cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
635Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ትዝ ይልሻል?… "መርሳት ባንችል ኖሮ ሁላችንም እናብድ ነበር" የሚለውን አባባል ሰምተን የሳቅን ቀን? … አንቺ እንዲያውም በጣም ነበር የሳቅሽው። ከልክ በላይ መሳቅሽ አስገርሞኝ ያሳቀን ነገር አንድ አይደለም ይሆናል ብዬ እንድታብራሪልኝ ጠየቅኩሽ። «መርሳት ምን ይገርማል ብዬ ነዋ… እስኪያሳብደኝ ድረስ መርሳት ሲያቅተኝ አስበኸዋል?» ብለሽኝ አሁንም ሳቅሽ። ጨዋታችንን ወደ ቁም ነገር ወሰድኩት። ኮስተር አልኩ። «እኔንም ቶሎ ትረሺኛለሽ?…» አልኩሽ። «ያው ከተለያየን ህይወት መቀጠሉ ይቀራል…?» አልሽኝ… እንዳልናደድ ፈራ ተባ እያልሽ። እኩል እንደማንዋደድ የገባኝ በዛች ቅፅበት ነበር። ያን ጊዜ ደነገጥኩኝ። ድንጋጤ እና ፍርሃት አንድ ላይ ሰፈሩብኝ። አንቺን የማጣት ይሁን ወይ አንቺን መርሳት ያለመቻል፤ የትኛው እንደሆነ በቅጡ ያልተረዳሁት ፍርሃት ወረረኝ። ሁለታችንም በተለያየ perspective እንደሳቅን ሲገባኝ በጣም አዝኛለሁ። አንቺ «እንኳንና አንተን ስንቱን ረስቼዋለሁ» በሚል። እኔ ደግሞ «አንቺን ከምረሳ ማበድ አይቀለኝም?» በሚል ነበር የሳቅነው። ተለያየን። ከተለያየን ደግሞ ብዙዙዙ ጊዜ ሆነን። አንቺ ህይወቴ ውስጥ ከመምጣትሽ በፊት እንዴት እኖር እንደነበር ጠፋብኝ። ወደዛ ለመመለስ ሞክሬያለሁ። ግን ረሳሁት። ብሞክርም ላስታውሰው አልቻልኩኝም። አንቺ ደግሞ እኔን ረስተሽኛል። እኔ ግን ልረሳሽ በመታገሉ ውስጥ ራሴን እያበድኩኝ አገኘሁት። ከመርሳቱ እና ከማበዱ የቱ እንደሚቀድምልኝ አላውቅም። ቶሎ በረሳሁሽ። አንቺን ስለመርሳት እያሰብኩኝ ባላስታወስኩሽ። አንቺን ስለመርሳት ራሱ በረሳሁ። ብቻ… ከዚህ ሁሉ ነገር የቱ ነፃ እንደሚያወጣኝ የቱ እንደሚያድነኝ አላውቅም። ወይ መርሳቴ ይቀድማል ወይ ደግሞ ማበዴ። @dirshayeabonehmulatu
Show all...
«ፀልይ!» የሚል አነቃቂ በፈላበት አገር ላይ እኛ ካልተጨመርንበትኮ በቃ ህዝቡ ነፍዞ መቅረቱ ነው እናንተ?… ማለቴ መፀለይ የጠፋው ሰው አለ ወይ? «ያለህ ይበቃኛል በል…» ይልሃል አንዱ መጥቶ። «ይቺ አለም አላፊ ጠፊ ነች አትጨነቅ» ይሄ ቆይ ስብከት ነው ማነቃቃት?… እንግዲህ እንደፈረደብኝ እኔው ላነቃቃችሁ። ወንድሜ ሆይ እባክህን አትቆጥብ!… አዎ i said it. አ… ት… ቆ… ጥ… ብ!! እያዳመጥከኝ ነው ወይስ ሄድክ? … ብር አጥፍተኸው ተርፎህ በራሱ ጊዜ ሲቆጠብ ብቻ ነው ደስ የሚለው። ዛሬ ያለህን አውጥተህ ተጠቀምበት… ለነገዬስ እያልክ አትጨናነቅ። 🎶አትጨናነቅ አትጨናነቅ🎶 🕺💃 ና ቆይ የምልህን ስማኝ… ብዙ ጊዜ ከላይ ከላይ የሚባለውን "ዛሬን ኑር" cliché አይደለም ልደጋግምብህ የፈለግኩት። ሃሳቡ በእርግጥ አንድ ነው። ግን ሃሳቡን በደንብ እንድትረዳው "ዛሬን ኑር" ሳይሆን… "ነገ ብትሞትስ?"… እልሃለሁ። ነገ ብትሞትስ? መልስልኝ። አስበኸዋል… ገንዘብህን አጠራቅመህ አጠራቅመህ ነገ ጠዋት ሸኔ አግቶ ብርህን ተቀብሎ ቢደፋህ? … worst way to die. የት ነው የምትሄደው ና ገና አስገድጄ እመክርሃለሁ… እኔ የምልህ ምን መሰለህ… ብርህ ከተረፈህ ብቻ ይደር። ይሄን ስልህ ደግሞ ያለህን ብር አውጥተህ በትን እያልኩህ እንዳይመስልህ። የግድ የሚያስፈልግህ ነገር እያለ ግን ነገን ብለህ አታሳድረው። ዛሬ የሚገባህን ኑሮ መኖር አለብህ። የለብህም? ቆይ ንገረኝ እስቲ የለብህም ወይ? … አለብህ! (ትንሽ ስሜታዊ ሆንኩ) እያለህ ከሰው ለምን ታንሳለህ?… ለምሳሌ በራይድ አትሄድም ኣ?… ሂድ እንጂ። ብር ያለቀብህ ቀን ደግሞ ያው በባስ ትሄዳለህ… ገንዘብ እስካለህ ድረስ ለምን ከህዝብ ጋር ትጋፋለህ? ለምን የሰው ብብት ውስጥ ትወሸቃለህ? ገንዘብ እያለህ? ለነገህ ብለህ?… ነገ ሲያልቅብህ ወደ ባስ መምጣትህ ይቀራል? ብትሞትስ…? አንዴ እስቲ ሁላችንም አንድ ላይ ብሞትስ እንላለን… "ብሞትስ? " ከምሬንኮ ነው እስቲ አሁን አካውንትህ ውስጥ ያለውን ብር ሳትጠቀምበት ብትሞት… አንተ ተሰቃይተህ… ሳትበላ ሳትጠጣ፣ ታክሲ ተጋፍተህ፣ ደህና ልብስ ሳትለብስ፣ ደህና ቦታ ሳታይ፣ የችጋር ኑሮ ኖረህ… ልክ የሞትክ ቀን አካውንትህ ውስጥ ያለውን ብር መንግስት ሲወርሰው አስበኸዋል? ያውም ይሄ መንግስት። (የህግ ባለሙያዎች ብሩን ለቤተሰብ ሚተላለፍበትን አሰራር ካለ እንዳታስረዱኝ ልቀደድበት)… አስበኸዋል ወይ… በጣም አሳዛኝ ሟች ነው የምትሆነው… በፌስቡክ ራሱ RIP የሚልህ አይኖርም… የካርድ ብር ለመቆጠብ ብለህ ፌስቡክ ራሱ አትገባማ አንተ። ታበዛዋለህ እኮ ለዛ ነው። እና እባክህ በኋላ ልትሞት ስለምትችል ዛሬን በደንበ ኑረው። ሳይኖርህ ሲቀር ደግሞ ወደ ሌለው ሰው ኑሮህ ትመለሳለህ። እያለህ ግን ችጋራም ችጋራም አትጫወት… እመነኝ የመኖር አላማ አሁን ደስተኛ መሆን ብቻ ነው። ዛሬን የሚገባህን ኑሮ መኖር አለብህ። አለቀ። አይ አንተን አልሰማህም ካልክ ግን እንደፈለግህ… ሂድ… ያለህ ይበቃኛል በል…ምናምን የሚሉት ያነቃቁህ አያገባኝም። እኔ ግን እልሃለሁ… ነገ ብትሞትስ? P.S ይሄ ነገር… ባለፈው ሰሞን ቆጥቡ ካልኩት ጋር ከተጋጨም ይጋጭ ምናባቱ… እንግዲህ ምን ይደረጋል 🙂 መልካም ቀን 🙂 #motivationforሰኞ @dirshayeabonehmulatu
Show all...
😁 1
ደግ አ'ረገ .... ረጭ ባለው ምሽት በጀርባዬ ተንጋልዬ፣ እግሮቼን እርስ በእራሳቸው ነባብሬ፣ ጆሮዬ ላይ በሰካሁት ኢርፎን የሚፈሰውን የሙዚቃ ድምፅ ከልክ በላይ ጨምሬ፣ አይኖቼን በስሱ ከድኜ፣ በልል ተመስጦ አስባለሁ። በመብሰልሰል እኳትናለሁ። ማሰብ ወደማልፈልገው ነገር ላለመግባት አእምሮዬን፤ ማጅራቱን ይዤ አታገለዋለሁ። ጉልበቱን ማሸነፍ ግን አልተቻለኝም። ነገሩን አለ-ማስታወስ ብፈልግም ጉልበተኛ ሆነብኝ። አእምሮዬ ውስጥ ያለውን ጩኸት በሙዚቃው ጩኸት ልሸፍነው ብሞክርም ልቤን ከሚበላኝ ሀሳብ መሸሽ አቃተኝ። ይባስ ብሎ፤ ከስልኬ የሚንቆረቆረው የሙዚቃ ዝርዝር በቅድም ተከተል ትዝታን ቀስቃሽ ዜማዎች ከስንኛቸው ጋር እየወረወረ አደከመኝ። ስለፍቅር የሚቀኙት ዜማዎች እየሸሸሁት ያለውን ሀሳብ መለመላውን ከፊቴ ገተሩት። አጠፋሁ?! ማለት ጀመርኩ ለራሴ። ማስታወስ፣ ማሰብ ያልፈለኩትን ሀሳብ ራሴን በመጠየቅ ጀመርኩት። አጠፋሁ? እውነት ነው! እርሷ የቀረበችኝ ንጹህ ጓደኝነት ሽታ ነው። መጀመርያም የእኔ ፍላጎት እርሱ ነበር። በጊዜ ሂደት ግን ተመኘኋት። ወደድኳት። አፈቀርኳት። የጓደኝነት ብቻ ሳይሆን የልቤን ጉድለት ሁሉ እንደሸፈነችልኝ ስረዳ ለሚስትነት አጨኋት። አጠፋሁ?! የተመኘሁኋት ለእለት ርሃቤ አይደለም። በህይወት እስካለሁ ለእለት ተእለት ህይወት ቅኝቴ፤ ለመኖሬ ለዛ፤ ለመተንፈሴም ምክንያት እንድትሆነኝ እንጂ። ስሜት ማስታገሻ ወይም አምሮቴን መወጫ ፈልጌም አይደለም። የልቤ ንግስት፣ የቤቴ እመቤት ሆና፤ ከእጇ የሙያዋን ውጤት፣ ከአፉ የሴትነቷን በረከት ከትንፋሿ የህይወትን እስትንፋስ ለመቋደስ እንጂ። እንዲህ አይነትን ፍቅር በጓደኝነት ላይ መካብ ምን ጉዳት አለሁ? አጠፉሁ?! እርግጥ ነው! ንፁህ ጓደኝነትን አስባ ስትቀርበኝ እኔ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝ ይሆናል… ይሆናል። የመጀመርያ ጊዜ ስሜቱን ያጤንኩት ዕለትም የተሰማኝ በመልካም ልቧ ላይ ስለት የሻጥኩባት ያክል ነበር። ፍርሃት ይዞኝ ፍቅሬን ሳልገልፅላት እስካሁንም መቆየቴ "ማፍቀሬን ስነግራት ምን ትለኝ ይሆን?" እያልኩ ስለሰጋሁ፤ ጓደኝነታችንን አደጋ ላይ እንዳልጥል አንድም እንዳላጣት በማሰብ ነው። አይሆንም ብላ ጥላኝ ብትሄድ ምን ይውጠኛል? እእእ? ትልልቅ ዓይኖቿን የት አባቴ ሄጄ አያቸዋለሁ? ጥርሶቿንስ የት አግንቼ እጠግባቸሃለው? ጡቶቿስ የት ይኖራሉ? ገላ ውብቷስ ወዴት ይገኛል? አሪቲ ጠባይዋ፣ አደስ ማንነቷስ መነሻው የት ይሆን? ማጣትን ፈርቼ ዝም አልኩ። ለካ ፍቅር ፈርሃት ያወርዳል። ደፋሩን ያብረከርካል። በፍርሃት ከመራዴ፤ አእምሮዬ ሲወስን ልቤ አልወስን እያለ ሰላም ነሳኝ። ነገሩ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሆነብኝ። ዳግም መብሰልሰል። ዳግም መጨነቅ። ልንገራት? አልንገራት? መነውለል። ጓደኛዬን ማፍቀር ተገቢ ነው? አይደለም? ማበድ። ልቤ በስሜት፤ አእምሮዬ በምክንያታዊነት ለየቅል እየሄዱ ነፍሴን መካከል ላይ ወጥረው ጭንቅ ውስጥ አገቧት። ልቤ ሊያፈቅራት ሲል ጓደኝነቱ አልያዘውም፤አእምሮዬ ግን አብሮነትን ሲያስብ "ጓደኝነትን ብቻ አስቦ ለቀረበ ሰው፤ አፈቀርኩህ ማለት ትክክል አይደለም።" እያለ ከመንገድ ይቆማል። "don't allow ur heart to betray ur better judgement" የሚለውን ብሂል ባምንበትም፤ ፍቅር ግን የማምነውን የምተገብርበት አቅም ነሳኝ። ምክንያታዊነቴ ይሻለኛል? ስሜታዊነቴ? እላለሁ። ይሄም ምክንያታዊ መሆን ነውና፤ የማፍቀሬን ስህተት እፈለጋለሁ። ማፈቀሬ ስህተቱ ምኑ ጋር ነው? ስንቱ እየሰበረ የሄደውን ልቧን ከጠባሳው አክሜ በፍቅር ላድናት መውደዴ፤ የልቤን ሴት ፍለጋ የተንከራተትኩበትን ስንክሳር በርሷ ለመጣፍ ማሰቤ፤ ከደህና'ደሪ ከደህና'ደር አብሮ ማደርን መምረጤ፤ ጸያፉ ምኑ ጋር ነው? እንደውም እንደኔ የሚረዳት፣ የሚንከባከባት፣ የሚያስብላት አይኖርም። ለምን? በጓደኝነት በደንብ አውቃታለሁ። በጓደኝነት ቆይተው ፍቅረኛሞች ወደመሆን ያደጉ ሰዎች የሚያጭዱትን የፍቅር ሰብል ማን ባሳየልኝ። ህዝቤ የፍቅር ህይወቱ ዳገት የሚሆንበት እኮ የፍቅር ህይወቱ እና የልብ ጓደኝነት ሆድና ጀርባ ስለሚሆንበት ነው። እንደኔ ማንም እንደማያውቃት አውቃለሁ። ጓደኝነት ደጉ! ለፍቅረኛዋ የማትነግራቸውን ብዙ ምስጢሮች አጫውታኛለች። የትኛውም ግን እርሷን ከማፍቀር አላገደኝም። አልቀናሁምም… ይልቅስ ወደርሳ አቀረበኝ እንጂ። ታዲያ ውስጣዊ ማንነቷን ርቃኑን አይቼው ላፈቅራት ካልተጠየፍኩ፤ ምን ቀረ? ከግዜ ወዲህ ግን ይህ የኔ ፍቅር ሳይገለጥላት አይቀርም መሰል መራቅ ጀመረች። እርሷም እንደሌላው መጀነንን ሽቱዋ አደረገች። ሁሉም ሴቶች አንድ ናቸው የሚባለው ለካ፤ እውነት ነው። በአንድ መነፅር ካየናቸው! አዎ ሁሉም አንድ ናቸው። እርሷ የተለየች መልአክ የመሰለችኝ በፍቅር መነፅርነት እስካሁን ስላላየኋት ነበር። ልክ የጓደኝነት መነፅሩ ወልቆ የፍቅሩ ሲተካ እርኩስ ሴተነቱ ጎላ። ልቤም በባይተዋርነት እና በትካዜ መዋጥ አበዛ። በጥፋቴም የምቀጣ መሰለኝ። ማን ጓደኛህን አፍቅር አለህ? ገጽ አንድን ክፈት ስትባል ገፅ 17 ላይ ምን ወሰደህ? ራሴን እወቅሳለሁ። አፍታም ሳልቆይ ደግሞ መልሼ እገለበጣለሁ። ለምን ራሴን እወቅሳለሁ? እላለሁ። ማፍቀርን ወንጀል ያደረገ ማነው? ይብላኝ ፍቅሬን ላልተረዳ፤ ፍቅር ጎደለበት፤ እንጂ እኔ ምን አጠፋሁ? ይብላኝ ለርሷ ፤ እኔስ በእንባ አሻገረዋለሁ። ጓደኝነትን ስታስብ አፈቅርኳት? እንኳን አፈቀርኳት። ዘመን የተሻገረ እንባዋን ላብስ ባልኩ፤ በጠለፍኩልሽ የመውደድ ሸማ እርቃን ገላሽን ሸፍኚ ባልኩ። ሁሌ ተቀምጦ ሚስትህ አትመጣም? ባልሽ አይመጣም እየተባባሉ ከመነፋረቅ እኛው ባልም ሚስትም እንሁነው ባልኩ?። አጉራሽ ከማለም እንጎራረስ፣ አፍቃሪ ከመጠማት በልባችን ፍቅር እንርካ፣ ብቸኝነትን ከማውራት መዋደዳችንን እናውጋው ባልኩ፤ ከኔ ለመራቅ መሞከር ተገቢ ነው? ባፈቅራትስ ጥፋት አለው? እንኳን አፈቀርኳት! ደግ አደረኩ። እሰይ! ደግ አደረኩ!። እርሷ ባትፈቅድለትም፤ የባከነ ልቧን በልቤ አሳረፍኩት። የሚዋልል አይኗን ከአድማስ ገታሁት፤ በቅርብ አሳደርኩት። ደግ አደረኩ። እንኳን አፈቀርኳት። ሳላውቀው እንባዬ በእልህ ከአይኔ ወረደ። ባዶ ቤት፣ አልጋዬ ላይ ብቻዬን ተንጋልይ እንደተኛሁ ነበርና፤ በዝግታ የሚወርድ እንባዬን ከመውረድ አልከለከልኩትም። ግማሽ ቀልቤን ከመብሰልሰል ወዳላዳነኝና ጆሮዬ ላይ ወደሚጮኸው የሙዚቃ ደምፅ ጣልኩት። ስንኞቹ ኮረኮሩኝ። ባትመጣ አትመጣ፣ አሳዛኝ ጠባቂ፤ እዚህ ላብድልሽ ነው ፣ አንቺ እዚያ ስትርቂ ፤ አልፈርድም በልቤ ምን ባ'ረገ፤ ነገ ጠባ አንቺን እየፈለገ ፤ ደግ አ'ረገ! ኤይ... ደግ አ'ረገ! ደግ አ'ረገ! ኤይ....ደግ አ'ረገ! ደግ አ'ረገ! አንቺን ፈለገ! ሃሃሃሃሃሃሃሃ… ሳቅሁ… @dirshayeabonehmulatu
Show all...
የሆነ አዲስ ስራ ልትጀምር ብለህ የስራውን ሁኔታ በደንብ ስለማታውቀው ፈርተህ እያመነታህ ነው?… እንግዲያውስ ይህንን አድርግ። ብራዘረይ… ሰፈር ውስጥ ምን አይነት የተመቱ ሴትዮ አሉ መሰለህ… ልክ የሆነ ፀጉረ ልውጥ ሰው እናንተ ሰፈር ለመኖር ሲመጣ ድንገት እንዳዩት "ይሄ ልጅ ሌባ ነው አሉ" የሚሉትን ሴትዮ አወቅካቸው?… የትም አያውቁትምኮ ልጁን። ዝም ብለው "ሌባ ነው አሉ" ብለው ይፈርጁታል።… መጡልህ ኣ ሴትዮዋ?… ከዛ ልጁ የምርም ሌባ ሆኖ የሚገኘው? እሳቸው ጋር ትሄድና እንደዚህ እንደዚህ ስራ ልጀምር ነበር ምን ያስባሉ በላቸው። ወዲያው ነው react የሚያደርጉት። "አዬ ልጄ እኔ ምኑን አውቄው… " አይሉህም። "እሱ ነገር ጥሩ ነው አሉ"… ወይም ደሞ… "ተው ልጄ ይቅርብህ… " ይሉሃል። በቃ የሚሉህን ነገር ቶሎ ብሎ ማድረግ ነው። ምን አልባት የቢዝነሱ መነሻ ብር ብዙ ሆኖብህ የእሳቸው ነገር ካላስተማመነህ አንድ ሰው ልጨመርልህ። ጓደኛህን። ያ ዝም ብሎ ምንም ቢሞክር የማይሳካለት ጀለስህ። ቤተሰቦቹ ሦስት ጊዜ የስራ መጀመሪያ ብር ሰጥተውት ሞክሮ ሁል ጊዜ የሚከስረው… አሁንም ካንተ እኩል እከካም የሆነው ልጅ። ቤቲንግ ሲጫወት እንኳን 12.5 እና 1.1 odd ላይ 1.1ዱን win ብሎ ሄዶ 12.5ቱ የሚያሸንፍበት ልጅ አለ ኣ?… ወላ እድሉ ጠማማ ከመሆኑ የተነሳ ወረፋ እንኳን ቶሎ የማይደርሰው… ከኋላው የመጣ ሰው ቀድሞ የሚስተናገድበት ልጅ?። ይሄኛው ጀለስህ ጋር ሂድና እንዲህ አይነት ስራ አለኝ በለው። አሪፍ ነው ካለህ በቃ እርግፍ አድርገህ መተው ነው አለቀ። ጭራሽ እንዳታስበው ወንድሜ። በጣም ከፈራህ ደግሞ ለማስተማመኛ እንዲሆንህ ሦስተኛ ሰው ልጨምርልህ… ይሄ ወሳኝ ሰው ነው! አብይ አህመድ ስልጣን ሲይዝ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሰውየውን በጭራሽ የማይወደው ሰው ፈልግ፣ ገና ስሙን ስታነሳበት ያንገሸግሸዋል፣ ድሮም ስልጣን ሲይዝ ምንም ቀልቡ አልወደደውም። ይሄ ሰውዬ ህይወትህ ውስጥ ካለህ… እድለኛ ነህ። በቃ በጣም ወሳኝ ሰው ነው። ተጠቀምበት። ስለ ስራህ ንገረውና የእሱን ስሜት እና ቀልብ ተከተል… ጀምር ካለህ አይንህን እንዳታሽ። ተው ካለህም እንደዛው። የአገር ጥናት ምናምን አንብበህ ከምታውቀው ትንበያ ይልቅ የዚህ ሰው foresight አስተማማኝ ነው። ገራሚ ቀልብ ነው ያለው በቃ እመነው። ስማኝ ወንድም አለም… አይ እኔ አውቃለሁ፣ ገበያውን አጠናለሁ፣ ኢኮኖሚው ይገባኛል፣ የሃገሪቱን ሁኔታ እና መንግስትን አይቼ ስራዬን እጀምራለሁ ካልከኝምኮ መብትህ ነው። እኔ ግን የሚሻልህን ነግሬሃለሁ። ሴትዮዋ ስራውን ጀምረው ካሉህ፣ ጓደኛህ ተወው ካለህና እና ይሄ አብይን ሲፀየፍ የኖረው ሰውዬ ደግሞ ካፀደቀልህ… እመነኝ አንተ በአጭር ጊዜ ውስጥ multimillionaire ትሆናለህ። መልካም ቀን 🙂 @dirshayeabonehmulatu
Show all...
😁 2
Show all...
😁 2 1
ትልልቅ ሰው ሁሉ ማሊያ እየለበሰ ነውኮ መንገድ ላይ የማየው… ኧረ ኳስ በጣም seriously እየተወሰደ ነው እዚህ ሃገር… በኋላ መንግስት ላይ የኑሮ ውድነት እና የሰላም ጥያቄ ስናነሳ ኳስ እያያችሁ አይደል እንዴ ነው የሚሉን። እና ብናይስ ምን አገናኘው ብትል ማንም አይሰማህም። «ሃገራችን አድጋለች። ሰዉን ተመልከቱት። ኳስ ያያል ጥሬ ስጋ ይበላል… ጥሬ ስጋ እያየ ሁሉ ኳስ ይበላል» ጠሚ አ.አ anyway ስለኳሱ… i hope they both lose. @dirshayeabonehmulatu
Show all...
እንደምን አደርክ ወንድሜ… ስማኝ ጨላጣው… አንተ አንድ ያልገባህ ነገር አለ…እስቲ ሰግጥ በቃ… ለምን አትሰግጥም? ምን አስፈራህ? አንተስ እንደሌሎቹ ለምን ዝም ብለህ ሰግጠህ አያልፍልህም? የሰገጡት የት እንደደረሱ እያየህ ነው?… በቃ አንተም ደደብ ደንቆሮ ሁን እና እየው እስቲ ደሞ። ይኸውልህ ሳሙናው… እስቲ ያንን ሰውዬ ተመልከተው… ገገማ ስለሆነ ነውኮ እዚህ የደረሰው። እንዳንተ ቢያስብ፣ ቢጨነቅ፣ ሰው ምን ይለኛል ምናምን ቢልማ ይሄን ጊዜ አንዱ ቀበሌ ውስጥ ድራፍት በአረቄ በርዞ ጠጥቶ ሀንጎቨር ላይ ሆኖ ይሄንን ፅሁፍ ዕንኳን አያነበውም ነበር። ግን በቃ እሱ ገገመ… ማንንም አልሰማም! … ይኸው ዛሬ ቤተ መንግስት ነው ያደረው… ይመቸው! ምን እያደረገ እንደሆነ እግዜር ይወቅ… (መቼም ድንገት ተነስቶበት ለሚያስበው ነገር ፈጣሪ ይሁነን ) ምን መሰለህ አረፋው… ብዙ ሰው አንተ እንደሚመስልህ ያን ያህል ስላንተ ጉዳይ አይበሰለሰልም… ብዙ አይጨነቅም። የሆነ ነገር ብታደርግ እንኳን… አንድ ጊዜ አየት አድርጎህ ወደ ራሱ ህይወት ነው የሚመለሰው… ሁሉም ሰው እንዳንተ አይነት ሰው ነው… የራሱ ህይወት አለው። እና በቃ የምትፈልገውን ነገር ዝም ብለህ አድርጋ… አሁን ላይ እኮ ሀብታም እና ታዋቂው ሰው በሙሉ ይሉኝታ የሌለው ሰው ጥርቅም ነው። የእነሱን ቦታ እንደ ስኬት ከቆጠርከው በቃ ቀላል ነው በእነሱ መንገድ ሂድ… ሰይፉ ፋንታሁንን እየው እስቲ። እድሜ ዘመኑን በትችት የኖረ ሰውዬ ነው አሁን ላይ እሁድ እሁድ አርቲስት እየጠራ የሚዛለፈው… ሬዲዮ ሲሰራ ጀምሮ የማይሰድበው አልነበረም። ያለ ገደብ ይጫወት ስለነበር ፅንፍ የወጣ ቀልድ እና ስድብ የሚላከክበት ሰው ነበር ሰይፉ ፋንታሁን። እሱ ግን ማንንም ሳይሰማ… (ሰገጠ እንኳን አንልውም) አሁን ላይ ትልቁን ቲቪ ሾው ያዘጋጃል። በቃ ይችላል! ቅዳሜን ከሰዓት እና እሁድን በኢቢኤስ አይተህ ታውቃለህ? እንሱ እንኳን ለቀረፃ ሲጠሩ ብቻ መሰለኝ የሚሄዱት… አንድም ነገር አይዘጋጁም። በቃ ደፋር ናቸው… ማንንም አይሰሙም። (እንደነሱ እንኳን ባይኮን ይሻላል) ብቻ አረፋው ይሄንን ልብ በል… ሰው ብዙ የሚያስጨንቀው የራሱ ጉዳይ አለበት። ሌላ ሰው ሳትጎዳ አንተ የመሰለህን ብቻ አድርግ። ልክ ከመሰለህ ልክ ነህ… ከተሳሳትክም ተሳሳት። ነገ ሁሉም ይረሳዋል። ሌላ ቀን ደግሞ አሻሽለህ ትሞክራለህ ምን አባቱ… ማን ያዘዋልን አታየውም እንዴ? ሦስት ሰው አያነቃም እኮ ግን ሶስት መቶ ሺህ ተከታይ አለው… ከዛ ይሸቅላል። አነቃሃለው ብዬሃለሁ አነቃሃለሁ እያለ ነውኮ ስራ የሚሰራው… አንተም ነኝ ብያለሁ ነኝ ብለህ መሰገጥ አለብህ። መንሱርን እየውማ… ይሄ ፋራ ትለዋለህ… እሱ ፋራ አንተ ጨላጣ… ግን እሱ ጠዋት ሽቶውን እየነፋ ላይቭ ይገባና ይሸልምሃል አንተ ኮመንት ላይ ለመሸለም ትራኮታለህ… ማነው ፋራ ማናው ጨላጣ እሺ? tiktok ላይ ያሉትን አብዛኞቹን አታያቸውም? ቀን በቀን አንዳይነት ነገር እያደረጉ ከዛ የመቶ እና የሁለት መቶ ሺህ ብር የማስታወቂያ ስራ መስራት ላይ ይደርሳሉ… አንተኮ ይቺ ልጅ ጨለለች እንዴ…? እየዞረች ሰው የምታቅፈው ብለህ አልፈሃት ነበር… አንተ ነህ የጨለልከው ብሮ… ጨልል ብሮ ጨልል ሰግጥ አባቴ ሰግጥ ደንቁር ጌታዬ! ጊዜው እንደዛ ነው! #motivationforሰኞ @dirshayeabonehmulatu
Show all...
👍 1
እስቲ አብዛኞቹን ሃብታሞች ተመልከታቸው… ቋጣሪኮ ናቸው። በጣም ነው የሚቆጥቡት… 10 ብር ራሱ ብዙ ብር ነው የሚመስላቸው። በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በተዓምር ብር አያወጡም። ያው ሰርተው ለፍተው ያገኙትን ሀብታሞች ነው የምልህ… የዘረፉትን አይደለም። አንተ ደሞ አለህ በተራህ… ገንዘብ የለህም ግን ያለህንም ዝም ብለህ ትበትነዋለህ… ለራስህ እንኳን የሚበቃህ ብር ሳይኖርህ ከበር መልስ ካልጋበዝኩ ማለት ሁሉ ያምርሃል። ስማኝ አሁን ልመክርህ ነው… ላነቃቃህ! እምቢ አልከፍልም በል… ቋጥር… ቆጥብ በቃ። የጀበና ቡና 5 ብር ካልሆነ አልጠጣም ያዋጣሻል በላት… እምቢ ካለች አትጠጣ… አትሞት ቡና ስላልጠጣህ። የራይድ ሹፌር ዝርዝር የለኝም ሲልህ በሼም እንዳትሄድለት… ዞር ዞር ብለህ ዘርዝረህም ቢሆን ስጠው። አይ ካለ በእግርህ ሂድ በቃ። ጓደኛህ ዛሬ ጋባዥ ነህ ምናምን እያለ ማኖ ሲያስነካህ ተኮሳተርበት እንዳትሰማው… ጓደኝነታችን ሊቀር ይችላል በለው። ታክሲ ውስጥ የምታውቀው ሰው ካየህ ውረድ። አለዛ ደሞ ሰላም ሲለህ "ወሮ በላ የት ታውቀኛለህ?" በለው… "አቡቹ ነኝ እኮ" ሊልህ ይችላል። በጥፊ አጩለው። የዕቃ ዋጋ ጠይቀህ ልትወጣ ገብተህ በሼም የማያስፈልግህን ዕቃ እንዳትገዛ። እሺ ስንት ላድርግልህ… ስንት ትወስደዋለህ ስትልህ… አይ ልጠይቅ ነው የገባሁት በል። ቆፍጠን በል… በቃ እምቢ በል። አንተምኮ እንደሃብታሞቹ እየሰራህ ነው… ስላልቆጠብክ ዝም ብለህ ብር ስለምታጠፋ፣ ቸር ስለሆንክ ይሆናል ያላለፈልህ። እስቲ ኧገሌ ታመመ፣ ኧገለ ወለደ መዋጮ ምናምን ሲሉህ አላዋጣም በል፣ ብር የለኝም ቸግሮኛል በል በቃ። ሳታስበው የምታወጣው ትንንሽ ብር ነው የሚያደኸይህ። በቃ እምቢኝ በል አልኩህ። "ይሄ ባክህ ብር አይደማውም" የሚል ቅፅል ስም እስኪወጣልህ ድረስ ቋጥር። ከዛ ነው ሀብታም የምትሆነው ጌታዬ። መልካም የመቋጠር ሳምንት ይሁንልህ 😄 #motivationforሰኞ @dirshayeabonehmulatu
Show all...
👍 1
"በቃ እንደዋወል" ከምትሉ ሰዎች ውጪ… እንዴት አደራችሁ?… የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ 🙂 @dirshayeabonehmulatu
Show all...
😁 1
አንዲት ህጻን እናቷን "እማዬ እማዬ" "አቤት" " ለምንድን ነው ሴቶች የሰርጋቸው ቀን ከፀጉራቸው ጀምሮ ነጭ የሚለብሱት?" " የመሞሸሪያቸው ቀን ስለሆነ፤ ነጭ ደሞ የደስታ መግለጫ ስለሆነ የደስታችን ቀን ነው ብለው ነው" " እና እማዬ ታዲያ ለምን ወንዶች ለሰርጋቸው ጥቁር ይለብሳሉ? " እስኪ እየጠጣን እንወያይበት ጎበዝ 🍺 @dirshayeabonehmulatu
Show all...