Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
@telemetr_io_bot
Telegram analytics bot

The bot can:

  • analyze channel audience
  • channels intersections
Category
Channel location and language
✅ህይወት ትቀጥላለች አንዱን ከሌላው ድርና ማግ እያደረገች። ✅ውድ የቻናሉ ቤተሰቦች ፍቅርን እንዝራ ፍቅርን እንስበክ ፍቅርን እናቀንቅን። ✅ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችንና ሌሎች መጻጽፎችን ያገኙበታል። . . For paid & cross promotion  @lucita100  
Show more
127 212-142
~8 205
~6
6.45%
Telegram general rating
Globally
9 413place
of 3 824 617
9place
of 899
In category
61place
of 2 066

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

😘ለፍቅር ስል😘 🔥ክፍል 13 ✍️ደራሲ፦ጎስ """ """ """ """ ......ይሄ እፅ ከተያዘ የምንከስረውን ኪሳራ ታውቀዋለህ እንዴ" አለው....ግን ኤስኮባር መልስ ሳይመልስ የኬንያ ፖሊሶችና የደህንነት ሀላፊዎች ከበባቸው....ተኩስም ከፈቱባቸው በዛ መሀል ኤስኮባር አቃስቶ ወደቀ....የሰውነቱን ቅርፁን አጉልቶ የሚያሳየው ጥብቅ ያለው ጥቁሩ ቲሸርት በደሞ ተለወሰ...የተኩሱ ልውውጥ ዘለግ ያለ ሰአት ፈጅቶ እየተታኮሲ ሊያመልጡ የነበሩት የኪንግ ሰራዊትም ከያሉበት ተለቃቅመው ተያዙ.....ኤስኮባርም ወደ ሆስፒታል ገባ....የኪንግ ሰራዊት አባላት መያዛቸው በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ማፍያዎች በደስታ ሰከሩ መሪያቸውም ስለተያዘ የተቀሩትን ደምስሰው ግዛታቸውን ለማስፋፋት እቅዶችን ነደፉ....የሀገሬው ህዝብ የኪንግ አባላት መያዛቸው አልወደዱትም ልክ ከአርባ አመታት በፊት የብላክ ኤንጅልስ የማፍያ ቡድን ከያሉበት ታድነው እርምጃ ሲወሰድባቸው የእነሱን ቦታ ለመውረስ እነሱን ተከትለው የሚመጡት የፋየር ስታር ኪንግ ድሪምና ሌሎች ጥቃቅን ማፍያዎች ባደረጉት ግብግብ ቡዙሀኑ የኬንያ ህዝብ ተጎድቷል....ልጆቻውንም ለመሬት ሲሳይ አድርገዋል....ኪንግ በወቅቱ አሸንፎ ወደ መንበረ ስልጣኑ ከመጣ ጀምሮ እሱን የሚገዳደር ሀይል ስለሌለ በማህበረሰቡ ውስጥ ግድያ የለም ግድያም ካለ ያ ሰው የነሱን ስራ ደርሶበታል አልያም ደሞ ከነሱ በተቃራኒ ጎን ቆሞ ከሆነ ብቻ ነው.......በኬንያ ያለውን መረብ ለመበጠስ ሀ ብሎ ርምጃ መውሰድ የጀመረው የፖሊስና የደህንነት መስሪያ ቤቱ በመግለጫ ሚዲያዎቹን አጥለቅልቆታል የኪንግ መሪው ጭምር መያዙ አይደለም የሀገር ውስጥ ዜናዎች ቀርቶ ትላልቆቹ የሚድያ አውታሮች ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል...... ኬንያ አሉኝ ከምትላቸው ታላላቅ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚመደበው ዘ ናይሮቢ ሆስፒታል ውስጥ የፀጥታ አካላቶች ጋጋታና የዶክተሮች ሩጫ ሀገሪቷን ሊያሸብር የመጣ የእፅ አዘዋዋሪን ህይወት ለማትረፍ ሳይሆን ቱባ ባለስልጣንን ለማከም የሚደረግ ነበረ የሚመስለው...."ዶክተር የልብ ምቱ እየቀነሰ ነው"አለች ሰማያዊ የለበሰችው ነርስ የልብ ትርታን የሚለካው ማሽን እስክሪን ላይ እያፈጠጠች.... "አሁኑኑ መርፌውን ዉጊው" አሏት አሁንም ስራቸውን ሳያቋርጥጡ....መርፌውን ስትወጋው እየቀነሰ የነበረው የልብ ምቱ እየጨመረ መጣ.....ዶክተሮቹም ልቡ ላይና ሳንባው ለይ የተቀረቀረችውን እርሳስ ለማውጣት ውስብስቡን ስራ ጨረሱ....."ዶክተር ታማሚው የመትረፍ እድል አለው?" አለ የፖሊስ ልብ የለበሰና የኮማንደርነት መአረግ ትገሻው ላይ ያንጠለጠለ ፖሊስ.... "እኛ የተቻለንን አድርገናል የሚቀጥሉት ሀያ አራት ሰአታ ነው ወሳኙ....እኛ የተቻለንን አደርገናል ቀጣዩ ተታካሚው ጥንካሬ ይወስነዋል" ብለው ዶክተሩ ለሰባት ሰአታት ኦፕራስዬን በማድረጋቸው እረፍት ለማድረግ ወደ ቢሯቸው ገቡ......ቀናት ቀናቶችን በተኩ ቁጥር የኤስኮባር ጤንነት መሻሻልግ ሊያሳይ አልቻለም እንደውም ድጋሜ የኤስኮባር ልብ ምት መውረድ ጀመረ...."ዶክተር ኪሊያን አሁኑኑ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል መግባት አለብን ታካሚው ልብ ምቱ እየወረደ ነው" ብላ ነርሷ ዶክተሩን ጠርታ እየበረረች ወደ ቀዶ ጥገናዎ ክፍል አመራች.....እዛ ሲደርሲ ልብ መስራቱን አቁሟል... "አሁኑኑ የኤሌክትሪክ ሾኩን ማሽን አዘጋጁ" እንዳለ ዶክተሩ ነርሷ የኤሌክትሪክ ሾኩን ለዶክተሩ አቀበለችው "180 ላይ አድርጊው" አለ ነርሷም እንደታዘዘችው አደረገች ዶክተሩ ደጋግሞ ልቡ ላይ የኤሌክትሪክ ንዝረት ቢያሳርፍም ልቡ መልሶ ሊነሳ አልቻለም... "280 ላይ አድርጊው" ብሎ ዶክተሩ እርስ በእርስ እያፋተጉ ወደ ደረቱ አስጠግተው ደረቱ ላይ ሲያሳረፉ ወደ ላይ እየዘለለ ወደ አልጋው ይመለስ ጀመረ.... "አጎቴ እንዴት አምሮበካል ሙሉ ነጭ በነጭ ነው የለበስከወሰ ነጭ ልብስ እኮ አትወድም ነበረ" አለው ኤስኮባር ከመታት በፊት ከመቶው አጎቱ ፊት ለፊት ቆሞ..... "ኤስኮባር የሰጠውክን አደራ መወጣት ሳትችል ወደኔ መጣክ የሰጠውክ አደራስ አደራዬን በላክ ጩቤዬን አሳልፈክ ሰጠክ በጩቤው ላይ ያለውን ሚስጥርም ሳትፈታ ጩቤውን ለጠላቶችህ አሳልፈህ ሰጠክ እንደዚህ ፈሪና ቦቅቧቃ መሆንክን አላውቅም ነበረ....አሁን ወደ እኔ ስለመጣክ ሁሉም መና መቅረቱ ነው አደራዬን ስለበላክ ይቅር አልልህም" አለው ነጭ ልብስና ነጭ ሪዙን እያሻሸ የሚያወራው አጎቱ.....ወድያው " ማሬ ጥለኸኝ ልትሄድ ነው እኔን ለማን ጥለክ እኔ አንተን ለማስታመም ከኢትዮጵያ ድረስ መጥቻለሁ እኮ እባክህ ጥሐከኝ አትሂድ" የሚል የማራናታ ምስል ተደቀነ....."ውዱ ኤስኮባር ዳግም በመንፈስም ሆነ በአካል ልለይክ መሆኑን ሳስብ ምን አለ ያን ቀን ባልተዋወቅን ብዬ አስባለሁ ግን ፈጣሪ የወደደውን አደረገ የሱ ፍቃድ ሆኖ ወደ ፈጣሪ ቀርበካል እዛ መጥቼ እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሰንብት" የሚል ምስል ገና ባልሞተው አንጎሉ ውስጥ የትርታ ምስል ተመላለሰ.... "ለመጨረሻ ጊዜ አንዴ በ380 እንሞክር አለ"ዶክተሩ....ነርሶቹም ማሽኑን ወደ 380 ቮልት ከፍ አደረጉት "1 2 3 አሁን" ድም የሚል ድምፅ ደግመው ደጋግመው ሞከሩ...... ከሳምንታት በሁዋላ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ውስጥ ከወትሮው የተለየ ግርግር ተፈጥሯል ጊቢውን ውስጥ የጋዜጠኞች ቡድን ይርመሰመሳሉ ከጋዜጠኞች በተጨማሪ የአሜሪካና የተወሰኑ ሀገር አምባሳደሮችም ይገኙበታል....ወደ ውስጥ እንዳይገቡ የተከለከሉት ጋዜጠኞች ውስጥ የሚፈጠረውን ለመስማት ቸኩለዋል.....አንዳንዶቹ ማይካቸውን ወደ ውስጥ ቀስረው ለመስማት የጓጉትም ጋዜጠኞች ሙከራቸው መና ቀረ ከደቂቃዎች በሁዋላ የስብሰባ አዳራሿ ወደ ጩኸት ተቀየረች...... #የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን https://t.me/lovestorey1 ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
4 123
16
🇪🇹ሀገር ፤ አፈር ፤ ሰው🇪🇹 "አገር ማለት ሰዉ ነው እያሉ በትዉልድህ እንቅልፍ ላይ ብርድ ልብስ ይደርባሉ።አገር ማለት አፈር ነው።ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ የሞቱት ሰዎችን ስጋ እና አጥንት አፈር ሆኖ ይሄው" አሉና መሬቱን በጎራዴዉ ጫፍ ጫር ጫር አደረጉት "አየህ አሁን አፈር አይደለም የጫርኩት የሰዉ ስጋ ነው! ሲጫር የሚያመዉ ፣ ሲወጋ የሚያቃስት ሰው ነው አፈሩ!! ይሄንን ነው ቆርሰዉ የሚወስዱት።አገር ማለት ሰው ከሆነ፣ ሰዉ አፈር ነዉና አፈርህን ሲነኩ እንቢ ልትል ይገባል! ልጄ "ህንፃ እና መንገድ አይግረምህ፣ የሰዉ ልጅ የሚሰራው የእጅ ጥበብ ሁሉ አይድነቅህ ነገም ልጆችህ ከአንተ በተሻለ ይሰሩታልና! ልጆችህ መቼም ለማያገኙት ስንዝር መሬት ግን ያለህን ሁሉ ክፈል..." "ስንዝር መሬት ሰጥተህ ዘመናዊነትን ከምታመጣ፣ ቅንጣት አፈርህን ሳታስነካ እድሜ ልክህን በዘላልነት ኑር! ለልጅህ መቀመጫውን ተዉለት። ዛሬ ተሰርቶ ነገ ለሚፈርስ መንገድ ና ድልድይ፣ ህንፃ ና ግድብ ለልጅህ ሀብት አይደለም።መሬት መሬት መሬት-ምንም ቃል፣ ምንም ስምምነት መሬትህን ካሳጣህ የታሪክ ጉድፍ ነው።መሬትህ ሲነጠቅ አጨብጭብ የሚሉህም የታሪክ አተላ፣ የማንነት ጉድፍ ናቸው! ያለህን ይባርከዉ ሲሉህ፣ ምርቃት መስሎህ አሜን እንዳትል! ከዚህ የባሰ መርገምት የለም! የተሸረፈ ባርኮት፣ ከእርግማን እኩል ነው!" አሌክስ አብረሀም (ዙበይዳ) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
4 682
15
ጠብቄሽ ነበረ (በላይበቀለ ወያ) . . የቆሸሸትሪ ፣ ድስት እና መክተፊያ ሰብስቤ አስቀምጬ ፣ በአንድ መዘፍዘፊያ ጠብቄሽ ነበረ መምጣትሽን አምኜ በናፍቆት ውስጥ ሆኜ የቆሸሸ ልብሴን ፣ ደጅ ላይ ቆልዬ ሳሙና ገዝቼ ፣ ተስፋን አንጠልጥዬ እጄን ጉሮሮዬን ፣ በአልኮል ወልውዬ ጠብቄሽ ነበረ! ጥምእያቃጠልኝ ፣ ደርሶ እንደ በረሃ ወይ አልገዛሽ ነገር መሆኔን እያወቅሽ ፣ የናጠጠ ደሃ ስትቀሪ ጊዜ ደረቅ ቧንቧ እያየሁ ፣ አዘንኩብሽ ውሃ ።።። ጠብቄሽ ነበረ ፣ ጎመን አጎምኜ ድንች አደንቼ ፣ በቤቴ ውስጥ ሆኜ አብስዬ ለመብላት ፣ቁርስ ምሳና እራት ከቤት ባለመውጣት ፣ ሀገሬን ለመሥራት ጠብቄሽ ነበረ ስትጠፊብኝ ጊዜ ፣ አዘንኩብሽ መብራት😂 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
4 203
46
ከ ‹‹ፈሮግራምህ›› ውልፍት የለም ! ( የህዝብ ወግ) (አሌክስ አብርሃም ) (ይህ ፅሁፍ ባለፍ ገደም ‹ብልግና› ቢጤ ስላለበት የማይስማማው ሰው እንዳያነበው እመክራለሁ ) አንሾ ባልታወቀ ምክንያት የምትወደው ባሏ አባተ ጋር ትጣላለች እናም ኮብልላ ወላጆቿ ቤት ታድራለች ! በበነጋታው የአገር ሽማግሌወች ባልና ሚስትን ሊያስታርቁ ሽምግልና ይቀመጣሉ ! ‹‹ ችግርሽ ምንድነው ?›› ‹‹ምንም›› ‹‹እንዴት ያለምንም ችግር ትዳርሽን ታፈርሻለሽ ?›› ‹‹ በቃ አልፈልግም ›› ‹‹እኮ ለምን ?›› አሉ ሽማግሌወች በማግባባት ሴትዮዋ ስትፈራ ስትቸር አንዲት ነገር ተናገረች ‹‹ አሱ ሰው አይደለም ዝንጆሮ ነው ›› ሽማግሌወቹ ገባቸው ! ባሏ እንደዝንጆሮ ወሲብ ያበዛል አልቻለችውም ማለት ነበር ትረጉሙ…. እናም ሽማግሌወቹ ጉዳዩን በዝርዝር እንድታስረዳቸው ጠየቁ… እ,ሷም አንዴ ከአፏ ወጥቷልና በዝርዝር ጉዳዩን ታስረዳ ጀመረ ! ‹‹ እንደው በኔ የደረሰ አይድረስባችሁ ባለቤቴ ሳያገባኝ በፊት ጎበዝ ገበሬ …. አገር ያወቀው ጀግና ነበር ታውቃላችሁ መቸስ ….ከተጋባን ጀምሮ መሬቱ ሁሉ ጦም አደረ በሬወቹ እንደተጠመዱ ትቷቸው ይመጣና እኔን ይጠምደኛል …. ሌሊት ወገቤ አያርፍ እግሬ አይገጠም ጧት በግድ ተነስቸ ያዘጋጀሁትን ቁርስ ቀመስ አድርጎ ይተውና ወደመደቡ መጎተት ነው ….ውሃ ቀድቸ ስመለስ እንስራየን አውርዶ ወዲያ ይወረውርና ‹ያዥ እንግዲህ › ነው … አልቻልኩም በዛብኝ ምነው ሸዋ ! ›› አለችና ሽማግሌወቹ ፊት አለቀሰች ! ሽማግሌወቹም ችግሯን ስለተረዱ እዛው ተቀምጦ ጉዱን የሚሰማውን ባሏን ጠሩና መከሩት ‹‹አባተ ›› ‹‹አቤት አባቶቸ ›› አለ እየተቅለሰለሰ ‹‹እንግዲህ የተባለውን ሰምተሃል እውነት ነው ሃሰት ? ›› ‹‹ኧረ ሃቅ ነው አባቶቸ ….›› ሲል አመነ ‹‹ ጥሩ እንግዲህ ጥፋት አይተንብሃል በል አሁን የምንመክርህን ስማ ›› አሉና ሽማግሌወቹ ተመካክረው በአንድ ወግ አዋቂ ሽማግሌ በኩል እንዲህ አሉት ‹‹ እንግዲህ አባተ <እንትን > እንደሆነ ዝም ብለው ቢውሉበት ቁርስ አይሆን ምሳ ርስት አይሆን ሃብት …. እየናፈቀ ሲገኝ ነው ደጉ …ይሄው አረጀንበት ከልጅነት እስከእውቀት ኖርንበት እሱ እንደሆን እያደር አዲስ ነው ከምን እንደሰራው አንድየ ይወቀው …..እና አሁንም አንተም ሚስትህን አንሻን እንዳታማርራት በ ‹ፈሮግራም › እንዲሆን ወስነንበሃል ›› ሲሉ አስረዱተ ‹‹ እሽ አባቶቸ እንዳላችሁ ….ግ…..ን ‹ፈሮግራሙ› እንዴት እንዴት ነው ›› አለ አባተ ‹‹ እንግዲህ ፈሮግራሙ እንዲህ ነው …. ቀን ቀን እቤት ድርሽ ሳትል እርሻላህ ላይ ትውልና ማታ ጀምበር ሲያዘቀዝቅ ከብቶችህን አስገብተህ ስታበቃ አንሾም ናፍቃህ ትውል የለም …..አንደዜ ! ….ደሞ ራት ተተበላ በኋላ ኩራዝ ጠፍቶ ጋደም ስትሉ ….አንደዜ ! ወደንጋጋቱ ላይ ዶሮ ሲጮህ ደሞ አንደዜ ! ሶስት ሃቅህ ነው !›› አሉት አባተ ቅር እያለው እንዲህ አለ ‹‹ እንደ…..ው ኣባቶቸ ምክራችሁ ጥሩ ነበር ግ…..ን እነደው …. ለጠራራውም ለውሃ ጥሙም ቀን ላይ አንደዜ ብትጨምሩልኝ ›› ሲል ጠየቀ አንሾ በተራዋ ‹‹ የዶሮ ጩኸቱን ብታነሱልኝ ምናለ …. ሁለቴ ካገኘ ምን አነሰው ›› ስትል ቅሬታዋን አቀረበች ! ሽማግሌወቹ ግራ ቀኙን አድምጠው ‹‹ አንሾ አንችም አትሰስች ….አንተም ከ ‹ፈሮግራምህ› ውልፍት የለም ! ከተሜው ሁሉ እንዲሁ ነው የሚያረግ ›› አሉና በውሳኔያቸው ፀኑ ! አንሾና አባተም እርቅ አውርደው ወደቤታቸው ሄዱ ! ልክ እቤታቸው ሲደርሱ ጀምበር አዘቅዝቆ ስለነበር አባተ እየተጣደፈ አንሾን ወደመደቡ ጎተታት …. አንሾም ተጣልተው ስለቆዩ ናፍቋት ስለነበር አልከፋትም ኧረ እንደውም ደስ አላት ! ‹‹ አንድ በል ቁጥር እነዳትስት ›› አለች ቀሚሷን እያጠለቀች ! አፍታ ሳይቆይ አባተ አንሾ አማረችው ! አለፍ ስትል ሳብ አደረገና እነሆ ! ሁለት ! ገና እራት ሳይቀርብ አንሾ ጉድ ጉድ ስትል ጠይም ፊቷ በምድጃው እሳት ወጋገን ወርቅ መስሎ ታየው አባተ አላስችል አለው በቃ ሳብ አደረጋና ሶስተኛውን ሃቁን አነሳ ! እራት ቀርቦ በሉና ጋደም እንዳሉ አባተ የአንሾ አርቲ እና አሽኩቲ ጠረን አቅሉን ነሳው ! ሽማግሌወች የወሰኑለትን ኮታ ደግሞ ጨርሷል እናም በጨለማው ውስጥ ቀስ ብሎ እንዲህ አለ ‹‹አንሾ ›› ‹‹ምን ፈለክ…..የዛሬውን ድርሻ ሶስትህን ጨርስሃል ነገር ትፈልገኝና ውርድ ከራሴ ›› አለች አንሾ በቁጣ ‹‹ እንደው አፈር ትሆንልሽ …..ተነገው አንድ አበድሪኝ አንሾዋ ›› አላት ያልሆነ ቦታ እየደባበሳት .....አንሾ አሰብ አደረገች እሽ እንዳትል ኩራቷ ያዛት እምቢ እንዳትል የአባተ እጅ ቀልቧን ወስዶታል እናም እንዲህ አለች ‹‹ ምን የነገውን አበዳደረህ የትላንቱስ ሶስቱ መች ተነካ ›› ትላንት ተጣልተው አብረው አላደሩም !! ወደቁም ነገራችን ስንመለስ በባልና በሚስት መሃል ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄው ሶስተኛ ወገን ሳይሆን ፍቅር ራሱ ነው ! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
3 855
62
••●🍃 ኢትዮጵያዊ ነኝ! ●🍃 ,,,,,,,,,,,, 'ላገሬ ሞቼ ሀገር የማኖር ፣ ሞት የማልፈራ የማልበገር፣ ሽጉጥ የሌለኝ ከሞላው ባገር፣ በሀሳብ ብቻ የምደራደር። ለሸፈተብኝ የማልረታ፣ በብዕር ጦሬ ትጥቅ ማስፈታ፣ አሽቼ 'ማሽር የአፍ ወለምታ ኢትዮጵያዊ ነኝ! በደም አሻራ በአንጥንት ክስካሽ፣ ድልን አብሳሪ ለወገን ደራሽ፣ አለኝታ ለ'ናት እንባዋን አባሽ፣ ከኋላ ሲሉኝ ከፊት የምገኝ፣ የኢትዔል ልጅ ኢትዮጵያዊ ነኝ ።! የሰው መገኛ የስልጣኔ፣ ችጋር ያልረታኝ የኖርኩ በወኔ፣ "ሞተሃል" ሲሉኝ ኖሬ የምገኝ፣ የሀበሻ ልጅ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ለጀግንነቴ አለም ምስክር፣ ወኔ ነው ልኬ ጅግን ለሀገር፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ደመ መራራ፣ የሀበሻ ልጅ የወርቅ አዝመራ ። ጠይቆ ላጣ፤ ግራ ለገባው ለጠፋው ውሉ፣ የኩሽ በረከት ሀገር መባሉ፣ የአምላክ ፀጋ ታላቅ ማንነት፣ ስውር ቅኔ ነው ኢትዮጲያዊነት !!! ✍ቶፊቅ መሀመድ @Tufaw_muhe ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
4 132
25
ዘለዓለሜ ቅፅበቷ ውስጥ ተደብቋል!😔
4 460
3
የልጅ ነገር ቶሎ በስሎ ለመጋገር፣ መ ቸ ኮ ሏ..... ጥሬነቷን አላወቀች በሀሳብ ላይ ቡኮ ሀሳብ ለቀለቀች፣ ልምሻ አእምሮ ልምሻ እጅ እግሯ ቢደነድን ቢጠነክር የእናቷን ጡት መጋተሯ፣ እሷነቷስ ወተት መጋት ተጠይፋ ጥሬ ስጋ ትሸጣለች በዓደባባይ ተሰልፋ። የአፍላ ነገር......... ቶሎ በስሎ ለመበላት ተበልቶ አልቆ ለመጋገር። ******* አዝጎ : የብስል : መሀል : ጥሬ : መሆን። የበሰለው : ወርቀዘቦን :ሲጎናፀፍ: ያልበሰለው :ትድግና : ልብስና ትራሱ የሱ እንደሆኑ : ለመገመት : አያዳግትም። እህልን: በማጭድ : ገዝግዞ : ጎተራ የሚከምር : ገበሬ : ይመስል አገቦአተውን እንደህል : ለሚወቁ ወፈሰማይ አንበጦች ሽቅብ : አንጋጠን : ብናይ : ማጠጣተው ቁልጭ : ብሎ : ይታይ : ነበር። እሷም : አንገቷን : ቀና አድርጋ ብታማትር ቢራቢሮ : በአክናፉ : ነፋስን ሰንጥቆ ሲቀዝፍ : ተመለከተችና: በቀለሙ ተሳበች የመጣበትን : መንገድም : ቢያሳያት : አባጨጓሬነቱ : ኮሰኮሳት። ህመሙንም : በወርቅ ቅብ ደጉሶት ነበርና... ደመመራራነቱ : ገዘፈባት። መች :እሱ ቆዳውን : ሊያስወድዳት :ሻተና እሱ ቋንጣ እሷ ለንቋንጣ ሆነው እንጂ!! ✍️ቅዱስ አርዮስ✍️ 🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Show more ...
5 452
19
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 9 ✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ "" "" መኪናው ሲገለበጥ ግማሾቻችን ደነዝዘን ግማሾቻችን ጮክን ሌሎቻችን ደሞ ለማምለጥ በመስኮት ሞከርን ግን አልሆነም መኪናው ተገልብጦ ሁላችንንም ጣር እና ስቃይ ላይ ሆንን በጣም ተስቃየን አንዱ ጓደኛችን በትንሽ ማቃሰት በኋላ ህይወቱ አለፈ ከዛም በተራ በተራ ቀስ በቀስ የጣር ድምፅ ጠፋ ካንደኛው ጓደኛዬ በስተቀር። ከዛም ከብዙ ስቃይ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች መጥተው ወደ ጣሬዛ እያርጉ በመኪና ይዘውን ሄዱ ኡፍፍፍፍፍፍ ስቃይ ውስጥ ሆኔ ከጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩትን እያስብኩ አዘንኩኝ በጣም እወዳቸው ነበር ልክ እንደ ነብሴ ከ ነብሴ እኩል ብወዳቸውም የራሴን ነብስ እንጂ የእነሱን ማትርፍ አልቻልኩም ለነገሩ የኔንም ነብስ ፈጣሪ በጥበብ ነው ያተርፍው የአንደኛው ጓደኛዬን ጭምር አጋጣሚ እኛ ሁለታችን ከ ጋቢናው እና ከኋላኛው ወንበሮች መሀል ያለው ወንበር ላይ ነበር የተቀመጥነው መሀለኛው ቦታ ብዙ አልተጎዳም አለ አዳም ባዘነ ድምፅ ዲና እየሰማች ሳታስበው ማልቀስ ጀመርች አልቻለችም አዳምም አብሯት አለቀሰ አዳም እንባውን ጠርጎ ወደ ወሬው ተመለስ እምምም እና ከዛ እኔ ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ብቻ የሆነ ጊዜ ላይ ካለሁበት ድንዛዜ ስነቃ ሆስፒታል ነኝ ሳሚን አየውት ሳሚ ማለት መዝናናት የሚባል ነበር በጭራሽ የማይወድ እና ከራሱ ጋር ጊዜ የሚያሳልፍ ሰው ነው በእዛ ምክንያት እኛ ለመዝናናት ስንሄድ እሱ አልመጣም ነበር የሚለን ሁሌም እንዲህ አይነት ነገሮች ላይ አይሳተፍም ሳሚን ሳየው ፈገግ አልኩኝ እሱም ፈጠን ብሎ እ አንዴት ነክ ብሎ ረጋ ባለ መልኩ ጠየቀኝ እኔም በፊቴ ደህንነቴን ገለፅኩለት ነርስ ጠርቶ እስኪመጣ እርፍት እንዳደርግ እና አንድ ጓደኛው ከሻይ ቤት ቡና ልታመጣ እንደሄደች እና እንደምትመጣ ነገረኝ ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ እሺ አልኩት ከዛም ሄደ እንደሄደ በእጇ 2 ሻይ ይዛ መጣች ሳያት በጣም ደነገጥኩኝ በጣም ልቤ ሲመታ ክፍሉን ያናወጠው መሰለኝ የፈጣሪ ያለ እንዴት መጣች ብዬ ገረረመኝ ሄዋን ነበርች ደስስስ አለኝ ስታየኝ ሞቅ ደመቅ ባለ ደምፅ እንዴዴዴዴ አዲዬ ፍቅር ነቃክ ብላ ጭምቅ አድርጋ አቅፋኝ ማውራት ጀመረች የድምጿ ጩሀት እና የተጫነችኝ ቁስሌን መቆጣጠር እስኪሳነኝ አቅፍኝ ስማኝ አዲዬ አስደነገጥከን እኮ የኔን ውድ እያለች ትጨምቀኝ ጀመር ቢያመኝም ህመሜን ዋጥ አደርኩት ምክንያቱም ስታቅፍኝ ካመመኝ ይልቅ ስላቀፈችኝ ብቻ ደስታዬ በጣምም ትልቅ ስለነበር ከዛም ሁለቱን አይኔን ግንባሬን ሁለት ጉንጮቼን እና አገጬን አንገቴን ያለ ፋታ እያፈራርቀች ሳመችኝ ደስታዬ ወደር አልነበርውም የቁስሌም ህመም በጣም አየለብኝ እእእእ ይቅርታ ግን ቁስሌን ስላት ኣ ይቅርታ በጣም ስለተደስትኩኝ አላስተዋልኩም የሆነ ነገር ልንገርክ አለችኝ እሺ አልኳት በጉጉት አፍ አፍፏን ማየት ጀመርኩኝ ቀኝ እጄን ብድግ አድርጋ ልቧ ላይ አደርገችው የልብ ምቷን እጆቼን አስጠግታ አስዳሰሰችኝ ልብዋ በጣም ይመታል እጄ ከ አካሏ ጋር ሲነካካ ትንፍሽ አጠራት ዲና አስቆመችው እና እሺ እና አንተስ አለችው አዳምም ቀጠለ የኔን ነገርማ ተይው እንደ ውሀ ፈስሼ እንደሻማ ቀለጬ ምንም አላልኩም ከዛ እሷ በድጋሚ አይኔን ትኩር ብላ አየችው አየዋት የሆነ ነገር በለኝ እንጂ አለችኝ ምን ልበልሽ አልኳት በፍቅር አይን አያየዋት አዲዬ አፍቅርካለው ካላንተ መኖር አልችልም እያልኩክ እኮ ነው አለች እንባ እየተናነቃት እየተናነቃት መጣና ማልቀስ ጀመርች በጣም ደነገጥኩ እና በድንጋጤ ብድግ ብዬ እንባዋን ጠርኩላት አቀፍኳት ለምን ታለቅሻለሽ አልኳት እንባዋን በእጄ እያበስኩ በጣም ደስስስ ብሎኝ አለችኝ እኔም በምኑ ስላት እንደማፍቅርክ ስነግርክ አይንክ ውስጥ አንደምታፈቅረኝ ስላየው አላስቻለኝም እውነተኛ ግን ያልጠበኩት መልስ ስለሆነ በድጋሚ ደነገጥኩኝ ምንም ቃል ካፌ ሊወጣልኝ አልቻለም በውጤ ግን ለካ ፍቅር እንዲ ነው? አልኩኝ ከዛም ህመሜ ተነሳብኝ አአ አ አአ ስል ድንግጥ ብላ ምነው ምን ሆንክ ስትለኝ አይ ምንም ትንሽ አመመኝ አልኳት እሺ እርፍት አድርግ በላኝ አመቻችታኝ ተኛው ግን እንቅልፍ አልወሰደኝም ከዛ ትንሽ ቆይቼ እእ ስል ከወንበሯ ብድግ ብላ ምነው አለችኝ አፍቅርሻለው ያላንቺ መኖር አልችልም እንዳትተይኝ ልልላት አሰብኩና ፈራው አይ ተይው ምንም አልኳት ልቤ ግን ያለ ማቋርጥ ይመታል ደስስስ እያለኝ መጣ ከዛ ስናወራ ሰው የሰማን ይመስልሻለል አልኳት እኔጃ ግን ለምን ጠየከኝ ስትለኝ አይ ምን አልባት ስላት ፊቷን አኮሰታትራ እ መልስልኛ ምን ልትለኝ ነው ሰው ከሰማስ ምን ይሁን እ ንገርኛ አለች እየጮከች ድምጿ እንኳን ጮሃበት እንዲሁም በጣም ጮክ ያለ ስለሆነ ሽምቅቅ ድንግጥ አልኩኝ ክትክት ብላ መሳቅ ጀመርች ግራ ገብቶኝ አፍጥጬ ዝም ብዬ አያት ጀመር ሳቋን ገታ አድርጋ አትደንግጥ የጮኩብክ ላስደነግጥክ ነው ደሞ ተሳክቶልኛል አይደል አለችኝ እኔም ቁስሌን በማይጎዳ መልኩ ስቄ በጣም ጓበዝ ነሽ አልኮት አይዞክ አትደንግጥብኝ የኔ ፍቅር ጓደኛክ ደሞ ነገ ነው የሚመጣው ቅድም ቡናውን ይዤ ወደክፍል ስመጣ አግኝቼው እንዳይመጣ እና እኔ ካንተ ጋር ብቻዬን መሆን ስለምፈለግ እንዳይመጣ ነግሬዋለው ሀኪሞቹም ካላመመክ አይመጡም ማለቴ ካልጠራናቸው ጠዋት ነው የሚመጡት አለችኝና በል አሁን ተኛ ብላ አደላድላ በድጋሜ አስተኛችኝ ግንባሬን ሳመችኝና ወንበሯ ላይ ልትቀመጥ ስትል እጇኝ ያዝ አረኳትና አጠገቤ ሁኚ አልኳት ት አላርም ቅጠሪና ዶክተሮች ሳይመጡ ትነሻለሽ አልኳት ፈገግ እያለች እሺ ብላኝ ለሊቱን ሙሉ ተቃቅፍን ተኛን ከሚያፍቅሩት ከሚወዱት ጋር መሆን እንዴት ደስስስ ይላል ። አላርሙ ጩኸ አልስማነውም ነበር ጠዋት ዶክተሩ ሊያየኝ ከ ነርሷቹ ጋር ሲመጣ አየን ሁሉም በስሱ ፍገግ ብለው ቁልቁል ሲያዩን ጀመር አይኔን ስገልጥ እና ሳያቸው ደነገጥኩኝ ሄዋንም ተነሳች ግን እሷ ምንም አልመስላትም ደና አደራቹ ብላ ዘብነን ብላ ጉንጮቼን ስማኝ እርቦኛል ቁርስ በልቼ እመጣለው ውዴ ብላኝ ወጣች ብሎ አዳም ንግግሩን ገታ። ዲና አዳምን ኮስተር ብላ እያየችው እንዴ ቀጥልልኛ አለችው ብዙ አስወራሽኝ የቀር ረው ለነገ ይሁንልሽ ነገስ ማን አለው አላት እሺ አለችው ዛሬ አላስጨነቀችውም ሄዋን ክፍል ተያይዘው ገቡ። ሄዋን ጣራ ላይ አይኗን ልክ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ስው ተክለዋለች አተኩሮም ሆነ ሳያተኩር ላያት አንድ በጣም ትንሽ ነገር ጠፍታት ወዴትም እንዳትሄድ ጠብቂያት የተባለች ትመስላለች አዳም እና ዲናን አላየቻቸውም በመጨርሻ ዲና እህም እህም ብላ ከተመስጦዋ አነቃቻት ሄዋንም ሁለቱንም እያፈራርቀች አየቻቸው ከዛም አዳም ላይ አይኖን ጥላ ቀርች አፈጠጠች አስተያየቷ የፍቅር ነው ልክ ከአደጋው በፊት እንደምታየው አስተያየት አዳም እንባው በአይኖቹ ሊወጡ ክፉኛ ታገሉት ታገሉት ከዛም አዳም ክፍሉን በፍጥነት ጥሎ ወጣ ሄዋንም በደከመ ድምፅ እናንተ ማናቹ አለቻቸው ዲና ምን እንደምትል ጠፍባት ተርበተበተች ከዛ...... ✨ይቀጥላል........ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 112
28
~~~ተምረው ገደሏት ============== የተማረ ይግደለኝ~በምትለው ተረት ዶክተር ፕሮፌሰር ~ሊቅ ናቸው የተባሉት ኢትዮጵያ ሀገሬን~እንደተመኘችው~ተምረው ገደልዋት ~ ጥሪቷን አሟጧ~ካላት ላይ ቀንሳ አባብላ አስተምራ~በቸር እጇ ዳብሳ እየተቀበለች~ሲመረቁ በእቅፍ~በጉንጉን አበባ የተማሩት ናቸው~ሚወጒዋት ከጀርባ ~ በድህነት አቅሟ~ከእጇ እየጎረሱ የተማሩት ናቸው~እጇን የሚነክሱ ✍️✍️✍️ ከድር አሊ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 234
37
ደሞ እንኩ ዜማ አንቺማ ለኔ ብርሀኔ 🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥

file

5 510
27
ምን ያረጋል ቆይ ስሞታ? ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, በልተን ምንባላ ችጋር አናቅ ወይ ተድላ ጌታ ጌታ ጥዋት ማታ ምን ያረጋል ቆይ ስሞታ ሰላም ብለን ስንታገል በዘር ድንበር ምንጋደል ፍቅር ፍቅር ብለን ቀን ለሊት አደግድገን የምንቆም ተራርቀን አስታማሚ ተመስለን የዳነ ቁስል አመርቃዠ ነን ሰርግ ሲባል ስንደግስ ሞተ ሲባል ስናለቅስ በዛው ልክም ምናፈርስ የምድሩ የላይ ጌታ ብለን ምንጮህ ጥዋት ማታ ዝቅዝቅ የዶሮ ሸክም ክፋታችን አያገግም ወይ አይበቃን አናቆምም እያየነው ባአይናችን እየሰማን በጆሮአችን ለየቅል ነው ተግባራችን ነጋ ስንል ቢጨልምም ሰጠን ስንል ቢነፍገንም ክፋታችን አያገግም ጌታ ጌታ ጥዋት ማታ ምን ያረጋል ቆይ ስሞታ ካየን በላይ ማንሊያሳየን ከሰማነው ማን ሊነግረን አጥፊ ሆነን አልሚ ናፍቀን ጥያቄ እንጂ መልስ የሌለን የለመነው ማታ አልቅሰን ያገኘን ለት መች ታወሰን እንዴት ብሎስ ይታረቀን አድሮ ቃሪ ታጥቦ ጭቃ የማንበስል የማነቃ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ፍይዳቢስ ሆነን ዙዋሪ ጌታ ጌታ ጥዋት ማታ ምን ያረጋል ቆይ ስሞታ? ✍ቶፊቅ መሀመድ @Tufaw_muhe ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 430
31
ወድጄ እኮ አዉቃለሁ። 'ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ፍቅር ደርሶብኛል' ይል የለ ከያኒዉ። የእዉነት!! ብዙ ጊዜም የወደድኩ መስሎኝ ከስሜቴ ጋ ድብብቆሽ ተጫዉቼ ያለፍኩባቸዉ ጊዜያት ቁጥር አልባ ናቸዉ። የመጣዉን ጊዜ ሳየዉ ያለፈዉ ቀላልነቱ በደንብ ታየኝ። ብዙ ጊዜ ለመዉደድ አልታገልም። ለመወደድም እንደዛዉ። ዝም ብሎ ፍስስ ... ልስልስ ያለ ነገር እወዳለሁ። መያያዝ እንጂ መተናነቅ አይስበኝም። ከተወኝ ጋ ፊትህን መልስ ብዬ ዳኛ ፊት አልቆምም። እንዲያዉም እንዲያዘልቅለት ፣ በመሄዱ እንዳይቆጭ ሱባኤ እገባለት ይሆናል። ሂሂሂ! መታገል ያደክመኛላ!! ከወደደኩት ጋ መቋሰል አልሻም። መድሐኒቴ ብዬዉ ከነበረ ሰዉ ህመም አልሸምትም። ሲደላ ብዙ ነገር ቀላል አይደል? ትዉት ሲያደርጉት ትዉት ፤ ራመድ ሲሉ ሰበር ሰካ አይደል የሚሆነዉ? ቢኳሉት ድምቅ ፣ ቢለብሱት ስክት ይል የለ? ይገርማል። ዉስጣችን ስንት የተሸመነ ስሜት ያላቸዉ ማንነቶችን ይዘን እንደምንዞር። ቀላል ነዉ ያሉት ከአለት ሲጠነክር ምን ይሉታል? ... የመጀመሪያዎቹ ሰሞን እንደ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ትከሻ ለትከሻ ተሻሽቶ የማለፍን ያክል ነበር ቅርርባችን። ከሁለት ምልልስ ያልዘለለ ሰላምታ ብቻ። ስንቆይ እንደ ጆንያ ያለ እህል እንደማይቆመዉ ያለፈገግታዉ መቆም አቃተኝ። ከእናቷ ተለይታ እንደምትያዝ ጥጃ ሲለቋት ወደ እናቷ ጡት እንደምትሮጠዉ፤ ነግቶ ምድር ከሰማይ ስትላቀቅ ወደ እሱ ለመሄድ መደፋት ቀረሽ መጣደፍ ዉስጥ እገባለሁ። ፈገግ እላለሁ። ስለማገኘዉ ፣ ላወራዉ ስለሆነ ፣ ሲስቅ ልሰማዉ ስለሆነ እና በእሱ ዙሪያ ስለማገኛቸዉ መልካም ነገሮች ሁሉ እያሰብኩ እፈግጋለሁ። ምን እየሆንኩ ነዉ ብዬ ራሴን መታዘቢያ ጊዜ እስከማይኖረኝ። ህልሞቻችንን አንድ ላይ ላስር ቸኮልኩ። ስቸኩል ነገር ሳትኩ። የሆነ ነገሬ ጎደለ። የቱ ጋ? እንጃ!! ... ብዙ ያልነገርኩት ናፍቆት አለኝ። ሲተኛ ስለተናደድኩባቸዉ ፤ አሁን በነቃ አሁን በነቃ እያልኩ ስላሰብኩባቸዉ ምሽቶች ፣ ሲደክመዉ ስለሚያምር ድምፁ ፣ ስለሚያስቀኑኝ ትዝታዎቹ ፣ አካላቸዉ መሆን ስለምመኛቸዉ ህልሞቹ አልነገርኩትም። ገና መቼ ወድጄዉ ጠገብኩ? የመዉደዴ ሀገር መሃል ይዤ የቆምኩት ያልተቀባባ ፍቅር ነዉ። አልኳልኩትም። ስላልኳልኩት አያምር ይሆናል። ነበርን ለመባባል ደርሰናል? መቼ ተራምደን የመራራቅ ኩርባ ጋ ደረስን? አንተ ሆይ ያዘኝ! አንተ ሆይ ያዘኝ። የምፈራዉን መታገል እያደረኩት ነዉ። ፊትህን መልስ እያልኩ ... ሱባኤ ልገባ ነዉ። ከቀናኝ እንደ እስከዛሬዉ ቀኔ ላይ ልኩለዉ። #Ruth Habte Mariyam ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
4 658
61
#ነግሬሽ_ከበረ! ፡ ሴት ክብሯን ረስታ፣ ጭኗን እንዳታምነው ሁሉን ያጣል ብዬ፣ የሁሉም የሆነው!!! ።።።።።።።።።።።። ነግሬሽ ነበረ ውበት ደም-ግባትሽ፣ ሁሉን እንደሚስብ የወንድ ልጅ አይን... ከተበተነበት፣ እንደሚሰበስብ ነግሬሽ ነበረ ትንሽ ስትዘነጊኝ፣ ብዙ እንደማስብ!!! ።።።።።።።።።።።።።። ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ ሳሙና ነው ብዬ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ እድፋም ስሜቶችን... አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!! ።።።።።።።።።።።።።።። ነግሬሽ ነበረ... ሴት ልጅ ስታማርጥ፣ ለ'ራሷ ምራጭ ናት በክብር ነው እንጂ... በመውለድ አይደለም፣ የሚኮነው እናት። ነግሬሽ ነበረ ክብረ-ቢስ ህይወቶች፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም ነግሬሽ ነበረ እናትነት ስሟ ከክብሯ ነው እንጂ፣ ከልጇ እንዳልወጣ ወልዳም ምንም ነች፣ ሴት ክብሯን ስታጣ። ።።።።።።።።።።።።።። ነግሬሽ ነበረ ሴት ክብሯን ስትጥል፣ እድሜዋ ይሄዳል የወንድ ልጅ ቤቱ... የሴት ልጅ ውበት ነው፣ ካየበት ይለምዳል። ።።።።።።።።።።።።።።። ነግሬሽ ነበረ... ጭንሽ ጭንቅላቴን፣ ከቶ እንደማይበልጠው ቁንጅናም ይረክሳል! ብቻውን እንዲቀር፣ ሁሉም ከመረጠው! ።።።።።።።። ብነግርሽ ብነግርሽ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ "ሰደበኝ" በማለት፣ ታወሪያለሽ አሉ ልክ ነሽ አንዳንዴ እውነቶች ውሽት ፊት፣ ስድብ ይመስላሉ። ግን እነግርሻለሁ፣ ዛሬም ሳልታበይ ነግሪያት ነበር ስል፣ አንቺ "ሰደበኝ" በይ። ።።።።።።።።።።። ግን እነግርሻለሁ... ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል፣ ውበቷ አይመችም ሁሉም ያፈቅራታል፣ አንዱም ጋር የለችም። _//_____ ገጣሚ፦ በላይ በቀለ ወያ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 033
91
😘ለፍቅር ስል😘 🔥ክፍል አስራ ሁለት ✍️ደራሲ፦ጎስ """ """ """ """ ክፍሉን የሲሊንደሩ ጋዝ ሽታ አወደው.....የጋዙን ሽታ ተከትሎ ጭስ ተተካ...ከዛ በሁዋላ የሚሆነው ነገር በሙሉ ግራ ገባኝ ነገሮች በፍጥነት ተለዋወጡ ጭምብል ያጠለቁ ሰዎች መሳርያ ደግነው ወደ እኛ ሲመጡ በጋዙ ሽታ እና በጪሱ ወደ መሬት ተዝለፍልፌ ወደኩ ለመጨረሻም ለመጨረሻ ጊዜ የተመለከትኩት ጭንብል ያደረጉት ሰዎች ወደ ፎቁ ሲወጡ ነው.......እራሴን ከሳትኩበት ስነቃ የክፍሉ እቃዎች ተመሰቃቅለዋል ሰዎች እኔን ከበው እስክነቃ ይጠባበቁ ነበረ...."አዎ ይሄ ነው ሌባው" አለ ሰለሞን እጁን ወደ እኔ እየጠቆመ....የሚሆነው ነገር ግራ ገብቶኛል ሰለሞን እራሱ እየመራ እንዳላመጣኝ አሁን እኔን እራሴን ወጥመድ ውስጥ ከተተኝ....ሌባ ብሎ ሰዎች በተሰበሰቡበት ጣቱን እኔ ላይ ቀሰረ...."አዎ ጠዋት ሰፈሩ ውስጥ ሲገባ ተመልክተነዋል አዎ ወዘናውም የሌባ ነው...በዛ ላይ ስለት ይዞ የሚዞረው አደገኛ ተዋጊና ወሮበላ ስለሆነ ነው" እያሉ አብረውት የነበሩት እና ጠዋት ወደ አፖርትመንቱ ጊቢ ስገባ በጥርጣሬ አይን ሲመለከቱኝ የነበሩ ሰዎች ወሬውን አጋጋሉት...የነሱን ማጋጋል የሰማው ሰለሞን እዚህ እሱን ከበን ከምንቆም ለምን ለፖሊስ አናስረክበውም" አለ ሁሉንም በጥያቄ አይን እያየ...."አዎ ይወሰድ ፖሊስ ይጠራና ቀፍድዶ ይውሰደዎ ማንም ነጫጭባ እከካም ሰፈራችንን መርገጥ እንደሌለበት ማሳየት አለብን" አሉ ሁሉም ለፖሊስ ስልክ ለመደወል እያነሱ....የሚሆነውን አይኔን እያቁለጨለጭኩ ከመመልከት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ግን ደሞ በአይምሮዬ ላይ እየደጋገመ ይሄ ነጫጭባ መናጢ ደሀ ሰፈራችንን መርገጥ የለበትም የሚለው ንግግራቸው ልቤን አደማው ሁሉንም የተሰበሰቡትን እዚሁ ብፈጃቸው ብዬ ተመኘሁ.....ቆይ የሀብት መለኪያው ምንድነው....ገንዘብ ስልጣን ወይስ ዝና? ያላቸው ገንዘብም ሆነ ሀይል ደስታን ሊያጨልም ይችል ይሆናል እንጂ ደስታን አይገዛም.....ፍቅር ደስታ መረዳዳት ማህበራዊ ኑሮ ያለው በደሀው ማህበረሰብ እንጂ በሀብታሙ ማህበረሰብ ወንድ አይደለም ያለኝ አጎቴ ታወሰኝ....አዎ አጎቴ ልክ ነበረ በሀብታሞች ሰፈር በግሎባላይዜሽን እና በአጓጉል ልማድ አብሮነትን ጥለዋል...."ለፖሊስ አትደውሉ እኔው አስረክበዋለሁ...ጩቤውን ስጡኝ" ብሎ የፊጥኝ የታሰረውን እጄን እያንከዋለለ ይዞኝ ወደ መኪናው ወሰደኝ አሱን ተከትለው ሁለት ሰዎች ወደ እሱ መኪና ገቡ....በንዴት ብዛት መናገር አቃተኝ ከሱ ጋር የተገናኘውበትን ቀን እየረገምኩ ብቻ ሰዉነቴ ወባ እንደያዘው ሰው ይንዘፈዘፍ ጀመረ.. ወደ ፖሊስ ጣብያ በድንገት መኪናውን አቁም "ትሰማኛለክ ወንዴ አሁን ተራው ያንተ ነው" ብሎ ኖክያ ገና ስልክ ማምረት የጀመረ ጊዜ ያመረተውን ስልክ አቀበለኝ... ከወደዛኛው ጫፍ በጎርናና ድምፅ "ኤስኮባር ውዴ እንዴት ነህልኝ አሁን የንግስናህ ጊዜ መቷል" አለኝ....የሰማውትን ቃል ማመን አቃተኝ ከአመታት በፊት የሚነገረኝ ንግግር ቃል በቃል ተደገመልኝ...."በላይ ምን ፈለክ ደሞ?" አልኩት በብስጭት... "ከኬንያ፤ከኤርትራ እና ከሱዳን" የሚገቡ አርባ ቶን አሽሾች አሉ...እነሱን አሽሾች ወደ ኢትዮጵያ አስገብተህ ለኤንባሲ ሰዎች የተወሰኑትን ታድላለህ የተቀረውን" ብሎ ፀጥ ረጭ አለ በላይ ወደ አሽሽ አዘዋዋሪነት እንድገባ ያደረገኝ ሂወቴን መላ ቅጡን እንዲወጣ ያደረገኝ ሰው..... "አልችልም አላደርገውም እኔ ከዘመህ በሁዋላ እናንተ በምታስገቡት አሺሽ ብዙ እንቡጥ ልጃገረዶች እድሚያቸው እንኳን ወደ 15 ያልተጠጉትን ተማሪዎች ለእነዛ ቆሻሻ ዲፕሎማቶች መጫወቻ እንዲሆኑ አላደርግም" አልኩት አሺሹን በየትምህርት ቤት በር ላይ እያደሉ እድሚያቸው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ እንስቶችን ወደ ወሲብ ንግድ ያስገቧቸዋል የሚገርመው ገና ባልጠነከረ ገላ ላይ ጨረታ የሚጫረቱት ባለስልጣናቶች ናቸው....ገና አለምን ሳያዩ ክብረ ንፅህናቸው ሀገራችንን ወክለን ነው የመጣነው በሚሉ ዲፕሎማቶች ይጎድፍል....በወንዶቹ ላይ ተመሳሳዩን ነው የሚሰራው....በሀገሪቷም ግብረሰዶምን እያስፋፋ ያሉት እነዚሁ ዲፕሎማቶና እነሱ በሚያስመጡት አሺሽ ነው.... "ለሱ እንኳን ፈቃድ አልሰጥክም ያንተ ሰዎች ያሉት እኔ ጋር ነው" አለኝ ከጣራ በላይ እየሳቀ.... "እነማን ይሆኑ የኔ ሰዎች ውዱ አለቃዬ" አልኩት እኔም እየሳኩ.... "መንትዮቹና ያንተ ውዷ ትርታክ ናቸው" አለኝ "ምን?" ብዬ በድንጋጤ ከወንበሬ ላይ ስነሳ የመኪናው ጣራ አናቴን ብሎ ወደ ነበርኩበት መለሰኝ....."እንዳልኩህ ነው ስራውን የማትሰራ ከሆነ መጀመርያ ሶስቱንም እየደፈርኳቸው በቪዲዮ ቀድቼ ቅጂውን የኢንተርኔት አውታሮችን እንዲያጨናንቅ ነው የማደርገው....በመቀጠል ደሞ ለቤተሰቦቻቸው ቪዲዬውን እና አስክሬናቸውን አንድ ላይ እልክላቸዋለሁ"አለኝ "እሺ እነሱን አትጉዳቸው እኔን እንደፈለክ አድርገኝ እኔ ስራውን እሰራለሁ ሁሉንም ለኔ ተወው.....ትርታዬ ቁስለኛ ነች እባክ ተዋት ማራናታም ቢሆን እራሷን አታቅም ዳግም አትግደላት" አልኩት እንባዬ ከአይኔ ላይ ያለከልካይ እየወረደ.... "ክክክ የወሀ ሆነካል ማለት ነው ኤስኮባር ትርታክ እኮ አንድም ጭረት አልነካትም እኛ ነን እንዲደውሉልክ ያደረግነው...አንተን ማጥመጃ ነው እንጂ ትርታክም ቢሆን ሆስፒታል አልገባችም" አለኝ....ከዛ በሁዋላ ሁሉንም ትዕዛዝ ከሰለሞን እንድበቀል ነግሮኝ ስልኩን ዘጋው ሰለሞንም ወደ ሞያሌ የሚወስደኝን መኪና አዘጋጅቶ ትዕዛዝ ሰጠኝ..... በሰለሞን አማካኝነት የማራናታን ህይወት ለመቅጠፍ የመጣውት ልጅ አሁን በሰለሞን አማካኝነት የፖሊስም ሆነ የህሊነሠ ታዳኝ ሆንኩ....... ከዚህ በሁዋላ ሶስተኛ ወገን ነው ትረካውን የሚቀጥለው... ሞያሌ ፀሀዩ ክርር ብሏል ለወንደሰን አስቀድሞ በዲፕሎማቶች በተዘጋጀለት መኪና የከተማዋን ወጣ ገባ እያጠና ነው...ድንበሩ በስንት ሰአት ተከፍቶ ስንት ሰአት ዝግ እንደሚሆንም ጭምር እያጠና ነው ጥናቱ የሚያካትተው ከኬንያ የሚነሳው አስር ፖውንድ ኮኬይን በኬንያ ፖሊሶች እንዴት ሳይያዝና በቀላሉ እንደሚያመልጥ ነው ለዚህ ደሞ ኤስኮባርን እንዲያግዘው በኬንያ ያለ ኪንግ የሚል ስም የተሰጠው ህቡ ነው.....በሞያሌ የማይሸጥ እቃ የለም መሳርያ እንኳን እንደ ሰልባጅ ነው የሚቸበቸበው.....የኬንያ እንስቶች ከሀበሻ ወንዶች ጋር ተገናኝተው የሀበሻ ወንድን የሚያወድሱበት ከተማ ነው.... ኤስኮባር በዚህ ተግባሩ ለ አስራ ዘጠኝ ቀናትን ከቆየ በሁዋላ ወደ አጋዡ ህቡው ወደ ሆነው ወደ ኪንግ ግዛቶች ነጎደ...ኪንጎች በሱማልያ ከፍተኛ የሆነ የመሳርያ ሽያጭ ድርሻ ያላቸው ሲሆኑ ዋነኛ አጋራቸውም አልሸባብ ነው..... "ኤስኮባር ማለት አንተ ነክ?" አለው የኪንጉ ዋና መሪ የያዘው ፎቶ የኤስኮባር መሆኑን አይቶ ለማረጋገጥ ያህል... "አዎ እኔ ነኝ" አለው ኤስኮባርም በልበ ሙሉነት የኪንጉን መሪ እያየ... "አስማር እባላለሁ የኪንግ ህቡ መሪ ነኝ አንተስ" አለው ዳግም የኤስኮባርን ማንነት ለማረጋገጥ በሚመስል መልኩ...
Show more ...
5 855
27
"ኤስኮባር እባላለሁ" አለው እሱም ፊቱን እንዳጨፈገገ... "የምትመራው ህቡስ ስም ወይስ ተላላኪ ነህ?" አለው አሁንም ከሹፌሩ ጎን የቆመው የማፍያዎች መሪ.... "እኔ የምመራው ህቡ የለኝም እኔ በሀይል አላምን ከዛ ይልቅ በጭንቅላት ነው የማምነው" አለው ቅጭም ብሎ.... "ለስሙ የታላቁን ኤስኮባር ስም ነው የያዝከው ግን ደሞ አንድም ሀይል አልፈልግም ትላለህ ይሄ እኮ ፊልም አይደለም ለመጀገን የምትሯሯጠው ይሄ እፅ ከተያዘ የምንከስረውን ኪሳራ ታውቀዋለህ እንዴ" አለው....ግን ኤስኮባር መልስ ሳይመልስ የኬንያ ፖሊሶችና የደህንነት ሀላፊዎች ከበባቸው....ተኩስም ከፈቱባቸው በዛ መሀል ኤስኮባር አቃስቶ.... #የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን https://t.me/lovestorey1 ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 789
14
🍃 ጠብቃት ብለወኝ ●🍃 ,,,,,,,, ጠብቃት ብለወኝ ከመንገዱ እዳር ስጠብቃት ነበር ቆሜ ያለአዳር አሁን ግን አያኃት ለሌላ ስትዳር ✍ቶፊቅ መሀመድ (@Tufaw_muhe) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 909
37
ወግ መፃፍ ለምን እንዳቆምኩኝ... ✍ሚካኤል. አስጨናቂ ነገሩ እንዲህ ነው! .... አንድ ቀን ሚስቴ እንደ ሲኦል እሳት የሚፋጅ ፍርፍር ሰራችልኝ...ያፈላችው ሻይ የጣናን ቱሪስት በጀልባ አንሳፎ ወደ ደሴት ለመውሰድ የተዘጋጀ በሚመስል ሰፊ ኩባያ አቀረበችልኝ ምናምን የሚል ቀደዳ የታከለበት ፅሁፍ ሞነጫጭሬ ነበር ። ፌስቡክ ላይ በሽ ላይክና ኮመንት ሸቅዬበትም ነበር ። አንድ ወግ ፀሀፊ በምናቡ በሚፈጥራቸው ካራክተሮች ሰክሮ ብዙ ሊቀላምድ ይችላል ። ብዙ ሊበጠረቅም ይችላል ። ይሄን ህዝብ ለማሳቅ ብብቱ ውስጥ ገብቶ የሚኮረኩረው ቀለም መጣል የግድ ነው ። የተፃፈው ሁሉ የወግ ፀሀፊው ታሪክ የሚመስለው ብዙ አንባቢ ደግሞ አለ ። ባለቤቴ ከነሱ ውስጥ አንዷ ነች። አንዳንዴ ስናደድ አንቺ የንግድ ፍቃድ ያወጣሽ ላይሰንስድ ሰገጤ ነሽ እላታለሁ። አትሰማኝም! ስለማትሰማኝም ነው ቀን ላይክ የሸቃቀልኩበት ፅሁፌ በዛኑ ዕለት ምሽት ጦሱን ይዞ ከተፍ ያለው ። ሀገር ሰላም ብሎ.. .አንድ ሁለት ቡትሌ አረቄውን ልፎ ወደ ጎጆው ለመግባት የተጣደፈው አባት አስፈሪው የሚስቱ ቁጣ ተቀበለው። "እናት ፍርፍር ነገር ካለ ራቴን ስጭኝ " ርቦኝ ነበረ... "አንተ ?!... ቆይ ቆይ ... ፍርፍር ስትል? ከመቼ ጀምሮ ነው እዚህ ቤት እንደ ሲኦል የሚፋጅ ፍርፍር በልተህ የምታውቀው? የአባቴ አምላክ ሲኦል ያንቦራጭቅህና! " "ማሬ" "ማርህን ጎዣም ፈልግ !" "እናቴ ወግ እኮ ነው። የኔ ታሪክ ሳይሆን የገፀ ባህሪው ..." "አይ ...አይ እንግዲህ አትሞላፈጥብኝ። የቤትህን ታሪክ እያወጣህ አደባባይ አትበትን።" እየተንቀራፈፈች ከተቀመጠችበት ሶፍ ላይ ተነሳች። "ገፀ ባህሪይ ይላል እንዴ? ይልቅ ባህሪህን አስተካክል... Stupid! "...ወደ ጓዳዋ ገብታ የሽንኩርት ቢላዋን አነሳች። ታድያ ይሄ አጋጣሚ ተከስቶ ሳምንት ሳይሞላው ማስጠንቀቂያውን ዘንግቼ... "ውሽማዬ የሰራችልኝ የቂጣ ጭብጦ ከስሯ እንዳልጠፋ አስቀረኝ ጨብጦ😊 " የሚል ግጥም ፃፍኩኝ። ግጥሙን ባለቤቴ ቡና እያፈላችልኝ ጋደም ብዬ ነበር የፃፍኩት። ላይክና የሳቅ ሪአክት ገፄን አጨናነቀው ። (ላይኩ ብዙ አይደለም...300 ላይክ ብርቅ ስለሚሆንብኝ ነው ...ይ ) አቦል ቡናው ደርሶ ... ጀበናዋ ከከሰል ማንደጃው ተነስታ ክበቧ ላይ ተቀመጠች። ባለቤቴ ቡናው እስኪሰክን ብላ ስልኳን ስትጎረጉር ቆየችና እዛው እያየኋት ፊቷን አመድ ወረሰው። አጠገቤ ሆረር ፊልም እየተረፀ ይሆን እንዴ? ብዬ ሳሎኔን ለመቃኘት ሁሉ ዳዳኝ! ቆመች ! አባጅፋር ከነ ቡልኳቸው ላዬ ላይ የተከመሩ ይመስል ከበደችኝ። ከሻሿ ስር አፈንግጠው ያሉ ቡናማ የፀጉር ዘለላዎቿን አየኋቸው። "ምነው? " ተንደርድራ ጓዳዋ ገባችና ብረቱ እንደ አዲስ አበባ ኑሮ የሚከብደውን የእንቁላል መጥበሻዋን አንስታ አሽቀነጠረችው። ራሴን ገመሰኝ። "ምን ሆነሻል ሴትዮ?" " ጭራሽ እኔን ሴትዮ ! የውሽማህ ቂጣ ነዋ ያጠገበህ.. . " "የምን ውሽማ? " ... " ከስሯ የማያርቅ የቂጣ ጭብጦ የምትሰራልህ ጭማሪ ሚስትህን ነዋ !" "እንዴ.. . ይሄ እኮ ገፀባህሪይ.. .. " ባለቤቴ አላስጨረሰችኝም.. . " ባህሪህን ማስተካከል ካልቻልክ ይህችን ያዝበት.. . " ሰፊው የአጥሚት ኩባያ ሀማስ እንዳስወነጨፈው ሮኬት ተምዘግዝጎ ወደ ግንባሬ አቅጣጫ ተወነጨፈ.. .. :) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 695
39
የሴተኛ አዳሪ ልጅ ነኝ (በላይበቀለ ወያ) . . ያባቴንማንነት ፣ ድንገት ስጠይቃት እንባና ትዝታ ፣ እየተናነቃት እንዲህ ትለኛለች... "አንተንበመሀፀን ፣ እኔን በእርግዝና ልጁን እና ፍቅሩን ፣ ክዶ ሄዱዋልና አንተን ለማሳደግ... ታክቶኝየለመድኩት ፣ የብዙ ሰው ገላ አንተን ካሳደገህ... ሁሉምአባትህ ነው! ከፍሎኝየሚተኛ ፣ ወንድ አዳሪው ሁላ።" ብላ የምትነግረኝ የሴተኛ አዳሪ ፣ የተከፋይ ልጅ ነኝ ። ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ይሄ ነው ታሪኩዋ... ሴትአዳሪነቱዋን፣ ቀድሞ ያስጀመራት የሆነ ዘመን ላይ ፣ ፍቅረኛ ነበራት "የዘላለሜ ነሽ" ብሎ የሚነግራት ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ የሆነ ዘመን ላይ... "አረገዝኩ"አለችው ፣ ማስረገዙን ካደ ዘላለም ስታምነው... እኔንበመሐፀን ፣ እሷን በችግር ላይ ፣ ጥሎ ተሰደደ። ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ የሆነ ዘመን ላይ... እኔተወለድኩኝ ፣ እሱዋ ተቸገረች እኔን ለማሳደግ.... ከብዙወንዶች ጋር ፣ መተኛት ጀመረች። ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ.... ሲመሽትወጣለች ፣ በፍጥነት ተኩላ ማልዳ ትመጣለች ደክሙዋት ተጎሳቁላ አንተን ካሳደገህ... ከፍሎተኚ ሁሉ ፣ አባትህ ነው ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 175
56
✍️🌹ህይወት ውስጥ "ማለፍ" የሚባል ክህሎት ያለ ይመስለኛል። ስንኖር በማለፍ ውስጥ ካላለፍን የህይወት ቀጣይነትና ምንነት ላይገባን ይችላል። ፍርሃትህን ማለፍ፣ ሽንፈትህን ማለፍና አንዳንድ ሰዎችንም ማለፍ ያስፈልጋል። በማለፍ ውስጥ እለፍና የሚታለፉ ነገሮችን እለፋቸው። የሚያስጨንቁህ ነገሮችም ይሁን ነገሮች አላፊ ስለሆኑ ስታልፋቸው ታርፋለህ። ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 043
34
✨የህልሜ ጓደኛ ክፍል 2 (የመጨረሻው ክፍል) ሰላምታ ተለዋወጥንና ከእኔ ፊት ያለው ወንበር ላይ ተቀመጡ፡፡ ለስሙ ነው እንጂ ከጐኔ የተቀመጡ ያህል ነበር፡፡ ባወራሁ ቁጥር ፊታቸውን ወደኔ እያዞሩ ነው የሚያዳምጡኝ - ወግ በዓይን ይገባል እንዲሉ፡፡ መቼም የዛን ዕለት “ቀልዶች” ከየት እንደመጣልኝ እግዜር ይወቀው! አንዳንዶቹን እኔም ራሴ አላውቃቸውም፡፡ በቃ እኔ አወራለሁ፡፡ እነሱ ይስቃሉ፡፡ በተለይ በህልሜ ሻማ የሰጠችኝ ልጅ ከልቧ ነው የምትስቀው፡፡ ጥርሷ ብቻ ሳይሆን ዓይኗም ይስቃል፡፡ በዝናቡ በስብሶ የነበረው ኮቴ በምን ተዓምር እንደደረቀ ግራ ገብቶኝ ልጅቷን ጠየቅኋት፡፡ ያደላት ናት - እሷ! ሥራዋ መሳቅ ብቻ ነው! “ሳቅሽ ይሆናል ያደረቀው!” - አልኳት ሳላስበው። የባሰ ለቀቀችው - ሷቋን፡፡ ብዙ ዓይኖች ወደ እኛ ተወረወሩ፡፡ አጠገቧ የተቀመጠችው የሥራ ባልደረባዬ “ኧረ ቀስ በሉ!” አለች - በተወረወሩት ዓይኖች ተሸማቃ፡፡ እኛ ግን ዓይነ ጥላችን ተገለጠልን መሰለኝ ባሰብን፡፡ ከዚያ በኋላማ ማን ይቻለን! የማናወራው ወሬ፤ የማንስቀው ሳቅ የለም፡፡ መተሃራ ጉዳያችንን ጨርሰን ስንመለስም በአንድ አውቶብስ ላይ ነበርን - እዚያው መቀመጫችን ላይ፡፡ አሁንም ከጣራ በላይ እየሳቅንና እያወጋን አዲስ አበባ ገባን፡፡ የሥራ ባልደረባዬ ግን እኛን ትታ መፅሃፍዋን መርጣ ነበር። ወሬያችንና ሳቃችን ፋታ ስላልሰጠኝ ልጅቷን በህልሜ እንዳየኋት የነገርኳት ከወረድን በኋላ ነው፡፡ በህልሜ አየሁሽ አልኳት እንጂ ዝርዝሩን ግን አልነገርኳትም፡፡ እንኳንም አልነገርኳት ሳልል አልቀረሁም፡፡ የሞባይል ቁጥሯን ለመቀበል ሁነኛ ምክንያት አገኘሁ፡፡ “ስልክሽን ስጪኝና ማታ ደውዬ ህልሙን እነግርሻለሁ” አልኳት፡፡ እሷ እንደሆነ ፈጣሪ እጁን ታጥባ የፈጠራት ናት - ቅንጣት ጥርጣሬ ሳይታይባት በተለመደው ሳቋ አጅባ ቁጥሯን ነገረችኝ፡፡ ማታ ደወልኩላት፡፡ ሳቋ ናፍቆኝ እንጂ ህልሙን ልነግራት አልነበረም። የማይቋረጠውን ንፁህ ሳቋን ሰማሁና ለውለታዋ ሁለት ግጥሞችን በጆሮዋ አንቆረቆርኩላት - የጥበብ ስሜቷን ለመፈተሽ፡፡ አላወቅሁም እንጂ ልጅቷ ሁለመናዋ ከጥበብ የተሰራ ነው፡፡ ሳቅ ራሱ ጥበብ አይደለም እንዴ! በየቀኑ መደወል ጀመርኩ - በህልሜ ያየኋት ልጅ ጋ፡፡ ህልሙን ግን አልነገርኳትም - ልቧን ለማንጠልጠል ሳይሆን ለመገናኘት ምክንያት እንዲሆነን ብዬ ነው፡፡ በዚያው ሰሞን ህልሙን ልንገርሽ ብዬ ምሳ አብረን ለመብላት ተቀጣጠርን፡፡ ፍልውሃ ሬስቶራንት ምሳ በልተን ማኪያቶ እየጠጣን ህልሜን ከሀ እስከ ፐ ነገርኳት፡፡ በጆሮዋ ብቻ አይደለም የሰማችኝ - በሁለመናዋ ነው፡፡ ሁሉ ነገሯ ከእኔ ጋር እንደነበር ታስታውቃለች። የተለመደው ሳቋ ጆሮዬ ውስጥ ይፈሳል - እንደ ጣፋጭ ዜማ፡፡ ያየሁትን ህልም ለእናቷ አስፈትታ እንድትመጣ ተስማማን፡፡ የህልሙ ነገር በዚህ ቢቋጭም ሳናውቀው ሌላ ነገር ጀምረን ነበር፡፡ መነካካት፤ ትክ ብሎ መተያየት … እና የተለመደው የሳቅ ጅረት! … ጅረቱ እንደ ጉድ ጆሮዬ ውስጥ ይፈሳል … ይፈሳል … ይፈሳል፡፡ ተቀራርበን ስናወራ ሁለተኛ ቀናችን ነው፡፡ በህልሜ ያየኋት ቀን ከተቆጠረ ምናልባት ሦስተኛ ቀናችን ሊባል ይችላል፡፡ ለታዘበን ግን ከዓመት በላይ እንደሚተዋወቅ ሆነን ነበር፡፡ መነካካቱና መደባበሱ አቅሌን አሳጣው መሰለኝ ሳላስበው ጠጋ አልኳትና የግራ ጆሮዋ ላይ ከንፈሬን አሳረፍኩባት። እኔ ደነገጥኩ፤ እሷ ግን ሳቀች፡፡ ሳቅዋ ድንጋጤዬን አባረረውና ዓይኔን በጨው አጥቤ የግራ ዓይንዋ ላይ ደገምኳት፡፡ አሁን አልሳቀችም፤ ትክ ብላ አየችኝ፡፡ እቺ የሳቅ ዥረት የፍቅር ዥረትም ሳትሆን እንደማትቀር ልቤ ጠረጠረ። ከዚህ በኋላ ማን ይቻለን! የፍቅር አክተሮች ሆነን ቁጭ አልን፡፡ ወሬያችን፣ ሳቃችን፣ ፍቅራችን ሞቀ፤ ደመቀ፡፡ ሌላ ቀን (ምናልባት ከዓመት ገደማ በኋላ) ሳቂታዋ የህልሜ ጓደኛ እንዲህ ስትል ጠየቀችኝ “ለምን ወደድኩህ?” ደንግጬ አየኋትና “ምን አልሽ?” አልኳት፡፡ “ለምን  ወደድኩህ?” ደገመችው - ዓይኗን ዓይኔ ላይ እያንከባለለች “ፈጣሪዬን ጨቅጭቄው ነበር” አልኳት - ለጥያቄዋ መልስ እንደማይሆን እያወቅሁኝ፡፡ “ምን ብለህ?” አለችኝ - እየሳቀች “አምላኬ ስጠኝ በልኬ ብዬ” - አልኳት፡፡ የበለጠ ሳቀች፡፡ በጣም ሳቀች፡፡ ብዙ ሳቀች። ሳቋን እንዳገባደደች በተራዬ ድንገተኛ ጥያቄ ሰነዘርኩ፡፡ “ፍቅሬ፤ ህልሙ እኮ አልተፈታም” አልኳት “ኧረ ባክህ … ከዚህ በላይ እንዴት ይፈታ!” አለችኝ - ገፋ ብሎ ወደሚታየው ሆዷ በእጇ እያመለከተችኝ፡፡ በህልሜ ያበረከተችልኝ ሻማ ፍቺው ገባኝ። በህልም ሻማ ማለት ሳቅ … ደስታ … ፍቅር… ደግነት… ህይወት… ልጅ… ነው ለካ!! ፈጣሪዬ በልኬ የተሰፋ ፍቅር ስለሰጠኝ አመሰገንኩት፡፡ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 354
41
🍃 ተይ_አታገላብጪው ●🍃 ,,,,,,,,,,, ፍቅርሽ ተቸንክሮ መስቀያ በሌለው የምኞት መስቀል ላይ፣ ላልወረድ ተሰቅዬ ቀን ለሊት ስሰቃይ፣ ከልቤ አፀድ ውስጥ፤ የማይነጥፍ እንባ በደም ተለውሶ፣ በይሆናል ተስፋ እንደ ጅረት ፈሶ፣ አንቺ ባጠፋሽው እኔ እያልኩ ማሪኝ፣ ጭራሽ እንዳጠፋ ዘውትር ስትርቂኝ፣ ሰርክ እየማለድሁ፤ ስርሽ ባ'ደገድግ ምህረትን ፍለጋ፣ አስረሽ ስትገርፊኝ በናፍቆት አለጋ፣ ተገራፊው ልቤ ዘውትር እየደማ፣ አንቺነትሽ ልቆ እኔነት ስቅማ፣ መከረኛው ልቤ፤ ፍሰስ ፍሰስ አለኝ ከትዝታ ማዕበል፣ ባልኖርሽበት አለም፣ ልምዱ ስለሆነ አንቺን መቀላቀል። የልብሽን መገቢያ ቆልፈሽ ላትገልጪው፣ የረጋውን ማዕበል ተይ አታገላብጪው። ✍ቶፊቅ መሀመድ (@Tufaw_muhe) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 690
33
✨ማመን እና ማወቅ (በላይ በቀለ ወያ) . . ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ ያወኩትን እውነት ... ማመን ቢቸግረኝ ፣ "ትመጣለች " እያልኩ ፣ እጠብቅሻለሁ፡፡ "አትመጣም" እያለ... ለሚነግረኝ ሁሉ ፣ መቅረትሽን አውቆ "የቀረበት እንጂ ... የመጣለትማ ፣ አያውቅም ጠብቆ" ብዬ እመለሳለሁ በቃ ትመጫለሽ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ!!! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 617
41
አልቦ መጋት
ፀሀፊ ና አንባቢ
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️ 🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

አልቦ መጋት🌗 የግማሽ አለም ጣኦት🌗.mp3

6 016
8
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 8 ✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ "" "" ዲና ስልኳን አንስታ አንተ እድሜክ እርዥም ነው አሁን በልቤ ሳነሳክ ነበር አለችው አዳምም አዎ እድሜዬማ በጣም እረጅም ነው ዛሬ እድሜዬ ጨምሯል እልልልል በይ ዲናዬ ሄዋኔ ነቅታለች እናትዬ ነቅታልኛለች ፍቅሬ ነቅታለችችችች አላት ዲና አፏን ከፍታ ቀርች አዳምም ዲና ኧር ምነው ዝም አለሽ ሄሎ ዲና ሲላት የምርህን ነው አለችው እጅግ ፈገግ እያለ የምሬን እኮ ነው ነቃች ታውቂያለሽ ለአያሌ ቀናት የተሰማኝን ስሜት እንዴት እንደተሰቃየው አሁን ግን ያ ሁሉ አልፎ ሄዋኔ ስትነቃ የተሰማኝ ደስታ በቃላት አይገለፅም አለ ዲናም ቀጠል አድርጋ ቆይ እሺሺ መጣው ላያት በጣም ነው የምፍልገው አሁን አንተ የት ነክ ውስጥ ከሷ ጋር ነህ እንዴ የማገገሚያ ክፍል አስገብተዋት እዛው በር ላይ ሆኔ ነው የምደውልልሽ ግን አለ አዳም እረጅም የጭንቀት ትንፋሽ እያወጣ አሷ እኔን አታስታወሰኝም ለኔ በጣም ከባድ ነው ቢሆንም በመትረፏ ግን በጣም ደስስስ ብሎኛል ፈጣሪን አመሰግነዋለው አለ አዴም እና አሁን እንዴት ናት አለች ዲና ለመውጣት እየንጎዳጎደች አዘነ አሁን ጥሩ ስሜት ላይ አደለችም መስለኝ ፊቷ ላይ ብዙ ጥያቄዎች እንዳሏት ያሳብቃል እና ደሞ ዳክተሩ ማንነትህን ከጠየቀችክ ላለመንገር ጣር ስላለኝ ስለእሱ እቅድ እንድናወጣ ነይ እባክሽ አላት ዲናም እሺሺ ስልኩን ዝጋው እየመጣው ነው አለችና ለባብሳ ወጣች የዲናና የአዳምን ቅርርብ ያየ ሰው ረዥም ጊዜያት በጓደኝነት የቆዩ ነው የሚመስሉት አዳም ይህ ቅርርባቸው ያሰጋዋል ምክንያቱም ያ ሰይጣን ጊዲዮን ጓደኛ እንደሆኑ ካወቀ ይገላታል ስለዚህ ያስጋዋል። ዲና ሀኪም ቤት ደረሰች ሄዌን ወደተኛችበት ሄዳ በሩ ላይ ቆመች ሄዋን በግሉኮስ ተኝታ አዳም ደሞ በፍቅር ወንበሩን ወደ አልጋው አስጠግቶ ተቀምጦ በሀሳብ ነጉዷል የደስታ የመከፋት የማዘን ስሜት ይንፀባረቅበታል ዲና በሩን እንደማንኳኳት ብላ ገባችና ራቅ ብሎ የተቀሙጠውን ወንበር አምጥታ ቁጭ አለች ክፍሉ በዝምታ ተዋጠ ዲናም አዳም አለችው ሄዌንን አተኩሮ ሲመለከታት የነበረው አዳም ወደ ዲና ዞር አለ ሄዋን ንገረኛ ምንድነው ዶክተሩ ያለህ በዝምታ ላብድ እኮ ነው አለችው እሱም ወደ መውጫው በር ሄዶ በአይኑ ተነሽ የሚል ምልክት ለዲና ስጣት ዲናም ወጣች ምንድነው አለችው ዲናዬ ሄዋን ምንም አታስታውስም እንዴት ልለምደው እችላለው አላት እጁን ጭንቅላቱ ላይ እያረገ ከምንም ቅድሚያ ያንተ መረጋጋት ይቀድማል ቢያንስ አንተ በብዙ ከሷ ትሻላለህ ቢያንስ ስላሳለፋችሁት ነገሮች ታውቃለህ ሁሉንም ታውቃለህ ጤነኛ ነህ ስለዚህ ተረጋጋ አዳም አለችው በረጅሙ እየተነፈሰ ልክ ነሽ መረጋጋት አለብኝ አለ ግን ዲናዬ በፈጠርሽ መላ ዘይጂ ሄዋኔን ማን ብዬ ልተዋወቃት አላት ዲናም እንዴ ለካ እሱም አለ ለምን ታዲያ ፍቅርኛሽ ነኝ በላታ አለችው በተዝናኖት በሞላው አነጋገር አዳም ጭንቅላቱን በቀስታ እያወዛወዘ አይ አይሆንም ዶክተሩ ምንም ስላለፈው ህይወቷ እንዳትነግራት በሽታዋ ይብስባታል ነው ያለኝ ስለዚህ ምን እናድርግ አለች አዳምም ቀጠል አድርጎ እንቺና እሷ እህትማማች እንደሆናቹ እና እኔ ደሞ የሁለታችውም ጓደኛ እንደሆንኩ እና ደሞ ሶስታችን አንድ ቤት ስንኖር እንደነበር አንቺ ደሞ ቤት መቀመጥ ስለማትወጂ ውጪ እንደምታድሪ እና አንዳንድ ቀን ነው የምትመጪው እንደዛ ብለን በ ብንነግራትስ አለ። ቀጠል አድጎ የሆነ ጊዜ ነው ከጓደኞቼ ለመዝናናት ወጣን ሹፊሩ ጠጥቶ ስለነበር መኪናውን በፍጥነት ነበር ሲያሽከርክር የነበረው መኪናው ፍጥነቱን ጨመረ ጨመረ በመጨረሻ መኪናው ተገለበጠ። ✨ይቀጥላል...... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 771
30
‹‹ ኦቨር ዶዝ ›› (አሌክስ አብርሃም ) ትላንት ጎረቤቴ ሚስቱን ሊገላት ለትንሽ ተረፈች !! ትላንት ማታ ሲጮሁና ሲንጫጩ ሰምቸ …‹‹ዘራፍ…ያንበሳው ግልገል ›› ብየ መቀረቀሪያ ነገር ይዠ ሮጥኩ …እና ጎረቤቴ ቤት ስደርስ ‹‹ምንድነው ሌባ ነው የታለ …›› እያልኩ ቀውጢ ሳደርገው ‹‹ኧረ ተረጋጋ እትየ አልማዝ እራሷን ስታ ወድቃ ነው ›› አሉኝ ….እውነትም እትየ አልማዝ ሶፋው ላይ ዝርግትግት ብላ ወዟ ፍልቅ ፍልቅ እያለ ….አንዱ ‹‹ፀበል እርጩባት ›› ይላል ሌላው ‹‹አውድቅ ይሆናል ክብሪት አምጡ ›› ሌላኛው ‹‹አምቡላስ ይጠራ ›› አለ … ዓለሙ የሚባለው የላዳ ታክሲ ባለቤት ‹‹አምቡላንስ እስኪመጣ ትሙት እንዴ …ባይሆን በኩንትራት ታክሲ እንውሰዳት ›› እያለ ስራውን ያመቻቻል …. ደግነቱ እትየ አልማዝ ወዲያው አይኗን ገልጣ ፈገግ አለች !ጎረቤቴን ካወኳት ጀምሮ ፈገግ ስትል አይቻት አላውቅም ..ምን ታያት …መለዓክት ተገልጦ ምን ሹክ አላት …እያልኩ አሰብኩ ! በኋላ ዛሬ ጧት ላይ የአልማዝ ልጅ ሚጢ ትምህርት ቤት ስትሄድ አግኝቻት ‹‹ምን ሁና ነው እትየ አልማዝ እራሷን የሳተችው ›› ብየ ብጠይቃት … ‹‹አባቴ ተናግሯት ›› አለችኝ …በጣም ተበሳጨሁ ይሄ ሰውየ አበዛው… ሁልጊዜ ሚስቱን እትየ አልማዝን እንደነዘነዛት እንደሰደባት አንዳንዴም እንደነረታት ነው በቃ…ጭራሽ እንዲህ ራሷን እስክትስት ደግሞ ይናገራታል እንዴ ያበሻ ወንድ ሲባል …ሴት እናት ናት ሴት እህት ናት …ሚስት ናት …ብየ በቃ ተብከነከንኩ ! ‹‹ሚጢ ለመሆኑ አባትሽ ምን ቢናገራት ነው እንዲህ ራሷን እስክትስት … ›› ብየ ሳልጨርስ ‹‹አይይይ የማታው እንኳን ትንሽ ይለያል… እኔም ልዘረር ነበር …አባባ ሁልጊዜ ሲገባ ..አንች ከርፋፋ ጀሪካውን ውጭ የጣልሽው ምናባሽ ሁነሽ ነው …አንች ደነዝ ድመቷ ላይ ለምን በር ዘጋሽባት …ውሃውን አትዘጊውም እንዴ ለነገሩ ምን ታረጊ ብሩን የምገፈገፍ እኔ ….ተጎልተሸ ቴሌቪዥን ታያለሽ ….ነበር የሚለው ….ማታ ግን …ድንገት ገባና ማሚ ሶፋው ላይ እንደተቀመጠች ….‹የኔ ፍቅር ደህና አመሸሽ ›ብሎ ጉንጯን ሲስማት በቃ ራሷን ሳተች፡)ብላኝ ፈገግ ሚጢ !! ‹‹ኦቨር ዶዝ››፡)ከንፈሯን ቢስማት …አበባም ይዞ ቢገባ ኑሮማ ዛሬ ቀብር መዋሌ ነበር፡) !! ከምር ግን ዝም ብየ ባልና ሚስት ጎረቤቶቸን ስመለከት …. አንዳንድ ሚስቶች መፈቀር መከበር የናፈቃቸው ይመስለኛል …ቀልዱን ከነግነቱ በቁም ነገር እዩልኝና ባሎች በናታችሁ አፍቅሯቸው አትከፍሉበት …አንዳንዱ ባል ሚስቱን አቢዮት ሲፈነዳ እወድሻለሁ ያላት እስከዛሬ ደግሞት አያውቅም ! ውጭ ፖለቲካውን ሲያወራ ኳሱን ሲጠርቅ ዘና ሲል አምሽቶ ቤት ሲገባ ፊቱን የሚጥል ስንት ባል አለ … በቃ ፈገግታውን ‹‹ሚስት የማትደርስበት ቦታ አስቀምጥ ›› ብሎ ሃኪም ያዘዘለት ነው የሚመስለው ! ‹ባል ፊት› አለች ያች ልጅ …ምናይነት ባል ማለቷ እንደሆነ እንጃ ! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 732
74
የፍቅር ፀብ ( በላይ በቀለ ወያ ) ባብሮነታችን ውስጥ ጥላቻ ባይኖርም - መናናቅ ነበረ በመናናቃችን መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ አብሮ መብላት ቀረ አብሮ መዋል ቀረ አብሮ ማደር ቀረ ቀረ ቀረ ቀረ ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡ ባብሮነታችን ልክ መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ አሁን የሚታየኝ ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡ እንኳን ተለያየን! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 998
48
"እየጠሉ ማግኘት" (✍በላይ በቀለ ወያ✍) አለ ወዶ ማጣት ፣ አለ ጠልቶ ማግኘት የሚሆን አልሆን ሲል ፣ የማይሆን መመኘት ቀጥ ያለ ሲታጣ መመልመል ጎባጣ አለ ጠልቶ ያገኘ ፣ አለ አፍቅሮ ያጣ፡፡ አለ ቡዙ ብዙ .. . ምንም ብርቄ አይደለም ! ኖሬ ያለፍኩት ነው ፣ ስንኖር ያየሽኝ ወድጄሽ አጣሁሽ ፣ ጠልተሽ አገኘሽኝ፡፡ ብኖር የለሁሽም ፣ ባትኖሪም አለሽኝ!!! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 910
63
የህልሜ ጓደኛ(በሁለት ክፍል የሚፈፀም) ክፍል.....1 ህልም - ወለድ ታሪክ  ቀኑን ሙሉ በሥራ ተወጥሬ ስለምውል ስለብቸኝነቴ ለማሰብ ፋታ የለኝም፡፡ ብቸኝነቴ ትዝ የሚለኝ ሲጨልም ነው - ፀሃይ ስትጠልቅ። ጨለማው ከች ሲል የብቸኝነትን ብርድ ልብስ ያከናንበኛል፡፡ በተለይ ወደ ተከራየኋት አንዲት ክፍል ቤት ሳመራ ብቻዬን ሆኜ አላውቅም፡፡ ከጐኔ ብቸኝነት አለ - የባጥ የቆጡን እያወራ፡፡ ብቸኝነትን ለማባረር የዘየድኩት መላ ምሽቱን በድራፍት ቤት ማሳለፍ ነበር፡፡ ግን ደግሞ ድራፍት ቤት ውስጥ ዝንተ ዓለም መቀመጥ አይቻልም፡፡ በዚያ ላይ አከራዮቼ የውጭውን በር ይከረችሙታል። ከርፊው ከምሽቱ 4 ሰዓት ተኩል ላይ ነው፡፡ ስለዚህ በጊዜ ሦስት ወይም አራት ጃምቦዬን ተከናንቤ ወደ ማደሪያዬ ማዝገም አለብኝ፡፡ ከድራፍት ቤቱ እንደወጣሁ ሞቅታው ባጐናፀፈኝ መነቃቃት ታጅቤ የምሽቱን ነፋሻማ አየር እየማግሁ እጓዛለሁ - ወደ ብቸኝነቴ፡፡ በተለይ ሰፈሬ ስደርስ ድብርት ይጫጫነኛል፡፡ የገዛ ቤቴ ያስፈራራኛል፡፡ ይሄኔ ትንሽ መራር ፀሎት ወደ ሰማዩ ጌታ እልካለሁ፡፡ “አምላኬ ስጠኝ በልኬ!” እለዋለሁ - ሁልጊዜ ማታ ማታ ከድራፍት በኋላ። አንዳንዴ ግን እራሴን እጠይቃለሁ - “ፈጣሪ የሞቅታ ፀሎት ይሰማ ይሆን?” እያልኩ፡፡ ትንሽ ጥርጣሬ ይገባኝና ወዲያው ደግሞ “እሱ እንደሰው አይደለም፤ የልብ ያውቃል” እልና እፅናናለሁ። ነገም፤ ከነገ ወዲያም፤ ከዛ ወዲያም ያው ነው። ሆዴን በድራፍት ፀበል አጥብና “ኧረ ዓምላኬ ስጠኝ በልኬ!” እያልኩ ውትውት አደርገዋለሁ - “ዝምታ ወርቅ ነው” ያለ የሚመስለውን ፈጣሪዬን። ከዛ እተኛለሁ - ብቻዬን። ሌሊት ላይ ድንገት ከእንቅልፌ ስባንን ግን ብቻዬን አይደለሁም፡፡ ከጐኔ ብቸኝነት ተጋድሟል፡፡ በእርግጫ ብዬ ከአልጋዬ ላይ ብወረውረው ደስታዬ ነው፡፡ ግን አቅመ ከየት ይምጣ! እሱ እንደሆነ አንዳች ነው የሚያህለው። አንድ ሌሊት ግን እልህ ያዘኝ፡፡ ተነሳሁና ጐትቼ መሬት ፈጠፈጥኩት፡፡ ሊታገለኝ አልሞከረም፡፡ “ምናባህ ትፈልጋለህ?” ብዬ አምባረቅሁበት፡፡ እሱ እቴ! ጋግርታም ነው። ትቢቱ የበለጠ አሳረረኝ። እየጐተትኩ ከቤቴ አስወጥቼ ደጅ ብርድ ላይ ወረወርኩት - በቀትር ሌሊት፡፡ ደግነቱ ካልገባሁ ብሎ አልታገለኝም። በሬን ቀረቀርኩና ትልቅ ሳፋ አስደግፌ ተመልሼ ተኛሁ - ገና ከሌሊቱ 9 ሰዓት ነበር፡፡ ለካስ መኝታው ሲጐረብጠኝ የነበረው ይሄ ጋግርታም ያለ ሃሳብ እላዬ ላይ እየተጋደመ ነበር፡፡ አሁን ዘና ብዬ በምቾት ለጥ አልኩኝ፡፡ በሚቀጥለው ክፍል እናቴ እንጀራ ትጋግራለች። እኔ አልጋዬ ላይ ተቀምጬ መፅሃፍ አነባለሁ። ትልቋ እህቴ በሬ ላይ ቆማ ስትጠራኝ ቀና ብዬ አየኋት - አቤትም እመትም ሳልላት፡፡ “ስጥልኝ ብላኝ ነው” አለችና በእጇ የያዘችውን ሦስት ነጫጭ ሻማዎች አሳየችኝ፡፡ “ማነው ያለሽ?” አልኳት ተገርሜ፡፡ ሻማ ያዋስኩት ሰው እንደሌለ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ አንዲት ረዘም ያለች የምታምር ቀይ ወጣት ድንገት ብቅ አለች፡፡ ተያየን፡፡ ከፈገግታ ውጭ አንዲት ቃል አልተነፈሰችም፡፡ የሻማዎቹ ባለቤት እኔ ነኝ ማለቷ እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ ሻማዎቹን ለምን እንዳመጣችልኝ እኔም አልጠየኳትም፤ እሷም አልነገረችኝም፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ የአዕምሮዬ የመጀመሪያ ሥራ ስለ ህልሙ ማሰላሰል ነበር፡፡ ልጅቷን በዓይን አውቃታለሁ - አልፎ አልፎ መ/ቤታችን ብቅ ትላለች፡፡ ከሰላምታ ያለፈ ትውውቅ ግን የለንም። በህልም ሻማ መስጠትና መቀበል ምን ይሆን እያልኩኝ ወደ ሥራዬ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ በጣም የገረመኝ ግን ከዚያን ሌሊት ወዲህ ብቸኝነትን አይቼው አላውቅም፡፡ ማታ ማታ ድራፍቴን ተከናንቤ ወደ ቤቴ ሳዘግም ብቸኝነት አጠገቤ የለም - ሁሌም ብቻዬን ነኝ፡፡ ፀሎቴን ግን ዘንግቼ አላውቅም - “አምላኬ ስጠኝ በልኬ”  እለዋለሁ - በየምሽቱ ወደ ላይ አንጋጥጬ። ከጥቂት ወራት በኋላ ለሥራ ጉዳይ ወደ መተሃራ የሚሄድ አውቶብስ ላይ ተሳፍሬያለሁ። በጠዋቱ ዝናቡ እየረገጠው ስለነበር ብስብስ ብያለሁ፡፡ ከኋላ ወንበር ላይ ነበር የተቀመጠኩት፡፡ አውቶብሱ ሊነቃነቅ ሲል አንድ የሥራ ባልደረባዬና በህልሜ ሦስት ሻማዎች የሰጠችኝ ረዥሟ ቀይ ልጅ አውቶብሱ ውስጥ ገቡ፡፡ ክው አልኩኝ፡፡ መጀመርያ ያየችኝ ባልደረባዬ ነበረች - ፈገግታ ለገሰችኝና ተያይዘው ወደ እኔ መጡ፡፡ ✨ይቀጥላል..... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 825
61
🍁ይህ ተረት አይደለም! የዘመንታሪክ ነው ፣ ዓለም ሁሉ ያውቃል "ተዋርደህ ሙት" ያለው ፣ ኢትዮጵያን ይንቃል!!! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 622
16
ተልባ_ቢንጫጫ_በአንድ_ሙቀጫ ብዙ የተንጫጫ ፣ግርግር ያበዛ፣ ያሸነፈ መስሎት ፣ሽህ ጊዜ ቢንዛዛ፣ እልፍ ዝም ያለ አለ፣አንገቱን የደፋ፣ ቀና ያለ ጊዜ፣ ባፍጢም የሚያዳፋ፣ እምቡር እምቡር ቢሉ፣ቢዘሉ እንደፌንጣ፣ ሁሉም ልኩን ያውቃል፣ቁርጥ ቀን ሲመጣ። ✍ሜሮን ጌትነት ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 810
50
😘ለፍቅር ስል😘 🔥ክፍል አስራ አንድ ✍️ደራሲ፦ጎስ """ """ """ """ የድስቱ ድምፅ ክፍሉን በአንድ እግሩ አቆመው.... "ሉሊት ውዴ እንደዚህ አትደንግጪ እንጂ" አልኳት ሴንጢዬን አስሬ ወደሰገባው እየመለስኩና እያወጣው...ጩቤውን ስታይ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች.....አመዷ ቡን አለ....ወደሁዋላ እየሸሸች.."አትጠጋኝ" አለችኝ እኔ ግን የምሰባት ግዜ ላይ አይደለውም የማዳምጠው ልቤ ውስጥ የሚነደውን የበቀል ጣዕም እንጂ....ወደሷ አንድ እርምጃ በቀረብኩ ቁጥር ምድጃው ላይ የጣደቻቸውን ድስቶች እያነሳቻች ወረወረችብኝ....ቤቱን ከሷ በሚወረወረው የድስት ድምፅ ታወከ....ድስቱን አንስታ ስትወረውር እርቃኑን የቀረው ሲሊንደር ክፍት በሆነው መስኮት በኩል በሚገባው ንፍስ እሳቱን አወዛወዘው....የንፋሱን ማየል ተከትሎ መጋረጃዎቹ ከቀኝ ወደ ግራ ተወዛወዙ....."እባክህ ወንዴ እባክህ ተው በሁዋላ የሚፀፅትክን ነገር አታርግ እባክህ" አስሬ ከሰገባው እየተንቀለቀለ የሚወጣውን ጩቤ እያየች ተናገረች..."ምነው ውዴ እንደዚ ለቅሶ ማብዛት ያኔ ስትፎክሪ አልነበረ እንዴ" አልኳት በፍርሀት የሚንቀጠቀጡ ከናፍሮቿን እያየዋት የመጨረሻውን እርምጃ ለመውሰድ ወደሷ ፈጠን ፈጠን ብዬ መሄድ ጀመርኩ....በዚህ ጊዜ ኪችኑን ለቃ ለመውጣት ሩጫዋን ጀመረች ግን ወደ ላይ የሚያስወጣውን የፎቁን ደረጃ የሚብረከረኩት እግሮቿ መውጣት አቅቷቸው ገና ሁለት ደረጃዎች እንደወጣች ወደቀች...ከደረጃው ላይ ተንሸራታ በግንባራ ከወለሉ ጋር ተላተመችበት ወድያው ከግንባሯ ደም ይፈስ ጀመረ ግን አሁንም ምላሷ አይብረከረክም..."እባክህ ወንዴ እባክህ አንዴ እንኳን የምልክን ስማ የምትፀፀትበትን ድርጊት እንዳታረግ?" አለቸኝ በማልቀስ እና በመለመን የሚደማውን ግንባሯን ደሙ ይቆም ይመስል በእጇ ግጥም አድርጋ እየያዘች......እኔ የሷ መጎዳትም ሆነ እያለቀሰች መለመን ምንም አልመሰለኝም አጋጣሚውንም በፍጥነት ጩቤዬን ወደ ኪሴ ጨምሬ ምላጬን አወጣው ወደሷ አንድ ስንዝር በተጠጋው ቁጥር ልመናዋን ድምጿን ከፍ አድርጋ መማፀንና መለመን ጀመረች....በዛ የሰው በረት በሆነበት ሰፈር ውስጥ ማንም አይመጣልክም ሊረዳክም አይነሳም...ይሄኔ ይሄ ጩኸት እኛ ሰፈር ቢሆን የተደጋገፈውን የአፈር ቤትም ያፈርሰዋል...ህዝቡ ግልብጥ ብሎ ከወጣም ቆይቷል....እዚህ ግን እንደ ደመኛ ሰዉ አይነጋገርም ጎረቤት ለጎረቤቱ አይቆምም....ሴቶቹ ቡና ተጠራርተው ሰፈርተኛውን ሙልጭ አድርገው ሚያሙበት...ወንዶች ቤታቸው ውስጥ ካርታ እየተጫወቱ ስለ ኳስ እና ስለፖለቲካ የሚያደቁበት የኢትዮጵያ ባህል አይታወቅም...."ኦ ውዴ ውዴ ጩሂ ማንም አ..." ተናግሬ ሳልጨርስ ከፎቁ ላይ እህቴ ምን ሆነሽ ነው የምትጮሂው"የሚል ድምፅ በጆሮዬ ተንቆረቆረ....ድምፁ ወደ መጣበት የላይኛው የፎቅ ክፍል አይኔን ላኩ.....ባለውበት ደርቄ ቀረሁ የተጣራውም ሰው ባለበት ደርቆ ቀረ.......አንድ አይነት መልክ አንድ አይነት ልብስና አንድ አይነት ድምፅ ያላቸው እንስቶች....ማንኛዋ ማራናታ ወይም ሉሊት እንደሆነች ማወቅ አቃተኝ....ባለውበት ፈዝዤ እንደቆምኩ "ወንዴ ወንዴ እኔን ፈልገህ መጣክ አይደል አውቄው ነበረ" እያለች ከላይ የነበረችው እንስት እየበረረች ወደ እኔ መጣች እኔ ግን የባሰ በድንጋጤና በግራ በመጋባት ደርቄ ቀረሁ....ከመቼው ከፎቅ ላይ ወርዳ እላዬ ላይ ተጠምጥማ እንደምትወደኝ ድሮም አውቄው ነበረ ኤስኮ የሆንኩትን ሰምተክ እኔን ፍለጋ እንደምትመጣ አውቅ ነበረ" እንባዋን እያዘራች ተናገረች እኔ አሁንም ግራ እንደተጋባው ነው......"ኤስኮ ተናገር እንጂ ምን ሆነካል ተናገር እንጂ" ብላ ከናፍሮቿን ከከንፈሬ ስትገጥመው ነው በርግጌ የተነሳውት...."እባክሽ ወደ ሁላ ተመለሺ አንቺ ማነሽ ደሞ?" ስል "ማራናታ ነኛ ወንዴ ምነው በዛው ጥዬህ ስለጠፋው ተናደድክ እንዴ?" አለችኝ አይኖቿን እያርገበገበች... " አረሳውሽ ግን አንቺ እና" ብዬ ወደ ወደቀችው ልጅ ፊቴን መለስ አድርጌ ባገጬ ጠቆምኳት....እሷም የእኔን አይን ተከትላ የምታለቅሰውን እንስት ስትመለከተ....ወደሁዋላ ተመለሰች እየተርበተበተች "እባክ አትንካኝ እባክህ አትንካኝ እባክህ ፍቅረኛዬ ይጠብቀኛል እባክህ" እያለች እያለቀሰችና እየተንዘፈዘፈች ጆሮዋን ይዛ ወደ መሬት ላይ ተቀመጠች..... "ማራ ማራ አይነካሽም አይዞሽ እኔ አብሬሽ አለው" አለች ቅድም እስከነደሟ ተነክራ ፈገግ ስትል የነበረችው እንስት ወደሷ ሮጣ ሄዳ አቅፋ እያባበለቻት......በዚህ ጊዜ ሰለሞን ከየት መጣ ሳልለው አጠገቤ ደርሶ.."ቆዪኝ ሉሊት እኔ ወደ ፎቁ ላውጣት"ብሎ ተሸክሟት ወደ ደረጃው ወጣ እሷም ተከተለችው....እኔ በድንጋጤና ግራ በመጋባት ካለውበት ቦታ እንደተገተርኩ ደቂቃዎች ነገዱ ምን ያህል ደቂቃ ከዛ ሳልንቀሳቀስ እንደቆምኩ አላውቀውም ግን ከገባውበት ሰመመን ያነቃኝ "እስከ አሁን ድረስ እዚሁ ቆመካል እንዴ" የሚለው የሰለሞን ድምፅ ነበረ.....ባትቼ ስነሳ እና እሱን አፍጥጬ ሳየው....."ወንዴ ይቅርታ አድርግልኝ ይሄን ሁሉ ያደረኩት ለማፈቅራት ሉሊት ስል ነው....ሉሊት ማለት የአንተ ፍቅረኛ የነበረችው የማራናታ መንትያ እህት ናት..." ተናግሮ ሳይጨርስ ጣልቃ ገባውበት እና "ሉሊት እና ማራናታ የተለያዩ ሰዎች ናቸው ማለት ነው?" ባይኔ ያየውትን መልሶ እንዲያረጋግጥልኝ ጠየኩት...."አዎ ወንዴ መንታያዋ ነች....ሁለቱ በጣም የሚዋደዱና ሁሌም ቢሆን ከፊታቸው ላይ ሳቅና ጨዋታ የማይጠፋ የሚዋደዱ....የአንዷን ስሜት አንደኛዋ የሚሰማቸው መንትዬዎች ናቸው ግን በአንድ በተረገመች ቀን ሁሉም ተቀያየረ...አንተና ማራናታ በዛ ጭራቅ በሆነው የአዛርያስ ሰዎች ተተኮሰባቹ....የዛኔ የማራናታ ቤተሰቦች ብር ስላላቸውና ለደህንነቷ ስለሰጉ ወደ ውጪ ወስደው እንድትታከም ለማድረግ ብዙ ሞከሩ ዳሩ ግን ለልቧ የቀረቡት እስራሶች ከተቀረቀሩበት በአፋጣኝ ካልወጡ መንቀሳቀስ እንደማትችል ለቤተሰቦቿ አረዷቸው....ህክምናዋንም በዛው እንድትከታተል የሆስፒታሉ ቦርድ በመወሱ እዛው ክትትል ይደረግላት ጀመረ ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ አባቷም ዱባይ እና እዚሁ አዲስ አበባ ትላልቅ ሆስፒታሎች ስላሏቸው ከቀዶው ጥገና በሁዋላ የራሳቸውን ዶክተሮች አስመጥተው እሷን በሄሊኮፕተር ይዘዋት ሄዱ....በወቅቱ አንተንም ይዘውክ ሊሄዱ አስበው ነበረ ግን አንተ ላይ የደረሰው አደጋ ከባድ ስለነበረ መንቀሳቀስ የለበትም ስለተባለ በሳቸው ዶክተርና አራት ጥበቃዎች እንድትጠበቅ አደረጉ...ከዱባይና ከጀርመን ድረስ መድሀኒት እያስመጡ በቶሎ እንድታገግም አስደረጉክ....እንደምታውቀው ከኮማ ውስጥ የነቃከው ከወር በሁዋላ ነው በዛ አንድ ወር ውስጥ ማራናታ ወደ አንተ ለመምጣት ብትጥርም በሉሊት እና በአቧቷ ቁጣና ተግፃስ ያንተን መንቃት በየደቂቃው እየደወለች ትጠይቅ ነበረ....ነቅተህም ወደሸገር እንድትመጣ የተደረክ ቀን ማራናታ እና አንተ እራት እንድትበሉ እኔና ሉሊት ተነጋግረን ለጓደኞችህ ነገርናቸው ጓደኞችህም እየተደሰቱ ሙሉ ፕሮግራሙን ከእኛ ጋር አሰናዱና አንተና እሷ በጉጉት የምትጠብቁት የእራት ግብዧ ደረሰ.....ማራናታ ደስታዋ ወደር የለውም ነበረ" ወሬውን ገታ አድርጎ ለቅሶውን ቀጠለው.....እኔም እንደሱ ባላለቅስም በአይምሮ ላይ ወንዴ ሞትኩልህ ወንዴ ሞትኩልህ" የሚለው የላዳው ሹፌር ድምፅ ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ....ወንዴ ቀጣዩን ባይናገረው ብዬ ተመኘሁ....ግን ደሞ እሱ ያለኝ አመት እኔ በጥይት ከተመታውበት የበለጠ መሆኑ ትንሽ ፍታ ሰጠኝ....ወንዴም
Show more ...
6 318
36
እንባውን እየጠራረገ..."እናቷን እና አቧቷን ተሰናብታ ሉሊትን ለእኔ አደራ ሰጥታ ወጣች ያ የተረገመ ቀን ለቆ አለቀቃትምና በአንድ አረመኔ የሰው አውሬ ከአዛርያስ የሚበልጥ አውሬ በሆነ ሰው ተደፈረች......በወቅቱ አንድ አባት ከወደቀችበት አንስተው ወደ ሆስፒታል ወሰዷት....ግን ሲያገኟት ነግቶ ነበረ...ወደ አንተ ጋር አንድ ሰአት ተኩል የተነሳች ልጅ ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰአት ነው የተገኘችው ምን እና እንዴት እንዳደረጋት ሙሉ ታሪኩን ባታጫውተንም ስለደፋሪዋ መልክና ቁመና እስከ ልዩ ምልክቱ ከነገረችን በሁዋላ የወንድ ድምፅ በሰማች ቁጥር ወንዴ ሞትኩልህ ወንዴ ሞትኩልህ እያለች ነው የምታለቅሰው በጣም ሰዎችን ትፈራለች ሰው ሲቀርባት በፍርሀት ብዛት ራሷን ትስታለች....እጅጉኑ ሰው ተጠራጣሪ ሆነች...እንደነገርኩህ በተነገረን ምልክት በትንሽ ቀናት ውስጥ የአባቷ ሰዎች አገኙት....አባቷም ለፖሊስ ከመጠቆም ይልቅ እራሳቸው ለመበቀል ተነሱ...ልጁንም ደጋግመው በጥይት መቱት ...." ተናግረው ሳይጨርስ ከላዳ ሹፌሩ ጋር ታሪኩ ተመሳሰለብኝ "ግንባሩ ላይ ባሉት ሁለት ጠባሳዎችና" ተናግሮ ሳይጨርስ "አዱኛ ገጀራው ነው የልጁ ስም እንዴ?"አልኩት ሳላስበው ከአይኔ የሚወርደውን እንባ እየጠራረኩ....ሰለሞን በድንጋጤ ከተቀመጠበት ተነሳ እኔን ቁልቁል አፍጥጦ እያየኝ "ታውቀዋለክ እንዴ?" አለኝ ፊቱ በንዴት እየተቀያየረ...."አዎ" አልኩት ቃላቱን እየጎተትኩ.......በዚህ ግዜ የት ነው የምታውቀው? ለመሆኑ በሱ ምክንያት ከአንድ ወር በፊት አባቷንና እናቷን መግደሉን ታውቃለህ?" አለኝ በብስጭት "ምን?" ብዬ ከወንበሬ ላይ ተነስቼ አፈጠጥኩኝ ወድያው ክፍሉን የሲሊንደሩ ጋዝ ሽታ አወደው.....የጋዙን ሽታ ተከትሎ ጭስ ተተካ...ከዛ በሁዋላ ነገሮች በፍጥነት ተለዋወጡ የማራናታን ህይወት ለመቅጠፍ የመጣውት ልጅ አሁን ታዳኝ ሆንኩ....... #የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን https://t.me/lovestorey1 ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 215
24
"የመፃተኛው ኑዛዜ" ካገር ጫፍ እስከ ጫፍ በጥላህ ከልለህ ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ? ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ? እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ'ንተ አይደለህ፡፡ : እኔ መፃተኛ አንተ ኗሪ ነኝ ባይ እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ ስቀርብህ ገፋሀኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ ድንኳን ብትተክል፤ ነፋስ ሆኜ መጣሁ፡፡ : ያ'ባትህ ያ'ባቴ ጠበኛ ስማቸው ጠበኛ ህልማቸው በህይወት ተጣሉ ፤ ታረቁ ባፅማቸው ባ'ፈር ተቃቃሩ አፈሩ አስማማቸው በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ መተቃቀፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ፡፡ : ይችላል ይሉሀል ፍልሚያ ማዘጋጀት ያ'ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወደቅህ አካሌ ደረቴ መሆንህን መች አወቅህ?! ((በዕውቀቱ ስዪም)) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 725
30
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ አየህ አንፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም፡፡ አንፖል ተቃጥሏል ብሎ ቤት የሚቀይር ሞኝ ነው፡፡ አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ አልተሳካም ብለህ ራስህን አታጥፋ፡፡ ይልቅስ አምፖልህን ቀይር ችግርህን ተጋፈጠው፡፡ ጭንቀትህን አስጨንቀው፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡፡ መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው። የምን ተስፋ መቁረጥ....... ©ጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 419
50
እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ:: የበጎ ሰው ሀሳብ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር :: ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው ፥ በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤ አዎ ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል :: ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፥ ቢሆን የሞት ሽረት ዳገት ይወጣሉ፥ በንጥፍጣፊ አቅም የመኖር ፍላጎት ዘመም ይላል እንጂ ፥ተገርስሶ አይወድቅም :: ( አዳምኤል ) Bewketu Seyoum ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 223
29
✨የሰው ልጅ ፍፁም ታማኝ እንዳልሆነ መጠራጠራችን ምስክር ነው እርግጥ አንዳንድ ግዜ ማፍቀር በሚባል መጋረጃ ሁሉም ነገሮች በሰመመን ያልፉናል ። ሀሳባችንም ምናባችንም ከግርዶሹ ፈቀቅ አይሉም ። መካሪ እንደጠላት አይሆንም ባዮች አንደቅናተኛ ተፈርጀው በመስመሬ ጣልቃ አትግብ ይመጣል ። በመጋረጃው ተጋርደው ከሚያልፍብን ነገሮች አንዱ 'ጤነኛ ጥርጣሪ'ን ማጣትና በምትኩ ፍፁም አማኝነትን መላበስ ። እውነት ነው ማመን ከመታመን የሚቀዳ ንፁህ ወራጅ ነው ። ግን አንዳንዴ ደሞ አምላካችንን በማናምነው ልክ ስህተት ባንቀልባው አዝሎ የሚዞርን የሰው ልጅ ከራሳችን በላይ አምነን እንገኛለን ። ለዛም ነው አንድ ስህተት ባገኘን ቁጥር ባመነው ልክ ምንሰበረው ፣ ጥርጣሬን ባላበረታታም ፍፁም አማኝነትን ከአምላክ ውጪ ለ ስጋ ለባሽ ማልበስ ከግብዝነት አይተናነ ስም ባይ ነኝ!! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 859
35
እማ አለም ለምኔ ገጣሚ Dave mr Trump አቅራቢ JoJo Alex ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

file

5 968
34
‹‹ቲማቲም ወርውሮ ትላንትና አንድ ሰው አንዱን ጓደኛውን ግንባሩን ገመሰው›› (አሌክስ አብርሃም) የሆነ ጊዜ ሃላፊየ ወክለውኝ ሃላፊ ሁኘ ስሰራ . . . ሁለት ወጣቶች ቢሮየ መጡ . . . ሴትና ወንድ ናቸው ! ሁለቱም መስሪያ ቤቴ አካባቢ ካለ የሃብታም ልጆች ትምህርት🏢 ቤት ነበር አመጣጣቸው . . . የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪወች ሲሆኑ የሴቷ አለባበስ ያለማጋነን የኦስካር እጩ አስመስሏታል . . .በዛ ላይ ኑሮ ምችት ያላት ቆንጆ . . .በእንግሊዝኛ አፏን ስለፈታች ነው መሰል አማረኛ ገደል ሁኖባት ቃላትን እየፈለገች ነው የምትናገረው …ወንዱም እንደልጅቱ ባይሆንም ሽክ ብሏል …. 👱‍♀‹‹ የመጣነው ላሰብነው ፕሮግራም ስፖ….ንሰር እንድትሆኑን ነው ›› አለች ልጅቱ ብዙ ጊዜ ወደቢሮ ብቅ እያሉ ስፖንሰርየሚጠይቁን የቀበሌ የወጣቶች ..የሴቶች …የምንትስ ሰወች ወይም የተቸገሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ‹‹ስፖንሰር ›› የሚለው ፅንሰሃሳቡ ወይ የድሆች ወይ የፖለቲከኞች እየመሰለኝ ከመጣ ቆይቷል . . . እነዚህ ምቾት ያሰቃያቸው ልጆች እንዴት ‹‹ስፖንሰር ሁኑን ›› እንዳሉ ገርሞኝ ጉደዩን ጠየኩ 👱‍♀‹‹ ዩ ኖ . . . በትምህርት ቤታችን ‹የቲማቲም ቀን ልናከብር አስበናል . . . ዛት ማች ብዙ ብር ምናምን የሚፈልግ አይደለም …›› 👨‍💼‹‹የቲማቲም ቀን ? ›› ስል ጠየኩ 👱‍♀‹‹ያ …በቃ ተማወች የሆነ ሰአት ይወስኑና ግቢ ውስጥ ቲማቲም መወራወር ምናምን በጣም ያዝናናል ...ውጭ ምናምን የተለመደ ነው ..እናም በጎ ነገሮችን ወደሃገራችን ብናስገባ ቀስ እያለ ከትምህርት ቤት ወደሁሉም ትምህርት ቤቶች ከዛ በአገር ደረጃ በቃ የቲማቲም ቀን ተብሎ በአመት አንዴ ይከበራል . . . ›› ሁለቱም ገርመውኝ ተራ በተራ እያየኋቸው 👨‍💼‹‹እና ቲማቲም እየተወራወራችሁ ቀኑን ልታከብሩ ነው . . ?>> 👱‍♀<> 👨‍💼<<.አላማው ግን ምንድነው ?›› 👱‹‹ ጀስት ፈን! …እና ደግሞ አለ አይደል ሌላው <ወርል ድ> በፋሚን ድሮውውት ምናምን ነው ኢትዮጲያን የሚያውቃት ..የቲማቲም ቀን በማክበር ግን አገራችን ጀስት ከእርሃብ እንደወጣች ለማሳየት … በዛ ላይ ቦንብ ምናምን ድንጋይ የሚወረወርበት ጊዜ እንዳለፈና ፒስ መሆናችንን ለማሳየት ›› አለ ወንዱ ልጅ 👱‍♀‹‹በተጨማሪም ›› አለች ሴቷ ‹‹በተጨማሪም አሁን ያለንን የአበላል ሃቢት አለ አይደል ፒፕሉ ስጋ ቁርጥ ምናምን ያበዛል .. ይሄ ለብዙ በሽታ ስለሚያጋልጥ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲመገብ ፕሮሞት ማድረግም ይቻላል ›› ስትል አብራራችልኝ ! 👨‍💼ጎበዝ ተበላን ! እነዚህ የሃብታም ትምህርት ቤቶች ባለራእይ ትውልድ እያመረቱ ነው . . . ትክዝ ብየ አየኋቸው . . . ደመወዝ ጨምሩልኝ እያለ ሁለት ወር ቢሮየ የተመላለሰው የአራት ልጆች አባት ጋሽ ወጋየሁ ቢሮየ በር ላይ ቁሞ ይታየኛል ልጆቹ እስኪወጡ እየጠበቀ . . . ሁለት መቶ ብር ጨምሩልኝ ብሎ ሁለት ገፅ ማመልከቻ ፅፏል …ሚስኪን የቲማቲም ቀን ሲከበር ይሄ ሰውየ ‹‹የአበላል ሃቢቱን ያስተካክል ይሆን ? ›› እላለሁ . . . 👱‍♀‹‹ አስር ሽ ብር ምናምን ስፖንሰር ብትሆኑን . . . ›› ልጅቱ ቀጥላለች . . . እኔም በዓሉ ላይ ብገኝ እና ቲማቲም እነዚህ ልጆች ላይ እንዲሁም መምህራኖቻቸው ላይ ብወረውር ብየ ተመኘሁ ...እና በተለይ ወላጆቻቸው ላይ ....ግን እኔ የምወረውረው ቲማቲም በጣሳ የታሸገ መሆን አለበት . . . ግንባር ግንባራቸውን ! ቲማቲም ወርውሮ ትላንትና አንድ ሰው አንዱን ጓደኛውን ግንባሩን ገመሰው ደነገጥኩ አይቸ ሲንዠቀዠቅ ደሙ በጣሳ ውስጥ ነበር ለካስ ቲማቲሙ …..እንዲል ገጣሚው ! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 929
67
💚ህይወት💚 የገደል ማሚቶ ነው‼️ አንዲት ትንሽ ልጅ በእናቷ ተናዳባት <አሎድሽም!ብላ ትጮሀለች እንዳትገስፃትም ፈርታ በሩጫ ከቤቷ ወጥታ ርቃ ትሔዳለች ገደል አፋፍ ላይ ደርሳ አሁንም <አሎድሽም!<አሎድሽም!ብላ ስትጮህ የገደል ማሚቱ <አሎድሽም!<አሎድሽም!በማለት አስተጋባ ከዚህ በፊት የገደል ማሚቶ ድምፅ ሰምታ ባለማወቋ በሁኔታው እጅግ ትደናገጥና ታድናት ዘንድ ተመልሳ ወደ እናቷ በመሮጥ በገደል ውስጥ <አሎድሽም!<አሎድሽም!እያለች የምትጮህ መጥፎ ልጅ አንዳለች ትነግራታለች እናትየው ሁኔታው ስለገባት ለልጇ ተመልሳ ወደ ገደሉ በመሄድ <እወድሻለሁ!<እወድሻለሁ!ብላ እንድትጮህ ነገረቻት ልጅቱም ተመልሳ በመሄድ እናቷ እንዳለቻት <እወድሻለሁ!<እወድሻለሁ!እያለች እያለች ስትጮህ የገደል ማሚቶውም ያለችውን አስተጋባ፡፡ በዚህ አይነት ትንሿ ልጅ አንድ ትምህርት አገኘች ⚠️ - ህይወታችን የገደል ማሚቶ መሆኑን ፡፡ የምናገኘው የሰጠነውን ነው መልካም ነገረ ስንሰጥ መልካም ነገር ይመለስልናል በጎ ካላረግንም እንዲሁ ስለዚህ መልካም ነገረ እንድናገኝ ሁሌም ቢሆን መልካምነታችን ይብዛ🙏 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 271
34
በእውነት ጦርነት አስቀያሚ ነው ያስጠላል !...ግንየሰው ልጅ ያለ ጦርነት የኖረበት ጊዜ የለም !የሰው ልጅ ታሪክ የጦርነት ታሪክ ነው። የሰው ልጅ ያለጦርነት የሚኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን ?ምኞት ነው። የጦርነትን ጥፋት በሰው ልጆች ላይ የሚጋብዙ ሰይጣናዊ ኃይሎች እስካሉ ድረስ ምን ተስፋ ይኖራል ...? በአሉግርማ ፤ ኦሮማይ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 269
7
••●🍃 አይ'ኔ ●🍃 ,,,,,,,, የጥርስሽነፃቱ መች ይታያል ለእኔ አንቺን የሚያይበት ድፍረት የለው አይኔ ቆንጆ ነሽ ብትባይ አቻ የለሽ ወደር ውበትሽ ቢሰላ ባአድናቂሽ ቀመር በመአዛሽ ብቻ ልቤ እየሸፈተ አይኔ በሌለበት ምስልሽ ተከፈተ አይኔ የት ሂዶ ይሆን ማየት የተሳነው በህልም አለሜ ላይ ፍቅርሽ የተሳለው ከሚታየው መልክሽ በልጦ ማይታየው ለዛ ይሆን እንዴ እኔ ምሰቃየው ✍ቶፊቅ መሀመድ @Tufaw_muhe ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 419
33
እውነት … እኔኮ ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም … ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም … አብዝቶ ቅር ይለኛል … በሃገሬ በኑሮዬ በህይወቴ በእጣፈንታዬ በእድለቢስነቴ በቤተሰቤ አብዝቶ ቅር ይለኛል … ስጠጋው የሸሸኝ አይኑን ያዞረብኝ አምላኬን ካኮረፍኩት ብዙ ጊዜ ሆኖኛል … ብዙ ጊዜ ፀልዬ ጆሮ-ዳባ ልበስ ስላለኝ … የምወዳቸውን ከቀማኝ … ቀምቶም ልቤን እያሳዘነኝ አብዝቼ አኮረፍኩት … “የለህማ!” አልኩት … ብዙ ጊዜ ስለእናቴ ህመም ወተወትኩትና “እሷን ተውልኝ እኔን እንዳሻህ !” ስለው አልሰማህ አለኝና “ብትኖርማ …!” አልኩት ስስቅ ጊዜ ኩርፊያየን ረስቼ ገና “ተመስገን …!” ብዬ ሳልጨርስ ካሳቀኝ በላይ እያስለቀሰኝ አኮረፍኩት … የእድሌ መምረር ቢበዘብኝ … ለኤሊው እኔ ከፊቴ የደቀነብኝ የመከራ ተራራ ግማሹ ጋር ሳልደርስ ተንሸራትቼ ከጀመርኩበት ወዲያ ስወድቅ … ትክት አለኝና ለእምነቴ ያሰርኩትን ማህተብ በጥሼ “የለህም በቃ!” ብዬ አኮረፍኩት … ለመሮጥ ሳልሰንፍ … አቅም ሳያጥረኝ … ደረስኩ ያልኩበት ሲርቀኝ …. ድካሜ ሁሉ መና ሲቀር ክፉኛ አኮረፍኩትና “ትቼሃለሁ ተወኝ!” አልኩት … ግን … ሰው አይደለሁ ደግሞ !... በትንሽ ነገር እናቴ ስትበረታ … በልጇ ሳቅ ስትበራ … ለምስጋና ከከፈተችው አንደበቷ ተሸቀዳድሜ ደግሞ “ተመስገን !” እለዋለሁ … ኩርፊያዬን ረስቼ ነውኮ … ከዛ በፊት ስንት ለሊት በብርድልብሴ አፌን አፍኜ አለቀስኩ … ስንቴ እናቱ ድንግል ማርያምን “ልጅሽን ተው በይልኝ !” እያልኩ ተማፀንኳት … የትኛው ለሌቴ ያለእንባ ነጋልኝ… “ቅንጦት አይደለም የምለምንህኮ…. “ እያልኩ ጥርሴን ያልነከስኩበት እለት አልነበረም !... ደስ ብሎኝ የዋልኩበትን ቀን ረሳሁ … ሳላለቅስ የነጋብኝ ቀን አጣሁ … የህይወቴን ሽንቁር ልደፍን ተስፋ ሰንቄ ላይ ታች ብዬ ስባትል ደግሞ ሌላው ጎኔ ይቦረደሳል … ሞቴን እስኪያስመኘኝ … እረፍት እስኪናፍቀኝ … “ሰበሰብኩ!” ያልኩት ነፋስ እንዳገኘው ዱቄት ይበተናል !... ድክም አለኝ ድክም አለኝና “የለህም “ አልኩት “ ካለህ ግን በቃ የማትሰጠኝን አሳይተህ አታጓጓኝ … !” እና ብዙ ጊዜ ደስ አይለኝም ! … አብዝቶ ይከፋኛል ….በራሴ በእድሌ በሃገሬ በቤተሰቤ በፈጣሪዬ አብዝቶ ቅር እያለኝ ይከፋኛል አየህ! በዚህ ሁሉ የመከፋት እሳት ተለብልቦ ነው ልቤ የጠቆረው !🖤 ዘምሽ የአልግዬ 🖤የጠቆረ ልብ🖤 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 156
53
5 591
5
እኔ ማን ነኝ? እናንተስ? @My_life_is_amovie
6 004
7
መኪናውን… ሰውን … ቁልቁል እያየሁ … ! እዚህ ቦታ ስቀመጥ ሁልጊዜ ቀጠሮ ያለኝ ይመስለኛል …ያልቀጠርኩትን ሰው የምጠብቅ አይነት . . . ለነገሩ ህይወት ከቀጠርነው በላይ ያልቀጠርነው አጋጣሚ ጋር ስታጋጫን ነው ጣእሟ የሚሰማን . . . ድንገት ከፊቴ ካለውና አንድ ጠረጴዛ ከምጋራው የፕላስቲክ ወንበር ኋላ የቆመች አንዲት ምቾት መድረሻ ያሳጣት ሴትዮ‹‹ሰው አለው ?›› አለችኝ ፊት ለፊት ቁጭ አለች … ቁመቷ የትየለሌ …..አለባበሷ የሆነ የማይገልፁት ግን የሚያምር አይነት …ነገረ ስራዋ ሁሉ ረጋ ያለ ነው … መጀመሪያ ዣንጥላዋን አጠፈችና በስርአት ጠቅልላ የድሮውን ባለስሙኒ ባኒ ዳቦ አሳክላ ቦርሳዋ ውስጥ ከተተቻት …ቀጥላ ጥቁር መነፅረዋን አውልቃ ጠረቤዛውን በሶፍት እንደመወልወል አድርጋ አለመቆሸሹን ካየች በኋላ መነፅሩን የወለወለችው ቦታ ላይ አስቀመጠች … ወደደረቷ ግድም ያለ ልብሷን …ሳብ ሳብ እያደረገች ጡቶቿን እንደመሸፈን ይሁን እንደመግለጥ ባልገባኝ መሽሞንሞን !…. ተለቅ ያለች ሴት ናት ግን ደግሞ ሸንቀጥ ብላ ራሷን ላለፉት አስር አመታት በምግብ …በስፖርት በሳውና ባዝ እና በወዘተ በሚባሉ ስጋዊ ድሎቶች የጠበቀች አይነት …. ነፋስ ከበስተጀርባዋ ነፈሰ ….ሽቶዋን አምጥቶ አወደኝ …ከዛን ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ አራዳ ህንፃ ምንምን ይሸታል ቢሉኝ ያንን ያንን ሽቶ እላለሁ !አንድ ሰው ድንገት የዚችን ሴትዮ እድሜ ቢጠየቅ አፉ አምልጦት 30 ካለ በኋላ ቀና ባለ ቁጥር አምስት እየጨመረ አለ አይደል 35 …40 …45… እያለ 50 ድረስ መሄዱ አይቀርም ! 50 ከደረሰ በኋላም እንደገና መመለስና 45 …እያለ መገመቱ አይቀርም አለ ግራ አጋቢ ስጋ ! ይሄን ሁሉ ካደረገች በኋላ አንገቷን ቀና አድርጋ( ቀይ አንገቷ ላይ አግድም አራት የሚሆኑ ወደቡናአይነት የሚያደሉ እድሜ ወለድ መስመሮች አሉ የኮንሶን እርከን የመሳሰሉ ) አይኖቿን ወደሰማይ አንስታ ቁልቁል የተለቀቀ ፀጉሯን አርገፈገፈችና ‹‹ እፎፎፎይይይይ አሉ እተጌ ጣይቱ›› አለች ….ልክ እንዲህ ስትል ፊቷ ላይ ያለው እርግጠኝነት እቴጌ ጣይቱን በቅርበት የምታውቃቸው መስሎ እንዲሰማኝ አደረገኝ ….ያው ንግስቲቱ ፍልውሃ አረፋፍደው ወይ ቤተ ስኪያን ስመው እዛ እንጦጦ ሲመለሱ ‹‹ውይ እትየ መጡ እንዴ ›› እያለች ተቀብላ እግራቸውን ቀዝቃዛ ውሃ በተሞላ የእንጨት ገበቴ ለቅለቅ የምታደርግ እዛ ስታለቀልቅ አንድቀን ‹‹እፎይ›› ሲሉ በጆሮዋ የሰማች የአይን ምስክር መሰለችኝ….የንግስቲቱ አገልጋይ ጋር አንድ ጠረጴዛ የተጋራንም መሰለኝ …!በመምሰል ነው ነገር የሚጀምረው! እንደውም አፈጠጥክ እንዳልባል በተሸራረፈ ማፍጠጥ አይቸ አእምሮየ ውስጥ ሳገጣጥማት እድሜዋ ወደዛው ግድም የሚደርስ አይነት ትልቅ የማታረጅና የማትሞት ሴትዮ መስላ ታየችኝ … (አእምሮኮ ፊት ከሰጡት ) አይኖቿ ስር ያሉት በእድሜ ያኮፈኮፉ ከዛ ሳውና ባዝና ከዛ ጉድ የስጋ ጦርነት ያመለጡ የእድሜ አሻራዎች ብራና መስለው ትላንቷን ሹክ አሉኝ . . . የሴት ልጅ እድሜ ሃቀኛ ክታቡ ከአይን ስር ያለ ቆዳ ላይ እንደሆነ ያወኩትም ያኔ ነው . . . ሴት ጋር ስናወራ አይን አይናቸውን ስናያቸው ‹‹እፍር ›› አልን የሚሉት በተሽኮረመመ ማቀርቀር እድሜን የመሰዎር ጥበብ እንደሆነ ማን ያውቃል !! ብዙ ዘፈኖች ስለሴት ልጅ አይን እንጅ ከአይን ስር ስላለው ቆዳ ዘፍነው የማያውቁት ለምንድነው እላለሁ …ምናልባት ቦታው በአማርኛ ስም ስለሌለው ይሆናል … (ማነው የዛን ቦታ ስም የሚያውቅ) ደግሞ ለክፋቱ ይሄ ዘመነ ‹‹ሜካፕ›› ከአይን በላይ ላለው ሽፋሽፍት ‹‹ሻዶ›› ሲያዘጋጅ ከአይን በታች ላለው ክፍል ይሄ ነው የሚባል ሜካፕ እንኳን አለመስራቱ ይገርመኛል ! ኑሮስ እንደሆነ ምን አውቃለሁ ….ሰው አላዋቂ ነው… ይመስለዋል እንጅ ….ያወቀ የመጠቀ! ሴትዮዋ ድንገት ወደኔ ዞር አለችና ‹‹ውይ ቀይ አበዙበት እንጅ ዲዛየኑ ያምራል›› አለችኝ … ስለምን እንደምታወራ ግራ ገብቶኝ ስደናበር ቀይ ጥፍር ቀለም በተቀባ ጣቷ መንገዱን ተሻግሮ ወደሚገኘው ምንጣፍ መሸጫ እድሜ ጠገብ ቤት ጠቆመችኝ …ቀይ ምንጣፍ አሮጌው የጣውላ በረንዳ ክፈፍ ላይ ተሰቅሏል …ትክ ብየ አየሁት እባብ የሚመስል ጥቁር መስመር የተጠማዘዘበት ቀይ ምንጣፍ … ‹‹እ …አዎ›› አልኩ እንደው አልኩ እንጅ ጥሎብኝ የምንጣፍ ዲዛየን የመጋረጃ ቀለም የሚባል ውበት አይገባኝም !! ሴትዮዋ ዘና ያለች ናት …አስተናጋጇ ፊታችን መጥታ ቆመችና ‹‹ምን ልታዘዝ ›› አለቻት …ወደእኔ ዞር ብላ ቡናቸው እንዴት ነው ›› አለችኝ …አስተናጋጇፊት መጥፎ ነገር ተናግሬ አንድ መተከዣ ካፌየ ጋር ልጠማመድ እንዴ …ምኗን ጠንከኛ ላከብኝ . . . ‹‹ጥሩ ነው›› አልኩ ! ‹‹ቡና ›› ብላ አዘዘች ….ቡና እስከሚመጣ ምንም አላወራንም የሆነ አገሩ የናፈቃት ትመስላለች ዝም ብላ ታያለች አስተያየቷ የሆነ የራበው ሰው ምግብ ሲቀርብ እንስፍስፍ ብሎ የሚያየው አይነት ነው . . . ቡናዋ መጣ ….ቀመስ አደረገችና ቀና ብላ አይታኝ ‹‹ ሰራህልኝ ›› አለችኝ አነጋገሯ የወዳጅነት ነው ! ‹‹እንዴ አስተናጋጇ ፊት ስትጠይቂኝኮ ….›› ‹‹ፈገግ አለች …›› ፈገግ ስትል ድዷ ይታያል ጥሎብኝ ሲስቁ ድዳቸው የሚታይ ሰዎች ይሸክኩኛል … የሆነ አላጋጭ ነው የሚመስሉኝ …አለ አይደል ብዙ አመት በማላገጥ ጥርሳቸው እያጠረ እያጠረ ሂዶ ድዳቸውን መጠቀም የጀመሩ ! እንዲህ ነበር የተዋወቅነው አርፌ በተቀመጥኩበት …እጇን ዘርግታ በፈገግታ ስሟን ነገረችኝ ! ጥሩ ትውውቅ ነበር ይሄን ድዷን ብትሸፍንልኝ !! ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 202
39
‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ›› ከድድ አድማስ ኋላ አሌክስ አብርሃም እዚህ አራዳ ህንፃ የሚባለው አንደኛ ፎቅ የሚገኝ ካፌ በረንዳ ላይ ተቀምጨ ቁልቁል እመለከታለሁ …. እየተመለከትኩ ከዚህ በፊት ስለፈረሰው ትዳሬ አስባለሁ ….እንኳን የከበረውን ትዳር ለመተንተን ራሳቸውን ችለው መቆም የማይችሉ መደዴዎችን የትዳር ትንታኔ ስሰማ መኖሬ ነው ስለትዳር የተጣመመ እይታ እንዲኖረኝ ያደረገው እያልኩ እቆላጫለሁ ! ትዳር በማንም አፉን በየመንደሩ መክፈት በለመደ ቡሃቃ አፍ ሲተነተን ያቅለሸልሸኛል ! ትዳር መንፈስ ነው ለዛም ነው የስጋ እንቶፈንቶን መቁጠር ሲጀምር ጎጆ የሚያዘመው ….. እንደኔ እንደኔ ከዘልዛላ አብሮነት ‹‹ፍቅር›› ከሚመስልም መጓተት የፈረሰ ትዳር የተሻለ ክብር ይገባዋል እላለሁ !የግድ ጎትተው ፍቅረኝነት እና ትዳር አንድ ነው ልዩ ነቱ ያው ህጋዊ አለመሆኑ ምናምን ሲሉ መጀመሪያ አእምሮየ ውስጥ የሚመጣው ‹‹ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ጅግራ ነሽ ይሏታል›› ይሉት ፈሊጥ ነው !! አይቻለሁ በዚህ ፈሊጥ ስታመልጥ ፍልጣቸውን መዘው ዘራፍ ሲሉ ! ፍልጥም ፈሊጥም እጣ ፋንታን አይገዛም እንጅ!! ለዛም ነው ‹‹በፍቅር ያሳለፍነው ጊዜ እነዛ ጣፋጭ ጊዜያት ዋው ምናምን›› እያሉ ከሚያላዝኑብኝ የድሮ ፍቅረኛዎቸ በላይ ተፋተንም ቢሆን በትዳር አብሪያት ለነበርኩት ሴት ልቤ የሚደነግጠው ! የሆነ ማንትስ የሚባል ፈላስፋ ትዛዝ አይደለማ ትዳር ! አምናለሁ መለኮታዊ እስትንፋስ እንዳለበት …አየህ ፈጣሪህን በብዙ ነገር እንደማትታዘዘው ሁሉ በዚህም እሱን እምቢ ማለት በትዳር መፍረስ ውስጥ ዋናው መዘዝ ነው እላለሁ ! እውነት ነው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ላይስማሙ ይችላሉ (ሰበቡ ብዙ ነው) ….ትዳራቸው ሊፈርስም ይችላል ….ግን የማይፈርስ እውነት ውስጥህ አለ … ትዳር የሚባለው መለኮታዊ ጉዳይ አንተ ራስህ ስርአት ባይኖርህ እንኳን አንዳች መለኮታዊ ጥበቃ ያለው ክቡር አብሮነት ነው !! ለምን ይመስልሃል ፍቅረኞች ሲለያዩ ማንም የማይደንቀው …እ ተለያዩ እንዴ ብሎ ዝም ! እንደውም ‹‹ለበጎ ነው›› ይልሃል ! ባለትዳሮች ተፋቱ ሲባል ግን አግብቶ የማያውቀው ሰው ልብ እንኳን ሲደነግጥ ትታዘባለህ(ምን አስደነገጠው እስቲ) . . . የተፈጥሮ ህግ አክብዶ ልብህ ላይ የከተበው እውነት አለቻ …ትዳር አብሮ ጮርናቄ የመብላት አብሮ አልጋ ላይ የመንከባለል ተራ ጥምረት አለመሆኑን ሹክ ይልሃል ! አየህ የአንተ ማንነት ወይም የሚስትህ ምንነት ሳይሆን የቃሉ ህያውነት በጥምረቱ ውስጥ አንዳች ፍርሃትን የሚነዛ ሃይል ይለቅበታል … አንተ ርኩስ ብትሆን እንኳን (ያልረከሰ ሰው የለም እንጅ) ትዳር ቅዱስ ነው ሲል ነገሩ እዛው ላይ አብቅቷል ! ያንተ ስራ የፈጣሪን የድምፅ ሞገድ የሚያስቀይር ‹‹ሪሞት ኮንትሮል›› አይደለም ! ያ ነው ለሰው ያልገባው …. እዚች ልጅ ጋር ይሄን የመሰለ ልጅ እንዴት በትዳር ቆየ ወይም ውይ ይች መልአክ ልጅ እንዴት እዚህ ጋር አንድ ቤት ኖረች ….የሚል ጥያቄ ….የሰው ማንነት ላይ አይደለም ትዳር የሚመሰረተው አትድከም …እፍ የተባለበት ሃይል አለ ! ህያው የሆነ ቃል ! ለዛ ነው በምድር ታላላቆቹ የሆሊውድ ሰዎች ሳይቀሩ የትዳር ፍቻቸው አለምን የሚሞላ ዜና ሁኖ የሚራገበው !! በየምሽቱ ማንም ጋር ሲጋደሙ ማን ያወራል ቢበዛ ተራ ዜና ነው ! ማርታ ጋር ከተፋታን አመት ሆነን …አልዋሽም አንዳንዴ ትናፍቀኛለች …አለ አይደል በቀጥታ ወደቤቴ ሂጀ እንደድሮው ጉንጯን ስሜ እሽ ውሎ እንዴት ነበር ብየ ምንም እንዳልተፈጠረ ነገሩን ከቆመበት ልጀምረው ያምረኛል ሃሳቡ ራሱ ያረካኛል !ይሄ ሁሉ ለመሳም ተወልውሎ የሚወጣ ጉንጭ የብርጭቆ ወረቀት ነገር ይሆንብኛል ! አንዳንዴ ታዲያ የሚያውቁኝ ሴቶች ጋር እገናኝና ስናወራ …ስናወራ ብቻ አይደለም በተፋታ ሂሳብ መንጎዳጎድም አለ ….‹‹ውይ ይሄኮ ያጋጥማል አትጨናነቅ ባክህ ህይዎት ብዙ አማራጭ አላት ምናምን›› እያሉ ያወለቁትን ቀሚስ ወላ ሱሪ መልሰው እየለበሱ . . . ይሄ ቀሚስ ስንት ቦታ ወልቆ ይሆን እላለሁ ….የአወላለቅና የአለባበስ ፍጥነታቸው አንዳንዴ ልምዳቸውን ይናገር የለ !ደግሞ ተኝተው ከተነሱ በኋላ ፊታቸው ላይ የሆነ ርካታ አለ ‹‹ጣልኩት›› አይነት የድል ፈገግታ ….ሰው አብሮ ወድቆ ሌላውን የጣለ ሲመስለውኮ ነው የምደመመው ! በአይናቸው የተከፈለ ማንነቴን ከራሳቸው የተረገመ ግማሽ ጋር ሊቀላቅሉት ሲቋምጡ እየታዘብኩ እገረማለሁ ! በነገራችን ላይ ታዝቢያለሁ ብዙ ሴቶች ከነመፈጠሩ እንኳን ትዝ የማይላቸው ወንድ ባለትዳር መሆኑን ሲያውቁ የሚያንቀዠቅዣቸው ነገር አለ …!!ትዳር ፈረሰ ሲባል ያልደነገጠች ሴት እንዴት ነው ትዳር ከእርሷ ጋር መመስረት አክብዳ የምታየው …የእህቷ ስጋ ፈራሽ የሷ ዘላለማዊ የፀና ግንብ ነው እንዴ …‹‹እኔ እንደሌሎች ሴቶች አይደለሁም ›› ይባልልኛላ ….ለምን ብትላት ፀጉሬን የምሰራው ውድ ቤት ነው ለማለት ! ፀጉርም መንፈስ ነው ልብስም መንፈስ ነው … ታከብረው ዘንድ የተሰጠህን አንተነት በፍቅርም ስም በለው በምን የጣልከው ቀን ሁሉም መላጣ ነው ! በቃ ትዳር ቦርሳ አንጠልጥሎ የባልን ክንድ ይዞና ቀለበት ሰክቶ ሰበር ሰካ ይመስላቸዋል ….እንዲህና እንዲያ እያሰብኩ አራዳ ህንፃ ላይ ተቀምጨ ቁልቁል አላፊ አግዳሚውን አያለሁ . . . አራዳ ህንፃ ለምን እንደሆነ እንጃ ህንፃ አይመስለኝም ….መሃል ፒያሳ ቁሞ ጥርሱን የሚፍቅ ጎልማሳ ነው የሚመስለኝ ! ህንፃው የሆነ ሌላ ህንፃ ቀጥሮ የሚጠብቅ ጎልማሳ ….አለ አይደል ሌላ ሴት ህንፃ ምናምን… ምናልባትም ህንፂት የምትባል የመስታዋት ቀሚስ የለበሰች የአሉሚኒየም ብራዝሌት የደረደረች ዘመናዊ ሴት ህንፃ … ህንፃ ነብስ የለውም ያለው ማነው ?…የስንት ወዛደር ደምና ላብ ትንፋሽና ምሬት ከስሚንቶና ብሎኬት ጋር ሰርጎ ሰዋዊ መሻት እፍ ብሎበት ቢሆንስ ….ማንም አያውቅም በተለይ ሰው አላዋቂ ፍጡር ነው ! ፊታችን የቆመውን ሰማኒያ ኪሎ ስጋና አጥንት ባይን ከመመዘን ያለፈ ምን እውቀት አለን ….ቃል አጋጭተን ከጨመቅነው አመክንዮ እውነት ያልነውን ጭማቂ ከመጨለጥና ከማግሳት ያለፈ ምን መገለጥ አለን ….ሰው ነና …ቆይ በደንብ ይጨመቅ አንል ነገር ጥማችን ፋታ አይሰጠንም) ህንፃና ህንፃ ፒያሳ ሲቀጣጠሩ ህንፂት ከወደሜክሲኮ ወላ ከወደሃያሁለትና ቦሌ እየተራመደች ትመጣለች ማለት ነው ? አይደለም! …ግን ፊት ለፊት ያሉ አሮጌ ቤቶችን በአመፀኛ ዳሌዋ ገፋ አድርጋ እነሱ ቦታ ላይ ልክ በቀጠሮ ሰዓቷ ብትበቅልስ … አሁን አራዳ ህንፃ ፊት ለፊት ያሉትን ጭርንቁስ ቤቶች አፈራርሳ አንዲት ሴት ህንፃ ብትቆም ‹‹ታሪክ ተደመሰሰ ›› እንጅ አራዳ ህንፃ ሲጠብቃት የኖረችው ሴት ህንፃ መጣችለት … ብሎ ለህንጻዎች ፍቅር የሚያጨበጭብ ማነው …. እያልኩ ቡና እጠጣለሁ. . . አቤት ቡና ስወድ ! እኔ መቸም ሊገድለኝ የሚፈልግ ጥሩ ጠላት ቢኖረኝ ቡና ውስጥ መርዝ ጨምሮ እንዲሰጠኝ ነበር የምመክረው ! ሞት በምትወደው ነገር ሲገለጥኮ የሆነ ውበት አለው ….ከሞቱ አሟሟቱ ማለትኮ አሟሟት ከሞት እኩል ዋጋ እንዳለው አመላካች ፈሊጥ ነው !
Show more ...
5 797
51
"የፍቅር ቃጠሎ" (ገብረክርስቶስ ደስታ) ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ፡፡ የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡ ቆንጆ ነሽ አንቺዬ እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ ሆነሻል ሙቀቴ ሆነሻል ህይወቴ፡፡ የጋለው ትንፋሽሽ የሞቀው ምላስሽ ማርኮኝ በከንፈርሽ እጄን ሰጥቻለሁ እስረኛ ሆኛለሁ፡፡ ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ ልቤን አስፈራርቶ ትኩሳት አምጥቶ፡፡ ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ እቀፊኝ ልቀዝቅዝ ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 950
51
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 7 ✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ "" "" የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወርቀቱ እንዲህ ይላል ሰላም ላንተ ይሁን ጠበቃ አዳም የጠበቃ እስማኤል ወዳጅ ነኝ ወዳጅ ብቻ አይደለሁም መከታዬ ነው ወንድሜም ጓደኛዬም ሁሉም ነገሬ ነው ለፍትህ ዘብ የቆመክ ለእውነት የምታድር ሰው መሆንህን አውቃለው እስማኤል ፍትህ ለተራበ የሚያጠግብ ለጎደለበት የሚሞላ ነው እስከኖረበት ጊዜ ለእውነት ኖሯል በመጨረሻም ግን ለአንድ አውሬ ሰው ተበገረ ይህ አውሬ የወዳጄ እስማኤልን ህይወት ቀጥፎብኛል አንተም እንደሱ ነህ ባንተ በኩል ፍትህ ያገኙት ስላንተ አውርተው አይጠግቡም እጅግ የጠበቀን ወዳጄን ህልም እንደምታስጨርስው እርግጠኛ ነኝ ትወጣዋለክ እንደምትወጣው አምናለው አንብቦ እንደጨርሰ ያን በተለያዩ ልኮች የተፃፈውን እና አርንጎዴ ክር የተያዘውን ደብተር ከፍተው ውስጡ በሉኮቹ ላይ የሰፈሩትን ተመለከተ ፅሁፎቹ እጅግ የተዋቡ ናቸው በሰማያዊ እና በጥቁር እስኪብርቶ የተፃፈ ነው የታሪኩ ርእስ መንገደኛው ሎሌ ይሰኛል መንገደኛው ሎሌ መሄድ የለመደው አንድ ቀን ተነስቶ መጓዝ የጀመርው በሄደበት ሁሉ ብዙ ይታዘባል ተመልካች ታዛቢ ሁሉንም ይሆናል ዛሬ ከቆመበት መንገዱን ጀምሮል ብሎ አጠር ባለ መልኩ መንገደኛው ሎሌን ገልፇታል መንገደኛ ስሙን ደሞ በሎሌ ቀይሮ የእዛን አውሬ ስራ አስፍሮታል። አዳም መፅሀፍን ማንበብ ቀጠለ መፅሀፉም እንዲህ ይላል። ይገርማችዋል ዛሬ መንገዱኛው ሎሌ እንደለመደው ጉዞውን ቀጥሏል እየሄደ በመንገዱ ያጋጠሙት ደሀ እናት እና ልጅ ን አየ እስከሚችለው ሊከተላቸው ወስኖ ሳይሆን እግር መንገዱን እያያቸው መጓዝ ጀመር እናትና ልጅ በፀጥታ ከተጓዙ በኋላ ልጅየው እናቷን ሽቅብ አንጋጣ እያየች እናቴ አለቻች እናት የስማቻት አትመስልም የእኔ እናት እናትዬ እማ እያለች ስትጎቶጉታት ሀሳቧን እና መንገዷን ገታ አድርጋ ወዬ የእኔ ልጅ አለች በጣም በደከመና ትንፋሽ በተቀላቀለበት መለኩ እማ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ እሽ እሺ ልጄ ጠይቂኝ ፍቅር እና መውደድ ልዩነት አላቸው እንዴ እንዴ እናትም ልጄ በጣም እንጂ በጣም ልዩነት አላቸው ልጅየው እንዴት አለቻት እናት ልጆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ልጄ አለቻት ልጅም እሺ እማ አለቻት ጥንድ ጥንድ የሆኑ አካላቶችሽን ንገሪኝ ብላ እናት ከመናገሯ ልጅት ጥንድ ጥንድ የሆኑት ለምሳሌ አይናችን ሁለት ነው አለች እናት እሺ ሌላስ አለቻት ሌላ ደሞ እጃችን እግራችን ሌላስ አለች እናት ልጅቱ ሌላ ጆሮአችን ሌላ ግን የለም አለቻት እናት ፈገግ ብላ ተሳስተሻል የእኔ ውድ ልጅ አለቻት ልጅም እኔ የምልሽ እማ ይህ አሁን ከጠየቅሽኝ ጥያቄ ጋር ምን አገናኘው ያገናኘዋል እንጂ ልጄ እይውልሽ እንዳልሽው እጃችን እግራችን አይናችን እና ጆሮችን ብቻ ሳይሆን ከልባችን በቀር ሁሉም አጋዥ አለው ልጅየው ግራ ገባትና እንዴት እናቴ አለቻት ለምሳሌ ጣትሽ ስንት ነው 10 እሺ ጨንጓራችንንስ እኔጃ እማ እሱም ትንሹ እና ትልቁ አንጀት የሚባሉ አጋዦች አሉት ፀጉሯችንንም ብዙ አሉት ከንፍራችን ደሞ ከላይና ከታች አለ ጥርሳችንን ተመልከች ብዙ ናቸው ሊላም ብዙ ጥንድ ነገሮች አሉ ሁለም አጋዥ የላችውም ልባችን ግን ብቸኛ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ደሞ ሊ ሌላኛው ልባችን ጋር ሌላ ሰው ጋረ ስለሆነ ነው አለች እናት ልጅቱ እየተገረመች ማን ጋር? ብላ ጠየቀቻት እናትም የወደፊት የህይወትሽ አጋር ጋር እሱ ጋር ነው ለዛም ነው ፍቅር ሲይዘን ሁሉም ነገራችንን የሚቆጣጠርን ፍቅር ሲይዘን ሁሉም አካላታችን ስራውን አቁሞ ልባችን የሚስራው ፍቅር ሲይዘን ልባችንን የሚስማን ፍቅር ሲይዝሽ በ ፍቅር ካፍቀሩት ጋር መኖር እድለኝነት ነው። አዳም ንባብን በእዚህ ገታ እና ወርቀቱን ከደነው። የማያልፍ ቀናት የለም አለፈ ዛሬ ሄዋን ከጥቄት ሰአታት በኋላ ትነቃለች አዳም ውስጡ ደስ አለው ቀጥሎ የሚፈጠረው ነገር መልካም እንደሚሆን አሰበ ስትነቃስ አለ በልቡ ስትነቃስ እንዴት ነው የምቀርባት ሁሉንም ነገር እኮ እረስታለች ድጋሚ እንድትወደኝ ላረግ ነው ስቀርባት ማነህ ብትለኝስ ልቡ ፈራ ውዴ እረሳሽኝ ወይ እስቲ መልሽለኝ ምነው ቢሆን ለእኔ ሁሉን ባርገልኝ ብዬ ለመንኩትኝ ሀሳቤን ቢስማኝ ብዬ በመጠበቅ ይህው ወራት ሞላኝ ለእሱ ብዙ ነገሩ ናት የሄዋን እጃች በትንሹ መንቀሳቀስ ጀመሩ አላመነም ዶክተሩ ትነቃለች ቢለውም የሚንቀሳቀስ እጇን ሲያስ አዳም ደስስስ አለው ዶክተሩን ለመጣራት ከነፈ አጠገቡ ማንም አልነበርም ዲና በጠዋት ቤቷ ፍቅድ ጠይቃ ሄዳለች ዲና በመንገድ ላይ እና ቤቷም ከገባች በኋላ ሰለ አዳም ያለ ማቆርጥ ታስባለች ዲና ስልኳ ጠራ አዳም ነበር ሄሎ አለችው በተርጋጋ ድምፅ....... ✨ይቀጥላል........ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 113
55
#repost በሂወቴ ከሰራዋቸው ትላልቅ ስህተቶች መሀል ፈርጄህ በምንም ተአምር ስህተትን ላለመድገም ምዬ ተገዝቼ ነበር:: ቀናት በወራት ሲተኩ ወራት አመታትን ቢወልዱ አለፈ መባሉ አልፎ ታሪክ ሆነ ቢባልም አብሮነታችን አንጂ እኛ ታሪክ አልሆንም.....ታውቃለህ አለሜ ያ ሀሉ ጊዜ አልፎ ዳግም ስነገናኝ...ዳግም አይንህ ሳይ...ስረግምህ አንዳልኖርኩ አፌ ተሳሰረ ....ወኔዬ ሁሉ ጠፍቶ ልቤም ባንዴ ራደ!!ለካ......ጠላውት ብዬ ራሴን አታልያለው በቃ አለፈ ብልም ያለፈውን ናፍቅያለው!! .....ቆይ ግን ለምንድን ነው የገዛ አጆቼ ወደ አቅፍህ የሮጡት አንዴትስ ሆኖ ነው አንደበቴ ክዶ አይኖቼ ያሳበቁት? በምን ተአምር ነው የለቀኩት መዳፍ ዳግም ሲዳስሰኝ እምቢ ልል ያልቻልኩት??..... በደልህን ብቻ ሳይሆን ራሴንም የረሳሁት የ አመታት ጥላቻን የዛው ቀን ቀበርኩት.......ግንኮ ሀቅ ነው!! አንደ ድሮ አልነበረንም የደሮውንም አኖንም ግና በዛች ቅፅበት የዛሬን ረስቼ ትላንትን ኖርያለው..... ......✍elu jaz🦋 @Elujaz ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 407
50
ትዕግስተኛ ሰው ውሃን በወንፊት መያዝ ይችላል ፡፡ ዋናው ነገር ውሃው ወደ በረዶ እሲኪቀየር መታገሱ ላይ ነው ፡፡ አንተም ህይወቴ አሁን ተቦክቶ ፤ አሁን ኩፍ ብሎ ፤ አሁን ተጋግር ፤ አሁን ካልቆረስኩት ሙቼ እገኛለው አትበል ፡፡ ሁሉም ነገር የሂደትና የትዕግስት (የመጠበቅ) ጉዳይ ነው ፡፡ ከእንቁላል ጫጬት እንደሚገኝ የታወቀ ነው ፡፡ ነገር ግን ጫጬቱ እንቁላሉን ሰብሮ ሳይወጣ ተቻኩለክ አንተ ብትሰብረው የምታገኘው ሁለት እግር ያለው ጫጬት ሳይሆን ፈሰሽ አስኳልን ነው ፡፡ የአብዛኞቻችን ችግር ምን እንደሆነ ታውቃለክ ወዳጄ ? መጠበቅ ሚባል ነገር አንወድም! አዎ ትዕግስት ብሎ ነገር አልፈጠረብንም ፡፡ ለማንኛውም መልካምና ታጋሽ ሁናችሁ ዋሉ ፡፡ የረጋ ወተት ቅቤ ይወጠዋል ይላሉ አበው ሲተርቱ እኔም ቀበል አድርጌ ረጋ እንበል እላለሁ ፡፡ በመረጋጋት ውስጥ ልምድ መውሰድ ፣ በመረጋጋት ውስጥ ያሉንን አማራጮች ማየት ፣ በመረጋጋት ውስጥ መብሰል አለና እንረጋጋ እላለሁ ፡፡ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 487
61
እንደ ሰው .... ተፋቀርን ጥል ቢጤ ጣል ጣል በፍትወት መጋል ... ሁሉን አደረገን ሙቀትሽን ሞቅኳት ... እንደ ተቃቀፍን ኩርፊያ ጥሎ መሄድ ጥፊ ፊቴ እስኪነድ ጉርሻ እስኪልሽ ትን "ዎክም" እስኪደክመን ስንዴ በእጄ ይዤ እንደተጠጋኋት ... ወፊቷ ሳትበሪ መሆን ያለብሽን ሆነሻል ለእኔ ... ቅንጣት ሳታስቀሪ ግን ተውኩሽ ጠፋሁ ጥዬሽ .... ምናልባት ካልሽ " ለምን? " ይንገሩሽ ይህንን " ስላልሆንሽ ለእኔ ፥ መሆን የሌለብሽን ! " ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 868
43
""አትርሺው"" ።።።።።።።።።።።።።።።። አይረሳም ለኔ ያንን ሁሉ ጊዜ አረሳው ብሎኛል የውስጤን አባዜ እንዴት ይረሳሻል ጭቃ ያቦከንበት በማያቅ ልባችን ፍቅርን ያየንበት እረሺኝ ለኔ ባዮን እሱን ከምትረሺ ያን ሁሉ ህግጋት ባንዴ ከምጥሺ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። "አትርሺው" አትርሺው እባክሽ እኔ ብትረሺኝም ያሳለፋነው ጊዜ አስታውሺው ሁሌንም እኔ አ..ረሣውም ከልቤ አዮጣም ያንን ጣፋጭ ጊዜ ሚረሳ የላኝ ልብም "ይረሳል ወይ?" እስኪነጋ ጨንቆን አንድ ላይ እስክኖን ጸሀይ ስትገባም በናፍቆት ተላቅሰን እንዴት ይረሳሻል ያን ሁሉ ትዝታ እኔስ ልብ ተቀብሯል መቼም ላይገታ ........... ካሳለፍነው ይልቅ ተለያይተን ብንኖር ምትጠብቂኝ መስሎኝ ቃላችን በክብር ግን ዛሬ እረሳሽ ሁሉንም ቀበርሺው ቃል የገባሽውም ብለሽ ላረሳው "አትርሺው" እርሺው ቢሉሽ እንኳን እኔን ላይሆንሽ ጉጉታቸው አርገው ለነሱ ሊያረጉሽ አታውጪው ከልብሽ ዘላለም አኑሪው ልብሽ ባዮደውም በብእር ቅረጪው አትርሺው እኔ ብትረሺኝም ትዝታው አትርሺው ✍ በቶኒ ይፋቱ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 082
40
ነፍስ ይማር ስለ'ኔ ስላንቺ ካህናት በወረብ ፣ ሼሆች በመንዙማ ባርምሞም በጩኸት፤ ይቀኛሉ ቅኔ ፣ ይዜማሉ ዜማ ቅዱስ ለፍቅራችን ቅዱስ ለጠባችን ቅዱስ ለፍጻሜው በ'ንባሽ ታንቆ ፍቅር ፣ ላለቀበት እድሜው ስብሃት ሶስቴ ላንቺ ፣ ስብሃት ደግሞ ለ'ኔ ለደከመው አካል ፣ ለደቀቀው ጎኔ ፍትሃት ለዛ ፍቅር ፣ ፍትሃት ለዛ ተስፋ በኩርፊያሽ ተዳፍኖ ፣ በእምባሽ ለጠፋ ወዩ ለትግስትሽ ፣ ሞቷል መጠበቄ ነፍስ ይማር ለሳቅሽ ፣ ነፍስ ይማር ለሳቄ [ቶማስ ትግስቱ] ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
6 420
36
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 6 ✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ "" "" አዳም ድካም እየተስማው ሲመጣ ሌላኛው አግዳሚ ወንበር ላይ ሄዶ ጋደም አለ ግን ነገ ሄዋን ስለምትነቃ በጉጉት ሊሞት ነው ሄዋን ከነቃች በኋላ ለሚፈጠርው ነገር እራሱን አእምሮውን አዘጋጀ ሄዋን ነገ ከኮማ ስትነቃ ልክ እንደማታቀኝ ልታስመስል ነው ወይ ብሎ እራሱን ከጠየቀ በኋላ መልሶ ለእራሱ አይ አይ ሄዋኔ ወዳ አደለም የረሳችኝ እንደዚህ መሆኗስ ለእኔ ስትል አደል አለና እራሱን አፅናና እንዲ ከራሱ ጋር በሀሳብ ሲሞገት ሳያስበው እንቅልፍ አሽለበው። የሆነ የሚያስፍራ ኮቴ ሰማ በቀስታ የሚጓዝ ማን እንደሆነ ለማየት ቀና አለ ምንም አይነት ሰው አልታየውም መልሶ ተኛ አሁን የሚንሾካሾክ ድምፅ ሰማ ቀና ሲል ከእሱ ትይዩ የተኛችው ዲና የለችም የት እንደሄደች ግራ በመጋባት እና በፍርሀት ስሜት ወደ ሄዋን ክፍል እያመራ ሳለ ዲና በ2 ትልልቅ አቅም ባላቸው ስዎች ተይዛ በጥቁር ፕላስተር እጇ አፏ እና እግሯ ተይዟል በአስተማሚ ወንበር ላይ ጥብቅ አድርገው አስርዋታል ። አዳምን ስታየው በተቀመጠችበት ወንበር ላይ መወዛወዝ ጀመርች አዳም ከታስረችው ዲና ትይዩ ኮማ ውስጥ ያለችውን ሄዋንን አንድ ጭንብል ያርገ ሰው በህይወት እና በሞት መካከል እስትንፋሷ የሆነውን ማሽን አዳምን ፍገግ ብሎ በ ሰራውልክ አይነት አስተያየት እያየው ነቀለው አጭር ጩሀት ሰማ ዞር ሲል ዲናን ድምፅ በሌለው መሳሪያ አናቷን በታተኑት አዳም አይይይይይሆሆሆሆንንምምምምምምም ብሎ ጮከ ኧረ ድረሱልኝ ሰው የለም እንዴ እያለ ቢጮክም ምንም አይነት ሰው ሊደርስለት አልቻለም አዳምን የሆነ ባትሪ መሰል መብራት ነገር ስውነቱ ላይ ጭንብል ከለበሱት ውስጥ አበራበት አዳም አቅም አጠርው መንቀሳቀስም አልቻለም ከቆይታ በኋላ የአንድ ሰው ኮቴ ተሰማው ይህንን ኮቴ ያውቀዋል ሁለት እግር አንድ ከዘራ ባለ ከዘራው እና ባለ ብዙ ሀጢያቶች ባለቤት ይህ ሰው ሄዋን ለእዚህ ችግር እንድትጋለጥ ያረገው ሰው ነው ፈገግ እያለ ወደ አዳም ቀረበው አዳምም አይሆንምም ብሎ ከህልሙ ነቃ ዲና ደንግጣ በርግጋ ተነሳች ምንነው ችግር አለ አዳም አለችው እሱም የለም ተኚ ብሏት በጥድፊያ ሄዋን ጋር ሄዶ በመስታወቱ ያያት ጀመር። እውነት ቢሆንስ ቆይ ህልሜ ካንቺ ተለይቼ እንዴት እኖራለው ብሎ ተንስቀሰቀ። ይህ ሰው ጌዲዬን ይባላል በወንጀል የታወቀ ነገር ግን መፍትሄ ያልተገኘለት ሰው ለብዙ ህፃናት ደሀዎች እና ፍትህ ፍላጊዎች እልቂት ተጠያቂ እጁ እስከ ከፍተኛ የወንጀልም ሆነ የቢዝነስ ነክ ጉዳዎች ላይ የሚረዝም ከፈለገ ምንም ማድርግ የማያቅተው ህይወት ያለው ሰው የሚታዘዘው ነው። ታዲያ ለእሱ አለታዘዝ ያለ ስው በህይወቱ ፈርዶ ነው ባአስቃቂ እና በሚዘገንን መልኩ ያስቃየዋል በቁሙ በህይወት እንዳለ ያለ በለዚያ ፈፅሞ አይርካም አንድን ሰው ገደለ ማለት በጣም ጥሩ ስራ እንደስራ ነው የሚስማው ሰውን በቁሙ ማስቃየት በአለም ላይ ለእሱ ትልቅ ፌሽታ ነው ሁሉም ሰው የእዚህ ስው ስም ሲነሳ ይንቀጠቀጣል። አዳም በጥብቅና ሙያው ማንም የማይስተካከለው እልልልል የተባለለት ጠበቃ ነው ስራ የጀመርው ከአመት በፊት ቢሆንም ባጭር ጊዜ ባጭር የፍርድ ቀጠሮ ብዙ አልበገር ባይ እና ወንጀል ስርተው የሚሸሽጉ ስዎችን አጋፍጦ ለፍርድ ልኳል ወደ ሚገባቸው አስናብቶቸዋል ።ጠበቃ አዳም ማለት ለወንጀለኖች ስይጣን ፍትህ ለተነፈጉ ደሞ መላክ ነው። ጌዲዮን የአዳምን የጥብቅና ችሎታ እና ዝናውን ሰምቶ በቢዝነስ ይሁን በማንኛቸውም አይነት ጉዳዮችን አብሮት እንዲሆን በረብጣ ገንዘብ ድርድር ያቀርብለታል ጊዲዮን በዙሪያው ሌሎች የእራሱ ጠበቆች ቢኖሩትም የአዳምን ጥብቅና ግን አብዝቶ ፈልጎታል አዳም ግን የጊዲዮን ድርድር ሆነ ገንዘብ አላማለለውም ጠበቃ አዳም ለህሊናው የተገዛ ለፍትህ ጥብቅና የቆመ ለእውነት የሚኖር ሰው ነው ። ልክ እንደ አዳም በጊዲዮን አልመራ ያለ እና ጊዲዮን በቁሙ አስቃይቶ የገደለው እስማኤል የተባለ እሳት የላስ ጠበቃ ነበር እስማኤል የጊድዮንን ትእዛዝ አለመቀበል ብቻ ሳይሆን ሊያስፈርድበት ሂደት ጀምሮ ነበር በጊዲዮን ሴራነት ሰውን ያለ ምክንያት በሀሰት በመፍርድ ተብሎ ተከሶ ለእርዥም አመት ታስሮ የታሰርበት እስር ቤት ውስጥ በጊዲዮን ትዛዝ መሰርት የታሳሪያን ሻውር ቤት ውስጥ ሞቶ ነበር የተገኘው ይህንን ጠበቃ መጀመሪያ የሚወዳቸውን ስዎች በመግደል ነበር አይምሮውን የገደለው ጌዲዮን ይህ ነው ቁመቱ እጅግ የረዘመ የአይኑ ብሌንን ትኩር ብሎ ለተመለከተው ልክ እንደ በርበሬ የቀላ መልኩም ወደ ጥቁር ያደላ ሰው ነው። ጋሞ ጎፋ እንደሆነና ይህንን ፀባዩን ከአባቱ እስከ ሰውነት አቆሙ እንደወርሰው ይወራል ብዙ ሴቶችን አስርግዞ አረገዝኩ ብለው ሲነግሩት የፀነሱትን ፇታ ካወቀ በኋላ ሴት ከሆነች ከእነ እናትየው ይገላታል የተረገዘው ወንድ ከሆነ ግን እስኪወለድ ጠብቆ እሱን ካልመስለ ይገለዋል ከመሰለ ግን አሳድጎ ገረዱ ያርገዋል ይህንን ታሪኩን መንጉደኛው ሎሌ በሚል ርእስ ያ እሳት የላስ ጠበቃው እስማኤል ፅፎታል እንዲፅፍ የረዳው ደሞ የጌዲዮን አሽከር ነበር፡፡ አዳም ጠረፔዛው ላይ ፒያሳ አራዳ ጋር 9ስአት ጠብቀኝ የሚል አጠር ያለ ፅሁፍ አገኘ አዳም የሰውየውን ማንነት ሳያውቅ የተባለበት ቦታደረሰ ምናልባት ፍትህ የተነፈገ ሰው ስለሱ ሰምቶ ሊያገኘው እንደፈለገ አልተጠራጠረም ፒያሳ ጋር እንደደረሰ የሆነ ኩትት ያለ ልብስ የለበሰ ሰው ላዳ ይዞ ና ግባ እኔ ነኝ የጠራውክ ብሎ ካስገባው በኋላ ጭር ያለ ቦታ ወሰደው ሲደርሱ የተቀመጥከበትን ወንበር ግለጠው እና እየው ብቻህን ሆነክ ክፈተው ተጠንቀቅ ማንም እንዳያይክ እዚህ ውስጥ ስለከተትኩህ ይቅር በለኝ ግን እንደምታስተካክለው አውቃለው አለውና ቤቱን ሳይነግርው ወደ ቤቱ አደርሰው አዳም ቤቴን እና መስሪያ ቤቴን እንዴት አወቀ ብሎ ለእራሱ ጠይቆ ለስውየው ሳይጠይቅ ወረደ ቤቱ በጥድፊያ እንደገባ ቦርሳውን ከፈተው ቦርሳ ውስጥ በብዙ የተለያዩ ልሙጥ እና ባለ መስመር ሉክ ለሁለት ታጥፈው በእስቴፕራል ሳይሆን በአርንጓዴ ክር የተሰፋ ደብተር አለ ሳያነበው እየገላለለጠ ማየት ጀመር የብዙ ስው ፎቶዎች እና ከፎቶዎች ስር ማብራሪያ ተፅፏል ደብተሩን ከደነው እና ቦርሳ ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ ስአት አገኘ በድጋሜ እጁን ሰደደው የሆነች እጥፍጥፍ ያለች ወረቀት አገኘ ወረቀቱ እንዲህ ይላል.... ✨ይቀጥላል.... ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 676
51
ጥቁር_ነኝ የፈርጦች ፈርጥ እንቁ መልኬ የሚያበራ፣ የልዩዎች ልዩ ሆኖ የተሰራ፣ የተሰጠኝ ከላይ ለጋስ እጆች ካሉት፣ መልኬ ኩራቴ ነው ለዛ ነጫጭባ ሂዱና ንገሩት። ወድቄ የማልወድቅ ዳግም የምነሳ፣ ለኔዎቹ ኩራት ለጠላት አበሳ፣ ዛሬም ነገም ጥቁር ጀግና ነኝ አንበሳ። ባያቶቼ የደም ዥረት በላባቸው፣ ተሰቶኛል የቀና ቤት በነፍሳቸው፣ ለኔ መቆም ባደባባይ በከተማ፣ አብርተዋል የድል ችቦ የድል ሻማ። ሽንፈት የታባቱ ጭራሽ የኔ አይደለም፣ ድሮም አልነበረ ወደፊትም የለም፣ የታነፅኩኝ ልባም የጀግና ክብር ያለኝ፣ ዛሬም ነገም ሁሌም እኔኮ ጥቁር ነኝ። በእጁ ለሠራኝ ለፈጠረኝ ጌታ፣ አመስጋኝ ነኘ እኔ ላለብኝ ውለታ፣ ያለኝን ሚባርክ አለሁኝ ለሚለኝ፣ የማላማርረው እኔኮ ጥቁር ነኝ፣ የደሜ ምንጭ ቅጂ የመልኬ ሚስጥሩ፣ ሲያናንቁኝ ኖረው ሲረግጡኝ ለኖሩ፣ የትርጉም ባለቤት የዐለም ጀማሪ፣ የሁሉ ጠቅላይ ገዥ ያቦጊዳው መሪ፣ ዛሬም ነገም ጥቁር ክንፍ አለኝ በራሪ። ✍ ቤተልሔም ሰለሞን ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 292
47
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 📖“ሰው የሚማር አንድም በፊደል፣ አንድም በመከራ ነው፣ አንድም በሳር “ሀ” ብሎ፣ አንድም በኣሳር “ዋ” ብሎ።” ✍ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ________________________ 🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
6 659
55
"ባለ መሆን ውስጥ ያዝሽኝ፡፡ ከጨለማው ነጥቀሽ ብርሀን አሳየሽኝ፡፡ብርሀኔ ... በዙሪያሽ እንደ ንፋስ መሆን ፈለኩ...ቢራቢሮ ነፍስሽን ልከባት ላያት፡፡ በደመና ይዘሽኝ ስትሄጅ አንችን ብቻ አመንኩ...ነፍሴ ተጠጋችሽ፡፡ ፀሀፊ✍ የእናቱ ልጅ አንባቢ🗣 ለይላ For any comment @l_e_l_u

file

6 707
28
ደሞ እንኩ ወኔ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

file

6 627
12
ቬሎና ቦሎ (አሌክስ አብረሃም) የዮርዳኖስ የሰርግ ቪዲዮ ከሌሎች የሰርግ ቪዲዮወች የሚለየው ሰርጉ ላይ የትራፊክ ፖሊስ አጭር ትእይንት ስለተካተተበት ነበር እንዴት ማለት ጥሩ ነው ለዮርዳኖስ ሰርግ ጊዜ አጃቢ ሁነን ለምሳ ወደሙሽሪት ቤት እየሄድን ነበር ድንገት ከሰማይ ዱብ ያለ የሚመስል የትራፊክ ፖሊስ የሙሽራውን መኪና ከነሙሽሮቹ አስቆመና ‹‹መንጃ ፈቃድ ›› አለ ኮስተር ብሎ ፍጥነቱና መኮሳተሩን ለተመለከተው በሙሽሮቹ መኪና ጥንዶቹ ሳይሆኑ ጥንድ ፈንጅወች ተጭነዋል የሚል ጥቆማ የደረሰው ነበር የሚመስለው ‹‹ምን አጠፋሁ ሙሽራ እኮ ነው የጫንኩት ›› አለ ሹፌሩ ‹‹ እሱን ማን ጠየቀህ የመኪናው ቦሎ አልታደሰም ›› ብሎ ሹፌሩ ጋር ክርክር ገጠመ :: ድፍን ሚዜ ወርዶ ትራፊክ ፖሊሱን መለመን ጀመረ ‹‹ኧረ በናትህ ሙድ የለውም ሰርግና ሞት አንድ ነው ሲባል አልሰማህም ምናለ ብታልፈን ለዛሬ ›› አለች አንዷ ግማሽ ጀርባዋ የተራቆተ መዘነጥ ያለመደባት የምትመስል ዘናጭ በያዘችው አበባ የትራፊክ ፖሊሱን አይን ልትመነቁለው ደርሳ ነበር ‹‹እኮ ...ይሄ መኪና ‹ቴክኒካል› ችግር ቢኖርበትስ በሰርጋችሁ ቀን ሃዘን ሆነ ማለት አይደል ...ሰርግና ሞት አንድ ነው ማለት ያነው አደጋ ሙድ የለውም ብሎ አያልፍም አለ ሙሽሪትን በአይኑ እየቃኘ ‹‹እሱማ ልክ ነህ ግን አሁን ሙሽሮቹን ጭነን ወደምርመራ እንሂድ እንዴ ›› አለ አንዱ ሞቅ ያለው ሹፌር በማሾፍ ‹‹ ሙሽራ ጭነህ እንጦሮጦስ ከመውረድ ይሻላል ›› አለና ኩም አደረገው የሙሽራው ንስሃ አባት ወርደው ትራፊክ ፖሊሱን ለመኑት ‹‹የኔ ልጅ ቃሉ እንደሚል እ.....ጋብቻ ቅዱስ ... ምኝታውም ንፁህ ነውና ማበረታታት ነው ያለብን ›› እያሉ ስብከት ጀመሩ ‹‹አባቴ እኔ መች መኝታቸውን ህገወጥ ነው አልኩ መኪናቸውን እንጅ ›› አለ ትራፊኩ ቀዝቀዝ ብሎ ነበር በብዙ ልመና ትራፊክ ፖሊሱ የሙሽሮቹን መኪና ከለቀቀ በኋላ አንዷ ከጎኔ የተቀመጠች በጣም ቆንጆ እና ነብሷን እስክትስት የዘነጠች ወጣት (ለሰርግ አጃቢነት የተፈጠረች የምትመስል ) እንዲህ አለች ‹‹....ትራፊክ ፖሊሱ ሙሽሪት ሰፈር ነበር በፊት ጠይቋት እንቢ ብለዋለች ወ.......ይ ወንዶች ! ›› አሙቁልኙ እንዲህ አለ በዜማ ‹‹የኛ ሙሽራ ባለቬሎ አስቆማት ባለቦሎ አስቆማት ባለ ቦሎ .... እልልልልልልልልል ቦሎው ያልታደሰ መኪና ተከትለን ወደሰርጉ ቤት .... ይሄ ሁሉ ሲሆን ካሜራ ማኑ እየቀረፀ ነበር ፡፡ የሰርግ ቪዲዮውን ስናየው ታዲያ የትራፊክ ፖሊሱና የሰርገኛው ንትርክ አጠቃላይ ሰርጉን ‹ቬሎና ቦሎ› የሚል ‹ከሆሊውድ የመጡ ባለሙያወች › የተሳተፉበት የፍቅር ኮሜዲ ፊልም አስመስሎት ነበር ፡፡ (የሰርግ ኮሜዲ የሚባል የለም ብየ ነው ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 160
55
ትንታ ደም እያባበለ ጣር ከሚያሽሞነሙን የዘመን ቁስል ላይ ስንት እንባ ዘነበ ሳግ ከሚደውረው የልባችን ሰማይ?? በረከሱ ነፍሶች ጎባጣ ወገብ ላይ ድንጋይ ተቀርቅቦ መዳህ ሳይጀመር መንከባለል ሆነ ሸክም ሸክምን ስቦ። መከረኛ ዛሬ ለቅጽበት ሽራፊ እንቅልፍ ቢዞረው ሰመመኑ ባሰ ከህልም ተኳርፎ ቅዠት ተዋረሰው። በጽልመት ብርሀን በሰካራም ስሌት በዛር በቅሎ ሽምጥ በነፍሰጡር ቅስቻ በውቃቢ ጥሪ በእልፍ መሀን ምጥ ነፍስሽ ስታቃስት ማርያም ማርያም ይላል እድምተኛሽ ከቦ ከእግሮችሽ ሰፈረን ዳናሽ በዳናችን በሲቃ ተከትቦ። መሻር ያላደለው እዥ የተዋደደው መግል ያዘለ ቁስል ምርኩዝ ያልሽው እንጨት ህማም ተጠፍሮ አንቺን ነው እሚያማስል። ከትብታብ ጎዳና ከአስማተኞች መንደር ጻድቅ ቢገኝልሽ መተት ለመደ አሉ ከደጁ ፈውሶ ከእልፍኙ ሊገድልሽ። እህህ እህህ እንደው እህህ ነው። እህህ ልበለው ቃል ቅኔ የለውም ግራ ነው ነገሩ የአድባሬን እሮሮ የጦቢያዬን ስቃይ ለአዝማሪው ንገሩ ይዘምር ይዝፈነው የመገፋት ልኳን በቅኝት ይዘርዝር ልብ እየተደቃ ሙሾ ይውረድላት ባለ ቀን ይጨፍር። ወትሮም ከኔ ቢጤ ደጃፍ ከአዳፋ መቀነት ከለማኝ ቤት ጓዳ የቁንጣን ጭቅቅት የግፈኛ ሳቅ ነው በገፍ የሚቀዳ። ሁሉን አሜን ብላ ለተጎናበሰች ብሶተኛ ሀገር ስብራቷ ሊድን ተራው ሲደርሳት ነው ወጌሻው እሚሰበር። መባው ሳይጓደል አዝመራው ሳይነጥፍ መሸመን ቧገታ ጥምሽን ላይሽረው የሰጡሽ ጭላጭ ነው ያስያዘሽ ትንታ!! መርምሪውአለሜ በጭላጭ ከመሞት ጥም ገደላት ያምራል ሸምጋይ ከተገኘ ቀን ከቀን ሲታረቅ ድርቅ ያረሰርሳል። በዘመን ፍርርም በቃል ኪዳን ስሌት ነፍስ ተረክዞ የኢትዮጵያን ምድር መቼ ነው የሚረግጠው ሙሴችን ተጉዞ?? ርግጥነው አልክድም፦ የሙሴ ባለችው ታምረኛ በትር በቀጣት ነው ልምዷ የአካሏን ህቅታ በተስፋ ማሰር ነው የዚች ሀገር ገዷ። ከሳብዕ የራቀ ማሳረጊያ ያጣ የፈተና ግዕዝ ምስካይ ነበርሽ ያኔ የፊትሽ ላይ ቆዳ ማዳትን ሳይበርዝ። አለም ነበርሽ ያኔ የአዲስ ኪዳን እልፍኝ የአብርሃም ጓዳ እኔ ላውዛሽ ያለ ከለጋስ ልቦናሽ ወዝሽን ሳይቀዳ። ፊደል ነበርሽ ያኔ የሰማዩ ጥዑም ልሳን ባለ ቆብ የኔታ A ና B ሳይጻፍ ሀሁለሉ ወርዶ ከፊደል ገበታ!! ዛሬስ????????? ዛሬስእንደምን ሆንሽ ያንን መንሰራፋት ምን ገመድ አሰረ? ምንኛቢሰብኩሽ ያሰረውን ኪዳን ልብሽ ወረወረ በማን ልክ ተሰፍሮ ከደርባባ ቀሚስ እርቃን ተመረጠ? በስንኩልገበያ አሞሌና ጠጠር ግብር ተላወጠ!! ዛሬማ፦ የወረትየወረት የክንንብ ሆኗል ዱአና ፀሎቱ ለበረከት ሳይሆን ሆድ ለመሙላት ሆነ እሚበላ መክለፍቱ። ዛሬማ፦ ጥቁር ሆኖብሻል የፀዳል ቀሚሱ የመሞሸሪያሽ ጨርቅ ከምዕራቡ አለም እንዳሻው እሚደወር እንዳሻው እሚለቀቅ። ዛሬማ፦ ልክሽ እንዲህ ለካ የቀን ወለፈንዲ የአልማዝ ገለባ ጨቅላሽን አውርደሽ ሞች አዝለሽበታል በነተበ አንቀልባ። አሸወይናን ቀዳ የሽማግሌ አዘን የህጻናት ለቅሶ ከእልፋ አንበሳ መሀል ተኩላ ከበረ የበግ ለምድ ለብሶ። ዛሬማ፦ ትላንትና ነገ በዛሬ ሰንሰለት እየተጠፈ ትዉልድ የሚያብላላው የመከራ በቀት ቅኔ እየዘረፈ አለን እስከዛሬ ነፍስያችን ናውዛ በባሩዱ ሽታ በዛለ ጉሮሮ አካል እየሳለ በዘመን ትንታ!!!!! 29/02/2014 ✍ሳሮናዊትእንድሪስ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 804
42
ፋራ እኮ ነኝ መሳቅ መጫወትን የማዉቅ በአላማዬ ቀልድ የማላቅ ለናቀና ላንጓጠጠኝ በቃላቶች ላሽሟጠጠኝ ቀና እንዳልል ለሚራገም የዉድቀት ቀኔን ለሚያልም ሳቅ ነዉ መልሴ ዝምታ ነዉ እስትንፋሴ ፓሪ ኦቨር የማያምረኝ ጌመር መሆን ማይታየኝ በሠዎች ፊት የሠገጥኩ እራሴን ግን ያከበርኩ ለሩቅ ህልሜ የታመንኩ። ለእድሜ እኩያ የማልመች አካባጅ ነች የተባለች እኔ ማለት ያቺ ሴት ነኝ ባንተ ቃላት የማይበርደኝ የማይሞቀኝ። በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 576
102
ከአንዱ ዛፍ አንዱ ዛፍ በእረፍት አልባ ኑሮ አንቺን ተከትሎ ... ከሰማይ ላይ መቅዘፍ ሲሰለቸኝ ጊዜ ክንፎቼን ገንጥዬ ከምድር ወደቅኩኝ በቃኝ .... ሠከንኩኝ ፥ ታድያ በአመት አንዴ እንደ መስቀሏ ወፍ ብቅ ስትይ ውዴ አብሬሽ መብረሩ ... ካማረኝ በእውነቱ ክንፋ አልባ አርጎ ያኔ ያስቀረኝ ውሳኔ .... ዘፍቆኝ በፀፀቱ ከተጫወተብኝ ወፍ መሆኔ ቀርቶ ... ዛሬ ይኸው ሠው ሆንኩኝ። Ⓒ በቀቀኑ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 512
18
✨✨✨ አንድ ሰውዬ ከጥርሶቹ መሀል አንዲት የበሰበሰች ጥርስ ነበረችው ፡፡ ይህቺ ጥርሱ ሌት ከእንቅልፉ እያነቃች በጣም ታሰቃየው ነበር ፡፡ ወደ አንድ ሀኪም ሄደና እንዲነቅልለት ጠየቀው ፡፡ ሀኪሙም የተሻለ መፍትሄ እያለ ለምን ትነቅለዋለህ ብሎ ጥርሱን እየበሳ ካከመው በሃላ በወርቅ ፍቅፉቂ ሞልቶ አሁን ይሻልሀል ብሎ ሸኘው ፡፡ ነገር ግን የበሰበሰው ጥርስ ሳምንት ሳይሞላው ክፉኛ ያሰቃየው ጀመር ፡፡ በዚህ ትእግስት ያጣው ሰውዬው ወደ ሌላ ሀኪም ሄዶ ምንም ሳትለኝ ይህን ጥርስ ነቅለህ ጣልልኝ አለው ፡፡ ሀኪሙም የበሰበሰውን ጥርስ ነቀለለት ሰውዬውም ጤናው ተመለሰ ፡፡ በማህበረሰብም አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ ጥርሶች አሉ ፡፡ የበሰበሱ አመለካከቶች ንግርቶችና ሰዎች በጤናማው መሀል ገብተው ያምሱታል፡፡ ህመም ስቃዩ ይሆናሉ ፡፡ ሀኪም ነን ባዮች ደግሞ የበሰበሰን ነቅሎ እንደመጣል ፤ ህመምን ለማስታገስ የወርቅ ፍቅፋቂ እየሞሉ ያስታምማሉ ፡፡እነሱ ግባቸው ጤና ሳይሆን የተሻለ ህመም መፍጠር ነው ፡፡ በህይወታችንም ውስጥ እንደዚህ የበሰበሱ ጥርሶች አሉ፡፡ በሽተኛ ጥርስ በሽተኛ ጨጓራ እንደሚፈጥረው ሁሉ አንዳንድ ሰዎች በሂወታችን ላለ የስቃይ ህይወት መነሻ ይሆናሉ ፡፡ ታዲያ ይህ ጥርስ እስካልተነቀለ ድረስ ጤነኝነት የለም ፡፡ ከህይወታችን መውጣት ያለባቸውን ነገሮች በወርቅ ፍቅፋቂ ከመሙላት ይልቅ ብናስወግዳቸው ትክክለኛ መፍትሄ ይሆናል ፡፡ ካህሊል ጂብራን ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 793
33
የአልበርት አንስታይን እና የቻርል ቻፕሊን አስደናቂ ንግግር !! አልበርት አንስታይን ከሀገሩ ወደ አሜሪካ ሲሄድ አሜሪካ ስትደርስ ማግኘት የምትፈልገው ማንን ነው ተብሎ ሲጠየቅ ማግኘት የሚፈልገው ሰው ቻርሊ ቻፕሊን ነው ብሎ መናገሩ ይነገራል። እ.ኤ.አ በ1931 አልበርት "የCity Light" መሪ ተዋናዩን ቻርሊ ለማናገር እድሉን አገኘ። እንደተገናኙም እንዲህ ተባብለው ነበር። አንስታይን:- "ስላንተ ጥበብ በጣም ከሚያስደንቀኝ ነገር አለማቀፋዊነትህ ነው። አንድም ቃል ሳታወጣ መላው ዓለም ይረዳሃል" ቻፕሊን:- "ትክክል ነህ! ነገር ግን ክብሩ ያንተ ይበልጣል እኮ። የምትናገረውን አንዱንም ሳይገባቸው መላው ዓለም ያደንቅሃል" ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 290
52
መኖር መኖር ላንተ ነበር መሞትም እንደዛው ሂወቴ ላንተ ስል እየጠፋ ደብዛው ኧረ እንዴት ይታይህ እንደምን አብቦ የዃላ ትናንቴ እየጣለኝ ከቦ ላንተ እኔ ማለት የትናንቷ ሰው ነኝ እንደምን አድርጌ እንደምንስ ብዬ ብነግርህ አይገባህ ባስረዳህ አይሆንም እንደሰው አይደለሁ መግለፅምአልችልም ፋቅሬ አከላቴ አይታመን ምንም ሁሉን ላንተ ሰቶ ለኔ አላስቀረም እኔስ ግራገባኝ ላንተ ስል ምን መሆን እንዳለብኝ ፍቅሬ ሆይ ተረዳኝ ሂወትን አልችላት አንተ ካላገዝከኝ አልችለውምና መውደዴን ተረዳኝ ✍ሰሊ(አሚ)
7 012
61
አስራ ኹለት ግጥም ፀሀፊ ✍️ሰለሞን ሽፈራው✍️ አንባቢ🌗 የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

12_ግጥም_በሰለሞን_ሽፈራው_አንባቢ_🌗የግማሽ_ዓለም_ጣኦት🌗.mp3

6 860
11
አልቸገርም ሰለሞንም ቤቱ ውስጥ ብዙ ጊዜ ስለማትኖርበት ጥበቃ እንደሌለ ስለነገረኝ በነበረኝ ልምድና ማስተር ኪ ተጠቅሜ በሩን ከፈትኩት....ግቢው አረንጓዴና ሰፊ ነው ጊቢው በእኛ ሰፈር የአሰርና ከዛ በላይ የአባወራ ቤቶች ነው የሚሆነው....ድምፅ ሳላሰማ ጊቢ ውስጥ የቆመችውን ፎርድ መኪና አልፌ የቤቱ መግብያ የሆነው ግዙፉ የእንጨት በር ጋር ተፋጠጥኩ....የያዝኩት ማስተር ኪ አል ከፍተው ስላለ ከዋሌቴ ውስጥ ሴንጤዬንና ሽቦ አውጥቼ በሩን በስንት ትግል ከፈትኩት.....ሰለሞን እንደነገረኝ በአራትና አምስት ወራት ውስጥ አንዴ የሚኖርበት ቤት ሳይሆን በየቀኑ ሰው የሚኖርበት ነው የሚመስለው ከቤቱ ፅዳት እና በየቦታው ያሉ ባስኬት ውስጥ እዛም እዚም ብዛት ያላቸው ተጠቅልለው የተጠቀለሉ ወረቀቶች ይታያሉ....ወድያው ከኩሽና አንድ ድምፅ አስተጋባ...ድምፁ ወደተሰማበት ቦታ ጆሮዬን ቀስሬ ኮቴዬን አጥፍቼ ወደ ቦታው ስጠጋ ጥሩ መአዛ ያለው የምግብ ሽታ ሸተተኝ...እንደምንም ብዬ ወደ ኪችኑ ስቀርብ ሉሊት ከዪቱብ ላይ በስልኳ ግጥም እየሰማች ነው.... ቃላት ያንሳል ላንቺ የለም የሚገልፅሽ ገምነግርሽ በላይ ለኔ ልዩ ነሽ። አንቺ ነሽ አለሜ የመኖሬ ምክንያት ሁሉንም ምረሳብሽ የህይወቴ እረፍት። ስምሽ እንደ እህት ስራሽ ከዛ የላቀ ላንቺ ያለኝ ስሜት ድንቅ ነው የረቀቀ። እወድሻለሁ በጣም ነሽ ለኔ ስስቴ በማንም የማልተካሽ የማለውጥሽ ለብቴ። እወቂልኝ እድሜ ልኬን ሙሉ ምንም ብል ስላንቺ ባይበቃ ፊደሉ። የኔ ውዷ እህቴ የጎደለሽ ሞልቶ ኑሪልኝ በደህና ያብሽው ተሳክቶ...... "ዋው መርዬ ዋው አንተ ባትኖር ኖሮ ማን በግጥም ልባችንን ያሞቀው ነበረ" አለች የምተሰራውን እንቁላል እያማሰለች... "እንዴት ነሽ ሉሊት ውዴ" ስላት በድንጋጤ እያማሰለች የነበረውን እንቁላል መሬት ላይ ዘረገፈችው...የድስቱ ድምፅ ክፍሉን በአንድ እግሩ አቆመው.... "ሊሊት ውዴ እንደዚህ አትደንግጪ እንጂ" አልኳት ሴንጢዬን አስሬ ወደሰገባው እየመለስኩና እያወጣው...ጩቤውን ስታይ በድንጋጤ ደርቃ ቀረች..... #የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን https://t.me/lovestorey1 ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 664
30
😘ለፍቅር ስል😘 🔥ክፍል፦አስር ✍️ደራሲ፦ጎስ """" """" """" """" .."ሉሊት ዱባይ አይደለም ያለችው እዚሁ ነው ከዱባይ ማን እና እንዴት እንደደወሉልክ ባላቅም አሁን ያለችበትን ቦታ እልክልሀለው"ብሎ ስልኩን ዘጋው....በንዴት ጦፌ በንዴት ግዬ ለበቀል የሉሊትን መገኛ ወደሆነው ቦታ እየገሰገስኩ ነው...የ ሰው ልጅ ከተፈጠረ ጀምሮ በሁለት የስሜት መአበል ውስጥ እየተናጠ ማለፍ ግድ ይለዋል....ፍቅር አልያም በቀል...ሁሉም ሰው ለምዕተ አመት አብሮ ከኖረበት እና አንድ ከሚያደርገው ጉርብትና ይልቅ በሽርፍራፊ ሰከንድ የተፈጠረውን ጥል ሚዛን ይደፋል.....አብሮነቱን አፈር ከድሜ አብልቶ ልቡን ለበቀል ያነሳሳዋል...መሳርያውን ከየቀበረበት አውጥቶ ይወለውላል ስለቱን እስኪነጣ ድረስ ይስላል...እኔም በዚህ ውህደት ውስጥ እያለፍኩ ነው...ሉሊት ማራናታ በነበረችበት ሰአት በሷ ፍቅር ብን ባልኩበት ሰአት እራሴን አሳልፌ የሰጠዋት ከአንቺ በፌት የኔን ሞት ያድርገው ብዬ ያልኳት ማራናታን የጉዞዬን መንገድ ሀ ብዬ ከጀመርኩ ቆየሁ.......አንድ ሰሞን እሷን አይቼ ካላደርኩ ያለሷ ሰው ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ በልቤ ያነገስኳትን እንስት አሁን በበቀል ታውሬ አውሬነቴን ላሳያት ነው.....ብዙ ፈተና ያየውባት ሴት አሁን ልቤን ጥቁር ጥላሸት ቀብታዋለች እንደ አይኔ ብሌን ምሳሳላትን ትርታዬን ጎድታብኛለች.....የመኖሬ ሚስጥ የሆነችው ትርታዬ ስትነቃ ከጎኗ ባታገኘኝም የእሷን ደም ለመበቀል ቆርጬ ተነስቻለሁ.......የበቀሌን ጥም ለመወጣት በማደርገው ጉዞ መሀል የሰው ልጅን እጅግ በከፍተኛ ደረጃ የመጉዳትና የመግደል አቅም ያለው ግን ብዙ ሰው ጎጂ መሳርያ የማይመስል ምላጭን አንድ ፖኬት ገዝቼ....ከጥንተ ጀምሮ ከዋሌቴ የማይለየኝ በ1996 አጎቴ የሰጠኝን ተወንጫፊዋን ጩቤዬን ከዋሌ ውስጥ ከሰደርኩባት ቦታ መኖራን አራግጬ ጨርሻለሁ አሁን የቀረኝ ወደ ሉሊት ቤት የሚወስደኝ ላዳ እስኪመጣ መጠበቅ ነው። የማለዳዋ ፀሀይ በምስራቅ በኩል ከተራራው አናት ላይ ብቅ ማለት ጀምራለች...የነዋሪውና የመኪናው ግርግር ለከተማዋ አንዳች ድምቀት ሰቷቷል.....እናቶች ከጫካ የሰበሩትን እንጨት ተሸክመው ዳገት ቁልቁለቱን ያዘግማሉ....ወጠምሻዎችና እንስቶች ጥንድ ጥንድ ሆነው ስፖርት ይሰራሉ....ወደየ ስራ ገበታቸው ለመሄድ የማይገፋውን የታክሲ ሰልፍ የተሰለፉ የእትየ ለሌ ናቸው... "አይ ሸገር ፍትሀዉ ያልሆነች ከተማ ነች" አለኝ ባለ ላዳው ሹፌር በውስጥ መመልከቻ ስፖክዬ እያየኝ.... "ማለት? ምኗ ነው ፍትሀዊ ያልሆነው?" አልኩት በበቀል ስሜት እሳት የሚተፉትን አይኖቼን በሚመለከተው ስፖክዬ እየወረወርኩ.... "እየውልህ የኔ ወንድም እነዚህን እናቶች ተመልከት የእለት ጉርሳቸውን ለመፈለግ ጎህ ሳይቀድ ከቤታቸው ዘተው በዛ ድቅድቅ ጭለማ ከጅቦች ጋር ታግለው እንጨየት እየሰበሩ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን እየተጓዙ ይሸጣሉ በተቃራኒው ደሞ እዚህ የምታያቸው ስፖርተኞች የፈለጉትን እየበሉና እየጠጡ ቦርጫቸው ይቆዘራል...በምግም ብዛት የተወጠረውን ቦርጫቸውን ለማጥፋት በሺዎች እያወጡ በቡድን እና በተናጠል አሰልጣኝ ይቀጥራሉ....እዚህ ጋር የሚገርመው ነገር እነዚህ በሀብት ማማ ላይ እንልባቸው የሚሆኑት እንጨት ሰብረው የለት ጉርሳቸውን በሚያገኙት እናቶችና በነሱ መሰለ የደሀው ጉልበትና ደም ነው" አለ በስጨት ብሎ ሆዳቸው ተቆዝሮ የዘጠኝ ወር እርጉዝ የመሰሉት ስፖርተኞች ላይ አይኑን ተክሎ... "ይሄ የዚ ከተማ ችግር ብቻ አደለም በመላው አለም ያለ ነው...ምድር ስትፈጠር ጀምሮ ፍትሀዊ አይደለችም ስለዚህ ሸገር ሀበሻ ማለቱ አያስፈልግም "አልኩት እሱ ግን እኔ የተናገርኩትን ከቁብ ሳይቆጥረው "ያልገባህ ነገር እኮ ቅድም የመጣንበትን ሰፈር እይ አሁን ያለንበትንም እይ" እያለ የሸገር ውበት የሆነውን መሀል ቦሌን ዙሪያ ገባውን እየቃኘ... "አዎ ልክ ነህ...በቃ እዚህ ጋር አውርደኝ"አልኩት ከመውረጃዬ ገና 3km ቢቀረኝም ሉሊትን እንዴት እንደምበቀላት የማሰብያ ጊዜ ስላልሰጠኝና ከሱ ጋር ላለመከራከር ብዬ ቦታው ላይ ሳልደር የተነጋገርነውን 300ብር ከፍዬ ከመኪናው ወረድኩኝ...ልክ ከመውረዴ የእጅ ስልኩን አንስቶ ይጎረጉር ጀመረ.... ዘመናዊ የቤት መኪናዎች ላዳዎችና ራይድ አልፎ አልፎ የሚታይበት ሰፈር ፀጥ ረጭ ብሏል...እንደኔ አይነቱ አብሮ መኖርና ጫጫታና ሁካታ ለለመደ ሰው ያስፈራል...በዛ አካባቢ ብቸኛው የተፈጥሮ ተሽከርካሪ ተጠቃሚው እኔ ነኝ....ብቸኛ እግረኛ ስሆንኩ ሁሉም በጥርጣሬ አይንና በንቀት እየገላመጠኝ መኪናውን ያስወነጭፋል...በፊት በደቂቃ ውስጥ የምጨርሳት 3km አሁን የቀናት ያህል ረዘመብኝ......በምስራቅ የወጣችዋ ፀሀይ ግለቷ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የኔም የበቀል ጥም በልቤ እየተቀጣጠለ ሄደ.... "ኤስኮ እዚህ ጋር ነኝ" አለኝ አድራሻዋን የላከልኝ የላከልኝ ዩንቨርስቲ ውስጥ የተዋወኩት ጓደኛዬ እጁን እያውለበለበ.....እኔም ቀልጠፍ ብዬ ወደሱ ሄጄ ለሰላምታ የተዘረጋውን እጁን ጨብጬ..."የት ነው ያለችው " አልኩት ለስለስ ብዬ ለበቀል እንደመጣው እንዳያውቅብኝ.... "ያው ፊት ለፊት ያለው ነጭ የተቀባው ፎቅ ነው" አለኝ አመላካች ጣጡትን ወደ ፎቁ እየጠቆመ... "ሶልሽ ለሌላ ጊዜ አመላካች ጣትህን እንደዚህ ወደ ሌላ ቦታ ወይም ሰው ላይ አትጠቁም....አንተ አንዱን ስትጠቁም ሌሎቹ ሶስቱ ወደራስክ ነው የሚጠቁሙት"አልኩት....ደንጥ ብሎ "እ...እ...እሺ" አለኝ ቃሉን እየጎተተ... "ሶልሽ በጣም አመሰግናለሁ አንተ ባትኖር ኖሮ ማን የሉሊትን መገኛ ይጠቁመኝ ነበረ" አልኩት ሶል የዛው ሰፈር ልጅ ስለሆነ እንደ ቤተመንግሥት የሚጠበቀውን አፖርታማ ውስ ስላስገባኝ እና የሉሊትን መገኛ ስለነገረኝ ከልቤ እጅ ነስቼ አመሰገንኩት... "ምጋናው ሁለታቹ ተነጋግራቹ ሰላም ስታወርዱ ይደርሳል ሰላም አውርዳቹ ፍቅር በፍቅር ስትሆኑ ጋባዥ እኔ ነኝ" አለኝ እየሳቀ....አይ ሰሌ የወሀ እኮ ነህ እኔ የመጣውት ለዕርቅ ሳይሆን ደም ለመቃባት መሆኑን ሲያውቅ ምን ይሰማው ይሆን በእሱ መሪነት ሉሊት ታሪክ ስትሆን ፀፀቱን ይችለው ይሆን....ይቅርታ ሶል ሉሊትን ስገድላት ፀፀቱን አትችለውም ግን ደሞ እራስ ወዳድ አትበለኝ ይሄ ለሁሉም ሰላም ስል የተደረገ መስዋትነት ነው....እሷ ወይ እኔ ካልሞትን የኔ ትርታዬም ሆነ ጓደኞቼ በሂወት መኖራቸው አጠያያቂ ይሆናል.....ሶል እባክህ ይቅር በለኝ ለብዙዋን ሰላም ሲባል እኔና አንተ እንደሻማ መቅለጥ ግድ ይለናል.....አልኩት በሆዴ..."ምን አልከኝ?"ሲለኝ ቃላቶቹን አውጥቼ ተናገርኩ እንዴ ብዬ ደንገጬ.."አንተ አዚህ በሁዋላ አታስፈልገኝም የሰው በር ሰብሬ ልገባ ስለምችል አንተ በተከበርክበት ሰፈር መዋረድ የለብክም" አልኩት እየተርበተበትኩ....."ኤስኮባር ግን እርግጠኛ ነህ ነገሮቹን በሰላም ለመፍታት ነው የመጣከው" አለኝ በጥርጣሬ አይኝ እያየኝ "አዎ" አልኩ ፈርጠም ብዬ ከዛ በሉዋላ ብዙ ክርክር አድርገን እሱ ሊመለስ ተስማማን ግን አሁን ድረስ ፊቱ ላይ የጥርጣሬ መንፈስ ይታያል...."ሰሌን ተሰናብቼ ወደ ውቡ ፎቅ አመራው....የቤቱ ዙሪያ ገባውን ብቃኘውም በግንብ ለመዝለል አዳጋች ነው...ሶስት ሜትር ከሚረዝመው ግንብ ላይከተገጠመለት የአደገኛ አጥር በተጨማሪ ግንቡ ላይ የኮሽም ዛፎች በስነስርአት ተከርክመው ቅርፅ ይዘው ይታያሉ...የቤቱ ብቸኛ መግብያ ባለወርቃማ ቀለሙ በር ነው....ወርቃማ ቀለም የተቀባውን በር ለመክፈት በፊት አሽሽ በምሸጥበት ጊዜ የሰለጠንኩት ስልጠና ስላለ
Show more ...
6 808
39
ከዕለታት በአንደኛው ቀን ሰራተኞች ቢሮ ሲገቡ ከመግቢያ በሩ ላይ የተጻፈ ማሳሰቢያ ቢጤ ይመለከታሉ። "በካምፓኒው ውስጥ እድገታችሁን ሲያደናቅፍ የነበረው ግለሰብ በትናንትናው ዕለት ስላረፈ በስርዓተ-ቀብሩ ላይ እንድትቀላቀሉን እንጋብዛችኋለን" ይላል። የመስሪያ ቤት የስራ ባልደረባቸው ስላረፈ ብዙሃኑ ሰራተኞች አዘኑ። ዳሩ ግን ቢከፉም ሁሉም ተደነቁ። "ምንም እንኳን ቢሞትም እድገቴን ሲያደናቅፍ የነበረው ሰውዬ ግን ማን ነበር?" ሲሉ አሰቡ። ለማየትም ጓግተው አንድ በአንድ ከሬሳ ሳጥኑ እየቀረቡ ቢመለከቱ ድንገት የሚናገሩት ቃል ጠፋቸው። አልጠበቁም። ሌላ ሰው ጥልቅ ስሜታቸውን የነካ ይመስል ከሬሳ ሳጥኑ አጠገብ ቆመው ፈዘው ዝም አሉ። የሬሳ ሳጥኑ ከውስጡ መስታውት ቢሆን እንጂ አንዳችም አልነበረውም። ሁሉም ወደ ውስጥ ቢመለከቱ፣ ያዩት የራሳቸውን ምስል ብቻ ነው። ከመስታውቱ አጠገብ አንድ ጥቆማ ሰፍሯል። "ስኬትህን የመገደብ ብቃት ያለው አንድ ግለሰብ አለ። እሱም እራስህ ነህ።" ይላል። ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 151
72
​​ካልዳሰስኩ አላምንም ! ሊነጋ ነው ሲሉኝ ለኮስኩት ፋኖሴን ፤ ሊወብቅ ነው ሲሉኝ ደረብኩት በርኖሴን ፤ ሰላም ወርዷል ሲሉኝ ጋሻዬን አራገፍኩ ፤ ሰው አልሰማ ብል ነው ክፉ ቀኔን ያለፍኩ ! ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ ፤ ያገር ልማድ ሆኗል.. እንጀራ እንደመብላት በበሬ እንደማረስ! ፍቅር ስጋ ለብሶ በ'ጁ ካላቀፈኝ ፤ ተስፋም ብብቴ ስር ገብቶ ካልደገፈኝ ፤ ኢምንት ነው ምንም ፤ ካልዳሰስኩ አላምንም !! ✍በእውቀቱ ስዩም ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
6 291
30
🍵ቅዠቴ… እኔማ በቤቴ አልሜኮ ነበር እርቄ ስወጣ ከትውልዴ መንደር… ነገን ለማሸነፍ ቆሜ ሳለው ዛሬ ወለም ዘለም ሳልል ተምሬ ተምሬ የጥበብን ጥልቀት በክንዴ መትሬ በእውቀት ባህር ውስጥ እራሴን ነክሬ በግርማ በሞገስ ከፍ ብዬ ለመኖር እኔማ እንደስው አልሜኮ ነበር ከዚህ ውጪ ሌላም እጅግ ብዙ ብዙ ፣ ብዙ ብዙ ነገር። በሥልጣን በልጬው ያገሩን ሰው ሁላ ጥረቴም አብቦ ቡሪያውን ሲያጠላ ማንም ላይደርስብኝ መጥቄ በላዩ ሃውልት አስተክዬ በያደባባዩ ዝንትአለም ስመለክ ከተራው በልዩ ለመኖር ነበረ የሩቁ ውጥኔ ስመኘው የኖርኩት በሕይወት ዘመኔ። ቪላ ቤት ሰርቼ ደልቶኝ ስንፈላሰስ ለሽርሽር ብቻ ገዝቼ ማርቸዲስ የቆንጆዋን ቆንጆ አድባሯን አግብቼ በዲግሪ ላይ ደግሞ ማስተርሴን ሰርቼ ለመኖር ነበረ ሳለው በዝች ምድር የልጅነት ሕልሜ ቅዠት ሆኖ ባይቀር። ✍መሰለ ከልካይ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 890
28
የዘመኑ ትምርት !🚶‍♂ በተቆረጠ ግንድ ቅጠል በጎደለው እንጨት ላይ ተቀምጦ እስትንፋስ በሌለው መምሩ በውሸት ሲያሳምን በተስፋ ህዝቡ አሜን ይላል ሆዱን እያሰፋ ✍ዳዊት ጥዑማይ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 807
32
የዘንድሮ ትዳር ወንዶች ብር ሲያጡ ሴቶች ልብ እያጡ ፍቅር ሳይገባቸው እየተጃጃሉ ትዳር ትዳር ብለው ዘለው ይጋባሉ ትናንት የተጋቡት ዛሬ እየተጣሉ ወንዱ ብር ሲያገኝ አይምሮ እየሸጠ ሴትን እንደ ሸቀጥ እየለዋወጠ ሴቶች በተራቸው ልብ አገኙ ሲባል ገንዘብ ያምራቸዋል ሀብታም የሆነ ባል አንዱ አንዱን ሲፋልግ አንዱን እየሸሸ የዘንድሮ ትዳር ነግቶም አላመሽ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
6 017
70
እመጣለሁ ብለህ 😢 ትመጣለህ ብዬ ድንኳን ባደኩንም ንፍሮ ባስቀቅልም ምስር ባስለቅምም ጥቁር አገልድሜ አስለቃሽ ብቀጥርም አንተ ግን ቀርተሀል ዛሬም እንደ ድሮ ከልቤ ለመሞት ከያዝከዉ ቀጠሮ። ገዳይ ሰዉ አላዉቅም............ ሟቹም ወንጀለኛዉ ከሳሹም ፈራጁም አንተዉ ራስህ ሆነህ ከችሎት ቆመሀል መከራከር አላዉቅ አሁን ምን ይባላል። ና ላንጎራጉርልህ............. ለአርባና ሰልስትህ አልተዉሽም ብሎ ጥሎኝ ሄደ ብዬ ሰዉ ላስለቅስልህ ጋሻ ነበር ብዬ ጦር ላሰብቅልህ። ና እስቲ አንዴ ሙትልኝ.......... ከአፈር ተደባለቅ ስጋህን ብል ይብላዉ አይኔ እያየህ እለቅ። የኮራህበት ገላህ ይፈራርስ አለሜ እኔም ገለሞተች ልባል ገደምዳሜ። ና እስቲ ወጉ ይድረስህ........... ሟችነት ይሻላል በቁምህ ከመሞት በመቃብር ያምራል። ና እስቲ አንዴ ሙትልኝ............. እኔም እርሜን ላዉጣ ትቶኝ ሄዶ ሳይሆን ሞቶ ነዉ እያልኩኝ አስሬ ልቀጣ። በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 403
63
ላያበቃልሽ ክታብ ተፅፎ ከዶፍ እኔኑ ለማዳን ስትይ መታሽ ወጨፎ እበረሀ ላይ ላንቺ ሳትጠጪ ለኔ ጨልፈሽ ያመጣሻው ውሃ ከመንገዱ ላይ ተኖ ሚያልቅብሽ ኩንስንስ እንስት ምስጠትሽ ከላይ እመት መበለት ስራሽ በልብሽ እንደ ወይዛዝርት የሰው ምንተእፍረት ከለበሽው ላይ ቀደሽ አንስተሽ የምትሸፍኚ እርቃን ለመሆን ቀርቶሽ እራፊ የኔን ቡትቶ የምታጣፊ የኔን ገመና በስንደዶ ስፍ ስውር ምትሰፊ ሟችን ሰራቂ ክንፍሽን ገንጣይ ቆመሽ ልታይኝ በሀሤት ስበር ከበላይሽ ላይ አላርፍ እያልኩኝ ፥ ስሆን ከልዋሳ በጉርሻሽ ጠጋኝ አለበደልሽ የምትከፍይ ሰርክ ለኔ ካሳ ሳቅሽ ሚከፍን ከራሱ አልፎ የሰው ሀዘንን መበታተኔን ደርቄ አጥቼ ኋኝ ለኔ ውብ ወዝ ደርሰሽ ሰብሳቢ ምትሆኚኝ ጥራዝ ፥ ልቀሽም ከእናት ከሴትም ምስጠት ከሴትም ውበት የፈሰሰባት መንገድ አሳብራ ከሰውም ውራ የሆነም ጭራ እንደ ደራሽ ወንዝ ይዛ ጠራርጋ ብትኑን ጣቃ የባላባቱን ጥልፍ የምትቀይር ልቤን ዘምዝማ ምታደናግር ከጎደፈር ሸሽታ የማትርቅ ጥልን በአንድ ቃል በእንባ አራጭታ ፥ በእቅፍ ምታርቅ ከሴትም ውበት ከሴትም እንስት ወርሳው ነው የሄደች የማላውቀውን ያለኝን እርስት ጥዴ ባይበሰል የጠፋ እሳቴን በእፍታዋ ምታቀጣጥል በአፍ ፍላፃ እንዳልሰበር የምታድነኝ ሆናልኝ ጥሩር ጥግ ጥጉ ላይ ችንክር ሚስማር ላይ የተሰቀሉ ውብ ፎቶዋቿ በቀን እሩጫ ግድግዳ ሞልተው ነፍስ አረግራጊ እንባ አፍላቂ ... ንፁህ ሳቆቿ ውሽልሽል ልቤን በናፍቆት መርፌ ሲጠቀጥቁ ከትዝታ ውስጥ እኔን ሲያጠልቁ ስመጣት እኔ ከነመቅኔዋ ከነመረቁ ሚታየኝ አሁን ነፍስ አለላዋን ስተረትረው የሰፋችውን ስበታትነው ፥ ስምሰው ስርቡን የቤት ማገሩን ከምስጥም ብሼ ስገነድሰው ደንገት ደርሼ ጣዝሙት ንግስቴን ገድያታለሁ እመቤቲቴን መስሎኝ ዘላለም ከጎኔ ምትኖር በልቧ በዓት ሰርክ አለሀሳብ ተኝቼ ምቀር ...... አያልቅም ካንቺ መሆን በፊት ፥ ባዶ ሚሆን ቀለም Ⓒ በቀቀኑ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 636
21
1 ቀን ቢመለስ..... ቀኑ ይናፍቀኛል እማይመለስ ነገር አንዴ ሆኖብኛል 1ቀን መመለስ ቢቻል ኑሮ ያኔ ያን ቀን መልስልኝ እለው ነበር እኔ እኔና አንተ ሆነን የፎረፍንበትን ከአስተማሪያችን ጋር የተሯሯጥንበትን በ15 ዴቃዋ ሻይ የጠጣንበትን ከጓድኞቻችን የጠፈንበትን ደሞም እጄን ይዘህ አንገቴ ስር ገብተህ የወደፊት ሚስቴ አንቺ ነሽ እያልከኝ ከጓድኞቼ ፊት ሳሩን ያሰርክልኝ በቬሎ መጋባት አደለም ብርቃችን እኛ ተጋብተናል በዩኒፎርማችን በፊርማ የተጋባን እስኪመስለን ድረስ ተማሪ አስተማሪ እስኪረገን ርዕስ እንዋደድ ነበር እንዲያ ነበር ፍቅር ተማሪ ቢሆንም ምንም ባይኖረው ብር ከታክሲው ቀንሶ ይጋብዙኝ ነበር አትዘልቁም አትልፉ አትደርሱም ከአፋፉ ያሉኝን ሰምቼ ትቼህ የሄድኩበትን ዛሬም ረግመዋለው አንተን የተውኩበትን ✍️ ሐና ይመር ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 948
67
#አውቆ_አለማወቅ እርግጥ ነው አፌን ፈትቼ መናገር አልቻልኩም። በውስጤ ግን ቃል መሆን ያልቻሉ ካለመሆን የታበዩ እልፍ እላፍ ጩኸቶች አይምሮዬን ሰንገው ይዘውታል። እያንዳንዱን ጩኸት ላድምጣቸው ብል እራሴን አግንቼ ማጣው ይመስለኛል። እራሴን ካለማግኘት ደግሞ እራሴን አግንቼ ማጣቱ ይበልጥ ይጎዳኛል በማለት ዝምታዬ ያዘላቸውን እልፍ አዕላፍ ጩኸቶች ባለማድመጥ ውስጥ ሆኜ አደምጣቸዋለው። ግን እራሴን እሸውደው ይሆን? አላቅም። አለም ላይ እራስን እንደመሸወድ ያለ ከባድ ነገር ይኖራል ብዬ አላምንም። ግን ድርጊቱ ሚያመጣውን ተፅዕኖ በማሰብ ድርጊቱ እንዲሆን አለመፍቀድ እራስን ከመሸወድ ይልቅ ብልሀት ይመስለኛል። ምክንያቱም አንዳንዴ ማወቅ ብዙ ነገሮችን በአመክንዮ ለማየት የሚደረግ ጥረት ቢሆንም ያን ጥረት ማድረግ ደግሞ ደስታ የተባለ የሂወትን ፍሬ በገዛ ፍቃድ መሬት ላይ በትኖ ለመልቀም እንደመታተር ተደርጎ ይወሰዳል።ነገሮችን ላፍታም ያህል ቆሞ ብለን ካስተዋልናቸው ደግሞ አለም ላይ ደስታን ከሚፈጥሩ ቁልፍ ነገሮች መካከል አለማወቅ ግንባር ቀደሙ ነው። የማወቅ ጉዞ ባያበቃም ሽንፈትን መቀበል ድል እንደመደገስ ይቆጠራል። ከዚ ሁሉ ውጥረት ከባዱ ግን አውቆ አለማወቅ እንደሆነ ጥርጥር የለኝም !። ✍ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ ) @Tufaw_muhe ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 752
44
የማይነጋ ህልም ሳልም የማይድን በሽታ ሳክም የማያድግ ችግኝ ሳርም የሰው ሕይወት ስከረክም እኔ ለኔ ኖሬ አላውቅም ✍️ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድኅን ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 628
57
እጠብቃታለው አይን የማያየውን ሀሳብ ያያል ሄዶ እጅ የማይነካውን ልብ ያንቃል አሳዶ ተመለሽ አልልም ሞት ለያይቶን እንደው ያባት ያያት እርስት የመጨረሻው ቤት ለፀጥታው አለም እንግዳ አይደለንም መለየት እንደሆን ለይቶ ያስቀረን ሃሳብ ይላላካል ሃሳብ ይገናኛል አይን የማያየውን ሀሳብ ያያል ሄዶ ጆሮ የማይሰማውን በፀጥታው ቦታ ልብ ያንቃል አሳዶ ማን ያውቃል ለሞትም ይኖራል መቃብር ጉዞ አይቋረጥም አለም እያረጀ አለም ይፈጠራል አበባ በፍሬው ህይወትን ያድሳል የፅጌረዳ እሾህ ያበባው ጠባቂ ሳቂ የለም ሳቂ እሾህ እሆናለው የምወዳትን ልጅ እጠብቃታለው በቁም ያሰረኝን የሃሳብ ሰንሰለት ሰብሬ በጥሼ እኮበልላለሁ፡፡ እስከ ዓለም ዳርቻ እከተላታለሁ ሳላያት አልቀርም አለ ስጦታዋ አለ ትዝታዋ እሷን የሚያስታውስ ስበላ ስጠጣ ስተኛ ስነቃ ሳስብ ስተነፍስ እሷን መርሳት አልችል ፍቅር እምነት ህይወት አብረን ተደስተን አብረን ተቸግረን አበባ ለቅመናል ከወንዝ ዳር ሄደን እሸት ፈልፍለናል መስክ ላይ በልተናል ልብሳችን በስብሶ በዝናብ ሄደናል እሳት አንድደናል ፍሙን ተርኩሰናል በርዷት ተኮራምታ ህፃኗ ጨረቃ ፊቷ ደም ሲመስል ፀሀይ ተዘቅዝቃ ሁሉንም አይተናል በሁሉም ስቀናል ህይወት እንደዚህ ነው ዓለም ነው ብለናል እርሷን መርሳት አልችል እፈልጋታለው እከተላታለው እጠብቃታለው፡፡ ✍️ገብረክርስቶስ ጸስታ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
5 778
46
" #አርፋጅ_ጮራ " ጀንበር ወጣች ጎህ ቀደደ ህልም እያየው ጊዜው ሄደ ሳልጨርሰው ድንገት ነቃሁ አርፋጅ ጮራ ህልሜን ደቃው ተነስ አለኝ ከህልሜ ላይ የወገገ ጥቁር ሰማይ የጠቆረ "አርፋጅ ጮራ " ጅስሜን ይዞ ነብሴን ጠራ አቤት አልኩኝ እየሰጋው በሷ ነበር ሌቱ የነጋሁ ሄጄ ሄጄ ተመለሰኩኝ ከእቅፉ ላይ ተፀነስኩኝ ከመንፈሷ እኔን ሰራሁ ከነብሷ ላይ ነብሴን ገራው ቃሏ አነጋኝ ከፅልመቱ ተቀደሰ ፅልማሞቱ ተንጠራራሁ ህልሜን ነካው እግሯ ስር ነው ለካ ዱካው ✍ቱፋው ሙሄ (አዲብ) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
5 873
32
እራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር !

 በህይወታችን ውድቀት የሚጀምረው እራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደር በጀመርን ቅፅበት እንደሆነ መዘንጋት የለብንም ።

አብዛኛው ሰው እራሱን የበታች አድርጎ የማየቱ ትልቁ ምክኒያት እራሱን ከሌሎች ጋር በማወዳደር በሚያስበው በተሳሳተ አስተሳሰብ ነው ። 

ሁሌም ማወቅ ያለብን ነገር ብኖር እኛ ለራሳችን #ልዩ እንደሆንን ነው ።
ይሄንን ደግሞ አዘወትረን ለራሶቻችን የሚንነግር ከሆነ በራስ የመተማመንን ክህሎት ማዳበር እንጀምራለን ።

በተቃራኒው እራሱን ከሌሎች ጋር በማወዳደር የተጠቃ ሰው ዘወትር በእራሱ ደስተኛ ለመሆን ይቸገራል ከዛም ባሻገር #በበታችነት ስሜት የተጠቃ አሳዛኝ ሰው ይሆናል ። 

ስለዚህ ደስተኛና ስኬታማ ለመሆን ከፈለግን በራሳችን ማንነትና በእኛነታችን ደስተኞች መሆን መቻል ይኖርብናል ።
@eth_tibeb ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 765
46
ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታህል አንዲቷን  ለአፍሽ ጥለት  ከመሰለው  ስስ  መስመሮች  መሃል ብርሃን  ፈንጥቆ  ደምቄ  እንድስምሽ መንታ  ለአይኖችሽ ጸሊም  ፊቴ  ፈክቶ አብርቼ  እንድታይሽ አንዲቷን  'ላፍንጫሽ ለተንሰለከከው 'ብስብስ መዓዛዬን አርቅቆ ቢልከው ቆንጥሬ ብሰጥሽ ጥቂቱን   ለጭንሽ የ'ርግማን  ምጥሽን በዘመን  ያረጀ ወልድን  ሳትማልጂ  ጣርሽ ቢሻርልሽ አልቦ ተስፋው እኔ በቅዠት እጆቼ ዛቅ እፍስ  ከሰማይ ከከዋክብት መሃል መዳፎቼን  ዝርግት እንደው 'ላመል ታሀል። አድርጌ  ልቸርሽ ከልቤ  ባሻገር ሙላተ  ዓለሙን  ላንቺ  እንደምለግስ ትዝ  ትውስ ቢልሽ። ብሩክ (ዝብርቅርቅ) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 832
21
ፀሀፊና አንባቢ ብሩክ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

biruk.mp3

7 372
8
🐵የዝንጀሮ ዕርሻ 🐵 የቱ ዘር ዘሪ ነው ከሰማዩ ዕርሻ የሚበትናችኹ ጠብቆ በማምሻ? እንደ ዝንጀሮ ዐመል … እንዲታጨድ ማታ ጠዋቱን ተዘርቶ ሲበትን አመሸ ሊለቅማችኹ ማልዶ! ✍ ረድኤት ተረፈ ( ከ'አንድ ኅሙስ' የግጥም መድብል) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
7 695
14
በፍቅር ሱባኤ በረሀብ በረሀ በስጋ ጠውልገን በፍቅር ሰማይ ስር ከሚያፈሰው ዝናብ በመንፈስ አብበን ከንፈራችን ደርቆ አየተዛዘንን አናርሰው ነበር እየተቃመስን እስትንፋስ ሳይቀረን እየተዋዋስን ከቤታችን ጀርባ ባለች ትንሽ ደብር ከሚካኤል እቤት አንዳችን ላንዳችን ስንፀልይ ውለን ባገኘናት ጉርሻ አፋችን አብሰን በፍቅር ሱባኤ ደስተኞች ነበርን ትዝ ይልሻል ወዴ? ክረምትና በጋን የአልጋችንን ቦታ ሳንቀይር ረስተን ሁሌ በጋ መስሎን ዝናብ የጣለ ቀን አልጋችን እርሶ እረጥቦ ገላችን ተቃቅፈን ያደርነው እያንቀጠቀጠን ለሌላ ያየ ሰው የችግር ቢመስልም ለኛ ፍቅር ነበር ደግሞ ለበዓል ቀን ፊታችን ሲያበራ ለስላሳ እንጀራ በወጥ ተፈትፍታ ቤታችን ስትገባ ሙቀቱ ሲያጅበን የጠጅ እና የጠላ ሰው ሆንን እያልን አቅም በአንድ ቀን እንደተላበስን ስንጮት ያደርነው ቀኑ እስኪነጋ እንቅልፍ ሳየጥለን የዛች ቀኗን ማግስት ከአልጋችን ወለን ላንነሳ ምለን ያሳለፍነው ሁሉ እውነት ትዝ ይልሻል አውቃለሁኝ ውዴ አዎን አስታውሰሻል ከቤታችን መሀል የጣልሽው ትዝታሽ አግኝቶ ነግሮሻል ድሮስ ያለ ፍቅር አሁን ያለሽ ሁሉ መቼ ይጠቅምሻል ልብሽ ከኔ ኋሏ ብዙ ጠይቆሻል ያኔ ግን ከኔ ጋራ ሳለሽ ደሀ እንኳ ብኖንም ቤታችንን በግንብ ባናንፅ ባናሽቆጠቁጥም ሆዳችን ለሁሌ ጠግቦልን ባያድርም የኔና ያንቺ ህይወት አንድ ቀን ተሳስቶ አማሮን አያውቅም ✍ @abelyohannes12 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 746
23
............አየሽ ? ይሄንን ምኞት ነው ይሄንን እሳት ነው የፍቅርሽ ማዕበል ድራሹን ያጠፋው በፍቅርሽ ወተት ነው እንስሳነት ከስሞ ሠው መሆን የፋፋው ይሄን ጉድ ምኞት ነው ፍቅርሽ ያከሸፈው ሚሊዮን ብልግና እልፍ መሻት ገሎ ውስጤ የገዘፈው ........አየሽ......? ✍አሌክስ አብርሀም @poemmylove ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
6 463
23
ቅርጥፍ... ድብን...... ቁርጥ ስንጥቅ.... ትርክክ..... ፍልጥ እጥፍጥፍ.. ድብስብስ.. ግልብጥብጥ . . . . ከግንባር መሾሌ፣ሳይከፋኝ ማጠሬ ምናል ዘንባባውን ባደረገኝ ዛሬ . . ሰውን ከሰውነት ምታሳንስ ቆሌ እፅዋት አድርገኝ...... ቆርጠህ ከቁመቴ አሹለህ ካካሌ . . . ትናንት ሰው እንደሆንኩ ዛሬን ለምለም ሆኜ ነገን በዛው ባልቀር ዘንባባ አርገኝና ላንድቀን ዘንባባ ሺ አመት ልገብር . . . ቅርጥፍ በጣቶቿ ድብን በእጆቿ ቁርጥ በጥርሶቿ ስንጥቅ በጥፍሮቿ . . . ድብስብስ ግልብጥብጥ እጥፍጥፍ ኡፍፍፍፍፍፍ፤ ምናል ዝንጥፍ ሆኜ ከግንባሯ ላይ ባርፍ . . ሰውመሆኔ ይቅር ሰውነት ተወዷል ሰውመሆን ይቅርብኝ ሰባዊነት ወርዷል ይልቅ.... . . ዘንባባውን ልሁን ከአዳሞች ልላቅ ከከንፈርሽ ጓዳ በጥርስሽ ልሰንጠቅ። ሰውነት ይንራል ሰው ከመሆን በላይ ተክል ሆኜ ልኑር በቅናሽ ገላሽ ላይ . . . ምናልባት ዘንባባው ከ ቀለበት ጣትሽ ምናልባት ዝንጣፉ ከ ብርሌ አንገትሽ ምናልባትም ደሞ ከምወደው ፊትሽ ምናልባት ካካልሽ የሆነን እንደሆን ምናለበት ታዲያ ዘንባባውን ብሆን . . ማቆያ እንዲሆነኝ ለሳምንት ህማማት ከጣቷ ጠልቄ ግንባሯን ልሳማት በጫፌ እየወጋሁ ወየው ስትል ልስማት ልጅት የጻፍኩላት................ ✍tomi ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
6 853
30
ሀገር ሚያህል ፥ ዋርካ ከሰው ተጠልሎ፣ ለቆረጥነው ነገ ፥ ታሪክ ተቀጥሎ፣ ዛሬ ለሆድ አድሮ ፥ በጥጋብ ሲባዝን፣ ሰርገን እየገባን ፥ በሰርጉ ተከዘን። [ጥያቄ ውድቀት ቢያሸንፍም ፥ ድልን አሳስቆ ዛፍ እንዴት ፥ ይገፋል በቀጭን ሸንበቆ? #ናታን_ኤርሚያስ @UniqueDy ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
6 584
13
አላስብም መቼስ እጣዬ አደል ማጣት፣ ቢሆንም ይከፋል እድለቢስ ስትል እድሌ የምላት። ብትገፋኝ ብትንጠኝ ካሳቧ ብወጣ፣ ሽሽት ይይዘኛል መልሼ እንዳልመጣ፣ ለፍቅሯ ብሰዋ እራሴን አርግፌ፣ መንገዴን ብስተው እግሯን ተደግፌ፣ ዛሬ ጎረበጠኝ ህመም እየሆነ፣ የጨበጥኩት ተስፋ ከእጄ እየበነነ፣ የወጣልኝ ፀሀይ በፅልመት ዳመነ፣ ስቃዬ እየበዛ በፍቅር ማለዳ፣ ከአይኖቼ ማድጋ እንባ እየተቀዳ፣ መንፈሷ ካልቀና ልባዋን ካላራሰው፣ ባ'ካሄዴ ልፅና በመንገድ ልካሰው፣ . . ምን አልባት ስቃዬ በደስታዋ እንዲሽር፣ በመራቅ አምኜ ተስፋዬን ልሸርሽር ✍ናታን ኤርሚያስ @UniqueDy ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
7 313
28
ናፍቆት ፀሀፊ ና አንባቢ ✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️ 🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

ናፍቆት×2 የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗.mp3

8 172
21
😘አለሜ ነሽ😘 🔥ክፍል 5 ✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ "" "" ይኸውልሽ ከሳመችኝ በኋላ ምንም ያልኳት ነገር የለም ፈዝዤ ነበር የሳመችውን ጉንጬን ይዤ የቀረውት እሷ ፊት ላይ ግን ስስመኝ በመፍዘዜ ምክንያት ሳቅ ይታይባታል ደግማ ጠጋ ብላ "ምነው ችግር አለ?" አለችኝ አይ ስላት እና "ፈዘካል እኮ እሺ በቃ ቻው እንገናኛለን በቀጣይ ለእኔም ግጥም ገጥመክ ይዘክ ና እሺ" ስትለኝ "እሺ መቼ አልኳት".... "ነገ ማታ 12 ስአት ላይ እዚህ አለችኝና አትፍዘዝ ስስምክ ስትፈዝ እኮ ሳቄም መጥቶ ድንጋጤም ያዘኝ" ብላ በድጋሚ ግንባሬን ግጥም አድርጋ ስማኝ ሄደች ከሄደች በሆላ ድንጋጤዬ አለቀቀኝም ዲና በወሬው መሀል ገባችና እንዴት ግን" አለች ምን እንዴት አለው ያኔ ጓደኛዬ የለከፋት ለት ገና ሳያት እኮ ነው ልቤን የስርቀችው ኡፍፍፍፍፍፍ በጣም ደስስስስ እሚል ስሜት ነበር የተሰማኝ የምር ከሳመችኝ በኋላ ያለውን ጊዜ ዝም ብዬ ስስቅ አሳለፍኩት ነገ በድጋሜ ተገናኝተን ግንባሬን እና ጉንጭኤን በደንብ እንድትስመኝ ምርጥ ግጥም ልገጥምላት ወስኩኝ ዲና አፉ ውስጥ ልትገባ ምንም አልቀራትም እሱም በጣም በተመስጦ ነበር ሲነግራት የነበርው ጉሮሮውን ጠራርጎ ሊያወራ ሲል "ንገረኛ" አለችው እሱም ልነግሽ እኮ ነው ከዛ ማታ ለእሷ ግጥም ስፅፍ አመሸው ዲናም ፈጠን ብላ ምን የሚል እስቲ በልልኝ ስትል ኧረ ተረጋጊ አላትና ወደወሬው ተመለሰ ማታ ግጥም ገጥሜላት ግጥሙን12 ሰአት ደርሶ እስከማነብላት ቸኮልኩኝ በጣምም ጓጓውኝ ሰአተለ እንደምንም ደረሰልኝ እና 11:40 ላይ የግራሩ ዛፍ ስር ቁጭ ብዬ ጠበኳት 11:50 ሆነ ሰአቱ አልሄድ አለ በመከራ 12 ስአት ሞላልኝ አልመጣችም ባትመጭም ቅጠሪኝ አለ ገጣሚው ባትመጣም ስለ ቀጠርችኝ ደስስ ብሎኝ ነበር ከባትመጭም ቅጠሪኝ ግጥም ውስጥ የነፍስ ጥርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ በቆመ አውሎ ንፍስ ተመቶ እንደመውደቅ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ የሚያሳቅቅ ነበር እንደሌለ የገጠመው ግጥም ውል አለብኝ ትዝዝም አለኝ 12:15ሲል ሄዋኔ ጥቁር የቱታ ሱሪ ሌዘር ጃኬት አድርጋ እስኒከር ጫማ ተጫምታ ስትመጣ አየዋት ልቤ እሷ በቀረበችኝ ቁጥር እርምጃዋን ባፈጠነችው ቁጥር የእኔም የልብ ምት ይፈጥን ጀመር በስተመጨርሻ እኔ ካለሁበት ደረሰች እና ጉንጬን ስማኝ ቀልጠፍ ብል ተቀመጠች እንደተቀመጠች እጇን ወደፊቴ ዘርጋችው አፍጠጠች አፈጠጥኩባት እ ምን ታፈጥብኛለክ ልትለኝ ነው እንዴ በል ግጥሜን ስጠኝ እንደውም አንተ እራስክ አንብብልኝ አለችኝ ከዛ እኔም ድምፄን ለሰለስ አርጌ ግጥሙን ማንበብ ጀመርኩ ግጥሙ እንዲህ ይላል ዲና በጣምም ተመስጣ እሺ በልልኝ አለችው ከግራሩ ዛፍ ስር ከግራሩ ዛፍ ስር ልክ እንደለመድኩት እያነበብኩ ሳለ ግጥም የገጠምኩት በጩከት ውስጥ እና በመመስጥ ውስጥ አንድ ድምፅ ተስማኝ የሚመስጥ ድንገት ከየት መጣ ብዬ ደነገጥኩኝ አንድ ልጅ ነበርች ግጥሜን ስቀኝ ከተመጥኩበት ከግራሩ ዛፍስር ከጀመርዬ ሆና ቃላቶችን ሳስር ልጅት ብቃቴ እጅክ ተደምማ ጉንጭና ግንባሬን በአድናቆት ስማ ለኔም ግጠምኝ ብላ ብጠይቀኝ 12 ሰአት ላይ ልጅት ቀጠርችኝ ትእዛዝንን አክብሬ ይህው ግጥም ገጠምኩኝ የሚል ነበር እና ልክ ግጥሙን አንብቤ ሰጨርስ አመሰግናለው የኔ ውድ ብላ ሁለቱን ጉንጮቼን እና ግንባሬን ሳመችኝ ዲናም ወሬውን እኔ እምለው ሄዋን ግን እንደተርዳዋት በጣም ሰውን መሳም ትወዳለች አለች አዳምም ቀጠል አድርጓ ሄዋኔ መሳም ትወዳለች አዎ መሳም ትወዳለች አለ እና ዝም አለ ዲና እሺ ቀጥላ አለችው አዳምም ወሬውን ቀጠለ ከዛ በነጋታው ጠዋት ክላስ ልገባ ሰል ሄዋንን ከብዙ ወንዶች ጋር ቆማ ስትሳሳቅ አየዋት ቅናት ቢጤ ጫር አረገኝ ቆሜ የሚሆነውን ማየት ጀመርኩ ትንሽ ካወሩ በኋላ ሄዋኔ ሁሉንም እየዞረች ግንባራቸውን ሰማቸው ሄደች እራቅ ካለች በኋላም እጆን እያውለበለበች ተሰናብታቸው ወጣች ልከተላት ስለፈለኩኝ መከተል ጀመርኩኝ። አዳም ዲናን እንደደከማት እያስተዋለ ውይ በጣም ደከመሽ አይደል እንቅልፍሽ መጥቷል ታስታውቄያለሽ በቃ ተኚ ነገ እነግርሻለው አላት አይ ንገርኝ አለችና ድርቅ አለች ግን ደሞ እሱም ድርቅ ብሎ እንድትተኛ ነገራት እሺ ብላ ካመጣችው አነስተኛ ኩኪስ ውሀ እና ጋቢ ሰጠችው እሱም ወደ ሄዋን ሄዶ ሄዋንን በተመስጦ እና በፍቅር አይን ማየት ጀመር #የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን https://t.me/lovestorey1 ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
8 696
47
እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል……… እንባ ግን የታባቱ ደርቋል ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል ስቆ ላይስቅ ጥርሴ ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነፍሴ፡፡ ✍በዓሉ ግርማ (ኦሮማይ) ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
8 718
74
መሸ ደሞ አንባ ልውጣ በፀጋዬ ገ/መድህን ቅዱስ ዓርዮስ 🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

file

8 599
5
❤️አከላቴ❤️ ታውቃለክ አከላቴ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነህ በቃ ምን ብዬ ልንገርህ ሰው እንዴት ሁሉን መሆን ይችላል አንተ ማለት ለኔ ጓደኛ,ወንድም,እህት ሁሉ ሳይቀር መሆን ትችልበታለህ 💋አንተ የምታቅልኝን ነገር ምን አልባት ቤተሰቤ እንኳን ቢያቅ ይጠላኛል አንተ ድክመቴን የምትወድ ከፈገግታዬ ጀርባ ያለዉን ሀዘንና ጨለማ የምታውቅ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ያንን ጨለማ በየትኛውም ቅፅበት ወደ ብርሃን የምትቀይር አንተ የኔ ሁሉ ነገር ነህ እኔ አንተን አለማመን አልችልም ም/ክ አንተ 👫 ከኔ ጋር ነህ አንተን ለማውራት ምንም አልፈራም ኸረ እንደውም በተቃራኒው አለማውራቴ ያስጨንቀኛል የኔ አድማጭ እንኳን ለኔ ሆንክልኝ ባትሆን ምን እሆን ነበር ብዬ እራሴን ሳስበው እኔ እንጃ ብቻ እወድሃለሁ ✍ አሚ(ሰሊ)
8 555
149
😘የወጀቡ ጥግ😘 🔥ክፍል 33 ✍ደራሲ ፡ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ 🎤🔥ተራኪ ፡ ሀና #Share ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

file

8 581
24
😘ለፍቅር ስል😘 🔥ደራሲ፦ጎስ ✍️ክፍል ዘጠኝ """ """ """ 'ሄይ አንተ ወንዴ ወዴት ሄድክ' እያለች ፊቴን መታ መታ ስታደርገኝ ባትቼ 'እ ምን አልሽን' አልኳት የጠወለገ ሰውነቷን ከላይ እስከታች እያየው ለመናገር ፋታ ሳታገኝ 'ምን ሆነሽ ነው እንደዚህ የከሳሽው...' አልኳት....እሷ ግን ከመልስ ይልቅ ዘላ ተጠመጠመችብኝ 'እባክህ ጥያቄ አትጠይቀኝ ዝም ብለክ እቀፈኝ' አለችኝ.....ዘለግ ላሉ ደቂቃዎች ፀጥ ረጭ ብላ አጥብቃ ከእቅፏ ውስጥ አስገባችኝ....ለኔ መተቃቀፋ የተለየ ስሜት ቢሰጠኝም ዝምታዋ አስፈራኝ ከዝምታው ጀርባ የሚመጣው ማዕበል ሆዴን ረበሸኝ.....ለወትሮው በሳቅ እየታጀበች ከማውራት የማትቆጠበው ልጅ አሁን በዝምታ ተውጣ እላዩ ላይ ተጠምጥማብኛለች...'ማራናታ እባክሽ እያስጨነቅሽኝ ነው ምን ሆነሽ ነው ዝምታሽ እያስፈራኝ ነው'አልኳት ከእቅፏ እየወጣው...' እባክህ ምንም ጥያቄ አጠይቀኝ አልኩክ እኮ ኤስኮ' ብላ ካይኖቿ መንታ መንታ እየሆነ የእንባ ዘለላዎች ወረዱ........ምን እንደተፈጠረ ሳይገባኝ በቆምኩበት ጥላኝ ከነፈች.......በድንጋጤ ባለውበት ክው ብዬ ቀረው..... ****************** እለተ ሰንበት....የማለዳዋ ፀሀይ በምስራቅ በኩል ብቅ ብላ ጮራዋን ስትለቅ ሁሉም ፈጣሪውን ለማመስገን....ፀሎቱን ለማድረስ ወደ ቤተክርስትያን እያመራ ነው....እኔም መቱ እግሬ ከረገጥኩ ጀምሮ ለመጀመርያ ጊዜ ቤተክርስቲያን ሄድኩ......'ፈጣሪ ሆይ ማራናታን ምን አጋጥሟት ይሆን ምንስ ሆና ነው እኔን ማየት እስከማትችልበት ድረስ ጥላኝ እንድትሄድና ለሳምንታት ከአይኔ እንድትርቅ ያደረጋት......ፈጣሪዬ ሆይ እሷን በግድ የኔ እንድትሆን አልፈልግም ባለችበት ሰላም እንድትሆንልኝ ብቻ ነው የምፈልገው....ፈጣሪሆይ ለእኔም የፍቅሯን ወላፈን የምቋቋምበት ጥንካሬ ስጠኝ ከሷ የመራቅንም ጥበብ ስጠኝ' ብዬ በተንበረከኩበት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ...... ወራቶች ወራቶችን እየተኩ ሄዱ 5 ወራት የሚለው መልዕክት ከገባ ጀምሮ ሶስተኛ ወሩን አስቆጥሮ ወደ አራተኛው እየተንደረደረ ነው....ቀኑ በጨመረ ቁጥር ስጋቴ እያየለ ይመጣል ማንነቱንና ምንነቱን ከማላውቀው መልዕክት ጀርባ ያለው ሴራ የሚያዝ አይደለም ምን አልባትም ትልቅ የሆነ ድግስ ተደግሶልኝ ይሆናል ብዬ በመብሰልሰል ከሰውነት ተራ ወጣው...የሴትን ጡት የሚያስንቀው ደረቴ ሙሽሽ አለ....አይኖቼ ሙሽሽ አሉ....ከሰውነት ተራ ወጣው ግን በዚህ ሁሉ ሀሳብ ውስጥ ሆኜ የአይኔ ማረፍያ የነበረችውን ማራናታን ተደብቄ እሷ ሳታየን እያየሁዋት ፍቅሯን አስታግሳለው ምንም እንኳን ፍልቅልቅ ማንነቷ እና የበፊት ደም ግባቷ በጥርጣሬ አይን አስሬ አካባቢውን በሚቃኙ የጠቋቆሩ እና በጎደጎዱ አይኖች ቢተካም ውበቷ አሁንም እንዳለ ነው......በዚህ ሁኔታ እንደ ሰዶ አሳዳጅ በድብብቆሽ እሷን በመከታተል ወራቶችን አሳለፍኩ.... የፋይናል ፈተና በመድረሱ ሁሉም በየቦታው መሯሯጥ ጀምሯል....ወራቶችን ባስቆጠረው የማስተማር ሂደት ውስጥ ምንም ለፈተና ደንታ ሳይሰጣቸው የቢራ ጠርሙስ ላይ ተተክለው የዋሉና በየመሽታ ቤቱ አሸሸገዳሜ ሲሉ የነበሩት ተማሪዎች መመገብያ ግዜ አጥተው በየዶርማቸው እና በየላይብረሪው እያጠኑ ነው.....እኔ ዶርሜ ውስጥ ሳጠና ጓደኞቼ ውሎና አዳራቸውን ላይብረሪ አደረጉት........ፀሀይ ጠልቃ ተራውን ለጭለማ ለማስረከብ ስትቃረብ ዶርም ብቻዬን ማጥናቴን ትቼ ጓደኞቼን ለመቀላቀል ደንገዝ ገዝ ባለው ብርሀን ወደ ላይብራሪ ጉዞ እንደጀመርኩ ከማራናታ ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠምን.....ሁለታችንም በድንጋጤ ተዋጥን እሷ ከወራቶች በፊት እንዳደረገችው ጥላኝ ለመሮጥ እግሯን እንዳነሳች ተከትዬ ይዣት....'ማራናታ ጥለሽኝ አትሂጂ እባክሽ ጥለሽኝ አትሂጂ' አልኳት ከአይኔ እንባ እየተንጠባጠበ.....'ወንዴ ለሁላችንም ሰላም ስል ጥዬክ መሄድ አለብን እባክ አለበለዚያ ያ እርኩስ እኔን ያደረገኝን ያደርግካል'አለችኝ እያለቀሰች....ይሄን ስትናገር ሰውነቴን ወረረኝ ውስጤ ተላወሰ...'ማነው ሴጣኑ? ምንድነው ያደረገሽ?' አልኳት በውስጤ ከወራቶች በፊት የተጣላውት ሰው በአይምሮዬ ላይ እየተመላለሰ.....'እባክህ ወንዴ አትጠይቀኝ እባክህ ላንተም ለኔም ደህንነት...' ገና ተናግራ ሳትጨርስ 'ገን እኮ አፈቅርሻለሁ' አልካት አይናን እያየው...በዚህ ጊዜ ካፏ ምንም ቃል ሳይወጣ ከንፈራን ከከንፈሬ ላይ አጣበቀችው......እለተ ሀሙስ የቀን ቅዱስ አይደል የሚባለው....በተቆራረ ድምፅ 'እኔም እወድካለው ከተጣላን ቀን ጀምሮ ስላንተ ማሰብ አላቆሙኩም' አለችኝ ቁና ቁና እየተነፈሰች.....አለምን በእጄ ያስገባው ያህል በደስታ ፈገግ አልኩ......ግን ያ ደስታችን የዘለቀው ደስታችንን ለማክበር ከጊቢ እስከወጣንበት ሰአት ድረስ ነው.....የቀን ቅዱስ ያልነው ቀን የተረገመች ቀን ሆነችብን....ከትምህርት ቤት ጊቢ ውስጥ እንደወጣን ሰፈሩን የጥይት ብልጭታ አደመቀው....ወድያው ማራናታ ተዝለፍልፋ ወደቀች.....ዋይታው በረከተ እኔም ማራናታ ብዬ ለመጮውኩ በጉልበቴ ተዘረርኩ...ማራናታ የለበሰችው ነጭ ልብስ በቀይ ደም ተጨማለቀ...የሰዎች ዋይዋታ እየበረታና እየጠነከረ ሄደ...'እረ አንፑላስ ጥሩ የፖሊስ ያለ' የሚሉ ቃሎች በሰመመን ይሰሙኝ ጀመረ.......ህዝቡ መሰብሰብ ሲጀምር ሌላ ብልጭታ ተከተለ እኔምም በተንበረከኩበት የማራናታን እጅ እንደያዝኩ ከጎኗ ተዘረርኩ....በሽርፍራፊ ሰከንድ ውስጥ ደስታችን ወደ ሀዘን ተቀየረ....... * * * """"" * * * እኔ ከገባውበት ኮማ ውስጥ የነቃውት ከአንድ ወር በሁዋላ ነው.....'ማ ማራናታ' እያልኩ በተቻለኝ አቆም ተጣራው ድምፄን የሰማው ጓደኛም በደስታ እየዘለለ 'ኤስኮ ነቃህ ነቃህ ቆይ ዶክተር ልጥራ' ብሎ ነርስ ዶክተር እያለ እየበረረ ከክፍሉ ወጣ.... ዶክተሮቹ የሚያስፈልገውን ምርመራ አድርገው ከአንድ ሳምንታት በሁዋላ እንድወጣ ተደረገ...በዚሁ ሁሉ ጊዜ ግን ማራናታ ምን ሆና ነው የት ነች ተረፈች ለሚለው ጥያቄዬ ሁሉም ደህና ነች ከዚህ ስትወጣ ታያታለህ እያሉ ደረቅ ፈገግታ ከመለገስ ውጪ ማንም ቁርጥ ያለ መልስ ሊሰጠኝ አልቻለም.... ከተመታው ሁለት ሳምንታት በሁዋላ ወጀ ትውልድ ሀገሬ ሸገር ተመለስኩ እዛ ግን የጠበቀኝ ደስታ ነው ውዷ ማራናታ ደውላ ደውላ እራት ልትጋብዘኝ እንደምትፈልግ ነገረችኝ...ግብዣው ሁለት ቀናት ቢቀርም እኔ ግን ዝግጅት ማድረግ የጀመርኩት ከተነገረኝ ቀን ጀምሮ ነው.....ፅዱ ሆኖ ለመገኘት ያጎፈረውን ፀጉሬንና የከረደደውን ሪዜን ወግ ለማስያዝ ወደ ፀጉር ቤት የሄድኩት.....የማይደርስ ቀን የለምና ቀኑ ደርሶ ግብዣው ቦታ ብሄድም ማራናታ የውሀ ሽታ ሆና ቀረች....ከዛ ቀን ጀምሮ አይቻት አላውቅም ስልኳም ቢሆን ዝግ ነው....ለሷ ብዬ ደሜን አፍስሼ ሰውነቴ ላይ ሶስት ቦታ ጠባሳ ባሳርፍም መልሷ ክህደት ሆነ ትምህርቴን ዳግም አንድ አመት እንድደግም ሆኜ እሷ ግን ጥላኝ ጠፋች.....ከአመታት በሁዋላም አስር ቤት ዳግም ተከሰተች ከዛ በሁዋላ ያለውን ታሪክ የምታውቂው ነው" አልኳት ለትርታዬ ከአይኖቼ እንባ እንደሚፈሱ ያወኩት በእጆቿ እንባዬን ስትጠራርግለኝ ነው...
Show more ...
8 670
46
"ወንዴ ግን ቅጥያ ስምህ ለምን ኤስኮባር ተባለ" አለችኝ እንባ ባቀረሩ አይኖቿ እየተመለከተችኝ... "የስሜን ስያሜ የገኘውት በ90ዎቹ አሜሪካንንና ሜክሲኮን ያስጨነቀው ብቻውን የአለምን የማፍያዎንች ህግ የቀየረና አለቃቸው ከሆነው ፖብሎ ኤስኮባር የተወሰደ ነው....እኔም አንድ ሰሞን አሺሽ እኘግድ ስለነበረ እና እንደሱ ጨካኝ ስለሆንኩ ነው ስሙ የወጣልኝ" አልኳት.....ከገባውበት ሰመመን የሚጠራው ስልኬ አባነነኝ.....ቅድም ሲደማ የነበረው እጄ በፋሻ ተጠቅልሏል....እንደምንም እጄን እየጎተትኩ ስልኩን አነሳውት.....ጓደኛዬ ነበረ የደወለው.."ሉሊት ዱባይ አይደለም ያለችው እዚሁ ነው ከዱባይ ማን እንደደወለልክ ባላቅም አሁን ያለችበትን ቦታ እልክልሀለው"ብሎ ስልኩን ዘጋው....በንዴት ጦፌ በንዴት ግዬ ለበቀል ሉሊትን እንደ ጨርቅ....... #የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን https://t.me/lovestorey1 ይቀጥላል ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
8 637
36
⚡️አብረን ዝም እንበል ⚡️ ከሰው መንጋ እንገንጠል ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል ምነው አዋሽ ማዶ ቆቃ የሸለቆ ግርጌ ሸሽተን የቆቃን ሰቆቃ ሰምተን ሲቃውን ሲሰብቀው አይተን ሰቀቀኑን ተወያይተን የምሽት ጀንበር ቢውጠን ውሃ አንደ ዱታ ሲተምም በድን ሸለቆ ሲናገር ሰማያዊ ፈረስ ተጭኖ ከአጥናፍ አጥናፍ ሲንደረደር ሲያስጉተመትም ሲያስገመግም በአይነ ህሊና ለመመስከር ሳንጨነቅ ሳንገደብ ለማንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር ካይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብራር አዋሽ ማዶ አብረን እንውረድ አጉል ነው ብለን ሳንፈርድ ድንቅም ነው ሳንል ሳንወድ ዝም ብለን አብረን ብንወርድ ከሰው መንጋ ተለይተን ከጠረኑ ተነጥለን ከጉምጉምታው ተገንጥለን ከኳኳታው ብንከለል ከላንቃው ከድምፁ ሸሽተን በእፎይታ ጥላ እንጠለል በቆይታ በፀጥታ ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል መቼም አይሆንም ካልሽ ቅሪ ግድ የለም አትገደሪ ልቦናሽ በመተረልሽ ባሳደረብሽ እደሪ ተስፋ መቀነን ነው መቼም የሰው ልብ አይችለው የለም ብቻ ዳግመኛ ሞት ሳንሞት አዲስ ቀን ሳይጨልምብን ድፍን ደመና ሳይቋጥር ክረምት ውጅት ሳይወርድብን ኮከባችንን ሳንጠራ ሳንቆጥርባት ሳትቆጥርብን ሞራችንን ሳናስነብብ ሳናሳያት ሳታይብን ጨረቃን መስክሪ ሳንል ሳናውቅባት ሳታውቅብን አዋሽ ማዶ ቆቃ በረን እባክሽ ጀንበር ትጥለቅብን ውሃ እንደ ዱታ ሲተምም በድን ሸለቆ ሲናገር በሰማይ ፈረስ ተጭኖ ከአጥናፍ አጥናፍ ሲንደረደር ሲያስጉተመትም ሲያስገመግም በአይነ ህሊና ለመመስከር ሳንጨነቅ ሳንገደብ ለማንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር ካይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር ከሰው ኳኳታ እንነጠል ላንድ አፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል ✍ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥
Show more ...
9 448
106
ከምኔው ✍️ዘምሽ የአልግዬ✍️ 🖤የጠቆረ ልብ🖤 አንባቢ መሳይ ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

ከምኔው…በመሳይ.mp3

9 107
24
✍️ቅዱስ ዓርዮስ✍️ 🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ @fikerdertogada1 ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝ 4 any comment @fikerdertogada_bot ❥❥________⚘_______❥❥

file

9 314
11
Last updated: 27.11.21
Privacy Policy