cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳሰሳ አዲስ-Access Addis

በዳሰሳ አዲስ ኅትመት እና ማስታወቂያ ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ኮንሰርት፣ የተለያዩ ኪነ-ጥበብ ቱርፋቶች፣ የታዋቂ ሰዎች ግለ ታሪክ እንዲሁም በወር አንዴ ጊዜ "ዙር ሰላሳ" የተሰኝች በመዝናኛው ዘርፍ ላይ ብቻ አትኩሮቷን ያደረገች ዲጂታል መፅሔት ተዘጋጅቶ ይቀርባል! ለማንኛውም አስተያየት 👇 [email protected] +251924312097 @InfoDasesaBot

Show more
Advertising posts
9 287Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
የ9ተኛው ዙር የጉማ ሽልማት ጋዜጣዊ መግለጫ በ2014 አ.ም በሀገራችን ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ለእይታ የቀረቡ ፊልሞች ውስጥ 22 ፊልሞች ለውድድር ቀርበዋል። በተጨማሪም ከጉማ ጅማሬ አንስቶ በተለያዩ ሙያተኞች ሲጠየቅ የነበረው የተከታታይ ፊልም ምድብ እና የዘጋቢ ፊልሞችን በዚህ አመት እንዲካተቱ ተደርጔል። በዚህ አሞት ዘርፎቹ ወደ 29 አካባቢ ከፍ ያሉ ሲሆን የጉማ የህይወት ዘን ተሸላሜ ዘርፍ ፤የጉማ የሄርሜላ የሴቶች ሽልማት ተሸላሚ፤ የጉማ የበጎ ስራ ተሸላሚ ብቻ ያለውድድር በኮሚቴው ጥናትና ምርጭ ይወሰናሉ፡፡ #gummaawards #accessaddis #AddisAbeba #BedeleSpecial #heninkin #skylight
Show all...
የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል ! (ይትባረክ ዋለልኝ) በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ እንደሚወጣ ሰዋሰው መልቲሚድያ አስታውቋል፡፡ በያዝነው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ የተዋወቀው እና ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻዊያንን በጋራ ለመስራት ያስፈረመው ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ፤ አስር የሙዚቃ ስራዎችን ያካተተው የድምጻዊቷ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበምን የጥምቀት ዋዜማ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል፡፡ ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም ድምጻዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር ስትፈራረም የሰዋሰው የማኔጅመንት አባላት ድምጻዊ አስቴር አወቀ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት ሃያ አራት የሚደርሱ ዘመን አይሽሬ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው፡፡ ድምጻዊቷ ከሃገር ውስጥም በተጨማሪ በታላላቅ ዓለማቀፍ መድረኮች ስራዎቿን በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆትን በማግኘት ኢትዮጵያዊቷ የሶል ሙዚቃ ንግስት በመባልም ትታወቃለች፡፡ ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጥበበኞች የሚገባቸውን የፈጠራ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ የሃገራችን ጥበብ ባህር ማዶ ተሸጋሪ እንዲሆን ለማስቻል በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡
Show all...
ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ ስለታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)... "እስከ መች ኢንተርቪው እንቢ ትላለህ ? አንተ እኮ በዚህኛው ዘመን ላለው የሀገራችን ፊልም ቀለም ከሆኑ ወጣት አርቲስቶች አንዱ ነህ ፡ በጣም ብዙ አድናቂዎችህ ፡ ያንተን ፈለግ መከተል የሚፈልጉ ወጣቶች ስላንተ ማወቅ መስማት ይፈልጋሉ አዱ ግድ የለህም ይለፈኝ በዚህ ጉዳይ ከሰይፉም ጋር ተጨቃጭቀናል እኔ ሚዲያ ላይ መቅረብ ብዙም አልወድም ፡ ፊቴ መቀያየሩን ሲያይ አዱ ተክልዬን ከደበረ ኢንተርቪውን ዝም በለን እንስራው እና አንድ ቀን ደስ ካለኝ አሁን አስተላልፈው እልሃለው ለኔ ስትል ከሆነ አሁን ይቅርና ደስ ያለ ቀን ኢንተርቪው ትሰጠኛለህ አልኩት እንቢ ሲለኝ ደብሮኝ ነበር ቀርፀን እናስቀምጠው ያለኝን እሺ ባለማለቴ ደግሞ የበለጠ እንድከፋ አድርጎኛል
Show all...
ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ። ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምተና ሲል ዘግቧል:: ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል:: *** ዳሰሳ አዲስ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል።
Show all...
ነብስህ በሰላም ትረፍ
Show all...
እግዚአብሔር ይመስገን::
Show all...
​​​ለዛ ሽልማት በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ በሂልተን ሆቴል ይካየዳል። በሂልተን ሆቴል የሚደረገው 10ኛው የለዛ ሽልማት በ 12 የተለያዩ የሽልማት ዘርፎች እጭዎችን አወዳድሮ ይሸልማል። የመጨረሻ እጩዎች ምርጫ Lezashow.com ላይ በመግባት ይምረጡ @AccessAddis
Show all...
8ተኛው ጉማ አዋርድ አሸናፊዎች 👉 የህይወት ዘመን ተሸላሚ፦ ፕሮፌሰር ሰሌማ መኩሪያ 👉 የተማሪዎች አጭር ፊልም፦ መባ አብርሃም ከበረ 👉 ምርጥ አጭር ፊልም፦ አይቀር አሸናፊ መስፍን 👉 ምርጥ ዶክመንተሪ ፊልም፦ የውበት ሻማ ፍቃዱ ከምባታ ተከታታይ ድራማ ዘርፍ #️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ፅሁፍ፦ ቤዛ፣ አዜብ እና ቅድስት እረኛዬ #️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይት፦ ሳያት ደምሴ በእረኛዬ #️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይ፦ ብርሀኑ ድጋፌ የእግር እሳት #️⃣ ምርጥ ሲትኮም፦ 9ኛው ሺ ወንድምአገኝ ለማ #️⃣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ዳይሬክተር፦ አብርሃም ገዛኸኝ የእግር እሳት ምርጥ ድራማ፦ እረኛዬ በፊልሞች 1️⃣ ምርጥ ድምፅ፦ አብርሃም ዳንኤል በከርቤ 2️⃣ ምርጥ ኤዲተር፦ ዳንኤል ግርማ በምን አለሽ 3️⃣ ምርጥ ስኮር፦ ጆርካ መስፍን በምን አለሽ 4️⃣ ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ እሱባለው ይታየሁ የፍቅር ጥግ 5️⃣ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ዳንኤል ግርማ በስንብት 6️⃣ ምርጥ ሜኬአፕ፦ ዳግማዊ አለማየሁ በምን አለሽ 7️⃣ ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ አንተነህ ሀይሌ ስንብት 8️⃣ ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ ህፃን መቅደላዊት አስተርይ በየፍቅር ጥግ 9️⃣ ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ ህፃን ሳሙኤል ወንድይፍራው በስንብት 🔟 ምርጥ ረ/ተዋናይት፦ እታፈራሁ መብራቴ በማንያዘዋል 1️⃣1️⃣ ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ ሽመልስ አበራ በየፍቅር ጥግ 1️⃣2️⃣ ምርጥ ተዋናይት፦ አምልሰት ሙጬ በምን አለሽ 1️⃣3️⃣ ምርጥ ተዋናይ፧ እንግዳሰው ሀብቴ (ቴዲ) በግዛት 1️⃣4️⃣ የተመልካች ምርጫ (በደሌ እስፔሻል)፦ የፍቅር ጥግ 1️⃣5️⃣ ምርጥ ዳይሬክተር፦ ኑር አክመል በማን ያዘዋል 1️⃣6️⃣ ምርጥ ፊልም፦ ማን ያዘዋል
Show all...
ትላንት ምሽት ለ8ኛ ጊዜ ጉማ የፊልም ሽልማት በስካይ ላይት ሆቴል የተካየደ ሲሆን ሽልማት አሸናፊ ፊልሞች ዝርዝር የህይወት ዘመን ተሸላሚ ፕሮፌሰር ሰሌማ መኩሪያ፣ የተማሪዎች አጭር ፊልም መባ አብርሃም ከበረ፣ ምርጥ አጭር ፊልም አይቀር አሸናፊ መስፍን፣ ምርጥ ዶክመንተሪ ፊልም የውበት ሻማ ፍቃዱ ከምባታ፣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ፅሁፍ፦ ቤዛ፣ አዜብ እና ቅድስት እረኛዬ፣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይት ሳያት ደምሴ በእረኛዬ፣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ተዋናይ ብርሀኑ ድጋፌ የእግር እሳት፣ ምርጥ ሲትኮም፦ 9ኛው ሺ ወንድምአገኝ ለማ፣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ ዳይሬክተር አብርሃም ገዛኸኝ የእግር እሳት፣ ምርጥ ተከታታይ ድራማ እረኛዬ፣ ምርጥ ድምፅአብርሃም ዳንኤል በከርቤ፣ ምርጥ ኤዲተር ዳንኤል ግርማ በምን አለሽ፣ ምርጥ ስኮር ጆርካ መስፍን በምን አለሽ፣ ምርጥ ማጀቢያ ሙዚቃ፦ እሱባለው ይታየሁ የፍቅር ጥግ፣ ምርጥ ሲኒማቶግራፈር፦ ዳንኤል ግርማ በስንብት፣ ምርጥ ሜኬአፕ፦ ዳግማዊ አለማየሁ በምን አለሽ፣ ምርጥ የፊልም ፅሁፍ፦ አንተነህ ሀይሌ ስንብት፣ ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት፦ ህፃን መቅደላዊት አስተርይ በየፍቅር ጥግ፣ ተስፋ የተጣለበት ተዋናይ፦ ህፃን ሳሙኤል ወንድይፍራው በስንብት፣ ምርጥ ረ/ተዋናይት፦ እታፈራሁ መብራቴ በማንያዘዋል፣ ምርጥ ረ/ተዋናይ፦ ሽመልስ አበራ በየፍቅር ጥግ፣ ምርጥ ተዋናይት፦ አምልሰት ሙጬ በቲቪ ድራማ እራኛዬ 3ት በማሸነፍ በልጦል 2ት በማሸነፍ ደሞ የእግር እሳት አለ በፊልም ደሞ 4 አዋርድ በመውሰድ ምን አለሽ እና የፍቅር ጥግ ከፊት ናቸው፣ ማንያዘዋል እና ስንብት ደሞ 3ት በመውሰድ ይከተላሉ ከርቤ እና ግዛት ፊልም ደሞ አንድ አንድ አዋርድ ወስደዋል።
Show all...
ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ (ዶክሌ) ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሜድስታር ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ግንቦት 11, 2014 በተወለደ በ57 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ዶክሌ ላለፋት ሁለት አስርተ አመታት በኮሜዲው ዘርፍ አዝናኝ፣ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። ዶክሌ ሀገራችን ካፈራቻቸው ብርቅዬና ግንባር ቀደም ኮሜዲያኖች ውስጥ አንዱ ሲሆን ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር። የኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸመው በትውልድ ሀገሩ ኢትዩጵያ ስለሆነ ለዚህም ማስፈጸሚያ የሚሆን እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይህ የጎፈንድሚ አካውንት ተከፍቷል።
Show all...
ለ ለዛ ሽልማት ለመጨረሻው ዙር በ10ሩም ዘርፎች የተመረጡት ዕጩዎች ታውቀዋል :: እባክዎ www.lezashow.com በመግባት ዕጩዎቹን ይመልከቱ ድምፅዎን ይስጡ:: መልዕክቱን ያጋሩ ::
Show all...
ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮችን ለመሳተፍ የሀገሬ ቴቪን ቻናል ይቀላቀሉ። ቻናሉን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ።
Show all...
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለሰሙነ ሕማማት አደረሳችሁ።
Show all...
የለዛ ሽልማት ድምፅ መስጠት ተጀመረ ::
Show all...
መልዕክት ለዛ ሽልማት አዘጋጆች የተከበራችሁ የኪነጥበብ ቤተሰቦች እንዴት ከረማችሁ አምላክ ፈቅዶ ዘንድሮ በለዛ የሽልማት ስነ ስርዓት ልንገናኝ ነው። ዘንድሮም ታላላቆችን በስራቸው እናከብራለን። በዚህ ዓመት የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምጻዊ ምድብን ከዚህ ዓመት ሽልማት ጀምሮ በታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ፣ዜማ ና ግጥም ደራሲ የኤልያስ መልካ መታሰቢያ ሽልማት እንዲሆን ወስነናል። እናም የሽልማቱ ዘርፍ በለዛ ሽልማት ላይ ሲጠራ ፦ የኤልያስ መልካ ሽልማት ፦ የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ ፦ ተብሎ ይጠራል ማለት ነው። ኤሊያስ መልካ የአገራችንን ምርጥ አዳዲስ ድምፃውያንን በማበቃቱ ሂደት ድርሻው የገዘፈ ነውና ለውሳኔያችን ገዢው ምክንያት ይሄው ነው። የመጀመሪያ አልበማቸውን እሡ ሰርቶላቸው ፈልጎ አግኝቷቸው ቀርጾ አውጥቷቸው የየራሳቸው ሙዚቃዊ ማንነት አላብሶ በስራቸው አንቱ ያስባላቸው ክብሩን ያወቁታልና የሃሳባችን ተጋሪዎች ናቸው ብለን እና ስባለን። እናንተስ የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች ? ውሣኔያችንን እንዴት አግኝታችሁት ይሆን ? ለማናቸውም ድምፆችሁን ለምትወዱት የኪነጥበብ ስራና ጥበበኛ www.lezashow.com በመግባት vote የሚለውን በመጫን ድምፆችሁን ሰጡ የኪነጥበብ ቤተሰብን አበርቱ :: ድምፅ መስጠት ሠኞ መጋቢት 12 ይጀመራል :: የለዛ ሽልማት
Show all...
በቅርቡ 10ኛው የለዛ ሽልማት ...
Show all...
ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አርማሽ(ቀናበል) የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቋል @AccessAddis
Show all...
ድምፃዊ ቴድሮስ ካሳሁን አዲስ ነጠላ ዜማ ለህዝብ ሊያደርስ ነው። ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አርማሽ(ቀናበል) የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ በነገው ዕለት ለህዝብ ሊያደርስ መሆኑን በይፋዊ ማህበራዊ ገፁ አሳውቋል። @AccessAddis
Show all...
አርቲስት ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን አስታወቀች አርቲስቷ ከ219 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ቬሪፋይድ የሆነዉ የፌስቡክ ገጿ መጠለፉን በኢንስታግራም አካዉንቷ ባሰፈረችዉ ጽሁፍ አስታዉቃለች። “የፌስቡክ ገጼ መጠለፉን ሳሳዉቃቹ እያዘንኩ ነዉ። ይህን ጉዳይ ለመፍታት እየሰራን እንገኛለን። ከተጠለፈዉ ፌስቡክ ገጼም ሆነ ትክክለኛ ካልሆኑ (unofficial) አካዉንቶች የሚተላለፉ መልዕክቶች የኔ አይደሉም” ብላለች። የአርቲስቷ ፌስቡክ ገጽ ፕሮፋይል ምስል ከአስር ቀናት በፊት መቀየሩንና ከዛ ወዲህም የተለያዩ መልዕክቶች በገጹ ላይ መለጠፋቸዉን ተመልክተናል። @AccessAddis
Show all...
ቴዲ አፍሮ ለ 'ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር' ኮንሰርት አዘጋጁን አስር ሚሊየን ብር እንዲከፍለው ክስ አቀረበ የቴዲ አፍሮ ክስ የካቲት 14 2012 ዓ.ም "ኢትዮጽያ ወደ ፍቅር" የተሰኘ ኮንሰርት አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል። በመስቀል አደባባይ የተዘጋጀውን ይህን ኮንሰርት ካዘጋጀው ከላየን ኢቨንትስ ጋር የሙዚቃ ኮንሰርቱን ላቀረብኩበት አስር ሚሊዮን ሊከፍለኝ የፅሁፍ ውል ስላደረግን ይክፈለኝ የሚል ነው ያቀረበው ክስ። @AccessAddis
Show all...
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ Maal Mallisaa አልበም ለ2022 የግራሚ ሽልማት እጩ ሆኖ ቀርቧል! የቢልቦርድ መፅሄት በዛሬው እትሙ "የአለም ምርጥ የሙዚቃ አልበም- Best Global Music Album" በሚባለው ምድብ ለ2022 የግራሚ ሽልማት የአርቲስቱን አልበም በእጩነት አቅርቧል። መፅሄቱ በአለም ዙርያ ላሉ የግራሚ ሽልማት ድምፅ ሰጪዎች የሚሰራጭ ሲሆን በዚህ እትም ላይ ከወጡ ሌሎች አርቲስቶች መሀል ድሬክ፣ ቢሊ ኤሊሽ፣ ሊል ናስ ወዘተ ይገኙበታል Via:- Eliyas Mesert @AccessAddis
Show all...
የምትወጂውን ነገር ሳትሰስቺ ስለሰጠሽን፤ የላቀ ክብር እና ምስጋና ይገባሻል። 🙏 ባለ ቅኔዋ ድምፃዊት እጅጋየው ሽባባው (ጂጂ) መልካም ልደት! 🎂🍾 @AccessAddis
Show all...
"ከክሊፑ ቀረፃ ቀን በኋላ ያሬድ ነጉን አግኝቼው አላውቅም" ሚለን ኃይሉ ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ስለ ድምጻዊት ሚለን ሀይሉ ትላንት በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ያሰፈረውን መልዕክት ለእናት ማቅረባችን ይታወሳል። ድምፃዊት ሚለን ዛሬ ከታዲያስ አዲስ ሰይፍ ጋር በነበራት ቆይታ ይህን ብላለች "ያሬድ ነጉን ከክሊፑ ቀረፃ በኋላ አግኝቼው አላውቅም ለምን እንደዛ ብሎ እንደለቀቀም ለመጠየቅ እና ማስተካክያ እንዲያደርግ በሶስቱም ስልክ ሲደወል ስልኩ ዝግ ነው፣ መኖሪያ ቤቱም ሄደን ነበር ቤት የለም።" በማለት ተናግራለች። @AccessAddis
Show all...
ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ከድምፃዊት ሚለን ኃይሉ ጋር ... "አንዳንዴ ነፍስ ማረፊያዋን አታውቅም? እኔ ከሚለን ጋር በዚህ ደረጃ እቀራረባለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም:: እውነታው ግን እንደሚታየው ነው:: በአንቺ ውስጥ የማላውቀው እኔን አግኝቻለሁ ፣በአንቺ ውስጥ ምግባርሽን ፣ባህልሽን፣ ፍቅርሽን፣ አስተሳሰብሽን ተካፍያለሁ ስለሁሉም አመሰግንሻለሁ :: ሲል ድምፃዊት ያሬድ ሃሳቡን በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ሀሳቡን አስፍሯል።
Show all...
አንጋፋው እና ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ጎዳና ወጣ። በርካታ ዘመን አይሽሬ ስራዎችን ያበረከተው ድምፃዊ ቴዎድሮስ በዋሽግተን በሚኖርበት ጊዜ ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች ተደብድቦ ጉዳት እንደረሰበት እና ህክምና ተደርጎለት ወደ ቀድሞ ጤንነቱ ቢመለስም ከባለቤቱ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ጉዳዩ ከሽምግልና አቅም በላይ በመሆኑ ባለቤቱ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዳው ነበር፣ ፍርድ ቤትም ቴዲ ሚስቱ እና ልጁ ጋር እንዳይደርስ ወስኗል ይላል ኢትዮጵካሊንክ። ከዚህ በፊትም ጥሩ ያልነበረው የቴዲ ጤንነት አሁን ተባባሰ ይላል የኢትዮፒካሊንክ ዘገና። አሁን በቅርቡ ከዲሲ ለቆ ሄዶ በኒውዮርክ ጎዳናዎች ላይ በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሆነ ታይቷል ተብሏል። @AccessAddis
Show all...
ድምፃዊ ዮሀና ሁለተኛ አልበሙን መልቀቁ አሳወቅ። በሬጌ ስልት በማቀንቀን እና በመጀመሪያ አልበሙ ተወዳጅነት ያተረፈው ዮሀና ዕረፍት የተሰኝውን ሁለተኛ አልበም በራሱ የዩቲዩብ ቻናል መልቀቁን ነው የገለፀው። @AccessAddis
Show all...
ታላቁ የሙዚቃ ሰው ጥላሁን ገሠሠ በሕይወት ቢኖር ኖሮ ዛሬ 80 ዓመት የልደት በዓሉ ነበር። ጥላሁን ለአራት አስርት ዓመታት በዘለቀ የሙያ ሕይወቱ የተጫወታቸው ዜማዎች የየዘመኑ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶች ማኅደር ለመሆን በቅተዋል። ጥላሁን በረጅሙ የድምፃዊነት ሕይወቱ፣ በቁጥር ብዙ ዘፈኖች ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ርዕሰ ጉዳዮችም ላይ ዘፍኗል። በሕይወት ዘመኑ የዘፈናቸውን ዘፈኖች ትክክለኛ ቁጥር ደፍሮ ለመናገር ያስቸግራል። @AccessAddis
Show all...
ጁሊያን ማርሊ በጥቅምት ወር ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ነው። እውቁ የሬጌ ንጉስ የቦብ ማርሊ ልጅ የሆነውን ጁሊያን ማርሊ በአይዞን ፋውንዴሽን ግብዣ በአዲስ አበባ የራሱንና የአባቱን የሙዚቃ ሥራዎች ሊያቀርብ ነው። የሙዚቃ ዝግጅቱ በጥበብ እና መዝናኛ አማካኝነት ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ፤ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሰዎችን በአንድ ላይ ለማሰባሰብ እና በአለምአቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ለመገንባት ያለመ ነው። እንዲሁም የጥቁር ሕዝቦች ባህልን እና ሙዚቃን አጉልቶ በሚያሳየው ጥበብ ውስጥ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ያላትን ስፍራ ለማሳየት ያለመ ነው። በአይዞን ፋውንዴሽን የተዘጋጀው ይህ የሙዚቃ ዝግጅት በጥቅምት 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጊዮን ሆቴል ይደረጋል ተብሏል፡፡ @accessaddis
Show all...
Show all...
ሮፍናን 3 አዳዲስ ስራዎችን አወጣ። ድምፃዊው ከረጅም ጊዜ በኃላ በሀገር ጉዳይ ላይ ትክረትን ያደረገ 3 መልክት አዘል ስራዎችን ለቋል። ሮፊ ሦሥት የተሰኝ 3 የተለያዩ አዳዲስ ስራዎችን በራሱ ዩትዩብ ቻናል ለቋል። @AccessAddis
Show all...
እንኳን ለ1442ኛዉ የኢድ አል ፊጥር በአል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!🌙 #ኢድ_ሙባረክ❤️ @AccessAddis
Show all...
የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ለሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መልካም የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ። ዳሰሳ አዲስ ኅትመትና ማስታወቂያ @AccessAddis
Show all...
ምርጦቹን ያሰባሰበው የሙዚቃ ቪዲዮ ተለቋል. ኩኩ ሰብስቤ - ፍቅራአዲስ ነቃጥበብ- ዘሪቱ ከበደ- ሳያት ደምሴ-ራሄል ጌቱ - ጌታቸው ሃ/ማሪያም- ልጅ ሚካኤል-አስጌ ዴንደሾው እና ኤፍሬም አስራት ሙዚቃው ተጫውተዉታል። https://youtu.be/mvu4U2xomXI
Show all...
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! @AccessAddis
Show all...
ኮከቦቹን ያሰባሰበው ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል ኩኩ ሰብስቤ፣ ፍቅራአዲስ ነቃጥበብ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሳያት ደምሴ፣ ራሄል ጌቱ፣ ጌታቸው ሃ/ማሪያም፣ ልጅ ሚካኤል፣ አስጌ ዴንነሾው፣ ኤፍሬም አስራት በጥረታቸው ከፍ ብለው የታዩ ሴቶችን የሚያወድሰው ሙዚቃው ፣ በሀገር ሰላም ፣ ፍቅር እና አንድነት ፣ በሀገር ከፍ ብሎ መታየት ላይ ሁሉ የሴቶች ሚና ትልቅ መሆኑን ያነሳል። ቅንብሩን ሚካኤል ሐይሉ (ሚኪ ጃኖ) ዜማ ምህረታብ ደስታ ተጨማሪ ዜማ ዘሪቱ ከበደ ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸዉ እና ፍርድያዉቃል ንጉሴ ፅፈውታል። በUN WOMEN እና ሎሚ ሚዲያ ፕሮዱዩስ የተደረገው ሙዚቃው ዛሬ ከሰዓት የሚለቀቅ ሲሆን የሙዚቃ ቪዲዮ ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ሮዕብ ይለቀቃል ተብሏል። @AcceesAddis
Show all...
በ50 ዓመቱ ኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት ህይወቱ የተቀጠፈው ታዋቂው የኢትዮጵያ የጥበብ አርቲስት መስፍን ጌታቸውን የቀብር ስነ ስርዓት ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ የስራ አጋሮቹ፣ ጓደኞቹ በተገኙበት ትላንት በቅድስት ስላሴ ካቴድትል ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። እስክንድር ላቀው የአርቲስት መስፍን ጓደኛ ሲሆን መስፍን በታመመበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ገልፆታል፥ "የነበረው ጉጉት ድኖ ለመነሳት ነበር፥ ይህ ጊዜ አልፎ ብዙ ነገር ሰራለሁ የሚል ህልም ነበረው ድንገት ግን ተለይቶናል። አሁን የሚያሳዝነኝ እንደቀላል ነበር ነገሮችን ያያቸው ደግሞ የነበረበት ሁኔታ ጥሩ ነበር በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ብዙ ርብርብ ተደርጎለታል ፤ አለ የሚባለው ጥረት ሁሉ ተደርጎለታል ፤ እንደፈጣሪ ሆነና መስፍን ሄደ እንጂ እንደ ተደረገው ጥረት ቢሆን መስፍን አይሞትም" ነበር። ሌላኛው የአርቲስት መስፍን ጌታቸው ጓደኛ አበበ ፈለቀ ፥"...ይሄ ምስክር ነው ጓደኛችንን ከ15 ቀን በፊት አውርቼዋለሁ ደህንና ነበረ ፤ አሞኝ ገባሁ እያለ ነው ገብቶ ሳይወጣ የቀረው። አንድ ሰው ጠንካራ ነኝ ፣ ወጣት ነኝ ፣ አይዘኝም ፣ እንደዚህ ነው የምበላው ሽንኩርት ነው፣ ቃሪያ ነው የምበላው ማለት አይሰራም፤ በሽታው የምር ነው ፤ የምናውቃቸው ከአጠገባችን ያሉ ሰዎችን እየነጠቀን ነው ፤ ስለዚህ ሁሉም ሰው ለራሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለዘመድ ለጓደኞቹ ሲል እራሱን መጠበቅ አለበት" ብሏል። በዘመን ፣ በሰው ለሰው ፣ በሌሎችም የጥበብ ስራዎች የሚታወቀው አርቲስት መስፍን ጌታቸውን ባለትዳር እና የ2 ሴቶች እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር። @AccessAddis
Show all...
መስፍን ላለፉት ሁለት ወራት በኮቪድ ተይዞ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል የነበረ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ወዲህ በፅኑ ህሙማን ክፍል ገብቶ ነበር። አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር። አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር። አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል። አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር። ዳሰሳ አዲስ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል! @AccessAddis
Show all...
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲቀርቡ የነበሩት ድራማዎች ደራሲና ዳይሬክተር የነበረው መስፍን ጌታቸው ዛሬ ማምሻዉን ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፤ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል! @AccessAddis
Show all...