እቺን ቃል ንገሯት
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለየት ተስኖኝ..
ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ......
የቀረች ይመስል....
ዞር ባለች ቁጥር....
አትራቂኝ እያልኩኝ..
የምለማመጣት.....
ልቻለው ብዬ እንጂ
ምሳሌ ከመሆን....
አፍቅሮ ከማጣት...
ገደል ግቢ በሏት
ይሄው ደግሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ...
አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች
ደመቀች በሽንሽን
ከንፈሯን ምን ይሆን
ደሞ የቀባችው....
የእጇን አይበሉባ...
በቄንጥ አኮናትራ...
ሰዐቷን አየችው.....
ገና ነው መሰለኝ....
ጊዜን ታዘበችው....
በአፏ ሸብረክ አርጋ
እየገረመመች.....
መንቀር አለችና....
እግሯን አመሳቅላ...
መስታወት ፊት ቆመች
ደግሞ ፈገግ አለች....
ጥራሷ ይርገፍ እና.....
ማርያምን ታምራለች😊😊