cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ ልጆች

ተግተን እንጸልይ ወደ ፈተና እንዳገባ ንስሐ እንግባ እንቁረብ ወንድም እህቶቼ https://telegram.me/ortodoxs_lijoch

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
187Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰሙን ‹ሰመነ – ስምንት አደረገ› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲኾን ትርጕሙም ሳምንት፣ ስምንት ማለት ነው፡፡ ‹ሕማማት› ቃሉ ‹ሐመ – ታመመ› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም ብዙ ሕማምን ያመላክታል፡፡ ‹ሰሙነ ሕማማት› ስንልም ‹የሕማም ሳምንት› ማለታችን ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ዅሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ለማውጣት ሲል የተቀበለውን መከራ የምናስብበት ወቅት ነው፡፡ መቼ ይጀምራል መቼስ ያበቃል?❓❓ 👇 ሰሙነ ሕማማት ከዕለተ ሆሣዕና ሠርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኵነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፤ የሚያለቅሱበት፤ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው እግዚአብሔርን የሚማጸኑበት፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት፤ ኃጢአታቸውን ለካህን የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ልዩ ሳምንት ነው፡፡ ለየት የሚያረገው ነገር ምንድነው ?❓ በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልዕት (የምግብ ዓይነቶች) አይበሉም፤ ይልቁን በመራብ፣ በመጠማት፣ በመውጣት፣ በመውረድ፣ በመስገድ፣ በመጸለይ፣ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራ በማሰብ ወቅቱን እናሳልፋለን፡፡ በዚህ ሳምንት የማይፈቀዱ ሥርዓቶች ምን ምን ናቸው❓❓ በዚህ ሳምንት አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን፣ ሕማሙን፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ቅዱሳት መጻሕፍት በየሰዓቱ ይነበባሉ፡፡ በዚህ ሳምንት መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም ‹‹እግዚአብሔር ይፍታህ›› አይሉም፡፡ ሥርዓተ ፍትሐት አይደረግም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመኾኑ ነው፡፡ ዲያቆኑ ቃጭል የሚያቃጭለው ለምንድነው ? ምሳሌውስ?🔔🔔🔔 በዕለተ ምጽአት መላእክት የሚያሰሙትን የመለከት ድምፅ፤ በዚያች ሰዓት ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ከሞት እንደሚነሡ ለማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡
Show all...
​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው ከነገ ጀምሮ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ። 👉 በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው። እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋ የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን። የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን። ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን። ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን። ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን። 👉 በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳኛት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው። በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና።
Show all...
🔔 ✞✞✞ ሰሙነ ሕማማት ✞✞✞ 🔔 (ከዕለተ ሰኑይ እስከ ቀዳሚት ሰንበት) ✒ መግቢያ 📚 ከአባታችን አዳም በደል ወይም ስሕተት በኋላ በሕማማት፣ በደዌያት፣ በመቅሠፍታት፣ ወዘተ በብዙ መከራ የሰው ልጅ ሊኖርባቸው ግድ የኾነባቸው ዘመናት ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ የሰው ልጅ ቢያጠፋ፣ ቢበድል፣ ከሕገ እግዚአብሔር ቢወጣ እንኳን የዋህ፣ ታጋሽ፣ ቸር፣ አዛኝ የኾነው አምላክ የጠፋውን ሊፈልግ፣ የተራበውን ሊያጠግብ የታረዘውን ሊያለብስ፣ ፍቅር ላጣው ፍጹም ፍቅር ሊለግስ፣ ሰላም ለሌለው ፍጹም ሰላም ሊሰጥ፣ ተስፋ ለሌለው ተስፋ ሊያጐናጽፍ ከሰማይ ወረደ፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ ቀንና ሌሊት ጾመ፡፡ በጾሙም የኀጢአት ሥሮች ወይም ራሶች የተባሉትን ስስትን፣ ትዕቢትንና ፍቅረ ንዋይን ድል አደረገልን፡፡ እኛ እርሱ የጾመውን ጾም እንድናከብር እንድንጾም ምሳሌ ኾነን፡፡ ዲያብሎስን ድል አድርጐ ድል እንድንነሣው ኃይልና ምሳሌ ኾነን፡፡ ✒ ሰሙነ ሕማማት ምንድን ነው? 📌 ‹ሰሙን› – ‹‹ሰመነ ስምንት (ሳምንት) አደረገ›› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከዕለተ ሆሣዕና ሠርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ‹ሕማም (ሕማማት)› – ‹ሐመ ታመመ› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ይህም የሰውን ዘር ዂሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኵነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት፤ ኀጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልዕት አይበሉም፤ ይልቁን በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን፣ ሕማሙን፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት፣ ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡ መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም ‹‹እግዚአብሔር ይፍታህ›› አይሉም፡፡ ሥርዓተ ፍትሐት አይፈጸምም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመኾኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምፅ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መኾናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡
Show all...
#ሰሙነ_ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ #ሰኞ #መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። #አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። #ማክሰኞ #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። #የትምህርት_ቀን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። #ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። #የእንባ_ቀን_ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። #ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። #ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። #ቅዳሜ #ቀዳም_ስዑር_ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። #ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። #ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። (ስምዐ ጽድቅ መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም)
Show all...
ክርስቲያን ሆይ፦ ሊነበብ የሚገባ ሰሞነኛ ጦማዕር ©በዲያቆን ዶክተር ኢያሱ አልቃሻ አትሁን እባክህ! ብዙ መከራዎች እየደረሱብህ እንደኾነ ይታወቃል፤ እርሱን ለአምላክህ ሂድና ንገረው። ከቻልክ በመንበሩ ፊት ተደፍተህ አልቅስ። እንደጴጥሮስ አልቅስ፣ እንደ ዳዊት አልቅስ፣ እንደ አዳም አልቅስ። የሚሰማ አምላክ አለህና ወደ አምላክህ አልቅስ። እዚህ ፌስቡክ ላይ ግን አታልቅስ። ያንተን ችግርና መከራ ለማስታገስ የተቋቋመ ፌስቡክ የሚባል ድርጅት የለም። ወደመንግሥትም አታልቅስ፣ የክርስቲያንን ዕንባ ለማስቆም የሚሰራ መንግሥት የለም። ይህንን ቀድመህ አልሰራህማ! አሁንም ያንን መስራት ረትፈልግም፣ ነገ ከዚህ ሊብስ እንደሚችል እንኳን በቅጡ መገንዘብህን እንጃ! ፖለቲካን እንደአገልግሎት ሳይሆን እንደነውር ትቆጥራለህ፣ ኃጢአት ነው እያልክ ቤተክርስቲያን ያላስተማረችህን ትሰብካለህ። በስንፍናህ ምክንያት በአማሌቃውያን ሠይፍ ስትታረድ እራስህን እንደሰማዕት ትቆጥራለህ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ተኝቶ አልታረደም፣ ፋሲለደስም፣ መርቆሬዎስም፣ አርሴማም፣ እስጢፋኖስም፣ ገብረክርስቶስም በስንፍና ተጠፍረውና እቤታቸው ተኝተው አልታረዱም፤ አንተ ግን ለአራጆችህ እራስህን አዘጋጅተህ እየሰጠህ የቂርቆስ ተከታይ እንደኾንክ ታስባለህ። ክርስቲያን ሆይ፦ ፖለቲካን ስትጠየፍ መስቀልን በአንድ እጃቸው፣ በትረ መንግሥትን ደግሞ በሌላ እጃቸው ይዘው አገርን ለዘመናት ካስተዳደሩ ከነቅዱስ ላሊበላ፣ ከነቅዱስ ነአኵቶ ለአብ፣ ከነይምርሃነ ክርስቶስ፣ ከነ ገብረማርያም የተሻልኩ ነኝ ብለህ እየታበይክ መሆኑን እንኳን አለመገንዘብህ ያሳዝናል። የላሊበላ ልጅ ነኝ ትላለህ፣ ግን ሓላፊነትን ዛሬ ተረክበህ መቃድሱን ለማሳደስ አትፈልግም፣ የፈረንሳይ መንግሥት ቤተ ጊዮርጊስ መቅደስ ገብቶ እንዲያድስልህ ትመኛለህ። ክርስቲያን ሆይ፦ ወታደር ኾነህ፣ የወታደር አዛዥ ኾነህ ቤተክርስቲያንን መጠበቅና ማስጠበቅ አትወድም፣ ግን ካህን በቅዳሴ መሐል ታረደ የካህን ደም ፈሰሰ እያልክ ፌስቡክ ላይ ታለቅሳለህ። በሆሳዕና፣ በስልጤ፣ በደብረዘይት የጥምቀት በአል፣ የመስቀል በአል ተከለከለ እያልክ ብዙ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ትለጥፋለህ፤ አንተ ግን የሆሳዕና፣ የደብረዘይት፣ የወራቤ ከተሞች ከንቲባ ኾነህ የሕዝብህን ደስታ በእጅህ መስራት አትፈልግም። ክርስቲያን ሆይ፦ ግብረሰዶማዊነት በኢትዮጵያ መፈቀድም መስፋፋትም የለበትም እያልክ ትቃወማለህ፤ ግን የተቃወምከው ነገር ሕጋዊ ኾኖ ከአንድ ወር በኋላ ታገኘዋለህ። እራስህ ያንን ዕድል ተጠቅመህ የማትፈልገውን ለማስቆም ቆርጠህ አልተነሣህማ! መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንዳይገባ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን እንዲያከብር ትፈልጋለህ፤ ግን ፍላጎት ብቻ ነው። ቅርስ እንዲከበር፣ የኢትዮጵያ ነባር ጥበብ ተመልሶ እንዲመጣ ትፈልጋለህ። የኑሮ ውድነት ቁጥጥር እንዲደረግበት፣ የተማረ ስራ እንዲያገኝ ትፈልጋለህ። ክርስቲያን ሆይ፦ ዘረኝነት፣ መከፋፈል፣ ጎጠኝነት እንዲጠፋ ትፈልጋለህ። ይህም ፍላጎት ብቻ ነው፣ ተነሥተህ አትሰራማ። ኹልጊዜም አሸናፊዎችን ለመከተል ተዘጋጅተህ ትጠብቃለህ እንጂ አንተ እራስህ አሸናፊ ለመኾን አልቆረጥክም። ልክ እንደሌሎቹ አስመሳይ መኾን ጀምረሃል። ለምትሰራውና ለምታደርገው ሓላፊነትን መውሰድ ትተሃል። ሓላፊነትን ወስደህ ወቀሳውንም ምስጋናቸውንም ለመቀበል ዝግጁ አይደለህም። ተደብቀህ ታነብባለህ፣ ስምህን ቀይረህ ትጽፋለህ፣ ብዙዎች ባመኑበት ላይ ትክክል ባይሆን እንኳን ታምናለህ። ብዙ ሰዎች ሼር ያደረጉትን ሼር ታደርጋለህ፣ አስተያየት የሰጡበትን አስተያየት ትሰጣለህ። ክርስቲያን ሆይ፦ ፌስቡክ ላይ ኹለት መስመር ስለጻፍክ መተከል ላይ ለታረዱ ካህናት ልቅሶ የደረስክ ያህል የሚሰማህ እስከመቼ ነው? የተላከልህን ፎቶ መልሰህ በመላክህ ለወገንህ አድዋ ላይ ድል የነሣህለት ያህል የምትረካውና ኵራት የሚሰማህ እስከመቼ ነው? ንገረኝ እስኪ ፌስቡክ ላይ ዋይ ዋይ ብለህ ችግርህን የፈታኸው የሚመስልህ እስከመቼ ነው? በተደበቀ ስም ፌስቡክ ላይ ተሳድበህ ገብተህ እግርህን ታጥበህና አፍህን ተጉመጥምጠህ ወደ አልጋህ የምትሮጠው እስከመቼ ነው? አሁን አንተ የአሉላ አባነጋ ልጅ ነህ? የሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ልጅ ነህ? የዳርሳሞ ኬሮ ልጅ ነህ፣ የአብርሃ ወአጽብሃ ልጅ ነህ? የበላይ ዘለቀ ልጅ ነህ? አንቺ የጣይቹ ልጅ ነሽ? የመስቀል ክብራ ልጅ ነሽ? የቃቄ ወርድወት ልጅ ነሽ? አዎን ብትዪኝ አላምንሽም! ክርስቲያን ሆይ፦ አንዳንዴ እንደገዳማውያን ያደርግሃል። ገዳማዊ በኾንክ በምን ዕድላችን! ከሰብአ ዓለም የከፋ ሕይወት እየኖርክ ስራ ላለመስራት እራስህን ገዳም እንደዘጋ ስትቆጥር ምን ይሰማሃል? ኹሉንም ነነር በጸሎቴ እፈታዋለሁ፣ ስራ አልሰራም ብለህ እንዴት ታስባለህ? ክርስቲያን ሆይ የገዛ ወገንህ ላይ የሚደሥሰው ኹሉ እንዳይሰማህ ምን ተደርጎብሃል? ስሜታዊ ኾነህ ላንድ ቀን ስትጮህ ውለህ ወዲያው እንድትረሳው ምን ተደርጎብሃል? ወዲያው ተበሳጭተህ ወዲያው እንድትረካ ምን ተሰርቶብሃል? ክርስቲያን ሆይ፣ ምክርን የማትሰማ ኹሉንም ነገር አውቃለሁ የምትል ኾነሃል፣ ስለቤተክርስቲያንህ የሚነግርህን ለሌላ መጥፎ አላማ እንደሚቀሰቅስህ መቁጠርና ታዝበህ ማለፍ ለምደሃል። ማጽደቅና መኰነንን ታውቃለህ፤ ተከራክረህ ማሸነፍን ታውቃለህ - ያው መከረኛ ፌስቡክ ላይ። ለሚያርዱህ መሟገት ታውቃለህ። ክርስቲያን ሆይ ማደንዘዣ ተወግተሃል እንዴ? ካልሆነ ተነሣና ዘወር ዘወር በል፣ የቤተክርስቲያንን አጥሯ፣ ቤተልሔሟ፣ ደጀሰላሟ እንዴት እንደኾነ አየት አየት አድርግ። በቃ አታልቅስ! ኢያሱ አንጋኒ መጋቢት ፲፪/፳፻፲፫ ዓ.ም. አዲስ አአበባ
Show all...