cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Follow Jesus

በዚ ቻናል ጌታ ብቻ ይወራል፣ይሰበካል፣ይመለካል "፤ ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። " (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4: 18) @onlygospel @kal1286 Our bot👉 @hiwetnflegabot 👈

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
208Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

。☆✼★━━━━━━━━━━━★✼☆。 #መንታ ሞት አለም ያለ አጥር የምታኖር ሰፊ ደሴት ናት ግን ነፃነት ብቻ ሳይሆን ያለው በነፃ ለሚወስደን መንታ ሞት ሃላፊነቱን እወስዳለን።ነፍስን አሲዞ ውስኪ ቢያወርዱ ምን ጥቅም። 。☆✼★━━━━━━━━━★✼☆。 Join us 👉@poem_4_Lord👈Join us 👉click here👈 。☆✼★━━━━━━━━━★✼☆。 ✍hosi
Show all...
🙏ግጥም🙏
🙏መዝሙር 🙏
🙏ትምህርቶች 🙏
🙏መጽሐፍት🙏
🙏ስለ ህይወት 🙏
🙏ስለ እየሱስ🙏
🙏መንፈስ ቅዱስ🙏
🙏ስብከቶች 🙏
🙏👉Join us👈🙏
🙏👉ይቀላቀላሉን👈🙏
Dont forget to share for ur christan friends and group......join the group also ....ሀሁ.....https://t.me/joinchat/AAAAAE61Qd5EaaUO-54iuA. ..nowwwwwww .....
Show all...
Hahu evangel

Christian dating and love stories አዝናኝ እና አስተማሪ For any info @teddym22

#የሚመጥን_ሀሳብ ማሰብ ከእ/ር የተካፈልነው አንድ ባህሪ ነው። ሃሳብን መርጦ መተግበር ደግሞ ሰው በራሱ ላይ የሚያመጣው በረከት ነው። ማንም #ለሆዱ የሚስማማውን ምግብ #እንደሚመርጠው ሁሉ ለአዕምሮውም #የሚመጥን_ሃሳብን መመገብ ራስን መጥቀም ነው። ንፁህ ምግብ ሰውን ከበሽታ እንደሚከላከለው ሁሉ ንጹህና መልካም ሀሳብ ሰይጣናዊ ተልዕኮ ካለው ተግባር ያቅበዋል። አንድ ሰው #ምርጥ_አሳቢ የሚባለው መልካም ሃሳቦችን #መርጦ ለሌሎች #አካፍሎ #ምርጥ አሳቢዎችን ለማፍራት #የሚተርፍና የሚጠቅም #አሳቢ ሲሆን ነው።ቃሉ ሁሉም ሰው በደረሰበት ይመላለስ ይላል ግን ያ ማለት #ያልደረስክበት ሀሳብ ሲነገርህ ፥ አይ እኔ #በደረስኩበት ነው #ምመላለሰው ብለህ #የማሰቢያህን በር እንዳትዘጋ። ዛሬ በደረስክበት #እውነት ስትመላለስ ፥ ያልደረስክበት #እውቀት ላይ #ነገ ለመድረስ #ዛሬ በአይምሮህ #እባብ(አስተዋይ) ፥ በልብህ #እርግብ(ቅን) መሆን አለብህ። ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...
#በትዕግስት_እንሩጥ 🏃🏃‍♀ ፨አብርሀም 👉 የ #100 አመት ሰው #በጉልበት ሳይሆን #በእምነት እንደወለደ.. #ቀይ ባህርን 👉 #355 ኪ.ሜ #በመርከብ ሳይሆን #በእግር እንደ ተሻገሩ.. #ኢያሪኮን 👉 ባለ #4 ሜትር ግንብ #በመድፍ ሳይሆን #በጩኸት እንደፈረሰ... #ዮርዳኖስን 👉 #3.2 ኪ.ሜ #በድልድይ ሳይሆን #በእግር እንዳቋረጡ.... #ጎልያድን 👉 #2.06 ሜትሩን ፣ #በጥይት ሳይሆን #በጠጠር እንደጣለው... #ዮናስ 👉 ለ #3 ቀን #አልጋ ላይ ሳይሆን #በአሳነባሪ ሆድ ውስጥ እንዳደረ #ውሀውን 👉 #3 እንስራ ውሀን ወደ ወይን #በኬሚስትሪ ሳይሆን #በቃል እንደለወጠ #ፊሊጶስ 👉 #37 ኪ.ሜ በ #አይሮፕላን ሳይሆን #በመንፈስ እንደ ተነጠቀ.... #ህመምተኛውን 👉 የ #1 ወር ቀጠሮ ሰጥቶ ሳይሆን ፣ #በሰከንድ እንደፈወሰ... #ከዳተኛውን 👉 በመውቀስ ፥ #በማማት ሳይሆን ፣ #በሹመት እንደተቀበለው... #ክርስቶስ 👉 #አለምን #በAk47 ሳይሆን #በፍቅር እንዳሸነፈ... ✍" እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ #ምስክሮች እንደ ደመና #በዙሪያችን ካሉልን፥.......... ... የእምነታችንንም #ራስና #ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ #በትዕግሥት እንሩጥ 🏃🏃‍♀🏃 (ወደ ዕብራውያን 12:1-2) ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...
#በስተመጨረሻ_ይዘነው_የምንሄደው_ምንድነው? ✳️ ጠቢቡ #ሰለሞን ሁሉን #አየ ሁሉን #አጣጣመ በስተመጨረሻ “ሁሉም ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ፤ ነፋስንም እንደመከተል ነው” ሲል #ኑሮን ደመደመ። እንደኔ ሁሉም ከንቱ ነው ሲል #ተስፋ ሊያስቆርጠን አይመስለኝም፤ ተስፋን #ሊሰጠን እንጂ። #ህይወታችን ከማንኛውም አለማዊ #ሃብት፤ ከማንኛውም #ዝና ከማንኛውም #ክብር #የላቀች መሆኗን #ሲነግረን ይመስለኛል። ይህንን #በቅጡ መረዳት #ስለሚሳነን፤ በስተመጨረሻ ይዘናቸው በማንሄዳቸው #አላፊ ነገሮችን ኑሮዋችንን #እንበጠብጣለን። ✳️ ኑሮ ማለት #በውልደት እና #በሞት መካከል ያለ #የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በጊዜ #ተጀምሮ በጊዜ #የሚቆም መሸጋገሪያ። #ጥቂቶች ይህንን የተረዱ ጊዜያቸውን #አጣጥመው ይኖራሉ። አብዛኛዎቻችን ግን ምድር ላይ ዘላለም እንደሚኖር ሰው #ተዘናግተን እንኖራለን። መልካም ነገር ለህሊናችንም ለእ/ርም ሚያስደስቱ ነገሮችን ሳናደርግባቸው #በተራ ነገር የሚያልፉ #ቀናቶች ከቆምንበት #ህንጻ ስር #እየተሸረፉ እንደሚወድቁ #ጡቦች ይቆጠራሉ። ቀስ እያሉ ከከፍታው የሚያወርዱን። ✳️ ሁሉም ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ ምክንያቱም ምንም ነገር #በሞት ፊት ቆሞ #ሞትን የሚጋፈጥ ነገር #ስለሌለ። ይህን #የተረዳ ሰው ትልቁን ቀንበር ከላዩ ላይ #አወረደ ማለት ነው። የሚያደርገውን ነገር ሁሉ #ከልቡ ያደርጋል ምክንያቱም #እድሉ አንደ ብቻ እንደሆነች #ስለሚረዳ። እውነት ከሞት ፊት ቆሞ #በቀልን የሚያስብ ማነው? ከመቃብሩ ላይ ቆሞ #ገንዘቡ የሚያሳሳው ማነው? በከፈን ውስጥ ሆኖ የሚጠላውን ሰው #የሚያስብ የሚቀና ማን ነው? በእርግጠኝነት ማንም። በሞት ፊት ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ። ✳️ በስተመጨረሻ ይዘነው የምንሄድ #ምንም ነገር #የለም።ይልቅ #የመሸጋገሪያ #ጊዜያችንን #መልካም #እናድርገው። የራሳችንን #አሻራ አኑረን፤ ነበሩ ለመባል ያብቃን። ሰለሞን ከንቱ ናቸው ያላቸው ነገሮች #ህይወታችንን የሚያጨልሙና የምድር #ቆይታችንን መራራ የሚያደርጉትን ነገሮች ነው። ህይወታችን #ክቡር ናት፤ ከማንኛውም ነገሮች ሁሉ የከበረች የፈጣሪ ስጦታ። በኪሳራ የማትቸረቸር። #ፍቅር የሌላት ህይወት፤ #እምነት የራቃት ህይወት፤ #ሰላም የጎደላት ህይወት፤ #ደስታ የሌለባት ህይወት ያለዋጋዋ #የተሸጠች ናት። ምክንያቱም በዚህ ምድር #የህይወታችንን_ዋጋ የሚስተካከል አለማዊ ነገር #ስለሌለ። " በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:23) 🔱 አንተ ፦እ/ር #በልጁ የገዛህ ፣ #የአለም ባሪያ እንዳትሆን ፣ለስጋ #ምኞት ተገዢ እንዳትሆን ፣ #ለተስፋ_መቁረጥ ተገዢ እንዳትሆን!! እሩቅ ከአድማስ ባሻገር #ሀገር አለህ ፣ #ተስፋ አለህ፤ ሰማያዊ #ዜግነት ያለህ ፣ በምድር የሰማይ #እንደራሴ ነህ! ፣ እ/ር #ርስትህ ነው ፣ ምድር ደግሞ #የኪራይ_ቤትህ ናት!!😏 ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...
#የክብር_ተስፋ ያለው #ክርስቶስ_በእኛ_ውስጥ ነው (ቆላስያስ 1:27) ✳️ በሁሉ #እንገፋለን እንጂ #አንጨነቅም፤ #እናመነታለን እንጂ #ተስፋ_አንቆርጥም ፤ #እንሰደዳለን እንጂ #አንጣልም፤ #እንወድቃለን እንጂ #አንጠፋም፤ (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡8-9) ✳️ #ተስፋ_መቁረጥ የህይወት #ፈተና ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ እንደ #ሙሴ አይነቶቹን #አገልጋዮች ፈትኗል፡፡ #ተስፋ_መቁረጥ እንደ #ኤልያስ ያሉትን ታላቅ #ነቢያት ተፈታትኗል፡፡ ✳️ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ለመተውና እጅ ለመስጠት የማይፈተን ሰው ካለ በህይወት የሌለ ሰው ብቻ ነው፡፡ ተስፋና የገሃዱ አለም ሁሌም በተቃራኒዉ ይገኛሉ። #ተስፋ በቀላሉ የሚገለፅ ነገር ባይሆንም ተስፋን ግለፅ ካለከኝ በቃ #ተስፋ ማለት ምርጥ #ቁርስ ነዉ ። #ተስፈኛ ስትሆን ደግሞ ብዙ #መሰናክል ይመጣል። #ህልም ያላቸው #ታሪኮች ህልም #የሌላቸውን ሰዎች #ያናድዳሉና። ታዲያ በዛን ግዜ #አቁም የሚል #ተስፋ_የሚያስቆርጥ ብዙ #ድምፅ ባለበት ሁኔታ ውስጥ #ተስፋ የማንቆርጥባቸው #ከአልጋችን ላይ መነሳት በማይሰማን ጊዜ ለጌታ እንደገና በሃይል ለመኖርና #በአዲስ ጉልበት ጌታን ለማገልገል #አስፈንጥሮ ከአልጋችን #የሚያስነሳን ዋና ምክንያት.. ✳️ ለምንም እጅ #የማንሰጠበት ምክንያት፦ በህይወታችን #የምንሰራው ነገር #በዘላለማዊ_እይታ ትርጕም ስላለው ነው፡፡#በህይወታችን የምንኖረው #ለምድራዊው ነገር ብቻ ቢሆን #ተስፋ_መቁረጥ ቀላል ነበር፡፡ ነገር ግን ከምድር ህይወት በኋላ ህይወት እንዳለ #በክርስቶስ ፍርድ ፊት #እንደምንቀርብ ስለምናውቅ #ተስፋ_መቁረጥ አይታሰብም፡፡ የምድር ኑሮ #አጭር እንደሆነ እና እኛ በህይወት #ከቆየን ክርስቶስ #ተመልሶ እንደሚመጣና #እንደሚወስድን ስለምናውቅ ተስፋ #እንቆርጥም፡፡ (1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ 3) ---------- 2፤ ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን። 3፤ በእርሱም ይህን #ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል። ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...
. | #ታውቀኛለህ| ዘማሪ ቃልአብ ጎአ @onlygospel @hiwetnflegabot
Show all...
✳️ እኔ የሚገርመኝ ፦ #እግዚአብሔር ኮሮና #የሚልክ ከሆነ : #እግዜር አምበጣ #የሚልክ ከሆነ ፣ #ጌታ በጎርፍ #የሚያጠፋ ከሆነ..... #ሰይጣን ምን #ሲሰራ ሊውል ነው???? #የሰይጣን ስራ #ምንድን ነው ታዲያ ?? ✳️ #በመጨረሻው ዘመን የተለያዩ #አስከፊ ነገሮች እንደሚመጡ #መፅሀፍ_ቅዱስ ይናገራል። ነገር ግን ያ ማለት #እ/ር ያመጣቸዋል ማለት ሳይሆን እርሱ ቀድሞ #በምድር ላይ ሊከሰት ያለውን አይቶ #እንጠነቀቅ ዘንድና ዘመኑ ሊያልቅ እንደሆነ በማወቅ #በመጠን_እንኖር ዘንድ #ፃፈልን ማለት ነው እንጂ #ሀላፊነቱን_ይወስዳል ማለት አይደለም! ወይም #ተጠያቂው እርሱ ነው ማለት አይደለም!!! ✳️ ይህን #የአዲሱን_ኪዳን ክፍል አንብበኸዋል?👇 (የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ 1) ---------- 13፤ ማንም ሲፈተን። በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። 14፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። 15፤ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች። 16፤ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። 17፤ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ። ✳️ ለክፋት ምንጭ ለሆነው ሰይጣን ሰዎች ፍቃዳቸውን በመስጠት #በምኞት ሲንገዋለሉ ምኞት ደግሞ #ሀጥያትን ፀንሳ ፥ ሀጥያት ደግሞ #ሞትን ወለደች ነው የሚለው መፅሀፉ!! ✳️ በመቀጠልም አትሳቱ ከላይ ከብርሀናት አባት የሚወርደው #ሞት ሳይሆን #በጎ_ስጦታ እና #ፍፁም_በረከት ነው የሚፈልቁት ይለናል!! አይ አይደለም ምድር በሀጥያት ተበላሽታለች ስለዚህ እየቀጣን ነው #ሊያስተምረን የምትሉ ደግሞ ልክ ካልሆነ አስተያየት ተቆጠቡ!! እ/ር ከ200,000 በላይ ሰው #ገድሎ #አንተን አያስተምርህም። መፅሀፍ ቅዱስ የሚለን፦ ✳️ #ጌታ አይዘገይም ይመጣል ነገር ግን ሁሉ #ንስሀ_ገብቶ #ይተርፍ ዘንድና ማንም #እንዳይጠፋ ወዶ ይታገሳል ይላል እንጂ አንተ እንዳልከው ሀጥያተኛውን #ይጨርሰዋል አይልም!! ሀጥያተኛውን ይቀጣ ዘንድ ከፈለገማ ያኔ ነበር #ሚጨርሰን ፥ #ልጁን ኢየሱስን መላክ አይጠበቅበትም ነበር!! ግን እርሱ እንደ #ሰው አይደለም #ሀጥያትን እንጂ #ሀጥያተኛን አይጠላም!!!! አሁንም #ይታገሳል!! የሁሉም ሰው #ዋጋ በእጁ ነው ያለው #በስተመጨረሻ ለሁላችንም ይከፍለናል። " ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን #ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም #እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።" (2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:9) 💫 ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...
✳️ #ወንድሜ/እህቴ ፥ ምንም ነገር ብታገኙ #የበቃኝ ኑሮ መኖር አይቻልም። #አለመርካት የሰው #ባህሪ ነውና። #የበቃኝ_ኑሮ የምትኖረው እግዚአብሔርን #ስታይ ብቻ ነው። ፊሊጶስ ያለው "አብን አሳየንና ይበቃናል " ነው (ዮሀ 14 ፣8 ) ። #እግዚአብሔርን ማየት ከመኖር በላይ #ህይወት ነው። #ከማግኘት በላይ #ሙላት ነው ። እርሱ የልባችን ጉጉት #ጥግ ነው። ከሀሳቦቻችን እጅግ #የላቀ ነው። የነፍሳችን #ወደብ ነው። መገኘቱ #እርካታችን ነው!! ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...
#እምነት_እኮ.... ✳️ #እምነት ከጊዜያዊ ፍላጎት #መሟላትና #መርካት ባሻገር የሆነ #አርቆ #የሚያይ ማንነትን ይፈልጋል። እግዚአብሔርን ይበልጥ #በቀረብን መጠን እግዚአብሔር #የእኛን_ፈቃድ እንዲያሟላ ከምንፈልገውና #ከምንጥረው በላይ እኛ #የእርሱን_ፈቃድ ማሟላት እርካታችን ይሆናል። ✳️ ውስጣዊ #ማንነቱ ላይ ማየትና ማስተካከል የሚገባውን ነገር መጋፈጥ #የማይፈልግ ሰው ከውስጡ #በመሸሽ በውጭ የሚስተጋባውን ብቻ ውስጡ ሳያስገባ “አሜን” በማለትና ሌሎች የሚሆኑትን #ለመምሰል በመጣር ብቻ #በጅምላ #ገደል ማሚታዊ ክርስቲያን ሊሆን ይዳዳዋል፤ ይህን መሰል ክርስቲያን በየትኛውም የክርስትና እምነት ውስጥ አይታጣም፤ የክርስቶስ ተከታይነት ግን እኛን በመላ ማንነታችን #የሚፈልገን ነውና #በሁለንተናችን ለእርሱ መገኘትን ይጠይቀናል። ✳️ ስለዚህም #እምነታችንን በሙሉ #ማንነታችን ለእግዚአብሔር #ክብር መኖር ካለብን በሙሉ ማንነታችን #በምድራዊ ፈቃዶች ሳንገደብ ወደ #ሰማይኛው ፈቃድ እንመልከት ፤ #ከማግለል አባዜ ወደ #ማገልገል፤ ከምድራዊው የቤት #ቁሳቁስ ማሟላት ጸሎት ወደ #ዘላለማዊው ቤት #ግንባታ እንበራታ፤ #ሆዳችንን መሙላት አግባብ ያለው ነገር ቢሆንም ከዚያም #ጠለቅ ወዳለው #የሕይወት_እንጀራ ወደ ሆነው ክርስቶስ እንሩጥ። ━━━━━⊱✿⊰━━━━━ 〽️ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ〽️ ♻️ @Hope_ministry ♻️ 🔱 Revealing the truth 🔱
Show all...