cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እግዚአብሔር ፍቅር ነው 🇬‌🇴‌🇩‌ 🇮‌🇸‌ 🇱‌🇴‌🇻‌🇪‌

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 1ኛ ዪሀ 4፥8 Hᴇ ᴛʜᴀᴛ ʟᴏᴠᴇᴛʜ ɴᴏᴛ ᴋɴᴏᴡᴇᴛʜ ɴᴏᴛ Gᴏᴅ; ғᴏʀ Gᴏᴅ ɪs ʟᴏᴠᴇ.1 Jᴏʜɴ 4:8 @EGEZIABHER_FKRNeW

Show more
Advertising posts
247Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✝መድኃኔዓለም በአበው አንደበት📖 ጽሐፉ የተወሰደው፡-ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከብሂለ አበው ነው። "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”        ዮሐንስ 1 : 2 “እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” (አቡነ ሺኖዳ) “ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” (ዮሐ 3፡13) “ከእባብ ማሳት ምክንያት በበደልን ጊዜ ከዘለዓለማዊ ሕይወት ራቅን፣ ደስታ ካለበት ከገነትም ወጣን፣ አንተ ግን ለዘለዓለሙ አልጣልኸንም፤ … በኋላ ዘመንም በጨለማና በሞት ለምንኖር ለእኛ ታየህልን፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ሰው የሆነ የአንድ ልጁንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን በእኛ ላይ አኖርህ” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “ማዳኑም ከወደረኞቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ እጅ ነው ይህም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው፡፡ ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል” (ካህኑ ዘካርያስ በሉቃ 1፡71-79) “የሰው ልጅ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሔር መምሰል ተነጥቆ ነበር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ያጣነውን መልክ ሊመልስልን ነው” (ቅዱስ ሚናስ) “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአል” (ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 8፡29) “ባለመታዘዝ የእንጨት ፍሬን በመብላት ምክንያት የመጣውን ሞት፣ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በመታዘዝ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞትን አስወግዶ ሕይወትን ሰጠን” (ቅዱስ ሄሬኔዎስ) “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” (ፊልጵ 2፡8) “እኛ ሁላችን አምላካችን እግዚአብሔር መሆኑንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰው ቃል መሆኑን እናምናለን፡፡ እርሱ በመለኮቱና ሰው በመሆኑ ፍጹም እንደሆነ እናምናለን፡፡ አምላክነቱ ከሰውነቱ ለቅጽበት እንኳ እንዳልተለየም እናምናለን፡፡ ሰው መሆኑ ከመለኮተ ጋር ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ፣ ያለ መከፋፈልና መለያየት የሆነ ነው” (ቅዱስ ቄርሎስ) “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ” (ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 8፡9) “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፡፡ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” (ቅዱስ ጳውሎስ ፊልጵ 2፡6-7) “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) “መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል” (ሉቃ 1፡35) “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4፡4) “የጠፋ በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን ክርስቶስ ነው” (ተአምረ ማርያም) “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?…ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል…የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል” (ሉቃ 15፡ 4-6) “ማንም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምን ፀረ ክርስቶስ ነው፡፡ በመስቀል ላይ መከራን በመቀበል ኃጢአታችንን ተሸከመ” (ቅዱስ ፖሊካርፐስ) “ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና፡፡ እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ…ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” (1ኛ ጴጥ 2፡22-24) “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል…እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም” (ኢሳ53፡1-12) “ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለእኛ ንስሐ ለገባነው ክቡር የሆነ ሰማያዊ አክሊልን ታቀዳጀን ዘንድ የእሾህ አክሊል ደፋህ” (ቅዱስ በርተሎሚዎስ) “ኢየሱስ ክርስቶስ ድል አድራጊ ንጉሥ ነው የምንለው ተሰቅሎ ሞቶ ስለተነሣ ስላየሁት ብቻ አይደለም፤ እርሱ ለዘመናት ድል አድራጊ ነውና” (ዮሐንስ አፈወርቅ) ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።1ዩሐ.1፥9 “አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል” (ራእይ 5፡5) “በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል” (ራእይ 17፡14) “ኢየሱስ ክርስቶስ የማይጠልቅ ፀሐይ፣ የማይጠፋ መብራት፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ ነው” (ባስልዮስ ዘቂሳርያ) “እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህንእንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ” (ራእይ 22፡16) "ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው" ሮሜ 9-5 ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። 🇪🇹@ethiopianorthodoxs⛪️⛪️
Show all...
+++++#ነጻነታችንን_አናስወስደው+++++++ እግዚአብሔር በፍጥረት ጊዜ ለሁላችንም ከሰጠን መሠረታዊ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነጻ ነት ነው። በዚህ ስጦታ አማካኝነት ሰጪውን እግዚአብሔርን ምን ያህል ቸር እንደ ኾነ እናጣጥምበታለን። በተለይ በሐዲስ ኪዳን ያገኘነውን ነጻነት በተመለከተ ዮስጢኖስ እንዲህ ይላል “በእውነታው አንድ ነጻነት ብቻ ነው ያለው። ይኸውም ከኃጢአት፣ ከክፋትና ከዲያብሎስ ነጻ ያደረገን የክርስቶስ ቅዱስ ነጻነት ነው። በዚህ ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን። ሌሎች ነጻነቶች በሙሉ እውነት የሚመስሉ፣ የተሳሳቱ፣ በእርግጥም በአጠቃላይ ባርነቶች ናቸው" (St. Justin Popovich, Ascetical and Theological Chapters, II.36) አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ተለይቶ የወደደውን ለማድረግ በመፈለጉና አንዳንዴም ተሳክቶለት በማድረጉ ምክንያት የተሰጠውን ስጦታ ተጠቅሟል ማለት አይደለም። ነጻነታችንን መልካም የኾነውን ለመምረጥ ብቻ የማንጠቀም ከኾነ እንጎዳበታለን። እግዚአብሔር ነጻነትን የሰጠን ከልባችን እርሱን ፈልገን እንድናመልከው ስለሚፈልግ ነው። ክርስቲያን ማለት ክርስቶስን የሚመርጥና ፈቃዱን በማድረግ ደስ የሚሰኝ ማለት ነው። ከእውነተኛው ነጻነት እውነተኛ ደስታ ይመነጫል፤ ይህ ደስታ ደግሞ የእኛ ብቻ ሳይኾን የሰማይ መላእክትም ደስታ ነው። ፍጹም የኾነውን ነጻነት የምናገኘው በፍቅረ እግዚአብሔርና በፍቅረ ቢጽ ውስጥ ነው። ፍቅር የሌለው ሰው ነጻነት የለውም። እግዚአብሔርንና ሰውን የምንወድ ከኾነ ፍጹሙን ነጻነት ገንዘብ አድርገናል ማለት ነው። በዚህ ውስጥ ደግሞ ፍጹም የኾነ እኩልነት አለ። ስሎዋን እንዲህ ይላል “ሁሉም ሰው ንጉሥ፣ አባት፣ አለቃ መኾን አይችልም። ነገር ግን በማንኛውም የሥልጣን ደረጃ ውስጥ ኾኖ እግዚአብሔርን መውደድና ማስደሰት ይችላል፤ ይህ ብቻ ጠቃሚ ነውና። ማንም እግዚአብሔርን በምድር ላይ አብልጦ ቢወድ፣ በእግዚአብሔር መንግሥት በታላቅ ክብር ይኾናል።" (St. Silouan the Athonite, Writings, VI.23)። እንግዲህ በእውነተኛው ነጻነት ውስጥ መኖር ማለት እግዚአብሔርን በማፍቀርና በማስደሰት መኖር ማለት ነው። በነጻነት ውስጥ አለን ማለት በዚህ መልካም ነገር ውስጥ አለን ማለት ነው። ተወዳጆች ሆይ! ይህን ቅዱሱን ነጻነት ክፉ ምኞታችን አላጠፋብንምን? የዚህ ዓለም ኃላፊ ነገሮች እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኙን ራሳችንን ለኃጢአት ባርያ በማድረጋችን ምክንያት ከቅዱሱ ነጻነች ስለ ራቅን መኾኑን መዘንጋት የለብንም። ሐሳባችን ከመልካምነት ሲወጣ አእምሯችን ለአጋንንት ባርያ ወደ መኾን መውረዱን እናስተውል! ቶሎ ብለንም ውስጣችንን እንመርምር፥ ስለ ፍቅር ብሎ ፈጥሮን በፍቅሩ የሚያኖረንን አምላክ የሰጠንን ነጻነት ፍሬ በማፍራት እናስደስተው! ለዚህ ዓለም ማንኛውም ኃላፊ ነገር ውስጣችንን ባርያ በማድረግ ነጻነታችንን አናበላሽ። እስከ ዛሬ ድረስ የፈጸምናቸው ክፉ ሥራዎች እጅግ መብዛታቸውን አስበን ፈጣሪያችንን በአንብዓ ንስሓ ማረን እንበለው። ቅዱስ ማርቆስ “መንፈሳዊ ሕይወትን የሚኖር ትሑት ሰው፥ ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚያነብበት ጊዜ፥ ሁሉንም ነገር ከራሱ ሕይወት ጋር ያገናኛል እንጂ ከሌሎች አይደለም።" ይላል። (St. Mark the Ascetic, Sermon, 1.6)። ስለዚህ ነጻነትን ጠብቆና ቀድሶ ለመኖርን የራስን ሕይወት መመርመር ያስፈልጋል። የራሳችንን ሕይወት ሳንቀድስ ስለ ሌላው ብቻ በማወራት የምንኖር ከኾነ በአጋንንት ወጥመድ ውስጥ መጠመዳችንን ልብ እንበል! ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ብርሃን የሌላቸው ቀጥ ብለው መሄድ እንደማይችሉ የቅዱሳት መጻሕፍትን ጨረር ያላዩ በጨለማ ስለሚጓዙ ኃጢአትን ይሠራሉ።" (St. John Chrysostom, Conversations on the Epistle to the Romans, 0.1)። በመኾኑም ነጻነታችንን በቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያ ውስጥ እናድርገው። በራሳችን ምድራዊ ፍላጎት ምክንያት እግዚአብሔር የሰጠንን ልዩ ስጦታ በሰይጣን አናስወስደው! እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን፥ በብዙ የኃጢአት ዱላ ተደብድቦ የደነዘዘውን ልቡናችንን ይፈውስል፤ የሐሳቡንም ብርሃን በልባችን ያብራልን፤ በፈቃዳችን ከታሠርንበትን የኃጢአት ባሪነት በቸርነቱ ያላቅቀን፤ ቅዱስ ቃሉንም ወደ መረዳትና በገቢራዊ ሕይወት ወደ መኖር ልዕልና ያሣርገን አሜን።
Show all...
+ አልፋና ኦሜጋ ክርስቶስ + መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ‘አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ’ አለ:: A እና Ω የግሪክ የመጀመሪያና የመጨረሻ ፊደላት ናቸው፡፡ ጌታችን መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ ሲል ከዓለም መፈጠር በፊት የነበርሁ ዓለምንም አሳልፌ ለዘላለም የምኖር እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ ወደ ጥልቁ መለኮታዊ ዘላለማዊነት ሳንገባ ያለንባትን የምድርን ታሪክ ይዘን ብቻ እንዲሁ ካየነው ክርስቶስ መጀመሪያም መጨረሻም ነው፡፡ ‘እግዚአብሔር ‘በመጀመሪያ’ ሰማይና ምድርን ፈጠረ’  ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር አብ ‘መጀመሪያ’ በተባለው በልጁ በክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ፈጥሮአል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ የሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህችን ምድር በግርማው መጥቶ የሚያሳልፋትም እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ ለምድርም መጀመሪያዋና መጨረሻዋ ክርስቶስ ነው፡፡ መቼም እኛም ከምድር ተፈጥረናልና ይህ ነገር እኛንም ሳይመለከተን አይቀርም፡፡ ነቢዩ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ እንዳለ በእናታችን ማሕፀን የሳለንና በኋላም ለእኛ ምጽዓት በሆነችው የሞታችን ዕለት ነፍሳችንን ወደ እርሱ የሚወስዳት መጀመሪያችንና መጨረሻችን እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ግን ለሁሉ የማይቀር ነው፡፡ ወዳጄ ክርስቶስን አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑን ታምናለህ፡፡ በአንተ ሕይወት ውስጥ ግን ክርስቶስ እውነት መጀመሪያና መጨረሻ ነው? ለአንዳንዶች ክርስቶስ መጀመሪያቸው ነበር፡፡ ዴማስ ለክርስቶስ አልፋ ብሎ ዘምሮለት ነበር፡፡ ከጳውሎስ ጋር ሆኖ ለፊልሞና ሰላምታ ሲልክም ነበረ፡፡ በኋላ ግን ዓይኑ በተሰሎንቄ ውበት ተማረከ፡፡ የአሁኑን ዓለም ወደደና ከሐዋርያት ጋር ማገልገሉን ተወ፡፡ ክርስቶስ ለእርሱ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልሆነም፡፡ ‘ሰውን ፍጻሜውን ሳታይ አታመስግነው’ የሚለውን ቃል ዘንግተን ያመሰገንናቸው እንደ ሰማልያል አብርተው ጀምረው እንደ ሰይጣን ጨልመው የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ‘የዛሬን አያድርገውና እንዲህ እንዲህ ነበርሁ’ ብለው የሚተርኩ መነሻዬ ቤተ ክርስቲያን ነበረ የሚሉ መዳረሻቸው ሌላ የሆኑ በመንፈስ ጀምረው በሥጋ የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ ግን መነሻም መድረሻም እኔ ነኝ ይላል፡፡ ክርስቶስ የማጣት ጊዜ አምላክህ የማግኘት ጊዜ ትዝታህ አይደለም፡፡ በማግኘትህ ውስጥም እግሩን አትልቀቀው፡፡ በደጅ ጥናትህ ጊዜ ጌታዬ ካልከው ስትሾምም አትርሳው፡፡  ቀንህን ስትጀምር ስሙን ጠርተህ ከጀመርህ ወደ ሥራህ ቦታም ስትሔድ ቤትህ አስቀምጠኸው አትውጣ፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነውና በእርሱ የጀመርከውን ቀንህን ከእርሱ ጋር ጨርሰው፡፡ ሰው በሥራ ቦታው በንግዱ ብዙ ወንጀል የሚሠራው ፈጣሪውን ሥራ ማስጀመሪያ ብቻ ሲያደርገው ነው፡፡ እግዚአብሔር መፍጠር የጀመረባትን የሳምንቱን መጀመሪያ እሑድ ዕለትን አሐዱ ብለን በቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር እንጀምራለን፡፡ በማግሥቱ ወደ ሥራና ማኅበራዊ ሕይወታችን ስንገባ ግን ክርስትናችን ይጠፋል፡፡ ሳምንቱን አልፋ ብለን የጀመርንበት አምላክ ኦሜጋ ሆኖ አብሮን እንዳይሰነብት እናደርገዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያው እንጂ መቃብሩ አይደለችም፡፡ እርሱ በቤተ ክርስቲያን በረድኤት ቢገለጥም በሁሉ ቦታም የሞላ አምላክ ነው፡፡ ክርስቶስን የምናስበው እሑድ ብቻ ከሆነና በሌሎቹ ቀናት በምንውልበት ሥፍራ የማናስበው ከሆነ ፤ ‘’ሥራ ሌላ ክርስትና ሌላ’’ ብለን የምንገድበው ከሆነ ትንሣኤውን ሳይሰሙ እሑድ ዕለት በመቃብሩ ሽቱ ሊቀቡ እንደሔዱት ቅዱሳት ሴቶች በእኛ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ገና አልተነሣም ማለት ነው፡፡ ‘ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ ክርስቶስን ከረሳኸው ክርስቶስ ለአንተ አልተነሣም ማለት ነው’ ይላል ቅዱስ አምብሮስ፡፡ ሐዋርያት ጌታ በምድር ሲመላለስ በነበረ ጊዜ ሁሉን ትተው የተከተሉት መጀመሪያቸው እርሱ ነበር፡፡ ዐርብ ዕለት ግን ከመካከላቸው ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ ኮበለለ፡፡ እነርሱም መከራ ፈርተው ተበተኑ፡፡ ዮሐንስ ብቻ የወደደውን እስከ መጨረሻው ወድዶ ተከተለው፡፡ እርግጥ ነው የቀሩት ወንድሞቹም ከትንሣኤው ወዲያ በንስሓ ተመልሰው መጀመሪያቸውን ክርስቶስ መጨረሻቸው አደረጉት፡፡ ክርስቶስን ከማንም በላይ መጀመሪያዋም መጨረሻዋም ያደረገችው አልፋና ኦሜጋ የተጻፈባት ድንግል ማርያም ነበረች፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለዓለም ሊሠጥ ሲፈቅድ ዓለምን ወክላ የተቀበለችው ድንግል አልፋ ክርስቶስ በማሕፀንዋ ተጽፎባት በቤተልሔም ግርግም በእቅፍዋ ነበረ፡፡ ከመስቀሉ ሥርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር፡፡ ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ ዕለት በልጅዋ ሥቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና ‘እነሆ ልጅሽ’ ብሎ ዮሐንስን ሠጣት፡፡ በእርስዋ ሕይወት ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ ነበረ፡፡ ወዳጆች ሆይ ዛሬ የእግዚአብሔር ልጆች ነን ፤ ነገ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ አልክድህም ብለን እንዳንዝት ሦስቴ እንዳንክደው እንፈራለን፡፡ መጀመሪያችን የሆነው አምላክ መጨረሻችን እንዲሆን ግን ‘እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን’ እያልን ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጸልያለን፡፡             ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 14 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4 Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

#እውነተኛውን_ጥበብ_እንዴት_እንቀበል? ማክሲመስ መስካሪው እንዲህ ይላል፦ "አንድ ክርስቲያን አምላካዊውን ጥበብ የሚቀበለው በሦስት መንገድ ነው። በትእዛዝ፣ በትምህርትና በእውነት። ትእዛዝ ሐሳብን ከክፉ ስሜት ያነጻል፤ ትምህርት ወደ ርቱዕ የተፈጥሮ ዕውቀት ይመራል፤ እምነት በተቀደሰ ሦስትነት ወደ መመሰጥ ይመራል።" St. Maximus the Confessor, Chapters on Love, 4.47)። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚያውቅና በዚያም  ለመጓዝ የሚፈቅድ ሰው ሐሳቡን በርቱዕ መሠረት ላይ ያንጻል። የሐሳብ ጥራት መነሻው በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ ባለችው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና። ሐሳባችን የሚበከለው በማንኛውም መንገድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ አፈንግጠን ስንወጣ ነው። ጥበብ ማለት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ውስጥ የመኖር ጉዳይ ነው። ከዚያ ውጭ ስንኾን ርቱዕ ከኾነው ጥበብ ውጭ እንኾናለን፤ ያን ጊዜ ድንቍርናው በራሱ ጥበብ መስሎ ሐሳባችንን ይረብሸዋል፡ ወደ ርኲሰትም ይመራዋል! ትምህርተ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ወደ እውነተኛው ዕውቀት መግቢያ በር ነው። በዓለም ከሚወረወረው የስሕተት ቀስት የምንጠበቀው በኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው። ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትን መውደድ ማለት እውነተኛ ዕውቀትን መውደድ ማለት ነው። ስለ ዓለም ያለን ዕውቀት ትክክለኛ ቅርጹን የሚዪዘው በቤተ ክርስቲያን ትምህርት በኩል ነው። ቤተ ክርስቲያን በዋናነት እውነትን ትገልጣለች፡ በትምህርት በኩልም በልጆቿ ልብ ውስጥ እውነትን ትዘራለች፡ በዘራችው እውነትም ወደ ርቱዕ ዕውቀት የልጆቿን ልብ ትመራለች። እንግዲህ በዚህ ደግሞ ጥበብ ራሱ ርቱዕ ዕውቀት መኾኑን ርቱዐዊነት ባለው ዕውቀት በኩል መቅመስ እንችላለን። እምነት ደግሞ የማይመረመረውን ምሥጢረ ሥላሴ በምንችለው ልክ ቀምሰን እንድንመሰጥበት ወደዚያ የሚመራ ረቂቅ መሣሪያ ነው። እምነት የምእመናንን ልብ ከምድር ወደ ሰማይ የሚያስገባ ታላቅ ኃይል ነው። የማይታየውን የሚያሳይ፣ ልቡናን በጽኑዕ መሠረት ላይ የሚያንጽ መንፈሳዊ ኃይል ነው። በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን። እርሱ ደግሞ የጥበብ ቤቷ ነው። እንግዲያውስ ከእርሱ ንጹሕ ጥበብን በእምነት ቀድተን ለዓለም እናፈሳለን። ዓለምንም ወደ ርቱዕ እምነትና ጥበብ እናስገባ ዘንድ አደራ አለብን። ምክንያቱም የጥበብ ምንጭ የኾነው ክርስቶስ አምላካችን ራስ ኾኖን ክርስቲያን ተሰኝተናልና። እርሱ ደግሞ ኹሉን ወደ እርሱ እንድንማርክ ይፈልጋል። ይህም የሚኾነው ከንግግር ባለፈ እርሱ ክርስቶስን በእውነተኛ ሕይወት ስንገልጠው ነው። የእርሱን ፈቃድ ትተን የየግላችንን አጽድቀን የምንኖር ከኾነ ክርስቲያን የሚለው ስሙ እንጅ ትክክለኛ ትርጒሙ በእኛ ገቢራዊ ሕይወት አይገለጥምና ሌሎች ከሕይወት ድንቍርና ይላቀቁ ዘንድ ቀርቶ እኛው ራሳችን በራሳችን የፈቃድ ጥመት ድንቍርና ውስጥ ተቀብረን ያለን አሳዛኞች እንኾናለን። ትእዛዛተ እግዚአብሔር ሕይወታችንን የሚያጣፍጥ ኾኖ ሳለ ከዚያ አፈንግጠን ምሬትን ገንዘብ በማድርግ ትእዛዙን ከመፈጸም ደንቍረናል። በዚህም ላይ እንደ ገና ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንንም ጠልተን ወይም ከልብ ለመማር ወይም ለመረዳት ባለመፈለጋችንም ሌላ ድንቍርናን ጨምረናል። ስለዚህ በንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ምሥጢር ከመመሰጥ እና ከመደነቅ ይልቅ የጥርጣሬን ብርድልብስ ለራሳችንን ደራርበናል። እንግዲያውስ ጥበብ ከወዴት ይደርብን? ሕይወታችንስ እንዴት አይምረር? ፍሬ ምግባርስ እንዴት አይጉደልብን? ጸጋስ እንዴት አይራቀን? ሕማመ ነፍስስ እንዴት አይጽናብን? ሌሎችስ እውነት የሌለን እንዴት አይምሰላቸው? ወዳጆች ሆይ ትእዛዘ እግዚአብሔርን በመፈጸም፤ ትምህርቱንም (እውነተኛ ዕውቀት የሚቀዳበትን መንገድ) በመጠጣት፣ በርቱዕ እምነት ሰውነታችንን አጽንተን የጠቢባንን አኗኗር አሐዱ ብለን እስኪ እንጀምረው!
Show all...
Show all...
MK TV || የብፁዕ አቡነ ሰላማ ሥርዓተ ቀብር በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

የመንፈሳዊ ትምህርት ጥቆማ የሰአሊተ ምህረት ሰንበት ት/ቤት በሳምንት አንድ ቀን አርብ ከምሽቱ 12:00-1:30 ለአንድ አመት የሚቆይ ትምህርት አዘጋጅቶልናል እንጠቀምበት ትምርቱ ዛሬ በፀሎት ይጀመራል። ሌሎችም እናጋራ
Show all...
"ቤተ ክርስቲያን የተፈተነችበት ሥርዓቷን እና ልጆችዋን ያጣችበት ጊዜ ስለሆነ ለሀገራችን እና ለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም እንዲመጣ የጳጉሜን 6 ቀናት ወደ እግዚአብሔር እንጸልይ።" ብፁዕ አቡነ አብርሃም ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በተሰጠው መግለጫ መሠረት የጳጉሜን ወር 6 ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምሕላ እንዲያሳልፍ መታወጁን ነው የገለጹት። በመግለጫውም ዘመኑ ከደስታ እና የምሥራች ይልቅ ኀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾም እና በጸሎት እንዲያሳልፉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ 13ተኛ ወር በሆነችው ወርኀ ጳጉሜን ዕለተ ምጽዓትን የምናስብበት ፤ ሰማይ የሚከፈትበት ፤ ጸሎት የሚሰማበት ምሥጢራዊ የሆነች ወር ነችና የበደሉንን ይቅር ብለን በንጹሕ ልቡና የቻልን ጾመን ያልቻልን በጸሎት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት እና የምንለምንበት ወር ሊሆን ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።
Show all...
Show all...
የ11 ቀን ቆይታችሁ እንዴት እንደነበር እየደወላችሁ ንገሩን ፡ call and donate #live #worldwide #ethiopia #GIGI #graduation

ለኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ገዳም መሬቱ ሲገዛ የተበደርነውን 6 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል የተዘጋጀ ኘሮግራም። Subscribe Saint JTBM

https://www.youtube.com/channel/UC-Oz6JMSNgYLXG7xJpOXe4w

ይህን link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

https://www.saintjtbm.org/subscription

በቀጥታ -Live 👉🏽ከሳን ሙጉዌል ካሊፎርኒያ አሜሪካ👈 👉🏽ገዳሙ ሲገዛ የቀረውን የገንዘብ ዕዳ ከፍለን እንጨርስ! በረከታችሁን ውሰዱ : ትልቁ ገዳም በሳን ሙጉዌል ካሊፎርኒያ 🇺🇸 አሜሪካ !!! Call Donate your support !!! ስለ ቦታው- ሥፍራው ስለከተማ በካርታ ለማየት ከፈለጉ ከታች ያለውን አያያዥውን ይጫኑ

https://www.city-data.com/city/San-Miguel-California.html

—————————————————— ቀጥታ Live ስርጭቱን በዶንኪ ቱዩብ ለመከታተል ከታች ያለውን አያያዥ ይጫኑ

https://youtube.com/live/tmZsva9mP5k?feature=share

—————————————————— በጎፋንድ Go Fund ለመለገስ ከወሰኑ በቀጥታ አያያዥውን ይጫኑ I'd really appreciate it if you would share or donate to this GoFundMe.

https://www.gofundme.com/f/eotjtbm

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመርዳት EOTC SAINT JOHN THE BAPTIST&ST.ARES-ETB-1273 1000508231273 *ወርቃማው ገዳም በሳን ሙጉዌል ካሊፎርኒያ አሜሪካ * DonkeyTube is organizing this fundraiser to benefit The Gateway to Heaven Saint John the Baptist and St. Arsema EOT Monastery in California. Forward this message to your contacts to help this campaign reach its goal! —————————————————— በዜል ለመለገስ ስልክ ቁጥሩ # 213-218-8471 City-Data (

https://www.city-data.com/city/San-Miguel-California.html)

San Miguel, California (CA 93451) profile: population, maps, real estate, averages, homes, statistics, relocation, travel, jobs, hospitals, schools, moving, houses, news Subscribe Medane Tube

https://youtube.com/@UCoo2tr1SKeKF4qSbMaOVE-Q

Subscribe Maya Media

https://www.youtube.com/@UCINp2J7JKd6tSxkAhbZu6mQ

WebSite: www.SaintJTBM.org ZELLE: [email protected] TEL: (844) 203 5826 Bank of America ACCOUNT # 325176793117 ROUTING # 121000358 WIRE ROUTING #026009593 SWIFT CODE: BOFAUS3N Bank of America Address: 6611LA Cienega Westway St. Los Angeles, CA 90056 Tel: (310) 410 7076 #GIGI #graduation DonkeyTube@Saint JTBM.org GO FUND ME:

https://www.gofundme.com/f/eotjtbm

WebSite: www.SaintJTBM.org #charity #habesha #willsmith #hailegebresilase #hailegerima #jadapinkettsmith #rastefari #church #orthodox #hospital #live #unversity #america #ethiopia #california #million #dollar #farmer #parent #child #life #israel #worldwidelive