cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ንብረት አበበ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
763Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከእስር የተለቀቁት የኦፌኮ አመራር አቶ ደጀኔ ጣፋ የተፈቱበት ክስተት ያልጠበቀና የማይታመን እንደነበር ተናግረዋል። ፖለቲከኛው በመንግሥት ዓርብ ዕለት ምሽት ድንገት ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁት ፖለቲከኞች ክስተቱ ያልጠበቀና የማይታመን እንደነበር ተናግረዋል፡፡የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ደጄኔ ጣፋ ውሳኔው የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸው ፍሬ እንዲያመጣ የዓላማው ቀጣይ ሂደት ላይ እንድያተኮር ጠይቀዋል፡፡ፖለቲከኛው የእስሩ ገጠመኞቻቸውን በገለጹበት ቃለ ምልልሳቸው በይቅርታ መንገድ መወያየት እና መደራደር በኢትዮጵያ ለራቀው ሰላምና መረጋጋት እልባት ያመጣል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል፡፡ [DW]
Show all...
ሰበር መረጃ ፋኖ ህይወቱን የሰዋው ለሀገርና ለህዝቡ ክብር ተፋልሞ ብቻ አደለም ፥ መንግሥት አለኝ የሚለው ሰራዊትን ጭምር ከጠላት ከበባ ለመታደግና አይነኬ ምሽጎችን ደረማምሶም ጭምር ነው፡፡ ታዲያ! "አሸባሪ" ተብለው የተፈረጁት እነኦነግ ሸኔን በጉያው ወሽቆ በየቀኑ እያሰለጠኑና እያስመረቁ እንዲደረጁ የሚያደርገው መንግሥት ፥ ይህን የሀገር አለኝታ የሆነ ፣ በራሱ ጥይትና ሎጂስቲክ የሚፋለም ፋኖ ፥ ሠነድ አዘጋጅቶ " ለህልውና ስጋት ነው!" ሲል ከመስማት በላይ ፥ ምን መፈጠርን የሚያስጠላ ህሊና ቢስነት ይኖራል ትላላችሁ? ወርቅ ላበደረ ጠጠር መላሽ የሆኑት የመላው ኢትዮጵያ የገዢው መንግሥት ካድሬዎች ፥ በብሌናችን ፋኖ ላይ ሰነድ አዘጋጅተው "ስጋት ነው!" ሲሉ ፈርጀው እየመከሩበት ነው! አይንህን ለአፍታም ከድነህ እንዳተኛ! "ፋኖነት" ለህዝብና ለሀገር ክብር ፥ ራስን በደስታ አሳልፎ የመስጠት ከፍፍፍ... ያለ የሞራል ልዕልና ነው ከሰሞኑ የፌደራል እና የክልል የበላይ አመራሮች 48 ገጽ ያለው እንደነገሩ በተሰናዳ ሰነድ ላይ በአብይ አህመድ እና የብልጽግና ሰዎች አወያይነት ውይይት ተደርጓል። በሰነዱ የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የድህረ ጦርነት ስጋት የተባሉ ጉዳዮች ተለይተው ተቀምጠዋል። በመጀመሪያ የተዳሰሰው የአማራ ክልል ሁኔታ ሲሆን ተጀምሮ እስኪያልቅ የሚወራው በክልሉ ስላለው ፋኖ እና ከዘመቻ የተመለሱ ግለሰቦች ነው። እነዚህን አካላት የኢትዮጵያ ስጋት ተብለው ተቀምጠዋል። ኢመደበኛ አደረጃጀቱ የታጠቀውን መሳሪያ በመጠቀም ህዝቡን በግድ ግብር እንደሚቀበል፣ ተደራጅቶ ወደ ዘረፋ እንደሚገባ፣ በየመስሪያ ቤቱ እየሄደ ስልጣንና ጥቅም ይሰጠኝ ብሎ እንደሚያስገድድ፣ አስገድዶ መድፈር እንደሚፈጽም፣ የመንግስት ስልጣንን እንደሚቀማ፣ በአጠቃላይ ፋኖና ታጣቂው ከኦነግና ወያኔ በላይ የአገሪቷ ስጋት ተደርጎ ተቀምጧል። በመሆኑም በአስቸኳይ ትጥቅ እንዲወርድ ያዛል። የድል ሽሚያ፣ የድል አጥቢያ አርበኛ፣ የተካድን ፖለቲካ አራማጅ፣ ወዘተ የሚሉ ፍረጃዎች ለአማራው ተሰጥተዋል። የትግራይ ህዝብ ላይ የበቀል እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል፣ መንገዶችን በመዝጋት እርምጃ መውሰድ እና ሌሎች ክሶችም ቀርበዋል። የኦሮሚያን ክልል ሁኔታ በሚዳስሰው ክፍል ኢመደበኛ አደረጃጀት የለም ይላል። በሌላ በኩል በጣም በሚያሳዝን መልኩ ከኦሮሚያ ሊመጣ የሚችለው ችግር የተባለው ኢትዮጵያን የታደግናት እኛ ነን፣ ብዙ ወደመከላከያ ያስገባን እኛ ነን፣ መስዋእት የከፈልን እኛ ነን ፣ ስለዚህ ልዩ ስልጣንና ጥቅም ማግኘት ያለብን እኛ ነን የሚል ነው። እጅግ አሳፋሪና በመሬት ያለውን ሁኔታ ያላገናዘበ ድርሰት ነው የቀረበው። የአማራ አመራሮች ይህንን ተቀብለው ሄደዋል። በየአካባቢውም ይህንኑ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ነው። "#ፋኖን_ከሼኔ_እኩል_በኢ_መደበኛ_አደረጃጀት_መፈረጃችሁን_ስንሰማ_እኛም_ደንግጠን_ነበር" "ፋኖ ከመከላከያ፣ ከአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሺያ ጎን ሆኖ ሃገርን ከመፍረስ በደሙ የታደገ ቡድን ነው። መሪዎቹ የጀግና ሜዳይ ይገባቸው ነበር። ይህም ይቅር። እቅዳችሁን ሰምተናል የክህደት ጥግ ብለነዋል። እኛ ግን ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን !!! መዘጋጀት አሁን ነው። The worst is coming!
Show all...
መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያየ #Ethiopia | ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መንፈሳዊና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ የተነሱ የመብትና የይዞታ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም ዓ.ም ረፋድ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጉባኤ አካሒዷል። በጉባኤውም ከፍ ሲል የተገለጸውን ርዕስ መሰረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ክብርት ከንቲባዋ አርብ ጥር ፮ ቀን ፳ ፻ ወ ፲ ፬ ዓ.ም ጠዋት አራት ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሔደው በጉባኤ ጉባዔ ላይ እንዲገኙና ማብራሪያ እንዲሰጡ ቀጠሮ አሰንዲያዝ አና ጉዳዩ በተረጋጋ መንገድ ውሳኔ እንዲያገኝ መመሪያ ሰጥቷል። ይህ ሲኖዶሳዊ ውሳኔ የቤተክርስቲያኒቱ የመጨረሻ የሥልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ ለውሳኔው ተግባራዊነት ሁሉም ወገን የድሻውን ማበርከት የሚጠበቅበት መሆኑን በመገንዘብ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ አርብ ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በሚካሔደው ጉባዔ እልባት እስከሚሰጠው ይታመናል። ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ እምነት ተከታይ ህግና ሥርዓትን ጠብቆ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚሰጠውን ውሳኔ ማክ በር እንደሚገባው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች ሲል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። (ኢኦተቤ ቴቪ)
Show all...
ሰበር ዜና - አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠራ! የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በመስቀል አደባባይ ጉዳይ ለመነጋገር አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል። በሀገር ውስጥ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች በምልዓተ ጉባኤው እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለብፁዓን አባቶች የስልክ ጥሪ እያደረገ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ከቀትር በኋላከ 9:00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከናወን ይጠበቃል። (መምህር ምህረትዓብ አሰፋ )
Show all...
የኢሳያስ ቃለ ምልልስ ዋና ነጥቦች በአማርኛ - ደብረፂዮንን በሁመራ ለምን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ ጠየኩት። - ህወሓት በኤርትራ ውስጥ ከ100 በላይ ቦታዎች ላይ ኢላማ ለማድረግ ማቀዱን የሚያሳይ ማስረጃ አለን። - የህወሓት ጀብዱ የተሳሳተ ስሌት ነበር። - በህዳር 2020 የመጀመሪያ ሳምንት ከ5000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች የኤርትራን ድንበር አቋርጠዋል። - የኢትዮጵያ ጦር ከመቀሌ ይወጣል ብለን አልጠበቅንም። - የህወሓት አመራር ከስልጣን መውጣቱን እንኳን አልጠበቀም። የውጭ አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ እንዲወጣ ግፊት ያደርጉ ነበር። - ማንኛውም ጤነኛ ወታደራዊ አመራር ያለ ሎጂስቲክስ እስከ ኮምቦልቻ እና ደሴ ድረስ ሊገባ ባልደፈረ ነበር። - የህወሓት የውጭ ሃይሎች በጦርነቱ ውጤት አልረኩም። - ወያኔ በኤርትራ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከኃይለሥላሴና ከመንግስቱ ኃ/ማርያም የከፋ ነው። - የትግራይ የነጻነት ሪፐብሊክ የለም፣ አይሆንምም። - ወያኔ የኢትዮጵያን የተረቀቀውን ሕገ መንግሥት ከማንም በፊት እንዳነብ ሰጠኝ። ሕገ መንግሥቱ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነበር፣ እናም ቅሬታዬን አንስቻለሁ። - ከብሄር ፌደራሊዝም ፖሊሲ የበለጠ አደጋ የለም። - አገሪቱ አንድ ካልሆነ ለውጭ አገሮች በሉዓላዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ቀላል ነው። - ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ አንድነት ለኒዮ-ቅኝ ገዢ አገሮች ትምህርት ሆኖ ቆይቷል። - የአሜሪካን ህዝብ እና መንግስትን መለየት አለብን። በአለም አቀፍ ደረጃ ውድመትን የሚፈጥሩት መቶኛ ከአሜሪካ ህዝብ 0.1% እንኳን አይደለም። - በአሁኑ ጊዜ በዩኤስኤ ውስጥ የተሰራ የለም. ሁሉም ነገር በቻይና የተሰራ ነው. - ቻይና ሩብ የአሜሪካ ዕዳ አለባት። ዩኤስኤ በኢኮኖሚ ኃያል አገር ናት የሚለው ግምት የተሳሳተ ነው። - ስማቸው እንጂ ኢጋድ ወይም AU የሉም። የግል ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አበላሽተውታል። - ቻይና ምዕራባውያንን አንቀሳቅሳለች። ምዕራባውያን አገሮች ሩሲያንና ቻይናን መያዝ አልቻሉም። - በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ዓለም ለበጎ ነገር የተለየ ይሆናል. - የዓለም ልዕለ ኃያል መንግሥት እንደ ኤርትራ ትንሿን አገር ለስምንት ዓመታት እንዴት ማዕቀብ ይጥላል? ይህ በእነርሱ በኩል ተስፋ መቁረጥ ነው, እኛ ለመሾም ፈቃደኛ ባለመሆኑ. - የአሜሪካ ልዑክ ሥራ ለአገሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማዘዝ ነው። - ሽብርተኝነት የተፈጠረው ‘በነሱ’ ነው። - ባለፈው አመት ሲሰራጭ የነበረው 40% ዶላር በህገ ወጥ መንገድ በአሜሪካ ታትሟል። -በአሜሪካ መንግስት ላይ 'immunity' ፈጥረናል። - የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፖሊሲዎች እና 'የዓለም ስርዓት' የጫካ ህግ ናቸው. ተሃድሶ ተከልክሏል። - ኤርትራን ሰይጣናዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። - የአፍጋኒስታን ሰዎች ለምን ይሰቃያሉ? - በተሞክሮአችን ምክንያት የዩኤስን ማዕቀብ መቃወም እና ማቆየት እንችላለን። - የሰማንያ አመታት ታሪካችን ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው። የእነሱ ሰላም እና ብልጽግና ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው. - በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው አስከፊው ነገር ወያነ ነው። - ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን ያጠናክራሉ። - ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና አንድነት እንዲኖር የጎሳ ፌደራሊዝምን ማሻሻል ወይም ማስወገድ አለባት። - ህወሀት ለተጋሩ ከአማራ ያነሱ መሆናቸውን በመንገር ጥላቻን እየዘራ ነበር። -የመጀመሪያው ወያነ አስተሳሰብ ከሁለተኛው እና ከአሁኑ ወያነ የተለየ ነበር። - አሁን በሱዳን ያለው መጥፎው የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ነው። Ertrean press
Show all...
በኢትዮጵያ 🇪🇹 የመጀመሪያ የሆነውን የፊልድ ማርሻል ወታደራዊ ማዕረግ ለጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተሰጠ። በተጨማሪ ፦ • 4 ሌትናል ጀነራሎች ወደ ሙሉ ጀነራልነት፣ • 14 ሜጀር ጀነራሎች ወደ ሌትናል ጀነራልነት፣ • 24 ብርጋዴር ጀነራሎች ወደ ሜጀር ጀነራልነት፣ • 58 ኮሎኔሎች ወደ ብርጋዴር ጀነራልነት በአጠቃላይ 100 ከፍተኛ የጦር አመራሮች እድገት ተሰጥቷል። ሹመቱ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኩል ነው የተሰጠው። መረጃው የኢብኮ ነው።
Show all...
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ሀሙስ አዲስ አበባ መጣ አርብ ፖለቲከኞች ተፈቱ።
Show all...
የወያኔ ወንጀለኞችን ከእስር ቤት ለመልቀቅ መወሰኑ በጣም አስገርሞኛል። በአገር ውስጥም ሆነ በዲያስፖራ ውስጥ ያሉ ሰዎች ድርጊቱን እንደ ግልፅ ማታለል ይቆጥሩታል :: ታላቅነት በድል? የምን ድል?! ይህ የጅልነት ተግባር አስከፊ መዘዝ ያስከትላል አንዳርጋቸው ፅጌ
Show all...
በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱት ግለሰቦች ከማረሚያ ቤት ወጡ‼️ አቶ ጃዋር መሀመድ ፣አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ አቶ ሀምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጣአን ጨምሮ በነጃዋር መዝገብ የተካተቱ ሁሉም እስረኞች ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል።
Show all...
ጃዋር መሐመድና በቀለ ገርባ ከሰአታት በኋላ ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Show all...