cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሸገር NEWS

የሚያምኑት መረጃ!! እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ አሁኑኑ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ #ሸገር የናንተ #ሸገር የኛ

Show more
Advertising posts
24 317Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#ጤናመረጃ ለስላሳ መጠጥ አዘዉትሮ እና በመደበኛነት መጠጣት የሚያስከትለው ጉዳት!! ይህ እውነታ ሊያስደነግጥህ ይችላል። ለስላሳ መጠጥ ያለማቋረጥ እና በመደበኛነት መጠጣት የኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ይህ የሚከሰተው በአሲድ እና በማዕድን ራዲካል ሚዛን ምክንያት ነው። ለስላሳ መጠጦች ለውፍረት መንስኤ ከሚሆኑት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ እንደሆነ በሙከራ ተረጋግጧል። ለስላሳ መጠጥ አዘውትሮ መጠጣት ለአጥንት መዳከም እና ኦስቲዮፖሮሲስን እንደሚያመጣ ተረጋግጧል። ለጥርስ መበስበስ ያጋልጣሉ። ለስላሳ መጠጦች አሲዳማ ይዘት ያለው የጥርስ መስተዋት በማሟት ደካማ ያደርጋቸዋል። ለስላሳ መጠጦች ጠንካራ የካፌይን ይዘት አላቸው። ካፌይን ብስጭት፣ እረፍት ማጣት፣ ውጥረት፣የደም ግፊት፣ከመጠን በላይ ሽንት እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላል። ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር|share በማድረግ ይተባበሩ! "በዶ/ር ሀይለልኡል መኮንን የቀረበ" @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2014 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም፣ የጤናና የስኬት ይሁንልን። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ፕሬዝደንት ባይደን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ አሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በራሳቸውና በባለቤታቸው ስም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን እንዲሁም ከእነዚሁ አገራት የዘር ሐረጋቸው ለሚመዘዝ በመቶሺህዎች ለሚቆጠሩ አሜሪካውያን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዚሁ መልዕክታቸው ላይ ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች ሪፖርቶች በእጅጉ እንዳሳሳባቸው ገልጸው፤ አስተዳደራቸው በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከአጋሮቻችን ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ሰላምን ማምጣት ቀላል እንዳልሆነ ነገር ግን በውይይት ሊጀመር እንደሚችል በመግለጽ “ታላቋና ባለብዝሃነቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የገጠማትን መከፋፈል እንደምትወጣውና በድርድር ላይ በተመሰረተ የተኩስ አቁም በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንደምትፈታው እንምናለን” ብለዋል። በመልዕክታቸው ላይ በአማርኛ “መልካም አዲስ ዓመት” በማለት በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ የተመኙት ፕሬዝዳንት ባይደን “አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በዓለም ዙሪያ ላሉ ቤተሰቦችና ማኅበረሰቦች ሰላም፣ እርቅ እና ፈውስ የሚመጣበት እንዲሆን እጸልያሉ” ብለዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሰልጣኝ ወታደሮችን እያስመረቀ ይገኛል። የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምረቃውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት እያካሄደ ነው። የሁርሶ ወታደራዊ ኮንቲንጀት ማሰልጠኛ ከሁለት ቀናት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ማስመረቁን አስታውሶ ኢዜአ ዘግቧል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረ የጁንታው ቅጥረኛ ሃይል ተደመሰሰ! በዚህ ተልዕኮ የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ በሱዳን ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ 50 የሽብር መልዕክተኞችና የጁንታው ቅጥረኞች ሲደመሰሱ ከ70 በላይ የሚሆት ደግሞ ቆስለዋል፡፡ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ÷ ቅጥረኛው የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ የሞከረ ቢሆንም መቋቋም ተስኖት ተበታትኗል ብለዋል፡፡ ጠላት አሳቻ ሰዓት ጠብቆ አካባቢውን ለማተራመስ ቢንቀሳቀስም የጠላትን እንቅስቃሴ ከመነሻው በንቃት ሲከታተሉ የነበሩት የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍሎች ተቀናጅተው እርምጃ እንደወሰዱበት ነው የገለጹት። የጠላት ሃይል የቻለውን ያህል ለመከላከል ቢሞክርም በጀግናው ሰራዊት የበላይነት ተወስዶበት የተረፈው ሃይል አግሬ አውጪኝ ብሎ መፈርጠጡን ኮ/ል ሰይፈ ተናግረዋል፡፡ የጥፋት ሃይሉ ሲጠቀምባቸው እና ለእኩይ ስራው ሲያዘጋጃቸው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች ፣ ፈንጂዎች የወደሙ ሲሆን÷ የተቀሩት በጀግናው ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብተዋል ነው ያሉት፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በግንባር ድል አልቀና ሲለው አብዛኝው ጦር ወደ ሰሜኑ ክፍል አቅንቷል በሚል ከታሪካዊ ጠላቶች ተቀናጅቶ የህዳሴ ግድቡን ስራ ለማስተጓጎልና ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ነው የተናገሩት፡፡ በአሁኑ ስዓት በአካባቢው ጀግናው የመከላከያ ሃይል፣ እግረኛና ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች እንዲሁም የክልል ልዩ ሐይሎች አስፈላጊውን ዝግጁነት በማረጋገጥ ግዳጃቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ኮ/ል ሰይፈ መገለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በጎንደር ከተማ ህገ-ወጥ የነዋሪነት መታወቂያ ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች ተያዙ የመምሪያው የመረጃና ክትትል ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተገኘ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ መታወቂያዎቹ የተያዙት በማተሚያ ድርጅቱ ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ቁጥጥር ነው፡፡ መታወቂያዎቹ በሀሰተኛ ደብዳቤና ምንም አይነት የይታተምልን የትእዛዝ ደብዳቤ በሌለበት ሁኔታ ታትመው እጅ ከፍንጅ የተያዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ህገ-ወጥ መታወቂያዎቹ በላይ አርማጭሆ ወረዳ የአምበዞ ቀበሌ 200 እንዲሁም በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ስም 198 የተዘጋጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም በማእከላዊ ጎንደር ዞን መሃል አርማጭሆ ወረዳ ፈልፈል ቀበሌ ስም የተዘጋጁ 146 ህገ-ወጥ መታወቂያዎች በማተሚያ ቤቱ ታትተመው ለስርጭት በዝግጅት ላይ እንዳሉ መያዙን ገልፀዋል። ከህገ-ወጥ የመታወቂያ ህትመቱ ጋር በተያያዘም የማተሚያ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ አራት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በህግ-ቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአሜሪካ ጥሪ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ አካባቢ በሆነው የአፍሪካ ቀንድና በአጠቃላይ አፍሪካ ውስጥ ለሚኖር ሰላምና እድገት አሜሪካ ኢትዮጵያን በመደገፍ አጋርነቷን ማሳየት እንደሚገባት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአሜሪካ ቅርንጫፍ ገለጸ። የጉባኤው አሜሪካ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ለአንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ደብዳቤ አስገብቷል። በደብዳቤው አሁን በኢትዮጵያ የሚታየውን ችግር ለመረዳት ሀገሪቱ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የቆየችበትን የፖለቲካ ሂደት ማወቅ ያስፈልጋል ብሏል። በነዚህ ዓመታት በኢትዮጵያውያን መካከል ቅራኔና መለያየት እንዲፈጠር በተለያዩ መንገዶች መሠራቱን አመልክቷል። አሸባሪው ሕወሓት ይመራው በነበረው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የህዝብ ሀብት ዝርፊያ እንዲሁም በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በጋዜጠኞችና በግለሰቦች ላይ መንግስታዊ የሽብር ወንጀል ሲፈጸም ነበር ብሏል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ከወር በኋላ መንግስት ይመሰረታል ተባለ ከወር በኋላ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ መንግስት እንደሚመሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ስድስተኛው ዙር የመንግስት ምስረታ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ይካሄዳል ብሏል። ሰኔ 2014 የተካሄደውን 6ኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ ማሸነፉን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጹ ይታወሳል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀብት 1.1 ተሪሊዮን ደረሰ ለሃገር መከላክያ ሠራዊትና ለጸጥታ ኃይሎች 800 ሚሊዮን ብር ሰጠ የኢትዮያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሀብት ከ 1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡ የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቢ ሳኖ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣የባንኩ ሀብት ከ1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የ2013 በጀት ዓመት መጣናቀቂያ ድረስ መሆኑን ተናገረዋል፡፡ እንደ ፕሬዝደንቱ ገለፃ፣ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የጠቆሙት አቶ አቢ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልል የጸጥታ ኃይሎች ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች፣ ባንኩ 300 ሚሊዮ ብርና ሠራተኛው 500 ሚሊዮን ብር በድምሩ 800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ናቻው! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብዣ ወደ ሀገሪቱ ማቅናታቸው ታውቋል። ኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በትዊተረ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍም በዛሩው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መቀበቻለውን እና እየተወያዩ መሆኑን አስታውቀዋል። [Alain] @shegernewsBot @shegernewsETH
Show all...
#Breaking News ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለማምራት መስማማቱን ክለቡ በይፋ አሳወቀ! ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ፖርቹጋላዊው የ ባሎን ዶር አሸናፊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ልጅነት ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ መመለሱ እውን ሆኗል።
Show all...
አሽራፍ ጋኒ ሀገር ለቀው ሲወጡ የያዙት ብር መጠን ከተሳፈሩበት ሂሊኮፕተር በላይ በመሆኑ የተወሰነ ገንዘብ ኤየር ፖርት ውስጥ ጥለው ለመሄድ ተገደዋል:: ትናንት ታሊባንን ሸሽተው ሀገር ለቀው የሄዱት የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት በአራት መኪና ብር አጭቀው ቢወጡም የተሳፈሩበት ሂሊኮፕተር የያዙትን ብር ባለመቻሉ የተወሰነ ብር ኤየር ፖርት ትተው ሄደዋል ሲል በካቡል የሚገኘው የራሺያ ኢምባሲ ዛሬ ገልፇል። የብሩን መጠን ግን ኢምባሲው አልገለፀም። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
#PMDrAbiyAhmed የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ቃል እንደገባነው እጅን አፍ ላይ የሚያስጭን ገድል መፈፀማችንን የምናበስርበት ጊዜ ቅርብ ነው" አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ "ጠላት ወደወጥመዳችን እየገባ ነው" ያሉ ሲሆን የማሸነፍ አቅማችም ተጠናክሮ እየወጣ ነው ሲሉ አሳውቀዋል፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥም እጅን በአፍ የሚያስጭን ገድል መፈፀማችንን እናበስራለን ብለዋል። የያዝነው የኢትዮጵያን አምላክ ነው ያሉት ጠ/ ሚኒስትሩ የምንታገለው ለኢትዮጵያ ነው ፤ የሚዋጋው የኢትዮጵያ ጦር ነው ፤ በመጨረሻም ታሪክ እንደሚነግረን አሸናፊዋ ኢትዮጵያ ናት ሲሉ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠ/ሚኒስትሩ ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ፦ - በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን የሚዲያ ዘመቻ እና የዴፕሎማሲ ጫና ለመመከት እንዲረባረብ፤ - የውሸት ዜናዎችን እየተከታተለ እንዲያመክን፤ - ህወሓት በሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ሳይደናበር፤ የሴራ ትንታኔ ውስጥ የገቡ ከሴራ ትንታኔ በመውጣት ህወሓት ጦርነት የከፈተበትን የዴፕሎማሲና የጦር ግንባር እንዲቀላቀሉ፤ - ሁሉም ለሀገሩ አምባሳደር ሆኖ ለሀገሩ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
መንግሥት በአገሪቱ የሚገኙ ቅዱሳ ቦታዎች እና ተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ይህን ያለው ለቅዱሳን ቦታዎች እና ተቋማት የሚደረግ ጥበቃን በተመለከተ የፕሬስ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው። የውጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው በቅርቡ በተወሰኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች አሸባሪው የህወሃት ቡድን በከፈተው ጥቃት የኢትዮጵያ ህዝብ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገለጫ በሆኑ እድሜ ጠገብ ቅርሶች ላይ የደህንነት ስጋት ደቅኗል ብሏል፡፡ ስጋቱ ቡድኑ ባለፉት ስምንት ወራት ከፈጸመው መሰል ዝርፊያና ዉድመት ተግባሩ የሚመነጭ ነዉ ያለው። የሽብር ቡድኑ በአዋሳኝ ክልሎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የእርዳታ አቅርቦትን በማስተጓጎል ሚሊዮኖችን አደጋ ላይ ጥሏል። አሸባሪው ህወሓት ቡድን መንግሥት እርዳታ ተደራሸ እንዲሆንና አርሶ አደሩ የዝናብ ወቅቱ ን በመጠቀም የግብርና ስራዉን እንዲያከናዉን በማሰብ የወሰደዉ የተናጠል የተኩስ አቁም ዉሳኔን ወደ ጎን በመተው እንዲሁም በአለም አቀፉ ማህበረሰብ የቀረበለትን የተኩስ አቁም ጥሪ ቸል በማለት ትንኮሳውን ቀጥሏል። በመሆኑም በአገሪቱ የሚገኙ ቅዱሳ ቦታዎች እና ተቋማትን ደህንነት ለመጠበቅ መንግሥት አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም የአሸባሪውን ቡድን የጥፋት ድርጊት እንዲያወግዝ መንግስት ጥሪ ያቀርባል። Via #AMN @shegernewsBot @shegernewsETH
Show all...
የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት ጋር ድርድር እንደማያደርግ ገለጸ የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ጋር ድርድር እንደማያደርግ የአገሪቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ዛዲግ አብረሃ ለቢቢሲ ተናገሩ። በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኘውን አብዛኛውን የትግራይ ክልል ከተቆጣጡሩት ከህወሓት አማጽያን ጋር ለወራት በዘለቀ ጦርነት ውስጥ የቆየው የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ካለው ቡድን ጋር እንደማይደራደር አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ከአማጺው ኃይል አመራሮች አንዱ የሆኑት ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቶ የተኩስ አቁሙ እንዲደረግና ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ ውይይት ተደርጎ የሽግግር ሂደት መጀመር አለበት ማለታቸው ይታወሳል። በዚህ ላይ ለቢቢሲ ምላሽ የሰጡት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብረሃ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ለድርድር እንደማይቀመጥ ገልጸዋል። አሁን በሰሜኑ የአገሪቱ አካባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከትም መንግሥት በተናጠል ተኩስ አቁም ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው "አሁን በህወሓት በኩል የሚታየው ነገር ራስን አጋኖ ከማየት የመነጨ ነው" ብለዋል። ነገር ግን መንግሥት ትዕግስቱ ሲሟጠጥ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ "አቅማችንን ማየት ከፈለጋችሁ የተወሰኑ ሳምንታት መጠበቅ ይኖርባችኋል። ትዕግስታችን የተሟጠጠ ዕለት እንዴት ከእያንዳንዱ ከተማና መንደር ጠራርገን እንደምናስወጣቸው ታያላችሁ። ጦርነት ከሆነ ፍላጎታቸው....ያገኙታል" ሲሉ ተናግረዋል
Show all...
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቶኪዮ ኦሎምፒክ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ በተገኘው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስፈሩት ጽሑፍ እንዳሉት በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር ሩጫ አትሌት ሰለሞን ባረጋ በውድድሩ 1ኛ ሆኖ በአሸናፊነት ማጠናቀቁን ተከትሎ ለእናት ሀገሩ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማስገኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን። "በቀጣይ ውድድሮች የሀገራችን ሰንደቅ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ብርቱ ጥረት ለሚያደርጉ ተወዳዳሪዎች መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው እመኛለሁ" ብለዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ቴዲ አፍሮ የክብር ዶክትሬት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ዛሬ ባካሄደው የሴኔት ስብሰባ አፀደቀ፡፡ በዚህም ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በተማሪዎች ምረቃ ዕለት ተገኝቶ የክብር ዶክትሬቱን እንደሚቀበል ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
አራት ሰዎችን አሳፍሮ ከድሬድዋ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ የነበረ ET-AMI መለስተኛ አውሮፕላን በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ዛሬ ወደቀ በፕሌኑ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በህይወት መትረፋቸውም ታውቋል፡፡ አውሮፕላኑ ዛሬ ሐምሌ 20/2013 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 አካባቢ በኮምቦልቻ ወረዳ ቄረንሳ ጋረአሮ በተባለ ቦታ መውደቁን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ ተናግረዋል፡፡ ከተሳፋሪዎች መካከል በአንደኛው ተጓዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ ወደ ድሬደዋ ለህክምና መላኩንም ገልጸዋል፡፡ ሌሎች ተጓዦች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን በስፍራው ተገኝተው እንደተመለከቷቸው የገለጹት ኃላፊው በአካባቢው ያለው የአየር ሁኔታ ጭጋጋማ እንደነበረም ተናግረዋል፡፡ ©የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ @shegernewsBot @shegernewsETH
Show all...
የሲዳማ ክልል ሁለተኛ ዙር የልዩ ሀይል አባላትን ለአገራዊ ጥሪ ለመላክ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ ልዩ ሀይሉ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑንና አገራዊ ጥሪን በመቀበለም ለአገር እድገት ነቀርሳ የሆነውን የህወሐት አጥፊ ቡድን ለማስወገድ ቆርጠው ተነስተዋል ነው ያለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፡፡ ህውሐት በፊትም ለህዝብ መለወጥና አንድነት ደንታ የሌለዉ ቡድን በመሆኑ የህዝቦችን አነድነት ለማረጋገጥና ቡድኑን እንዲወገድ ልዩ ሀይሉ የሚተጋ መሆኑን ነዉ ኮሚሺኑ የገለጸው፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና የገጽታ ግንባታ ዳሬክተር ኮማንደር መስፍን ዴቢሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ልዩ ሀይሉ የአገራዊ ጥሪዉን በመቀበል በወኔ እየተንቀሳቀሰ ነዉ፡፡ ጥሪዉን በማክበር ለአገሪቷ አንድነት የሚሰሩት የልዩ ሀይል አባላቱ ዛሬ 10፡00 ላይ በሀዋሳ ሽኝት እንደሚደረግላቸውም ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ ተናግረዋል፡፡ Via FBC @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ዐቃቤ ሕግ በእነ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መዝገብ በ62 ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ፡፡ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውሳኔ በመስጠት ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው የህውሀት መዓከላዊ ኮሚቴ አባላትና የክልል መንግስቱ ካቢኔ አባላት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በትጥቅ ጥቃት ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢፈርት ድርጅቶች፣ የግልና የመንግስት ድርጅት አመራሮች፣ የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አመራር አባላት፣ በትግራይ በተካሄደው ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ምርጫ ላይ ተሳትፎ ያደረጉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሊቃነ-መናብርትና የቀድሞ የህውሀት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ታዋቂ ግለሰቦች ላይ ነው የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተው፡፡ ክሱ የተመሰረተው በሁለት የወንጀል አንቀጽ ስር ሲሆን÷ የመጀመሪያው በሀይል፣ በዛቻ በአድማና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ኢ-ሕገመንግስታዊ ምርጫ በማካሄድ በሕገ-መንግስት የተቋቋመና እውቅና ያለው የክልል መንግስት መለወጥ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ሲሆን በሁለተኛ ክስ የፌዴራሉን መንግስት በሀይል ለመለወጥ በማሰብ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል መንግስትን በመሳሪያ ጥቃት መለወጥ የሚችል የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ የተባለ የጦር ሀይል በማደራጀት የፌዴራል መንግስት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት በማድረስ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1176/2011 አንቀጽ 3/1እና 3/2 በመተላለፍ ወንጀል ነው፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለክሱ አስረጅነት 510 የሰው ምስክሮችን እና እና 5329 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎችን በማያያዝ ለፍርድ ቤቱ መቅረቡን ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ህወሀት ልጆቹን ወደ ትግል ላልላከ ቤተሰብ እርዳታ እንዳይሰጥ መወሰኑ ተሰማ! "ማንኛውም የትግራይ አባት ልጆቹን ወደ ትግል ካላከ በስተቀር እርዳታ እንዳይሰጠው የሚል መመሪያ የህወሀት አፈቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ለካድሬዎቹ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተጨባጭ መረጃ እንደደረሰው መንግስት አስታወቀ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሃትን አሸባሪ ብድን ብሎ መሰየሙ ይታወቃል፡፡ መንግስት ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ህወህት እርዳታን እንደመያዣ እየተጠቀመ መሆኑን ገልጿል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ለኩላሊት ድክመት የሚዳርጉ ስድስት አደገኛ ልማዶች የኩላሊት ድክመት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣና አደገኛ በሽታ ነው። በ2017 ብቻ 697.5 ሚሊዮን ሰዎች በዚህ በሽታ የተጠቁ ሲሆን 1.2 ሚሊዮን ሰዎች በዚሁ ዓመት ውስጥ ብቻ በኩላሊት ድክመት የተነሳ ህይወታቸው አልፏል።የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ዋነኛ መንሴዎች ሲሆኑ ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ለዚህ በሽታ ያጋልጣል። አደገኛ የሆኑና ለኩላሊት ድክመት ሊዳርጉ የሚችሉ ልማዶችን እነሆ። 1.ጨው ማብዛት ፦ ጨው በሰውነታችን ውስጥ ውሃ እንዲቆይ በማድረግ የደም ግፊታችን እንዲጨምር ያደርጋል ። የደም ግፊት ደሞ የኩላሊት ድክመት በማምጣት 2ኛውን ደረጃ ይይዛል።ይህ ደሞ ወደ ዳያሊሲስ(የኩላሊት እጥበት ) ወይም ወደ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ያመራል። ጨው በመቀነስ የኩላሊት ጤናን መጠበቅ ይቻላል። 2.የሰውነት ፈሳሽ(ውሃ ማነስ)፦ በሰውነት ውስጥ ያለው የፈሳሽ መጠን አነስተኛ ሲሆን ኩላሊት ላይ ጉዳት ያደርሳል። ይህም ፕሪ ሬናል አዞቴሚያ በመባል ሲታወቅ አ(acute kidney injury ) ያስከትላል። ይህንንም ለመከላከል በቀን ከ2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። ነገር ግን የልብ ድካም ፣የሳንባ ችግር ካለቦት ምን ያህል ውሃ መውሰድ እዳለቦት ከሐኪሞ ጋር ይወያዩ። እነዚህ በሽታዎች ያሉበት ሰው ከጤነኛ ሰው ያነሰ ውሃ ይወስዳል።ሌላው ሻይ ፣ ቡና፣ ለስላሳ መጠጥና ቢራ ውሃን አይተኩም። 3.ማስታገሻ ማብዛት ፦ነን ስቴሮይዳል አንቲ ኢንፍላማቶሪ ድረግስ(Non steroidal anti-inflammatory drugs) የተባሉት የመስታገሻ ዝርያዎች በብዛት ከምንጠቀምባቸው መድኃኒቶች ውስጥ ናቸው። እነዚህ መድኃኒቶች ለአብዛኛው ሰው ለአጭር ጊዜ ቢወሰዱ ችግር የማይፈጥሩ ቢሆኑም አብዝቶ በተደጋጋሚ መውሰድ ግን ለኩላሊት ችግር ይዳርጋል። በተለይ የደም ግፊት ና ስኳር ባለባቸው ሰዎች ላይ እነዚህ መድኃኒቶች በብዛት ለረጅም ጊዜ መወሰድ የለባቸውም። በሀገራችን በብዛት የሚገኙት የዚህ ዝርያ መድኋኒቶች፦ ዳይክሎፌናክ፣አይቡፕሮፌ፣ሜሎክሲካም፣ ሪሊፍ የመሳሰሉት ይገኙበታል። የጀርባ ህመም ፣ሪህ፣ቁርጥማት ያለባቸው ስዎች ለነዚህ መድሀኒቶች የተጋለጡ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ውሃ በብዛት መውሰድና ያለሐኪ ትዛዝ ተጨማሪ ማስታገሻ አለመውሰድ ይኖርባቸዋል። 4.አልኮል ማብዛት ፦አልኮል በብዛት መጠጣት ወደ ግፊት ያመራል። ግፊት ከላይ እንደጠቀስኩት ወደ ኩላሊት ድክመት ያመራል። በተጨማሪም አልኮል በብዛት መጠጣት ቶሎቶሎ ስለሚያሸና በሰውነት ውስጥ ያለው ፈሳሽ እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህም ኩላሊት ይጎዳል። 5.ሲጋራ ማጨስ ፦ በርግጥ ሲጋራ በጣም ለበርካታ በሽታዎች አጋላጭ መሆኑ ይታወቃል። ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ፍሰት በመቀነስ በኩላሊትም ጉዳት ያደርሳል። በተጨማሪም ለኩላሊት ካንሰር ያጋልጣል። ሲጋራ ማጨስ አደገኛና ለኩላሊት ድክመት የሚያጋልጥ ልማድ ነው። 6.አደገኛ እፆች፦እንደ ኮኬይን ፣ ሄሮይንና ኤክስታሲ የቸሰኙ እፆች ኩላሊትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለድክመት ሊዳርጉ ይችላሉ። ኮኬይን በተጨማሪም ለደም ግፊት ይዳርጋል። ዶ/ር ሸምስ(ስፔሻሊስት ሐኪም) @shegernewsETH
Show all...
እንኳን አደረሳችሁ ! ለመላው እስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ @shegernewsETH
Show all...
ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ላይ ÷ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል ብለዋል። 🗣ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ @shegernewsETH
Show all...
ሼይኽ መሐመድ አል አሙዲ 106 በሬዎችን እና 100በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አደረጉ ኢትዮጵያዊው ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ለመጪው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በወሎ በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ላይ ላሉ እና በአዲስ አበባ ከተማም ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የሚከፋፈል 106 በሬዎችን እና 100 በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አድርገዋል:: ሼይኽ መሀመድ አል አሙዲ ለኡዲሂያ እንዲሆን በማሰብ ድጋፍ ያደረጓቸው በሬዎች ፣በጎች እና ፍየሎች በወሎ በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችም በተለያዩ መስጂዶች እና ተቋማት በኩል እንዲከፋፈል ተደርጓል:: 🗣ustaz abubker ahmed @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ለኢትዮጵያ እና ለሱዳን ጥሪ አቀረቡ የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ለጋራ ሰላም ጥሪ አቀረቡ። ጥሪያቸውን ያቀረቡት ለግብፃውያን፣ ለኢትዮጵያውያን እና ለሱዳኖች ነው። ህጋዊ ድርድር በሰላም አብሮ ለመኖር እና ለመብልጸግ ያስፈልጋል ያሉት አለሲሲ፣ በኢትዮጵያ በኩል ከቀረበው ሀሳብ ጎን መቆም አለብን ብለዋል። እንደ ኢጅብት ቱደይ ሜጋዚን ዘገባ የህዳሴው ግድብ ልማት እንጂ ሌላ አላማ የለውም ብለዋል:: ለሌሎች መንገር የምንፈልገው ስጋት ቢኖረንም፣ያን ያህል አሳሳቢ አይደለም ሲሉ ገልፅዋል ሲል ፋናቢሲ ዘግቧል:: @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፤ የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የኦሮሚያ ክልል ሕዝብና መንግስት ኢትዮጵያን በመገንባት ዉስጥ የሚመጥነዉን አስተዋፅኦ ሲያበረክት ቆይቷል። የሀገርና የህዝብ ሉአላዊነትና ነፃነትን ለማስከበር በሚከፈለዉ መስዋዕትነት ላይ እራሱን ቆጥቦ አያውቅም። በዉጪ ወረራና በታሪክ አጋጣሚ የባንዳነትን ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩት ኃይሎች ላይ በየ ታሪክ ምዕራፉ እራሱን ሰጥቶ ኢትዮጵያን የገጠሙዋትን ችግሮች ለማክሸፍ መስዋዕትነትን ከፍሏል። እንደ ሐገር ስናስመዘግብ በቆየናቸው ድሎች ዉስጥ ተወራራሽ ታሪክ አስመዝግቧል። ዛሬም እንደ ትናንቱ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ህዝብ በማቀናጀት በወንድሞቻችን አብሮነት በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን የውስጥና የውጪ ትንኮሳ ለማክሸፍ ዝግጁነቱን ይገልፃል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፌደራል መንግስቱ የወሰደውን የአንድ ወገን ተኩስ የማቆም እርምጃ ለሕዝብ ጥሩ የጥሞና ጊዜ የፈጠረ መሆኑን አምኖ ሲደግፍ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ከአፈጣጠሩ የተጣመመው ሕወሃት/ጁንታ ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ ለተደረገው ጥሪ ቦታ እንደሌለዉ በግልፅ አሳይቷል፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በአሮጌ የፖለቲካ እይታ ተሞልቶ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል፡፡ የሕወሃት የፖለቲካ ፅንሰ ሐሳብ ህዝብን እንደ ጠላት በመፈረጅ ላይ ያተኮረ ነው። የግጭት መነሻ የአንድነት ፀርና ለሐገራዊ ብሔርተኝነት መውደቅ ምክንያት ሆኗል። የጁንታው ፀረ አንድነት ፈንጂ በየቀኑ እየፈነዳ ለዜጎች ሞትና ስቃይ ምክንያት በመሆን ዓመታትን አስቆጥሯል። የድህነትና የኋላ ቀርነትን እሽክርክሪት ዘመን አራዝሞብናል። ለእድገታችንና የብልፅግና ጉዞ እንቅፋት በመሆን እንድንሸማቀቅ አርጎናል። በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ሀገርና ህዝብ በቀዳሚነት እየተጎዱ ነው። አሸባሪው ሕወሃት እታገልላቸዋለሁ ብሎ የሚናገረውና በስማቸው እየኖረ ያለውን የትግራዋይ ሕዝብን ጨምሮ አስቦላቸው ወይም ተቆርቁሮላቸው አያውቅም። ይህ ቡድን ትናንት የሐውዜን ህዝብ በሚገበያይበት ቦታ ላይ ቦምብ በማዝነብ የጅምላ ጭፍጨፋ ሲፈፅም ለፕሮፖጋንዳ ግብአትነት እንጂ ለሉአላዊነት ትግል አልነበረም። ሕዝብን በመጨፍጨፍ ህዝብን ነፃ ማውጣት በየትኛውም መስፈርት የሚታረቅ አስተሳሰብ አይደለም። ዛሬም ቢሆን በተባበሩት መንግስታት የወጣውን የሕፃናት መብት ድንጋጌ በመጣስ ጨቅላ ሕፃናትን ለጦርነት ከፊት አሰልፈው በመማገድ ላይ ይገኛል። አዛውንቶችን፡ እናቶችን እና የሐይማኖት አባቶችን እንደ ጋሻ ከፊት በማሰለፍ በእልቂታቸው የጀግንነት አክሊል ለመድፋት ይሞክራል። አሁንም ቢሆን አሸባሪው ሕወሃት የፌደራል መንግስት ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ካሳየው ፍላጎት በተቃራኒ በመሔድ ላይ ይገኛል። በፌደራል መንግስት የታወጀው የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት አርሶ አደሩ በክረምት ወቅት ተረጋግቶ እንዲያርስ፤ ለዜጎች እርዳታ እንዲደርስና ግጭት እንዳይባባስ ቢሆንም ጁንታው የተፈጠረበትን የጥፋት ስሜትና እጅ መቆጣጠር አልቻለም። የ1967ቱ ሕወሃት ማኒፌስቶ ህዝብና ህዝብን በማጋጨት ሰላምና መረጋጋትን ለመንፈግ የተወጠነ ነበር። ለኢትዮጵያ ግንባታ ቋሚና ማገር በመሆን ለዛሬ ያደረሳትን ህዝብ ለመበታተን ያለመ ነው። አሸባሪው ሕወሃት ላለፉት 27 ዓመታት ሀገር ሲመራ በነበረበት ወቅት በህዝብ ውስጥ ትቶት ያለፈው ሰቆቃ ሳያንስ ዛሬም በሐገር ላይ የጭካኔ ተግባራትን እየፈፀመ ነው። ሕወሓት/ጁንታ በማይካድራ የፈፀመው የዘር ማጥፋት ተግባር በብሄር ላይ ያተኮረ የህዝብ ጠላትነት ላይ የተመሰረተ እኩይ ተግባር ነው። አሁንም በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈፀም ሲቅበዘበዝ ይታያል። የጁንታ ኃይል የሕዝብና የሐገር ጥቅምን አሳልፎ ከመስጠት አይመለስም። እድገታችንንና ልማታችንን ለመግታት ከሚታገሉ የውስጥና ውጪ ጠላቶች ጋር በማበር የጥፋትና የማፍረስ ሴራዎችን በዋና ተዋናይነት ሲፈፅም እንደነበረ በገሀድ ታይቷል። አሸባሪው ሕወሃት ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከማስተጓጎል ጀምሮ ከነአካቴው እስከ ማደናቀፍ ድረስ የተላላኪነት እና የባንዳነት ትወና ድርሻውን ተወጥቷል። የአሸባሪው ሕወሃት ክህደት በህዝብ ንቀት ብቻ የተገታ አልነበረም፤ የሐገር ሉዓላዊነትን ጭምር ጥያቄ ውስጥ እስኪገባ አስነዋሪ ተግባር ፈፅሟል። ኢትዮጵያ ብትፈርስም፣ በውጪ ወራሪ ብትወረርም ደንታ እንደሌለው እስከ መግለፅ ደርሷል። ስለሆነም ጁንታ ለአንዱ የሚያስብ፣ ሌላውን የሚነፍግ ሳይሆን በጅምላ የመጨፍጨፍ እና የማፈራረስ አቅጣጫን ይከተላል። ከእሱ ተወልዶ፤ ከእጁ በልቶ ላደገዉ ህዝብ የማይራራ፡ ሌላ ዘመድ ሊኖረውም ሆነ ሊያፈቅር አይችልም። “ጅግራ ዘመድ መስሎ ወፊቱን በላት” እንደሚባለው ሁሉ፤ ለአንዱ አዝኖ፤ ሌላውን አኩርፎ ሌሎችን ደግሞ የተፀየፈ መስሎ የሚቀርበውን ፕሮፖጋንዳ አምኖ መቀበል ሞኝነት ነው። የአሸባሪው ሕወሃት ኃይል ተሸንፏል፤ በፖለቲካ ሜዳው አሸናፊ ሀሳብ ማቅረብ ተስኖት ለቆ ስደትን መርጧል። በማግስቱ የጦርነት ነጋሪትን መጎሰም ጀመረ። ውሎ ሳያድር በዜጎቻ ላብ የተገዛውን የሀገር ሉዓላዊነት የሚጠበቅበት መሳርያ በመዝረፍ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ዛተ። በከሀዲዎችና የውጪ ኃይሎች ማበረታቻ የሰከረው ሕወሓት በመከላከያ ሰራዊቱ ለይ የጥቃት እርምጃ ወሰደ። ከትግራይ ሕዝብ ጋር ከ20 ዓመታት በላይ የኖረውን የመከላከያ ሠራዊት በከባድ የጭነት መኪናዎች ከመጨፍለቅ ጀምሮ እጅግ አስነዋሪ እርምጃዎችን ወስዷል። የክልልና የሀገራችን ህዝብ በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ ሁሉ አቀፍ ድርሻውን ተወጥቷል። ዛሬም ቢሆን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ሕዝብ የሀገር ሉዓላዊነት ጋሻ ከሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመሆን ማናቸዉንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው። መንግስትም የህዝብ ተሳትፎን በማቀናጀት ሁለንተናዊ ስኬት ለማስመዝገብ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። ትናንት በችግር ውስጥ የመንግስትን ጥሪን በመስማት ሁለንተናዊ ድርሻችሁን የተወጣችሁና የአሸባሪዎች የጥፋት መርዝ እንዲደፋ ያደረጋችሁ የክልላችን የህብረተሰብ ክፍሎች ዛሬም እንደ ትናንቱ የጎላ ተሳትፎአችሁን እንድታበረክቱ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል። በሕዝባችን የተባበረ ክንድ ዘላቂ ሉዓላዊነታችን ይረጋገጣል!! የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሐምሌ 2013 @shegernewsETH @Shegernewsbot
Show all...
"የመከላከያ ሠራዊት በየት ቦታ እና መቼ ማጥቃት እንዳለበት ወስኖ እየሰራ ነው" #ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ህዝቡ መረዳት ያለበት ወታደራዊ ስራ በወታደሮች እንጂ በአክቲቪስቶች የሚከናወን አይደለም፤ ሠራዊቱ ደግሞ በየት ቦታ፣ መቼ ማጥቃት እንዳለበት ወስኖ እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነቱን አሸባሪው ኃይል ለመቀበል ባህሪው አይፈቅድለትም ያሉት ሌተናል ጀነራል ባጫ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበል ያልቻለው ጁንታው ከትግራይ ህዝብ የሚቀርብለትን የሰላም ጥያቄ ለመመለስ ስለማይችል እና ከህዝብ የሚነጥለው ጉዳይ ስለሆነም ጭምር ነው ብለዋል። የሚደረገው ጦርነት ኢትዮጵያን እንደሀገር የማስቀጠልን ጉዳይ ለማረጋገጥ እና ጁንታው የያዘውን ሀገር የመበታተን እቅድ እንደማይሳካ እና እንደማይቻል ለማሳየት ነው ብለዋል። ሠራዊቱ እየተዋጋ ያለው ለኢትዮጵያ ድንበር ነው፤ ድንበሩ ደግሞ መረብ ነው ያሉት ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ ሠራዊቱ የተቀመጠበትን ቦታ እና የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማንም ግልፅ አለመደረጉንም ገልፀዋል። መከላከያ ሠራዊቱ የአገሪቱን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን የገለፁት ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዲቆም እና ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የሲሚንቶ ግብይትን ለመቆጣጠር የወጣው መመሪያ መነሳቱ ተሰማ፡፡ ከዛሬ ጀምሮም ሲሚንቶ እንደቀድሞው ወደ ነፃ ግብይት እንዲመለስ መወሰኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ መመሪያው የተነሳው ላልተወሰነ ጊዜ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግሯል፡፡ የሲሚንቶ ዋጋን ተመን በማውጣት በተወሰኑ አከፋፋዮች በኩል ብቻ ሽያጩ እንዲከወን መመሪያ ወጥቶ ሲሰራበት መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ቁጥጥሩ ይበልጥ የሲሚንቶ ምርት እንዲጠፋ አድርጓል ፤ የእጅ መንሻ ፈላጊዎችንም ቁጥር አብዝቷል ሲሉ የስራ ተቋራጮች ያሰሙትን ቅሬታ ሸገር መዘገቡም አይዘነጋም፡፡ አሁን ወቅቱ ክረምት በመሆኑ የግንባታ ስራ ሰለሚቀዛቀዝና የሲሚንቶ ፍላጎትም ስለሚቀንስ እንዲሁም ከፋብሪካዎች ጋር ችግሩን ለመፍታት ስምምነት ላይ በመድረሱ የቁጥጥር መመሪያው ተነስቷል ተብሏል፡፡ የሲሚንቶ ምርት እጥረትን ለማሻሻልና ፋብሪካዎች በአቅማቸው ልክ እንዲያመርቱ ለማስቻል መንግስት 85 ሚሊዮን ዶላር መድቦ የመለዋወጫ ችግሮቻቸው ለመፍታት እየሰራሁ ነው ማለቱም ይታወሳል፡፡ ትግስት ዘሪሁን @shegernewsETH
Show all...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጡት መግለጫ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የተከበራችሁ ተመላሽ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች መስመራዊ መኮንኖች ባለሌላ ማዕረግተኞች፤ አሁን ያጋጠመን የህልውና አደጋ ለመመከት በምደርገው ትግል ከፀጥታ መዋቅራችን ጎን በመሰለፍ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪየን አስተላልፋለሁ የአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘደንት አቶ አገኘሁ ተሻገር @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በ2014 በጀት ዓመት ለካፒታል እና መደበኛ ስራዎች፤ የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል እና የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማስቻል በአጠቃላይ 70 ቢሊየን 670 ሚሊየን 216 ሺህ 28 ብር በጀት በመወሰን ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መርቷል፡፡ የ2014 በጀት ድልድል በ2013 በጀት ዓመት ከተያዘው በጀት ጋር ሲነጻጸር በ9 ቢሊየን 319 ሚሊየን 594 ሺህ613 ብር ወይም የ15 ነጥብ 19 በመቶ ዕድገት አለው ተብሏል፡፡ ከተማ አስተዳዳሩ የቀጣይ 10 ዓመት እና 5 ዓመት መሪ ዕቅድን የተመለከቱ የትኩረት አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂክ ግቦችን መሰረት ባደረገ መልኩ በ2014 በጀት ዓመት ለኮንስትራክሽን ዘርፍ፤ ለውሃና ፍሳሽ ዘርፍ፤ ለመንገድ ልማት ዘርፍ፤ ለትምህርትና ስልጠና ዘርፍ፤ ለትራንስፖርት ዘርፍ፤ የአረንጓዴ ልማት ዘርፍ፤ ጤና ዘርፍ እና ለቤቶች ልማት ዘርፎች ከፍተኛ በጀት እንደተመደበላቸው ተገልጿል። በከተማ ደረጃ ለሚገኙ የማዕከል መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው 46 ቢሊየን 559 ሚሊየን 320 ሺህ 315ብር የተመደበ ሲሆን ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 65 ነጥብ 88 በመቶ ድርሻ አለው ተብሏል፡፡ ለማዕከል መስሪያ ቤቶች ከተመደበው በጀት ውስጥ ለመደበኛ ብር 16 ቢሊየን 248 ሚሊየን 362 ሺህ 343 ነጥብ 73 እና ለካፒታል ብር 30 ቢሊየን 310 ሚሊየን 957 ሺህ 972 ብር መደልደሉ ተመላክቷል። ለክፍለ ከተሞች የተመደበ በጀት ደግሞ 24 ቢሊየን 110 ሚሊየን 895 ሺህ 712 ብር ከአጠቃላይ በጀት 34 ነጥብ 12 % እንዳለው ተገልጿል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡@shegernewsETH
Show all...
በሩቅ ሆኖ ስህተት በመፈለግና እርስ በእርስ በመነቋቆር ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቀን የምንታደገው አንዳችም ህልውና የለንም፡፡ በቂ መረጃ ባገኘንበትም ባላገኘንበትም ጉዳይ ላይ ተሳፍረን በተለያዩ አቅጣጫዎች መክነፍ ለጠላቶቻችን ተጨማሪ ጉልበት ከመሆን ባለፈ ለህዝባችን የሚሰጠው ጥቅም የለም፡፡ ስለሆነም የጋራ ዕጣ ፋንታችንን በጋራ ጥረት የምናስከብርበትና አደጋ የተጋረጠበትን የህዝባችንን ህልውና ከጠላት ጥቃት የምንታደግበት የታሪክ መድረክ ላይ ስለምንገኝ ከመቸውም ጊዜ በላይ ልዩነታችንን ወደጎን በመተው የህዝባችንን አንድነት ጠብቀን በጋራ እንድንረባረብ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡  6ኛ. መላው የክልላችን ህዝብ፣ በከተማና በገጠር የምትኖሩ የክልላችን ነዋሪዎች፣ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ የምትገኙ ምሁራንና የክልላችን ተወላጆች፣ በተለያየ ሙያ ተሰማርታችሁ አገርና ህዝብ በማገልገል ላይ የምትገኙ የክልላችን ነዋሪዎችና ባለሀብቶች የጀመርነውን የህልውና ትግል በማገዝ የትግል ሂደት አዎንታዊ ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡  በመጨረሻም የጀመርነው ትግል እልህ አስጨራሽ በጣም መራርና ረዥም ጊዜ የሚጠይቅ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ የእኛ አንድ መሆንና ለጋራ ግብ በጋራ መተባበር በመድረኩ አሸናፊ ሆነን እንደምንወጣ ያለምንም ጥርጥር ልናረጋግጥልችሁ እንወዳለን፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የአማራ ክልል ህዝብ ትግል ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የጋራ ተጠቃሚነት ውጭ እንደማይሳካ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ የምናደርገው ትግል  ለአገራችን ሉአላዊነት መከበርና የጭቁን ህዝባችን የህልውና ትግል እንጂ እላፊ ጥቅም ለማግኘት የምናደርው ትግል በፍጹም አይደለም፡፡  የአማራ ህዝብ ከፉክክር ይልቅ ትብብርን ከእብሪት ይልቅ ድርድርን የሚያስቀድም በፍትህ ከሄደች በቅሎየ ያለፍትህ ያጣኋት ጭብጦየ ትቆረቁረኛለች ብሎ የሚያምን ህዝብ ነው፡፡ ስለሆነም ዛሬ የምናደርገው ትግል ለልጅ ልጆቻችን የምናወርሰው የኩራትና የክብር ምንጭ እንደሚሆን አንጠራጠርም፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐፕሊክ መንግስት የወሰደው ተናጠላዊ የተኩስ አቁም ውሳኔን ተከትሎ የጠላት ኃይል አገርና ህዝብ ለማዋረድ የሚያደርገውን እብሪተኛ እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ በአጽንኦት እናሳስባለን፡፡ ትግላችን ለህልውናችን ©የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...