛል፤ እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን እፈራ ነበር፡፡ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ባስገደለች ጊዜ መቶውን የእግዚአብሔር ነቢያት ወስጄ አምሳ አምሳውንም በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እንጀራና ውኃ የመገብኋቸው ነበር፡፡ ይህ ያደርግሁት ነገር በውኑ ለጌታዬ አልታወቀህምን? አሁንም 'ሄደህ ኤልያስ ተገኘ ብለህ ለጌታህ ንገር ትላለህ' እርሱም ይገድለኛል" አለው፡፡ ኤልያስም ''በፊቱ የቆምሁት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ ዛሬ ለእርሱ እገለጣለሁ" አለ፡፡ አብድዩም አክዓብን ሊገናኘው ሄደ፣ ነገረውም፤ አክዓብም ኤልያስን ሊገናኘው መጣ፡፡ አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ "እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?" አለው፡፡ ኤልያስም "እስራኤልን የምትገለባብጡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ በኣሊምን የተከተላችሁ፣ አንተና የአባ
Show all...
in the country and prophesied; and when he died he was buried with his fathers in peace. Salutation to Obadiah who was clothed with the spirit of knowledge. And on this day also was consecrated the church of Marina. [This paragraph is wanting in the Bodleian MS]. Glory be to God Who is glorified in His Saints. Amen.
Show all...
#ኅዳር_24 ኅዳር ሃያ አራት በዚች ቀን #የሃያ_አራቱ_ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው፣ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑበት ነው፣ #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ ልደታቸው ነው፣ #ቅዱስ_አዝቂር_ሰማዕት ከአርባ ስምንት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት ያረፈበት ፣ #ቅዱስ_አባ_ዮሴፍ_ዘሀገረ_ፃን ያረፈበት ዕለት ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ ኅዳር ሃያ አራት በዚህች ቀን በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው ። እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋርነ እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለእነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዙአብሔር አይቀርብም። ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ። በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮች ላይም ሃያ አራት አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ። ሁለተኛም እንዲህ አለ ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የወርቅ ጽንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይም የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት ። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐረገ ። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም ። እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ ። እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆኑ በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእሱ ሰገዱለት ። አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው አቤቱ ፈጣሪያችን ኃይልና ምስጋና ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና ። እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ሁነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን በዚያው በሐይቅ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አክፍሎትንም በየሳምንቱ ያከፍላሉ፣ ከእሁድና ከቅዳሜ በቀር ምንም አይቀምሱም ነበር፡፡ በእነዚህም ዕለት የአጃ ቂጣ ወይም የዱር ቅጠል ይመጉ ነበር፡፡ ወዛቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድሪቷን እስኪያርሳት ድረስ እስከ 70 ሺህ ስግደትንም በመስገድ ራሳቸውን እጅግ አደከሙ፡፡ በእነደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ያቆማቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ስለሆነው ነገር ራሳቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሲናገሩ ‹‹…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ ‹ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን› የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ…..›› (ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገጽ 216-223) ይህንን ታላቅ በዓል ነው ዛሬ የምናከብረው፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት እንኳን አንደበታቸው የለበሱትም ልብሳቸውም ጭምር እግዚአብሔርን በሰው አንደበት እንደሚያመሰግን በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፏል። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አቡነ_ዜና_ማርቆስ አቡነ ዜና ማርቆስ በወንጌላዊ በቅዱስ ማርቆስ ብስራት እንደተወለዱ፦ አባታችን ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ስትሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻድቅ ልጅ እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል›› በማለት ብስራቱን ነግሮታል፡፡ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን ዜና ማርቆስ በዚህች ዕለት ኅዳር 24 ቀን በተወለዱ ጊዜ ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎች ሁሉ ታይቷል፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ዘወገግ አባት ቅዱስ እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም አቡነ ዜና ማርቆስን ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናታቸው ሰጧቸው፣ እናታቸው ግን ይህን አታውቅም ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው ‹‹አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ›› ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡ በ40 ቀናቸውም ሲጠመቁ የሚያጠምቃቸው ካህን የአባታቸው ወንድም እንድርያስ ውኃው ሲፈላ አይቶ ሸሽቷል፡፡ መልአኩም እንዳይፈራ ነግሮት ለእርሱም ተአምር እንደሚደረግለት አስረዳው፡፡ እንድርያስም ዕድሜው 72 ነበርና ራሰ በራ ስለነበር አባታችንን ባጠመቀበት በውኃው ራሱን ቢታጠብበት ጸጉር አብቅሏል፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይቶ አደነቀ፡፡ ያችም ውኃ ሌሎች በጣም ብዙ ተአምራትን አደረገች፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ አንድ ዓመት በሆናቸውም ጊዜ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየዳኹ ሲሄዱ መልአክ በክንፎቹ አቅፎ ነጥቆ ወደሰማይ ወስዶ ጌታችንና እመቤታችን ጋር አቅርቦ አስባርኳቸዋል፡፡ እንዲሁም የ15ቱን ነቢያት፣ የ12ቱን ሐዋርያት የ72ቱን አርድእት፣ ሃይማኖታቸው የቀና የ318ቱን ሊቃውንት፣ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን የእነዚህን ሁሉ በረከት እንዲቀበሉ ካደረጋቸው በኋላ ወደዚያች ቤተክርስቲያን መለሳቸው፡፡ የአቡነ ዜና ማርቆስን የዕረፍታቸውን በዓል ከ9 ቀናት በኋላ ታኅሣሥ 3 ቀን ስለምናከበር አምላካቸው ከዕረፍታቸው ቀን ያድርሰንና ያንጊዜ ሙሉን ዜና ገድላቸውን እናየዋለን፡፡ በረከታቸው ይደርብን
Show all...
በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አዝቂር_ሰማዕት በዚችም ዕለት የናግራን አገር ቄስ የከበረ አዝቂር የሐሚር ንጉሥ ሰራብሄል በነገሠበት ወራት ከእርሱ ጋር ካሉ አርባ ስምንት ሰዎች ጋር በሰማዕትነት አረፈ ። ይህም ንጉሥ አዝቂርን ወደ ወህኒ አስገብተው እንዲዘጉበት ጠባቂዎቹንም ከሰው ወገን ማንም እንዳይገባ ብሎ አዘዘ ። ቅዱስ አዝቂርም በጸለየ ጊዜ የወህኒ ቤቱ ደጃፍ ተከፈተና ሃምሳ ሰዎች ወደርሱ ገቡ እርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው ። ንጉሥ ሰራብሄልም በሰማ ጊዜ ከወህኒ ቤት አውጥተው ወደሌላ አገር እንዲወስዱት አዘዘ በጉዞም ላይ ስሙ ኪርያቅ ከሚባል ሰው ጋር ተገናኘ ቀሲስ አዝቂርም ኪርያቅን ኪርያቅ ሆይ ላንተ የምሥራች ይገባል ለሰማዕትነት ይወስድሃልና አለው ። የንጉሥ ሎሌዎችም ሰምተው አሥረው ከእርሱ ጋር ወሰዱት ። ዳግመኛም ሁለት ሰዎች ተገናኙትና ስለ ክርስቶስ አጥምቀን አሉት ያን ጊዜም ቅዱስ አዝቂር ጸለየና ከበረሀ ቦታ ውኃ አፍልቆ ከኪርያቅ ጋር አጠመቃቸው ። ከዚህም በኋላ ወደበረሀ ውስጥ በደረሱ ጊዜ ለእሳቸውም ለእንስሶቻቸውም የሚጠጡት ውኃ አጥተው ወደ እግዚአብሔር እንዲለምንላቸው ቅዱስ አዝቂርን ለመኑት በጸለየም ጊዜ ደመና መጣ በመሐል እጅ በሚታፈን መጠን በገበታ ላይ ዘነበ ሰባት መቶ ያህል ሰዎች ከእንስሶቻቸው ጋር ጠጥተው ረኩ ። ወደ ንጉሡም በአቀረቡት ጊዜ ወደ አገራችን ያመጣኸው ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው አለው ቅዱስ አዝቂርም ነቢያት በኦሪት ከሰበኩት በቀር ሌላ አዲስ ትምህርት አላመጣሁም አለ ንጉሡም ይህን ሰምቶ በክርስቲያን ሃይማኖት ላይ ተዘባበተ። ከአይሁድ መምህራንም አንዱ ተነሥቶ እንዲህ አለ ጌታዬ ሆይ ወደ አገሩ እንዲወስዱትና በዕንጨት ላይ ሰቅለው በሕይወት ሳለ በእሳት እንዲአቃጥሉት እዘዝ አለው ንጉሡም እንደ አይሁዳዊው ቃል አዘዘ። ወደ ናግራን አገርም በአደረሱት ጊዜ በዕንጨት ላይ ሰቅለው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ቅዱስ አዝቂርም ወደ ጌታችን ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከማሠሪያው ተፈትቶ ከእሳት ውስጥ በደኅና ወጣ አይሁድም በደንጊያ እንውገረው ተባብለው በወገሩት ጊዜ ደንጊያዎች ተመልሰው ከአይሁድ የሚበዙትን ገደሉ ። ከተረፉትም ሰይፍን አንሥተው የቅዱስ አዝቂርን ራስ ቆረጡ ምስክርነቱንም ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባ_ዮሴፍ_ዘሀገረ_ፃን በዚችም ቀን ፃን ከምትባል አገር የሆነ አባ ዮሴፍ አረፈ። ለዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በሃይማኖት የበለጸጉ ናቸው ነገር ግን ያለርሱ ልጅ አልነበራቸውም የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት መጻሕፍት ማንበብንም እያስተማሩ መልካም አስተዳደግን አሳደጉት መልኩም እንደ ያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ያማረ ነበር በአደገም ጊዜ ሞትን የዚህንም ዓለም ኃለፊነት ማሰብ በልቡ አደረ። ወደ አንድ ገዳምም ሒዶ መንኵሶ በጾም በጸሎት በመስገድ በተጋድሎ የተተከለ ሆኖ ጸና በአቱንም ዘግቶ በእለተ እሑድ ከቁርባን ጊዜ በቀር አይወጣም ነበር ። ዜናውም በተሰማ ጊዜ ከእርሱ በረከቱን ይቀበሉ ዘንድ በአገር ዙሪያ ያሉ ሰዎች የሚመጡ ሆኑ አባቱና እናቱም የልጃቸውን ወሬ በአጡ ጊዜ እርሱን ያገናኛቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ነበር። ወሬውንም በሰሙ ጊዜ ስለ ልጃቸው መገኘት እንዲጸልይላቸው ወደርሱ ሔዱ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ አላወቁምና ሰውም ገለል ባለ ጊዜ ልጃቸው መሆኑን እራሱን ገለጠላቸውና ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው ። እግዚአብሔርም ድንቆች ተአምራትን የማድረግ ሀብትን ሰጠው ሰይጣን እስከ ቀናበት ድረስ ወደ አገረ ገዢውም ሔዶ ይህ መነኵሴ ዮሴፍ ብዙ ገንዘብ እንዳለው አስመስሎ ነገር ስራበት ። መኰንኑም በሰንሰለት ማሰሪያዎች አሰረው። በማግሥቱም ማሰሪያዎቹ ከላዩ ወደ ምድር ወድቀው ተገኙ መኰንኑም አይቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዥ ሆነ ። ብዙ ከተጋደለና እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ። በክብርም ቀበሩት ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ብዙ ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
Show all...
ትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም" አለው፡፡ 1ኛ ነገ.18፥1-20፡፡ ቅዱስ አብድዩ የንጉሥ አክዓብ የቤቱን አዛዥነቱን ትቶ የኤልያስ ቀደ መዝሙሩ ሆኖ በነቢይነት እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ የትንቢቱ ወራት ሲፈጸም በዚህች ዕለት ዐርፏል፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
Show all...