cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው ! => በቻናሉ 📌 ፈጣን ፥ 📌 ትኩስ ፥ 📌 ወቅታዊ እና 📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! For promotion @Addis_reporter_bot #ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Show more
Advertising posts
40 639Subscribers
-424 hours
-1367 days
-43330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአማራ ክልል ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም ይቅርታውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ የይቅርታ አሠጣጥ መመሪያዎች መሠረት በበጀት አመቱ ሁለተኛ ዙር በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አንስተዋል። በይቅርታው በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በመታረምና በመታነፅ አርአያነት ያሳዩ፣ ከተበዳይ ወገኖች ጋር እርቅ የፈፀሙ፣ አስፈላጊውን ካሳ የከፈሉ እና ለማህበረሠቡ የወንጀልን አስከፊነት እንደሚያስተምሩ የታመነባቸው 1 ሺህ 431 ወንድ እንዲሁም 29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ገልፀዋል። በተጨማሪም መስተዳድር ምክር ቤቱ የተሠጣቸውን ይቅርታ ባለመጠበቅ ሌላ ወንጀል ፈፅመው በቻግኒ ማረሚያ ቤት የሚገኙ አምስት ግለሠቦችን ይቅርታ መሰረዙንም ኃላፊው ጠቁመዋል። የህግ የበላይነት የሁለንተናዊ ለውጥ እና ለዘላቂ ሠላም መሠረት ነው ያሉት ኃላፊው፤ በክልሉ በሚታየው የፀጥታ ችግርና በሌሎችም አጋጣሚዎች ከማረሚያ ቤት የወጡ ፍርደኞች እና ጉዳያቸው በሂደት ላይ የነበሩ ታራሚዎች ተመልሠው በህግ እንደሚዳኙም ገልፀዋል። @Addis_Reporter
Show all...
👍 1
ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት #Ethiopia | የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ማዋሉን በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት በወረዳው ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረው ፀብ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ አዛዡ አክለውም በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን ጉድጓድ እየቆፈረ እያለ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህፃኗን ጉዳት ሳይደርስባት መታደግ መቻሉንና በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናቷን እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የገለፀት ፖሊስ አዛዡ በቤተሰብ መካካል አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ችግሩን በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲሉ ፖሊስ አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን መረጃ ያመለክታል። @Addis_Reporter
Show all...
ራይድ እና ቪዛ የትራንስፖርት ክፍያን ለማቀላጠፍ ተጣመሩ፡፡ በኢትዮጵያ ቀዳሚው የጥሪ-ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ራይድ እና ታዋቂው ዓለም አቀፍ የድጂታል ከፍያ ተቋም ቪዛ ጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የትራንስፖርት ክፍያቸውን በራይድ መተግበሪያ አማካኝነት ለመፈጸም የሚያስችለውን ጥምረት በዛሬው ዕለት አበሰሩ። ይህ ጥምረት ጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና ዲያስፖራዎች የቪዛ ካርዳቸውን ብቻ በመጠቀም የመጓጓዣ ክፍያቸውን እንዲያከናውኑ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አማራጭ የማቅረቡ ጥረት ጅምር ነው፡፡ በዚህም መንገደኞች ስለ ገንዘብ እና ምንዛሪ ሳይጨነቁ በኢትዮጵያ አርኪ ቆይታ እንዲኖራቸው ያግዛል። የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳምራዊት ፍቅሩ “ለጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች እና ለዲያስፖራ አባላት ይህንን አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የክፍያ አማራጭ ለማቅረብ ከቪዛ ጋር መጣመራችን አርክቶናል'' ብለዋል። አያይዘውም “ትብብሩ የኤፌዲሪ መንግስት በቅርቡ ካስጀመረው የድጂታል ኢትዮጵያ 2025' ትልም ጋር በጥብቅ ከመተሳሰሩ በተጨማሪ፤ የራይድን መተግበሪያ ለመጠቀም በጎብኚዎች በኩል የታየውን ፍላጎት በብቃት ለማስተናገድ ያለንን ተነሳሽነት ያመላክታል" ሲሉ አክለዋል። በኢትዮጵያ የቪዛ ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ በበኩላቸው “ቪዛ የተቀላጠፈ እና አስተማማኝ የድጂታል ክፍያን ለሁሉም እና በሁሉም ቦታ ለማዳረስ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል። “ከራይድ ጋር የተጀመረው ጥምረት በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ አስተማማኝነቱ የተመሰከረለትን የቪዛ ክፍያ ሥርዓት በማቅረብ የኢትዮጵያን የጉዞ እና ቱሪዝም ዘርፍ ለመደገፍ ተቋማቸው ያነገበውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት" ጠቅሰዋል። ራይድ በቀልጣፋ የሞባይል መተግበሪያ እና በ8294 የጥሪ ማዕከል አማካኝነት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መንገደኞችን ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር የሚያገናኝ ፈር ቀዳጅ የጥሪ-ትራንስፖርት ድርጅት ነው። ራይድ ከተመሰረተበት ከ2006 ዓ.ም አንስቶ የአፍሪካዊያንን የዕለት ተዕለት ኑሮ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳለጥ ያለመ ተዓማኒ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተጋ ይገኛል። በኢትዮጵያ በሦስት ከተሞች የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቋሚ ደንበኞችን በብቃት ያገለግላል። እንዲሁም በዛሬዉ እለት ከራይድ ጋር ጥምረቱን  ያደረገዉ  ቪዛ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ደንበኞቹ፣ ለንግድ እና የገንዘብ ተቋማት እና ለመንግታዊ ድርጅቶች የድጂታል ከፍያንየሚያከናውን ዓለም አቀፋዊ ተቋም ነው። ቀዳሚ ተልዕኮውም ግለስቦች፣ የንግድ ድርጅቶች እና ኢኮኖሚዎች ኦይበልጥ እንዲጎለብቱ እና እንዲሳለጡ ማስቻል ነው። ቪዛ በዓለም ዙሪያ ከ 200 በላይ ሀገራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አሉት። ድጂታል ኢትዮጵያ “የአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ዋነኛ መገለጫ የሆነውን የድጂታል ትራንስፎርሜሽን በይፋ ተቀላቅሎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በኢፌዲሪ መንግስት አስተባባሪነት “ድጂታል ኢትዮጵያ 2025” የተሰኘ መርሐ ግብር ተቀርፆ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ፈጣን እና የተሳለጠ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊለውጥን ለመተግበር የድጂታል ቴክኖሎጂን ያማከለ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ተነድፏል። የድጂታል መታወቂያ፣ የድጂታልክፍያ እና የሳይበር ደህንነት ውጥኖች የዚህ ስትራቴጂ ቁልፍ ነጥቦች ናቸው። ለዚህም የዲጂታል ክፍያን ቀልጣፋ ለማድረግ አቢሲኒያ እና እናት ባንክ አንድ ላይ በመሆን እንደሚሰሩ አብስረዋል። @Addis_Reporter
Show all...
👍 4
ብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አቋቁሞ በሚቃወሙት እና በሚተቹት ላይ ስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሚያካሂድ ተገለጸ በገዢው ብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ። #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን ተከትሎ በወቅቱ የተሰራጩ መረጃዎችን ቢቢሲ በማሳያነት አቅርቧል። በቤተክርስቲያኗ እና በገዢው ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ተከትሎ “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ”፣ “አሜሪካዊው አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮብልለዋል!” እና “ከአሜሪካዊ አቡነ ጴጥሮስ ኩብለላ ጀርባ ያሉ እውነታዎች!” የሚል መግቢያ ያላቸው መረጃዎች በወቅቱ ተሰራጭተው እንደነበር አውስቷል። “ለምንድነው ላይክ፣ ሼር የማታደርጉት?” የሚል ጥያቄ ለተሳታፊዎቹ እንደሚያቀርብ፤ የሚዲያ ሠራዊት አባላት ላክይ፣ ኮሜንት እና ሼር ማድረጋቸውን የሚያሳይ “ስክሪን ሻት” እንዲልኩ እንደሚጠየቁ ቢቢሲ በግሩፑ የተደረጉ የመልዕክት ልውውጦችን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል። መንግስትን የሚቃወሙ ጽሁፎችን ባጋሩ የፌስቡክ ገጾች ላይ ‘የሚዲያ ሠራዊቱ’ አባላት ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን ጽሁፎች ኮሜንት እንደሚያደርጉ አረጋግጫለሁ ብሏል። @Addis_Reporter
Show all...
👍 22🤔 3🤯 2 1👏 1
እስራኤል ኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈፀሟ ተሰማ የእስራኤል ጦር በኢራኗ ኢስፋሃና ግዛት ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል፡፡ ከኢራን በተጨማሪም በሶሪያና ኢራቅ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ እየተሰማ ነዉ ተብሏል፡፡ ኒዮርክ ታይምስ የአሜሪካና የእስራኤል ባለስልጣናት ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበዉ ጥቃቱ በኢራን ወታደራዊ መሰረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ነዉ፡፡ በእስራኤል ሚሳኤል የተመታችዉ የኢራን ከተማም ኢስፋሃን ትሰኛለች፡፡ ኢራን በረራዎችን ማገዷን አስታዉቃለች፡፡ ከኢራን በተጨማሪም በሶሪያና ኢራቅ አካባቢ ፍንዳታዎች እንደተሰሙ ታይምስ ኦፍ እስራኤል በሰበር ዜናዉ እያስነበበ ነዉ፡፡ ይህንን ተከትሎም ኢራን በሶሪያ የሚገኘዉን ጦሯንና የሄዝቦላህን ታጣቂዎች ማስወጣጥ መጀመሯን እየሩሳሌም ፖስት ነዉ የዘገበዉ፡፡ የቀጠናዉ ሀገራትም ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ወድቀዋል፡፡ በእስራኤል ገሊላ አካባቢ የሳይረን ድምጽ ሌሊቱን ተሰምቷል ቢባልም የእስራኤል ጦር ግን ሃሰት ነዉ ብሏል፡፡ እስራኤል ተጨማሪ ጥቃቶችን በኢራን ላይ እንደምትወስድ አስታዉቃለች፡፡ ኢራንን በበኩሏ የመልስ ምቴ ከባለፈዉ እጅግ የከፋ ነዉ ስትል ማስጠንቀቂያ እየሰጠች ነዉ፡፡ @Addis_Reporter
Show all...
👏 8👍 6🔥 3🤯 1
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ ተዋቀረ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፏል። ኮሚቴው በአዲስ መልክ እንዲዋቀር መነሻ የሆነው ጥቅምት 19/2016 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፀደቀው የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደርያ ደንብ ሲሆን በደንቡ አንቀፅ 46 (ቁጥር 2) ላይ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚቋቋሙበት ሁኔታ ሲገልፅ "ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በቀር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይም ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ መስራት ይችላል። " ይላል። የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴን አወቃቀር እና አሠራር ገለልተኛ ለማድረግም አባላቱ ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ውጪ እንደሚሆኑ በደንቡ ላይ ተቀምጧል። በዚህም መሠረት የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደንብ ለፊፋ ተልኮ እንዲፀድቅ በመደረጉ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የተወሰነ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢንተርናሽናል ዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ግለሰቦች በአመራርነት ተመርጠዋል። በአዲሱ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተመረጡት አባላት የሚከተሉት ናቸው:- ዋና ሰብሳቢ - ሸዋንግዛው ተባባል ምክትል ሰብሳቢ - ሊዲያ ታፈሠ አባል - ለሚ ንጉሤ አባል - ክንዴ ሙሴ አባል - ክንፈ ይልማ @Addis_Reporter
Show all...
👍 6
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ ተዋቀረ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ አሳልፏል። ኮሚቴው በአዲስ መልክ እንዲዋቀር መነሻ የሆነው ጥቅምት 19/2016 በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የፀደቀው የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደርያ ደንብ ሲሆን በደንቡ አንቀፅ 46 (ቁጥር 2) ላይ ቋሚ ኮሚቴዎች የሚቋቋሙበት ሁኔታ ሲገልፅ "ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በቀር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይም ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ መስራት ይችላል። " ይላል። የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴን አወቃቀር እና አሠራር ገለልተኛ ለማድረግም አባላቱ ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ውጪ እንደሚሆኑ በደንቡ ላይ ተቀምጧል። በዚህም መሠረት የተሻሻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ደንብ ለፊፋ ተልኮ እንዲፀድቅ በመደረጉ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር የተወሰነ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢንተርናሽናል ዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ግለሰቦች በአመራርነት ተመርጠዋል። በአዲሱ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የተመረጡት አባላት የሚከተሉት ናቸው:- ዋና ሰብሳቢ - ሸዋንግዛው ተባባል ምክትል ሰብሳቢ - ሊዲያ ታፈሠ አባል - ለሚ ንጉሤ አባል - ክንዴ ሙሴ አባል - ክንፈ ይልማ
Show all...
ኬንያ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች በኬንያ በሄሊኮፕተር አደጋ የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥን ጨምሮ 9 የኬንያ ጦር አባላት መሞታውን ተከትሎ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጃለች። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማምሻወን በሰጡት መግለጫ፤ “የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋውም የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላ ህይወታቸው ማፉን ስገልጽ በትላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ነው” ብለዋል። ይህንን ተከትሎም በኬንያ ከነገ ጀምሮ የሚተገበር ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሀዘን ቀን መታወጁን ፕሬዝዳነቱ አስታውቀዋል። @Addis_Reporter
Show all...
👍 6 2
በጃኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ ማክሰኞ'ለት ለኢትዮጵያዊያን ተረጂዎች ገንዘብ ለማሰባሰብ ጄኔቫ ውስጥ በተካሄደው ዓለማቀፍ መርሃ ግብር ላይ የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞና ጩኸት ማሰማታቸውን አውግዟል። ፖሊስ ጩኸት ያሰሙትን ኢትዮጵያዊያን ይዞ ከአካባቢው እንዳራቃቸው ጽሕፈት ቤቱ ገልጧል። ጽሕፈት ቤቱ፣ ለድርቅ ተጎጂዎች ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ እርዳታ በሚያሰባስብበት መድረክ ላይ ጩኸት ማሰማት፣ የአገር ጠላትነት ፖለቲካ እንጂ የተቃውሞ ፖለቲካ አይደለም በማለት ተችቷል። የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ ማኅበረሰብ፣ ባልተገባ ቦታ ጩኸት በማሰማት "አገር አዋራጅ" የኾነ ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ሊቃወማቸው እንደሚገባም ጽሕፈት ቤቱ አሳስቧል። ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤቱ፣ በአገር ክብር ላይ እጃቸውን የሚዘረጉ ግለሰቦችን በሕግ አግባባብ የምጠይቅበትን አሠራር እከተላለሁ በማለትም አስጠንቅቋል። @Addis_Reporter
Show all...
👏 3🤯 1
🍀🍀መርጌታ ይልቃል ከፍተኛ የባህል  ህክምና             ☎️📞0952400019 የአባቶቻችንን ጥበብ ይፈልጋሉ? ከምንሰጣቸው በትንሹ 🍀ለመስተፋቀር 🍀ለጥይት መከላከያ 🍀 ለገበያ 🍀 ለበረከት 🍀ለስንፈተ ወሲብ 🍀ለሀብት 🍀ለቁማር 🍀ስልጣን ለመጨመር 🍀ለቀለም (ለትምህርት) 🍀 ገንዘብ ለማስመለስ 🍀ቡዳ ለበላው 🍀 እራስን ስቶ ለሚወድቅ 🍀ለህማም(ለማንኛውም) 🍀ለመድፍነ ፀር 🍀ሌባ የማያስነካ 🍀ለግርማ ሞገስ 🍀ለዓይነ ጥላ 🍀ለሁሉ መስተፋቅር 🍀ጸሎተ ዕለታት 🍀ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ 🍀ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 🍀ለድምፅ 🍀ጋኒን ለያዘው ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 🍀 የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ 🍀 ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ 🍀 ለንግድ 🍀 ገንዘብ ለሚያባክኑ 🍀 ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ  🍀 ለሀብት  🍀  ለስንፈተ ወሲብ 🍀 ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን 🍀 ትምህርት አልገባ ላለው 🍀 መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር 🍀 ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ አለን  ይደውሉ ያማክሩን ::ባላቹህበት እንሰራለን በአካል መምጣት ለማትችሉ መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን:: 🇪🇹 0952400019 በimo አና Telegram ማውራት ለምትፈልጉ በውስጥ መስመር ያውሩኝ!
Show all...
1