cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማኞች

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Question_Onley_Me You tube channel https://youtube.com/channel/UCQX7u78nbZUEfZchAsudWPw

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
316Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን 😭
Show all...
​​​​👉 ቅዳሜ ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo
Show all...
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞• አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2) በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2) ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ #አዝ••• ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ #አዝ••• በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ #አዝ••• ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ #አዝ••• የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo
Show all...
#​​​​ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) የዘንባባ ዝንጣፊ፡- 👉 ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ 👉 ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው( 👉 ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው 👉 ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው 👉 ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው 👉 ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። 👉 የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡- 👉 የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ 👉 የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ ከመጣብን መቅሰፍት መከራ እሱ በሀይል በስልጣኑ ይሰውረን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን። @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo
Show all...
​​​​ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) የዘንባባ ዝንጣፊ፡- 👉 ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ 👉 ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው( 👉 ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው 👉 ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው 👉 ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው 👉 ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። 👉 የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡- 👉 የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ 👉 የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። 👉 በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ ከመጣብን መቅሰፍት መከራ እሱ በሀይል በስልጣኑ ይሰውረን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን። @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo
Show all...
ርግብና ዋኔን ርግብና ዋኔን አብረዉ ዘመቱና ዋኔን ርግብ ደህና ገባች >> /2/ ዋኔን ገደሉና >> /2/ በዘርና ጎሳ ዋኔን ሠዉ ሁሉ ተከፍሎ >> ሰይፍንም ጨበጠ >> ልቦናዉ ቂም አዝሎ>> ሰላምን የሚያወርድ >> እንድ የሚያረገንን >> እባክህን አምላክ >> ሙሴን አድለን >> ሠላምህን አብዛ ምድሪቷን አሳርፍ የቅዱሳን አምላክ በጭንቃችን ድርስ /2/ በወገን ላይ ወገን ዋኔን ይብቃ መነሳቱ >> ይስፈን በምድር ላይ >> የእግዚአብሔር መንግስቱ >> ጦራችን ይሰቀል >> እንያዝ በገና >> ሠላምን እናዚም >> በፍቅር እንፅና >> ምድሪቷን አሳርፍ ሰላምህም ይብዛ በአንድነት አኑረን የአለሙ ቤዛ /2/ የመርገም ጨርቅ ሆነ ዋኔን ፅድቃችን በሙሉ >> አንተን ያልበደለ >> ማነዉ በዘመኑ>> አማነዉ በማታ >> ቀን ያከበርነዉን >> የኛ ስራ ሆኗል >> መክሰስ የበቃው >> ፍቅር ባትሆን ኖሮ ባያቅትህ መጥላት አይታይም ነበር የሰዉ ልጅ በህይወት ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሳሙኤል @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo
Show all...
2/07/2014 ዓ.ም ✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ሮሜ. ፯፥፩ - ፲፪፤ ፩ ዮሐ. ፬፥፲፰ - ፍ፤ ግብ ሐዋ. ፭፥፴፬ - ፍ፤ የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ ፲፮፥፫ ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፤ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው። ትርጉም፦ በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቤንም ፈተንኸው፤ ፈተንኸኝ ዓመፅ አልተገኘብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር። የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፫፥፩ - ፲፪ ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo @ethiopian_orthodoxtewahedo
Show all...