cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ግጥምን ለወንጌል

እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
385Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

# ሽቶ ሰባሪዋ# ፈሪሳዊው ቤትን ተጋብዛ በማታ እራት እንዲመገብ ተጠራና ጌታ ከእራት ግብዣው ሰፈር ሳትጠራ መታ ቀን ላይ ማያውቋት ሚጠሯት ለማታ አብረዋት ቆሽሸው ሚሏት ጋለሞታ ሳትጠራ መታ ውዷን አከበረች ውድ ምትለውን ከእግሩ አፈሰሰች የደስታዋን እንባ በፀጉሯ አበሰች በነሱ እይታ ቆሽሻ ያደፈች ከሰው ሚዛን ወርዳ ርካሽ የሆነች ለእለት ጉርሷ ብላ የምትኖር በሀፍረት ወዳው እንኳ ባይሆን ተዘፍቃ በሀጢአት ይች ሴት ምናልባት ባትገኝ ባትመጣ ከግብዣው ያንን አልባስጥሮስ ከእግሩ ባታፈሰው አክብረው ከጠሩት ክብር ካላገኘ እግሩን የሚያጥብ አንድም ካልተገኘ ከስሮ ይሆን ጌታ ባትሰብር አምጥታ ለሀጢአቷ ስርየት ፍለጋ ባትመጣ ትምህርት ሳያፅፍ ነበር ወይ ሊወጣ? እንደው ከስሮ ይሆን ? ሀጢአቷ ባይሻር ለሷ መዳን ባይሆን ይከስር ይሆን እንዴ ቦታውን ባትቀይር ተከስታ በአንዴ ከስሮ ይሆን ውዴ? ከስሮ ይሆን እንዴ??? ሰባሪዋ ባትደርስ እላለው አንዳንዴ ...... ገጣሚ:-በስዬ
Show all...
.... .. .........ትዝብት-1........... በሱ ገና ሰበብ ንግድ ተጧጡፏል ስጦታም ይሰጣል የገና ዛፍ ብለው ደግሞ ያቆሙታል ታስቦ ሚውለው santa claus ሆኗል አረ ምን ይሻላል ልደትህ ተዛብቷል ሰው ቀኑን እንጂ አንተን ማክበር ትቷል .......... ትዝብት-2......... ብዙዎች ይላሉ የአንድ ሰው ልደት ነው በቀኑ መብላት ነው ጠጥቶ መርካ..ት ሌሎችም ጨምረው ብዙ ነው ሚሉት .......................................... ሌሎች ብቻ አይደሉም እኔም ደግሞ እላለው ሁሉም ሲጨርሱ የሚሉትን ብለው እኔም ቀጠልኩና ድርሻዬን ስናገር አንድ የገባኝ ሚስጥር አንድ የገባኝ ነገር ዳግም ተወልጄ ዳግም ብፈጠር አንተ ሰው ባትሆን ሰው አልሆን ነበር ................ ትዝብት-2............. ሌሎች ደግሞ አሉ አልመጣም የሚሉ ደግሞ እኮ በኩራት አይሁድ ነን ይላሉ ስለ ሙሴ አብርሀም እየተናገሩ እንደምትወለድ ይጠባበቃሉ .................................. . እንደው ባገኛቸው እንዲህ ነው ምለቸው ሙሴና አብርሀም ለማየት የጓጉለት በራዕይ ትንቢታቸው የተናገሩለት ሰባ ሰገል ወድቀው የሰገዱለት ከዘመናት በፊት ነብያት ያዩት ድንቅ መካር ሀያል ብርቱ ነው ያሉት በግርግም ተኝቶ እረኞች ያዩት በማሪያም ክንዶች ታቅፎ ያገኙት የርህራሄ አባት የፍቅር ንጉስ ወደ አለም መቷል ተወልዷል እየሱስ ✍በበሲ ግጥምን ለወንጌል እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ https://t.me/besufikad123
Show all...
ግጥምን ለወንጌል

እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ

#የግጥም_ጊዜ 👉ሳይፀልዩ ማደር🙏😴 የተራበ ነብር 🐆 ከሩቅ ተመልክታ ሚዳቆ 🦌 ፀለየች "አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ ነብሩም 🐆 ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ🙏 የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም ሰማቸው ፈጣሪ አምላክም በድምጹ 🗣 ሚዳቆዋን 🦌 አላት "እሩጠሽ አምልጪ ከበረታው ጠላት።"🦌 🐆ነብሩንም አለው 🗣 "እሩጥ ተከተላት ምግብ 🍖🍗 አድርገህም ብላት" ሚዳቆዋ ስትሮጥ 🦌 ከነብር ለማምለጥ 🐆 ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ ሆዱን ብትረግጠው የተኛ ከርከሮ ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር አውጣኝ ያለው ወጥቶ አብላኝ ያለው በላ ሳይፀልይ ያደረው ከርከሮ 🐿 ተበላ!🙈 መልካም ጊዜ 🙏 ከግጥም ጊዜ የተወሰደ አቅረቢ ግጥምን ለወንጌል እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ https://t.me/besufikad123
Show all...
ግጥምን ለወንጌል

እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ

#ሰውነት ተረሳ-2# ሰው ተረሳ ከሚለው ልነሳ የልቤን ቅሬታ ስሞታዬን ላንሳ ሆነን ቢሆን ኖሮ ኖሮን ቢሆን ኖሮ ትንሽ ሰዋዊነት በኖርን ነበረ ሁላችን ባንድነት በደል - በደል - በደል ሆንን ፍርደ ገምደል ተበዳይ ሲያነባ ሁኖ ጉልበት አልባ በዳዩ ያጋሳል በተበዳይ እንባ በዳዩን መናገር ተበዳይ ቢያቅተው በዳዩ ተበዳይ ሆኖልን አረፈው ከፍርዱ ሸንጎ ፊት ለፍርድ ሊፋጠጡ ከሳሽም ተከሳሽ አብረው ተቀመጡ ተበዳይ ሲያነባ ሲያረገው እንደ እብድ ተበዳይ ሲሳቀቅ በስቃዩ ሲነድ እሚረዱት መስሎት ለሱ ሚፈርዱለት በዳዩ ሳይናገር አንድ እንኳ ከአፉ ዳኛው ወደ ፍርዱ በቶሎ አለፉ ''እሰይ የኔ ጌታ አለ ተበዳዩ ተንሰፈሰፈና ሊሰማ ቀጣዩን'' ዳኛውም ቀጠሉ እኽ - እኽ -እኽ አሉ ''በዛሬው ፍርዳችን በዳይ ከተበዳይ አሁን ለይተናል አሁን በመቀጠል ውሳኔው ይሰማል'' በዚህ ሁሉ መሀል በዳዩም ራሱ የተበዳይ ጨቋኝ ተበዳይም ራሱ ምስኪኑ ተጨቋኝ እስኪሰማ ድረስ የዳኛው ውሳኔ ተሰምቶት ነበረ ተበዳዩ ወኔ ዳኛው ቀጠሉ........ እንደለመደባቸው እኽ - እኽ አሉ ''ተከሳሽ በዳይ ነህ ተባዩ ከሱ ዘንዳ ጥፋት ስላልተገኘበት ይሄ ሸንጎ ሰቶታል ነፃነት'' ''ከሳሽም ተበደልኩኝ ባዩ ያለምንም ጥፋት በሀሰት በመክሰስ ጥፋት ስላጠፋ ራሱ ይከሰስ መዝገቡ ተዘግቶአል መዝገብ ቤት ይመለስ'' በተበዳይ ሁከት እሱ ሚረጋጋ በስቃይ ውጅንብር ተበዳይ ሲጣጋ ስጋው ሲገረፍ በጠኔ አለንጋ ለስጋው ሲዳክር መንፈሱን ሲረሳ በዳዩ...በዳዩ በምቾት ሲያጋሳ ተበዳይ ሲደቅ በአበሳ በበቀል እሳት ለበቀል ሲነሳ . . ክቡሩ ማንነት ሰውነት ተረሳ!!! ✍by:-besi(Ŝőņ ōf ķĩŋğ) ግጥምን ለወንጌል እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ https://t.me/besufikad123
Show all...
ግጥምን ለወንጌል

እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ

# እመለሳለው# ሉቃስ 15 አባቴ እያለኝ እባክህን ልጄ ጥዬ ኮበለልኩኝ ድርሻዬን ወስጄ የውጭውን ኑሮ አለምን ወድጄ ከቤቱ ስወጣ ደስታ ማገኝ መስሎኝ ማሰብ አቅቶኝ ማስተዋል ተስኖኝ መቼ ተጠቀምኩኝ ሁሉ ነገር ጎዳኝ ሀብቴን ጨረስኩኝ ክብሩንም ጣልኩና እርያን መረጥኩኝ ደስታን ለመቃረም ከቤቱ ወጥቼ እንዲሁ ተመለስኩ ሀብቴንም አጥፍቼ አሁን ይሻለኛል ወዳንተ ልመለስ አንተ ጋር ነው እንጂ ሌላው ልብ አያደርስ አንተ ሰላም አለህ እንደወንዝ የሚፈስ አንተ እረፍት አለህ መንፈስን የሚያድስ አባ ይሻለኛል በቤትህ ውስጥ ማደግ ካንተ ሌላ የለም ጌታ የሚታደግ ይቅርታን መጠየቅ ሰልችቶኝ ስታክት እሱ ማይሰለቸው እኔን ይቅር ማለት ለእኔ ለአንዱ እጅጉን ሚጨነቅ በኔ መጎሳቀል እሱ የሚሳቀቅ ሚያስብ ሚጨነቅ ለእኔ ለልጁ ሁሌ እሚጠብቅ መምጣቴን ከደጁ ስመለስ አይቶ ሂድ ብሎ ያልገፋኝ ልጄ ብሎ ያለኝ መቼም የማይተወኝ ከልቡ ሚወደኝ እኔስ አባት አለኝ ቀለበት አምጡለት ልብሱን ቀይሩለት ከጠቦቱም ሁሉ የሰባውን እረዱለት ልጄ መቷልና ሙሉ ነው ደስታዬ አለና አባዬ በፍቅር ተቀበለኝ ፍቅር አሳይቶ ልጄ አይደለህም አላለኝም ከቶ አቅፎ ተቀበለኝ እኔነቴን ናፍቆ ስህተቴን ሳይቆጥር ይቅር የሚለኝ በዘላለም መውደድ አንዴ የወደደኝ ስርቀው ማይርቀኝ ጠልቼው ማይጠላኝ ማይሰለች እማይተው እኔስ አባት አለኝ ከቤቱ ለራቅን መመለስ ይሁንልን ✍by:-besu(ŝőņ ŏf ķĩŋğ) ግጥምን ለወንጌል እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ https://t.me/besufikad123
Show all...
ግጥምን ለወንጌል

እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ

#የሴይጣን ስሞታ# ሴጣን;- ይግባኝ አለኝ ሰው ሚባል ፍጥረት በተንኮል በለጠኝ ክፋቱ በዛና በሁሉ አስናቀኝ የልቡን ስሞታ ሲናገር ሴጣኑ ያሳብቅበታል ከልቡ መሆኑ በሰው ልጅ ተግባሮች እጁጉን ተማሮ ሲያስማ ሮሮ አይ ሰው እእ..... እያለ ቆይ እኔን ሊስተካከል ታዲያ ምን ጎደለ አወይ የሰው ክፋት በተንኮል በሴራ ሆኖልኛል አባት በሀሜት በቅናት ማን ሊደርስበት? ከፍርዱ ወንበር ላይ ራሴን አስቀመጥኩ ከዚያም እንዲህ አልኩ :-አረ ተው ሴጣኑ ክሱን ተወዉና አንተው ቀጥልበት በክፋት ጎዳና ሰውን ለቀቅ አርገው ይመለሳልና ዳኛ ስለነበርኩ;- ሴጣን ሆይ ክስህ ውድቅ ተደርጎአልህ እስኪ አሰማን ስሞታ ካለህ ;-የኔ ክቡር ዳኛ ስለሰጡኝ እድል አመሰግናለው ያለኝንም ይግባኝ ቀጥዬ አቀርባለው ቀጥል ቀጥል;- እናም አቀርባለው ከልቤ ስሞታ ስለ ቀናሁበት ይስጠኝ የሱን ቦታ ለምን እኔ ብቻ ወንጀለኛ ልባል አረ የሰው ተንኮል ይኸው ከኔ ልቋል ;-እኔም ሰማውና የሴጣኑን ይግባኝ ቆርጦ ለመወሰን በጣም ግራ ገባኝ ከዛም እንዲህ አልኩኝ ሰዎች በሚሰሩት ሴጣን ተሳቀቀ አወይ የሰው ክፋት ሴጣንን አስናቀ ✍by:-besye(śőņ ŏf ķĩŋğ) ግጥምን ለወንጌል እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ https://t.me/besufikad123
Show all...
ግጥምን ለወንጌል

እናውራው ወንጌሉን ባለንበት ሁሉ በትልቅ ትንሹ ይሰበክ ቃሉ በሁሉ ይሰማ ይታወቅ ወንጌሉ

Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!