cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

DD M WORLD 🌎 News

DDM ነፃነት ለህዝባችን ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በትላንትናው እለት ከተከሰከሰው የቦይንግ አውሮፕላን እስካሁን በህይወት የተረፉ ሰዎች አልተገኙም ተባለ‼️ በትላንትናው እለት 132 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው የቦይንግ አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ እስካሁን በተደረገ የነፍስ አድን ስራ በህይወት የተገኘ ሰው አለመኖሩ ተዘገበ።የእንግሊዙ ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ የቻይናን መንግስታዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ በተራራማ ስፍራ የደረሰው አደጋው የነፍስ አድን ስራውን አስቸጋሪ ቢያደርገውም እስካሁን በህይወት ያለ ሰው ማግኘት አልተቻለም ብሏል። ቦይንግ 737-800 የተሰኘው አውሮፕላን ከ30 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ መከስከሱን የዘገበው ጋዜጣው፤ በቻይና ከረጅም ጊዜ በኋላ የተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ መሆኑን ገልጿል።የነፍስ አድን ባለሙያዎች ከሰዎች ህይወት ፍለጋ በተጨማሪ የአውሮፕላን መረጃዎችን የሚመዘግበው ‘ብላክ ቦክስ’ን እየፈለጉ ሲሆን የመረጃው መገኘት የአደጋውን መንሳኤ ለማጣራት ባለሙያዎችን እንደሚያግዝ ተስፋ ተደርጎበታል። በአሁኑ ወቅት በቻይና በርካታ በረራዎች እየተሰረዙ ነው ያለው የኢንዲፔንደንት ዘገባ፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን ባለቤት ቻይና ኢስተርን አየር መንገድ የቦይንግን ተመሳሳይ አውሮፕላኖች በሙሉ ከበረራ ውጪ ማድረጉን ገልጿል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ መስጠታቸውም ተሰምቷል።
Show all...
ኢዜማ “ለውጡ በጠበቅነው ልክ አልሄደም”ሲል መንግስትን ተቸ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2010 ዓ.ም በኋላ በኢትዮጵያ መጣ የተባው ፖለቲካዊ “ለውጥ” በተጠበቀው መልኩ እየቀጠለ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (አዜማ) ገለጸ።የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ለውጡ” በብዙ ኃይሎች ጥረት ዕውን ቢሆንም በተጠበቀው ልክ እየሄደ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ከዐልዐይን ያደረጉት ሙሉ ቆይታ: https://am.al-ain.com/article/ezema-says-the-change-the-government-embarked-on-fails-to-keep-going-in-tempo-as-expected
Show all...
ኢዜማ “ለውጡ በጠበቅነው ልክ አልሄደም”ሲል መንግስትን ተቸ

ከመንግስት ጋር መስራት የማንኛውም “ጤነኛ ፓርቲ ባህሪ መሆን አለበት”-የኢዜማ ሊቀመንር የሽዋስ አሰፋ

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ ኝጌሎ በ58 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ አቶ ኦኬሎ ከ1989 እስከ 1995 ዓ.ም ሶስተኛው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ሲሆን÷ ባደረባቸው ህመም ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ኦኬሎ ባለትዳር እና የ 3 ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን÷ የቀብር ስነ ስርአታቸው ዛሬ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት እየተፈፀመ ነው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
Show all...
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ የሚያመቻች የመንግስት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ሳዑዲ አረቢያ መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ዜጎቹን ከረመዳን ጾም መግባት በፊት ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚጀምሩ ገልጿል። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ የሚያመቻችና የሚከታተል የመንግስት ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን ሳዑዲ አረቢያ መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዜጎቹ ከእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን ጾም መግባት በፊት ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚጀምሩ ተናግረዋል። መንግስት በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ለመመለስ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። አምባሳደር ዲና ባለፈው ሳምንት በነበራቸው ሳምንታዊ መግለጫ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ እስካሁን 35 ሺህ ዜጎች መመዝገባቸውንና ተገቢው ማጣራት እየተካሄደ መሆኑን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የመንግሥት የፀጥታ አካላት  የትግራይ ተወላጅ  እሳት ውስጥ ወርውረው መግደላቸውንና ይህም እጅግ እንዳሳዘናቸው በገለጹበት በሰሞኑ ንግግራቸው ላይ የሰጡትን አስተያየት፣ ለአንድ ወገና ያደላና የተሳሳተ ሲል መንግሥት ተቃወመ። ቅዱስ ፓትርያርኩ «ትግራይ ሚዲያ ሀውስ» በተባለው መገናኛ ብዙሀን ባሰሙት ንግግራቸው በ2013 ዓ. ም "ትግሬዎችን ለማጥፋት ፣ የተጀመረው" ያሉት ጦርነት "አሁን በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ተስፋፍቶ በአብዛኛው ቦታ ሁከት ፣ ብጥብጥ ፣ ረሃብና ችግር እየደረሰ ነው" ሲሉ ተናግረው ነበር። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ "ፓትርያርኩ ያቀረቡት ክስ ለአንድ ወገን ያደላ፣ በቁጥር የጠቀሱት መረጃም የተሳሳተ እና ሆን ተብሎ መንግሥት ላይ ጫና ለማሳደር የተደረገ ነው።" ብለዋል። መንግሥት ድርጊታቸውን ሕዝብን ለመከፋፈል ሲባል የተደረገ አድርጎ ያየዋልም ብለዋል ሚኒስትሩ። የፓትርያርኩ ንግግር ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሕዝብ ዘንድ የድጋፍም ፣ የተቃውሞም  ሀሳቦች በስፋት እየተንሸራሸሩ ይገኛል።  Via DW
Show all...