cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Show more
Advertising posts
34 388Subscribers
+1024 hours
+2967 days
+1 90730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሊጉ ተፎካካሪዎች ሚኬል አርቴታ 🤝 ፔፕ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
💯 11👍 5 2👎 1
🇬🇧 29 ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች                     የጨዋታ አጋማሽ ውጤት '        🇬🇧 ኤቨርተን 1-0 ሊቨርፑል 🇬🇧       🇬🇧  ማን ዩናይትድ 1-1 ሼፊልድ 🇬🇧      🇬🇧 ክሪስታል ፓላስ 0-0 ኒውካስትል 🇬🇧         ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio                        #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
ዘ-ሪፖርተር ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ ፍፁም የተሳሳተ ነው - የትግራይ ጄኖሳይድ ኮምሽን ሰሞኑን ዘ-ሪፖርተር ጋዜጣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑት አቶ የማነ ዘርአይን በመጥቀስ የሰራውን ዘገባ በመቃወም ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ሪፖርተር ጋዜጣ የኢንግሊዘኛው እትም " የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ከፌደራል መንግስቱ እውቅና ተሰጠው" ፣ "የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ከፌደራል መንግስትና ከዓለም ባንክ ጋር በትብብር መስራት መጀመሩን ገለፀ" በማለት የተሰራጩት ዘገባዎችን ነው ሓሰተኛና ከእውነት የራቁ ሲል ኮሚሽኑ የገለፃቸው። አያይዞም ከፌደራል መንግስቱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግኑኙነት ኖሮት እንዲሰራ እሚጠበቀው በጊዝያዊ አስተዳደሩ ስር እሚገኘው የዳግም ግምባታ ፅህፈት ቤት ነው በዛ መሰረትም ከዓለም ባንክና ከገንዘብ ሚኒስተር ጋር አብሮ እየሰራ ነው ብሏል። እኛ እዚህ ላይ ማድረግ እሚጠበቅብን አስፈላጊ መረጃዎችንና ግኝቶችን ለፅሕፈት ቤቱ ማቅረብ ዠና ቴክኒካዊ እገዛ ማድረግ ነው እሱንም እየሰራን ነው ከዚህ ውጭ ግን የኮሚሽኑ በስልጣንም ሆነ ቅርፅ አልተቀየረም ሲል በመግለጫው አስታውቋል። አያይዞም ኮሚሽኑ ዘ-ሪፖርተር በሰራው ዘገባ ላይ ኮሚሽኑ ህግ ነክ የሆኑ ፆታዊ ጥቃትን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰት የተመለከቱ ግኝቶች ከሪፖርቱ እንደቀነሳቸው ተደርጎ የተዘገውም ፍፁም ስህተትና እርማት እሚያሰፈልገው ነው ሲል ገልፆታል። ኮሚሽኑ በሰሜን ኢትዮጲያ ጦርነት መካከል በ2014 ዓ/ም በይፋ የተመሰረተ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው አካላት በጥናት በመለየት ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም ግኝቶቹን እንደመነሻነት በመጠቀም ለዳግመ ግንባታ ስራዎች ግብአት እንዲሆኑ አለሞ በመስራቶ ላይ ያለ እንደሆነ ተነግራል።
Show all...
👍 1👏 1
ከኢትዮጵያ ከ 350 በላይ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ በተያዘዉ 2016 ዓመት ሰኔ ወር 4ሺ6 መቶ 8 ስደተኞች ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አይ ኦ ኤም አስታውቋል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ እንደሚያሳያው ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር እና በመተባበር በኢትዮጵያ የሚገኙ የሶስተኛ ሀገር ስደተኛ ዜጎች ወደ አደጉ ሀገራት የማሸገር ስራ ይሰራሉ፡፡ አይኦኤም በመልሶ ማቋቋሚያ ስር  ውስጥ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲደርሱ ለማድረግ ተከታታይ የቻርተር በረራ እንቅስቃሴዎችን እና እንዲሁም በንግድ አየር መንገዶች ላይ የቡድን ምዝገባዎችን ያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የዩናይትድ ስቴትስን የ2024 የስደተኞች መጤ ግብ ለማሳካት የስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ስራ እያሰፋ ይገኛል።ዩናይትድ ስቴትስ በ2024 ከ4ሺ500 በላይ ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል ቃል መግባቱን አይኦኤም አስታውቋል፡፡ ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ ብቻ አይኦኤም ከ1.19 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እና ሌሎች ስጋት ያለባቸውን በአለም ዙሪያ ካሉ 166 አካባቢዎች የመቋቋሚያ እንቅስቃሴዎችን አዘጋጅቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።በ2023 አይኦኤም 5ሺ3 መቶ4 ስደተኞችን ኢትዮጵያ አስፍሯል። ከእነዚህ ውስጥ 1ሺ1መቶ 94ቱ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል። በትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 22 4👎 1
ቻይናዊው የ88 ዓመት አዛውንት ጥንካሬያቸውን እንደጠበቁ በሞዴሊንግ ኢንዱስትሪው ላይ ተፅእኖ መፍጠር መቀጠላቸው ተሰማ ዋንግ ደሹን የሚባሉት አዛውንት እ.ኤ.አ በ2015 በቻይና ፋሽን ሳምንት በቤጂንግ በተካሄደው የመጀመሪያ የሞዴሊንግ ስራቸው ላይ ከታዩ ወዲህ 88ኛ ዓመታቸው ላይ እስኪደርሱ ድረስ በስኬት መቀጠላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። በቻይና የፋሽን ሳምንት በ79 ዓመታቸው ብቅ ካሉ ወዲህ በሁሉም ሰው አእምሮ ውስጥ መቅረት ችለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ደግሞ በዓለም ላይ ካሉ ታላልቅ የፋሽን ተቋማት የአብረን እንስራ ጥያቄ እየቀረበላቸው ቀጥለዋል።እ.ኤ.አ በ 1936 መካከለኛ ገቢ ካላቸው እና ዘመናዊ ከሆነ ቤተሰብ ውስጥ የተወለዱት ዋንግ ዱሹን አስር ልጆች ላሉበት ቤተሰብ ሁለተኛ ትልቁ ልጅ ነበሩ። ወላጆቻቸው ህልሜን እንድከተል ያበረታቱኝ ነበር ሲሉ አዛውንቱ ይናገራሉ። ተዋናይ ሆነው ሰርተዋል በበርካታ የጥበብ ስራዎች ቢሳተፉም በፋሽን ሞዴሊንግ ላይ ግን የሚያስደንቅ ስኬት ላይ ደርሰዋል። እውቅናቸውን ተከትሎ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ ማግኘትን ጨምሮ ሞተር ሳይክልና ፈረስ መንዳት ተምረዋል።ሰዎች በፈለጉት  ጊዜ ህይወታቸውን ለመለወጥ አቅም አላቸው ሲሉ ዋንግ ለታይምስ ተናግረዋል። በአእምሮ ጤናማ መሆን ማለት ምን ማድረግ እንዳለብህ ታውቃሉ ማለት ነው። ህልምህን ለመከታተል ዕድሜ በጭራሽ እንቅፋት ሆኖ አያውቅም ሲሉ ይደመጣሉ። ዋንግ ደሹን ወደ ፋሽን ሞዴሊንግ ኢንዱስትሪ የገቡት ስህተት በሆነ አጋጠሚ ነው። ቻይናዊቷ ዲዛይነር ሁ ሸጉዋንግ ከቻይና ፋሽን ሳምንት አዘጋጅ ዲጄ ጋር እየተጋገረች ነበር፣ በዚህ ውይይት ላይ ሌላ ኪው ኪው የምትባል ሴት በድንገት ስልኳ ይጠራል። ምላሽ ለመስጠት ለመስጠት ስልኳን ስታነሳ ስክሪኑ ላይ የአንድ አዛውንት ፎቶ ከወገብ በላይ ራቁታቸውን ሆነው ይታያሉ።ይህንን ምስል ደግሞ ዲዛይነሯ በድንገት ትመለከተዋለች እኚህ አዛውንት ደግሞ የኪውኪው አባት ዋንግ ነበሩ። ዲዛይነሯ እኚህ ሰው በፕሮግራሙ ላይ እንዲገኙ እፈልጋለው በማለቷ ስራውን ጀምረዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለተለያዩ ፋሽን ዲዛይነሮች በበርካታ ማስታወቂያዎች ላይ ኮከብ ሆነዋል ።ዋንግ ደሹን አሁንም በ88 ዓመታቸው ጠንካራ ሲሆኑ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሻንጋይ ፋሽን ሳምንት ደምቀው ታይተዋል።አብዛኞቹ በ30ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጡረታ በሚወጡበት የሞዴሊንግ ዘርፍ፣ ዋንግ ደሹን በህይወታቸው ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ስኬታቸውን ካገኙ ጥቂት ሞዴሎች መካከል አንዱ ሲሆኑ እንደ ካርመን ዴል ኦሬፊስ፣ የአለማችን አንጋፋ የፋሽን ሞዴል እና ከሌላኛዋ የእስያ አንጋፋ ሞዴል አሊስ ፓንግ ተርታ ተመድበዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 22 3👏 3😁 1
ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አስጀመረ ብሔራዊ መታወቂያ ዜጎች ታማኝነት ያለው መለያ እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ዲጂታል  መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን የሚፈጥር እንደሆነ የተናገሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዲጂታል መታወቂያው በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሁሉም ተሳታፊ እንዲሆን ያደርጋል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ሰምቷል። ሀገራት ለዜጎቻቸው ታማኝነት እና እውቅና ያለው መለያ የመስጠት ግዴታ አለባቸው። መለያዎቹ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ ነዋሪዎች እኩል አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል። የንግድ ተቋማትም መለያውን መሰረት አድርገው አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።እንዲሁም ለኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርግ እንደሆነ እና በርካታ ችግሮችን ለመፍታት እድሎችን የሚፈጥር መሆኑን ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
10👎 8👍 4🔥 1👏 1
የግለሰብ መኖሪያ ተደርምሶ ከሞቱ 7 ሰዎች  መካከል የአራት አመት ህፃን መኖሩ ተነገረ 👉🏼 በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራ አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት ቢተርፉም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን አጥተዋል በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራም አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት እንዲተርፉ ቢያደርጋቸውም በቤት ውስጥ ተኝተው ትተዋቸው በሄዱበት አጋጣሚ ሚስታቸውን እና ቤተሰባቸው የግንባታው እቃ ተደርምሶ እንደሞቱባቸው አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ዛሬ በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ጠሮ መስኪድ አካባቢ ለሊት 11:00 ሰዓት ላይ እየተገነባ ያለ የግለሰብ ቤት የግንባታ እቃ ተደርምሶ የ7ሰዎች ህይወት ማለፉን ብስራት መዘገቡ ይታወሳል። በአደጋው ከሞቱት ሰባት ሰዎች ውስጥ አራቱ ሴቶች ሲሆኑ የ28 ፤የ25 ፤የ12 አና የ11 ዓመት መሆናቸው አቶ ንጋቱ የተናገሩ ሲሆን ከሞቱት መሀከል የ30 የ12 እና የአራት አመት እድሜ ያላቸው ወንዶች ህይወታቸውን አተዋል። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
😢 28👍 8💔 2 1
በጎርፍ የተከበበውን ኬንያዊ ህፃን በአስደናቂ ሁኔታ መታደግ መቻሉ ተነገረ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ያታ ከተማ በጎርፍ ለብቻው የታገተው የአምስት አመት ልጅ በፖሊስ ሄሊኮፕተር ህይወቱን መታደግ ተችሏል። የህፃኑ ልጅ "የውሃው መጠን መጨመር ሲጀምር ወላጅ አባቱ ጥለውት መሄዳቸውን" ፖሊስ ተናግሯል። የልጁን ቦታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም የተቆጣጠረው አለማቀፉ የሰብአዊ እርዳታ በጎ አድራጎት ሴንተር ለፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን ሄሊኮፕተሩን ከናይሮቢ በመላክ የነፍስ አድን ስራው ተግባራዊ ሆኗል። ህፃኑን በጀልባ ለማዳን የተደረገው የመጀመሪያ ሙከራ ምቹ ባልሆነ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል። አክለውም “ሕፃኑ ለረጅም ጊዜ በጎርፉ ተከቦ በመቆየቱ የነፍስ አድን ስራው ከተከናወነ በኃላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዷል። ከቀናት በፊት በኬንያ እና በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እና  ውድመት አስከትሏል። በኬንያ የጎርፍ አደጋው በ 23 የሀገሪቱ 47 አውራጃዎች ተመዝግቧል ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን በጎርፍ እንዲከበቡ ምክንያት ሆኗል። የጎርፍ አደጋ ከተከሰተ ውዲህ ከ188 በላይ ሰዎች መታደጉን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል። የጎርፍ አደጋው ተከትሎ 11 ሺ 2 መቶ 6 አባወራዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ሲያፈናቅል 27 ሺ 7 መቶ 16 ሄክታር መሬት ውሰጥ የነበረ ምርትን አውድሟል።ከ4,800 በላይ የቤት እንስሳትን መሞታቸውንም የኬንያ ቀይ መስቀል ይፋ አድርጓል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 15 4👏 2🥰 1😢 1