cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወጣትነት እና ክርስትና

ወጣትነትን ከ መንፈሳዊ ሕይወታችን ጋር እንዴት መቀጠል እንደምንችል እና በወጣትነታች ያለን የክርስትና ሕይወት ምን መምሰል እንዳለበት በተለያየ መንገድ መንማርበት መንፈሳዊchannel ነው

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
183Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሌሎች የበላይ መሆን ምንም ፋይዳ የለውም። ይህም ይልቅስ ፋይዳ ያለው በቅድሞው ማንነትህ ላይ የበላይነትህን ማረጋገጥ መቻል ነው። የጥቅሱ ዋና መልዕክት ሕይወትህን ማሻሻል ከፈለግህ ውድድር ከራስህ ጋር ነው የሚሆነው። ሌሎች ሰለ አንተ በሚሉት አትጨናነቅ። ደግምም ልብህ ያመነበትን ማንኛውንም ነገር ማሳካት ትችላለህ። መቼም ቢሆን ራሰህን ከሌሎች ጋር እያነፃርክ ለራስህ ደረጃ አታውጣ። ስለሌሎች ሰዎች ህልምና ስኬት ባሰብክ ቁጥር ከራስህ ላይ ትቀንሳለህ። መልካም ምሽት
Show all...
አንድ ባል ለሚስቱ ደውሎ “የኔ ማር እኔ ከአለቃዬ እና ከብዙ ጓደኞቼ ጋር ወደ ባህር ዳርቻ አሣ ለማጥመድ ለአንድ ሳምንት እንሄዳለን፡፡ ይህ ለእኔ እድገት ለማግኘትና ከአለዬ ጋር ለመቀራረብ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ስለዚህ እባክሽን ለሳምንት ያህል የሚሆን በቂ ልብሶችን እና የዓሣ ማጥመጃዬን ሣጥን አዘጋጂልኝ፤ ከቢሮ እንደወጣው እቃዎቼን ለመውሰድ በቤት በኩል አልፋለው እናም አዲሱን ሰማያዊ ሐር ፒጃማዬን ማስገባቱን እንዳትረሺው፡፡" በማለት ስልኩን ዘጋው፡፡ሚስትየዋ ይህ ነገር የአውነት የአሣ ማጥመድ ጉዞ እንዳልሆነ ይሰማታል። ነገር ግን ጥሩ ሚስት በመሆኗ ባሏ በትክክል የጠየቀውን አደረገች፡፡ ቀጣዩን ቅዳሜና እሁድን አሳልፎ ወደ ቤቱ መጣ፡፡ ብዙም የድካም ስሜት ሳይታይበት እንደውም አምሮበት ነበር የተመለሰው፡፡ ሚስትየውም በደስታ ተቀበለችው እና ብዙ ዓሦችን እንደያዘ ጠየቀች? እሱ "አዎ! ብዙ አይነት አሳዎችን በሚገርም ሁኔታ አጠመድን፡፡ በጣም ጥሩ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው። ነገር ግን እንድታደርጊልኝ የጠየኩሽን ሰማያዊ ሐር ፒጃማዬን ለምን አላደረግሽልኝም ማር?" አላት፤ ሚስትየው “አረ አስገብቻለው ነገር ግን ልብሱን በአሳ ማጥመጃ ሳጥን ውስጥ ነው ያደረኩልክ፡፡” ብላ መለሰች... የምንዋሸው ውሽት በምን በኩል ሊጋለጥ እንደሚችል ስለማናቅ እውነትን ብቻ እንከተል፡፡ውሸትን ለመሸፈን ሁሉንም ቀዳዳዎች መድፈን እንችልም፡፡ ሼር በማድረግ ሌሎችም እንዲያነቡ እናድርግ ምንጭ:- social media
Show all...
❤️❤️❤️ የእግዚአብሔር ሕይወት የሚቀዳው ከእግዚአብሔር ቃል እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚደረግ የማይቋረጥ ህብረት ነዉ!!!! 👉የእግዚአብሔርን ቃል ያለማቋረጥ በማሰላሰል ቃሉ በሕይወታችሁ መገለጫ (Expression) እንድያገኝ ማድረግ ትችላላችሁ። መዝሙር 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። ³ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። 👉መዝሙረኛው ዳዊት በሚሰራው ነገር ሁሉ የሚከናወንበት ምስጥር የሄው ነዉ። የእግዚአብሔር ቃል ትዝታው ነበር። ከበጎች እረኝነት ጀምሮ የእስራኤል እረኛ እስክሆን ለአንድም ቀን ያላቆመው ነገር የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰል ነበር። ❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓ 👉ምንድነው መጽሐፍ ቅዱስ እንዳላነብ ቃሉን እንዳላሰላስል እና እንዳልጸልይ እንቅፋት የሆነብኝ??? የሴት ጓደኛ? ፣ የወንድ ጓደኛ? ፣ የማህበራዊ ድረገጽ? ወይስ የራሴ ድካም!??? ምንም ይሁን ምን ዛሬ በመሰጠት መሰዊያ ለይ ላቃጥለው ወስኛለሁ!!! 👉ለጌታ የተገባ ሰው ለመሆን ወስኛለሁ!! ማቴዎስ 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁷ ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ³⁸ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። ³⁹ ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። ➤የትኛውንም ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ካለኝ ህብረት አላወዳደርም። ይህንን ውሳኔ ከልባችሁ የእውነት ማድረግ ከቻላችሁ ለእግዚአብሔር ትውልድን የሚመልስበት የክብር እቃ ትሆናላችሁ። ደግሞ ለክርስቶስ ኖሮ እንደማለፍ ቁምነገር በአለም ውስጥ የለም፤ ሊኖርም አይችልም፡፡ ከዝህ ውጭ የሆኔ ኑሮ ሁሉ ዝም ብሎ ኑሮ ይባላል፡፡ ስለዝህ የቁምነገር ኑሮ ኖረህ ማለፍ ትፈልጋለህ? ትፈልግያለሽ? ዛሬ አንድ ብለህ ጀምር፡፡ ለክርስቶስ መኖር የትርፍ ግዜ ሥራችን ሳይሆን የሙሉ ግዜ ሥራችን ይሁን፤ ለነገሩ ለሌላ እንዳንኖርም ትርፍ ግዜ የለንም አይደል? አዎና በደንብ !!! ምክንያቱም ለምድራዊ ቆይታ ተወስኖ የተሰጠን ግዜ ለአንድ ነገር ብቻ የምበቃ ነው እሱም ለኢየሱስ መኖር ከዝህ ውጭ ሌላ አለ ካላችሁኝ እኔ አላውቅም! ማወቅም አልፈልግም ፡፡ ጌታ ይባረክ ብሩካን ጌታ ኢየሱስ ይወዳቿል፡፡
Show all...
ነፍሴ KALAB TEKIL ተለቀቀ ቪዲዮውን ሊንኩን በመካት ይመልከቱ SUBSCRIBE ያድርጉ https://youtu.be/9ZXRZ1XFz60 https://youtu.be/9ZXRZ1XFz60 https://youtu.be/9ZXRZ1XFz60
Show all...
ዛሬ ካለፉት የተለየች ከሚመጣው የቀደመች መልካም ለመስራት በእጅህ ያለች ወርቅ ነች። ምን መልካም ልትሰራ ትሻለክ? ✔ልትታዘዝባት ✔ይቅርታ ልታረግባት ✔በጎን ልትሰራባት ወ.ዘ.ተ የተመኘከውን ለመስራት ሳትታክት ለመጀመር በመሀል ላለመቆም በርታ የተነሳህበትን ሳትረሳ ግብህን እዳነገብክ እሩጥ......... እዳትቆም ግና ድገት ከቆምምክ ጥቂት ወደዋላ ተንደርድረክ ጀምር ካለፈው በላይ እሩጥ። ❝በህይወትህ ተስፋ አትቁረጥ..አልችልም አትበል ትችላለህ...ሞክር፤ተራመድ..መራመድ ቢያቅትህ ተንፏቀቅ ብቻ ምንም አድርገህ ምንም ወደፊት መጓዝህን መቀጠል አለብህ።❞
Show all...
ነፍሴ KALAB TEKIL NEW LYRICS VIDEO ቪዲዮው እንደተለቀሰ እንዲደርስዎ SUBSCRIBE ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UCQZIfBLlO2RrXh_S7Fej-7w https://www.youtube.com/channel/UCQZIfBLlO2RrXh_S7Fej-7w
Show all...
የመገደድ ስሜት! ውስጥህ ካለማቋረጥ ይናገርሃል፡፡ ውስጥህን ማድመጥ ግን የአንተ ሃላፊነት ነው፡፡ ስህተት ስትሰራ ህሊናህ እንደሚናገርህና እንዲሁም ሲያምህ፣ ሲርብህና ሲጠማህ አካልህ እንደሚናገርህ ሁሉ ውስጥህ ከሚነግርህ በርካታ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ በሰዎች የመገደድን ስሜትህን ነው፡፡ በሰዎች የመገደድን ስሜት ማድመጥ ማለት ከማንነታችን የሚያወጣንን የሰዎች ግፊት መለየት ማለት ነው፡፡ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች የማናምንበትን ነገር እንድናደርግ፣ የማንፈልገውን ውሳኔ እንድንወስንና ምቾት ወደማይሰማን የሕይወት ቀጠና ውስጥ እንድንገባ ካለማቋረጥ ግፊት ያደርጉብናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚጫኑንና የሚያስገድዱን ለእኛ መልካም የሰሩ እየመሰላቸው ሲሆን፣ ሌሎች ግን እኛን የመቆጣጠር ዝንባሌ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህች አለም ላይ ስትኖር ራስህን ከአስገዳጅና ከተቆጣጣሪ ሰዎች ነጻ ማውጣት ከቻልክ የድሎችን ሁሉ ድሎች ተጎናጽፈሃል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜህን ካባከንክ በኋላ የባነንክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ብታጤናቸው በሰዎች ግፊት ምክንያት ካደረካቸው ወይም ከማድረግ ከተቆጠብክባቸው ሁኔታዎች ጋር ተዛምደው ታገኛቸዋለህ፡፡ ከዚህ ሁኔታ ለመዳን ከፈለክ፣ ምንም አሰብክ ምንም ሃሳቡ ከውስጥህ የወጣ ወይም ውስጥህ ያመነበት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም፣ በሰዎች ከመገደድ አዙሪት ነጻ ለመውጣት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች አሉ፡፡ 1. የሕይወት መመሪያ ይኑርህ የሕይወትህን መመሪያ በመለየትና በማወቅ ያንን ማዳበርና በዚያ እውቀት መደላደል አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ራስህን ካልመራህ የመጣው ሰውና ገጠመኝ ይመራሃል፡፡ ራስህን ስትመራ ግን ሁሉን የምትመዝን ትሆናለህ፡፡ 2. ገደብህን እወቅ ለሰዎች ብለህ የት ድረስ መሄድ እንዳለብህ ለይተህ እወቅ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ ማድመትም ሆነ ለሰዎች ስትል ዋጋ መክፈል ታላቅ ብስለትና ጨዋት የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ያንን ማድረግ ያለብህ ግን በመገደድ ስሜት ሳይሆን ውስጥህ ስላመነበትና ያንን ለማድረግ ስለወሰንክ መሆን አለበት፡፡ 3. ለሰዎች ገደብን አብጅላቸው ያላመንክበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነትህን እንደሚሸረሽረውና ዘመንህን በከንቱ እንደሚበላው አትርሳ፡፡ ከፈዘዝክበትና ከደነዘዝክበት ሁኔታ ተነሳና ውጣ! ለማን ሰውና ለምን አይነት ሁኔታ እሺ እንደምትል ለይተህ እወቅ! የራስህ ጉዞ ከሰዎች እጅ አውጣና ወደራስህ እጅ አስገባ!
Show all...
@BeGubznachnWeratFetarinEnasb @BeGubznachnWeratFetarinEnasb @BeGubznachnWeratFetarinEnasb ✍ B.m Join and share ሃሳብ እና አስተያየት ካላቹ👇👇👇👇 @Betimula2
Show all...
#ከፈተናዎች_ጀርባ ትላልቅና ትክክል ነገሮች የወጡት ከትንንሽና ከስህተት ውስጥ መሆኑን እወቅ። መሳሳስትን አትፍራ >>ለፈተናዎች የምትሰጠው ትርጉም ፈተናዎችን የማለፍህንና አለማለፍህን ይወስናል። ፈተና አንተ እንደተጣለ ደካማና ሰነፍ ሰው እንደሆንክ ሊያሳይ እንደመጣብክ ካሰብክ በእርግጠኝነት የማማረር ህይወት ውስጥ ይጨምርሃል። >>ፈተና የምትፈተነው ጥንካሬን እንድታገኝ ጥንካሬህን እንድታሳይ ትናንት ከምታውቀው በላይ እውቀትን ሊሰጥክና ትልቁን የህይወት አክሊል እንድታገኝ ድልድይ ሊሆንልክ መሆኑን ስታሰብ ፈተናን እንደጥሩ የህይወት አጋጣሚ ማየት ትጀምራለህ። >>አትፈተንም እንድልህ አትጠብቅ አትኖርም ማለት ነውና። አንዴ ብቻ ትፈተናለህ እንድልህ አትጠብቅ በእያንዳንዱ ቀን መማር፣ማደግ፣መበርታትና ወደትልቅነት መሮጥ ያስፈልግሃልና።የምትኖርባቸው ቀኖች ካሉ የምትፈተንባቸውም ናቸው። >>ወዳጄ ዛሬ አንድ ምርጫ እሰጥሃለሁ በትልቁ ነገር መፈተን ወይስ በትንሹ መፈተንን ትመርጣለህ? ለአንበሳ አይጥን በመያዝ ወይስ ጅብን በመያዝ ቢፈተን ይሻለዋል? አንበሳን አይጥ በመያዝ መፈተን ማንነቱን ዝቅ ማድረግ ነው። ሰለዛ ትልቅ ስትሆን በትልቅነትህ ልክ ትፈተናለህ(የእዮብን ህይወት ተመልከት)። >>መርፌ መወጋት አልወድም ብለክ ከበሽታ ጋር መኖርን አትመርጥም፤ፈተና ከባድ አድካሚና አሰልቺ ነው ብለህ በታናሽነት፣በድካምና ያለ አክሊል መኖርን አትምረጥ። >>አንድ ሚስጥር ልንገርህ ትልልቅ ሰዎች ትልቅ የተባሉት ስላልተፈተኑ ሳይሆን ከፈተናዎች ስለተጠቀሙ ነው።ከፈተናዎች ምን ያክል ተጠቅመሃል? ብልህ ሰዎች ከፈተናዎችና ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች የህይወትን ብርታት ያገኛሉ። >>ፈተናዎች ትልቅ መሆንህን እንዲያሳዩ ከፈለክ ፈተናዎችህን ለሰይጣንና ለሁኔታዎች መጠቀሚያ ሳይሆን ለአንተና ለትውልድ መጥቀሚያ አድርጋቸው። ቃሉስ ቢሆን በምድር ሳላችሁ ፈተና አለባችሁ አይደል እንዴ? ወፍ የሚፈራ ዘንጋዳ አይዘራም! @BeGubznachnWeratFetarinEnasb @BeGubznachnWeratFetarinEnasb Join and share
Show all...