cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Zehabesha

Ethiopian News

Show more
Advertising posts
60 178Subscribers
+4024 hours
+2757 days
+83530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ የሴቶችን የውስጥ ሱሪ (ፓንት) በኦንላይን እየለጠፉ ይጫወታሉ ሲል ሬውተርስ ዘግቧል።
Show all...
😁 11🤬 7😱 3👍 1😭 1
ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳወቀ::
Show all...
5🤮 5
ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰታወቀ።
Show all...
🤔 11👍 4😱 3🤮 3
Show all...
Ethiopia: አሁን የደረሱን መረጃዎች | ዘ ኢትዮጵያ | The Ethiopia News NOW March 28, 2024

The Ethiopia News and Views Ethiopia: ዘ ኢትዮጵያ የዕለቱ ዜና | The Ethiopia Daily Ethiopia News March 28, 2024

😁 7👍 2 2
የምዕራብ ሸዋ ዞን ለቴራ ቀና የተባለው ግለሰብ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የ90 ዓመት ኣዛውንት በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ባሉበት ቤታቸውን ሰብሮ በመግባት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እንደፈጸመ ፖሊስ በህክምና ማስረጃ መረጋገጡን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ገልጧል፡፡ዓቃቢ ህግ ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልከቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲመለከት የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ለቴራ ቀና በ8 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ሠጥቷል።
Show all...
😡 17😱 6👍 2
ምዕራብ አርሲ : የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ በምዕራብ አርሲ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። የሰሌዳ ቁጥሩ "ET A07629" የሆነ ተሽከርካሪ ከአዳባ ወደ ሃንጌቱ እየተጓዘ ኤጀርሳ ጪሊሞ በተባለ ስፍራ ምሽት 2:00 ሰዓት አደጋው ያጋጠመው ተብሏል። የምዕራብ አርሲ ዞን ትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ከማል አማን እንዳሉት፤ አደጋው የደረሰው ከጉብሳ ወደ አዳባ እህል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ በመገልበጡ ነው። በአደጋው ሹፌሩ፣ ረዳቱን እና ከላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል።
Show all...
😢 18👍 5 1
👍 25👎 20🤮 10 6😁 6
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሠጠ መግለጫ! የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ምላሽ ሰጥቷል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ላይ ትንኮሳ መጀመሩንም አስታውቋል። የመግለጫው ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል፦ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል፡፡ ጊዜያዊ አሥተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ሥርዓትን በማጣቀስ የተሳሳተ ካርታ ተሠርቷል ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳች እና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ በመኾኑ እና በትናንትናው እለት ማለትም መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደል እና በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ ስለኾነም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መግለጫ መስጠት ተገቢ ኾኖ አግኝቶታል፡፡ ጊዜያዊ አሥተዳደሩ የአማራ ክልል የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍ ውስጥ የተሳሳተ ካርታ ተሠርቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ሊያመላክታቸው የተፈለጉት አካባቢዎች ካለፉት 30 ዓመታት በፊት ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያሉባቸው ወረዳዎች የማንነት እና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን ሲያቀርቡባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ መኾኑ ግልጽ ነው፡፡ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በተስተዋሉት የአሥተዳደራዊ መዋቅሮች እና አደረጃጀት ቅመራ ጅማሬ አንስቶ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸሙ ምክንያት ጦርነት እስከተቀሰቀሰበት ጊዜ ድረስ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መኾኑን በበርካታ ታሪካዊ ሁነቶችና ተጨባጭ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ ሕዝቦች እና አካባቢዎችን ለበርካታ ዘመናት በኃይል ሲገዛ የነበው የቀድሞው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ላነሱት ታሪካዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች ሕጋዊ አሠራርን የተከተለ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የአካባበው ተወላጆችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የማንነትና የአሥተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎችን በማሰር፣ በማሰደድ እና በመግደል የሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እስከ ሰሜኑ የሕግ ማስከበር ጊዜ ድረስ እንዲገፋ አድርጎታል፡፡ የማንነት እና የአሥተዳደር መብት ዙሪያ ላነሳቸው ጥቄዎች የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ትግል በተፋፋመበትና ከፍተኛ መሥዋዕትነት ጭምር እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ህወሓት የሠሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን አሰቃቂ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት ለሁለት ዓመታት የቆየ የሕግ ማስከበር እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ የማንነትና የአሥተዳደር ጥያቄዎቹ ለዘመናት የታፈኑበት ሕዝብም ከማዕከላዊው መንግሥት ጎን ተሰልፎ በህ.ወ.ሓ.ት የክህደት ተግባር በኢትዮጵያ ሕልውና እና ሉአላዊነትት ላይ የተጋረጠውን ግልጽ አደጋ እንዲቀለበስ የበኩሉን አስተዋጽዖ ከማበርከቱ ባሻገር በሂደቱ ህወሓት በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረውን የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማሥተዳደር ነጻነት የተቀዳጁበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በዚህም ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ሕዝብ እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል በመኾኑ በቀድሞው የህ.ወ.ኃ.ት እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት መካከል የፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም በትምህርቱም መስክ ተጠቃሚ እንዲኾኑ አድርጓል፡፡ አካባቢዎቹን በተመለከተ የነበረው፣ ያለው እና የሚኖረው እውነታ ይሄ ኾኖ ሳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በሥራ ላይ የዋሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማራ መብታቸው እንዲከበር የአማራ ክልል መንግሥት ግዴታውን መወጣቱን ሰበብ በማድረግ በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መኾኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ ማውጣቱ ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ የተፈጠሩ ችግሮችን በሕግ አግባብ እንዲፈታ እየተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ክልል መንግሥት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ በሕዝብ መጎሳቆልና በወጣቶች እልቂት ትምህርት አለመወሰዱና የተለመደ ትንኮሳ በማድረግ ላይ መኾኑ እጅጉን አሳዝኖናል፡፡ ስለሆነም የትግራይ ክልል ግዜያዊ አሥተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ፣ ሀገራችንንና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የሕዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላም እና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መጋቢት18-2016 ዓ/ም ባሕር ዳር
Show all...
👍 50👎 8 5🤮 5😁 2
💩 1
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!