cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማወቅ♻️

ማወቅ የሚጀምረው ራስን ከመሆን ነው!! ስለዚህ ማወቅ ከፈለክ መጀመርያ እራስክን ሁን!

Show more
EthiopiaThe language is not specifiedCryptocurrencies
Advertising posts
1 446Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ አባት የእጃቸው እና የእግራቸው ጣቶች አጥረው፣ማንቀሳቀስም ሆነ ምንም ስሜት ካጡ አመታት አልፏል፣አንደነገሩኝ ከሆነ የስጋ ደዌ (leprosy) እንደነበረባቸው እና መድሀኒቱን ወስደው እንደጨረሱ እና ለምን እጆቻቸው ወደነበረበት እንዳልተመለሰ የጠየቁኝን አስታውሳለሁ። የስጋ ደዌ በሽታ(Leprosy) ምንድን ነው? -የስጋ ደዌ በሽታ የምንለው ከተላላፊ በሽታዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ቆዳን፣የነርቭ ስርአትን፣አይንን፣የላይኛው የመተነፈሻ አካል፣መገጣጠሚያን፣የዘር ፍሬን የሚያጠቃ በተለይ በታዳጊ ሀገራት የሚስተዋል በሽታ ነው። -ይህ በሽታ ከጥንት በ600B.C ጀምሮ የነበረ ተብሎ ይታሰባል።ታሪክ እንደሚያሳየው አሁንም ድረስ ይህ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንደሚገለሉ ይስተዋላል። መንሰኤውስ? -የስጋ ደዌ በሽታ Mycobacterium leprae በሚባል ተህዋሲይ የሚመጣ በሽታ ነው። መተላለፊያውስ? -ይህ በሽታ መታከምና ሙሉ በሙሉ መዳን የሚችል ሲሆን ህመሙን በቶሎ መታከም ከአካል ጉዳታኛ መሆን ይከላከላል ። -መተላለፊያውም ከአፍና አፍንጫ በሚወጡ ጠብታዎች በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ ሲሆን በዚህም ምክንያት በበሽታው ከተጠቃና ህክምና ካላገኘ ሰው ጋር በሚደረግ ረዘም ላለ ጊዜ እና በተደጋጋሚ በሚኖር ንክኪ ይተላለፋል ። ምልክቶቹስ? -እንደ የአለም የጤና ድርጅት(WHO) አገላለፅ አነድ ሰው በስጋ ደዌ በሽታ ከተያዘ በዃላ ምልክት በአንድ አመት ውስጥ ሊያሳይ ይችላል።አንዳንዴም እሰከ 20 አመት ከዛም በላይ ቆይቶ ሊያሳይ ይችላል። -ነጣ ነጣ ወይም ቀላ ቀላ ያሉ የቆዳ ላይ ምልክቶች መጀመሪያ ላይ እና በብዛት የስጋ ደዌ ያለባቸው ሰዎች ላይ ይስተዋላል። -ፊት እና ጆሮ አካባቢ ህመም የሌለው እብጠት -ቆዳ ላይ የስሜት(sensation) መቀነስ ወይም ማጣት -እግር እና አጅ አካባቢ የመደንዘዝ እና የመጠዝጠዝ ስሜት -የአይን ቆብ ፀጉር መቀነስ -የአይን ሽፋሽፍት እና የጡነቻ መድከም -የቆዳ ማቃጠል፣የአፍንጫ መደፍጠጥ -ህመም የሌለው የእጅ ወይም የእግር ቁስል -የእጅ እና የእግር ኘርቭ ማበጥ(enlarged peripheral nerve)፣በቋሚነት የነርቭ መጎዳት ምርመራውስ? -የጤና ባለሙያው የታካሚውን ታሪክ እና አካላዊ ምርመራ ካደረገ በዃላ ለማረጋገጥ የቆዳ ምርመራ(skin smear ) ናሙና ተወስዶ በቤተሙከራ ውስጥ በሽታ አምጪው ተህዋሲው መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥ ይቻላል። የስጋ ደዌ መዘዞችስ? -የስጋ ደዌ በሽታ ካልታከመ አይነስውርነት፣የነርቭ መቆጣት እና መጎዳት፣የእጅ እና እግር ማጠር እና ሽባ መሆን(paralysis)፣ስነፈተ ወሲብ፣ልጅ ለመውለድ አለመቻል(infertility)፣የኩላሊት መድከም፣በማህበረሰቡ መገለል ይስተዋላል። ህክምናውስ? -የስጋ ደዌ በሽታ ሊያገረሽ የሚችል ነገር ግን ይህ በሽታ መዳን የሚችል ሲሆን ህመሙን በተሎ መታከም አካል ጉዳታኛነት እና ተየያዥ ችግሮችን ለመከላከል ይረዳል። -ከአንድ በላይ መድሀኒቶች(multidrug therapy) በማጣመር ከ6ወር አንዳንዴም ከአንድ አመት በላይ መታከም ሊጠበቅበት ይችላል።ይህም የሆነበት ምክንያት መድሀኒቱ ባክቴሪያው እንዳይላመድ(drug resistance) እንዳይኖር ያደረጋል። -ታካሚው በየወሩ ክትትል በማድረግ ከባለሙያ የሚሰጡ በቤት ውስጥ መደረግ ያለባቸውን ነገሮች መጠየቅ ፣አካላዊ ለውጦች እና በማለሙያው ስለ መድሀኒቶች አጠቃቀም እና የመድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ለምሳሌ ማሳከክ፣የምግብ ፍላጎት መመቀነስ፣ማቅለሽለሽ፣ሆድ ህመም፣የቆዳ መድረቅ፣እቅልፍ ማጣት፣የደም ማነስ፣የአይን እና የቆዳ ቢጫ መሆን ሊኖር እንደሚችል እና እነዚህ ነገሮች ሲኖሩ ለባለሙያው ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። -አነዴ የአካል ጉዳት ከተከሰተ በዃላ መድሀኒቱ የታካሚውን ሰውነት ወደነበረበት ይመልሳል ማለት አይደለም። -ማህበረሰባችንም ለእነዚህ ታማሚዎች ተገቢውን እንክብካባቤ ክብር መስጠት ይጠበቅበታል። ጤና ይብዛሎ! ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ @HakimEthio
Show all...
አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊወች በሙሉ ድግሪ ላላችሁ.....
Show all...
💪💯 በትናንቱ አትዳኘው! 💪💯 ለውጥን ከመንፈሱ ያቆራኘን ፣ ከውስጡ የጀመረን ፣ እራሱን አውቆ የመረጠን ፣ ከልቡ ለመለወጥ የወሰንን ፣ የቆረጠን ሰው ማንም አይያቆመውም ። ማናችንም ብንሆን መጥፎም ይሁን መልካም ፣ አኩሪም ሆነ አሳፋሪ ፣ አስመስጋኝ ሆነም አስኮናኝ የየራችን ታሪክ አለን ። ልኬታችን ግን ትናንት ሳይሆን ዛሬ ነው ፤ ቅድም ሳይሆን አሁን ነው ፤ ሃሳባችን ሳይሆን ተግባራችን ነው ። ሰዎች ይቀየራሉ ፣ ሰዎች ያድጋሉ ፣ የተለየ ማንነትን ይገነባሉ ፣ ከፍ ይላሉ ፣ አስቀድመው ከሚታወቁበት አስነዋሪ ተግባር ይላቀቃሉ ። ለውጣቸውም የሚታይ ነው ፣ እድገታቸውም የሚጨበጥ ነው ፣ ከፍታቸውም የሚነካ ነው ። ማንም በሰውነቱ የመቀየር አቅም አለውና ባለፈው ስህተቱና ጥፋቱ ፣ በቀድሞ ማንነቱ ሊተች ፣ ሊወቀስና ሊፈረድበት አይገባም ። ዛሬ ሌላ ሰው ሆኗል ፣ ዛሬ ከታሪኩ ተፋቷል ፣ እራሱን አድሷል ፣ ተሻሽሏል ። 💪💯 አዎ! ጀግናዬ..! ሰው ቁስ ሳይሆን አስተዋይ ህሊና ያለው ፣ የሚያመዛዝን ፣ እድገትን ፈልጎ የሚያገኝ ፣ ለውጥን አሳዶ መጨበት የሚችል ብርቱ ፍጥረት ነውና በትናንትቱ አትዳኘው ፣ በትናንቱ አትለካው ፤ አትፍረድበት ።  ትናንት ሌባ ቀማኝ ሊሆን ይችላል ዛሬ ግን ወገኑን የሚያግዝ በጎ ፍቃደኛ ሆኗል ፤ ትናንት ሱሰኛ ሴሰኛ ይሆናል ዛሬ ግን የሚፆም ፣ የሚፀልይ ፣ ዱዓ የሚያደርግ ሆኗል ። ትናንት ከሃዲ ፣ ሀገር አጥፊ ይሆናል ዛሬ ግን ለሀገሩ ክብር ቆሟል ። አንተ ጥሩ ነኝ ባልክበት ሰዓት ያልሰራሀውን በጎ ተግባር እርሱ ከተቀየረ ቦሃል ሰርቶታል ፤ አንተ ከእርሱ እሻላለው ባልክበት ሰዓት ያልጨረስከውን እቅድ እርሱ ፈፅሞታል ፤ አንተ አዋቂ ነኝ ባልክበት ጊዜ ያልፈታሀውን ችግር እርሱ በለውጥ መንገዱ ውስጥ ፈቶት መጥቷል ። 💪💯 አዎ! ብዙዎች ትናንታቸው ስላላማረ ተገልለዋል ፣ ጣት ተቀስሮባቸዋል ፤ ስማቸው ጠፍቷል ፤ ተሰደዋል ፤ ተሰቃይተዋል ። ነገር ግን ማንም ሰው ትናቱን አይደለም ፤ የትኛውም ሰው በታሪኩ አይወከልም ፣ አይለካም ። ትናንት የበደለ ሁሉ ዛሬም ይበድላል ማለት አይደለም ፣ ትናንት ያጣፋ ሁሉ እስከ ህይወት ፍፃሜው አጥፊ ነው ማለት አይደለም ። የሰው ልጅ ጠንካራ ነው ፤ የሰው ልጅ ብርቱ ነው ፤ ከስህተቱ መማር ይችላል ፣ ክፍተቱን መሙላ ይችላል ፣ ህይወቱን መቀየር ይችላል ። በቆራጥ ልቡ ከወሰነ ማንም አያቆመውም ፤ በእራሱ እስኪደነቅ ፣ ሰዎችን እስኪያስደንቅ መቀየር ፣ ማደግ ፣ መበልፀግ ይችላል ። ማንም አያቆመውም ፤ የትናነት ጠባሳው አያቆመውም ፤ መጥፎ ታሪኩ አይበግረውም ፤ የሰዎች ጥላቻ አያነቃንቀውም ። እናም ሌሎችንም ሆነ እራስህን ባለፈ ማንነት አትለካ ፣ በታሪክ ሚዛን አትመዝን ። በዛሬ ተግባርህ እራሰህን ለካ ፣ ለውጥህንም አፋጥን ። ═════════❁✿❁ ═════════ Join us 👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆  
Show all...
ብልህ ሰው በትናንሽ ነገሮች አይወሰንም ➪ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!"𑁍𑁍 በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖታልና አቅሙ አልፈቀደለትም፡፡ ሊረዳው የሚችለው ብቸኛ ልጁ ደሞ እስር ቤት ነው የሚገኘው፡፡ እናም አባት ለልጅ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈ፡፡ "ውዱ ልጄ ምንም ጥሩ ስሜት አሸየተሰማኝ አይደለም፤ ምክንያቱም የድንቹን ማሳ መቆፈር አልቻልኩም፡፡ አለመቆፈሬን አልወደድኩትም፤ ምክንያቱም እናተህ አትክልት በጣም ነበር የምትወደው፡፡ አንተ እስር ቤት ባትሆን አውቃለሁ ትቆፍርልኝ ነበር ፤ አባትህ" በቀጣዩ ቀን አባት አጠር ያለ ፁሁፍ ደረሳቸው፡፡ "በፈጣሪ ስም ይዤካለው አባ ጓሮውን እንዳትቆፍረው፤ ሽጉጡን የቀበርኩት እዚያ ነው" ከሰዓታት በኀላ በደርዘን የሚቆጠሩ የFBI መርማሪዎችና ፖሊሶች የሽማግሊውን ጓሮ በሙሉ በቁፋሮ ምስቅልቅሉን አወጡት፤ ነገር ግን ምንም ሽጉጥ እዛ አልነበረም፡፡ አባት በጣም ግራ በመጋባት አጠር አድርገው ለልጃቸው ምን እንደተፈጠረ እና ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፃፉለት፡፡ ልጅ "አሁን ድንችህን ትከል አባ፤ ከዚህ ሁኜ ላደርግልህ የምችለው ነገር ቢኖር ይህን ብቻ ነው" ብሎ ፃፈላቸው፡፡ ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ እኛን ሊወስነን አይገባም! Join us 👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆  
Show all...
የባከኑ ህልሞች መተኛት አልሻም ማለም እፈራለው ይሄን ያንን ሳስብ ሳልተኛ ነቃለው መናገር ያሰበው ለማይገባኝ ቅኔ ማለምን አልሻም ያንች ወዳጅ እኔ ከሁሉ ከሁሉ ፈራለው ምኝታ ህልም ብሎ እያሳየ ስለነሳኝ ፋታ ህልም ነው እያለ አንቺን ያሳይሻል በቢጫ ቀሚስሽ ስትበሪ ይስልሻል ፀጉርሽን ነስንሰሽ ስትስቂ ያመጣሻል ግን ልነካሽ ሳስብ መልሶ ያጠፋሻል እኔ አንችን ልነካ ሲቀረኝ በሳንቲ ሚሰውርሽ ከቶ ምን ሊያገኝ ነው እስቲ እናም ምኝታየን እፈራለው እኔ ህልም ብሎ እያሳየኝ የማልፈታው ቅኔ እሳቀቅ ጀመረ ቢያርቅሽ አቅርቦኝ ፍራሽም መቃብር እንቅልፍም ሞት መስሎኝ እናምልሽ ውዴ.... አሁን ላይ ሳስበው የፍራቴን ነገር ለካ አንቺን ማግኘቱ ይበልጥብኝ ነበር ሰሞኑን ስነሳ በሰላም ተኝቼ ይናፍቁኝ ጀመር የባከኑ ህልሞቼ። በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️ 👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆  
Show all...
የጉሽ ጠላን እና ያንቺን እምቡጥ ከንፈር ምን አገናኛቸው ? የቀመሱት ሁሉ  እኩል መስከራቸው? አዪ.... የጠላውስ ይሁን ጌሾ ነው ቅጠሉ በከንፈር አይከብድም ሰካራም መባሉ? . .   በሚኪያስ ፈይሳ 👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆  
Show all...
👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆
Show all...
📚For grade 11 and 12 students 📚And some freshman course pdf Check all pdf. they are useful all of them!! 👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆
Show all...
✍ቡሄ በሉ ቡሄ በሉ ፣ሰወች ሁሉ ደረሰልን ፣አመትበአሉ ተሰብሰቡ ፣ልጆችዬ እንጨፍር ፣ ሆያሆዬ በል ተነስ ህፃኑ ያንተ ነዉ ዘመኑ በል ተነስ ወጣቱ ደረሰልህ አመቱ በል ተነስ ፣ ጎረምሳዉ ልጅነትክን ፣ አትርሳዉ አታገኝም ፣ ይችን እለት፥ ሳትጠብቅ ፣ ድፍን አመት 'ሆያሆዬ ሆ ሆያሆዬ ሆ' እንበል አንድላይ ፣ ሰፈሩ ይድመቅ በደል ያለበት ፣ ሁሉም ይታረቅ ልብህን አንፃዉ ፣ ጥላቻው ይቅር ቂምን ስደደው ፣ ከዘመኑ ጋር በል ተነሳና ፣ አዋጣ ፍቅር ያለፈው አልፏል ፣ ቂምን እንሻረው እንሰባሰብ ፣ አመትበአል ነው አባት ይመርቅ ፣ ልጅ አሜን ይበል ቤታችን ይሙላ ፣ ፍቅር አይጉደል መጥፎው ይረሳ ፣ችግር ሀዘኑ ሁሉም ይጫወት ፣ ቡሄ ነዉ ቀኑ ✍KeyD እንኳን አደረሳችሁ !! 👇👇👇👇👇👇 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 ✅ @mawekb👈 👆👆👆👆👆👆
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!