cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Top መረጃ

Show more
Advertising posts
25 885Subscribers
-1224 hours
-837 days
-26030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አዲስ አበባ - ወልዲያ ትራንስፖርት ቆሟል‼ ከአዲስ አበባ-ደሴ-ወልድያ እንዲሁም ከደብረብርሃን-ሸዋሮቢት-ደሴ የህዝብ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከዛሬ ጀምሮ እንዲቆም ተደርጓል። መንግሥት ፅንፈኛ ብሎ በጠራቸው ሀይሎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ልዩ ያለውን ኦፕሬሽን ጀምሯል ተብሏል፣ህዝቡም ትብብር እንዲያደርግ ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ሰሞኑን በርካታ ህይወት መጥፋቱን እና እገታ መፈፀሙ ይታወሳል። ቀደምት መረጃዎች👇 https://t.me/Topmereja10 https://t.me/Topmereja10 https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 14 3
ወልቃይት ክልል?? መንግሥት የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የሚነሳበት ወልቃይት ራሳሱን የቻለ ክልል ሆኖ ሊደራጅ እንደሚችል መጠቆሙ ተሰምቷል። ጠ/ሚ አቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ሰሞኑን ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር በአራት ኪሎ ስለ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተግባራት ግምገማ አካሂደው ነበር። ከዚህ ወይይት በኋላም፣ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄ የሚነሳበትን ቦታ ለሁለቱም ክልሎች በመስጠት ፋንታና ራሱን ችሎ ክልል ሆኖ ቢደራጅ ይሻላል የሚል አዲስ እሳቤ በመንግሥት በኩል እንዳለ መነገሩን The reporter ዘግቧል። የወልቃይትና ራያን ጉዳይ በተመለከተ መፍትሄ ይሆናሉ ተብሎ ከዚህ በፊት ሲገለጽ የነበረው ሕዝበ ውሳኔ መካሄድ አለበት የሚል እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ውሳኔው በመዘግየቱ በተለይ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር እየገፉ መሆናቸው በተጋጋሚ እየተገለጸ ይገኛል። የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን በበኩሉ በጥር ወር ባወጣው መግለጫ፣ በሁለቱም ክልሎች የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በሚሰነዘርባቸው ያለውን ውዝግብ ለመፍታት "በሕገ መንግስቱ መሠረት" ሕዝበ ለማድረግ ከክልሎቹ ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር ቢገልጽም፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርም ባወጣው መግለጫ፣ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎትን መግለጫ “ተቀባይነት የለውም” ሲል ነቅፎት ነበር።
Show all...
👍 21 2
Show all...
👍 7 1
ጋሞ ዞን‼ ኢሰመኮ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ በቆላ ሻራ ቀበሌ ነሐሴ 18 በክልሉ ፖሊስና በቀበሌው ነዋሪዎች መካከል ከተፈጠረው አስተዳደራዊ ችግር ጋር በተያያዘ ለጠፋው ሕይወትና ለደረሰው የአካል ጉዳት ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቋል። ግጭቱ የተፈጠረው፣ በአርባ ምንጭ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የቆላ ሻራ ቀበሌ አስተዳደር ከጥር 2015 ዓ፣ም ጀምሮ ለ6 ወራት የራሱን ጸጥታ ኃይሎች መልምሎ የመንግሥት ጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው እንዳይገቡ በመከልከሉ እንደኾነ ኢሰመኮ ገልጧል። ኢሰመኮ፣ የመንግሥት ጸጥታ አካላት በቀበሌው በሦስት "ያልታጠቁ ሰዎች" ላይ "ከሕግ ውጪ ግድያ" እንደፈጸሙ በምርመራ አረጋግጫለኹ ብሏል። ለሟቾች ቤተሰቦችና ንብረት ለወደመባቸው ካሳ እንዲከፈላቸውም ኢሰመኮ ጠይቋል። https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 12🔥 6
ዛሬ እኩለ ቀን ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ መቐለ ሊያመራ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦንባርዲየር አውሮፕላን መቀሌ መጠነኛ ጉዳት ገጥሞት ነበር፡፡ አውሮፕላኑ በጎማው ላይ በገጠመው ችግር ከመንደርደሪያ መስመሩ ወጥቶ ጉዳት እንደደረሰበት የዘገበው ካፒታል  በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ጠቁሟል። ቤተሰብ❤ በቅንነት ይችን ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ‼👇🙏       https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 16 1
የዓለማችን ሀገራት ድምር ብድር 88 ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ፡፡ የዓለማችን ሀገራት መሪዎች በጋራ ችግሮቻቸው ዙሪያ ለመወያየት ወደ ስዊዘርላንዷ ዳቮስ እያመሩ ሲሆን በመድረኩ ላይ በዋና ዋና ችግሮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡ ባለሙያዎች አስቀድመው ወደ ቦታው ያመሩ ሲሆን ዋና ዋና የዓለማችን ችግሮች በሚባሉ ጉዳዮች ዙሪያ መፍትሔ ያሏቸውን ሀሳቦች መሪዎች እንዲወስኑባቸው በማመቻቸት ላይ ናቸው፡፡ የዓለማችን ሀገራት ከገጠማቸው ችግሮች ዙሪያ ዋነኛው የሀገራት ብድር መጠን መጨመር ዋነኛው ሲሆን የብድር መጠን 88 ትሪሊዮን ደርሷል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወቅት ሀገራት ዜጎቻቸውን ለመጠበቅ የወሰዷቸው እርምጃዎች የመንግስታትን ወጪ እንዲጨምር እንዳደረገም ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ብድር መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በተከሰተው የነዳጅ እና ምግብ ዋጋ መናር ሌላኛው የመንግስታትን ወጪ ያናረ ጉዳይ ሲሆን ተጨማሪ ግጭቶችም ሀገራት ተጨማሪ ብድር እንዲወስዱ አድርጓልም ተብሏል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ዓለማችን ተጨማሪ ጦርነት በቀይ ባህር አካባቢ ማስተናገዱን ተከትሎ የነዳጅ እና ምግብ ዋጋ እየጨመረ ሲሆን ለዓለም ኢኮኖሚ ሌላኛው ፈተና እየሆነ ይገኛል፡፡ በተያዘው ዓመትም አሜሪካ፣ ብሪታንያ እና ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪ እና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሀገራት ምርጫ ያደርጋሉ መባሉ ወደ ስልጣን የሚመጡ መንግስታት የሚወስኗቸው አዳዲስ ውሳኔዎች ኢኮኖሚውን ሊጎዱ እንደሚችሉ ተሰግቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የበይነ መረብ ደህንነት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለዓለም ኢኮኖሚ ፈተና ይሆናሉ ተብለው የተለዩ ሲሆን ሀገራት ይህን ችግር ለመፍታት ተጨማሪ ውሳኔዎችን በዳቮስ እንደሚወያዩበት ይጠበቃል፡፡(Alain) ቤተሰብ❤ በቅንነት ይችን ሰብስክራይብ https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 3
መቀሌ‼ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ባለፈው ኅዳር ያወጣው አዲስ ደንብ የዜጎችን መብት ይገድባል የሚል አቤቱታ ለሕገመንግሥት ትርጉም አጣሪ ጉባዔ እንደቀረበበት ሪፖርተር ዘግቧል። የሕገመንግሥት ትርጉም አቤቱታውን ያቀረበው፣ "ቅድሚያ ለሰብዓዊ መብቶች" የተሰኘው ሲቪል ማኅበር እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። ማኅበሩ አቤቱታ ያቀረበበት አንዱ የደንቡ ድንጋጌ፣ በመንግሥትና በግል ሠራተኞች ውዝፍ ደመወዝ ዙሪያ በፍርድ ቤት የተመሠረቱ ክሶች ለጊዜው ታግደው እንዲቆዩ የሚደነግገው አንቀጽ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል። አዲሱ የክልሉ ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ በነባር ፖሊሶች ፋንታ የትግራይ ተዋጊዎች ብቻ በፖሊስነት እንዲመለመሉ የሚጠይቀው የደንቡ ክፍልም፣ የሕገመንግሥት ትርጉም አቤቱታ ቀርቦበታል ተብሏል።(wazema) ቤተሰብ❤ በቅንነት ይችን ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ‼👇🙏       https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 6🥰 1
ADVERTISMENT ከአእምሮ እና ከአከርካሪ ጋር የተዛመዱ የጤና ችግሮች አሉዎት? ከአንጎል እና አከርካሪ ጋር በተያያዙ ችግሮች ላይ የባለሙያ ምክር ይፈልጋሉ? ይምጡ እና በኒውሮሎጂ እና አከርካሪ ጤና ላይ የተካኑ ታዋቂ የህንድ ሀኪሞችን ምክር በአዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል ያግኙ ቀን: ጥር 25 - 27 ቀን 2016 ዓ.ም ሰዓት : 3:30 - 11:00 አድራሻ : አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል | ሀያ ሁለት የህንድ ሀኪሞቻችን የባለሙያ መመሪያ እና ድጋፍ ለመስጠት እየመጡ ነው።   ለመመዝገብ ወይም ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን በሚከተለው አድራሻ ይደውሉልን 0922271348 (ሰናይት ታደሰ) አሁኑኑ ይመዝገቡ -https://forms.gle/uMRXX5ASq2gEevmw5 በጤንነትዎ ላይ አይደራደሩ የእርስዎ ጤና ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው፣ እና ሀኪሞቻችን የጤና ችግርዎን በተሻለ ሁኔታ ለመመርመር ቁርጠኛ ናቸው። ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ - https://t.me/unikutumb ለተጨማሪ ዝመናዎች - በፌስቡክ ይከታተሉን። - https://www.facebook.com/unikutumb    #ኒዉሮ ስፓይንካምፕ #የጤና እንክብካቤ ዝግጅት #አዲስ ሂወት አጠቃላይ ሆስፒታል https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 2 1
በኢትዮጵያን እና በራስ ገዟ ሶማሌላንድ መካከል የተደረሰውን የወደብ ስምምነት አስመልክቶ የአረብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ። የአረብ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ በሚቀጥለው ረቡዕ እንደሚያደርጉ የአረብ  ሊግ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪ አስታወቁ። ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር በፈረመችው የመግባቢያ ስምምነት ላይም ይወያያል። በሶማሊያ ጥያቄ መሰረት የሚካሄደው ስብሰባ ሞቃዲሾን በዚህ ጉዳይ በመደገፍ የሚፈለገውን ውጤት እንደሚያስገኝ ዛኪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልፆ ባለፉት ቀናት ለማካሄድ ከፍተኛ ሙከራዎች ሲደረጉ ቆይተው የነበረ ቢሆንም ሊመቻች ባለመቻሉ በ"ቪዲዮ ኮንፈረንስ" በኩል ለማካሄድ ታስቧል። ሶማሊያ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ለአባል ሀገራቱ ያከፋፈለች ሲሆን ጉባኤውን ለማካሄድ ከ12 በላይ ሀገራት ድጋፍ ማድረጉን አፅንዖት ሰጥቷል።ከዚህ በፊት የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የተደረገውን ስምምነት ያወገዘ ሲሆን በሶማሊያ አቋም እና ድጋፍ ላይ ሙሉ በሙሉ መግባባት እንዳለ ተነግሯል ሲል RT ዘግቧል። 👉በህዳሴ ግድቡ ሞከሩ ሞከሩ አልሆነም።ለነገሩ ስራ ፈተው ነበር😳ለማንኛውም ጩኸት የተለመደ ነው። https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 2 1
ሶማሊያ ከሰሞኑ የምትይዘውን የምትጨብጠውን አሳጥቷታል።በኢትዮጵያ ላይ በይፋ ጦርነት ወደማወጅ እየተንደረደረች ይመስላል...🇸🇴🇪🇹 የአለም ሀገራት ጀርባቸውን የሰጧቸው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸህ መሀመድ "ሶማሊያዊ ለማይቀረው ጦርነት ይዘጋጅ የሶማሊያ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ተጋርጦበታል" በማለት የጦርነት ቅስቀሳ እያካሄዱ እንዳለ ተሰምቷል።   ፕሬዝደንቱ ትናንትም ወጣቶችን ሲቀሰቅሱ እንደዋሉ ከመገናኛ ብዙሃናቸው ዘገባዎች መረዳት ተችሏል።በቅስቀሳቸው  ኢትዮጵያ አንድ እርምጃ ወደ ሶማሊያ ከገባች እኛ ደግሞ ሁለት እርምጃ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እናልፈለን አለም እኛን መውቀስ አይችልም ማለታቸው ሶና የሶማሊያ ቴሌቪዥን ዘግበዋል።ወጣቶችን መሳሪያ እያሸከሙ ፎቶ በማንሳት ለጦርነት ማነሳሳቱን ተያይዘውታል። =========================== https://t.me/Topmereja10
Show all...
👍 18👎 1
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!