cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Parrot Tech Talk

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝ በዚህ ቻናል 🔹A-Z kali-Linux Hacking Tutorials 🔹አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን 🔹Amazon ላይ የሚሸጡትን መፅሀፍቶችን በነፃ ያገኛሉ ። 🔹የዘመኑ ቴክኖሎጂ ስለሆነው ሰው ሰራሽ ክህሎት(Artificial intelligence) መረጃ በሰፊው ያገኛሉ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
278Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ልታውቋቸው_እና_ልትጠነቀቁዋቸው_የሚገቡ_ነገሮች Malware ማለት ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ሲሆን ዓላማው ኮምፒውተር ላይ ያሉ ፋይሎችን መስረቅ፤ ማጥፋት፤ማስተካከል ወይም ሲስተሞች እንዳይሰሩ ወይም የሚሰሩትን ስራዎችን ማደናቀፍ ነው፡፡ Malware ማለት ኮምፒውተሮች ወይም ሲስተሞች የቀን ተቀን ስራዎቻቸውን መስራት እንዳይችሉ የሚያደናቅፉ ጎጂ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጎጂ ፕሮግራሞች እኛ በተለምዶ ቫይረስ እንላቸዋለን፡፡ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም Malware ሲባል አንድ ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን እንደ ፕሮግራሞቹ ዓላማ የተለያዩ ዓይነት ፕሮግራሞችን የያዘ ነው፡፡ ቫይረስ ከፕሮግራሞቹ መካከል አንዱ ነው፡፡ Malware ኪሚባሉት ፕሮግራሞች መካከል የተወሰኑትን ላንሳላችሁ፦ 1ኛ፡- #Virus፦ Virus ማለት የኮምፒውተር ፕሮግራም ሲሆን እራሱን ኮምፒውተራችን ላይ ባሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ለምሳሌ ሚዚቃዎች፤ቪዲዮዎች ላይ በማጣበቅ ኮምፒውተራችን ላይ ይቀመጣል፡፡ እራሱን ያባዛል፡፡ ኢንተርኔት ኔትዎርክ ሲያገኝ በኔትዎርኩ አማክኝነት ከኮምፒውተር ወደ ኮሚፐውተር ይሰራጫል፡፡ ቫይረስ የተላያዩ ጉዳቶችን ያደርሳል፡፡ ለምሳሌ፡- · የኮምውተራችን ቡት ሴክተር ስራ ያዘባል (Infects boot sector) · የኮምውተራችን ሲስተም ፕሮግራሞች ስራቸውን እንዳይሰሩ ያደናቅፋል (Infects system programs) · የምንጠቀማቸው የተለያዩ ፕሮግራሞችን ይበክላል( Infects ordinary programs) 2ኛ፡- #Worms፦ Worms ማለት ልክ እንደ Virus እራሱን በራሱ የሚያበዛ ፕሮግራም ነው፡፡ ኮምፒውተራችሁ ላይ Worm ካለ የኮምፒውተራችሁ ስፔስ ይጠቀማል ስለዚህ ኮምፒውተራችሁ በጣም እንዲቀራፈፍ ያደርገዋል፡፡ 3ኛ፡- #Trojan_Horse ይህ ደሞ ዓላማው ኮምፒውተሮች ላይ ያሉ ፋይሎችን መስረቅ ወይም ሌላ ጎጂ ድርጊቶችን የሚፈፅም ፕሮግራም ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ጎጂ ፕሮግራም Trojan የሚል ስያሜ ያገኘው በጥንት ግዜ ግሪኮች ትሮይ የምትባለዋን ከተማ ሲወሩ የግሪክ ወታደሮች ፈረስ የሚመስል ነገር በእንጨት ቀርፆ በመስራት በዚህ በእንጨት ተቀርፆ በተሰራው ፈረስ ውስጥ ወታደሮቻቸውን በመደበቅ በከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል የምትጠበቀውን ወደ ትሮይ ከተማ በቀላሉ ይገባሉ፡፡ በወቅቱ ለትሮይ ከተማ ህዝብ ፈረስ በጣም የሚከበርና ውድ ስጦታ ነበር፡፡ለዛም ነበር እነዚህ በእንጨት የተሰሩ ፈረሶች ወደ ትሮይ ከተማ ያለምንም ጦርነት በቀላሉ መግባት የቻሉት ፈረሶቹን በስጦታ ለማበርከት ነው በሚል ምክንያት ነበር፡፡ ማታ ቀኑ ሲመሽ የግሪክ ወታደሮች ከእንጨት ከተሰሩት ፈረሶች ውስጥ በመውጣት ትሮይ ከተማን አጠቁ፡፡ 4ኛ፡-#Spyware ፦ Spyware ማለት ሶፍትዌር ሲሆን ስራው ዳውንሎድ የተደረገበት ኮምፒውተር ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እየለቀመ ይህንን ሶፍትዌር ለሰራው አካል ኢሜል ያደርጋል፡፡ Spyware ከሚባሉ ጎጂ ሶፍትዌሮች መካከል KEYLOGGER የሚባለው ይጠቀሳል፡፡ ይህ KEYLOGGER የተባለው Spyware ስራው በኮምፒውታረችሁ ኪቦርድ ላይ በተደጋጋሚ የምትጠቀማቸውን ፊደሎችን ያጠናል፡፡ ኮምውተራችሁ ላይ KEYLOGGER ካለ ለምሳሌ የፌስቡክ ዩዘር ኔም እና ፓስዎርድ ስታስገቡ ፊደሎቹን ለቅሞ ይዛል፡፡ እንደዚሁም የኦን ላይን ባንኪንግ ተጠቃሚ ከሆናችሁ የአካውንታችሁን ዩዘር ኔም እና ፓስዎርደ እየለቀመ ለባለቤቱ ይልካል፡፡ Spyware በራሱ ወደ ኮምፒውተራችን አይገባም፡፡ ቫይረስ ወይም ዎርም የተባሉት ጎጂ ሶፍትዌሮች ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ Spywareም አብራቸው ይገባል፡፡ 5ኛ፡- #Ransomware፦ ሌላው ጎጂ ሶፍትዌር ወይም ፕሮግራም ሲሆን ዋናው ስራው ኮምፒውተራችንን ሙሉ ለሙሉ ይዘገዋል፡፡በሌላ አነጋገር ኮምፒውተራችንን ለመጠቀም ስንከፍተው አይከፈትም፡፡ በ Ransomware የተጠቃ ኮምፒውተር ለመክፈት ስትሞክሩ ይቅርታ ይህንን ኮምፒውተር መክፈት አትችልም፡፡ ኮምፒውተርህን ለመክፈት ከፈለክ መጀመሪያ ገንዘብ ክፈል የሚል መልእክት ይመጣላችሃል፡፡ ገንዘቡን ካልከፈላችሁ ኮምፒውተራቸሁን መጠቀም አትችሉም፡፡ወይም ይህንን ፕሮግራም የሚያጠፋ አንቲ-ቫይረስ ጭናችሁ ማጥፋት አለባችሁ፡፡ ኮምፒውተራችሁ ወይም ሞባይል ስልካችሁ በነዚህ ጎጂ ፕሮግራሞች በሚጠቁበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና መፍትሔዎችን በሚቀጥለው ፖስት አደርጋለሁ።
Show all...
Show all...
Log in to Facebook

Log in to Facebook to start sharing and connecting with your friends, family and people you know.

አስገራሚው የአለም ክብረ-ወሰን ********************* እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ ከረጅም ርቀት የተቆጠረች የአለማችን ብቸኛ ጎል ባለቤት በመሆን በአለም የክብረወሰን መዝገብ ውስጥ ስሙን አስፍሯል፡፡ ኒውፖር ካንትሪና ቼልተንሃም ከተማ ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ በዚህ ጨዋታ የኒውፖርት ካንትሪው ግብ ጠባቂ ቶም ኪንግ ያስቆጠራት ግብ በአለማችን ከረጅም ርቀት የተቆጠረች በመሆን በክብር መዝገብ ውስጥ ሰፍራለች፡፡ ርቀቱም 96.01 ሜትር ተለክቷል፡፡ ያኛው ግብ ጠባቂ ምን የከበደ ነገር ገጥሞት ይሆን ሳያስብል አይቀርም፡፡ ቶም ኪንግ ኳሷን ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል መስመር ላይ አስቀምጦ እንደለጋት የገለጸው የመረጃ ምንጫችን መረብ ላይ ካረፈች በኋላ ነበር የቼልተንሃሙ ግብ ጠባቂ ኳሷን ማየት የቻለው፡፡ ከዚህ በፊት ለስቶክ ሲቲ ይጫወት የነበረው ቤጎቪክ ሳውዛምተን ላይ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2003 ያስቆጠራት ግብ በ91.9 ሜትር የአለምን ክብረ ወሰን ይዛ ነበር፡፡ ምንጭ Ginuss World Record
Show all...
የፊት መልክን በማየት ብቻ የፖለቲካ አስተሳሰብን የሚለየው አዲሱ ቴክኖሎጂ ========================= በስታንፎርድ ኒቨርሲቲ የሚገኝ አንድ የአጥኚዎች ቡድን የሰውን የፊት ገፅታ የሚያሳይ አንድ ምስልን በመመልከት ብቻ የዛን ሰው የፖለቲካ አሰላለፍ በ70 በመቶ ስኬት ማወቅ የሚችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓትን መስራት ችለዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በተለይም በምርጫ ሰሞን ሰዎች ፖለቲካዊ አመለካከታቸውን የሚያንፀባርቁ ከኔቴራ ወይም ኮፍያ መልበሳቸው የተለመደ ቢሆንም ለራሳቸው እንኳን በማይታወቃቸው ሁናቴ በፊት ገፅታቸው አማካኝነት የፖለቲካ ዕይታቸውን እንደሚገልፁ የጥናት ቡድኑ በሳይንቲፊክ ሪፖርትስ ጆርናል ላይ በሰጠው ማብራርያ ይገልፃል፡፡ አዲሱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓት ልክ እንደሌሎች መሰሎቹ ሁሉ የሰው ልጆች ብዙም የማያስተውሏቸውን አዳዲስ መረጃዎች እንዲሰበስብ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ አጥኚዎቹ ታድያ ውሃ አጣጭን ከሚያገናኙ ድረ-ገፆች የፕሮፋይል ምስልን እና ፖለቲካዊ አመለካከታቸውን የሚጠቁም መረጃ ወስደው ስርዓቱን በማለማመድ የሰዎች የፖለቲካ አመለካከት ከፊት ገፅታቸው አኳሀን እና የጭንቅላት አቀማመጣቸው ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲረዳ ለማድረግ ጥረዋል፡፡ ወደ ኋላ ስርዓቱን ምስሎችን በመስጠት ብቻ ሰዎቹ ወግ አጥባቂ አልያም ሊበራል መሆኑን መጠቆም ይችል እንደሆን ሲሞክሩትም ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑትን በትክክል መገመት መቻሉን ተረድተዋል፡፡ አጥኚዎቹ ስርዓታቸው በምን ምለኩ የፊት ገፅታ አኳሀንን በመጠቀም የፖለቲካ እምነትን መለየት እንደቻለ እርግጥ የሆነ ምላሽ ማግኘት ባይችሉም እንደ ጭንቅላት አቀማመጥ/አዟዟር እና ስሜት አገላለፅ ያሉ የተወሰኑ ነገሮችን ግን ለማወቅ ችለዋል፡፡ ለምሳሌ ቀጥታ ወደ ካሜራው ፊታቸውን ያዞሩ ሰዎች በይበልጥ ሊበራል የመሆን እድላቸው የላቀ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ በሌላ መልኩ የተቃውሞ አይነት መልክ የሚያሳዩት ደግሞ ወደ ወግ አጥባቂነት ያደሉ ሆነው አግኝተዋቸዋል፡፡ አጥኚዎቹ ከግለሰብ መብት ጋራ በተያያዘ ለጥናቱ የተጠቀሙባቸውን ምስሎች ለማጋራት ባለመቻላቸው ሳብያ ሌሎች እነርሱ ባሳዩት ልክ ውጤታማ የመገመት ተግባርን ማከናወኑ አዳጋች እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል፡፡ ምንጭ፡ Tech Xplore
Show all...
ስለ ሰው ሰራሽ እግሮች አዲስ ነገር ******************* የሰው ልጅ ባልተጠበቀ አጋጣሚም ይሁን በልዩ ልዩ አደጋዎች ምክንያት የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ሊደርስበት ይችላል፡፡ ታዲያ እነዚህ የአካል ጉዳቶች አንዳንዶቹ እንደ ተፈጥሯዊው ባይሆንም ሰው ሰራሽ ምትኮች ይሰራላቸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የተሻለ አገልግሎት የሚሰጠውና ጥሩ ተደራሽነት ያለው ሰው ሰራሽ እግር ነው፡፡ እዚህ ላይ ይህ ሰው ሰራሽ እግር ከሚሰጠው ጥቅም በተቃራኒው የሚነሱበት የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ከችግሮቹ መካከል እግሩ ከብረትና ከተለያዩ ቁሶች የተሰራ በመሆኑ በቀላሉ የማይታዘዝና ከአእምሮ ሀሳብና የእንቅስቃሴ ፍላጎት ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ለመንቀሳቀስ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑ ነው፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሰው ልጆች ከሚሰጧቸው ጥቅሞች መካከል እንደዚህ ለአጠቃቀም ምቹ ያልሆኑ መገልገያዎችን ሰዎች በቀላሉ መጠቀም እንዲችሉ የሚያግዙ የተለያዩ ምርምሮችን መስራት ነው፡፡ ዘመናዊው ሳይንስ ከእግር ማጣት ጋር በተያያዘ ለችግሩ ተጠቂዎች በልዩ ልዩ ጊዜያ የተለያዩ መፍትሔዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ በዙሪክ በሚገኘው የሲዊዝ የፌዴራል ቴክኖሎጂ ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ እግሮችን ከጉዳተኛው ስርዓተ ነርቭ ጋር ማገናኘት እግሮቹን ቀላልና ታዛዥ እንደሚያደርጋቸው ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ እዚህ ላይ ያለው መሰረታዊው ነገር እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ምንም ከባድና አስቸጋሪ ቢሆኑም ሰው ሰራሽ እግሮች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ለመቆምና ለመንቀሳቀስ የሚያስችሉት ሰው ሰራሽ እግሮች ከስርዓተ ተውነት ጋር የተቆራኙበት ምንም አይነት መንገድ ስለሌላቸው እንደ ተፈጥሯዊው እግር ግብረ-መልስ አይሰጡም፡፡ ከላይ በተጠቀሰው የምርምር ተቋም የተሰራው ግኝት ይህን ችግር መቅረፍ የሚያችል እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ ተመራማሪዎች ሰው ሰራሽ እግሮችን ከስርዓተ ነርቭ ጋር በማገናኘት ተፈጥሯዊ እግር የሚሰማውን ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ የሚያስችል መንገድ ነው ያገኙት፡፡ የህንንም የተወሰኑ የተጠቃሚውን ነርቭ ሴሎች ሰው ሰራሽ እግሩ ካሉት ሴንሰሮች ጋር በማገናኘት እንደሆነ ታውቋል፡፡ በሙከራ ወቅት ተመራማሪዎቹ የምርምሩ ተሳታፊ በሆኑ ሰዎች ላ የተለያዩ ሙከራዎችን አድገዋል፡፡ ከዚህም መካከል ኒውሮ ፊድባኩን በማብራትና በማጥፋት በተሰራ ሙከራ የሰው ሰራሽ እግሩ ክብደት ኒውሮ ፊድባኩ ሲበራ በ23 በመቶ መቀነስ ችሏል፡፡ ምንጭ Technology.Org
Show all...
#የጎግል_Google_አካውንታችሁ_ሊሰረዝባችሁ_Delete_ይችላል ሰዎች የጎግል አካውንት አውጥተው ነገር ግን ለረጅም ግዜ ሳይጠቀሙበት የቆዩ ሰዎች እ.ኤ.አ ከጁን ,2021 ጀምሮ አካውንታቸው ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰርዝ ጎግል(Google) ባለፈው ወር አስታውቋል፡፡ ስለዚህ የጎግል አካውነታችሁ እንዳይሰረዝ አካውንታችሁን አሁኑኑ መጠቀም በመጀመር አካውነታችሁን አክቲቭ እንዲሆን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ አካውነታችሁን አክቲቭ እንዲሆን ለምሳሌ በGmail ኢ-ሜል መላክ መጀመር አለባችሁ፡፡ ከGmail በተጨማሪ ሰዎች አካውንታቸው እንዳይሰረዝ Google Drive ፣ Google Photo እና የመሳሰሉ የጎግል አገልግሎቶችን ሊጠቀሙ ይገባል ብሏል-ጎግል፡፡ የጎግል አካውንታቸው የተሰረዘባቸው ሰዎች ከዚህ በፊት የተለዋዋጧቸው ኢሜሎችም ሆነ ሌሎች ግላዊ መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ እንደሚሰርዝ ጎግል አስጠንቅቋል፡፡ ስለዚህ የጎግል አካውነታችሁን ግዜው ሳይደርስ አሁኑኑ መጠቀም ጀምሩ። ይህ ዜና ለሌሎችም እንዲደርስ #ሼር_ይደረግ
Show all...
#አሪፍ_አፕሊኬሽን_ላስተዋውቃቸሁ ይህ አፕሊኬሽን Signal ይባላል፡፡ Signal አፕሊኬሽን እንደ WhatsApp፤ Facebook Messenger፤ Skype፤ Telegram…ወዘተ ፈጣን መልእክት(ቴክስት) መላላኪያ አፕሊኬሽን ነው፡፡ Signal አፕሊኬሽን ከሌሎቹ (WhatsApp፤ Facebook Messenger፤ Skype፤ Telegram) የሚለየው ሰዎች በ Signal የሚለዋወጡዋቸው ሚስጥራዊ መልእክቶች ከሰዎቹ በስተቀር ሌላ ሶስተኛ ወገን መልእክቶችን ማየትም ይሁን ማግኘት አይችሉም፡፡ በSignal የምንለዋወጠው መልእክት ሙሉ ለሙሉ አንድ መቶ ፐርሰንት ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው፡፡(End-to-end encrypted) ለምሳሌ እስካሁን ድረስ የምናውቀው በWhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች ሙሉ ለሙሉ ሚስጥራዊ እንደሆኑ ነበረ፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ በ በWhatsApp የምንለዋወጣቸው መልእክቶች በሙሉ ፌስቡክ ኩባንያ ማወቅ ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ Edward Snowden እና Elen Musk የመሳሰሉ ተዋቂ ሰዎች ከWhatsApp፤ Facebook Messenger፤ Skype፤ Telegram ይልቅ Signal አፕሊኬሽንን እንድንጠቀም ይመክራሉ፡፡ Signal አፕሊኬሽን ለAndroid፤ iPhoneና iPad እና ለኮምፒውተር እነዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አፕሊኬሽኑን ለመጠቀም የሚያስፈልገው ሞባይል ስልክ ቁጥር ብቻ ነው፡፡ በSignal አፕሊኬሽን አጭር መልእክቶችን ከመላላክ ባለፈ ግሩፕ መፍጠር ያስችላል፤ቪዲዮ ኮል አለው፤የተለያዩ ስቲከሮች አሉት፤ፋይል ማስተላለፍ ችላል..ወዘተ፡፡ የSignal አፕሊኬሽን የሚሰጣቸው ለየት ያሉ ሶስት ጥቅሞቸን ልንገራችሁ፡- 1ኛ፡- Block Screenshot ለምሳሌ ከአንድ ሰው ጋር በFacebook Messenger የተፃፃፋችሁትን መልእክት ያ ሰው መልእክቱን በስልኩ ስክሪን ሻት በማድረግ መረጃ ሊዝባችሁ ይችላል፡፡ Signal ላይ ግን ማንም ሰው የተፃፃፋችሁትን መልእክት ስክሪን ሻት እንዳያደርግ ብሎክ ማድረግ ይቻላል፡፡ 2ኛ፡- Blur Faces በSignal ማንነታችሁን የሚገልፅ ፎቶዎች ልትላላኩ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ፎቶዋችሁን የላካችሁለት ሰው ቢያስፈራራችሁ-ለምሳሌ ሼር አረገዋለሁ ወይም ለቤተሰባችሁ አሳያለሁ…እያለ ቢያስፈራራችሁ Signal ሴቲንግ ውስጥ ገብታችሁ የላካችሁትን ፎቶ ወይም ፎቶዎች ምስላችሁ እንዳይታይ (Blur )ማድረግ ይቻላል፡፡ 3ኛ፡-Disappearing Messages በSignal አፕሊኬሽን የምንለዋወጣቸው መልእክቶች የላክንለት ሰው ካነበበው በሁዋላ መልእክቶቹ ከሰውዬው ስልክ ላይ እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ Signal አፕሊኬሽንን ተጠቀሙት፡፡ትወዱታላችሁ፡፡ Signal አፕሊኬሽንን ፕሌይስቶር፤አፕስቶር ላይ በነፃ ታገኙታላችሁ፡፡ #ሼር_ይደረግ
Show all...