cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሆለታ ደብረገነት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
156Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለኖላዊ ሔር፣ ለቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ እንዲኹም ለአባ ይስሐቅ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ዳግመኛም ዛሬ ታኅሣሥ 21 ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ አበው ጎርጎርዮሳት፣ አቡነ ምዕመነ ድንግል፣ አቡነ አምደ ሥላሴ፣ አባ አሮን ሶርያዊ እንዲኹም አባ መርትያኖስ ጻድቅ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
Show all...
"አኹንም እግዚአብሔርን ፍሩ። በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችኹ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደኾነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።" ኢያሱ ፳፬:፲፬
Show all...
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 "እውነት እላችኋለኹ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም" (ማቴዎስ ፲፩፣፲፩) “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” መዝ.፻፲፭/፻፲፮፡፲፭ የዛሬዋ ዕለት የጌታ ባሪያ፣ የትሕትና መምህር፣ ካህን፣ ነቢይ፣ ባህታዊ ፣ የበረሃ ምርኮኛ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስለእውነት አንገቱ የተቆረጠችበት ዕለት ናት! ከዚኽ ደገኛ ነቢይ በረከት ይክፈለን! ሀገራችንንም እኛንም በእውነት ይማረን - አሜን! 🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
Show all...
⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿⚜🌿 ቅዱስ ዮሐንስ - መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ መጥምቀ መለኮት አባቱ ዘካርያስ (ከአብያ ምድብ የኾነ ሊቀ ካህን)፤ እናቱ ኤልሳቤጥ (ከአሮን ነገድ ነበረች)፤ ኹለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት ኹሉ ጠብቀው የሚኖሩ ቅዱሳን ነበሩ፤ ይኹን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመኾኗ ልጅ አልነበራቸውም። /ሉቃ.፩÷፭-፯/፡፡ አንድ ቀን ዘካርያስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት ወደ ቤተ መቅድስ ገብቶ ዕጣን የማጠን ተራ ደርሶት ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ መልአከ እግዚአብሔር ከዕጣን መሠዊያው በስተቀኝ ቆሞ ታየው፡፡ ዘካርያስም ባየው ጊዜ በፍርኃት ተዋጠ፡፡ መልአኩም "ዘካርያስ ኾይ አትፍራ ጸሎትኽ ተሰምቷል፤ ሚስትኽ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልኻለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለኽ፤ በእርሱ ተድላና ደስታ ታገኛለኽ ብዙዎችም በእርሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤ በጌታ ፊት ታላቅ ይኾናልና» በማለት ብሥራት ከነገረው በኋላ ስለሚወለደው ልጅ አራት ነገሮችን ነገረው (ሉቃ.፩÷፲፫-፲፯)፡፡ ፩. የወይን ጠጅም ኾነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም። ፪. በእናቱ ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፡፡ ፫. ከእስራኤል ወገን ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል። ፬. ለጌታ የሚገባ ሕዝብ ለማዘጋጀት በኤልያስ መንፈስና ኃይል በጌታ ፊት ይሔዳል፡፡ ዘካርያስ ይኽንን ከመልአኩ በሰማበት ወቅት እርሱ ሸምግሎ፥ ሚስቱም አርጅታና የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ በዚያም ላይ መካን ነበረችና "ይኽን በምን አውቃለኹ? እኔ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም በዕድሜ ገፍታለች" በማለት ጥርጣሬውን በጥያቄ መልክ አቀረበ፡፡ በዚኽን ጊዜ መልአኩ እንዲኽ አለው "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፡፡ ይኽን እነግርኽና ይኽን የምሥራች አመጣልኽ ዘንድ ተልኬያለኹ፤ እነኾ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንኽ ይኽ እስከሚፈጸምበት ቀን ድረስ ድዳ ትኾናለኽ፤ መናገርም አትችልም" አለው፤ በዚኽም መሠረት ዘካርያስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሲወጣ መስማትም ሆነ መናገር አልቻለም ነበር፡፡ መልአኩ እንደነገረውም ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ይኽ ከኾነ ከስድስት ወር በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጌታችንን እንደምትወልድ አበሰራት፡፡ መልአኩ እመቤታችንን ሲያበስራት ኤልሳቤጥ መፀነስዋንም ነግሯት ነበር፡፡ "እነኾ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወራት ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና" ብሏት ነበር፡፡ እመቤታችንም መልአኩ ስለ ኤልሳቤጥ የነገራትን ለማየት በዚያው ሰሞን ፈጥና ወደ ኤልሳቤጥ ኼደች፡፡ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ለኤልሳቤጥ ሰላምታ ስታቀርብላት እጅግ የሚያስደንቅ ነገር ተከሰተ፤ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማኅፀኗ ያለው ፅንስ ዘለለ፡፡ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች። ድምጽዋን ከፍ አድርጋ እንዲኽ አለች፡- "አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል? እነኾ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሏልና፡፡" ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ በስምንተኛውም ቀን ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤ እናቱ ግን መንፈስ ቅዱስ ገልጦላት "ዮሐንስ መባል አለበት" አለች፡፡ ዘካርያስን ለልጁ ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ጠይቆ "ስሙ ዮሐንስ ነው" ብሎ ጻፈ ወዲያውም አንደበቱ ተፈታ፡፡ ዮሐንስ ማለት ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ማለት ነው። ካህኑ ዘካርያስም በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ ስለ ሕፃኑ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ትንቢት ተናገረ (ሉቃ.፩÷፷፯-፸፱) "አንተ ሕፃን ኾይ የልዑል ነቢይ ትባላለኽ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትኼዳለኽና፤ እንደዚኹም የኃጢአታቸው ሥርየት የሆነውን የመዳን ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለኽ" በማለት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ እንደሚሆን - የሕዝቡ ልብ ጌታችንን እና ትምህርቱን እንዲቀበል የሚያዘጋጅ ትምህርት እንደሚያስተምር ተናገረ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም "የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲኽ ይላል - የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ" (ኢሳ.፵ ÷፫/ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ በዛሬዋ ዕለት መጥምቀ መለኮት ስለእውነት አንገቱ የተቆረጠበት መታሰቢያ በዓል ታስቦ ይውላል። አምላከ ቅዱሳን በቅዱሳኑ ቃልኪዳን ይማረን! የተወደደች ዕለት ትኹንልን! አሜን! ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
Show all...
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)፣ ለቅዱስ ዳስያ ሰማዕት፣ ለቅዱስ ዲዲሞስ ሰማዕት እንዲኹም ለቅድስት መሪና ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ 🙏 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ዳግመኛም ዛሬ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)፣ ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ፣ ቅዱስ አቤል ጻድቅ፣ ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)፣ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ እንዲኹም አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው 🙏🙏🙏 አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን 🤲 አሜን! "የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯ 🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
Show all...
"ለመስማት ጆሮ ያላችኹ እንስማ። ከዚኽ በኋላ ክርስቲያን ተመርጧልና መንፈሳዊ ወታደር ኹኑ።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 “ዓመቶችኽ ለልጅ ልጅ ናቸው። አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትኽ፥ ሰማያትም የእጅኽ ሥራ ናቸው። ... እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለኽ፤ ኹላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለኽ፥ ይለወጡማል፤ አንተ ግን ያው አንተ ነኽ፥ ዓመቶችኽም ከቶ አያልቁም።” መዝሙር ፻፪፥ ፳፬-፳፯ 🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
Show all...
"በቸርነትኽ ዓመታትን ታቀዳጃለኽ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል" 📖 መዝ- ፷፭ : ፲፩ ዘመኑን - የንስሐ፣ የፍስሐ፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት አድርጎ - አስከፊውን በሽታም ከዓለም አጥፍቶ ቤተ ክርስቲያናችንንም ከምዕመኗ ጋር አጣምሮ በአዲስ ተስፋ እና መነሣሣት የምሕረት ቀንን ያሳየን 🤲 አሜን።
Show all...
🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨ "የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኃጢኣት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿
Show all...
🌳🍁🌳🍁🌳🍁🌳🍁🌳🍁🌳🍁 እግዚአብሔር ሰውን እንዴት አዳነው? 🤔 👉 የአዳምን ዕዳ ፍጡራን ሊከፍሉት አልቻሉም። ስለዚኽም እግዚአብሔር ወልድ ሰው ኾኖ ዕዳችንን ከፈለልን 🙏 አዳም ሊቀበለው የሚገባውን ኹሉ ተቀብሎ አዳምን ነጻ አወጣው። 👉አዳም በበደሉ ከገነት ወደ ሲዖል ቢሰደድ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ያለ በደሉ የገነት ምሳሌ ከኾነች ከነዓን የሲዖል ምሳሌ ወደ ኾነች ግብጽ ተሰደደ 🙏 👉አዳም ከዓለመ መላእክት ተሰድዶ ከእንስሳት መካከል ቢገኝ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በእንስሳት በረት ተወለደ 🤲 👉አዳም በመብል ድል ተነሥቶ ከገነት ቢወጣ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ "ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚአብሔር ቃል ጭምር እንጂ"ብሎ ፈቃደ ሥጋን እና ስስትን ድል ነሣለት 🙏 👉 አዳም ሕግ ጥሶ ከጸጋ ቢራቆት፤ ክርስቶስ ራቁቱን በመልዕልተ መስቀል ተሰቀለለት 🙏 👉 የአዳም እጅና እግሮች ወደ ዕጸ በለስ ቢያመሩ፤ የክርስቶስ እጅና እግር በቅንዋት ተቸነከሩ 🙏🙏🙏 አቤቱ ጌታ ኾይ ማረን 🤲🤲🤲
Show all...