cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tigray Today ትግራይ ቱደይ

እዚ ናይ ትግራይ ቱደይ ዕላዊ ናይ ቴሌግራም ቻነል እዩ! ይህ የትግራይ ቱደይ ቻነል ነው! +251930314242 https://www.youtube.com/channel/UC2BZHeZULlpVm6aEnu_tpbA https://www.facebook.com/Tigraytoday24/

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
21 037Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከትላንት በስቲያ ከመቐለ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 25 ኪ.ሜ በምትገኝ እንደርታ ወረዳ ደብረናዝሬት ቀበሌ ተቶጋግ እዳጋ ሰሉስ በምትባል መንደር ለገበያ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች በነበሩበት ወቅት ተፈፅሟል የተባለውን የአየር ጥቃት መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል። ቶጎጋ እዳጋ ሰሉስ ላይ ተፈፅሟል በተባለው የአየር ድብደባ እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቀ ዜጎች ህይወት አልፏል፤ በርካቶችም ቁስለኛ ሆነዋል። የአይን እማኞች ድብደባው ማክሰኞ ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ለገበያ ተሰብስቦ በነበረ ህዝብ ላይ ነው የተፈፀመው ብለዋል። በድብደባው በሰዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በእንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል። የአይን እማኞቹ በቅድሚያ የተመታው ገበያው እንደሆነ በኃላም በቤቶች ላይ እንደነበር አስረድተዋል። ከቦታው ጉዳት ደርሶባቸው መቐለ አይደር ሆስፒታል የገቡት 5 ሰዎች ሲሆኑ ከእነሱ መካከል አንዷ የ2 ዓመት ከአራት ወር ህፃን ትገኛለች። ህፃኗ ከፍተኛ የሆኑ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን በአሁን ሰዓት መተንፈስ ስለማትችል የመተንፈሻ ቱቦ ተገጥሞላት ይገኛል። በሌላ በኩል የህፃኗ አባት ጉዳት ደርሶበት ወደ ህክምና እንዳይገባ በወታደሮች ተከልክሏል ተብሏል። አንድ የአይን እማኝ ደግሞ አጠገቡ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል። አህዮች ጨምሮ ብዙ እንስሶችም ሞተዋል ብሏል ፤ በአካባቢው ታጣቂዎች እንደነበሩ ተጠይቆ ምንም ታጣቂ አላየሁም ብሏል። ጉዳት የደረደባቸውን ሰዎች ለማምጣት የአምቡላንስ ሹፌሮች አምስት ጊዜ ተጉዘው አይቻልም ተብለው መመለሳቸውን ገልፀዋል።
Show all...
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው ተናገሩ፡፡ ዋና ጸሃፊው የትግራይ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡  የተጋረጠውን የረሃብ አደጋ ለመግታት ሰብአዊ እርዳታ ማዳረስ እንዲሁም በቂ ፈንድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ጸሃፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት አስታውቋል፡፡ "አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው"ም ነው ያሉት የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፡፡ የጉተሬዝ ትግራይን የተመለከተ መግለጫ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ያሉ የግጭቱ ተዋናዮች ተኩስ እንዲያቆሙና ያልተገደበ የስብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን አል ኣይን በድረገፁ አስነብቧል። የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ/ኦቻ/ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ከ1970ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ባለፈው ሳምንት አሳትውቋል።
Show all...
በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል። መግለጫው ሲጀምር "በ1984 እአአ በኢትዮጵያ በተራዘመ ድርቅ ሳቢያ በስፋት በተከሰተው የምግብ እጥረትና በመንግሥት አድላዊ ፖሊሲዎች የተነሳ የደረሰውን ከባድ ረሃብ በዚያም ምክንያት ብዙዎቹ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሰውነታቸው በረሃብ ያለቀ ፤ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የተሰደዱበትን የሚዘገንን ቸነፈር በደንብ አስታውሰዋለሁ" ቆይቶ ዝናብ መጣል ጀመረ። ስደተኞቹም ወደቀያቸው ተመለሱ። ይሁን እንጂ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሃገሪቱ በየጊዜው ግጭት እና የበቂ ምግብ ዕጦት ተለይቷት አያውቅም ሲሉም የዩናይትድ ስቴትሱ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል አክለዋል። ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዘግናኝ በሆነ ደረጃ ጭካኔ የተመላበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥቃት እየተፈጸመበት ነው ያሉት ሴኔተር ሌሂ ህዝቡ በአጣዳፊነት የሚያስፈልገው የምግብ እርዳታ እንዳይደርሰው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች እንዲሁም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች እየከለከሉ ናቸው" ብለዋል። “የአሜሪካ እና ሌሎችም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ግጭቱን አቁመው ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የወሰዱት አንዳችም ትርጉም ያለው እርምጃ የለም" ሲሉ አክለዋል። "ትግራይ ውስጥ የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ በግዴታ ከቀዬ ማፈናቀል፣ ወሲባዊ ጥቃቶች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በውሃ አቅርቦት ስፍራዎችና በሆስፒታሎችና በመሰል የጤና ማዕከሎች ላይ የሚደርሰውን ውድመት የአሜሪካ መንግሥት አውግዟል።
Show all...
#Shire የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መወሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል። የእርዳታ ሰራተኞቹና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል። ከእርዳታ ሠራተኞች መካከል አንዱ ፥ በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል ብለዋል። በአንዱ ካምፕ ውስጥ የሚኖር ክስተቱ በተፈፀመበት ወቅት የተደበቀ አንድ ግለሠብ ወታደሮች ሰብረው ገብተው ሰዎችን በዱላ መደብደባቸው ተናግሯል። ይኸው ስሙ በሚስጥር እንዲያዝ የጠየቀው ግለሰብ ፥ ወታደሮች በምሽት መጥተው ካምፑን በመክበብ ዋናውን በር በመስበር ያገኙትን ሁሉ በዱላ መደብደብ እንደጀመሩ ገልጾ በወቅቱ የ70 ዓመት አዛውንት መደብደባቸውን እና አንድ አይነስውር አፍነው መውሰዳቸውን ተናግሯል። እሱ ካለበት ፀሃዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ 400 ሰዎች መወሰዳቸውን አስረድቷል። የመከላከያ ቃል አቀባይ፣ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡበት መልዕክት ቢቀመጥላቸውም ምላሽ አልሰጡም ብሏል ሮይተርስ። የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ ኃላፊ ቴዎድሮስ አረጋይ ፥ ጥቂት መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ክሱን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሮፖጋንዳ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።
Show all...
ሰሞኑን በሐውዜን ወረዳና በተለይ ደግሞ በገርዓልታ ተራሮች ዙርያ ውግያ መካሄዱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከሚያዝያ 25/2013 ጀምሮ በሶስት ግንባሮች ውጊያ መካሄዱን ነዋሪዎች ገልፀዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሚያዝያ 29 2013 ዓ.ም ላይ ሐውዜን በከባድ መሳርያ ድብደባ ተፈጽሞባታል። በከተማዋ በ02 ቀበሌ የሚገኘው፤ የአቶ ብሩ በላይ መኖርያ ቤት ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ ነው። "ከባድ መሳርያ ከመውደቁ በፊት በከተማዋ ምንም አይነት ነገር አልነበረም። በመጋብና ድጉም አቅጣጫ ግን ከርቀት የውግያ ድምጽ ይሰማ ነበር። ቤቱ ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ሲደርስ በርከት ያሉ ሴቶች ነበሩ። በተለይ በአንድ ክፍል ደግሞ የጎረቤት ልጆችን ጨምሮ ሰባት ህጻናት ነበሩ" ብላለች ከአደጋው የተረፈችው ግደይ።
Show all...
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ • ከC2 99 ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ ወደግቢ አልሄዱም። • ከC1 ወደ 60 ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ ወደግቢ አልሄዱም። ከዚህ ቀደም ደግመን ደጋግመን በሰላም ጉዳይ በሰራንባቸው ወቅቶች እንደገለፅነው የአንድ ቦታ ሰላም እጦት ጉዳቱ ለዛ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ለሌላውም የሚተርፍ ነው። ሰላም ማጣት እዛው ያለውን ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላውን ሰላም ወዳድ ዜጋ የሚጎዳ ነው። በተለይም ጦርነት በቦታው ላይ ያሉ እናቶች፣ህፃናት፣ ሴቶች፣ ተማሪዎች በእጅጉ ይጎዳል። በትግራይ ያየነውም ይኸው ነው። በተለይ የተማሪዎች ጉዳይ አሳስቢ ነው። አንድም እዛው ትግራይ ያሉ እና በሌሎች ቦታዎች መማር ያለባቸው በሌላ በኩል ወደትግራይ ሄደው የሚማሩ ተማሪዎች የሚደርስባቸው ተፅእኖ ቀላል አይደለም። ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሜዲስን ተማሪዎች የቲክቫህ አባልት ከሰሞኑን ወደዓዲግራት ሄደው ለመማር እንደሚቸገሩ ገልፀውልናል። ዓዲግራት ተማሪዎቹን እንዲገቡ የጠራው ያለፈው ሚያዚያ 5 እስከ ሚያዚያ 7 ሲሆን የሜዲስን ተማሪዎች የኛ ጉዳይ ይለያል መፍትሄም ይፈልጋል ብለዋል። ዓዲግራት በጦርነቱ ምክንያት ያላት የጤና ተቋሟ ከተጎዱባት የትግራይ ከተሞች አንዷ ናት። በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ በቀራቸው ጊዜ በቂ የሆነ እና አስፈላጊውን ጥራት በጠበቀ መልኩ የጤና ትምህርታቸውን ተከታትለው ለመጨረስ እንደሚያስቸግራቸው ገልፀዋል። የዓዲግራት ሆስፒታል ተኝነተው የሚታከሙ ህምምተኞችን እስተናገደ እንዳልሆነ መረጃው እንዳላቸው ገልፀው የእነሱ ትምህርት ደግሞ በቀጥታ ከዚህ ጋር የሚገናኝ መሆኑን ነው ያነሱት።
Show all...
Show all...
Ryn Weaver - Pierre (Lyrics) | BABEL

Ryn Weaver - Pierre Lyrics BABELPierre by Ryn Weaver lyric videoSubscribe to BABEL here: http://bit.ly/babelchannelCheck out YUNGBLUD's new song:

https://bit...

#Adwa (ሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2013 ዓ/ም) • "...በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን በሚል ነው ጥቃት የፈፀሙት፤ ...አንድ ሰው ሞቷል" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም • "...በተኩሱ 8 ሰዎች ሞተዋል" - የአድዋ ነዋሪዎች • "...ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም" - የአድዋ ነዋሪ • "...2 የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ 3 ጊዜ ተኮሱብኝ" - የጥቃቱ ሰለባ • "...ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" - የጤና ባለሞያ • "... ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል መጥተው እርዳታ እንደተደረገላቸው ነው ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል" - MSF ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-04-14
Show all...
BBC

በአድዋ የኤርትራ ወታደሮች ተኩስ ከፍተው የሰው ህይወት ማጥፋታቸው ተገልጿል : ሚያዚያ 4 (ሰኞ) ረፋድ ላይ የኤርትራ ወታደሮች የከፈቱት ተኩስ ነዋሪዎችን ገድሏል ፤ ቁስለኛ አድርጓል። በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ፥ ተኩሱ በኤርትራ ወታደሮች መከፈቱን አሳውቆ ፥ ቢያንስ አንድ ሰው ሞቷል ብሏል። ነዋሪዎች ግን በተኩሱ 8 ሰዎች መሞታቸውን ነው የተናግሩት። የአክሱም ሆስፒታል ዶክተር ከትናንት ረፋድ ጀምሮ እስከ ከሰዓት በኋላ ድረስ 20 የቆሰሉ ሰዎች ከአድዋ እንደመጡ ተናግሯል። ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር (MSF) ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ከአድዋ ሆስፒታል እንዳመጣቸው የሚናገረው ይህ ዶክተር "2 ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" ብሏል። MSF ትናንት በትዊተር እንደገለጸው ፥ ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው…

ሰላም ኣብ መላእ ዓለም ዘለኹም ተጋሩ፡ ኣብ ግንባር ኣላማጣ #ዓወት ተመዝጊቡ ኣሎ። ክልተ ክፍለ-ሰራዊት ፀላኢ ምስ ሙሉእ ሓይሊ መካናይዝዱ፡ ተደምሲሱ ኣሎ። --- ኩሎም ሓይልታት ፀላእቲ ተኣኻኺቦም፡ ናይ #UAE ሓገዝ እዉን ወሲኾም፡ ይዋግኡና ኣለዉ። ይኹን እምበር፡ ኣብ ልዕሊ ሓይልታት ፀላኢ ነብፅሖ ዘለና #ክሳራታት ዘርዚርካ ዝዉዳእ ኣይኮነን። ሒዞምዎ ዝኣተዉ፡ #ሽሾ ሰራዊቶም ንሕምሽሾን ንበታትኖን ኣለና። ዝበፅሖም ዘሎ ክሳራታት ፈፂምካ ዘይመጣጠን እዩ። እቲ ኩነታት፡ ናይ ሓደ ትግራዋይ ክቡር መስዋእቲ vs ኣሽሓት ሞት ፀላእቲ እዩ ዘሎ። ትግራይ ሕዚ ኾነ ንቀፃሊ፡ ንፀላእቲ #ረመፅ እያ። ዝካየድ ዘሎ ኲናት እናከበደ ይኸይድ ኣሎ። ብኡ ልክዕ፡ ናይ ትግራይ ናይ ምምካት ዓቅምና እዉን፡ ብዝግባእ እናተጠናኸረ ይኸይድ ኣሎ። ካብ መጥቃዕቲና ዝተረፉ ሓይልታት ፀላእቲ፡ ኣብ ዝተፈላለዩ ዝወረሩዎም ከተማታትና፡ ኣብ ልዕሊ ንፁህ ህዝብና ናይ ምብስባስ ስራሕቲ ሰሪሖም እዮም። ኣራዊታዊ #ግፍዒታት ዉን ፈፂሞም እዮም። ኣብ ልዕሊ #ትግርኛ ተዛረብቲ፡ ናይ #ዘርኢ_ምፅናት ተግባራት ሞኪሮም እዮም። እንተኾነ እዚ ኲናት ምእንተ #ህላወናን_መንነትናን ንገብሮ ቃልሲ ስለዝኾነ፡ እዞም ግፍዒታት የሐርኑና እምበር ኣየምበርክኹናን። ምእንተ መንነትና፡ ኩሎም ዓይነት መስዋእቲታት ከፊልና ክንዕወት ኢና። ትግራይ ከምትዕወት ከይትጠራጠሩ!! ዓወት ንህዝቢ ትግራይ፡ ሞት ንፀላእቲ ትግራይ!! @tigraytoday24
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!