cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዜና ኢትዮጵያ®

አዳዲስ ወሬዎችን ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ #share * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * * ጣቢያ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
230Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቻይና የሳንባ ካንሰርን ማዳን የሚያስችል ትልቅ ግኝት ይፋ አደረገች‼️ በቻይና ቤጂንግ የሕክምና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኝ የሳንባ ካንሰር ምርመራ እና ሕክምና ምዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ዢ ዡዪ እንደተናገሩት ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሲካሄዱ የቆዩ የሳንባ ምርመራዎች ለሳንባ ካንሰር መነሻ የሆኑ ምክንያቶችን እንድንለይ አስችሎናል ብለዋል የሳንባ ካንሰርን በጊዜ መለየት ከተቻለና ሕክምና ከተደረገ የመዳን ዕድሉን በእጅጉ ማፍጠን እንደሚቻል ተመልክቷል፡፡ የሳንባ ካንሰር ሕሙማኑ እንደ ቀድሞው ቀዶ ጥገና ሳያስፈልጋቸው በደረት አካባቢ አነስተኛ ክፍተት በመፍጠር ቀጭን ቱቦ ላይ በተገጠመ ካሜራ እና ብርሃን ተመርቶ በሚሰራ አነስተኛ ቀዶ ጥገና እንደሚድኑም ነው ሲጂቲ ኤን የዘገበው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው ሪፖርት መሰረት የሳንባ ካንሰር በገዳይነቱ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠ ሕመም ነው፡፡ በቻይና የሳንባ ካንሰር በገዳይነቱ በቀዳሚነት የሚቀመጥ ሲሆን በየዓመቱ 820 ሺህ አዳዲስ ሰዎች በሕመሙ ይጠቃሉ 710 ሺህ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ @zenaethiopa
Show all...
ሩሲያ አዲስ አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔል ሞከረች!! ሩሲያ በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ ስማርት አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔል ሙከራ ማደረጓን አስታወቀች። አዲሱ የሩሲያ አህጉር አቋራጭ ሚሳዔል በደቡብ ምዕራብ ሩሲያ ከምትገኘው ፕሌስክ የተወነጨፈ ሲሆን፤ በሌላኛው የሩሲያ አካል በሆነችው ሩቅ ምስራቅ ካማችታካ ማረፉ ተነግሯል።አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔሉ በአጠቃላይ 6 ሺህ ኪሎ ሜትሮችን እንደተጓዘም ነው የተገለፀው። በሰዓት ከ6 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚምዘገዘገው ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል አዲሱ የሩሲያ ባላስቲክ ሚሳዔል የቴክኒክና የታክቲክ ብቃታቸው ከፍተኛ እንዲሁም ዘመናዊ የሚሳዔል መከላከያ ስርዓቶችን መቋቋም የሚችል ነው ተብሏል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ “ሚሳዔሉ እስካሁን ካሉት የተለየ መሳሪያ ነው፤ የሰራዊታችንን የመዋጋት አቅም ያሳድጋል” ያሉ ሲሆን፤ “በአስተማማኝ ሁኔታ ሩሲያን ከውጭ አደጋዎች መከላከል እንዲሁም ሩሲያን ለማስፈራራት ለሚሞክሩም በቂ ምለሽ ለመስጠት የሚያስችል ነው” ብለዋል። “ሙከራው ለሩሲያ ጠላቶች ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርግ የቤት ስራን የሰጠ ነው” ሲሉም ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል። የዓለም አቀፉ የስትራቴጂክ ጥናት ማእከል የኤሮስፔስ ባለሙያ የሆኑት ዶጉላስ ባሪ፤ ሩሲያ አዲስ ያደረገችው ሙከራ ለሀገሪቱ አዲስ የስኬት መንገድ መሆኑን አስታውቀዋል። ሩሲያ ሚሳዔሎችን በስራ ላይ ለማዋል ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ይጠበቅባታል ያሉት ባሪ፤ አዳዲሱቹ ሚሳዔሎች ስራ ላይ ሲውሉ SS-18 እና SS-19 የተባሉ እድሜ ጠገብ የሩሲያ ሚሳዔሎችን ይተካሉ ብለዋል። ስማርት የተባለው አዲሱ ሩሲያ ሚሳዔል በአንድ ጊዜ እስከ 10 የኒኩሌር አረር የመሸከም አቅም እንዳላቸውም ባለሙያው ተናግረዋል። @zenaethiopa መረጃ#shera
Show all...
የሱዳኑ ወቅታዊ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር እርቅ መፈፀም እንፈልጋለን ነገር ግን ኢትዮጵያ የአልፋሽጋ መሬት የሱዳን መሆኑን ባደባባይ ማወጅ አለባት አለ። ጀነራል ቡረሀን ከተመድ አመራረች ጋር በነበረው ውይይት ላይ ኢትዮጵያ ሱዳን ውስጥ አለኝ የምትለው መሬት የላትም። ከመቶ አመት በላይ በነፃ ስትጠቀምበት ኖራለች፣ አሁን ግን ሱዳን ድንበሯን ማስከበር ስላለባት መሬቷን ሙሉ በመሉ ተቆጣጥራለች። የቀራት ትንሽ መሬት ነው እሱንም እናስመልሳለን ብሏል። ከተመድ የፀጥታ አመራሮች ጋር በህዳሴው ግድብና በድንበሩ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ዙሪያ የመከረው ጀነራል ቡረሀን ኢትዮጵያ የሌላን አገር መሬት የኔ ነው እያለች እንዴት ነው መታረቅ የምንችለው እንዲህ አይነት ጨዋታ ውስጥ መግባት አንፈልግም። መሬቱ የኛ ነው። ኢትዮጵያም ታቃለች። ስለዚህ እውቅና ትስጥና እንታረቀለን ብሏል። በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አስተያየት የሰጠው ጀነራል ቡረሀን። ህጋዊና የሆነ ስምምነት ላይ መድረስ አለብን። ያለምንም ስምምነት ውሃውን ለብቻ እናስተዳድራለን የሚል ሀሳብ አንፈልግም ብሏል። እንደሚታወቀው ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ገብታ 60 ኪሎ ሜትር የኢትዮጵያን መሬት በወረራ ይዛለች። ለጀነራሉ ንግግር ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ መልስ የለም።(ANN) @zenaethiopa መረጃ #shera
Show all...
የባልደራስ አመራሮች በአርባምንጭ ታሰሩ!! አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የባልደራስ አመራሮች አርባ ምንጭ ከተማ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዝዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታውቋል። አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ልዑካን ዛሬ ወደ አርባምንጭ ያቀኑ ሲሆን ወደ አርባ ምንጭ የሄደቱ በደቡብ ክልል የፓርቲውን የሀገር አቀፍ ፊርማ ንቅናቄ ለማስጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ፓርቲው የፊርማ አሰባሰቡን ንቅናቄ ለማስጀመር በአርባ ምንጨ እና በወላይታ ሶዶ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ጠይቆ ከተፈቀደ ቦኃላ፣ " ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው " በሚል ስብሰባዎቹ እንዳይደረጉ እንደተከለከሉበት አስረድቷል። ከዚህ በኃላ ነው ፓርቲው ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ወደ አርባ ምንጭ የሄዱት ልዑካን በፖሊስ መታሰራቸውን ያሳወቀው። ባልደራስ እስሩ ያለምንም ምክንያት የተፈፀመ ነው ብሏል። @zenaethiop መረጃ #shera
Show all...
ተመድ በጸጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸውን ሀገራት ስልጣን ሊገድብ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ከአሜሪካ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ሲሆን ምክክሩ የሚካሄደው የተመድ አባል ሀገራት በተገኙበት መሆኑም ተገልጿል፡፡ አሜሪካ ቻይና፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ ሲሆኑ አምስቱም አባል አገራት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውሳኔዎችን የመሻር መብት አላቸው፡፡ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤም የነዚህን ሀገራት ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን በተወሰነ ደረጃ መገደብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡ ደምጽን በድምጽ የመሻር መብት ካላቸው አምስት ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደችው ያለው ጦርነት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት ምክንያት ሆኗልም ተብሏል፡፡ የዓለምን ጸጥታ ለመጠበቅ እንደተቋቋመ የሚነገረው የጸጥታው ምክር ቤትም የሩሲያን እና ዩክሬንን ጦርነት ሊያስቆም ባለመቻሉ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላት ሩሲያን ስልጣን ለመገደብ እንደሚወያይም ይጠበቃልም ተብሏል፡፡ የዛሬው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካንን ጨምሮ በ50 ሀገራት ድጋፍ የተጠራ ሲሆን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው አራቱ ቀሪ ሀገራት ድጋፍ እንዳልቸሩ የተመድ ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተመሰረተው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ እና ሁለት ዓመቱ የሚቀያየሩ 10 ቋሚ ያልሆኑ ሀገራትን ይዟል፡፡ Via Al Ain @zenaethiopa
Show all...
ሰሜን ሸዋ ውስጥ ካለፈው እሁድ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስካሳለፍነው ሌሊት በቀጠለ ጥቃት የሰው ሕይወት መጥፋቱ እና ቤት ንብረት መውደሙ ተገለጠ። በሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ነዋሪዎች፦ የተከሰተው ግጭት የበረደ ቢመስልም አሁንም  ስጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል። የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳደር ትናንት በነበረው ጥቃት ሞላሌ በተባለች መንደር የሁለት አርሶ አደሮች ሕይወት ማለፉን አመልክተዋል። የዐይን እማኞች ቢያንስ ሰባት ሰዎች በጥቃቱ መገደላቸውን እና ጎጆዎች በእሳት ተለኩሰው መጋየታቸውን ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል። ባለፈው እሁድ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ እንዲሁም በቀወትና ሸዋሮቢት አካባቢዎች ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናትና ነዋሪዎች ገልጠዋል። አንድ የሸዋ ሮቢት ከተማ ነዋሪ ባለፉት ሁለት ቀናት የነበረው ግጭት ዛሬ የበረደ ቢመስልም ታጣቂዎችና ሕዝብ ተፋጥተው ይገኛሉ ብለዋል። የገበያና የመንግስት ሥራ የለም፣ ሴቶችም ከተማውን ለቅቀው ወጥተዋል ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ሌላ የዐይን እማኝ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጉዳት ደርሶባት የነበረች ሞላሌ የተባለች መንደር ካገገመች በኋላ ትናንት በታጣቂዎች እንደገና መቃጠሏንና 7 ያህል ሰዎች መሞታቸውን አመልክተዋል። የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳ አቶ ችሮታው ባሳዝን በበኩላቸው በወረዳው አንዳንድ አካባቢዎች ታጣቂዎች ከኅብረተሰቡ ጋር ግጭት ፈጥረው ሞላሌ የተባለች መንደርን አቃጥለዋል ብለዋል። አሁን ሁኔታዎች የተረጋጉ መሆናቸውን ጠቁመው ሞላሌ ላይ በነበረው ግጭት ሁለት አርሶ አደሮች መገደላቸውንና የተጠቃለለ መረጃ ገና እየጠበቁ እነደሆነም ተናግረዋል።  @zenaethiopa #shera
Show all...
የሩሲያ TU-95 የኒውክሌር ቦምብ ተሸካሚ አውሮፕላኖች በዩክሬን ዳርቻ በኔቶ ድንበር አቅራቢያ ሲበሩ ውለዋል። ድላይ ሞል እንደዘገበው ከሆነ የሩሲያ ኒኩሌየር ቦንብ ተሸከሚ አውሮፕላኖች ከ70 አመት ቡኋላ ድምፃቸውን አጥፍተው በኔቶ ጦር አቅራቢያ ስር ሊቪቭ ከተማ ሲበሩ ታይተዋል ብሏል። ሊቪቭ ከተማ ከፖላንድ ድንበር 65ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝና በምዕራብ ዳርቻ የምትገኝ ትልቋ የዩክሬን ከተማ ናት። በዚህም ምክንያት በኔቶና በምዕራባውያኑ መንደር ከባድ መረባበሽና ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀዋል ያለ የእንግሊዝ ታርዝ ጋዜጣ ነው። ሩሲያ TU-95 አስፈሪ በራሪዎች ሊቪቭ በተባለችው የዩክሬን ምዕራባዊ ውብ ከተማ የሚገኙ ኢላማዎችን ከኒውክሌር ውጭ በሆኑ መሳሪያዎች በተለይም Kh-55 እና Kh-101 በተሰኙ ከአየር ላይ በሚተኮሱ የክሩዝ ሚሳይሎች ለመምታት ተጠቅመዋል። በጩኸቱ ብቻ የህንፃ ግድግዳ መስታወቶች የሚያረግፍ እጅግ በጣም አሰቃቂ በራሪ TU-95 ብቸኛው የፕሮፔለር ኃይል ያለው ስልታዊ የኒዩክለር ቦምብ ተሸካሚና ተዋጊ አውሮፕላን እስከ ዛሬ በዚህ ጦርነት አገልግሎት ላይ ያልዋለ ሲሆን አውሮፕላኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የበረረው ከ70 ዓመታት በፊት ነው። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ማሻሻያዎች ተደርጎለትና በብዙ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ተደራጅቶ በቁጥሩም በርክቶ ከ300 በላይ መድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል። ፕሬዚዳንት ፑቲን የኛን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ካየን ቦንቡን እንጠቀማለን ሲሉ ጦርነቱ በተጀመረ በሦስተኛ ቀኑ ተናግረዋል። (ANN) #zenaethiopa #shera
Show all...
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን አስመልክቶ ውሳኔ መተላለፉን አሳውቋል። ከውሳኔዎቹ አንደኛው ከዚህ በፊት በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግባት ከቻሉት የክልሉ ተማሪዎች #በተጨማሪ 4339 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ እንዲያገኙ ተወስኗል ብሏል። እነዚህ 4339 ተማሪዎች እንዴት እና በምን አግባብ ቅበላ ሊያገኙ እንደቻሉ (የተበላሸ ውጤታቸው ተስተካክሎ ወይስ ሌላ ስለሚለው) ቢሮው ዝርዝር ማብራሪያ አልስጠም። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሌላ ተላልፏል ያለው ውስኔ ፥ በ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመግቢያ ነጥብ ያላሟሉ የክልሉ #ሁሉም_ዞኖች ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመደበኛ ተማሪነት (as regular students) መፈተን እንደሚችሉ ነው። ቢሮው ፤ ትምህርት ሚኒስቴር የውጤት መቁረጫ ነጥብ ተወስኖ እና ያለፉት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻው ቀን ከተወሰነ በኋላ ከአማራ ክልል በተነሳ ቅሬታ መነሻነት ቅሬታውን አዳምጦ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ማድረጉ ትልቅ መደማመጥ የተስተዋለበት ነበር ሲል ገልጿል። "ይህም ለቀጣይ በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ የሀገር ግንባታ ጉዟችን አንድ ማሳያ ነው ብለን እናስባለን " ሲል አክሏል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከተፈጠረው ችግር አኳያ #ውሳኔው ያላረካቸው አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል ያለ ሲሆን የክልሉ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እድሉን በድጋሜ ማግኘታቸውን እንደ ትልቅ አጋጣሚ አድርገው ለውጤታማነት እንዲጠቀሙበት አሳስቧል። @zenaethiopa መረጃ#shera
Show all...
ሩሲያ ኢትዮጵያውያን ወዶ ዘማቾችን እየመለመለች ነው መባሉን አስተባበለች! የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ለምን ተሰለፉ ለሚለው ኤምባሲው አል-ዐይን አማርኛ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ መግቢያ በር ላይ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለሩሲያ ዩክሬንን ለመውጋት ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ አል ዐይን አማርኛ ጉዳዩን በሚመለከት በአዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ጠይቋል። የኤምባሲው ፕረስ አታቼ ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን እንዳሉት “ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል። ይሁንና ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት “በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢሜይል እና በአካል ከሩሲያ ጎን መሆናቸውን እያሳወቁን ነው ለዚህ እናመሰግናለን” ሲሉም አክለዋል። ኢትዮጵያዊያን ይሄንን እያደረጉ ያለው ረጅም እና ታሪካዊ በሆነው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወዳጅነት ላይ ስለሚተማመኑ እንደሆነም ኤምባሲው ተገልጿል። Via Alain @zenaethiopa መረጃ#shera
Show all...
"የመስጠት ተግባራትን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከበዓል ሰሞን ባሻገር የመስጠት ተግባራችንን በማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ። “ያለንን ማካፈል የባህላችን አንድ አካል ሆኖ የዘለቀ ዕሴት ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማካፈል ዐሥር እጥፍ መልሶ የሚያስሸልም ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። “ከበዓል ሰሞን ባሻገር በቀጣይነት የመስጠት ተግባራችንን ማስፋት በእኩልነት ተደራሽ የሆነ ማኅበረሰብን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ግብአቶች አንዱ ነው” ብለዋል። በተለያየ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሁሉ 'ማዕድ ማጋራት'ን እንዲያሰፉ አበረታታለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት። @zenaethiopa መረጃ #shera
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!