cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ

@zeftret👈👈

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
143Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

1 ቆንጆ ጫማ ለመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ🥾👟👞👢👡👠🥿
Show all...
#Update የብሄራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ማብሰሪያ ፕሮግራም ተካሄደ። በፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች እና የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች ተገኝተዋል። በመርሃ ግብሩ የሚሳተፉ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የዩኒቨርሲቲ እና የቴክኒክና ሙያ ምሩቃንም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የማብሰሪያ ስነ ስርአት ላይ ተገኝተዋል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በጎ ፈቃድ ማለት አንድ ሰው የራስን ጊዜና ሀብት ሰውቶ ሌላ ወንድም እና እህቱን ሲያግዝ መሆኑን አስረድተዋል። ወጣቱቹ ለዚህ ተግባር ተነሳስተው ሀገርን አስቀድመው በዚህ ደረጃ ሰውን ለማገልገል በመነሳታቸው እድለኛ ናቸው ብለዋል። “የምትፈፅሙት መልካም መቼ እና እንዴት እንደሚከፈላችሁ ባላውቅም የሆነ ጊዜ ግን ክፍያውን የምታገኙበት ኢንቨስትመንት ነው” ብለዋል ወጣቶቹን። በወጣቱ ውስጥ ያለውን እውቀት እና ማዕድን አውጥቶ ለመልካም ነገር መጠቀም እንደሚገባም ነው የተናገሩት። ወጣቶች በመርሀ ግብሩ በሙሉ ልባቸው እንዲሳተፋ እና የሚያገኟቸውን ክህሎቶች ለሕይወታቸው መሠረታዊ አድርገው እንዲቆጥሯቸውም መክረዋል። ወጣቶች ኃይላቸውን ለፍሬያማ ጉዳዮች እንዲጠቀሙ፣ ተግባራቶቻቸውን በጥበብ እንዲከውኑ፣ ጊዜያቸውን በጥንቃቄ በጥቅም ላይ እንዲያውሉ፣ ትኩረታቸውንም ሙሉ ለሙሉ በአዎንታዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያደርጉም አሳስበዋል። በመርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ አገራቸውን የሚወዱና የአገልጋይነት ስሜት የተላበሱ ወጣቶችን ለማፍራት ያለመ ነው። ለአገልግሎቱ አምስት የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች ተመርጠዋል፤አምባሳደሮቹም ሲስተር ዘቢዳር ዘውዴ፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ አርቲስት ቻቺ ታደሰ፣ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ፣ ወይዘሮ ፊልሰን አብደላሂ እና የመቄዶኒያ የአረጋዊያን ማህበር መስራች ቢኒያም በለጠ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የሠላም ሚኒስቴር ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የሚሰጠው መንግስታዊ ካልሆኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሆነ ገልጿል። መርሃ ግብሩ የዜጎችን አብሮ የመኖር እሴት ያዳብራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡ በመርሃ ግብሩ ለመሳተፍ ከ116 ሺህ በላይ ወጣቶች የተመዘገቡ ሲሆን፡ ዛሬ በማብሰሪያ ስነ ስርአቱ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት 10 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በመጀመሪያው ዙር ለሁለት ወራት ይሰለጥናሉ ተብሏል፡፡ ወጣቶቹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠታቸው ከሚያገኙት እርካታ በተጨማሪ በተለያዩ ተቋማት መቀጠር የሚያስችላቸው የስራ ልምድ ይሰጣቸዋልም ነው ያለው የሰላም ሚኒስቴር፡፡ በጎ ፈቃደኞቹ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከመመደባቸው በፊት በክህሎት፣ ስብዕና እና አካላዊ ግንባታ ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ይወስዳሉ፡፡ @zeftrert
Show all...