cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወንጌል በስነ-ፅሁፍ

አላማችን በስነፅሁፍ ወንጌልን ለአለም ሁሉ ማድረስ ነው ። የተፈጠርንለትም አላማ ነውና! -ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ -ግጥም -አዳዲስ ዝማሬዎች -ወግ ሌሎችንም ያገኙበታል ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት እንዲሁም አብሮ ለማገልገል በዚህ ያናግሩን። @AksanAdane @wengelbeArt_bot

Show more
Ethiopia3 077Amharic2 967The category is not specified
Advertising posts
2 799Subscribers
No data24 hours
-27 days
+1730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🩸የደም ልሳን🩸 ክፍል 10 ✍ written by Aksan Adane በወንጌል በስነ-ፅሁፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 ..........ይከተለኝ ጀመር እግዚአብሔር ይገስፀው በኢየሱስም እያልኩ እርምጃ ጨመርኩ ኢያኤል ቁሚ አለኝ ኡፍፍፍ ቁና ተነፈስኩ ማን ይሁን ብዬ እርምጃዬን ገታሁኝ ከጭንቅላቱ ላይ ኮፍያውን አነሳና የሆነ ወረቀት ከኪሱ አውጥቶ ሰጠኝ ማን ልበል አልኩት ያሬድ እባላለሁ እያደረግሽ ያለሽውን ነገር እንድታቆሚ ልነግርሽ ነው አመጣጤ አለኝ ። ግራ በመጋባት ማለት ምን አደረኩኝ አልኩት. ልጆቻንን በገንዘብ እያታለላችሁ ከውጪ በሚገባ በፈረንጅ እርዳታ እየደለላችሁ ሀይማኖት እያስቀየራችሁ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ታቆሚ እንደሆነ አቁሚ አለኝ ደም ስሩ ተገታትሮ ፈገግ አልኩና እኛ እንደ እሱ አናደርግም ይህን ማረጋገጥ ከፈለክ ደግሞ አብረኸኝ ና እና ማየት ትችላለህ አልኩት ኸረ ባክሽ እኔንም ልታታይኝ መሆኑ ነው ሰዉን በምን እንደምታደነዝዙት ምን ይታወቃል እኔ እንደ ሌሎቹ መስዬሽ እንዳይሆን ለሀይማኖቴ ደሜ እስኪፈስ ማድረግ ያለብኝን አደርጋለሁ አለኝ ለሀይማኖትህ ነው ለጌታህ ለመሆኑ ጌታህ ማነው አልኩት አይ እንግዲ እዚ አትነታረኪ ምትኖሪ ከሆነ የራስሽን ኑሪ የሌላውን እየፈተፈትሽ ትውልዱን ወደ ሞት አትውሰጂው አይ ካልሽ ግን እኔን አያድርገኝ ብሎ ሄደ ሆሆሆሆሆ እየሳኩኝ ወደ ፀሎቱ አመራሁ ተጀምሮ ነበር የሚገርም መንፈስ ነበር ማንም ማንንም አይመራም ግን የልብ አንድነት ነበር በመሀል የእግዚአብሔርን ቃል እየተከፋፈልን እየተዘመረ ግማሹ የታመመ ይዞ ይመጣል በህብረት እንፀልያለን ደህና ይሆናል ሊታዘብ የሚመጣ መዳን ሆኖለት እንደተለመደው አንድ27 ሰው በጌታ በኢየሱስ አምኖ ተደሰትን ሶስት ቀናት አነሱብን ብቻ ግን ሁሉም ወደ የመጣበት መመለስ ስለ ነበረበት በሶስተኛው ቀን ጌታ ቢፈቅድ ለቀጣይ ወር ተቀጣጥረን ተበተንን ። 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 ወደ ቤት እንደገባን መንገድ ላይ ያ ልጅ የሰጠኝን ወረቀት ለብሌን አሳየኋት የተለየ ነገር የለውም በአፉ ያወራኝን ነገር ማህተም ባለው ደብዳቤ ዛቻ ነበር ቆይ ማን መብት ሰጠው እንዴ ብዬ መናደድ ጀመርኩ ብሌን ፈገግ ብላ አንቺ ልጅ እና እልል ብሎ እንዲደግፍሽ ፈልገሽ ነበር እንዴ እንደዚህ አይነት ውጊያ ከሌለ እኮ ደስ አይልም አለችኝ አንቺ ደግሞ ታበዢዋለሽ እነሱም መብት እንዳላቸው ሁሉ እኛም መብት አለን ለምን ምዕመኑን ሁሉ ወደዚህ አናመጣም እርሱ ወደዚህ እንዳይመጡ ጠንክሮ ህይወት ያለበትን ትምህርት ማስተማር ነበራ አልኳት ። እቺን ለእርሱ ነው ምትነግሪው እንደዚህ ስሜታዊ አትሁኚ ክላስ መሄድ አለብኝ ብላኝ ሄደች። አረብኛ ቋንቋ እያጠናች ነው የተለያዩ የmissionary ስልጠናዎችንም እየወሰደች ነው እኔም ከእርሷ ጋር ስልጠናዎችን እካፈል ነበር ጎን ለጎን ትምህርቴንም እያስኬድኩ ነው ። ደብዳቤውን ባየሁት ቁጥር እናደዳለሁ የፀሎት ስፍራቹን እናዘጋለን ማነው እሱ ቆይ ሜዳ ላይ ከነቤተሰቦችሽ ትወድቂያለሽ ማን ስለሆነ ነው እንደዚህ ያለ ፅሁፍ የሚፅፈው እያልኩ ስበሰጫጭ እናቴ መጣች ምን ሆነሻል አንቺ ልጅ ብቻሽን የምታወሪው አለችኝ ደብዳቤውን አሳየኋትና ያለኝን ነገርኳት እና ለዚህ ነው አለችኝ እናቴ ምን ሆነሻል እኛም እኮ መብት አለን አልኳት መብት መብት አትበይ እውነት እንዳለው ቢያደርግስ ለፀብ ልትነሺ ነው? ልጄን ምን አገኘብኝ ሆሆሆሆሆ እያለች ወደ ጓዳ ገባች ከሰዓት ክላስ ነበረኝ ክላስ እያለሁ ደጋግማ ብሌን ትደውላለች ክላስ እንደሆንኩ መልዕክት ፃፍኩላት። እንደወጣሽ ደውይልኝ አስቸኳይ ነው ብላ መለሰችልኝ። አላስችል ቢለኝ ምንድነው ብዬ መልሼ ፃፍኩላት ። ምላሿ ያሬድ...... ይላል። ምን ሆነ? አልኳት ምንም አልመለሰችልኝም እንዴ እንደዛተው እነ እማዬን ተተናኮሉአቸው የፀሎት ቦታችን ላይ አደጋ ፈጠሩ ምንድነው በሀሳብ እብከነከን ጀመር መምህሩ ኢያኤል ደህና ነሽ አለኝ እእእ አዎ አይ ቀበጣጠርኩ ደህና አትመስይኝም ወይ ወደ ቤት ገብተሽ እረፍት አድርጊ አለኝ እሺ ብዬ ተነስቼ ወጣሁ ና ለብሌን ደወልኩላት..... ..............ይቀጥላል.............. ✍ written by Aksan Adane ፀሀፊት አክሳን አዳነ 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 👆👆👆join&shear 👆👆👆
Show all...
✍ እሠይ!! * ፍቅርህን ላወራ ፣ ባንተ መወደዴን ገና አንተ 'ኮ ብየ ፣ ስከፍት አንደበቴን ቃላት አቅም አ'ተው ፣ ይልፈሰፈሳሉ ቃል ለሆንከው ላንተ ፣ ቃል የለም እያሉ ሽርጉድ ይላሉ ፣ በብዕሬ ጫፍ ላይ አቦ እሠይ እላለሁ ፣ እኔም ይህንን ሳይ እሠይ እሠይ እሠይ ፣ እሠይ ለቃል መስነፍ እሠይ እሠይ እሠይ ፣ ለፍቅርህ መግዘፍ እሠይ ለመውደድህ እሠይ ለም'ረትህ እሠይ ለስጦታህ እሠይ ለችሎታህ እሠይ በፍቅርህ ፣ እሠይ ስላዳንከኝ እሠይ አሳርፈህ ፣ እሠይ ስላስባልከኝ እያልኩ እጽፋለሁ ፣ ወረቀቴ ይርሳል የብዕሬ ቀለም ፣ በእምባ ይለወሳል የልቤን ደስታ ፣ ብዕሬ ይገልጣል አንተን ካላገኙ ፣ እሠይ ኬት ይመጣል አሁንም ደሞ እሠይ ደሞ እንደገና እሠይ የማያባራ እሠይ!! ✍#ሄኖክ_አሸብር 💐💐 @wengelbeArt 💐💐
Show all...
ዋጋው ስንት ነው? ቀኑ ቅዳሜ ነበር ለጊቢ ተማሪ ቅዳሜ ማለት በሳምንቱ ሲታቀዱ የቆዩ ተግባራት የሚፈፀሙበት እንደመሆኑ ከጓደኞቼ ጋር የቅዳሜ አንዱ እቅዳችን እንደው ድንገት ደርሰው የከዱን ልብሶቻችንን ማስቀነስ(ማስጠበብ)ነበር ። ከጊቢያችን ፊትለፊት ወዳሉ አንድ በነጭ ፀጉርና ጢም ወዳሸበረቁ የልብስ ባለሙያ አባት አቀናን ። የስራ ና የእርጅና ብዛት በሸበሸበው በሚያሳዝን እጃቸው የልብስ መኪናቸውን እያሽከረከሩ በማለዳው ስራቸው ላይ ተጠምደዋል ። እንደ እኛው ደንበኛ ባለጉዳዮች አግዳሚ ወንበሩን ሞልተውታል ። የዚህኔ አባት ሰላም አደሩ ለሚል የሰላምታ ምላሻችን ፈገግ እያሉ የት እንደሚያስቀምጡን ግራ ተጋብተው በአይናቸው ወንዶቹን ተነሱላቸው አይነት አስተያየት ተመለከቱአቸው ። የዚህኔ ከአጠገባቸው ቡና የምትሸጥ ልጃገረድ እዚህ እረፍ በሉ ብላ ወንበሮች አመቻቸችልን የቡናዋ እና ዕጣኑ ሽታ ለቡናው የመጣን እስኪመስል እንድንጠጣ ጋበዘን እኔና ጓደኞቼ በሽታ ነው ምንለየው ቡና ቀማሽ ብንባል እንኳን ግነት አይሆንም ። አንግዲ በጠዋቱ ጨዋታው ደርቷል ቡና ባለበት ርዕስ አይጠፋም የልብስ ባለሙያው አባትም ይህቺን አጋጣሚ መጠቀም ሳይፈልጉ አልቀሩም ስለትምህርት ስለ ኑሮው ሲጠይቁን ያው የግቢ ተማሪ ማማረር ከደሙ የተዋሃደ ነውና ወንድሞች ኸረ ፋዘር በቃ ከተማ ውስጥ እየለፈለፍን መሄድ ነው የቀረን ምንድነው ኑሮው? በምሬት ነበር የሚያወሩት። ፈዘር ቀጠሉ በሉ ኑሮውን የምታዩት ነውና የያዛችሁትን ልብስ በ50 ብር ነው ምሰራላችሁ አሉን እንዴ ፋዘር አልተወደደም የነሱ ብዙ ስለሆነ ይሁን የኛ እኮ ሁለት ልብስ ብቻ ነው ተለያይተን ስለማንወጣ ነው ተንጋግተን የመጣነው ከአፌ ሳልጨርስ አንደኛው ወንድም ያምሻል እንዴ የኛስ የቱ ነው ብዙ የሚባለው? ቲሸርት ብቻ እኮ ነው የያዝነው ብሎ አምባረቀብኝ። ፈዘር ባቀረቀሩበት ፈገግ እያሉ ። የዋጋው ነገር አሳስቧቿል ካነሳችሁት አይቀር አንድ ነገር ላጫውታችሁ አሉን ሁሌም ወሬያቸው ቀልድ መሰል ቁምነገር አዘል መልዕክት በመሆኑ ልንሰማቸው ሰፍ አልን ። ስዕለ አድኖ የሚሸጥ አንድ ሰው ነበር ። ከቤተክርስቲያን ፊትለፊት ስዕለ አድኖ የሚባሉትን የማሪያም፣የገብርዔል፣የሚካኤል•••••••••••••••••ወዘተ ስዕሎች በመሸጥ ላይ ሳለ አንድ አውቆ አበድ ሊገዛ ወደ እርሱ መጣ የቱን እንደሚፈልግ ጥያቄ ሲቀርብለት አስመርጠኝ አለው። እያስመረጠው ልክ JESUS ፊልም ላይ ኢየሱስን ሆኖ የተወነውን ሰው የሚመስለው ላይ ሲደርስ ፈገግ እያለ ይህንን ስጠኝ የመድኃኒያለምን አለው ። አኛም ተመስጠን መስማታችንን ቀጠልን ። ከዚያም ዋጋው ስንት ነው አለ እጁን ወደ ኪሱ እየከተተ። ሻጩ 90 ብር ብቻ የሚል ምላሽ ሰጠው በቅፅበት እጁን ኪሱ መክተቱን ገታ አድርጎ እንዴ ምነው 90 ብር ተወደደ አለው። ምነው ምነው ለስንት ነገር ከዘጠና ብር በላይ ታወጣ የለም የሚል ምላሽ ሰጠው እንዴ ባለቤቱ ራሱ 30ብር ነው የተሸጠው ፎቶው ሶስት እጥፍ ብሎ ቁጭ አደረገው አሉን ሁላችንም በመገረም ሳቅን ። ሳቃችንን ካስጨረሱን በኋላ ለምን ይመስላችኋል ኀጢያተኛዋ ሴት የ300 ዲናር ሽቶ በጌታዋ ፊት ስትሰብር ይሁዳን የፀፀተው ለይሁዳ የኢየሱስ ዋጋ 30ዲናር ነበር ሰላሳ ዲናር ለሚገመት ሰው 300ዲናር ማባከን ተገቢ ነው? አይነት ነው ንግግሩ ።ይሁዳ ተው 18 ሽጥልን ? አይ በዚህ ዋጋ አልመጣም ። እሺ 20 አይ አይ ያዋጣም ። እሺ 30 ሰላሳ አይ በቂ ነው ሰላሳ እንኳን ያወጣል በቃ ሽጬላችኋለው ያለ ይመስለኛል አሉ በሀሳብ ሽቅብ እየተመለከቱ ተደራድሮ ለጌታ የገመተለት ዋጋ 30ነበር ያቺ ሴት የሰው ግብዣው ላይ ስትገኝ የድግስ ወጡ ሽታ አይደለም የጠራት የመጠጡ የፌሽታው ሳቢነት አይደለም የጠራት ድንኳን ሰባሪ ሆና አይደለም ። ጋባዡ እንኳን ምን ትሰራለች እቺ ሀጢያተኛ በእውነት ይህ ሰው ነብይ ቢሆን ባወቃት ነበር ለካ ነቢይ አይደለም ለካ ከኋላው ከኋላው ህዝብ የሚከተለው በስህተት ነው ድግስ ብዬ ገንዘቤን አባከንኩ አይነት ፀፀት ነው የፀፀተው እርሷ ግን ከምን እንዳዳናት ታውቃለች ሽቶ እንደማይመጥነው ብትረዳ እንባዋን አፈሰሰች አንድ ሲኒ እንባ ለማውጣት ስንት ዘመዶቻችን መሞት አለባቸው እንባ ኮ ቀላል አይደለም በአይሁዳዊያን ሴቶች ፀጉራቸው ክብራቸው ነው ክብሯን በአደባባይ በፊቱ አኖረችለት እግሩን በፀጉራ ታብሰው ነበር።ውስጣቸው እየነደደ እንባቸው እርግፍ እርግፍ እያለ እናንተ ጋር ኢየሱስ ዋጋው ስንት ነው አሉን? ሁላችንም ጥያቄያቸውን እያሰላሰልን አቀረቀርን ለኢየሱስ ምን ያክል ግዜ ትሰጡታላችሁ? ትታዘዙታላችሁ ወይ? ለሱ ደስታ ወይስ ለሰዎች ወይስ ለራሳችሁ ነው የምትኖሩት ? እናንተ ጋር ተመችቶት እየኖረ ነው ወይስ ለእርሱ የምትሰጡት ጥቂት ግዜ ይፀፅታቹአል? አንድ ታሪክ ልጨምርላችሁ አሉን አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጉባኤው በአምልኮ ቀን ተሰባስቦ ያመልካል ዝማሬ እንዳለቀ ስብከት ተጀመረ ፀጥታ በሰፈነበት ድንገት ተጮኸ ጉድ ሆንን ጉድ ሆንን እያሉ ዘበኛው ከውጪ እየሮጡ ገቡና በሩን ዘጉት ምንድነው ምንድነው? ተባለ................ ይቀጥል?ላል ። ✍️Aksan Adane 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 👆👆👆join&shear👆👆👆
Show all...
🩸የደም ልሳን🩸 ክፍል 9 ✍ written by Aksan Adane @wegelbeArt ..........እኛም ታዘን እንሄዳለን ሁሌ ይህንን ታወራለች ። የህብረት ፀሎታችን ይበዛና ይጨምር ነበር ። ብዙ ተግዳሮቶች ቢገጥሙንም ጌታ እየረዳን እያለፍን ነው ብሌን ተመረቀች በምርቃቷ ቀን በከተማው ወንጌል ስርጭት ስታካሂድ ነበር ። ምሳሌ የምትሆን ሴት ናት እቤታቸው በነበረው የምርቃቷ ፕሮግራም ስላሳለፈችው ታሪክ በአጭሩ እንድትናገር እድል ተሰጣት ሁሌ የማትቀይረው ርዕስ ኢየሱስ ብላ ጀመረች 20ደቂቃ በማትሞላ ንግግሯ ወደ 30ሰው ጌታ ኢየሱስን ተቀበለ እኔ መንፈስ ቅዱስ በእርሷ የሚሰራው ስራ እንባ ከማውረድ ውጪ ምናገረው ጠፋኝ ። ደስ የሚል ግዜ አሳልፈን ወደ ቤት ተመለስኩ ማሚ ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ነበር አይኗ ቀላልቷል ተደናግጬ ምነው እናቴ አልኳት ከነ ብሌን ቤት ተደውሎልኝ ነበር የመጣሁት አከራያችን ደውላልኝ አለችኝ እና አልኩኝ ለመስማት እየጓጓሁ ነገውኑ ቤቴን ልቀቁ ብላለች ሱቁንም እንደዛው አለችኝ ወንድምሽ ስሜታዊ ሆኖ ሊጣላቸው ሞከረና ወደ እስር ቤት ወሰዱት አለችኝ እንባዋ እርግፍ እርግፍ እያለ የኔ እናት ጠላትሽ ዲያቢሎስ ያልቅስ ለዚህች ነው ምታለቅሺው አልኳት ፈገግ እያልኩ ። ግራ በመጋባት ስሜት እያየችኝ አንቺ ልጅ ያልኩትን ሰምተሽኛል ግን ወይስ ማገናዘብ አቆምሽ አለችኝ ነገ በወር አንዴ ለሶስት ቀናት የሚደረገው ታላቁ ፀሎታችን የሚደረግበት ቀን ነው ። ጌታ መልካም ግዜ እንዲሰጠን ትንሽ ልፀልይ አታልቅሺ ብያት ወደ ጓዳ ገባሁ የሰይጣን መንደር ሲደበላለቅ ይታወቀኛል ነብሴን እረፍት እረፍት እረፍት ይሰማታል ዋስትና ካለው ጋር ፍቅር ጀምሯታል የሚለው መዝሙር በውስጤ እየሞላ በተንበረከኩበት ማመስገን ብቻ ጀመርኩ ።ምንም እናቴ የነገረችኝን ሁሉ ረስቼ ከጌታዬ ጋር አውርቼ ከሰአታት በኋላ ወደ ሳሎን ስመለስ 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 ብሌን አባቷና ወንድሜ ሳሎን ቁጭ ብለዋል እናቴ በደስታ ተፍለቅልቃለች የኔ ልጅ ቆይ እንደ ተፈታ አውቀው ነው ወይስ ምንድነው ስነግርሽ ምንም ያልመሠለሽ ግራ አጋባሽኝ እኮ አለችኝ ። ሲጀመር ታስሮ ነበር እንዴ አንተ ታስረህ ነበር አልኩት እየሳቀ ኸረ እህቴ ከእስራት ሁሉ ኢየሱስ ፈቶኛል አለኝ በቃ ብዬ ተሳሳቅን ያማችኋል እንዴ ቀልድ እኮ አይደለም አለችን ቡናዋን እየቀዳች ። በጌታ የዳነ ሰው አይደለም ቢታሰር ቢሞት ምን አስጨነቀሽ አልኳት ብሌኔም ትንሽ መንገድ ከከፈቱላት አትቻልም በብዙ ማፅናናት ቃል ተናገረቻት አባቷም እንግዳ አስቀምጠን ነው የመጣነው ልጃችሁን አምጥተናል እኛ እንሂድ ብለው ተነሱ እኔና ብሌኔም ለጠዋቱ ፀሎት ተቀጣጥረን ሸኘኋቸው። እናቴ ጌታን ስታመሰግን አመሸች አይዞሽ ቤት ልቀቁ የተባለውም አይሆንም እሺ ሰይጣን ሀሳቡ እኔ በእግዚአብሔር ላይ እንዳጉረመርም ነበር እኔ ደግሞ ያለኝን ሁሉ ጠራርጎ ቢወስድብኝም ጌታዬ ላይ ድርድር አላውቅም ያ ስለገባው ከምደክም ብሎ ትቶታል አትጨነቂ አልኳት ደስ ብሏት አቀፈችኝ ልጄ በእምነትሽ ፅኚልኝ አለችኝ ጌታ በአንድም በሌላም ይናገራል አሜን ጌታዬ ብዬ ተቀበልኩ ። እስኪነጋ እንቅልፍ አልወስድ አለኝ ሁሉም ከያሉበት መጥተዋል ማለዳ ፊታቸውን እስከማይ ናፈኩኝ በባለፈው ወር ፀሎታችን ሙሉ የሌላ ዕምነት መዘምራን ነበር የተገኙት ለክርክር መጥተው ጌታ አገኛቸው በየወሩ እንዲህ ያለ ተዐምር ስለሚደረግ ቀኑ ይናፍቀኛል እንደ ልማዴ በማለዳ ተነስቼ 11:45 ከቤት ወጣሁ በወፎች ጫጫታ እና በሊሊ ዝማሬ እየተደሰትኩ ወደ ፀሎት ስፍራችን አቀና ጀመር ብዙም የሰው እንቅስቃሴ አይታይም ከፊት ለፊቴ ተንሽ ራቅ ብሎ አንድ ጥቁር ካፖርት የለበሰ ሰው የመብራት ፖል ተደግፎ ቆሟል በኢየሱስ ስም አልኩና ጉዞዬን ቀጠልኩ እየቀረብኩት ስመጣ ትኩር ብሎ እያየኝ ነው በኢየሱስ ስም ማለቴን እየደጋገምኩ ቀጠልኩ ከአጠገቡ አለፍኩ ማለፌን አላመንኩም ነበር አንድ አራት እርምጃ እንደተራመድኩ ይከተለኝ ጀመር......... ...............ይቀጥላል............. ✍ written by Aksan Adane ፀሀፊት አክሳን አዳነ 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 👆👆👆join&shear👆👆👆
Show all...
🩸የደም ልሳን🩸 ክፍል8 ✍ written by Aksan Adane ................አንድ ነገር ተከሰተ በሰላም እየሄደ የነበረው መኪና በድንገት ወደቀ ከምንም ጋር ተጋጭቶም አይደለም ብቻ ተገለበጠ በአደጋ ግዜ መውጫ ወጣን ማንም ምንም አልሆነም ። ሰዉ ሁሉ ያለቅስ ጀመር እኛ ቢሆንም እልልታ ባይሆንም እልልታ ኢየሱስ ነው ጌታ የሚለውን መዝሙር ደስ እያለን እንዘምር ጀመር ቀስ በቀስ ሰዉ ማልቀሱን ትቶ ትኩረቱ ወደእኛ ዝማሬ ይሳብ ጀመር አላቆምንም ረጅም ደቂቃዎች ዘምረን በዚያው ከመካከላችን አንድ ወንድም እዮብ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ወንጌል መናገር ጀመረ ለዚህ የእውነት ቃል ሁላችንም ሰገድን የዚህኔ ነበር ከመጣው መንፈስ የተነሳ ሰዎች እያነቡ ይሰሙት ጀመር ከሹፌር እስከ ተሳፋሪ ድረስ ለዚህ ህያው ቃል ለእግዚአብሔር ድምፅ ምላሽ ሰጡ ሁሉ እጆቻቸውን አንስተው አለምን ሰይጣንን ክደው ለዘለዓለሙ ጌታ ህይወታቸውን ለመስጠት ቃል ገቡ አብዛኞቹ ሲነግሩን ህልም አይተው እንደወጡ አሁን የሆነውን ሁሉ ቀድመው አይተው የነበሩም ነበሩ እየተገረምን በእንባ ጌታን እያመሰገንን እንዘምር ነበር ይህ ሁሉ የሚሆነው ሌላ መኪና እስኪመጣ መንገድ ላይ ቆመን ነበር ። የዚህኔ አንደኛዋ እያነባች እባካችሁ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ እንሂድ ህይወቴ በስቃይ የተሞላ ነው ከቤተሰቤ የወርስኩት አምልኮ አለ ቡና ካላፈላሁለት እንኳን የሚቆጣ በዚህ ምክኒያት ባለቤቴን ሁለት ልጆቼን አጥቼያለሁ እንደዚህ ደስተኛ ሆናችሁ ሳይ መኪናው ሳይገለበጥም ወደ እናንተ ልመጣ ነበር ነገር ግን እንደሚገድለኝ እየዛተ አስፈራራኝ አለችን ከእኔ ጋር ተፋጠጥን አየችኝ አየኋት ያ ቤተሰቦቼን የጨረሰውን ዘንዶ በመንፈስ አየሁት ታላቅ ቁጣ ሞላብኝ የሁሉ ገዢ ከሆነው ከአምላኬ ለማይበልጥ አይደለም ለውደድር ለማይቀርብ ለዚህ ምናምንቴ መንፈስ እኔ እበቃዋለሁ ። በእኔ ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ እቀጠቅጠዋለሁ አለኝ ተጠጋኋት ወደ ኋላ ሸሸች ቁሚ አልኳት አይኖቿ ደም ለበሱ መንፈሱ አናቱን እንደተመታ እባብ ሲወራጭ ነው የማየው ። እንዲህ ማለቴን ብቻ አስታውሳለሁ ማንም ሊፈታው ያልቻለውን ማህተም በፈታው ሁሉን ድል በነሳው የይሁዳ አንበሳ በሆነው ገና ሳልጨር እንዳትጠሪው እለቃለሁ ብላ ወደቀች በታላቅ ጩኸት ይለምን ጀመር በጌታ በኢየሱስ ስም ብዬ አይኖቿን ስመለከት ደም እያስተፋ መንፈሱ ለቋት ሄደ ሁሉም ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለታረደው በግ ለርስታችን መያዣ መንፈስቅዱስ ክብር ሰጠ. ደስ እያለን እንዘምር ጀመር ትራፊክ ፖሊስ ሌላ እና መኪና መጥቶልን በሌላ መኪና ደረስን ሁሉም የመጣበትን ትቶ ከእኛ ጋር ወደ ፀሎቱ ተራራ ሄድን ። 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 በወንጌል በስነ-ፅሁፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ እንባዬን እንዴት ልግታው በሁለተኛው መኪና የነበሩት ወንድም እህቶቻችንም ከ አስር በላይ ለመሆኑ ሰዎች መስክረው ወደ ተራራው ይዘዋቸው መጡ ለአንድ ሁለት ሳምንት ያለማቋረጥ እዚያው ስንፀልይ ቃል ስናጠና ከረምን ብዙዎቹ በመንፈስ ቅዱስ እሳት ተጠመቁ ጌታ ብዙ ድንቅን እያደረገ ሰነበትን ግማሹ ከአዲስ አበባ ግማሹ ከጅማ ግማሹ ከሰሜኑ ክፍል በፊናው ዘመኑን ሊጠይቅ ለስራ ጉዳይ ብብዙ ምክኒያት ከቤቱ የወጣ ህዝብ መዳን ሆኖለት ለሌላው ሊመሰክር ወደ የመጣበት ተበተነ ስልክ ተቀያይረን እንደዋወል ጀመር ሁሉም በያሉበት አከባቢ ከወንዶሞች ጋራ ህብረት ማድረግ ጀመሩ በቤተክርስቲያን የድህነት ትምህርት ጀመሩ ጌታ በፀሎታችን የጀመረው ስራ አላቆመም እኛም መፀለይ አላቆምንም በወር አንዴ ሁላችንም ተሰባስበን ለሶስት ቀናት ታላቅ ፀሎት ላላመኑት ይደረጋል በየወሩ ሲመጡ የዳኑ ሰዎች ቁጥር ይጨምር ነበር መስከረም ብቻ አንተውም ደቀመዝሙር እስኪሆኑ እንከታተላቸዋለን እንፀልይላቸዋለን እነርሱም ለሌለው በድፍረት መናገር ሲጀምሩ ሲጠነክሩ እንተዋቸዋለን እኔም የግል ትምህርቴን ቀጠልኩኝ እናቴና ወንድሜም ስራ ጀምረው ጥሩ እየሄዱ ነው አክስቴ ባለትዳርም ስለሆነች እርሷን ላለመጫን ቤት ተከራይተን እንኖር ጀመር ያኔ በዚያ ትልቅ ቤት ስንኖር ደስታ ያልነበረን ሰዎች አሁን የማያቋርጥ የእግዚአብሔር ሰላምና ደስታ ያኖረናል ። የለንም እዛው ጊቢ ውስጥ ነብሳትን ወደ ጌታ መንግስት እንዲመጡ ማድረጓን አላቆመችም ደግሞ ሁሌም እንደ እኔ በታላላቅ የአጋንንት እስራት ተተብትበው ለነበሩ መፍትሄ ናት ይገርመኝ ነበር እግዚአብሔር ሊጠቀምባት ሲፈልግ አታንገራግርም እኔ እኮ አልችልም ብላ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት አትገድብም እራሱ እንደሚያደርግ አምና ስለምትታዘዝ ታላላቅ ነገሮችኝ በእርሷ ያደርጋል ።ዘንድሮ ትመረቃለች እኔ የሚቀጥለው አመት ተመርቃ እንደወጣች ሙሉ ጊዜዋን ሰጥታ በሚሽነሪነት ወደ ሌሎች የዓለም ሀገራት ለመሄድ ዝግጅት ላይ ናት ሁሌ ከአብ የማይጠፋው ቃል ማቴዎስ 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁷ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ³⁸ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው። ስለ መከሩ ሰራተኞች እንዲሄዱ እንፀልያለን እኛም ታዘን እንሄዳለን............. .................ይቀጥላል................... ✍ written by Aksan Adane ፀሀፊት አክሳን አዳነ 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 💐💐 @wengelbeArt 💐💐 👆👆👆join&shear👆👆👆
Show all...
🧎‍♀️🧎‍♂️🌍መድህኑ በዓለም ሁሉ ይታይ 🌎🧎‍♀️🧎‍♂️ “እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።” ኢሳይያስ 52፥10 የፎሮክ ሕዝብ የህዝቡ ስም: ፎሮክ የሚገኙበት ቦታ :ሱዳን የህዝቡ ቁጥር 1,021, 000 የህዝቡ ቋንቋ :ፉር ክርስትና በ% :0% የወንጌል አማኞች በ%: 0% መፅሐፍ ቅዱስ በቋንቋቸው :የለም የእየሱስ ፊልም በቋንቋቸው :የለም 🌍ለፎሮክ ሕዝብ የምልጃ ፅሎት🌎 መልካሙ እረኛ የነፍስ መልህቅ የዓለም ሁሉ መድሀኒት የሰማይ እና የምድር ዳርቻ ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር አባታች ሆይ የፎሮክ ሕዝቦች አንተን ወደ ማወቅ እንዲመጡና ድምጽህን መስማት እንዲጀምሩ እንለምንሀለን🙏 በዘመናችን አንተ ማድረግ ያቃተህን መርታት የከበደህን ልብ ከቶ አላየንምና ዛሬም በሁሉን ቻይነትህ የፎሮክን ሕዝቦች በፍቅርህ አሸንፈህ የራስህ መጠቀሚያ ገንዘብህ እንድታረጋቸው በልጅህ በእየሱስ ስም እንለምንሀለን🙏 ጌታ ሆይ! በቀራንዮ መስቀል ላይ የተከፈለላቸውን ዋጋ ማስተዋል እንዲችሉ መንፈስህ የልብ አይኖቻቸውን እንዲከፍትላቸው እንፅልያለን🙏 ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ማስተስሪያ ትሆን ዘንድ ራስህን የሰጠኸን መድህን በዛ ምድር ላይ ከፍ እንድትል ያቺን ምድር በፍቅርህ እንድትገዛት እንፅልያለን🙏 የመከሩ ጌታ የመከሩ ሠራተኞችን እኛኑ በኃይል አስታጥቀህ ወንጌል ወዳልደረሰባቸው አስቸጋሪ በተባሉ ሥፍራዎች ላይ መንግስትህን እንድታሰፈ እንለምንሀለን 🙏 "ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።ዮሐ14፥14" ብለህ በቃልህ እንደነገርከን የለመንህን ሁሉ ፈፅመህ እንድታስገርመን እያመንን እንፅልያለን በእየሱስ ስም ማንነትህ በዚያ ስፍራ እንዲጎላ የተቀደሰውን መልካሙን ክንድህን በመካከላቸው ገልጠህ በዛች ምድር ያሉ ሁሉ ማዳንህን እንዲያዩ በጌታ በእየሱስ ስም ፅለይን🙏 🙏አሜን🙏
Show all...
🧎‍♀️🧎‍♂️🌍እንዲልክ ለምኑት🌎🧎‍♂️🧎‍♀️ “አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት።”   — ሉቃስ 10፥2 የታይደም ጎሣ በቬትናም የሚኖሩ በቀለማቸው ጥቁር የሆኑ የታይደም ጎሣ 804‚000 የሕዝብ ብዛት ያላቸው ሲሆን ከዛም መካከል 0.1 % ክርስትያኖች ይገኛሉ:: የታይ ህዝቦች በሰሜናዊ ቬትናም ቀይና ጥቁር ወንዞች ዳርቻ የሚኖሩ ሲሆን ጥቁር ሕዝቦች የተባሉት የሴቶቻቸው ልብስ ጥቁር በመሆኑ ነው፡፡ ሕዝቡ ጨዋ፣ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይ ነው፡፡ ለሰው አዛኝና ተጨዋች ሲሆኑ በዓል ለማድረግ ማንኛውንም አጋጣሚ ይጠቀማሉ፡፡ ኢኮኖሚያቸው እርጥብ በሆነ የሩዝ ምርት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ለምግብና ለሽያጭ ይጠቀሙበታል፡፡ ወንድም ሆነ ሴት እርሻ ያርሳሉ፤ ይቆፍራሉ፤ ዓሣ ያጠምዳሉ፤ ምግብ ያበስላሉ፤ ልጆች ይጠብቃሉ፣ ቤት ያፀዳሉ፤ ልብስ ያጥባሉ። አብዛኛው የታይ ሕዝቦች ጎሳዊ ሃይማኖትን ይከተላሉ ይህም ቴራቫዳ ቡዲሂዝም ከባሕላዊ የቁስ አምልኮ ጋር የተቆራኘ ሲሆን ሕዝቡ እርዳታ ሲፈልግ ልመና የሚያቀርበው በእርኩሳን መናፍስትና በቁሳቁሶች አማካኝነት ነው፡፡ ወደ ሞቱ ቅድመ አያቶቻቸው በመፀለይ አያቶቻቸውን ያመልካሉ እንዲሁም በማንኛውም ሰውና ቁስ ውስጥ መናፍስት እንዳሉ ያምናሉ በጠባቂ መናፍስትና በአካባቢው መናፍስት ያምናሉ እነርሱን ማስቆጣት እንደሌለባቸው የሚያምኑ ሲሆን የመርገምና የበረከት ምክንያት እንደሆኑም ያምናሉ፡፡ 🧎‍♀️🧎‍♂️🌍ለታይደም ጎሳ የምልጃ ፅሎት🌎🧎‍♂️🧎‍♀️ በሰማይ በከፍታህ ያለህ ልዑል አምላክ ሆይ ስምህን በታይ ሕዝቦች ዘንድ ትቀድሰው ዘንድ ያቺ በሰማይ የሆነችው ፈቃድህ በታይ ምድርም እንድትሆን የታይ ምድርን በሉአላዊነትህ እና በኃይልህ እንድትገዛት እንማፅንሀለን🙏 አባት ሆይ ማንኛውም የፅድቅህ እና ያንተ መለኮታዊ አገዛዝ ጠላት ሁሉ በስምህ ስልጣን ከዛች ምድር እንዲነሳና ያንተን ቅዱሱን መንፈስን ተቀብለው ከክፉ መናፍስት አሰራር ሁሉ ነፃ እንድታወጣቸው እንለምንሃለን🙏 የበረከት ሁሉ ምንጭ የሆንከው ጌታ የታይ ሕዝቦችን መከርን እንድትባርክላቸው እውነተኛ የርኅራሄ፣ የደስታ እና የሰላም መገኛ እንደሆንክ እንዲገነዘቡ አንተ የዘላለም ህይወት ማግኛ ብቸኛ መንገድ እንደሆንክ እንዲበራላቸው እንለምንሃለን🙏 ጌታ ሆይ ካየነው አኅዛዊ መረጃ ወንጌል ያልደረሰባቸው የህዝብ ክፍሎች እጅግ ብዙ ናቸውና ወደ እዛች ምድር ወንጌልህን ይዘው የሚፈጥኑ የመከሩ ሰራተኞችን ሚሲዮናዊያንን እንድታዘጋጅላቸው ወደ ታይ ምድር እንድታፈጥንላቸው በልጅህ በእየሱስ ስም እንለምንሃለን🙏 አሜን🙏🙏
Show all...