cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio Students 9_university💡📚

9_university ሁሉንም መፅሐፍቶችን እና ጥያቄዎችን በ ትንሽ size እዚህ ያገኛሉ

Show more
Advertising posts
358Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✅ ለጥያቄዎቻችሁ የተጣራ መልስ : 🔎 100ሺ ከ50% በታች  ያመጡ ተማሪዎች እንዴት ይለያሉ ፤ መስፈርቱ ምንድነው ❓ 📚 የመጀመርያው ተፈታኞች መረዳት ያለባችሁ እውነት ፤ 860ሺ በላይ ተማሪ ለዮኒቨርስቲ መግቢያነት ብቁ የሚያረገውን ውጤት ወይም 50% አላመጣም ይሄ ማለት ወደ ዮኒቨርስቲ [እንደ መጀመርያ አመት[Freshman] ዮኒቨርስቲ ተማሪ አትገቡም ። በቃ ...ግልፅ ነው ለዮኒቨርስቲ ብቁ የሆኑት እና ወደ ዮኒቨርስቲ የሚገቡት ወደ 30ሺ ገዳማ የሚጠጉት ብቻ ናቸው ። 🏷 ለዮኒቨርስቲ ለመግባት የግድ : 🪧ለናቹራል ከ700 ውስጥ 350 ወይም በላይ 🪧ለሶሻል ከ600 ውስጥ 300 ወይም በላይ ማምጣት ያስፈልጋል ። 📚 ነገር ግን ከአጠቃላይ የመንግስት ዮኒቨርስቲዎች የመቀበል አቅም አንፃር ያለፉት ተማሪዎች ከ20 በመቶ ስለማይበልጡ ፤ 100ሺ ለሚሆኑት ተማሪዎች ድጋሜ ዕድል ይሰጣል ። እንዴት 😳❓ 📚100ሺ ከ50% በታች ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ዮኒቨርስቲ ይገባሉ ፤ ነገር ግን የመጀመርያ አመት የዮኒቨርስቲ ተማሪ አይሆኑም ። በድጋሜ የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መመዘኛ ትምህርቶችን በዮኒቨርስቲዎች ውስጥ በክለሳ መልክ እስከ ሰኔ ድረስ ይወስዳሉ /ይማራሉ ፤ ከዛም ከቀጣይ የ2015 ዓ.ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ጋር  ሰኔ /ግንቦት ላይ ተፈትነው ወደ ዮኒቨርስቲ ለመግቢያነት ብቁ የሚያረጋቸውን ውጤት ካመጡ ይቀጥላሉ ፤ ካላመጡ ደም ወደቤት ይመለሳሉ [ይጫራሉ] ። 📚 ታዲያ ይሄ ከprivate (የግል ተፈታኝ ) በምን ይለያል ❓ ከፈለኩ አሁንስ ቢሆን Private ሞልቼ ካለፍኩ ወደ ዮኒቨርስቲ እገባ የለ እንዴ ካላችሁ 👉 2 ከPrivate የሚለይበት ጉዳይ አለ ። 🏷 1ኛ ትምህርቱን በክለሳ መልክ በዮኒቨርስቲ ትማራላችሁ ፤ ማለትም እንደ ግል ተፈታኝ (private ) በራሳችሁ ጥረት ብቻ ፤ አንብባችሁ ሳይሆን በመምህራን ዕገዛ በዮኒቨርስቲው ትማራላችሁ ። 🏷2ተኛ ካለፋችሁ በዮኒቨርስቲው ትቀጥላላችሁ ፤ ከቀጣይ ተፈታኞች ጋር ተፈትናችሁ የምትወድቁ ከሆነ ግን ወደ ቤት ትመለሳላችሁ ። 👉 በአጭሩ የሁለተኛ አመት የ12ተኛ ክፍል ተማሪ እንድትሆኑ ዕድል ይሰጣቹሃል ። ✅ ታዲያ የ100ሺ ተማሪዎች ምልመላው እንዴት ነው የሚካሄደው ❓ 📚ይሄ የሚወሰነው በተማሪዎች የውጤት ዳታ መሰረት ነው ፤ ግልፅ የሆነው ነገር ለ50% ቅርበት ያለው ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ከሌሎች በተሻለ በምርጫው የመካተት ዕድል አላቸው ። ነገር ግን ተማሪው ብዙ በመሆኑ [900ሺ ገዳማ ] ተመሳሳይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በቁጥር ብዙ ነው የሚሆኑት ይሄም የውጤት ጥግግትን ይፈጥራለ : ለምሳሌ : 🏷 አንድ ተማሪ 348 ከ700 ቢያመጣ እንደሱ ያመጡ ተማሪዎች በብዙ ሺዎች ይኖራሉ ፤ ይሄ ማለት ከ50% ዝቅ እያለ ሲመጣ [ ከ50% ብዙም ሳንርቅ 100ሺው ይሞላል ] ...ይሄም መቁረጫ ውጤቱ ከ50% በጣም የቀረበ እንደሚሆን እና ብዙም ከግማሽ ዝቅ ያለ እንደማይሆን ያስገነዝበናል ። ✅ በይበልጥ ለማስረዳት ከ700 349 ያመጡ 20ሺ ቢኖሩ ፥ 348 25ሺ ቢኖሩ ... እስከ 340 ድረስ ደሞ 50ሺ ቢኖሩ 100ሺው ሞላ ማለት ነው ። ✅ አስተውሉ ነገር ግን ይሄ የ100ሺዎቹ ምልመላ ሲካሄድ በውጤት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ትንተና ተካሂዶ ነው ፤ ማለትም ተፈታኙ [ መደበኛ ፤ የግል ፤ የማታ ] ክልሉ [ ታዳጊ ፥ ከተማ ፥ ገጠር ] ...ፆታ [ወንድ፤ ሴት ] ወይም ሶሻል ወይም ናቹራል ፤ የዮኒቨርስቲዎች የመቀበል አቅም ተጠንቶ ተሰናስኖ ፤ ተተንትኖ ነው የመግቢያው መቁረጫ ነጥብ [ለክለሳ ትምህርቱ ] የሚወሰነው ። 💬 ስለዚህ አሁን ላይ ያንን ለመግለፅ የሚሆን የተሟላ መረጃ የለንም ። @ethio_stu @ethio_stu
Show all...
Point‼️ #መልስ ዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት 150ሺ አከባቢ ነው። 80 ሺ የተፈጥሮ ሳይንስ እና 70ሺ የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለው። ስለዚህ እንደሚታዩት አጠቃላይ ዩኒቨርስቲ የገቡት 30ሺ ብቻ ናቸው። ( 23ሺ NS And 7ሺ SS ) እነዚህ ተማሪዎች በቀጥተ የአንደኛ አመት ተማሪ ይሆናሉ ተብሏል። (ይህ ማለት Freshman አይማሩም ) ስለዚህ ከ 50% በታች ያመጡ ተማሪዎች 120ሺ የሚሆኑት ዩኒቨርስቲ ገብተው የማካካሻ ትምህርት ተምረው በድጋሚ የመፈተን እድል ይሰጣቸዋል። ( 57ሺ NS and 60ሺ+ SS) አድል የተሰጣቸው ተማሪዎች ውጤታቸው ዝቅ ባለበት የት/ት አይነቶች ላይ የማካካሻ ትምህርት ይማራሉ። የሚማሩት ግን ዩኒቨርስቲ ገብተው ነው። ከዛ በድጋሚ ይፈተናሉ እና ካለፉ እዛው ዩኒቨርስቲ 1ኛ አመት ይቀጥላሉ። ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ልያወጣ ነው። በዚህም መሰረት Freshman Course ልቀር ይችላል።  ኮሌጅ ላይም አዲሱ አሰራር ይተገበራል። ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ይደርሱናል። ሌሎች 700ሺ ተማሪዎች TVET(ቴክንክና ሙያ) ላይ ገብተው ድፕሎማ ይማራሉ ተብሏል። የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️ @ethio_stu @ethio_stu
Show all...
👉ከ350 በላይ ያመጣቹህ ናቹራሎች በሙሉ ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲ ገብታቹህ ለመማር አልፋቹሃል‼️ 👉ከ300 በላይ ያመጣቹህ ሶሻሎች በሙሉ ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲ ገብታቹህ ለመማር አልፋቹሃል‼️ ፨ከዚህ በታች ያላቹህ በተለይ ለ50% የቀረባቹህ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት ከሚወስዱ ተማሪዎች ውስጥ መሆን አለመሆናችሁን ትምህርት ሚንስቴር በቀጣይ ቀናት ያሳውቃቹሃል። ፨የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በተመለከተም ትምህርት ሚንስቴር የሚለውን አብረን እንሰማለን። @ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
Show all...
ማስተካከያ ከአዲስ ማለዳ❗️❗️ የ2014 የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ከ980 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር 28 ሺ ነው ስትል መረጃዋን አስተካክላለች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር፣ ዩኒቨርስቲዎች ካላቸው የመቀበል አቅም ጋር በፍፁም እንደማይጣጣም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች 130 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳላቸው የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው የቅበላ አቅም የ2014 ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገቡት ከዩኒቨርሲቲዎቹ የመቀበል አቅም ከ20 በመቶ የማይበልጥ ነው ማለት ነው፡፡ ከፍተኛ የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ማጋጠሙን የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች የሰሙ ሲሆን፣ ያጋጠመውን የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል ምን ይደረግ በሚለው ላይ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡ በውይይቱ የዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት አቅም ጋር የሚጣጣም ተማሪ፣ ወደ ዩኒቨርስቲ ሊገባ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንን ተከትሎ፣ ዩኒቨርስቲዎች በመቀበል አቅማቸው ልክ ተማሪዎችን እንዲቀበሉ አማራጭ እየተፈለገ ነው፡፡ በዚህም በልዩ ሁኔታ ለማለፊያ የቀረበ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት ወስደው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረግ የሚለው አንዱ አማራጭ ሆኖ በመንግሥት በኩል እየታየ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ሰምታለች፡፡ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲያውቁት የተደረገ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️ ትምህርት ሚኒስቴር https://t.me/Tmhrt_Minister https://t.me/Tmhrt_Minister
Show all...
ማስታወቂያ ለ2014 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ተፈታኞች በሙሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ፡- • በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም • በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ማሳሰቢያ፡- • ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ • የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ፡፡ ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ራስዎን ይጠብቁ፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥር 18/2015 ዓ.ም አዲስ አባባ - ኢትዮጵያ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02tbzVnEKH1qzyq2xCG3efDpJ9fJzfvWL6kieYRwwC8g2j4U6TpgXL8EMGCpGuTDUal&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz
Show all...
EAES 🇪🇹 Result bot

EAES: Educational Assessment and Examination Service Official Bot. Use this bot to check your Result.

ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? እጅግ በጣም በርካታ ወላጆች እና ተማሪዎች " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ይፋ የሚደረግበት ቀን ታውቋል ወይ ? " የሚሉ ጥያቄዎችን ካለፈው ሰኞ / ጥር 15 ጀምሮ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መቀበያ @OfficialTikvahethiopiaBot ላይ እያስቀመጡ ይገኛሉ። የተቀመጡት የወላጆች እና ተማሪዎች ጥያቄ ብዙ መሆናቸውን ተከትሎ እና ተማሪዎችም ያለመደበኛ ትምህርት እያሳለፉ ያሉት ቀናት እጨመረ በመሆኑ ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል። ባለፈው ሳምንት áˆ‹á‹­ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይፋ ይደረጋል ? " ብለን ጠይቀናቸው ፤ ከጥር 15 ጀምሮ ባሉት ቀናት የሚል ምላሽ ሰጥተውን ነበር። ዛሬ ይህንኑ ጥያቄ በድጋሚ ለትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አቅርበን ውጤት ይፋ ማድረጊያ ቀኑ  " ከነገ እንደማያልፍ " በዚገይ ደግሞ እስከ ቅዳሜ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመውናል። ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ930 ሺ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም። @tikvahethiopia
Show all...
#Resultsgrade12 📌የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት የሚያዩበት Website ተቀይሯል። አምና የነበሩት አራት ውጤት የምታዩበት አማራጮች ተቀይሯል። በዚህ አመት የተማሪዎች ብዛት በእጥፍ ስለጨመረ አማራጮችን ወደ ስድስት አሳድገዋል። የተማሪዎች ውጤት ወደ System እያገባ መሆኑን እና የተማሪዎች ቁጥር ብዛት ስላለው ለመዘግየት አንዱ ምክንያት መሆኑን ተጠቁሟል። አሁንም ውጤት መቼ ይፋ እንደሚሆን ማወቅ አልቻልንም ። ለማንኛውም ውጤት ልክ እንደወጣ ውጤታቹን የምታዩበት websites እነዚህ ናቸው። 1. eaes.edu.et 2. eaes.gov.et 3. eaes.et 4. result.neaea.gov.et 5. Telegram 👉 @EAESbot 6. SMS 8046 የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሲሆን በፈጣን ኔትወርክ ውጤታችሁን ለማየት እንሞክራለን። Registration no 👇👇👇 @Darik10
Show all...
ውጤት ለማየት የሚረዷችሁ ጠቃሚ መንገዶች‼️ ውጤት የሚለቀቅበት ሰዓቶችን 4:00,8:00 እና 10:00 ላይ በንቃት መጠበቅ አለባችሁ። ለማንኛውም ውጤት ልክ እንደወጣ ውጤታቹን የሚታዩበት websites እነዚህ ናቸው። 1.  result.neaea.gov.et 2.  result.ethernet.edu.et 🧣የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሲሆን በፈጣን ኔትወርክ ውጤታችሁን ለማየት እንሞክራለን። በውስጥ መሾመር አናግሩን 👇👇👇👇 @Darik10
Show all...
Join us for more 👇👇 @ethio_stu @ethio_stu
Show all...
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
Show all...