cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKH-VAH ethiopa

Promoting & post news

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
8 043Subscribers
No data24 hours
-27 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#Update የዓለም ጤና ድርጅት በዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ቅሬታ እና ክስ ቢቀርብም በጦርነት ለተጎዳው የትግራይ ክልል ህዝብ እርዳታ መጠየቁን እንደሚቀጥል አስታውቋል። ባለፈው ዓርብ የኢትዮጵያ መንግስት ዶክተር ቴድሮስ ጎጂ እንዲሁም የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት እና TPLFን በመደገፍ የተሳሳተ ተግባር ላይ መሳተፋቸውን በመግለፅ ከሶ ድርጅቱ ምርመራ እንዲያከናውን መጠየቁ ይታወሳል። ዛሬ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ክስ ማቅረቡን አረጋግጧል። ድርጅቱ ግን 7 ሚሊዮን ለሚደርሰው የትግራይ ክልል ህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈቅድ መጠየቁን እንደሚቀጥል አሳውቋል። ባለፈው ዓርብ ዕለት የኢትዮጵያ መንግስት ቅሬታውን ያቀረበው ባለፈው ሳምንት ዶ/ር ቴድሮስ መንግስት ወደትግራይ ክልል መድሃኒትና የነፍስ አድን እርዳታዎች እንዳይገባ እየከለከለ ነው በማለት በክልሉ ያለው ሁኔታ ሲኦል ነው ብለው ከገለፁ በኃላ ነው። መንግስት ፥ ዶ/ር ቴድሮስ የሰጡት አሰተያየት የዓለም የጤና ድርጅትን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚጥል ፤ የተጣለባቸውን ህጋዊ እና ሞያዊ ኃላፊነት ጥሰው በመገኘታቸው ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር። በተመድ የኢትዮጵያ ልዑክም ዶ/ር ቴድሮስ የፖለቲካ ውግንና እንዳላቸው በመግለፅ ኢትዮጵያን ከሚመለከቱ ጉዳዮች እራሳቸው እዲያርቁ ጠይቆ እንደነበር የፈረሳይ ዜና አገልግሎትን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ዶ/ር ቴድሮስ ከሰጡት አስተያየት ጋር በተያያዘ የአማራ እና አፋር ክልል ባለስልጣናት ጠንካራ ትችት ሰንዝረው ዶ/ር ቴድሮስ የተናገሩት ለህወሓት ፕሮፖጋንዳ መሆኑንና በአፋር እና አማራ ክልል ህወሓት ስላደረሰው ጥፋት ተናግረው እንደማያውቁ መግለፃቸው አይዘነጋም። @tikvahethiopia
Show all...
#ነፃ_ዋይፋይ ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ፣ እንጦጦ ፣ አንድነት ፓርክ እና የወዳጅነት አደባባዮች በከፍተኛ ወጪ የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት ገንብቶ በነጻ ማቅረቡን ዛሬ ገልጿል። @tikvahethiopia
Show all...
#Update የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር መሀመድ ሁሴን ሮቤል በሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ መሀመድ ኢብራሂም ሙአሊሙ ላይ ያነጣጠረውን አሰቃቂ ያሉትን የሽብር ጥቃት አወገዙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽብር ጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ቃል አቀባዩ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ጠ/ሚ መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ፥ ለመሀመድ ኢብራሂም ሙአሊሙ ፈጣን ማገገምን ተመኝተዋል። እስካሁን ለአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም። @tikvahethiopia
Show all...
#GERD🇪🇹 አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዚህ ሳምንት በሰጡት መግለጫ ከተናገሩት ፦ (ከሪፖርተር) " ... የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኤሌክተሪክ ማመንጨት የሚጀምርበትን ቀን ይህ ነው ብሎ መነገር ባይቻልም፣ በጣም በቅርብ ጊዜ ይጀምራል። የግድቡ ጉዳይ ሊለወጥ የማይችልና ያለቀ ነገር በመሆኑ፣ የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ከዚህ ካለቀ ጉዳይ ጋር አብረው መቆም አለባቸው። ከዚህ በኋላ ግድቡ ሲያመነጭ ለግብፆችም ሆነ ለሱዳኖች ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ ፣ በሚመነጨው ኃይል ሌሎችም አገሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እነዚህ አገሮች ቢሠሩ መልካም ነው። ነገር ግን የሦስትዮሽ ድርድሩ ይቁም ማለት አይደለም። ሱዳን እና ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከጀመራቸሁ ችግር ይፈጠራል፣ ሰማዩ ይገለባበጣል የሚሉት ነገር አዲስ አይደለም፡፡ ቀድሞውንም ሙሌት ከጀመራችሁ አደጋ ይፈጠራል፣ ጉድ ይፈላል ሲሉ ነበር ይህ ፉከራ የተለመደ ቢሆንም አሁን ግን ያረጀና ጊዜው ያለፈበት ሆኗል። በህዳሴ ግድቡ ውኃው ተርባይኑን አንቀሳቅሶ አልፎ ስለሚሄድ መጠኑ ስለማይቀንስ፣ ሱዳኖች የግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ሊያስደስታቸው እና ሊያከብሩት ይገባል። " @tikvahethiopia
Show all...
የአዲስ አበባ ድጋፍ ፦ አዲስ አበባ ከተማ ዛሬ እና ትላንት ለሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን በድምሩ የ150 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ አድርጋለች። ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር የአይነት ድጋፍ ተደርጓል። በመጀመርያ ዙር 51 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በሁለት ዙር በአጠቃላይ 101 ሚሊዮን ብር የሚሆን ድጋፍ ማድረስ ተችሏል። ትላንት ደግሞ በሶማሌ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ100 ሚሊዮን ብር የምግብ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል። ምንጭ፦ የአ/አ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ @tikvahethiopia
Show all...
" በአፋር በኩል ጦርነቱ አልቆመም "- አፋር ክልል የአፋር ክልል መንግስት ፥ ህወሓት በሰላም ወዳዱ የአፋር ህዝብ ላይ በድጋሚ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ማቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል። ክልሉ ፥ " አሸባሪው ህወሓት በኪልበቲ ረሱ / ዞን ሁለት / በአብአላ በኩል ከታህሳስ 10/2014 ጀምሮ በከፈተው አዲስ ግንባር በተከታታይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ ንፁሀን ዜጎችን መጨፍጨፉን ቀጥሏል" ብሏል። አክሎ ፥ "የትግራይን ህዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር ለማናከስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ህወሀት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነው በዚሁ አካባቢ የትግራይን ህዝብ ከጎረቤቱ ጋር በማናከስ፣ ጉርብትና እንዲሻክርና ጎረቤቶችን በማጣላት የራሳቸውን እድሜ ለማራዘም አፋር እና ትግራይ ጎረቤት ህዝቦችን እያናከሰ ይገኛል" ሲል አሳውቋል። ክልሉ፥ "ጎረቤታሞች በሰላም ውሎ እንዳያድር ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው" የሚለው የአፋር ክልል" የትግራይ ህዝብም ይሄንን የጀንታውን እብደት ሊቃወም ይገባል፤ በቃቹህ ሊሉ ይገባል" ሲል አስገንዝቧል። ቡድኑ በንፁሀን የአፋር ህዝብ ላይ በተለይም በኪልበቲ ረሲ ዞን አብአላና መጋሌ በኩል የከፈተውን በጥብቅ ሊያወግዝ ይባልም ብሏል። የአፋር ክልሉ መንግስት " ህወሓት በከባድ መሳሪያ ንፁሀንን የመግደል የመጨፍጨፍ ተግባሩን አሁንም አላቆመም፣በአፋር በኩል ጦርነቱ አልቆመም፣ ንፁሀን ሴት፣ ህፃናት እና አዛውንት አሁንም ሰለባ እየሆኑ ነው" ብሏል። የዓለም ህብረተሰብ የህወሓትን ድርጊት እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል። ህወሓት ፥ በሚቆጣጠረው የትግራይ ቲቪ በኩል ባወጣው መግለጫ የአፋር ልዩ ኃይል በህዝባችን ላይ ተከታታይ ግፎችና ጭፍጨፋዎች እየፈፀመ ሰንብቷል ሲል ከሷል። ያንብቡ : telegra.ph/Afar-Tigray-01-16 @tikvahethiopia
Show all...
ተወዳጁ የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያ የቤተሰብ ድግስ አዘጋጅቷል። ዝግጅቱ እሁድ ጥር 15, 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ጀምሮ ጦር ኃይሎች በሚገኘው በጎልፍ ክለብ ነው። ዝግጅቱ የልጆቻችን አእምሮ ዘና የሚልበት - በጨዋታ እየቦረቁ ቁምነገር የሚቀስሙበት ነው። መግቢያ ትኬት ለ1 ልጅ 300 ብር ሲሆን ለመጫዎቻዎች ምንም ክፍያ አይጠየቁም። ልጆቹን ይዞ የሚመጣ አንድ ወላጅ መግቢያ በነፃ። ትኬቱን በሁሉም የፍሬሽ ኮርነር ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 0970454545 በአቅራቢያዎ ለማግኘት ይደውሉ። የኢትዮጵያ ልጆች ሚዲያን ይከታተሉ - በኢትዮ ሳት - Frequency:- 11605, Polarization: horizontal, Symbol rate :- 45000 https://t.me/yeethiopialijochmedia
Show all...
#ውበት ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0911607446 ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!               ሙሉ ከወገብ በላይ (ቦዲ) - 950ብር የቦርጭ ብቻ (ጉርድ) -650  ብር ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ። ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ⏩ @wibet1 ( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ ቤዛ ህንፃ 2nd floor # webet
Show all...
#Update የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ተጠናቆ ለበዓል አከባበር ሥርዓቱ ዝግጁ ሆነ። ከአንድ ወር በፊት የግንባታ ሥራው የተጀመረው የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ መጠናቀቁና ለጥምቀት በዓል ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል። በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሥራ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል የባህረ ጥምቀቱን ገንዳ በአዲስና ዘመናዊ መንገድ የመገንባት ፣ የኤሌክትሪክና የውኃ መስመር ዝርጋታ ሥራዎች እንዲሁም ቅጽረ ጊቢውን የማስዋብና ቡራኬ ማከናወኛ ስፍራዎችን የማስጌጥ ሥራዎች ተከናውነዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጸበል መርጫ መስመሮች የተገጠሙ ሲሆን ብቃት ያላቸው የውኃ መሳቢያ ሞተሮች ገጠማም ተከናውኖ ዝግጁ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራም ተከናውኗል። በአጠቃላይ የዘንድሮን የጥምቀት በዓልን በጥሩ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሉ የግንባታሥራዎች፣ የታቦታት ማረፊይያ ቦታዎች፣ የክብር እኝግዶች የሚስተናገዱባቸው ስቴጆችና የድምጽ ማጉያ መስመር ዝርጋታዎች ተከናውኗል። ቀሪ የግንባታ ሥራዎችና ይዞታውን የማስከበር ተግባራትም በዓሉ ከተከበረ በኋላ ተጠናክረው መቀጠል ይችሉ ዘንድ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል። ቪድዮ : 25 MB (Wi-Fi ተጠቀሙ) @tikvahethiopia
Show all...
#AU ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች ተስማምተው የኅብረቱ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዲደረግ በመወሰናቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል። የኅብረቱን ጉባኤ በአካል በአዲስ አበባ ለማከናወን ያሳለፉትን ውሳኔ ኢትዮጵያ ታደንቃለች ብለዋል። ዶ/ር ዐቢይ ፥ " ወንድማዊ አጋርነታችሁን በምንሻበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የኮሮናን መስፋፋትንና ወቅታዊውን የጸጥታ ሁኔታ እንደ ምክንያት በማንሣት የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ አካላት ተግባራቸው ኢትዮጵያን አሳዝኖ ነበር " ብለዋል። አክለው ፥ " በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚደረጉት የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤያት መካከል በኮሮና ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የመጀመሪያው ጉባኤ ከ3 ዓመት በኋላ ዳግም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራትና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ጋር በመሆን መንግስት ልዩ ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። " ሲሉ አስረድተዋል። ዶክተር ዐቢይ፥ " ጉባኤው እዚህ መካሄዱ የሚኖረውን ትርጉም የተገነዘቡና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን ጠንካራ አቋም፣ ለአፍሪካ ኅብረት እውን መሆን ያበረከተችውን አስተዋጽኦ እና የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካውያን እንዲታዩ ያላትን የጸና መርሕ ከፍ ያለ ዋጋ የሰጡ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤው በአዲስ አበባ መካሄዱን መርጠዋል። በዚህም ኢትዮጵያ ደስ ተሰኝታለች፤ እንኳን ደስ ያለን " ሲሉ ገልፀዋል። * ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
Show all...