cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

LOGOS CHRISTIANS' CHANNEL

ሎጎስ ክርስቲያን ቻናል የተሐድሶ ድምፅ LOGOS CHRISTIANS' CHANNEL THE VOICE OF REVIVAL መጸሐፍቅዱሳዊ ፣ጥቅሶች ፣መልዕክቶች ፣መዝሙሮች ፣ጥያቄዎች እና ሌሎችንም ክርስቲያናዊ መርሐ ግብሮች ከፈለጉ ✝👇👇👇👇👇✝ @ logoschristianschannel @ logoschristianschannel @ logoschristianschannel

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
443Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from Zaphnath-paaneah
🔘ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም!! 📌ኤፌሶን 2 ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ✍ከደህንንነት ጋር በተያያዘ መፅሃፍ ቅዱሳችን ግልፅና ቀጥተኛ አቋም ይለው ሲሆን ብዙ ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ የኃይማኖት ተቋማት ግን ሲያወሳሰቡት ይስተዋላል....ይህም የመጀመሪያዎቹ ካለማወቅ የተነሣ ሲሆን(መፅሃፍ ቅዱስ ትተው ሌሎች በሰው የተደረሱ መፅሃፍትን በማንበብ) ሁለተኞቹ ግን እውነቱን በደንብ እያወቁ ነገር ግን እውነቱን መስበክ ቢጀምሩ የግል ጥቅማችን ሊነካ ይችላል ብለው በፍርሃትና በይሉኝታ ገመድ ተተብትበው የተቀመጡት ናቸው.....የአምላክ ቃል እንደሚያስረዳን ከሆነ ግን ወንጌላችን ሙሉ በሙሉ የሚነግረን የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነና እርሱም ደግሞ እንደተሰቀለ፣ በሶስተኛውም ቀን በክብር እንደተነሣ፣ ወደ ሰማይም እንዳረገ እና በአብ ቀኝም ተቀምጦ ስለ እኛ ዘወትር እየማለደልን ስላለው ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ ስለሆነው ጌታ ነው:- 📌ሮሜ 1 ¹-² ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ³-⁴ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ✍ይህ ጉዳይ ያለማናችንም አስተዋፅዖ በራሱ በእግዚአብሔር የተሰራልንን የቤዛነት ሥራ በመሆኑ በፍፁም ልባችን አምነን በመቀበልና በአፋችን ለሰዎች በመመስከር መፅደቅም ሆነ መዳን እንችላለን.....ምክንያቱም እርሱ የሠራልን ሥራ እኛን ለማፅደቅም ሆነ ለማዳን በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይ ነውና #ሃሌሉያ እግዚአብሔር ይመስገን#...በኤፌሶን ምዕራፍ ሁለት ላይ እግዚአብሔር በኃጢያት ምክንያት ጠፍቶ የነበረውን ሰው ለማዳን በነበረው ዕቅድ የማንንም አስተዋፅዖ ለምን እንዳልፈለገ ይነግረናል:- 📌ኤፌሶን 2 ⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ⁶-⁷ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ✍ከላይ በጥቅሱ ላይ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር መዳናችንን ሙሉ በሙሉ ራሱ የጨረሰው አንደኛ የፀጋው ባለጠግነት ይመሰገን ዘንድ ነው ሲቀጥል ደግሞ እኛ የሰው ልጆ በሥራ የመፅደቅ ብቃት ስለሌለን ነው....በስራ እንፀድቃለን ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች ከፀጋው ወድቃችኃል:- 📌“በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።”ገላትያ 5፥4 📌ኤፌሶን 2 ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ✍ከኢየሱስ ክርስቶስ ውጪ የሆነ ወንጌል ወንጌል ሳይሆን ወንጀል በመሆኑ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስጠይቅም ጉዳይ ነው....የኢየሱስ ወንጌል ሰዎችን የሚያድነውና ነፃ የሚያወጣው እንደወረደ ሲሰበክ ብቻ እንጂ ከተለያዩ የሰው ፍልስፍናዎች ጋር ሲደባለቅ አይደለም...ለዚህም ይመስላል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ወንጌል ጋር የማይስማማ ማንም ቢኖር የተረገመ ይሁን ብሎ በድፍረት የተናገረው:- 📌ገላትያ 1 ⁶ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ ⁷ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ⁸ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። ⁹ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። ✍እግዚአብሔር የልቦና አይኖቻችንን ይክፈትልን(..ነገ ብቀጥለው ሳይሻል አይቀርም..እወዳችኃለሁ) @ZaphnathPaaneah1 @Yoni4Christ #Share #Join
Show all...
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” — ሉቃስ 24፥5
Show all...
በእርሱ ቁስል እኔ ተፈወስኩ!!! የዛሬ 1989 አመታት በፊት በመስቀል ተሰቅሎ ብሉይን ዘግቶ አዲስን ሲከፍት ፤እኔ ዳንኩ። ያኔ ነው የዳንኩት ፤እርሱ ሲቆስል እኔ ግን ስፈወስ ፣ ያኔ ነው የዳንኩት፤ ❣በከበረው ደሙ አለሙን ሲቀድስ፣ እጆቹና እግሮች በሚስማር ተይዘው☦፣ ልብ ምቱ ደም ዝውውሩ ተዛብተው፣ ለኔ ብሎ ተሰቅሎ መተንፈስ ሲያቅተው፤ እኔ ግን በሰላሙ እወጣለሁ ፣እገባለሁ ፣ እተነፍሳለሁ ልብ ምቴም ጤነኛ ነው። አይኑን አስረው ሲመቱት፣ ግንባሩን በእሾህ ሲያስጨንቁት፣ መስቀል አሸክመው ሲገፉ ሲገፈትሩት ፣ ልብሱን ሲገፉት ፣እርቃኑን ሲያሳዩት፣ያለልክ ገርፈው ቆዳውን ሲያበላሹት ፤ እኔ ግን የፅድቅን አክሊል ደፍቼ ፣ብርሃንን ለብሼ 🧖፣ እንኳን ልመታ ይቅርና ፣ እንኳን ልገፋ ወዜ እያማረ መጣ ድሮ ከነበረው። ውሃ ቢለምን ሆምጣጤ ሲሰጡት ፣የደም ላብ እስኪያልበው ሲጨነቅ፤ እኔ ከሕይወት ውሃ ምንጭ 💧እየጠጣሁ ያለጭንቀት በደስታ ኖራለሁ።🤗 በእርሱ ቁስል እኔ ተፈወስኩ!!! ይህ ብቻ አይደለም እርሱ ተፈፀመ ሲል ፤ እኔ አዲስን ሕይወት ጀመርኩ፣ እርሱ ከአባቱ ሲለይ ፤ እኔ አባት አገኘሁ። ይህ ነው"በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን!" ማለት። “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” — ኢሳይያስ 53፥5 መልካም በዓል !!! @logoschristianschannel @logoschristianschannel @logoschristianschannel
Show all...
ቦታው የኔ ነው የሞተበት❤ #ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዶልናል🤍 @christian_mezmur
Show all...
ቦታው የኔ ነው የሞተበት❤ #ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዶልናል🤍 @christian_mezmur
Show all...
“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” — ሉቃስ 24፥5
Show all...
“ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።” — ኢሳይያስ 1፥18
Show all...