cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሸገር NEWS

የሚያምኑት መረጃ!! እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ አሁኑኑ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ #ሸገር የናንተ #ሸገር የኛ

Show more
Advertising posts
24 317Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ጤናመረጃ ለስላሳ መጠጥ አዘዉትሮ እና በመደበኛነት መጠጣት የሚያስከትለው ጉዳት!! ይህ እውነታ ሊያስደነግጥህ ይችላል። ለስላሳ መጠጥ ያለማቋረጥ እና በመደበኛነት መጠጣት የኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ይህ የሚከሰተው በአሲድ እና በማዕድን ራዲካል ሚዛን ምክንያት ነው። ለስላሳ መጠጦች ለውፍረት መንስኤ ከሚሆኑት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ እንደሆነ በሙከራ ተረጋግጧል። ለስላሳ መጠጥ አዘውትሮ መጠጣት ለአጥንት መዳከም እና ኦስቲዮፖሮሲስን እንደሚያመጣ ተረጋግጧል። ለጥርስ መበስበስ ያጋልጣሉ። ለስላሳ መጠጦች አሲዳማ ይዘት ያለው የጥርስ መስተዋት በማሟት ደካማ ያደርጋቸዋል። ለስላሳ መጠጦች ጠንካራ የካፌይን ይዘት አላቸው። ካፌይን ብስጭት፣ እረፍት ማጣት፣ ውጥረት፣የደም ግፊት፣ከመጠን በላይ ሽንት እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላል። ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር|share በማድረግ ይተባበሩ! "በዶ/ር ሀይለልኡል መኮንን የቀረበ" @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2014 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም፣ የጤናና የስኬት ይሁንልን። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ፕሬዝደንት ባይደን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ አሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በራሳቸውና በባለቤታቸው ስም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን እንዲሁም ከእነዚሁ አገራት የዘር ሐረጋቸው ለሚመዘዝ በመቶሺህዎች ለሚቆጠሩ አሜሪካውያን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። በዚሁ መልዕክታቸው ላይ ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች ሪፖርቶች በእጅጉ እንዳሳሳባቸው ገልጸው፤ አስተዳደራቸው በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከአጋሮቻችን ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ሰላምን ማምጣት ቀላል እንዳልሆነ ነገር ግን በውይይት ሊጀመር እንደሚችል በመግለጽ “ታላቋና ባለብዝሃነቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የገጠማትን መከፋፈል እንደምትወጣውና በድርድር ላይ በተመሰረተ የተኩስ አቁም በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንደምትፈታው እንምናለን” ብለዋል። በመልዕክታቸው ላይ በአማርኛ “መልካም አዲስ ዓመት” በማለት በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ የተመኙት ፕሬዝዳንት ባይደን “አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በዓለም ዙሪያ ላሉ ቤተሰቦችና ማኅበረሰቦች ሰላም፣ እርቅ እና ፈውስ የሚመጣበት እንዲሆን እጸልያሉ” ብለዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሰልጣኝ ወታደሮችን እያስመረቀ ይገኛል። የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምረቃውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት እያካሄደ ነው። የሁርሶ ወታደራዊ ኮንቲንጀት ማሰልጠኛ ከሁለት ቀናት በፊት በተመሳሳይ መልኩ ማስመረቁን አስታውሶ ኢዜአ ዘግቧል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረ የጁንታው ቅጥረኛ ሃይል ተደመሰሰ! በዚህ ተልዕኮ የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ በሱዳን ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ 50 የሽብር መልዕክተኞችና የጁንታው ቅጥረኞች ሲደመሰሱ ከ70 በላይ የሚሆት ደግሞ ቆስለዋል፡፡ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ÷ ቅጥረኛው የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ የሞከረ ቢሆንም መቋቋም ተስኖት ተበታትኗል ብለዋል፡፡ ጠላት አሳቻ ሰዓት ጠብቆ አካባቢውን ለማተራመስ ቢንቀሳቀስም የጠላትን እንቅስቃሴ ከመነሻው በንቃት ሲከታተሉ የነበሩት የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍሎች ተቀናጅተው እርምጃ እንደወሰዱበት ነው የገለጹት። የጠላት ሃይል የቻለውን ያህል ለመከላከል ቢሞክርም በጀግናው ሰራዊት የበላይነት ተወስዶበት የተረፈው ሃይል አግሬ አውጪኝ ብሎ መፈርጠጡን ኮ/ል ሰይፈ ተናግረዋል፡፡ የጥፋት ሃይሉ ሲጠቀምባቸው እና ለእኩይ ስራው ሲያዘጋጃቸው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች ፣ ፈንጂዎች የወደሙ ሲሆን÷ የተቀሩት በጀግናው ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብተዋል ነው ያሉት፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በግንባር ድል አልቀና ሲለው አብዛኝው ጦር ወደ ሰሜኑ ክፍል አቅንቷል በሚል ከታሪካዊ ጠላቶች ተቀናጅቶ የህዳሴ ግድቡን ስራ ለማስተጓጎልና ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ነው የተናገሩት፡፡ በአሁኑ ስዓት በአካባቢው ጀግናው የመከላከያ ሃይል፣ እግረኛና ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች እንዲሁም የክልል ልዩ ሐይሎች አስፈላጊውን ዝግጁነት በማረጋገጥ ግዳጃቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ኮ/ል ሰይፈ መገለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በጎንደር ከተማ ህገ-ወጥ የነዋሪነት መታወቂያ ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች ተያዙ የመምሪያው የመረጃና ክትትል ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተገኘ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ መታወቂያዎቹ የተያዙት በማተሚያ ድርጅቱ ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ቁጥጥር ነው፡፡ መታወቂያዎቹ በሀሰተኛ ደብዳቤና ምንም አይነት የይታተምልን የትእዛዝ ደብዳቤ በሌለበት ሁኔታ ታትመው እጅ ከፍንጅ የተያዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ህገ-ወጥ መታወቂያዎቹ በላይ አርማጭሆ ወረዳ የአምበዞ ቀበሌ 200 እንዲሁም በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ስም 198 የተዘጋጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም በማእከላዊ ጎንደር ዞን መሃል አርማጭሆ ወረዳ ፈልፈል ቀበሌ ስም የተዘጋጁ 146 ህገ-ወጥ መታወቂያዎች በማተሚያ ቤቱ ታትተመው ለስርጭት በዝግጅት ላይ እንዳሉ መያዙን ገልፀዋል። ከህገ-ወጥ የመታወቂያ ህትመቱ ጋር በተያያዘም የማተሚያ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ አራት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በህግ-ቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለአሜሪካ ጥሪ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ አካባቢ በሆነው የአፍሪካ ቀንድና በአጠቃላይ አፍሪካ ውስጥ ለሚኖር ሰላምና እድገት አሜሪካ ኢትዮጵያን በመደገፍ አጋርነቷን ማሳየት እንደሚገባት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአሜሪካ ቅርንጫፍ ገለጸ። የጉባኤው አሜሪካ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ለአንዳንድ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ደብዳቤ አስገብቷል። በደብዳቤው አሁን በኢትዮጵያ የሚታየውን ችግር ለመረዳት ሀገሪቱ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የቆየችበትን የፖለቲካ ሂደት ማወቅ ያስፈልጋል ብሏል። በነዚህ ዓመታት በኢትዮጵያውያን መካከል ቅራኔና መለያየት እንዲፈጠር በተለያዩ መንገዶች መሠራቱን አመልክቷል። አሸባሪው ሕወሓት ይመራው በነበረው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የህዝብ ሀብት ዝርፊያ እንዲሁም በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ በጋዜጠኞችና በግለሰቦች ላይ መንግስታዊ የሽብር ወንጀል ሲፈጸም ነበር ብሏል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ከወር በኋላ መንግስት ይመሰረታል ተባለ ከወር በኋላ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ መንግስት እንደሚመሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ ስድስተኛው ዙር የመንግስት ምስረታ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ይካሄዳል ብሏል። ሰኔ 2014 የተካሄደውን 6ኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ ማሸነፉን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጹ ይታወሳል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀብት 1.1 ተሪሊዮን ደረሰ ለሃገር መከላክያ ሠራዊትና ለጸጥታ ኃይሎች 800 ሚሊዮን ብር ሰጠ የኢትዮያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሀብት ከ 1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡ የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቢ ሳኖ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣የባንኩ ሀብት ከ1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የ2013 በጀት ዓመት መጣናቀቂያ ድረስ መሆኑን ተናገረዋል፡፡ እንደ ፕሬዝደንቱ ገለፃ፣ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የጠቆሙት አቶ አቢ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልል የጸጥታ ኃይሎች ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች፣ ባንኩ 300 ሚሊዮ ብርና ሠራተኛው 500 ሚሊዮን ብር በድምሩ 800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ናቻው! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብዣ ወደ ሀገሪቱ ማቅናታቸው ታውቋል። ኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ በትዊተረ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍም በዛሩው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መቀበቻለውን እና እየተወያዩ መሆኑን አስታውቀዋል። [Alain] @shegernewsBot @shegernewsETH
Show all...