cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሁሌ መረጃ.com/hule merja

የሰው ልጅ መረጃ የማግኘት መብቱ መገደብ የለበትም...እኛም ይህንን ፍላጎት ለመሙላት እዚ አለን፡፡ሁሌ መረጃ ሁሌ እውነት

Show more
Advertising posts
646Subscribers
+224 hours
+77 days
+2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችንና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆም ከደሙ ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል።" እናት ፓርቲ @EliasMeseret
Show all...
በአምቦ ወረዳ የ90 ዓመት አዛውንት አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ! በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ኢላሙ ጎሮሙጢ የተባለ አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣጡት የምዕራብ  ሸዋ ዞን  ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡  የምዕራብ ሸዋ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  መረጃ እንደሚያመላክተው ተከሳሽ ለቴራ ቀና የተባለው ግለሰብ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የ90 ዓመት ኣዛውንት በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው ባሉበት ቤታቸውን ሰብሮ በመግባት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እንደፈጸመ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ተከሳሽ በእድሜ የደከሙ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ አዛውንትን በጉልበት አስገድዶ መድፈሩ ፖሊስ በህክምና ማስረጃ ያረጋገጠ እና የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለ ዓቃቢህግ መላኩን ተገልፇል በዚኅም  ዓቃቢ ህግ  ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልከቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት ክስ መስርቷል፡፡ክሱን ሲመለከት የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ለቴራ ቀና በስምንት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ መረጃ ያመላክታል፡፡
Show all...
👍 1
ባጃጅ ሰርቀው ለመሸጥ በማሰብ የሰው ህይወት ያጠፉ ግለሰቦች ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ላይ 1ኛ ፍቃዱ ደርበው፣ 2ኛ አያልሰው አባይ፣ የተባሉ ሁለት ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት አስበው ሀምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ባጃጅ በሀይል ለመስረቅ ተስማምተው እና ተዘጋጅተው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጉልት ከሚባለው ቦታ በመሄድ ሟች ፍቃዱ ተሾመ ይነዳት የነበረውን ንብረትነቱ የሌላ ግለሰብ የሆነ ባጃጅ ተኮናትረው ወደ ቆሬ እንዲወስዳቸው ተስማምተው ሁለቱም ተከሳሾች ከሟች ኋላ በመቀመጥ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ባቱ ኮንደሚኒየም ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ 1ኛ ተከሳሽ በምልክት ውጋው በማለት ለ2ኛ ተከሳሽ ሲነግረው 2ኛ ተከሳሽም ሟችን በቢላዋ አንገቱ ላይ ሲወጋው 1ኛ ተከሳሽም ራሱን እንዳይከላከል በለበሰው ልብስ አንገቱ ላይ አንቆ ሲይዘው 2ኛ ተከሳሽ በድጋሜ ሟችን ትክሻው አካባቢ ሲወጋው ሟች ከባጃጁ ላይ ወርዶ አስፓልት ዳር ወድቆ ብዙ ደም ፈሶት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ባጃጇን እየነዳ ወደ ወልዲያ ወስደው ለመሸጥ አስበው ሸዋሮቢት ላይ አንደኛውን የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጠርተው 1ኛ ተከሳሽ በፔስታል ጠቅልሎ የባጃጁን ሰሌዳ አስቀምጥ ብሎ ሰጥቶት ምስክሩም ሰሌዳውን አስቀምጦላቸው አብረው ወደ ወልዲያ እየሄዱ እያለ ጨፋ ሮቢት ሲደርሱ ፖሊስ ይዟቸው ፖሊስ ባጃጇን ሲፈትሽ ሟችን የወጉበት ቢለዋ የተገኘ በመሆኑ በፈፀሙት ወንጀል በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና 671/2/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ክስ ቀርቦባቸው ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷቸው ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር አቅርበው ያሰሙ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ባለመቻላቸው ምክንያት ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት የቅጣት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በዚህም ሁለቱም ተከሳሾች በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡ (ፍትህ ሚኒስቴር)
Show all...
በድሬዳዋ ከተማ ትናንት መጋቢት 18 ማታ አካባቢ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በከተማዋ ድንገተኛ ጎርፍ ተከስቶ የንብረት ጉዳት ደርሷል። ለጉልት ገበያ ሲያገለግሉ የነበሩ በሸራ የተሰሩ ቤቶች በጎርፉ ተወስደዋል። እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም። የብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የዝናቡ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ድንገተኛ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ብሏል።
Show all...
የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ጋር ሊጋጭ ነበር መባሉን የኤምሬትስ አየር መንገድ አስተባብሏል፡፡ የሶማሊያ አየር ተቆጣጣሪዎች ያደረጉት እንደሆነ በተጠረጠረ ድርጊት አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እና ሌላ የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላን ባለፈው እሁድ ወደግጭት አምርተው በመጨረሻ በፓይለቶች ጥረት እንደተረፉ ተዘግቦ ነበር፡፡ ታዲያ ይህንን ጉዳይ የኤምሬትስ አየር መንገድ አስተባብሏል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተናፈሰ የሚገኘዉ የሁለቱ አየር መንገዶች አዉሮፕላኖች ወደ ግጭት አምርተዉ ነበር የሚለዉ ዜና ስህተት ነዉ ሲል አየር መንገዱ አስታዉቋል፡፡ ‹‹በተባለዉ ቀን እና ሰዓት ሁለቱ አዉሮፕላኖች አይደለም እስከ ግጭት የሚያደርስ ጉዳይ ይቅርና ለደህንነታቸዉ ስጋት የሚሆን ምንም ዓይነት መቀራረብ እንኳን እንዳልነበራቸዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ ማረጋገጫ ማቅረብ ይችላል›› ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የኤምሬትስ አየርመንገድ አዉሮፕላኖች ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ማድረግ እና ርቀታቸዉን ጠብቀዉ መጓዝ የሚያስችላቸዉ መሳሪያዎችን የያዙ ናቸዉ ሲሉም አክለዋል፡፡ የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን በቀድሞዉ ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሰረት ቦይንግ 777 የተሰኘ የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን ከኢትዮጵያዉ ቦይንግ 737 ማክስ አዉሮፕላን ጋር ለትንሽ ከመጋጨት መትረፉን አረጋግጫለሁ ሲል አስታዉቆ ነበር፡፡ ለዚህ ጉዳይም ተጠያቂ ያደረገዉ የሶማልያ አየር ተቆጣጣሪዎችን ሲሆን፤ የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ግን በጉዳዩ ላይ እስካሁን ምንም የሰጠዉ ምላሽም ሆነ ማስተባበያ የለም፡፡ በተመሳሳይ በአንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በሌላ የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላኖች ዙርያ ተመሳሳይ ድርጊት የዛሬ ወር ገደማ አጋጥሞ እንደነበር ይታወሳል።(ገልፍ ኒዉስ)
Show all...
ሚሊተሪ ለብሶ ቪዲዮ መስራት ያስቀጣል የፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ከተሰጣቸው ውጭ በተቋሙ የደንብ ልብስ ቪዲዮ በሚለቁ አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ የፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ከሰጠኋቸው ውጭ በተቋሙ የደንብ ልብስ በማህበራዊ ትሥሥር ገጾች ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በሚለቁ አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ። አሁን ላይ በስፋት በተለይም ቲክቶክ የተሰኘ መተግበሪያን በመጠቀም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እውቅና እና ፍቃድ ውጭ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የሚያጋሩ የፖሊስ አባላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ተቋሙ ገልጿል። ተቋሙ ወጣቱን ተደራሽ ለማድረግ በተለይ ቲክቶክን ተጠቅሞ አስተማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የሚያሰራቸው አባላት እንዳሉት ገልፆ ከእነሱ ውጭ ባሉት ላይ ግን እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል። ድርጊቱ ከደመወዝ ቅጣት እስከ ሥራ መባረር የደረሰ ቅጣት እንደሚያስከትልና እስከአሁንም ቅጣት የተጣለባቸው እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዱ ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልፀዋል:: አንዳንድ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተቋሙን እና የአባላቱን ክብር የማይመጥንና በማህበረሰቡም ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ በመሆኑ ይህን ለማስተካከል ይሰራልም ነው ያሉት። የማህበረሰቡን ሞራል የማይነኩ እንዲሁም ሃይማኖትና ፖለቲካ ውስጥ የማይገቡ ቪዲዮዎችን የሰሩና ከተቋሙ የማረጋገጫ ፍቃድ ያገኙት ግን ተንቀሳቃሽ ምስሉን ማጋራት ይችላሉ ብለዋል።
Show all...
👍 1
የ5 አመቷን ታዳጊ የደፈረው ላይ የ6 ወር እስራት የፈረደው ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታገደ። አቶ ሀብታሙ ሙሉነህ ለወንበራ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛ በወንጀል መዝገብ ቁጥር 8429 ተከሳሽ ተክለአብ ገላታ የወንጀል ህግ ቁጥር 622 ድንጋጌን በመተላለፍ የአምስት አመት ህጻን ልጅ አስገድዶ ድፍረት በደል ወንጀል ተከስዉ ጉዳዩን ሲዳኝ የነበረ ሲሆን ተከሳሽን በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ካልክ በኃላ ቅጣቱን 6 ወር ቀላል እስራት በማለት ወስናሀል ይህ ዉሳኔ ለህጻናት መብት ፍ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንዳልሰራና የመንግስትና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ዉሳኔ እንደሆነ በሰፊዉ አቤቱታዎች እየቀረቡ ስለሆነ ዉሳኔ ሰጪ ዳኛ በምን ምክንያት ይህን ዉሳኔ እንደሰጠ ማጣርት እና ማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ እንደ ተቋም ስለሚያስፈልግ መተከል ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ኮሚቴ በመላክ ጉዳዩን በአስቸካይ አጣርቶ እንዲልክልን ሆኖ እስከዛ ድረስ ይህ ዳኛ ስራዉን እየሰራ ይቀጥል ቢባል ሌላ በደል ሊያደርስ ይችላል የሚል እምነት ስላለን ሌላ ተለዋጭ ትእዛዝ እስከሚደርስ ድረስ ዳኛዉ ከስራ እና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይ ሲል በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱን ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ያመለክታል።
Show all...
የአለልኝ የሞቱ መንስኤ ከቤተሰብ ጋር በትዳሩ ምክንያት አለመግባባት ነው ! የካናል ፕሉሱ ጋዜጠኛ አብዱ ሞሀመድ "...ለእረፍት  ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አርባምንጭ  ባለቤቱን ይዞ እንደሄደና ፡ ቤተሰቦቹ ትዳሩን እንዳልወደዱለትና ጭቅጭቅ እንደነበር፡ ከዛም ሞተሩን አሰነስቶ አዲስ ወደሚያሰራው የግል ቤቱ በመሄድ የኤልትሪክ ምሰሶ ላይ ራሱን አጠፋ "  ብሏል በዘገባው ከመሰረተው ትዳር ጋር በተገናኘ ተደጋጋሚ ጭቅጭቆች እንደነበሩ በዩቲዩብ ቻናሉ አጋርቷል።
Show all...
በድሬዳዋ ከተማ የሶስት አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ለአስራ አንድ ወራት ከህግ ተሸሽጎ እንደነበር የገለጸው የድሬደዋ ፖሊስ ህጻን ቢሊሱማ መሃመድ የ3 ዓመት ታዳጊ ክፉን እና ደጉን በቅጡ ለይታ የማታውቅ መሆኑን ገልጿል፡፡ ተጠርጣሪው ግለሰብ  የእንጀራ አባቷ/ ሲሆን ይሄንን የጭካኔ በትር ከመሰንዘሩ በፊት የቢሊሱማ መሃመድ እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል አልቻለችም በመሃከላቸው መግባባት ባለመኖሩ ተለያይተዋል። የቢሊሱማ መሃመድ እናት ወደ ሀሮማያ ከተማ በመምጣት ሌላ ትዳር ትመሰርታለች። ለአጭር ቀናት ቢሆንም ቢሊሱማ መሃመድም በእንጀራ አባቷ ማደግ ግድ የሆነባት ሲሆን ተጠርጣሪው ግለሰብ /እንጀራ አባቷ/ አስከፊውን የወንጀል ደርጊት ፈጽሞ እስከተሰወረበት ቀን ድረስ አብራ በጋራ ትኖር ነበር ፡፡ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ቀን ግን ተከሳሽ የሶስት ዓመት ህጻን ቢሉስማ አስገድዶ ከደፈራት በኃላ ህይወቷን በማጥፋት ከአካባው ይሰወራል፡፡ ግለሰብቡ ድርጊቱን በመፈጸም ከአካባቢው ተሰውሮ ድሬዳዋ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ መቆየቱን የመልካ ጀብዱ ፖስ ጣቢያ አዛዥ ም/ኮማንደር ሻምበል ተካኝ ተናግረዋል፡፡ ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው ግለሰብ መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ተከሳሹ ግለሰብ/እንጀራ አባቷ/ ፍርድ ቤት ቀርቦ ለምን  ህጻን አስገድዶ በመድፈር ሊገላት እንደቻለ ሲጠየቅ ‹‹ሰይጣን አሳሳተኝ›› በማለት ምላሽ መስጠቱን ፖሊስ አስታውቃል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊስ የልጄ ደም ፈሶ እንዳይቀር ስላደረገው ጥረት አመሰግናለሁ ያሉት የቢሊሱማ መሃመድ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሮዳ በክሪ ልጄን አጥቼ በሃዘን ተቆራምጄ ባለሁበት ጊዜ የድሬዳዋ ፖሊስ የልጄን ገዳይ ስለያዘልኝ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።
Show all...
የኢትዮጵያ አወ‍እሮፕላን በሱማሌላንድ አየር እየበረረ በሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረ የኤሚሬትስ አውሮፕላን ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ከመጋጨት ለጥቂት ተረፈ በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ  አየር መንገድ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ከነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በድጋሚ ከመጋጨት ለጥቂት መትረፍ ተሰማ። ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሰጠዉ ትዕዛዝ በተመሳሳይ የጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ የነበሩት ንብረትነታቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የኢትዮጵያ መንግስት የሆኑት አዉሮፕላኖች በድጋሚ ከመጋጨት አደጋ መትረፋቸው የሶማሌላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለስልጣን ማስታወቁን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ባለፈው የካቲት ወር በተመሳሳይ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ አውሮፕላኖች ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸው ይታወሳል። እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በ 37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን UAE722 እና በተመሳሳይ በ 37,000 ከፍታ ላይ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ETH690 ለመጋጨት ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀራቸዉ የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ባደረጉት ጥረት አብራሪው በፍጥነት ከፍታውን በመቀየር ወደ 39, 000 ጫማ ከፍ እንዲል በማድረግ የተፈራው አደጋ ለጥቂት ሳይደርስ እንዲቀር አድርጓል። በድጋሚ ለተፈጠረዉ ክስተት የሶማሌላንድ የሲቪል አቪዬሽን እና አየር ማረፉያዎች ባለስልጣን  የሞቃዲሾ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን የወቀሰ ሲሆን። መሰል ቸልተኝነት እና የእውቀት ማነስ ሞቃዲሾ በሚገኙ የሱማልያ የአቪዬሽን ባለሞያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ መሆኑን አለም ይወቅ ሲል አክሏል። ሁኔታውም የአየር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ሁኔታውን ኮንኗል። Via ካፒታል
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!