Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
The best auto-posting service

Do you want the same buttons under the posts?

Channel location and language
በዳሰሳ አዲስ ኅትመት እና ማስታወቂያ ፊልም፣ ሙዚቃ፣ ኮንሰርት፣ የተለያዩ ኪነ-ጥበብ ቱርፋቶች፣ የታዋቂ ሰዎች ግለ ታሪክ እንዲሁም በወር አንዴ ጊዜ "ዙር ሰላሳ" የተሰኝች በመዝናኛው ዘርፍ ላይ ብቻ አትኩሮቷን ያደረገች ዲጂታል መፅሔት ተዘጋጅቶ ይቀርባል! ለማንኛውም አስተያየት 👇 [email protected] +251924312097  @InfoDasesaBot  
Show more
17 286-20
~5 799
~0
33.54%
Telegram general rating
Globally
95 463place
of 3 394 467
182place
of 902
In category
112place
of 535

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Subscribers count
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

III @AccessAddis

ROPHNAN III SOST.mp3

9 305
151
ሮፍናን 3 አዳዲስ ስራዎችን አወጣ። ድምፃዊው ከረጅም ጊዜ በኃላ በሀገር ጉዳይ ላይ ትክረትን ያደረገ 3 መልክት አዘል ስራዎችን ለቋል። ሮፊ ሦሥት የተሰኝ 3 የተለያዩ አዳዲስ ስራዎችን በራሱ ዩትዩብ ቻናል ለቋል። @AccessAddis
5 316
9
እንኳን ለ1442ኛዉ የኢድ አል ፊጥር በአል በሰላም አደረሰን! አደረሳችሁ!🌙 #ኢድ_ሙባረክ❤️ @AccessAddis
5 987
3
የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ለሆናችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መልካም የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ። ዳሰሳ አዲስ ኅትመትና ማስታወቂያ @AccessAddis
1
0
ምርጦቹን ያሰባሰበው የሙዚቃ ቪዲዮ ተለቋል. ኩኩ ሰብስቤ - ፍቅራአዲስ ነቃጥበብ- ዘሪቱ ከበደ- ሳያት ደምሴ-ራሄል ጌቱ - ጌታቸው ሃ/ማሪያም- ልጅ ሚካኤል-አስጌ ዴንደሾው እና ኤፍሬም አስራት ሙዚቃው ተጫውተዉታል። https://youtu.be/mvu4U2xomXI
7 493
13
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! @AccessAddis
7 950
5
ኮከቦቹን ያሰባሰበው ሙዚቃ ዛሬ ይለቀቃል ኩኩ ሰብስቤ፣ ፍቅራአዲስ ነቃጥበብ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሳያት ደምሴ፣ ራሄል ጌቱ፣ ጌታቸው ሃ/ማሪያም፣ ልጅ ሚካኤል፣ አስጌ ዴንነሾው፣ ኤፍሬም አስራት በጥረታቸው ከፍ ብለው የታዩ ሴቶችን የሚያወድሰው ሙዚቃው ፣ በሀገር ሰላም ፣ ፍቅር እና አንድነት ፣ በሀገር ከፍ ብሎ መታየት ላይ ሁሉ የሴቶች ሚና ትልቅ መሆኑን ያነሳል። ቅንብሩን ሚካኤል ሐይሉ (ሚኪ ጃኖ) ዜማ ምህረታብ ደስታ ተጨማሪ ዜማ ዘሪቱ ከበደ ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸዉ እና ፍርድያዉቃል ንጉሴ ፅፈውታል። በUN WOMEN እና ሎሚ ሚዲያ ፕሮዱዩስ የተደረገው ሙዚቃው ዛሬ ከሰዓት የሚለቀቅ ሲሆን የሙዚቃ ቪዲዮ ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ሮዕብ ይለቀቃል ተብሏል። @AcceesAddis
7 546
13
በ50 ዓመቱ ኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት ህይወቱ የተቀጠፈው ታዋቂው የኢትዮጵያ የጥበብ አርቲስት መስፍን ጌታቸውን የቀብር ስነ ስርዓት ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ የስራ አጋሮቹ፣ ጓደኞቹ በተገኙበት ትላንት በቅድስት ስላሴ ካቴድትል ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። እስክንድር ላቀው የአርቲስት መስፍን ጓደኛ ሲሆን መስፍን በታመመበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ገልፆታል፥ "የነበረው ጉጉት ድኖ ለመነሳት ነበር፥ ይህ ጊዜ አልፎ ብዙ ነገር ሰራለሁ የሚል ህልም ነበረው ድንገት ግን ተለይቶናል። አሁን የሚያሳዝነኝ እንደቀላል ነበር ነገሮችን ያያቸው ደግሞ የነበረበት ሁኔታ ጥሩ ነበር በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ብዙ ርብርብ ተደርጎለታል ፤ አለ የሚባለው ጥረት ሁሉ ተደርጎለታል ፤ እንደፈጣሪ ሆነና መስፍን ሄደ እንጂ እንደ ተደረገው ጥረት ቢሆን መስፍን አይሞትም" ነበር። ሌላኛው የአርቲስት መስፍን ጌታቸው ጓደኛ አበበ ፈለቀ ፥"...ይሄ ምስክር ነው ጓደኛችንን ከ15 ቀን በፊት አውርቼዋለሁ ደህንና ነበረ ፤ አሞኝ ገባሁ እያለ ነው ገብቶ ሳይወጣ የቀረው። አንድ ሰው ጠንካራ ነኝ ፣ ወጣት ነኝ ፣ አይዘኝም ፣ እንደዚህ ነው የምበላው ሽንኩርት ነው፣ ቃሪያ ነው የምበላው ማለት አይሰራም፤ በሽታው የምር ነው ፤ የምናውቃቸው ከአጠገባችን ያሉ ሰዎችን እየነጠቀን ነው ፤ ስለዚህ ሁሉም ሰው ለራሱ፣ ለቤተሰቡ፣ ለዘመድ ለጓደኞቹ ሲል እራሱን መጠበቅ አለበት" ብሏል። በዘመን ፣ በሰው ለሰው ፣ በሌሎችም የጥበብ ስራዎች የሚታወቀው አርቲስት መስፍን ጌታቸውን ባለትዳር እና የ2 ሴቶች እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር። @AccessAddis
Show more ...
3 511
3
መስፍን ላለፉት ሁለት ወራት በኮቪድ ተይዞ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል የነበረ ሲሆን ካለፈው ሳምንት ወዲህ በፅኑ ህሙማን ክፍል ገብቶ ነበር። አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር። አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር። አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል። አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር። ዳሰሳ አዲስ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል! @AccessAddis
Show more ...
4 514
42
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲቀርቡ የነበሩት ድራማዎች ደራሲና ዳይሬክተር የነበረው መስፍን ጌታቸው ዛሬ ማምሻዉን ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፤ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ እና አድናቂዎች ልባዊ መጽናናትን ይመኛል! @AccessAddis
4 559
71
ዘመናዊ ቴአትር በኢትዮጵያ የተጀመረበት 100ኛ አመት ክብረ በዓል ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳ ፣የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተከብሯል ። በዝግጅቱ ላይ በቴአትር ያልተማረ የለም ያሉት ወ/ሮ አዳነች በቴአትር ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው ታሪክ ሰርተዋል፤መስራታቸውንም ይቀጥላሉ ብለዋል። በከተማዋ ያሉ ቴአትር ቤቶች ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው ተገቢው እድሳት ተደርጎላቸው ለአገልግሎት እንዲበቁ ከማድረግ ባለፈ እየተሰሩ ባሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ የአምፊ ቴአትር ቦታዎች እንዲካተቱ መደረጉን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል ። ኪነጥበብ ለሀገር ግንባታ ትልቅ ሚና አለው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ የቴአትር እና የኪነ ጥበብ ስራዎች በሚፈለገው መንገድ እንዲጎለብት የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። ማምሻውን በተካሄደው መርሐግብር ቴአትር በኢትዮጵያ የ100 ዓመት ጉዞን የሚዘክሩ ዝግጅቶች ቀርበዋል። @AccessAddis
Show more ...
6 859
4
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዚህ ወር ዳሰሳ አዲስ ኅትመት እና ማስታወቂስ መልካም የፆም ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ረመዳን ከሪም! @AccessAddis
5 332
0
ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ዶ/ር) በሙዚቃ፣ በድርሰት፣በትያትርና በሥዕል ሞያ ያገለገሉ አንጋፋ አርቲስቶችን ሸለሙ። "ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች" በሚል በስነጥበብ ዘርፍ ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመንግስት ደረጃ ሲዘጋጅ የመጀመርያ በሆነው በዚህ የእውቅና ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተገኝተዋል። ስነ ስርዓቱ በእንጦጦ ፖርክ የአንፊ ትያትር የስነ ጥበብ ማዕከል ነው እየተከናወነ የሚገኘው። በትያትር፣ በሙዚቃ፣ ፊልም ጥበብ፣ ስዕል እና ስነ ቅርስ ዘርፍ የረጅም አመታት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አንጋፋ ባለሙያዎች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ በተለያዩ የስነ ጥበብ ዘርፍ ሀገራቸውን እያገለገሉ የሚገኙ ታዋቂ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። @AccessAddis
Show more ...
5 543
9
ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ዶ/ር) በሙዚቃ፣ በድርሰት፣በትያትርና በሥዕል ሞያ ያገለገሉ አንጋፋ አርቲስቶችን ሸለሙ። "ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች" በሚል በስነጥበብ ዘርፍ ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዘርፉ ባለሙያዎች የእውቅና እና ሽልማት ስነ ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመንግስት ደረጃ ሲዘጋጅ የመጀመርያ በሆነው በዚህ የእውቅና ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተገኝተዋል። ስነ ስርዓቱ በእንጦጦ ፖርክ የአንፊ ትያትር የስነ ጥበብ ማዕከል ነው እየተከናወነ የሚገኘው። በትያትር፣ በሙዚቃ፣ ፊልም ጥበብ፣ ስዕል እና ስነ ቅርስ ዘርፍ የረጅም አመታት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አንጋፋ ባለሙያዎች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ በተለያዩ የስነ ጥበብ ዘርፍ ሀገራቸውን እያገለገሉ የሚገኙ ታዋቂ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። @AccessAddis
Show more ...
1
0
ለጥላሁን ገሰሰ ብቻ ከ200 በላይ ግጥም እና ዜማ የሰጠው ማዶሊን በብቸኝነት የሚያናግረው አየለ ሞሞ ብዙነሽ በቀለ፣ ማህሙድ አህመድ፣ውብሻው ስለሺ ፣መንበረ በየነ፣ ኩኩ ሰብስቤ፣ሕብስት ጥሩነህ፣ኤፍሬም ታምሩ፣ ሐመልማል አባተ፣ ብፅአት ስዩም፣ ወረታው ውበት፣ አስቴር ከበደ ፣ እያዩ ማንያዘዋል፣ ሻንበል በላይነህ፣ ደረጄ ደገፋው፣ ጌታቸው ጋዲሳ፣ ምንያህል ጥላሁን ገሰሰ፣ ትዕግስት ይልማ፣ ከበቡሽ ነጋሽ (ሚሚ)፣ ገነነ ኃይሌ፣ ፣ ሀብታሙ ገ/ፃዲቅ (ፈረንጁ) ፣ ሔለን በርሄ፣ አብነት ግርማ (ትንሹ ጥላሁን)… ለነዚህ ሁሉ ግጥም እና ዜማ የሰጡት ጋሽ አየለ ማሞ የስራቸውን ያህል ያልተነገራላቸው ወጣትን የሚያቀርቡ ድንቅ ባለሙያ ናቸው። ህብስት ጥሩነህ ኦሮምኛ ቋንቋ አትችልም አለማምደው የአፍ መፍቻው እስኪመስል ያዘፈኖት ጋሽ አየለ ናቸው እሷንም ከህዝብ ጋር ያስተዋወቋት ጭምር ጋሽ አየለ ዘፋኝን ማብቃት ጭምር የታደሉ ነበሩ ነፍስ ይማር @AccessAddis
Show more ...
4 769
8
የማንዶሊን ንጉሥ፤ አየለ ማሞ ከዚህ አለም በሞት ተለየ በህመም ምክያት አልጋ ይዞ የነበረው የማንዶሊን ንጉሥ፤ አየለ ማሞ በ 80 አመቱ ዛሬ ማረፉን ሰምተናል፡፡ አየለ ማሞ ለቁጥር ለሚታክቱ አርቲስቶች ነው የግጥምና ዜማ ሥራዎችን የሰጠው፡፡ ለጥላሁን ገሰሰ ብቻ ከ200 በላይ ግጥምና ዜማ ያቀበለ ነው፡- አየለ ማሞ፡፡ በ 1949 ዓም ክብርዘበኛ ሙዚቃ ክፍልን የተቀላቀለው አየለ ማሞ ድምፃዊ ብቻ አልነበረም ተወዛዋዥም ጭምር እንጂ፤ ከተወዛዋዥነትም አልፎ እስከ አሰልጣኝነት ዘልቋል፤ በርካታ ሙያተኞችንም አፍርቷል፡፡ አየለ፤ በያኔው አጠራር ሸዋ ክ/ሃገር ፍቼ ነው የተወለደው በልጅነቱ ነው ወደ አዲስ አበባ የመጣው ፤እንደመጣ ዲያቆን ነበር የሆነው፡፡ የሙዚቃ መሳሪያን በክቡር ዘበኛ የተማረው አየለ ማሞ ከሊድ ጊታር በኃላ ወደ ማንዶሊን ነበር የተሻገረው፡፡ ብዙነሽ በቀለ ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ ያቀነቀነችውን “አሸብርቆ ደምቆ እንደፀሐይ” የሚለውን ዘፈን ያቀበላት አየለ ነው፡፡ ከመሐሙድ አህሙድ ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኖች ውስጥ የአየለ ማሞ ስራዎች አሉ፡፡ ውብሻው ስለሺ ፣መንበረ በየነ፣ ኩኩ ሰብስቤ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሐመልማል አባተ፣ ብፅአት ስዩም፣ ወረታው ውበት፣ አስቴር ከበደ ፣ እያዩ ማንያዘዋል፣ ሻንበል በላይነህ፣ ደረጄ ደገፋው፣ ጌታቸው ጋዲሳ፣ ምንያህል ጥላሁን ገሰሰ፣ ትዕግስት ይልማ፣ ከበቡሽ ነጋሽ (ሚሚ)፣ ገነነ ኃይሌ፣ ፣ ሀብታሙ ገ/ፃዲቅ (ፈረንጁ) ፣ሕብስት ጥሩነህ፣ ሔለን በርሄ፣ ዳዊት ፅጌ….ወዘተ የአየለ ማሞን የግጥምና የዜማ ሥራዎች ተቋድሰዋል፡፡ ዳሰሳ አዲስ ለቤተሰቦቹና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ተመኘ! ነፍሱን በገነት ያኑር @AccessAddis
Show more ...
4 337
11
አርቲስት ሰለሞን ቦጋለና ጓደኞቹ ለሚገነቡት ሆስፒታል 60,000 ካሬ (6 ሄክታር) ሜትር ተበረከተ። በአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እና በጓደኞቹ የተመሰረተው "ኅብረት ለበጎ ማኅበር" ~ በኩላሊት ህመም የሚሰቃዩ ወገኖቻችን በቀላል ወጪ በሀገራቸው እንዲታከሙ ለማስቻል ግብ ያደረገ ነው። በዛሬው ዕለት ለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር 60,000 ካሬ ሜትር ለአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ እና ጓደኞቹ አስረክቧል። የሆስፒታሉም የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል። @AccessAddis
3 955
4
ታዋቂው ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ። አቤል ተስፋዬ በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በረሃብ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበረ በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል። ዘ ዊኬንድ አሁን ላይም በትግራይ ክልል የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የገለፀው በአሜሪካ የአለም ምግብ ፕሮግራም በድምፃዊው የተደረገው ድጋፍ ወሳኝ ነው ብሏል። ድጋፉ የአለም ምግብ ፕሮግራም በመጪው ስድስት ወራት የአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት እንደሚያግዝ ተጠቁሟል። ለተጨማሪ:- ይህን ይጫኑ @AccessAddis
5 334
12
ጋዜጠኛ እና ተዋናይ ብርሃኑ ድጋፌ በትላንትናው ዕለት ከመኪናው ውስጥ ተዘርፎ የነበሩ እቃዎችን ማግኘቱን አስታወቀ። በማህበራዊ ድረገፅ እና እቃውን እንዲገኝ ድጋፍ እና ትብብር ላረጉት አካላት ምስጋና አቅርቧል @AccessAddis
5 250
12
ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ተናገረ። በሸገር ኤፍ ኤም ራዲዬ ለዛ ራዲዮ ፕሮግራም እንዲሁም ለዛ ሽልማት አዘጋጅ በቅርቡም በኢቢኤስ ቴቪ ሲተላለፍ በነበረው የእግር እሳት በተሰኝው ተከታታይ ድራማ በመሪ ተዋናይነት በመሳተፍ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ በዛሬው እለት ዝርፊያ እንደተፈፀመበት በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። መገናኛ ወረዳ 6 ቦሌ ክፍለ ከተማው ህንጻ ጀርባ ባለው የውሃና ፍሳሽ ፅ/ቤት ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ አከባቢ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት እና ላፕቶፕ ጨምሮ ለዘመናት የሰበሰባቸው የስራ ፋይሎችንና የዘመናት የሬድዬ ፕሮግራ ፋይሎች ሙዚቃዎች ወደፊት የታቀዱ ስራዎችን የያዙ 10 ቴራ ባይት የሚገመት አራት ሃርድ ዲስኮች ሙዚቃ ማድመጫ ስፒከሮችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶች መኪናው ተከፍቶ ባልታወቁ ሰዎች እንደተዘረፋ ገልፃል። ከንብረቶቹ ምናልባትም በላይ እጅግ የሚፈልጋቸው ፋይሎች የዕድሜ ልክ ስብ ሰቦቼ እንዳሉበት በመግለፅ በማንኛውም መልኩ ንበረቶቹን የማግኘት እድል የገጠመው ሰው እንዲተባበሩት ጠይቋል። @AccessAddis
Show more ...
5 792
11
ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት ተናገረ። በሸገር ኤፍ ኤም ራዲዬ ለዛ ራዲዮ ፕሮግራም እንዲሁም ለዛ ሽልማት አዘጋጅ በቅርቡም በኢቢኤስ ቴቪ ሲተላለፍ በነበረው የእግር እሳት በተሰኝው ተከታታይ ድራማ በመሪ ተዋናይነት በመሳተፍ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ በዛሬው እለት ዝርፊያ እንደተፈፀመበት በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል። መገናኛ ወረዳ 6 ቦሌ ክፍለ ከተማው ህንጻ ጀርባ ባለው የውሃና ፍሳሽ ፅ/ቤት ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ አከባቢ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት እና ላፕቶፕ ጨምሮ ለዘመናት የሰበሰባቸው የስራ ፋይሎችንና የዘመናት የሬድዬ ፕሮግራ ፋይሎች ሙዚቃዎች ወደፊት የታቀዱ ስራዎችን የያዙ 10 ቴራ ባይት የሚገመት አራት ሃርድ ዲስኮች ሙዚቃ ማድመጫ ስፒከሮችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶች መኪናው ተከፍቶ ባልታወቁ ሰዎች እንደተዘረፋ ገልፃል። ከንብረቶቹ ምናልባትም በላይ እጅግ የሚፈልጋቸው ፋይሎች የዕድሜ ልክ ስብ ሰቦቼ እንዳሉበት በመግለፅ በማንኛውም መልኩ ንበረቶቹን የማግኘት እድል የገጠመው ሰው እንዲተባበሩት ጠይቋል። @AccessAddis
Show more ...
1
0
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
5 953
7
ኢትዮጵያ ውስጥ ቅዳሜ ዕለት በተካሄደው 'የጉማ' ሽልማት ላይ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት የሽልማቱ ሥነ ሥርዓቶች የተለዩ መነጋገሪያ ጉዳዮች ተከስተዋል። በተለይ ደግሞ ሽልማቱን ካሸነፉ የፊልም ባለሙያ ዎች መካከል አንዱ የነበረው ኢሳያስ ታደሰ በመድረኩ ላይ "እናቴ ደም ስታለቅስ፣. . . . በዚህ ሽልማት ልደሰት አልችልም" ሲል መናገሩና የታዳሚዎች አለባበስ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በሰባተኛው የጉማ ሽልማት ላይ በአጭር ፊልም ዘርፍ ታጭቶ የነበረው የኢሳያስ ታደሰ ቀብድ የተሰኘ ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏል። ኢሳያስ አሸናፊነቱ ተገልጾ ወደ መድረኩ ከወጣ በኋላ አጭር ንግግር በትግርኛ ቋንቋ አድርጓል። በቅድምያ "አመሰግናለሁ " ካለ በኋላ ". . .እናቴ የደም ዕምባ እያለቀሰች፣ ወንድሜ ተረሽኖ ከገደል አፋፍ ላይ እየተገፈተረ፣ ክብሯን የጠበቀች እህቴ በባለጌዎች እየተደፈረች በዚህ ሽልማት ልደሰት አልችልም።" "የእናቴ እንባ ሲታበስ፣ አገሬ ወደ ቀደመ ክብሯ ስትመለስ እደርስበታለሁ" ሲል ነበር የተናገረው። @AccessAddis
Show more ...
6 417
12
#ስፖርት_መዝናኛ ሚሊዮን ብሮች ለዋሊያዎቹ ዋልያዎቹ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ 90 ደቂቃ ብቻ ቀርቷቸዋል። ነገ ከአይቮሪኮስት ጋር አቢጃን ላይ በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7:00 በእኛ ደግሞ 10:00 ሰዓት ላይ ታላቁን ፍልሚያ ያደርጋሉ። የሚያሸንፉ ወይም አቻ የሚወጡ ከሆነ የማዳጋስካር እና ኒጀርን ውጤት ሳይጠብቁ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን የሚያረጋግጡ ይሆናል። ይህንን ህልማችንን የሚያሳኩ ከሆነ ደግሞ ከልማቱ ጎን ለጎን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎቻቸውና በለጋስነታቸው የሚታወቁት ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ ወርቁ አይተነው ለቡድኑ አባላት የ5,000,000 (የአምስት ሚሊዮን ብር) ለቡድኑ አባላት ለሽልማት መመደባቸውን ይፋ አድርገዋል። ዳሰሳ አዲስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መልካም እድል ይመኛል @AccessAddis
260
0
ትላንት ምሽት ለ7ኛ ጊዜ ጉማ የፊልም ሽልማት በስካይ ላይት ሆቴል የተካየደ ሲሆን ሽልማት አሸናፊ ፊልሞች ዝርዝር ምርጥ አጭር ፊልም ቀብድ፣ ምርጥ ሳውንድ ወጣት በ97 ፣ ምርጥ የፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ህዳር ፊልም፣ ምርጥ ስኮር ቁራኛዬ ፊልም፣ ምርጥ ሜካፕ ቁራኛዬ፣ ምርጥ ስክርፕት ቁራኛዬ፣ ምርጥ ኤዲትንግ (ቅንብር )እንሳሮ፣ ምርጥ ሲኒማቶግራፊ እንሳሮ፣ ምርጥ ተስፋ የተጣለባት ተዋናይት ሱማሌው ቫንዳም፣ ምርጥ ተስፋ የተጣለበት ወንድ ተዋናይ ቁራኛዬ ዘሪሁን ሙላት፣ ምርጥ ረዳት የሴት ተዋናይት እንሳሮ መስከረም አበራ፣ ምርጥ ረዳት ወንድ ተዋናይ ቁራኛዬ፣ ምርጥ ዋና ሴት ተዋናይት ወጣት በ97 ዘርቱ ከበደ፣ ምርጥ ዋና ወንድ ተዋናይ ሱማለው ቫንዳም ሄኖክ ወንድሙ፣ ምርጥ የበደሌ ስፔሻል የህዝብ ምርጫ ፊልም እንሳሮ፣ ምርጥ ዳይሬክተር ቁራኛዬ ፊልም፣ ምርጥ ፊልም ቁራኛዬ በዚህም መሰረት ቁራኛዬ 7 ፣እንሳሮ 4 ፣ወጣት በ97 እና ሱማሌው ሻንዳም ሁለት ሁለት እና ህዳር አንድ ሽልማቶችን ወስደዋል። @AccessAddis
Show more ...
5 522
14
አሊ አብደላ ካይፋ (ዓሊ ታንጎ) አረፉ:: ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ከ1960ዎቹ እስከ 1970ዎቹ መካተቻ በሸክላና ካሴት ሕትመትና ሥርጭት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያበረከቱት እና የቀድሞው ታንጎ ሙዚቃ ቤት ባለቤት የነበሩት የበርካታ ስመጥርና ወጣት ድምፃውያንን እንዲሁም የሙዚቀኞች ሥራዎች ለኅብረተሰቡ በማቅረብ የሚታወቁት አሊ አብደላ ካይፋ (ዓሊ ታንጎ) ዛሬ በህክምና ላይ በነበሩበት አሜሪካ ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል!! ታንጎ ሙዚቃ ቤት ካይፋ ሪከርድስ በተለይም ለወጣት ድምፃውያንና ለሌሎችም ዕውቅ ድምፃውያን ከ1973 ዓ.ም. እስከ 1977 ዓ.ም. ብቻ ከ53 የሚሆኑ የሙዚቃ ሥራዎችን አሳትሞ ለሕዝብ አቅርቧል፡፡ ዓሊ ታንጎ በሸክላ ያስቀረፃቸውን ሥራዎችና የኢትዮጵያን ሙዚቃዎች በመውደዱ ‹‹ኢትዮጲስ›› በሚል የዘፈን ስብሰብ በማዘጋጀት ለዓለም ያስተዋወቀው ፍራንሲስ ፋልሲቶ የዓሊን የሸክላ ኅትመቶች በኢትዮጲስ የ13ኛ ሲዲ ኅትመት ላይ ‹‹ወርቃማዎቹ 70ዎቹ›› ተብለው ተጠቅሰዋል፡፡ ከ77 ዓመታት በፊት በጅማ ከተማ ውስጥ ከየመናዊ አባታቸው ከኢትዮጵያዊ እናታቸው የተወለዱት ዓሊ አብደላ ካይፋ (አሊ ታንጎ) በዕድገታቸው ከትምህርቱ ጎን ለጎን የአባታቸውን የቡና ንግድ ያከናውኑ የነበረ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ችሎታቸውም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ለአምስት ዓመት ተጫውተዋል፡፡ @AccessAddis
Show more ...
5 099
14
Privacy Policy