cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

📢 ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ገዳማት ስርዓት ፣አሁናዊ ዜና እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ፡ ቅዱሳን መካናት እና ገዳማት ታሪክ 📢 የቅዱሳን ገድላት 📢 ቅዱሳን አበው ሊቃውንት 📢 ህዝበ ክርስቲያንን ማንቃት 📢 ቅድመ ኢትዮጵያ ትንሳዔ እና የኢሉሚናቲ ኅቡእ ማኅበር ኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡትን ሴራዎችን ማጋለጥ ለውይይት @Tinsae_ze_ethiopiaofficialgrp

Show more
Advertising posts
4 227Subscribers
-1824 hours
-1167 days
+48730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

፪. አርዮስ እና አርዮሳዊነት (Arius) የአርዮስ ኑፋቄ ጥልቅና ሥር ነቀል የሆነ ጸረ ክርስትና የፈጠራ ትምህርት በመሆኑ በዚህ መጽሓፍ ላይ በዝርዝርና በስፋት አናየውም፡፡ ሆኖም የእርሱ ኑፋቄ የብዙዎቹ የኋላ መናፍቃን መፈልፈያ ኩሬ በመሆኑ፣ ኑፋቄውም ለኋላ አረመኔያዊ የአሕዛብ ትምህርቶች መነሻ ሆኖ ያገለገለ በመሆኑ በአጭሩ እንዳስሰዋለን፡፡ አርዮስ ከእርሱ በፊት የተነሣው ሰባልዮስ የተባለው መናፍቅ የአካላዊ ቃልን ቀዳማዊና ራሱን የቻለ ህልውና ክዶ አንዱ እግዚአብሔር በሆነ ዘመን የተገለጠበት የመገለጫ መንገድ (Modes of Divine Manifestation) ብቻ ነው የሚል ክህደት ይዞ ተነሥቶ ብዙ ሞኞችን ሲያስከትልና ግራ ሲያጋባ ነበር፡፡ ይህን የሰባልዮስን ኑፋቄ በመቃወምና አጸፋዊ መልስ ለመስጠት አካላዊ ቃል የራሱ የሆነ ህልውና አለው በማለት የተነሣው አርዮስ ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስን “በአብ የተፈጠረ ነው" (ሎቱ ክብር ወስብሐት አምልኮ ወስግደት) በማለት ለሰማይ ለምድር የሚቀፍ ክህደት ሲናገር ይህ የእርሱ አስተሳሰብ ኢየሱስ ክርስቶስን “ከኣንዱ ኣምላክ እየተከፈሉ ከሚመጡ ብናኞች አንዱ ነው” የሚለውን የግኖስቲኮችን አስተሳሰብ ቅርጹን ለውጦ መልሶ የሚያመጣ መሆኑን መመልከት አልቻለም ነበር፡፡ አርዮስ በድፍረት ኢየሱስ ክርስቶስን በባሕርዩ ከአብ ጋር አንድ ያልሆነ፣ ከኣብ ያነሰ፣ ያነሰ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ሌሎች ፍጥረታትን ለመፍጠር ይጠቀምበት ዘንድ መጀመሪያ የፈጠረው “ፍጡር” ነው ይል ነበር፡፡ የአርዮስ ተከታዮች እና የእርሱን ኑፋቄ በተለያየ ደረጃ የጠጡት እነ መቅዶንዮስና መሰል መናፍቃን ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን ግኖስቲኮች ከአምላክ እየወጡ ይመጣሉ እንደሚሏቸው ኤዎኖች (Aeons) ኣድርገው ይመለከቷቸው ነበር፡፡ 🔸 በዋናነት የአርዮስ ክህደት አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን ከአብ አሳንሶ ማሳየቱ፣ ፍጡር ነው ማለቱ ነው፡፡ ይህ ወልድን ከአብ የማሳነስ የመጨረሻ የክህደት ጥልቀት (Subordinationism) አርዮስ ተክሎት የሄደው መርዝ ነበር፡፡ 💢 ይህ ወልድን ከአብ አሳንሶማሰብና ማስተማር በተሐድሶዎችም የሚታይ በሽታ ነው፡፡ ራሳቸውን ክርስቲያን ነን ብለው በሚጠሩ የተለያዩ ድርጅቶች ዘንድ የሚታየው ኢየሱስ ክርስቶስን “ወንድሜ ጓዴ . . .” የሚሉት አስተሳሰቦችና ሌሎችም ለመናገር የሚከብዱ ነገሮቻቸው ከአብ ጋር በባሕርይ አንድ መሆኑንና የባሕርይ አምላክነቱን በግልጽም ባይሆን በስውር ካለማመን የሚመነጩ ሰወር ያሉ አርዮሳዊነት (Latent Arianism) ናቸው:: ©️መድሎት ጽድቅ ቅጽ ፩ (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) @Tinsae_ze_Ethiopia
Show all...
በሩሲያ ዋና ከተማ በሆነችው ሞስኮ በዛሬው እለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የታላቁ ጾመ(ሁዳዴ) የቅዳሴ ስነ ስርዓት ይህን ይመስላል። @Tinsae_ze_ethiopia
Show all...
የቤተ ክርስቲያን ቅርስ ውድመት ሕንፃውን በ24 ሰዓት ለቃችሁ ውጡ •••• መሀል ፒያሳ የሚገኘው ጥንታዊ ሕንፃ (የጽርሐ ሚኒልክ ሕንጻ ወይም መሀሙድ ሙዚቃ ቤት የሚገኝበት ሕንፃ ) ጉዳይን ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ችግሩን እንዲፈቱና የሕንጻውን እድሜና ታሪካዊነት ታሳቢ በአደረገ አግባብ እንዳይፈርስ ከመንግስት አካላት ጋር እንዲነጋገሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ በቋሚ ሲኖዶስ የተመደቡ ቢሆንም ቤተክርስቲያንን በገንዘብ የሸጠው ቀሲስ በላይ እና ግብራበሮቹ አስቀድመው ሕንጻው እንዲፈርስ በመስማማታቸው ምክንያት መንግስት ሕንጻውን ለማፍረስ በውስጡ ለሚኖሩ ተከራይ ሰዎች በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ ሕንጻውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። በአሁኑ ጊዜ በከተማው የሚገኙ የቤተክርስቲያናችን ሕንጻዎች አደጋ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠባቸው መሆኑንን የመረጃ ምንጮቻችን አድርሰውናል ፣ ©️ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ @Tinsae_ze_Ethiopia
Show all...
⬆️ የቀጠለ … ሌላው የግኖስቲኮች ትምህርት ስለ ብሉይ ኪዳን እና የኦሪትን ሕግ ስለ ሰጠው አምላክ ያላቸው የፈጠራ ትምህርት ነበር፡፡ ግኖስቲኮች “ብሉይ ኪዳንን የሠራው የአይሁድ አምላክ ክፉው አምላክ ነው፣ (ሎቱ ስብሐት) በሐዲስ ኪዳን ሰው ሆኖ የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ከብሉይ ኪዳኑ አምላክ የተለየ ከሆነው ከደጉ አምላክ ተልኮ የመጣ ነው” ይሉ ነበር፡፡ ከዚህም የተነሣ እንደ መርቅያን ያሉት ጽንፈኛ ግኖስቲኮች “መጽሐፍ ቅዱስ” በሚለው መድበል ውስጥ የሚቀበሉት ሐዲስ ኪዳንን፣ ያውም ሁሉንም የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሳይሆን ከወንጌል የሉቃስን ወንጌል ብቻ እና የቅዱስ ጳውሎስን (አሥሩን መልእክታት ብቻ ነበር፡፡ ግኖስቲኮች ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት መካከል መሠረታዊ እሳቤውንና ጽንሰ ሃሳቡን ሳይረዱ ሕገ ኦሪትን የሚነቅፍ የሚመስላቸውን በእጅጉ እያጎሉ ለማሳየት ይሞክሩ ነበር፡፡ ከሐዋርያት መካከል የኢየሱስ ትምህርት የገባው ጳውሎስ ብቻ ነው ይሉ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ለብሉይ ኪዳን ሕግና ያን የሠራው አምላክ ለሚሉት ከነበራቸው ከፍተኛ ጥላቻ የተነሣ ብሉይ ኪዳንን አጥብቀው ይጸየፉና ይጠሉ ነበር፡፡ መርቅያን የአይሁድ አምላክ ብሎ ለሚጠራው ብሉይ ኪዳንን ለሠራው አምላክ ከነበረው ጥላቻ የተነሣ እርሱ ዕረፍት ትሁን ብሎ ያዘዛትን ቀዳሚት ሰንበትን ተከታዮቹ እንዲጾሟት አዝዞ ነበር፡፡ መርቅያን ተቀበልኩት ያለውን የሉቃስን ወንጌል እንኳ ከብሉይ ኪዳን ጋር የሚያገናኙትን ታሪኮች በየጊዜው ትዝ ባለው ቁጥር እየነቀሰ እያወጣና እንደ አዲስ እየጻፈ እርሱ “ትክክለኛ ወንጌል" የሚለውን ጽፎ ሳይጨርስ ነበር የሞተው፡፡ ከፍተኛ ዋጋና ቅድሚያ ይሰጥ የነበረውም ለቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላትያ፣ ለቆሮንቶስ ካልእ እና ለሮሜ መልእክት ነበር፡፡ከእነዚህ ከተቀበላቸው መጻሕፍት እንኳ ሳይቀር ከእርሱ ንድፈ ሃሳብ (ቲዎሪ) ጋር የማይሄዱትን ሃሳቦች እየነቀሰ ያወጣቸው ነበር፡፡ ከዚያም የራሱን ሃሳብ በምትካቸው ያስገባ ነበር፡፡ በዚህ ረገድ በግኖስቲኮች ዘንድ የነበሩት ዋና ዋና የስህተት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡- ➢ ብሉይ ኪዳንን (የሕጉን መጻሕፍት፣ የነቢያትን መጻሕፍት እና ይዘታቸውን) አምርረው መጥላታቸው፣ ➢ ሌሎችን ሓዋርያት የኢየሱስን ትምህርት እንዳበላሹና እንደ ለወጡ አድርጎ ማሰብና ጳውሎስ የተላከው የእነዚያን ስህተት ለማስተካከል ነው ብለው ማሰባቸውና ማስተማራቸው፤ ለዚህም መርቅያን ቅዱስ ጳውሎስን ምስክር አድርጎ (በተለይ የገላትያ መልእክቱን) ለማሳየት መሞከሩ፣ ➢ ኢየሱስ ክርስቶስን “ከደጉ አምላክ እየወጡ የሚመጡ ነጸብራቆች ወይም ብናኞች (Aeons) አሉ” ይላሉና ከእነዚያ መካከል አንዱ አድርገው መቁጠራቸው፣ ➢ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት ትምህርቶች ውስጥ ይደግፉናል የሚሏቸውን አንዳንድ ጥቅሶች ብቻ በማንጠልጠል ያን ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር ከተባለበት ዳራና ርእሰ ጉዳይ አንጻር መረዳትን ትተው ለራሳቸው አስተሳሰብ ደጋፊ አድርገው ለማቅረብ መታገል ነበሩ፡፡ 🔴 እነዚህን የግኖስቲኮች እርሾዎች በተሐድሶዎች አስተሳሰብና ጽሑፎች ላይ በሰፊው እናገኛቸዋለን። ©️መድሎት ጽድቅ ቅጽ ፩ (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) @Tinsae_ze_Ethiopia
Show all...
፩. ግኖስቲኮች (Gnostics) በ2ኛውና በ3ኛው መ/ክ/ዘ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኳትና ሲፈትኗት የነበሩት መናፍቃን ብዙዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚያ መካከል በተለይም ግኖስቲኮች የተባሉት አካሄዳቸው አደገኛ ነበር፡፡
ግኖስቲኮች “ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ትምህርት ርቃለች፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማረው ትምህርት ተቃራኒ የሆነ ሌላ እንግዳ ትምህርት ታስተምራለች” እያሉ ይቃወሟትና ያብጠልጥሏት ነበር፡፡
ግኖስቲኮች እውነተኛው የክርስቶስ ትምህርት አለ የሚሉት ከእነርሱ ዘንድ ብቻ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ጽሑፎቻቸው ይፋዊ በሆነ ሁኔታ በውስጧ ምእመናንና ካህናትን ይዛ በጳጳሳት ስትመራ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን በኑፋቄ ይከስሷትና አበክረው ይነቅፏት ነበር፡፡ ግኖስቲኮች እውነተኛ ክርስቲያኖች አድርገው የሚቆጥሩትም ራሳቸውን ብቻ ነበር፡፡ እንዲሁም ግኖስቲኮች በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያፌዙና ይሳለቁ ነበር፡፡ ለምሳሌም በምሥጢረ ጥምቀት የሚገኘውን ጸጋ አምነው በምሥጢሩ ሂደት በሚሳተፉ ሰዎች ላይ “ወደ ውኃ ውስጥ ገብተው ምንም ነገር ሳይይዙ በባዶው የሚወጡ” እያሉ ሊቀልዱባቸውና ሊያፌዙባቸው ይሞክሩ ነበር፡፡ ግኖስቲኮች የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የነበሩ ጳጳሳትን “ሙሰኞች፣ ሥልጣን የጠማቸው፣ ስስታሞች ወዘተ እያሉ መራራና ጠንካራ በሆኑ ቃላት ይሰድቧቸውና ሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲጠላቸውና እንዲጸየፋቸው በማድረግ ከቤተ ክርስቲያን እየኮበለለ ወደ እነርሱ ጎራ እንዲገባ ለማድረግ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ያካሂዱ ነበር፡፡ ግኖስቲኮች ይሰብኩት የነበረው ክርስትና” አንድና ወጥ የሆነ አስተምህሮ ያላትና መዋቅር ያላት አንዲት ቤተ ክርስቲያን የሌለችበትና ደስ ባላቸው መንገድ እንዳሻቸው ሊያደርጉት የሚችሉት ውጥንቅጡ የወጣ የተበጣጠሱ ቡድኖች እንዲፈጠሩ በሚያደርግ ሁኔታ ነበር፡፡ ትምህርታቸውም ራሳቸው ብቻ ፈራጆችና አድራጊ ፈጣሪዎች የሆኑበት ስብስብ፣ ክህነትና ካህናት የሌለባት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምሥጢራት የሚባሉ ነገሮች የማይታወቁበት ዓይነት “ልዩ ክርስትና” ነበር፡፡ እነዚህ መናፍቃን ስለ መዳን ሲያስተምሩ በክርስቶስ አካል - በቤተ ክርስቲያን - ስለማያምኑ ግላዊ መዳን (በግል መዳን) የሚል ትምህርት ነበራቸው፡፡ ይህም ማለት “እያንዳንዱ ሰው በመዳን ሂደት ውስጥ የክርስቶስ አካል ይሆናል፣ በዚህም የክርስቶስ አካላት (ብልቶች) ከሆኑ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በክርስቶስ ራስነት አንድ ይሆናል” የሚለውን ትምህርት ትተው እያንዳንዱ ሰው ክርስቶስን እርሱ በተረዳው መንገድ በማመን ያለ ምሥጢራት አስፈላጊነት ይድናል ብለው ያስተምሩ ነበር፡፡ እነርሱ ከሚሉት ከዚህ ዓይነቱ የእነርሱ “ክርስትና” ውጭ የሆነን ሁሉ “የወንጌል ጸር፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ፣ አረመኔ ጌታ ያልተሰበከለት” ወዘተ የሚል ቅጽል ይደርቡለት ነበር፡፡” ከግኖስቲኮች መሪዎች መካከል ባሲሊደስ ቄሬንተስ፣ ቫሌንቲኑስ እና መርቅያን ዋና ዋናዎቹ ነበሩ፡፡ ግኖስቲኮች ቁስ አካላዊ የሆነ ነገር ሁሉ፡ የሰውን ሰውነት ወይም ሥጋን ጨምሮ፣ ክፉ (ኃጢአት) ነው፡ የእግዚአብሔር ፍጥረትም አይደለም ይሉ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሣም እግዚአብሔር ጸጋውን ለመስጠት እንዲሀ ክፉ ነው ያሉትን ቁስ አካልን ይጠቀማል ማለት በእነርሱ አስተሳሰብ ነውር ነበር፡፡ በሚታዩ ነገሮች አንጻር ጸጋ እግዚአብሔር የሚሰጥባቸው ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በእነርሱ ዘንድ የማይታሰቡ ነበሩ፤ ምክንያቱም ኃጢአት ወይም ክፉ በሆነ በቁስ አካል አንጻር (በውኃ ጥምቀት፣ በሜሮን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ በኅብስቱና በወይኑ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ) እንኳን ጸጋ እግዚአብሔር ሊሰጥባቸው ይቅርና እንደዚህ ካለት ቁስ አካሎች በተቻለ መጠን አብዝቶ መራቅና መለየት ይገባል እያሉ ያስተምሩ ስለ ነበር ነው። ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፣ ቅዱስ ፖሊካርፐስ፣ ቅዱስ ሄሬኔዎስ፣ ቅዱስ ሜሊጦስ ዘሳርዴስ እና ሌሎችም የ2ኛውና የ3ኛው መቶ ዓመት አባቶች የእነዚህን መናፍቃን ስህተት ለማጋለጥና እውነተኛውን ሐዋርያዊ ክርስትና ከግኖስቲኮች ብረዛ ለመጠበቅ በአፍም በመጽሐፍም ጽኑ ተጋድሎን ተጋድለዋል፡፡ ሆኖም የግኖስቲኮች ልብ ወለዳዊ የፈጠራ ትምህርት መልኩንና ዓይነቱን እየለዋወጠ በየዘመናቱ ሓዋርያዊት የሆነችውን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ማወኩ አልቀረም፡፡ እግዚአብሔር በሐዋርያው
በቅዱስ ጳውሎስ ቃል “ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታውቁምን? እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ” ሲል የመከረንና ያስጠነቀቀን ለዚህ ነበር፡፡ 1 ቆሮ. 5፡6-7
⚠️ ይህን የግኖስቲኮች እርሾ በእነዚህ በተሐድሶዎች የፈጠራ ትምህርት ውስጥም ጥላውን ጥሎ እናገኘዋለንና በጊዜው ጊዜ ከቦታው ስንደርስ እናነሳዋለን፡፡ በጊዜው አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ አረዳድና ልዩ መገለጥ እየተባሉና እየመሰሉ የሚወጡ ነገሮች አብዛኛዎቹ የጥንቶቹ መናፍቃን የግኖስቲኮች የአርዮሳውያንና የንስጥሮሳውያን እርሾዎችና ልቅምቃሚዎች የሆኑ ኑፋቄዎችን በተለያየ መጠንና ቅርጽ በማቡካትና በመጋገር የሚፈጠሩ ናቸው እንጂ አዲስ አይደሉም፡፡ በእነ ማርቲን ሉተር፣ በእነ ጆን ካልቪን፣ በእነ ኡልሪች ዝውንግሊ፣ በአሁኑ በአገራችንም ራሳቸውን “ተሐድሶ” ብለው በሚጠሩ አካላት የምናየው ይህንኑ ነው፡፡ ወደፊት በምናያቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተሐድሶ መናፍቃንን ትምህርት ጥንቱንና የትመጣውን ስናይ ይህ የበለጠ ግልጽ እየሆነ ይሄዳል፡፡ ለጊዜው ግን “የግል አዳኝ”፡ “ጌታን በተረዳኸው መንገድ ግለጠው፣ “ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለመዳን አያስፈልጉም፣ ወዘተ የሚሉት የፕሮቴስታንትና የተሐድሶ ባህሎች ምንጫቸው ግኖስቲካዊ እርሾ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡ ግኖስቲኮች የመናፍቃን ዋና መገለጫ የሆነውን የተዘበራረቀና በወጥነት ይህ ነው ተብሎ ሊገለጽ የማይችል፣ ነገር ግን እንደየ ግለሰቦቹና መሪዎቹ ስሜትና ምኞት የተቃኘ የተለያየና የተምታታ አስተምህሮ ነበራቸው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ግኖስቲኮችን በዋናነት በሁለት ከፍሏቸዋል፡፡ እነዚህም 🔸“አፍቃርያነ ትህርምት” እና 🔸“አፍቃርያነ ኃጢአት በሚል ነው፡፡ 🔶 “አፍቃርያነ ትህርምት“ ፦ እነዚህ ቡድኖች ቁስ አካል በሆነው ሰውነት ውስጥ የታሰረችውን ነፍስ ነጻ ለማውጣት ጽኑ ትህርምት ማድረግን፣ ጋብቻን መጸየፍንና መከልከልን ይሰብኩ የነበረ ሲሆን 🔶“አፍቃርያነ ኃጢአት”፦ እነዚህኞቹ ደግሞ ሰውነት ምንም ሊፈወስ በማይችልበት ሁኔታ የተበላሸ ስለሆነ በእውቀት የበለጸገች ነፍስ ሰውነቷ ምንም ዓይነት ኃጢአት ቢሠራ አንዳችም ጉዳት አይደርስባትም ባዮች ነበሩ፡፡ ለእነዚህኞቹ ኃጢአት ነው የሚባል ምንም ዓይነት ድርጊት አልነበረም፡፡ ለዳነች ነፍስ የሚጎዳት ምንም ዓይነት የርኩሰትም ሆነ የኃጢአት ድርጊት የለም ይሉ ስለ ነበር ኃጢኣትን ሁሉ ንቅስ ጥቅስ እያደረጉ መሥራትን ይሰብኩና ያበረታቱ ነበር፡፡ ይህን የግኖስቲኮች እርሾ በተሐድሰዎች ትምህርት ውስጥ እናገኘዋለንና በቦታው ስንደርስ እናየዋለን፡፡ ለምሳሌም ተሐድሶዎች “በእምነት ለዳነ ሰው ኃጢአት ቢሠራም ያገኘው ጸጋ አይወሰድበትም፣ ራሱን ለመግዛትና ከኃጢአት ጋር ለመጋደል ጥረት ማድረግ የለበትም፣ ኃጢኣት ማድረጉ በእግዚአብሔር ልጅነቱ ላይ የሚያመጣው አንዳችም ለውጥ የለም” እያሉ እንደ አባቶቻቸው እንደ ግኖስቲኮች ሲናገሩ እናገኛቸዋለን፡፡
Show all...
💢 ኑፋቄ ኑፋቄ ምንድን ነው? ኑፋቄ ማለት እግዚአብሔር የገለጠውን ሃይማኖት እንደ ምእመናን ሙሉ በሙሉ ሳይቀበሉ፣ እንደ ኢአማንያንም ሙሉ በሙሉ ሳይከዱ የተወሰነውን ተቀብሎ ሌላውን ደግሞ አለመቀበል ወይም መጠራጠር ነው፡፡ እንዲህ የሚያደርጉት ሰዎች ደግሞ መናፍቃን (ተጠራጣሪዎች) ይባላሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ መናፍቃንን እንዲህ ገልጸዋቸዋል፦
“የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሳይሆኑ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች መስለው ወይም ከቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት ግማሹን ይዘው ግማሹን ያልያዙ ጎሎዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች እንክርዳድ ስንዴ መስሎ እንዲያድግ በክርስቶስ ዐጸድ ወይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የበቀሉ አሳሳቾች ናቸው:: ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች ናቸው፡፡” 📔 (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣ ገጽ 50}
መናፍቃን የሚባሉት እግዚአብሔር እንድንበት ዘንድ የሰጠውን መንገድ (የክርስትናን ሃይማኖት) ተቀብለናል፤ እናምናለን ካሉ በኋላ ያን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የመዳን መንገድ ለእነርሱ የመሰላቸውን ያህል ቆንጽለውና ከፍለው እንጂ እንዳለ ሙሉ በሙሉ የማይቀበሉ ናቸው፡፡ ኢአማንያን የሚባሉት ከመጀመሪያውም የክርስትና ሃይማኖትን ያልቀተበሉ ሲሆኑ መናፍቃን የሚባሉት ግን ክርስቲያኖች ነን እያሉ ነገር ግን ከክርስትና አስተምህሮ ውስጥ ለራሳቸው አስተሳሰብና ምኞት የሚመቻውን ብቻ ተቀብለው ሌላውን የማይቀበሉና የሚጠራጠሩ፣ በእውነተኛው ትምህርት ፋንታም የራሳቸውን የፈጠራ ትምህርት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ እንደዚህ ያሉት ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ አገላለጾች ተገልጸዋል፡፡ ለምሳሌም 🔸“በመልካሙ እርሻ ጠላት የዘራው እንክርዳድ” (ማቴ. 13፡25-26)፣ 🔸"የክፉው ልጆች” (ማቴ. 13፡39)፣ 🔸“ሐሰተኞች ወንድሞች”፣ 🔸“ክፉዎች ሠራተኞች”፣ “ውሾች (ፊል. 3:2)፣ 🔸“መናፍቃን” (2 ጴጥ. 2፡1 ፣ 🔸የሐዋ. 24፡5) በሚል መጠሪያ ተጠርተዋል፡፡ ይህም ስድብ ሳይሆን የግብራቸው መገለጫ ነው፡፡ ለምሳሌ የሚሰርቅ ሰው “ሌባ” መባሉ የግብሩ መገለጫ እንጂ ሌላ አይደለም:: ሰው የአንድን ነገር ግብሩን ወድዶ ስሙን ብቻ ቢጠላ ትርጉም አይኖረውም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም ፦
“በሃይማኖት ላይ የሚጨምር ደፋር፣ የሚቀንስ ደግሞ ሌባ ነው” ሲል ይገልጻል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ የኑፋቄን ከባድ ኃጢአትነትና አጥፊነት አበክሮ ይገልጻል፡፡ ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፣ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ”፡፡ 2 ጴጥ. 2፡1 ኑፋቄ የእግዚአብሔርን መንግሥት የማያስወርስ ነው፤ "መለያየት፣ መናፍቅነት፣ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” ገላ. 5፡21 ክርስቲያኖች መስለው የክርስቶስን ሰም እየጠሩ፣ ነገር ግን የስህተት ትምህርት የሚያስተምሩ መናፍቃን እንደሚነሡ ጌታችን አስቀድሞ እንዲህ ሲል አስጠንቅቆናል፡- “በዚያን ጊዜ ማንም እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፣ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። እነሆ አስቀድሜ ነገርኋችሁ። እንግዲህ እነሆ በበረሀ ነው ቢሏችሁ አትውጡ፤ እነሆ በእልፍኝ ነው ቢሏችሁ አትመኑ” ማቴ. 24፡23-26
ጌታችን ካስተማረውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከጌታ ከተቀበለችው የድኅነት አስተምህሮ የተለየ ትምህርት የሚያስተምር መናፍቅ የተረገመ መሆኑንና ልንቀበለውም የማይገባ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ
“ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን” ሲል በጽኑ አስጠንቅቋል፡፡ ገላ. 1፡8-9
እንዲህ ካለ መናፍቅ መለየት እንደሚገባም ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ፣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት" ሲል ቅዱስ መጽሐፍ ያስጠነቅቀናል፡፡ 2 ዮሐ 10
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊም እንዲህ ብሏል፡-
ከመጀመሪያው ጀምሮ ከባለቤቱ ከጌታችን የተሰጣት የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት፣ ትምህርትና እምነት በሐዋርያት የተሰበከ እና በአባቶች የተጠበቀ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በዚህ ላይ ነው፤ ከዚህ የሚያፈነግጥ ማንም ቢሆን ክርስቲያን አይደለም፡ ክርስቲያን ተብሎ ሊጠራም አይገባውም፡፡ (ለጳጳስ ሴራፒዮን ዘትሙይስ የተላኩ አራት መልእክታት?}
ኑፋቄ ታላቅ ኃጢአት ነው፡፡ ኃጢአት ብቻም ሳይሆን በሰውነት ድክመት በምግባር ፍኖት ከሚፈጸሙ ኃጢአቶች ሁሉ በላይ የመጨረሻ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ ምክንያቱም በሃይማኖት ውስጥ ያለ ሰው የሚሠራው ኃጢአት ንስሐ ከገባ ሥርየትንና ምሕረትን ሊያገኝ ይችላል፤ ኑፋቄ ግን ሥርየትና ምሕረት በሚገኝበት በራሱ በሃይማኖት ላይ የሚፈጸም ኃጢአት በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ቢታመም በመድኃኒት አማካይነት ሊፈወስ ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ያ በሽተኛ በመድኃኒቱ ላይ የሚያምጽና የሚቀልድ ከሆነ ግን የመዳን ተስፋ እንኳ የለውም፣ ምክንያቱም በመድኃኒቱ ላይ አምጿልና፡፡ ለሰው ልጅ የተሰጠው ታላቁ ሀብትና ጸጋ እምነት ነው፡፡ ኑፋቄ ደግሞ ይህን ታላቅ ጸጋ የሚያሳጣ ስለሆነ እጅግ ከባዱ ኃጢአት እርሱ ነው፡፡ ሰዎች ወደ ኑፋቄ የሚገቡባቸው ከተለያዩ ምክንያቶች መካከል እውነተኛውን የክርስትና ትምህርት አለማወቅና በተሳሳቱ ሰዎች ትምህርት መለከፍ፣ በራስ አስተሳሰብና ስሜት ብቻ መመራት፡ እኔ አውቃለሁ ማለት፣ ከትዕቢት የተነሣ ሰህተትን ሲነገሩ አለመቀበልና በራስ መንገድ ብቻ መጓዝ አንድ ጥቅስ ወይም በጣም ጥቂት ጥቅሶች ላይ ብቻ መንጠልጠል፣ እምነትን ለቁሳዊ ጥቅም ማግኛ መንገድ ማድረግ፣ በዘመኑ ያሉ ኃይላትን ለማስደሰትና ሹመትና ሥልጣንን ለማግኘት ማሰብ ይገኙባቸዋል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን የኑፋቄ መሥራቾችና ተከታዮች የሆኑ መናፍቃንን ከሁሉም ይልቅ ክፉዎች መሆናቸውን ይናገሩ ነበር፡፡ ለአብነትም ቅዱስ ፖሊካርፐስ መርቅያን የተባለውን መናፍቅ "የዲያብሎስ የበኩር ልጅ” ይለው ነበር፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ ደግሞ “መናፍቃን መርዝን የተመሉ ናቸው” ይላቸው ነበር፣ እንዲሁም “በሰው መልክ ያሉ አራዊት ናቸው” ይላቸው ነበር፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮስጢኖስ ደግሞ መናፍቃንን “ዲያብሎስ ያነቃውን ስህተት የሚከተሉ” ይላቸው ነበር፡፡ አባ ሄሮኒመስ ደግሞ “መናፍቃንን የሰይጣን ምኩራቦች” ይላቸው ነበር፡፡ ከዚህም በመቀጠል በዘመናት የነበሩ ዋና ዋና መናፍቃንና ኑፋቄያቸው በአጭሩ * ግኖስቲኮች/ ኖስቲኮች * አርዮስ * ንስጥሮስ * ሄልቪዲየስ * ጆቪኒያን * ቪጂላንቲየስ * አርዮስ ዘሴባስቴ * ማርቲን ሉተር ©️መድሎት ጽድቅ ቅጽ ፩ (ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) @Tinsae_ze_Ethiopia
Show all...
"ልጆቼ! ከእሳተ ገሃነም እንዴት ልንተርፍ(ልንድን) እንደሚገባን እንጂ እሳተ ገሃነም የት እንዳለ ለማወቅ እጅግ የምንደክም አንኹን፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @Tinsae_Ze_Ethiopia
Show all...