👉በርባን
#ያ_በርባን_ማነው ? _በርባንን _ፍታልን!
👉 በከተማው ታዋቂ ሰው ነበር፨ በወቅቱ ያሉትን አይሁዳዊያንን ጠርተህ፥
#በርባን ማነው? ብለህ ብትጠይቅ የሚመልሱልህ መልስ እነዚህ ናቸው፦👉👉 _በርባን ወንጀለኛው፣በርባን ነፍሰገዳዩ፣በርባን ጉልበተኛው፣በርባን አጭበርባሪው ፣በርባን ፍቅር አልባው_በርባን ሰካራሙ_በርባን_ዝሙተኛው_በርባን አድመኛው_በርባን በርባን ተው እስቲ የበርባንን ጉዳይ....{ብለው ይመልሳሉ}፨
✍ ለእኛስ....ይህ በርባን ማነው??
👉ሁላችንም መፅሀፍ ቅዱስ ስናነብ ፈሪሳውያን
#ምስኪኑን ኢየሱስ
#ይሰቀል ብለው_ወንበዴውን በርባን
#ይፈታ ሲሉ
#ተበሳጭተናል #የኢየሱስን_ፊልም ለፋሲካ እቤታችን ስናይ ሳለ
#በርባን ተፈቶ እየሳቀ ወደ ህዝቡ ሲሄድ
#ብስጭት ብለናል፨
✍ጥያቄም ጠይቀናል እንዲህ ብለን፧፦
እንዴት
#ፃድቁ ይሰቀል ብለው
#ሀጥያተኛው ይፈታ ይላሉ? 🙏እንዴት
#ቅዱሱ ይሙት ብለው
#የረከሰው ይኑር ይላሉ?🙏እንዴት
#የሰላም_አለቃው ይገደል ብለው
#አመፀኛው ይለቀቅ ይላሉ?፨
✍
#ጲላጦስ ትልቅ
#ውጥረት ውስጥ ነበር፣ህዝቡም
#በርባንን ፍታልን ሲል እርሱም ህዝቡን ለማስደሰት
#በርባንን ሲፈታው በራሱ
#ስልጣን እንደ ፈታው አስቦ ይሆናል፨ነገር ግን
#በርባንን የፈታው ጲላጦስ
#አይደለም!! ታዲያ
#በርባንን የፈታው ማነው????
🎯ይህስ
#በርባን ማነው??.
✍ እግዚአብሔር አብ
#ልጁን ወደ ምድር ሲልክ
#በመስቀል ሞት ዋጋ እንዲከፍል ነው👉 ስለዚህ
#ጲላጦስ በምንም ስልጣን
#ኢየሱስን ይፈታው ዘንድ አይችልም ነበር {ልፈታህ እችላለው ቢለውም} ስለዚህ ቃሉ ይፈፀም ዘንድ አብ የገዛ ልጁን ይሰቀል ዘንድ ወስኖ በርባንን ፈታው😪
✍ ታዲያ ያ
#በርባን ማነው? እግዚአብሔር አብ
#ፈቶት ነገር ግን ልጁን ለሞት አሳልፎ
#በእርሱ_ፋንታ የሰጠለት??
✍ ያ በርባን ማነው?
#ኢየሱስ ስለ እርሱ ተሰቅሎ እርሱ ከሞት ያመለጠው?
✍ ያ በርባን ማነው?
#ጨዋው የሞተለት እርሱ አድመኛ ሳለ
✍ ያ በርባን ማነው?
#ወንጀለኛ ሳለ ንፁህ የተባለው
✍ ያ በርባን ማነው?
#በደስታ ተሞልቶ ፍርዱን ጌታ የወሰደለት
✍ ያ በርባን ማነው?
#ሀጥያቱ ተሽሮ ከእስር ቤት የወጣው _ጌታ የተመታለት _የተሰቀለለት _ሁለተኛ እድል_ ያገኘው
❗️ያ በርባን _እኔ ነኝ 🙏 ያ በርባን _አንተ ነህ 🙏
ያ በርባን _አንቺ ነሽ 🙏 ያ በርባን __እርሶ ኖት 🙏
ያ በርባን _እኛ ነን 🙏️_ፍርድ ሲገባን ሳለ 🙏_ሞት ሲገባን ሳለ፣በእኛ ፋንታ _ኢየሱስ የሞተልን _አብ የለቀቀን‼️ _እኛ ነን!!!!
📚“በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።”
— ማቴዎስ 27፥16_26
@KaluYiseral @KaluYiseralShow more ...