cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Coffee Bahir Dar

#በ1968_ተመሰረተ 👆 #ስለምንወደው_ክለባችን_ኢትዮጵያ_ቡና_መረጃዎችን_የምናገኝበት_ምርጥ_ቻናል_ነው 👆 http://t.me/coffeebahirdar

Show more
Advertising posts
328Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#የ12ኛ_ሳምንት_የኢትዮጵያ_ፕሪሚየር_ሊግ_ተስተካካይ_ጨዋታ ⚽ ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና 🗓 ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም 🕚 9:00 ሰዓት 🏟 በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም * ትኬት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ መሸጥ ይጀምራል። * የስታዲየም በሮች በተመሳሳይ ከ6:00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታሉ። * የክቡር ትሪቡን በር በተዘጋጁ ልዩ ባጆች ብቻ የሚገባበት ሲሆን ጥላ ፎቅ 200 ብር ፣ ከማን አንሼ 100 ብር ፣ ካታንጋ 50 ብር እንዲሁም ሚስማር ተራ እና ዳፍ መግቢያ  ዋጋ 20 ብር ነው። * ከስታዲየም ግቢ ውጭ ሁለት የዩንቨርሲቲው መግቢያ በሮች ለሁለቱም ክለቦች የተዘጋጁ ሲሆን ነፃ ከአልኮል ነፃ ማልት መጠጥ ከስታዲየም ውጪ ይቀርባል። * በእለቱ የኢትዮጵያ ቡና ማሊያ እና ቁሳቁሶች በዩኒቨርስቲ ስታዲየሙ ዙሪያ ለሽያጭ ይቀርባሉ።
Show all...
⚽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከፊታችን ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም በተስተካካይ ጨዋታዎች ይጀምራል። 🏟 የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታውን ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በማድረግ ይጀምራል። ✴ ከትኬት ሽያጭ እና ከጨዋታው ጋር የሚወጡ መረጃዎች እንደደረሱን የምናሳውቅ ይሆናል። @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...
🇪🇹ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዱ ይቀጥላል። 👉የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለቻን ላለበት ውድድር ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ከፊታችን ጥር 20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መካሄዱ ይቀጥላል። 👉በወጣው መርሃ ግብር መሰረት የ11ኛ ሳምንቱ ተስተካካይ ጨዋታ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ቅዳሜ ጥር 20 2015 ዓ.ም በ9፡00 ሰዓት ሲካሄድ ከ14ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች ከጥር 23 እስከ መጋቢት 03/2015 ዓ.ም ከሐሙስ እስከ እሁድ ባሉ ቀናት በ9 እና 12 ሰዓት ይካሄዳሉ። ➡️ፕሮግራሙም በምስሉ ላይ አያይዘነዋል! @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...
👉በዋልያዎቹ የቻን ተሳትፎ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበትን ቀን የውድድሩ የበላይ አካል ለክለቦች አሳውቋል። ✅በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የበላይነት የሚደረገው የሀገሪቱ ከፍተኛው የሊግ እርከን ውድድር ታኅሣሥ 16 ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ዝግጅት እና ውድድር መቋረጡ ይታወሳል። ብሔራዊ ቡድናችንም በውድድሩ ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን አድርጎ በአንድ ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ የመጨረሻ የምድብ ፍልሚያውን አከናውኖ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ እና አለማለፉን ይለያል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊጉ የበላይ አካል በዛሬው ዕለት ሊጉ የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ማከናወን የሚጀምርበትን ቀን ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። 🔻በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ተሳትፎውን ካገባደደ ከአምስት ቀናት በኋላ ሊጉ ጨዋታዎችን ማከናወን እንደሚጀምር ተጠቁሟል። ከ14ኛ ሳምንት ጀምሮ የሚደረጉት ጨዋታዎች ደግሞ በአዳማ ሳይንስ እና ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እንደሚከናወኑ ተገልጿል። ➡️የቀጣይ ሳምንታት መርሐ-ግብሮች ይፋ ባይሆኑም በአዳማ የሚደረጉት ጨዋታዎች በቀን ሁለት ጊዜ ዘጠኝ እና አስራ ሁለት ሰዓት ሊከወኑ እንደታሰበ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። Via Soccer Eth @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...
#የኢትዮጵይ_ቡና_ዋናው_ቡድን_ልምምዱን_ጀመረ ⚽ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ልምምዱን ለቡ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቡና የተጫዋቾች መኖሪያ ካምኘ አድርጎ ከባለፈው ማክሰኞ 26/04/2015 ዓ.ም ልምምዱን እያደረገ ይገኛል፡፡ 🎯 ለዕረፍት ወደ ሀገራቸው ከሄዱት ኩዋኩ ዱሀ፣ ሕዝቄል ሞራክ እና ሮቤል ተ/ሚካኤል እንዲሁም ለብሔራዊ ቡድን ከተመረጡት በረከት አማረ እና ገዛኽኝ ደሳለኝ ውጪ ሁሉም በልምምዱ ስፍራው ተገኝተዋል፡፡ 👉 ጉዳት ላይ ያሉ ተጫዋቾች የክለባችን አንደኛ እና ሁለተኛ አምበል የሆኑት አማኑኤል ዮሐንስ እና አስራት ቶንጆ እንዲሁም ወንድሜነህ ደረጀ አሁንም ወደ ልምምድ ያልተመለሱ ሲሆን የመሀል አማካኝ ተጫዋች #ሬድዋን_ናስር ከጉዳቱ አገግሞ መጠነኛ ልምምድ ከቡድኑ ጋር ማድረግ ጀምሯል፡፡ @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...
#በጣም_ያሳዝናል #የኢትዮጵያ_ቡና አባት #ጋሽ_ጫንያለው_ተኮላ  ነፍሶትን ፈጣሪ ይማርልን። #ለክለባችን የዋሉትን ውለታ #መቼም አንረሳውም። #ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው #መፅናናትን ፈጣሪ ይስጥ። @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...
በጉዳዩ ዙሪያ የተጠየቁት የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ግን ” በውላችን መሠረት አሰናብተነዋል። ውሉ ከጨዋታው 75 በመቶ ድል ማሳካት አለበለዚያ ከ1-3 መውጣት ከሚለው አንዱን ካላሳካ የማሰናበት መብት አለን ለዚህም ነው ያሰናበትነው” ሲሉ ገልጸዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ እንደተናገሩት “በውሉ መሠረት ከሁለቱ ተዋዋዮች አንዱ ውል ማቋረጥ ከፈለገ ከአንድ ወር በፊት አሳውቆ ውሉን ማቋረጥ ይችላል ይላል እኛም በውላችን መሠረት ከታህሳስ 30/2015 ጀምሮ ውላችንን አቋርጠናል ብለን ነግረነዋል ደመወዙን ይከፈለዋል ቡድኑ ጋር መሄድ ግን አይችልም” በማለት የክለቡን አቋም አሳውቀዋል። ኢትዮጵያ ቡና በሀድያ ሆሳዕና የደረሰበት የ1ለ0 ሽንፈት የአሰልጣኙን ስንብት ያረጋገጠ ሲሆን በያዘው 14 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ከአዳማ ከተማ ጋር አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው ከመሪዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ መድን በ8 ነጥብ አንሶ መገኘቱ አመራሮቹን ያበሳጨ ይመስላል። @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...
ተሰናባቹ የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ክለቡ ያቀረበለትን በስምምነት እንለያይ ጥያቄ ውድቅ አደረገ። ከደቂቃዎች በፊት አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እንደተናገረው” ከኢትዮጵያ ቡና የቀረበልኝ በስምምነት የመለያየት ጥያቄን ብቀበለውም የስምምነቱ ይዘት ላይ ጥያቄ በማንሳት የስንብት ደብዳቤውን ሳልቀበል ወጥቻለሁ ውሉ ላይ ከመጀመሪያ ዙር 30 ጨዋታ 75 በመቶ ወይም ከ1-3 ማሳካት ይላል በ15ቱ ጨዋታ ላይ ባላሳካም ከ1-3 የሚለውን አሳካለሁ ብልም አልተቀበሉኝም እኔም በስምምነት የሚለውን ጥቅማ ጥቅሜና ደመወዜ ላይ ያለውን ባለመቀበሌ የሰጡኝን ደብዳቤ ሳልወስድ ወጥቻለሁ” ብሏል። አሰልጣኙ እንዳለው ” በውል መቋረጡ ላይ ፍቃደኛ ነኝ ነገር ግን በውሌ መሠረት ያለኝ ክፍያና ጥቅማ ጥቅም ዙሪያ ላይ ከጠበቃዬ ጋር ተነጋግሬ አሳውቃለሁ” ብሏል። አሰልጣኙ ግን ደብዳቤውን ተቀብሎ ምላሽ መስጠት እየቻለ አልቀበልም ማለቱ ለሌላ ውዝግብ በር እንዳይከፍት ስጋት ፈጥሯል።
Show all...
#ሰበር ዜና ⚠️በመጨረሻም ኢትዮጵያ ቡና ውጤታማ አልሆነም በሚል አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ከክለባችን ጋር ተለያይተዋል። ✅አሰልጣኝ ተመስገን ዳና ቡድኑን ውጤታማ እንደሚያደርግ ቃል ቢገባም የተመዘገበው ውጤት በዝውውሩ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ቡና አመራሮችን ያስደሰተ አልሆነም። በዘንድሮ የውድድር አመት ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በአራቱ አሸንፎ በተመሳሳይ በአራቱ ተሸንፎ ሁለት ጨዋታ ብቻ አቻ የወጣው አሰልጣኙ በተለይ በሀድያ ሆሳዕና 1ለ0 መሸነፉ ለስንብቱ ትልቁን ሚና መጫወቱ ተገልጿል። ምንጭ፦ሀትሪክ ስፖርት @COFFEEBAHIRDAR @COFFEEBAHIRDAR
Show all...