cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

of all page/የሁሉም ገጽ🎤🎤🎤🎬🎬🎼📞☎️📡⏰🩸🩸🩸🎈🎈🎈💌💌📝🖊🖋✏️🖍🖌🖌❤️❤️🔓

join with us/ከእኛ ጋር ይቀላቀሉhttps://t.me/ofallpage2013ecbirethiopia

Show more
Advertising posts
194Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ትናንትና እና ዛሬ የታከለ ኡማ አባት በሸኔ ታገተዋል እየተባለ ሲወራ ነበረ። ሸኔ አባትህን መልሰህ ለማግኘት ከፈለክ 10 ሚሊየን ክፈል ብሎታል ሲባል ነበረ። ታከለ ኡማ ይህን ዜና አላስተባበለም። ግን በሌላ አነጋገር አባቱ ሰላም ስለመሆኑ ፃፈ። ይኸው፣ "አባቴ አርሶ አደር ነዉ። አሁንም ግብርና ላይ ነዉ።" አንዳንዶች ታኬ አባቱን ካስለቀቀ በኋላ ነው የፖሰተው እያሉ ነው። ታኬ ግን አባቱ ስለመታገቱ አላመነም፣ አላስተባበለም። ከውዝግቡ ገለል ያለ መልስ ነው የሰጠው። አባቱ ገበሬ ናቸው፣ አሁን በግብርና ላይ ናቸው። ተለቀዋል? ነው? አልታገቱም ቀድሞውንም ነው? ግልፅ አይደለም። ለማንኛውም በልጅ ስራ አባትን መያዝ አሳፋሪ ነው። ያባት እዳ ለልጅ ይባል ነበር ድሮ ይባላል። ሸኔዎች ገለበጡት መሰለኝ። የማይገለብጡት ነገር የለም።
Show all...
ወለጋ ኪራሙ… "…ባለፈው ሳምንት ከ50 በላይ ንፁሐን ዐማሮችን የጨፈጨፈው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነኝ የሚለው ሕጋዊ ገዳይ ቡድን ከርሸና የተረፉ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የዐማራ ህፃናት፣ ሴቶችንና አቅመደካሞችን በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ሰብስቦ እህልና ውኃ በመከልከል በራብ ሲያሰቃያቸው ከርሟል። "…ዛሬ ግን ከመረሸን የተረፉትን ከመቶ በላይ ዐማሮች ወይ እህል ውኃ ስጧቸው፣ ለፍርድ አቅርቧቸው፣ አልያ ደግሞ ፍቷቸው በሚል ማኅበረሰቡ ይጠይቃል። ምንም ፖለቲካ የማያውቁ አዛውንትና ህጻናትን አስሮ ማሰቃየት፣ በራብ መፍጀቱ ምን ይጠቅማችኋል? ቢባሉም እምቢ አሉ። ይባስ ብለው ዐማራ ይግጠመን፣ ይለይልን ብለውም ለያዥ ለገናዥ አስቸገሩ። "…በትምህርት ቤቱ ዙሪያም ከባባድ ምሽጎችንም ቆፈሩ። ሸኔም ሆነ ልዩ ኃይሉ የታጠቀው መሣሪያም ልዩ ነው። የተተኳሽ እጥረትም የለባቸውም። በአደረጃጀት ደረጃም ብዙ ናቸው። ዲሽቃ ጭምር የታጠቁ ናቸው። ዛሬ ጠዋት ንጋት 12:00 ሰዓት ጀምሮም ተኩስ ከፈቱ። ህዝቡም እንደድሮው መሮጡን ትቶ ሲዋጋ ዋለ። ምሽጋቸውንም ሰብሮ ገባ። በወንበዴው ሸኔ ሳይሆን በሕጋዊው ሸኔ ከታገቱት መካከልም የተወሰነው ህዝብ በነፃ ሊወጣ ችሏል። ከመካቹ ዐማራ ወገን ህክምና ስለሌለ ህክምና የማያገኙ የቆሰሉ ጥቂት የሞቱም አሉ። "…ከመሸም ደውዬ ነበር። "…ዘመዴ ውጊያው እንደቀጠለ ነው። መንግሥትም የሸኔን ሥራ በግልፅ እየሠራ ነው። አሁን ከመሸ ሸኔም ተጨምሮ ዙሪያውን ተኩስ ተከፍቶብናል። ሞትም መቁሰልም ቢኖር ግን ነገሩ እንደ ድሮው ንጹሓኑን እንደመጨፍጨፍ አለቀለላቸውም። የታገቱትን በከፊልም ቢሆን አስለቅቀናል። እየተዋጋን የምንገኘው ከራሱ ከሽመልስ አብዲሳ ጦር ጋር ነው። እኛ ድረስልንም ብንለው የሚደርስልን ስለሌለ ጥሎ ከመውደቅ በቀር ሌላ ምርጫ የለንም።" ብለዋል። •መፍትሄው ጥሎ መውደቅ ብቻ…!
Show all...
"…ይሄ ሁሉ ኦሮሚያ ውስጥ ነው። አስከ አሁን አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አልተደነገገባትም። ጉራጌ የክልል መሆን መብቱን ስለጠየቀ በመደበኛው ሕግ ማስከበር ጉራጌ ያለውን ሰላማዊ ጥያቄ ማስቆም ስላልቻልኩ ብሎ ጉራጌን በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ስር የጣላት ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ግን የቀለጠ ጦርነት ውስጥ ሆኖ ዝምታን መርጧል። "…ይሄ የሚታየው የኦሮሞ ሰልጣኝ፣ ከመንግሥት በገፍ በሚቀርብለት ስንቅና ትጥቅ ታግዞ የሚዋጋው ከዐማራ ምስኪን ገበሬ ጋር ነው። ዱርዬው መንግሥት መውደቁ፣ ጭቁኖች ነፃ መውጣታቸው አይቀርም። ሁሌ እንዳጭበረበሩም መኖር አይቻልም የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውጫ፣ መተንፈሻ አጥቶ እንዲህ ታመቀው የብሶት፣ የቁጭት፣ የእልህና የበቀል አየር አንድ ቀን መፈንዳቱ እንደሁ አይቀር…!! "…እስከአፍንጫው ከታጠቀ ከዚህ ሁሉ ጉግማንጉግ የሰው ዐውሬ ጋር ተዋግቶ መውደቅ በራሱ ጽድቅ ነው። ከፈጣሪ በቀር የሚሰማውም፣ የሚደርስለትም የሌለው የወለጋ ዐማራ በብላሽ ከመታረድ ጥሎ ወድቆ መሞቱ ክብሩ ነው። ለወሬም ያመቻል። አንዱ አስርሺ ያሳድድ ዘንድ ሞገስን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን። "…ዛሬ ዝም ያለ ሁሉ የወለጋ ዐማራ የቀመሰቅን ፅዋ ግን ሁሉም ሰው የግዱን ይጋታታል። አሁን ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ባህርዳር ጎንደር መሄድ አይቻልም። አሊዶሮ ላይ ኦነግ መንገድ ዘግቶ የቀለጠ ጦርነት ላይ ነው ያለው። መንገደኞች ማለፍ አልቻሉም እየተባለ ነው። ሰዉ ግን ኢትዮሳት በመቋረጡ ከአሜሪካና ከኢራን በእግር ኳስ ማን ያሸንፍ ይሆን ብሎ በጭንቀት ሊፈነዳ ነው። ጭንቀቱ ኳስ ባለማየቱ ነው። መልካም ጭንቀት የጭንቀት ዘመን ይሁንልን። "…እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥” መዝ 62፥11 • ድል ለቢዛሞ ወለጋ ዐማራ…!!
Show all...
መረጃ‼️ የጉራጌ ዞንን ጨምሮ አዲስ በሚመሰረተው"ማዕከላዊ ኢትዮጵያ" በተሰኘው ክልል ዙሪያ የደቡብ ክልል አመራሮች ተወያዩ የፌዴሬሽን  ምክር  ቤት ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት ጉራጌ፣ሀዲያ፣ ስልጤ፣ ከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ዞኖች  እንዲሁም የየም ልዩ ወረዳ 'በአንድ ክልል ተደራጅተው ' እንዲቀጥሉ እነዚህን ስድስት መዋቅሮች ይዞ  አዲስ በሚደራጀዉ 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል' አደረጃጀት  ዙሪያ የደቡብ  ክልል ርዕሰ መስተዳድር  አቶ  ርስቱ ይርዳዉ ፣  የክልል፣ የዞን እንዲሁም የልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በቡታጅራ ከተማ ላይ  ዛሬ  ዉይይት  አካሂደዋል ሲል የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አስታውቋል። አዲስ የሚደራጁ ክልሎችን  የማዋቀሩ  እንቅስቃሴ  ጎን ለጎን  እየተሠራ መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ ፣ የአደረጃጀት  ሥራዉን የሚያስተባብር  የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተዋቅሮ ተግባራዊ  እንቅስቃሴ  መጀመሩን  ገልጸዋል። በፌዴሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔ መሠረት ያለህዝበ ዉሳኔ በቀጥታ በአዲስ መልክ  ለሚደራጀዉ የ'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል'  አደረጃጀት  አስፈላጊ  የሆኑ ተግባራት  እየተከናወኑ  መሆናቸውንም ጠቁመዋል። 'ማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል' የሚል ስያሜ  ይዘዉ በአዲስ ክልልነት  የሚደራጁት፣ የየም ልዩ ወረዳ፣ የሀዲያ፣ የጉራጌ፣የስልጤ፣የሀላባ እንዲሁም  የከምባታ ጠምባሮ ዞኖች ህዝቦች  ጠንካራ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎችም  መስተጋብሮች  ያሏቸዉና በመልካም ምድር አቀማመጥም የተሳሰሩ በመሆናቸዉ  የህዝቦቹን አቅም አስተባብሮ  የህዝቦቹን የልማትና የመልካም አስተዳደር  ጥያቄ  ለመመለስ አዲሱ አደረጃጀት  ምቹ እድል መሆኑ ተነስቷል መባሉን ብስራት ራዲዮ ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።(ዳጉ_ጆርናል) @sheger_press
Show all...
የማይካድ ሀቅ ነው ይነበብ!! በጋዜጠኛ ፋሲል የኔ አለም የተፃፈ። ጠ/ሚ አብይ አህመድ 85 በመቶ የሚሆነውን የብልጽግና አመራር አስወግዶ፣ ሰፊና ጥልቅ አስተሳሰብ ባላቸው ተራማጆች ካልተካ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን ካለበት የአስተዳደር ሰቆቃ ነጻ ይወጣል ብዬ አላስብም። በህወሓት ዘመን እንደነበረው ሰዎች ሲያጠፉ ወይም አቅም ሲያንሳቸው ወንበር እየቀያየሩ ማስቀመጥ ኢትዮጵያን ከመግደል ውጭ ምንም ጥቅም የለውም። አሁን ላይ የባለስልጣኖች ትዕቢት የደረሰበትን ደረጃ ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ። የአብዛኞቹ ባለስልጣናት ንቀት የሚገርም ነው። ደግሞ እኮ የሆነ ታዕምር ሰርተው ወይም የሆነ የተለየ እውቀት ኑሯቸው ቢንቁ እሽ፣ እንዴው በየመንገዱ በሚቸበቸብ ዲግሪ ስልጣን ይዞ እንዲህ መንጠባረር ምን የሚሉት ነገር ነው? እንዴ! አሁን እኮ አንድ የወረዳ ባለስልጣን ከማናግር፣ የደችን ጠ/ሚንስትር ማናገር ቀላል ሆኖ እያገኘሁት ነው። ጠ/ሚንስትሩ ባይችል እንኳን የይቅርታ መልዕክት ያልክልሃል። የእኛዎቹ እኮ ስልክ ጆሮህ ላይ እስከመዝጋት ይደርሳሉ። እነዚህ ሰዎች ሙያህንም መንግስትህንም እንድትጠላ ያደርጉሃል።90 በመቶው ከሚዲያ የሚሸሹት በራስ የመተማመን ችግር ስላለባቸው ወይም አንዳች የሚደብቁት ነገር ስላለ እንደሆነ እገምታለሁ። እስከመቼ እነዚህን ሰዎች ቦታ እያቀያየሩ ተሸክሞ መጓዝ ይቻላል? የሃገሬ ህዝብና የሙያ ባልደረቦቼ ጽናቱን ይስጣችሁ። @sheger
Show all...
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ከኅዳር 25 ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ትምህርት ሚንስቴር በጻፉት ደብዳቤ ማሳወቃቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ዜና ምንጩ ለመረጃው በዋቢነት የጠቀሰው፣ መረጃ ሰጡኝ ያላቸውን የተወሰኑ የዩኒቨርስቲ መምህራን ነው። መምህራኑ የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የወሰኑት፣ ለመንግሥት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ባለማግኘታቸው እንደሆነ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ማኅበር የአባሎቹ የደመወዝ ጭማሪ፣ የደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት ድጎማና የመድኅን ሽፋን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ባለፈው ነሐሴ ለመንግሥት ደብዳቤ ማስገባቱን መግለጡ ይታወሳል።
Show all...
ደርሶናል ብለዋል። "…የጫካዎቹ ያሉበት ድረስ የቤተ መንግሥቶቹ በሰላም አድርሰውላቸዋል…!!😂😂😂… ሌላህ አልቅስ። "…መከላከያ ይሄን ጥቁር ክላሽ ሲያይ ያመዋል። ፋኖ የታጠቀው መከላከያ ገድሎ ነው አለ ኦነጉ ዐቢይ አሕመድ…እህዕ "…በድኑ ብአዴን የምሥራቅ ዐማራን ፋኖ ትጥቅ ፍታ ብሎ ወጥሮ ይዟል። 18 ሺ ፋኖ በዐማራና በአፋር ክልል ዘብጥያዎች እየበሰበሰ ነው። "…እኔየምለው ኦነግን የተቀበለ ጫካ ዐማራን አትምጣብኝ ብሎ ይጸየፋል እንዴ? …ስላልገባኝ ነው።
Show all...
#_ስልኬን_አፍዝዘው_ወሰዱብኝ_ሌቦች 😥" በምስሉ ላይ የምታዩት ቅጠል ተራ አበባ እንዳይመስላቹ ባንክ አቅራቢያ ፣ ገበያ ስፍራ ፣ መንገድ ላይ አንድ ሰው ከጨበጣቹ በውሃላ የምትሆኑትን ስለማታውቅ ያላችሁን ገንዘብ ስልክ ወርቅ ጌጥ በሙሉ አውልቃቹ እንድትሰጡ የሚያደርግ እፅዋት እንጂ የሚገርመው ደግሞ ሽታው በጣም ነው ደስ የሚለው... ከረዥም ጊዜ በውሃላ ወደ ፅሁፋችን ስንመለስ በዚህ ቅጠል ተከስተናል አንዲት የ60 አመት ሴት ቅጠሎችን ቀምማ ሻይ የማዘጋጀትና የመጠጣት ልምድ ነበራት ። ታድያ ከእለታት ባንዱ ቀን ይህን መዓዛው የሚማርክና አስተዳደጉም የሚለይ (ቅጠሉ ወደ ታች እንደ ትራምፔት ይዘቀዘቃል) ቅጠል ለሻይ ፈጭታ ጠጣች ። መቃዠት ጀመረች የሚሆነውን ነገር አታውቅም ውስጧ በካርበን ጭስ እንደታፈነ ሰው ትጨናነቅ ጀመር የድርቀቱ ጉዳይ ሌላ ነው ። ከ15 ሰአታት ምርመራ በውሃላ በብረግማንሲያ ቅጠል መመረዟ ተረጋገጠ ። ይህ የሆነው በሲሪላንካ ሲሆን ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ እንምጣ ። ብዙ ጊዜ ሰዎች አፍዝዘው ስልኬን ወሰዱብኝ ከባንክ እንደወጣሁ የሆነ ሰውን መከተል ጀመርኩ ከዛ ከሰአታት በውሃላ ስነቃ ምንም አላቅም ባዶ እጄን አንድ ካፌ ውስጥ ተቀምጬ ራሴን አገኘሁት ይሉናል ሰዎች ይህ የሌቦቹ ስራ ድግምት እንዳይመስላቹ ድግምት አይደለም የለምም ይህ የብራግማንሲያ ቅጠል ስራ ነው ። ሌቦቹ በመጀመሪያ ማን ብዙ ብር እንደያዘ ማን ደህና ስልክ እንደያዘ ካረጋገጡ በውሃላ ነው ። ይህን መርዛማ እፅዋት በየትኛውም አጋጣሚ ሰዎች እንዲነኩት የሚያደርጉት ለምሳሌ ባንክ የማውጫ ፎርም ስንሞላ እስክሪቢቶ የሚያቀብሉን ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ አሊያም የተጋጨን በመምሰል መንገድ ላይ ገፍተውን አልፈው ሄደውም ሊሆን ይችላል ። ኧረ 200 ብር ቅጠሉን ፈሳሽ ከቀቡ በውሃላም መንገድ ላይ የሚጥሉ አሉ ብቻ በተለያየ መንገድ እንድንነካው ያደርጉናል ። ታድያ እኛ ከዛ ቅጠል ጋር ከተገናኘን በውሃላ ምን ይፈጠራል ? መገናኛ እየሄድክ ነው እንደ አደገኛ ሙዚቃ ወዳጅ ኤርፎን በአንድ ጆሮህ አርገህ ጂም ሁለት ቀን ሰርተህ ቲሸርት ለብሰህ ስትዞር ከትከሻህ ወዲ ያለው ሰውነትህ ለማንኛውም ነገር የተጋለጠ ነው ። እኔ ደግሞ ደህናና ያለው ሰው ስለመሰለልከኝ ተከትዬህ ሙሉ ቅጠሉን በቀባሁት ጃኬቴ ገፍቼህ አለፍኩ ። ስራውን በደቂቃ ውስጥ የሚጀምረው ቅጠል ትከሻህን ታሽቶ ወደ ደምስርህ ገብቷል ። አሁን አዙሪቱ ይጀምራል ተመርዘሃል ሰውነትህ hallucinate ማድረግ ይጀምራል ። ምንድነው hallucination ? ሀሉሲኔሽን ማለት የተሳሳተ የስሜት ህዋስ መልእክት ሲሆን የሌለ ሽታ ይሸትሃል ፤ የሌለ ሰው እንዳለ ይሰማሃል ፤ ያልቀመስከውን ነገር ምላስህ አስሬ ማጣጣም ይጀምራል ፤ በአካባቢው የሌለ ድምፅ ይሰማሃል ። ይህን ጊዜ መጥቼ ጓደኛዬ ምን ሆነህ ነው እልሃለው ታየኛለህ በእውኑ አለም አታቀኝም እየተከናወነ ያለውን ነገር ግን ስለማትረዳ ከእኔ ጋር እየሄድክ እንደሆነ ታስባለህ ጓደኛዬ እያልክ ትከተለኛለህ እያወራን ወደ አንድ ስፍራ ከወሰድኩህ በውሃላ ምጠይቅህን ሁሉ ላንተማ ከሆነ እያልክ ታቀብለኛለህ ደክሞኛል እቃዬን ያዝልኝ ልትል ሁሉ ትችላለህ ። ይህ የሚሆነው የብራግማንሲያ ቅጠል ልክ ወደውስጣችን እንደገባ የመጀመሪያ የሚያደርገው ነገር ቢኖር የስሜት ህዋሶቻችን የሚቀበሉት እና በነርቫችን አማካኝነት የሚረዱት መልእክት የኒውሮትራንስሚተሮቻችን ስራ በማዛባት ነው ። ይህ መዛባት እየተከናወነ ያለውን ነገር ባለመረዳታችን ውስጥ ብዙ ነገር በእውኑ አለም እንድናጣ ያደርገናል ። ቅጠሉ መነሻው ደቡብ አሜሪካ ብራዚል ውስጥ ቢሆንም በአሁን ሰአት ግን ሂማሊያ ተራሮች እስከ ህንድ በቬትናም አድርግ እስከ ካሜሮን ማዳጋስካር ደርሶ ታንዛኒያ ኢትዮጲያ አሜሪካ ተመልሶ ሜክሲኮ አርጀንቲናና ቦሊቪያ ውስጥም ይገኛል ። ይህንን የወሰደ ሰው ከአንድ ሰዓት እስከ 48 ሰዓት ወይንም ለሁለት ቀን ከስሜቱ ላይላቀቅ የሚችል ሲሆን በሚከተሉት መንገዶችም አደጋውን መቀነስ ይቻላል ። እንደአደገኛ ሰው ቲሸርት አለመልበስ ወይንም ሙሉ እጅጌ ያለው አለባበስ ሰዎች በብዛት የሚሰበሰቡበት አካባቢ መጠቀም ። አእምሮአችን በቶሎ እንዳይበረዝ ነርቮቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰሩ የሚያደርጉ በVitamin B complex የበለፀጉ ምግቦች ፤ አሳ ፤ ጠቆር ያለ ቸኮሌት (ይህ የጎንዮሽ አደጋው ውፍረት እና የስኳር ህመምን ስለሚያመጣ በመጠኑ) መመገብ ፤ የአበባ ጎመን ፤ እንቁላል ፤ አቮካድ (ስጠላ ስልኬን ቢወስዱት ይሻለኛል ሃሃሃ...) ፤ የዱባ ፍሬ ( ዱባ ስወድ ደሞ🙄) ፤ እንዲሁም ለውዝ መመገብ የእፅዋቱ ማንኛውም ክፍሉ በአጋጣሚ ቢነካን እንኳ በቀላሉ እንዳይሰራ ሊያደርገው ስለሚችል መከላከል ይቻላል ። በስህተት የነካቹ ስልካቹን ከተዘረፋቹ በውሃላ ከፖሊስ ጣቢያ ይልቅ ወደ ጤና ጣቢያ ብትሄዱ አለበለዚያ ከሰአታቶች በውሃላ ከባድ ራስ ምታት ፤ ማቅለሽለሽ ፤ የአይን ብሌን መጥበብ ፤ ቅዠት ስለሚገጥማቹ ለሌላ አደጋ ነው የምትጋለጡት ። መልካም ቀን እኔ ደህና ነኝ ስልኬም አለ ላሳውቃችሁ በማሰብ ነው 😀 ═════════❁✿❁ ═════════
Show all...
✉️✉️✉️ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ✉️✉️✉️ አንድ ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡ በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ፡፡ በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነጋዴ የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ፡፡ በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም አስጠራው፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ‹ከተስማማነው ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ገበሬውም ‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡ ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ፡፡ ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሃለሁ› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡ ነጋዴው አፈረ፡፡ ‹የምታገኘው ለሌላው ባደረግከው ልክ ነው፡፡ 150 ሰጥተህ 300 ልታገኝ አትችልም፤ እባብ ሰጥተህ ርግብ፣ ድንጋይ ሰጥተህ ዳቦ፣ እሬት ሰጥተህ ማር ልታገኝ አትችልም፤ አንተ ብቻ ብልጥ ልትሆን አትችልም፤ ሻማውን አጥፍተህ ብርሃን ልታገኝ አትችልም፤ ሌላው ገድለህ አንተ በሰላም ልትኖር አትችልም› አለው ገበሬው፡፡
Show all...
አብን‼️ አብን በኦሮሚያ ክልል በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለመከላከል የክልሉ መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅና ፌደራል መንግሥቱም መከላከያ ሠራዊቱን እንዲያሠማራ መጠየቁን ዶይቸቨለ ዘግቧል። አብን ኦፌኮንና ኦነግን የአማራ ብሄር ተወላጆችን ግድያ በማባባስ የከሰሰ ሲሆን፣ ኦፌኮ ግን መልሶ አብንን ወንጅሏል። የአብን ከፍተኛ አመራር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ የክልሉ ልዩ ኃይልና ፖሊስ ጭምር በጥቃቱ ይሳተፋሉ ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በአካባቢው የአማራ ክልል ታጣቂዎች ይንቀሳቀሳሉ የሚባለው ሐሰት መሆኑን ቴዎድሮስ ተናግረዋል። የኦፌኮው አመራር ሙላት ገመቹ ግን፣ በአካባቢው የአማራ ብሄር ታጣቂዎች አሉ ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!