cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio Facts 🇪🇹 ኢትዮ ፋክት️

ኢትዮጵያ ትቅደም Walk a mile in my shoes, Then you will know how I feel.

Show more
Advertising posts
364Subscribers
+224 hours
+147 days
+6730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአይ ኤም ኤፍ መደራደሪያ ሀሳብ በኢትዮጵያ ያለውን የዋጋ ግሽበት  ሊያባብሰው እንደሚችል ተነገረ፡፡ በቅርቡ  አይ ኤም ኤፍ |IMF| እና ኢትዮጵያ  በብድር እና መሰል ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው  ይታወቃል። በአዲስ አበባ በነበረው ውይይቱ ከስምምነት ሳይደርሱ መለያየታቸው የተለያዩ ምንጮች መዘገባቸው  የሚታወስ ነው።   አይ ኤም ኤፍም ኢትዮጵያ ብድሩን ለማግኘት እንድተችል የተለያዩ አሰግዳጅ የፖሊሲ ቅድመ ሁኔታዎች  እያስቀመጠ እንደነበር ተዘግቧል። ሬውተርስ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ነግረውኛል ብሎ በሰራው ዘገባ አበዳሪው የገንዘብ ተቋም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በነበረው የመጨረሻው ውይይት ወቅት አገሪቱ የገንዘብን የመግዛት አቅም እንድታዳክም በግልጽ ባይጠይቅም፣ የሚለቀቀው ብድር ያንን ማድረግ የሚጠይቅ ነው ሲል ገልጿል። በዚህም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እያመነቱ የቆዩበትን ብርን ከዶላር ምንዛሬ አንጻር የማዳከም ውሳኔ ምናልባትም ካቀዱት ጊዜ ቀድመው ሊያሳልፉ  ይችላሉ ሲል ሬውተርስ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘው  ሀሳባቸውን ለጣቢያችን የሰጡን የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎችም ብድር ለማግኘት ተብሎ የሚወሰዱ እርምጃዎች ሀገሪቱ ላይ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያመጣ ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ የምጣኔ ሃብት ባለሞያው አቶ መቆያ ከበደ እንደሚሉትም፤ የአይ ኤም ኤፍ ጥያቄ የገንዘብ የመግዛት ዋጋን እንዲቀንስ የሚያደርግ  ከሆነ የዋጋ ግሽበቱን ሊያባብሰው ስለሚችል በጥንቃቄ መደረግ እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ ምንዛሬው በገበያ ይወሰን የሚለው ሃሳብ መንግስት አያደርገውም የሚሉት አቶ መቆያ ከበደ ንግዱ በገበያ ከሆነ ቆይቷል ከባንክ አሰራር ካለው ውጪ የእቃ ግብይቱ በጥቁር ገብያው ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሌላኛው  የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ዶ/ር አጥላው አለሙ በበኩላቸው፤ ገንዘብን የማዳከም አንዲሁም የፕራይቬታይዜሽን ጉዳይ  የአይ ኤም ኤፍ አስገዳጅ ሁኔታዎች እንደሆኑ በማነሳት የሚደረገው ውይይት ጥቅም አልባ እና መንግስት የተባለውን ቢቀበለም ብድር ይለቀቃል ስፊው ማህበረሰብን ግን በተባባሰ የዋጋ ግሽበት ውስጥ እንደሚኖር ተናግረዋል። ገንዘብን ማዳከም እና የዋጋ ንረት ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው የሚናገሩት ሌላኛው  የምጣኔ ሃበት ባለሞያው   አቶ ጌታቸው አስፋው መንግስት የብርን የመግዛት አቅም የማዳከም ውሳኔ ከወሰነ የዋጋ ንረቱም በዛው ልክ ከፍ እንደሚል አንስተው የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር ስለሚችል ገንዘብን እንዲዳከም ማድረግ ብዙም አይመከርም  ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
Show all...
የእስራኤል 'የተገደበ' ጥቃት በኢራን ላይ: እስካሁን የሚታወቀው 🌏 እስራኤል ኢራን ላይ የሚሳኤል ጥቃት አድርጋለች በቴህራን፣ኢስፋሃን እና ሺራዝ ከተሞች ፍንዳታዎች እንዲሁም የኢራን አየር ሃይል 8ኛ ጣቢያ አጠገብ ፍንዳታዎች እንደተሰሙ የአሜሪካ ሚዲያ ዘግቧል። 🌏 ፎክስ ኒውስ በበኩላቸው ቴህራን ባለፈው ሳምንት በእስራኤል ላይ የተተኮሱ ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመተኮሷ የአይሁዶች መንግስት አርብ መጀመሪያ ላይ በኢራን ላይ “የተገደበ ጥቃት” አድርጋለች ሲል ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮችን ጠቅሷል። 🌏 የአሜሪካ የዜና አውታሮችም ኢራን ውስጥ በሚገኘው የኒውክሌር ጣቢያ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን እና በኢስፋሃን አየር ማረፊያ አካባቢ ፍንዳታ እንደደረሰ ዘግበዋል። 🌏 የኢራን መንግስት ብሮድካስቲንግ IRIB ግን ኢስፋሃን "ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ" ነው ሲል የጥቃት ዘገባዎችን አሳንሷል። 🌏 የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው የእስራኤል ሚሳኤል በኢራን ግዛት ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንዳልደረሰበት የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ሰራዊት በአየር ላይ በርካታ የእስራኤል ድሮኖችን ወድቋል ኢስፋሃን። 🌏 ደቡባዊ ሶሪያ እና ኢራቅ ውስጥ የሚገኝ አንድ ግዛት በእስራኤል የአየር ጥቃት ተመትቷል ሲል የኢራን አይአርኤን የዜና አውታር ዘግቧል። 🌏 አርብ ጠዋት በበርካታ የኢራን አውሮፕላን ማረፊያዎች ስራ ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱን የኢራን ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቃል አቀባይ ጃፋር ያዛርሎ ተናግረዋል። 🌏 እስራኤልም ሆነች አሜሪካ ስለተዘገበው ጥቃት እስካሁን የሰጡት አስተያየት የለም።
Show all...
እስራኤል ኢራን ላይ ጥቃት ፈፀመች እስራኤል በኢራቅ፣ ሶሪያ እና ኢራን ላይ በተመሳሳይ ጊዜ ጥቃት መፈፀሟ ነው የተዘገበው። የኢራን ፀረ ሚሳይሎች ድሮኖችን በመመከት ተግባር ላይ መሆኑን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መሰራጨት ጀምረዋል። የኢራን ጦር IRGC የእስራኤልን የኑክሌር ጣቢያ የአፃፋ ጥቃት ኢላማ እንደሚያደርግ መግለፁም ተዘግቧል።
Show all...
ባግዳድ ኢራቅ የእስራኤል አየር ኃይል በኢራቅ ባግዳድ ጥቃት ማድረሱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል
Show all...
እስራኤል ኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈፀሟ ተሰማ የእስራኤል  ጦር  በኢራኗ ኢስፋሃና ግዛት ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል፡፡ ከኢራን በተጨማሪም  በሶሪያና ኢራቅ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ እየተሰማ ነዉ  ተብሏል፡፡ ኒዮርክ  ታይምስ የአሜሪካና የእስራኤል ባለስልጣናት ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበዉ  ጥቃቱ በኢራን   ወታደራዊ መሰረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ነዉ፡፡ በእስራኤል ሚሳኤል የተመታችዉ የኢራን  ከተማም  ኢስፋሃን ትሰኛለች፡፡ ኢራን በረራዎችን ማገዷን አስታዉቃለች፡፡ ከኢራን በተጨማሪም በሶሪያና ኢራቅ አካባቢ   ፍንዳታዎች እንደተሰሙ   ታይምስ ኦፍ እስራኤል  በሰበር ዜናዉ እያስነበበ ነዉ፡፡ ይህንን ተከትሎም   ኢራን በሶሪያ የሚገኘዉን ጦሯንና  የሄዝቦላህን  ታጣቂዎች ማስወጣጥ መጀመሯን  እየሩሳሌም ፖስት ነዉ የዘገበዉ፡፡ የቀጠናዉ ሀገራትም ከፍተኛ  ስጋት ዉስጥ  ወድቀዋል፡፡ በእስራኤል ገሊላ አካባቢ የሳይረን ድምጽ ሌሊቱን ተሰምቷል ቢባልም  የእስራኤል  ጦር ግን ሃሰት ነዉ ብሏል፡፡ እስራኤል ተጨማሪ ጥቃቶችን  በኢራን ላይ  እንደምትወስድ አስታዉቃለች፡፡ ኢራንን በበኩሏ የመልስ ምቴ ከባለፈዉ እጅግ የከፋ ነዉ ስትል  ማስጠንቀቂያ እየሰጠች ነዉ፡፡
Show all...
ኢዜማ፣ ፌደራል መንግሥቱ በፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት መሠረት የሕወሓት ታጣቂዎችን ባስቸኳይ ትጥቅ እንዲያስፈታ ጠይቋል። መንግሥት ሕወሃትን ትጥቅ ባለማስፈታቱ በሰዎችና ንብረት ላይ ለሚደርሰው ጉዳት “ሙሉ ኃላፊነቱን" እንደሚወስድ ፓርቲው አሳስቧል። ኢዜማ፣ የፓርቲነት ሕጋዊ እውቅና የሌለው ሕወሓት "የራሱን ታጣቂ ኃይል ያደራጀ ብቸኛ ስብስብ ኾኖ በነጻነት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል” በማለት መንግሥትን ተችቷል። ፓርቲው፣ የፌደራል መንግሥቱ በጉዳዩ ላይ ያሳየውን ደካማ መረጃ አሰጣጥና ቸልተኝነት ተችቷል።
Show all...
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ ነገ ድምፅ ይሰጣል! የፀጥታው ምክር ቤት የፍልስጤምን የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ላይ ድምጽ ለመስጠት ለመጭው አርብ ቀጠሮ ይዟል።በአሁኑ ጊዜ  ከ10 ተዘዋዋሪ አባላት አንዷ የሆነችው አልጄሪያ «የፍልስጤም ግዛት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል እንድትሆን» የሚል ጥያቄ አቅርባለች።የአልጄሪያን ጥያቄ ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በፍልስጤም አባልነት ላይ በነገው ዕለት ድምፅ እንደሚሰጥ  ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት ነገ ዓርብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ላይ፤«የፍልስጤም ግዛት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሆና እንድትገባ”በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምፅ ይሰጣል ሲል ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደ ሮይተርስ ዘገባ የምክር ቤቱ ውሳኔ ቢያንስ ዘጠኝ የድጋፍ ድምጽ የሚያስፈልገው ሲሆን ፤እርምጃው እስከ 13 የምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።ይህም ሀሳቡን በመቃወም ዩኤስ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንድትጠቀም ያስገድዳል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።
Show all...
👍 2
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አድርጋለች?? የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ፣ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስለተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እና ሌሎቹም ተጠቃሽ ናቸው። አቶ ነብዩ እንዳሉት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በድንበር አካባቢ ያሉ ማህበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መንገድ በሁለቱ ሀገራት በሚዋቀር ኮሚቴ ይፈታል ብለዋል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል ማለቱ አይዘነጋም። የኤርትራ ጦር በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን እንደተቆጣጠር እና አካባቢዎቹን ወደ ኤርትራ ማካለሉን እንዴት ኢትዮጵያ እንዴት ታየዋለች? በሚል ለቃል አቀባዩ ለቀረበላቸው ጥያቄም "ጥያቄው ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የማህበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደተነሳ እና ጉዳዩ በውይይት ይፈታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፣ አሁንም ማለት የምችለው ይህንን ነው" ብለዋል። ከአራት ወር በፊት በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተካሄደው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ጉዳይ ሌላኛው በዛሬው መግለጫ የተነሳ ጉዳይ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገራት ባደረሱት ጫና ምክንያት የአቋም ለውጥ ወይም ሌላ አዲስ ነገር ይኖር ይሆን? በሚል ጥያቄ ተነስቷል። ቃል አቀባዩ በሰጡት ምላሽም " ከሶማሊላንድ ጋር በተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ዙሪያ የተቀየረ አቋም የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔት የሚኖሩ 70 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ የተጀመረው ጥረት እንደቀጠለ ነው የተባለ ሲሆን በሳምንት 12 በረራዎች እየተደረጉ እንደሆነም ተገልጿል። ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን ለመቀላቀል የጀመረችው ድርድር በጥሩ መልኩ እየሄደ ነው የተባለ ሲሆን በተለይም ምርቶችን በመሸጥ ዙሪያ ጥሩ መሻሻል ሲያሳይ በቀጣይ ደግሞ በንግድ አገልግሎቶች ዙሪያ ተጨማሪ ድርድር እንደሚደረግ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ከ24 ዓመት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማሳለጥ የተቋቋመው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጥምረት በየጊዜው አዳዲስ አባላትን በመሳብ ላይ ይገኛል። ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከአንድ ዓመት በፊት ይህን ጥምረት ለመቀላቀል በይፋ ከጠየቀች በኋላ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ጀምሮ ስምነኛዋ አባል ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ የ300 ሚሊዮን ህዝብ መገበያያ መድረክ ሲሆን ኢትዮጵያ አባል ከሆነች የአባል ሀገራቱን ቁጥር ወደ ዘጠኝ የግብይት መጠኑንም ከ400 ሚሊዮን በላይ በማድረስ በአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኢኮኖሚ ትስስር ወደ መሆን ይሸጋገራል ተብላል። በድርቅ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን አንድ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለማሰባሰብ በስዊዘርላንድ ጀኔቭ በተካሄደው እርዳታ ላይ የታሰበውን ያህል ገንዘብ መሰብሰብ እንዳልተቻለም ተገልጿል። በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን ያህል ገንዘብ ማግኘት ያልተቻለው አፍሪካን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች በተመሳሳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች እና ተቋማት በመኖራቸው እንደሆነ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
Show all...
በአማራ ክልል ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በሚያደርገዉ ዉጊያ ላይ የባህር ሀይል ወታደሮች እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ባለው ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል። ዳጉ ጆርናል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንደተመለከተው"የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል" ብሏል። ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች ግዳጃቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ብሏል። ማሪን ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል መሆኑንም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ መናገራቸውን የሀገር መከላከያ ስራዊት ገልጿል። ማሪን ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ ዘገባ ላይ ተጠቅሷል። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁም አይዘነጋም። #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ በጅምላ እና ችርቻሮ እንዲሳተፉ ተፈቀደ ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ ተደረገ፡፡  በዚህም መሰረት የውጭ ባለሀብቶች በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው፤ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት ይችላሉ፡፡ የጅምላ ንግድን በተመለከተ ከማዳበሪያ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟሉ ለአገር ውስጥ ባለሃብት በተከለሉ ሁሉም የችርቻሮ ንግድ ስራዎች መሳተፍ እንዲችሉ መፈቀዱም ተጠቅሷል።  በጉዳዩ ላይ በባለድርሻ አካላት የተካሄዱ ዝርዝር ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ መሠረታዊ የፖሊሲ ለውጥ ያደረገው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድም አዲስ የአፈፃፀም መመሪያ አፅድቋል።
Show all...