cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃዎች መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Show more
Advertising posts
76 389Subscribers
No data24 hours
-1687 days
-75930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የለዛ አዋርድ የቀረበበት ቅሬታ እንዲሁም ከአዘጋጁ የተሰጠ መልስ በከተማችን ውስጥ ስለሚገኙ የሽልማት ዝግጅቶች ከጀርባ ብዙ የምንሰማቸው ነገሮች አሉ:: ከሰሞኑ ግን ግርም ያለኝ ክስተት አለ:: ለዛ አዋርድ ነው:: በሕግ አምላክ ድራማ በተለያዩ ዘርፎች የታጨ ሲሆን አንዱ በምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ምርጥ ተዋናይት ዘርፍ ፍሬዘር ሰለሞን ( ኤልዳ)  Frezer Solomon ታጭታ ለረጅም ሳምንታት በሁለተኛ ደረጃ በድምፅ እየመራች ነበር:: የውድድሩ አዘጋጆች ምንም ማብራሪያ ሳይሰጡ ከዛው ድራማ ላይ ሌላ ሰው ለዛውም መሪ ተዋናይት ያልሆነችን ባለሙያ በመተካት ፍሬዘር ሰለሞን ከውድድሩ አስወጥተዋታል:: በሁለተኛ ደረጃ ስትመራ የነበረችን ባለሙያ ለዛውም አንድ ጊዜ ተመርጣ ለህዝብ ይፋ ከተደረገ በኃላ ያለምንም ማብራሪያ ሰርዞ ከዛው ድራማ ያለምንም ማብራሪያና ገለፃ መተካት ምን የሚሉት አግባብ ነው ? መተካቷ በራሱ ችግር የለውም ሲተኩ ግን ለባለሙያው ክብር ማብራሪያ መስጠት ለሙያው እና ለባለሙያው ያላቸውን ክብር ሊያመላክት ይችል ነበር:: @Rafatoelworku *** የአዘጋጁ ምላሽ ስላም በጣም እናመሠግናለን ስለ አስተያየትና መልዕክቱ :: የሽልማት ስነ ሰርዓቱን  መመርያና ደንቦች በድረ ገጹ ላይ አስፍረናል :: ለእያንዳንዱ ጥያቄና ብዥታ ለማፅዳት በሚል :: እኛ ለየፊልሙ አዘጋጆች ሁለት፤ ሁለት ተዋንያን እንዲልኩ መልዕክት እንልካለን :: እነርሱ መርጠው የላኩት ደሞ የዳኞች ድምፅ እና የህዝብ ድምፅ ተዳብሎ ውጤቱ ይታወቃል። ይሄንን የሚያደርግ ክፍል አለን :: በህዝብ ድምፅ ቀዳሚ ቢኮንም የዳኞችስ መታየት አለበት :: ውድ አስተያየት ሰጪያቸን! በዚህ ጉዳይ ይመኑን ፍፁም በጥንቃቄ የሚከወንና ሁሉም ጥበበኛን በእኩል የሚያከብር ነው :: ምንም የተለየ ነገር የለም :: እነዚህም ሙያተኞች ከዚህ በዘለለ በመሰራታቸው ብቻም ቢሆን ክብር ይገባቸዋል :: እርስዎንም እናመሠግናለን ስለ ሽልማቱ ያገባኛል በማለትዎ ። (ብርሃኑ ድጋፌ - Berhanu Digaffe ) @Addis_News
Show all...
👍 23😐 3
ኬፕ ታውን ኤርፖርት የአፍሪካ ምርጥ አየር ማረፊያ ተብሎ ሲሰየም ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን የሚገኘው አየር ማረፊያ በደንበኞች ደረጃ አሰጣጥ ድርጅት ስካይትራክስ ባደረገው ጥናት የአህጉሪቱ ምርጥ አየር ማረፊያ ተብሎ ተሰይሟል።በአለም አቀፍ ደረጃ ኬፕ ታውን 54ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዝርዝሩ ላይ ያለው ቦታ አየር ማረፊያዉ የቀነሰበት ሲሆን በ 2020 23 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ በአህጉራዊ ዝርዝሩ ውስጥ ሌሎች ሁለት የደቡብ አፍሪካ አየር ማረፊያዎች ደርባን እና ጆሃንስበርግ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ተቀምጠዋል።በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የሚገኘው ቦሌ አየር ማረፊያ ከአፍሪካ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ የናይሮቢው ጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 10ኛ ደረጃን አግኝቷል።በሌላ በኩል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ጎረቤት ሀገራት እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ በዱባይ አየር ማረፊያ ስራው በእጅጉ አስተጓጉሏል፡፡አውሎ ነፋሱ ማክሰኞ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን በመምታቱ መንገዶችን እና  የአለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ክፍሎች በጎርፍ ተይዘዋል፡፡ድንገተኛ የጎርፍ አደጋዉ በኦማን 20 ሰዎችን እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ደግሞ የአንድ ሰው ህይወት ነጥቋል፡፡ አንዳንድ በረራዎች ሐሙስ እለት ቢደረጉም የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዋና የጉዞ ማዕከል ቢሆንም እምብዛም አገልግሎት እየሰጠ አይደለም፡፡የዓለማችን ሁለተኛዉ አውሮፕላን ማረፊያ ባለስልጣናት ሐሙስ እለት እንደተናገሩት በውጭ አገር አጓጓዦች በሚጠቀሙበት ተርሚናል 1 ወደ ውስጥ የሚደረጉ በረራዎችን መቀበል መጀመራቸውን፣ ነገር ግን ወደ ውጭ የሚደረጉ በረራዎች መጓተታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ተደምጠዋል።የዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ኃላፊ ፖል ግሪፊስ "አሁን በጣም ፈታኝ ጊዜ ነው፤ በህይወቱ ማንም ሰው እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን አይቶ አያውቅም" ብለዋል፡፡አየር ማረፊያው ለመድረስ በሚሞክሩ ሰዎች መጨናነቅ ምክንያት በዙሪያው ያሉት መንገዶች ተዘጋግተዋል።ረቡዕ እለት ብቻ ወደ 300 የሚጠጉ በረራዎች ሲሰረዙ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘግይተዋል ። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በታሪክ ከፍተኛውን የዝናብ መጠን ተመዝግቦባታል፡፡የመንግስት የዜና ወኪል የዝናብ መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ከ1949 ዓመት ጀምሮ ከተመዘገቡት ሁሉ የበለጠ ታሪካዊ የአየር ሁኔታ ክስተት ሲል ጠርቶታል። @Addis_News
Show all...
👍 14🤔 5
ኔስትሊ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት በሚልካቸው የወተት ምርቶቹ ላይ ስኳር እንደሚጨምር ተሰማ! የስዊዘርላንዱ የምግብና መጠጥ አምራች ኩባንያ ኔስትሊ ወደ አፍሪካ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚልካቸው የጨቅላ ህጻናት ወተት እና ሌሎች ምርቶቹ ላይ ስኳር እና ማር እንደሚጨምር "ፐብሊክ አይ" የተሰኘ ስዊዘርላንድ ውስጥ የሚገኝ የምርመራ ትቋም አጋልጧል። ቡድኑ ከላይ ወደተጠቀሱት ክፍለ አህጉራት የሚላኩ የኒዶ(Nido) እና ሴሪላክ(Cerelac) ምርቶችን ቤልጄም ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከው ያስመረመሩ ሲሆን በውስጡ በአለም የጤና ድርጅት መመሪያ መሰረት አለቅጥ መወፈርን እና ተያያዝ በሽታዎችን ለመከላከል ለጨቅላ ህጻናት የተከለከለ የስኳር መጠንን ይዞ መገኘቱ ተዘግቧል። በአንጻሩ ኩባንያው ለአውሮፓ ደምበኞቹ የሚልከው ስኳር የሌለበት እንደሆነ የዘ ጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል። ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ በሴሪላክ ምርት ላይ የሚጨመረው ስኳር መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።የመረጃው ይፋ መሆንን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎች የተቹት ሲሆን እስካሁን ኩባንያው ያለው ነገር የለም። @Addis_News
Show all...
👍 15😐 3
በካቴድራሉ ዙሪያ ያሉት ህንፃዎች ንብረትነታቸው የቤተክርስቲያኗ አይደለም ያለዉ አስተዳዳሪዉ በዚህ ምክንያት ለእድሳቱ አስፈላጊውን ገንዘብ እንዳይገኝ ማድረጉን ገለፀ ከ 90  ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ታሪካዊና አለም አቀፋዊ ካቴድራል የሆነዉ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የህንፃ እድሳት ሲጀመር የነበረዉ የገንዘብ መጠን 500 ሺህ ብር ገደማ መሆኑን የገለፀው የቤተክርስቲያኗ አስተዳደር የካቴድራሉ የገቢ ምንጭ ከሌሎች ገዳማትና አድባራት ሲነፃፀር እጅግ ያነሰ መሆኑን አስታዉቋል። ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን የህንፃ እድሳት ሲጀመር የነበረዉ ተቀማጭ ገንዘብ 500 ሺህ ብር ብቻ መሆኑን ያስታወቀዉ አስተዳደሩ ለዚህም በሰዎች ዘንድ ያለዉ የተሳሳተ ግምትና ይህን ለመረዳት ፍቃደኝነት አለማሳየታቸው እንደሆነ ገልጿል። የገቢ ምንጩ አነስተኛ እንዲሆን አድርገዉታል ካላቸዉ ምክንያቶች መካከል በካቴድራሉ ዙሪያ የነበሩ ነዋሪዎች በልማት ምክንያት መነሳታቸው እንዲሁም አብዛኞቹ ሰዎች በካቴድራሉ ዙሪያ ያሉ ህንፃዎች  የካቴደራሉ ንብረት እንደሆነ በማሰባቸው ምክንያት ለእድሳቱ የገንዘብ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ አድርጎታል ብለዋል። የቤተ ክስርስቲያኗ አስተዳዳሪ ሊቀ ስልጣን ቆሞስ አባ ሲራክ አድማሱ እንደገለጹት የካቴደራሉ እድሳት ከተጀመረ አንድ ዓመት ከግማሽ ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን መጋቢት 30 ቀን 2016 እንደሚጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ለሦስት ወራት እንዲራዘም መደረጉን አስረድተዋል ። የህንፃ እድሳቱ እስካሁን 65 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ለፕሮጀክቱ 90 ሚሊዮን ብር ገደማ በተለያዩ መንገዶች ማሰባሰብ እንደተቻለ ካፒታል ከመግለጫው ተከታትሏል ። በኢትዮጵያ የፓትሪያርክ ሹመት የሚፈጸምበቱ በቸኛ ስፍራ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በ1924 ከተመሰረተ ጀምሮ ከ90 ዓመታት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። Via:Capital @Addis_News
Show all...
👍 35💯 1
ከአላማጣ እና ከሌሎች የራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች፤ በቆቦ ኢንዱስትሪ መንደር እንዲጠለሉ መደረጋቸው ተነገረ በአማራ እና የትግራይ ክልሎች “የወሰን ይገባኛል” ጥያቄዎች ከሚነሱባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የራያ አካባቢ ባለፉት ቀናት ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ወቅት ከቆቦ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ የኢንዱስትሪ መንደር በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል። በአወዛጋቢዎቹ የራያ አካባቢዎች ውጊያ የተቀሰቀሰው፤ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በማይጨው እና መኾኒ ከተማዎች ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከሰላማዊ ሰልፎቹ  በኋላ በሪ ተኽላይ እና ገርጃለ በተባሉ አካባቢዎች፤ በትግራይ ኃይሎች እና በአማራ ክልል ታጣቂዎች መካከል “ከባድ የተኩስ ልውውጥ” ሲደረግ እንደነበር እማኞቹ አስረድተዋል። የአላማጣ ከተማ ከሰኞ አመሻሽ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥጥር ስር ከገባ በኋላ በከተማይቱ መረጋጋት መታየቱን “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የአላማጣ ነዋሪዎች አመልክተዋል። በትላንትናው እና በዛሬው ዕለት መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ቢቀጥልም፤ የህዝብ አገልግሎት ሰጪዎች እና ተቋማት ግን አሁንም ዝግ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።  የመንግስት ሰራተኞች በጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ስራ ገበታ ለመመለስ መቸገራቸውን እና የተወሰኑትም ከተማይቱን ለቅቀው መሄዳቸውን ነዋሪዎቹ አክለዋል። በአላማጣ ከተማ የነበሩ የስራ ኃላፊዎች፤ ከትላንት በስቲያ ከሰዓት በአጎራባች ወደምትገኘው ቆቦ ከተማ መግባታቸውን የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃይሉ አበራ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።  Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር @Addis_News
Show all...
👍 18🕊 2
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አድርጋለች? የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ፣ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስለተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እና ሌሎቹም ተጠቃሽ ናቸው። አቶ ነብዩ እንዳሉት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በድንበር አካባቢ ያሉ ማህበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መንገድ በሁለቱ ሀገራት በሚዋቀር ኮሚቴ ይፈታል ብለዋል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል ማለቱ አይዘነጋም። የኤርትራ ጦር በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን እንደተቆጣጠር እና አካባቢዎቹን ወደ ኤርትራ ማካለሉን እንዴት ኢትዮጵያ እንዴት ታየዋለች? በሚል ለቃል አቀባዩ ለቀረበላቸው ጥያቄም "ጥያቄው ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አህመድ ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የማህበረሰብ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደተነሳ እና ጉዳዩ በውይይት ይፈታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፣ አሁንም ማለት የምችለው ይህንን ነው" ብለዋል። ከአራት ወር በፊት በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተካሄደው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ጉዳይ ሌላኛው በዛሬው መግለጫ የተነሳ ጉዳይ ሲሆን ኢትዮጵያ ከሶማሊያ እና ሌሎች ሀገራት ባደረሱት ጫና ምክንያት የአቋም ለውጥ ወይም ሌላ አዲስ ነገር ይኖር ይሆን? በሚል ጥያቄ ተነስቷል። ቃል አቀባዩ በሰጡት ምላሽም " ከሶማሊላንድ ጋር በተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት ዙሪያ የተቀየረ አቋም የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔት የሚኖሩ 70 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ የተጀመረው ጥረት እንደቀጠለ ነው የተባለ ሲሆን በሳምንት 12 በረራዎች እየተደረጉ እንደሆነም ተገልጿል። ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብን ለመቀላቀል የጀመረችው ድርድር በጥሩ መልኩ እየሄደ ነው የተባለ ሲሆን በተለይም ምርቶችን በመሸጥ ዙሪያ ጥሩ መሻሻል ሲያሳይ በቀጣይ ደግሞ በንግድ አገልግሎቶች ዙሪያ ተጨማሪ ድርድር እንደሚደረግ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ከ24 ዓመት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማሳለጥ የተቋቋመው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጥምረት በየጊዜው አዳዲስ አባላትን በመሳብ ላይ ይገኛል። ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከአንድ ዓመት በፊት ይህን ጥምረት ለመቀላቀል በይፋ ከጠየቀች በኋላ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ጀምሮ ስምነኛዋ አባል ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ የ300 ሚሊዮን ህዝብ መገበያያ መድረክ ሲሆን ኢትዮጵያ አባል ከሆነች የአባል ሀገራቱን ቁጥር ወደ ዘጠኝ የግብይት መጠኑንም ከ400 ሚሊዮን በላይ በማድረስ በአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኢኮኖሚ ትስስር ወደ መሆን ይሸጋገራል ተብላል። በድርቅ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን አንድ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለማሰባሰብ በስዊዘርላንድ ጀኔቭ በተካሄደው እርዳታ ላይ የታሰበውን ያህል ገንዘብ መሰብሰብ እንዳልተቻለም ተገልጿል። በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የታሰበውን ያህል ገንዘብ ማግኘት ያልተቻለው አፍሪካን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች በተመሳሳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች እና ተቋማት በመኖራቸው እንደሆነ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። Via:አል ዓይን @Addis_News
Show all...
👍 18💯 2
የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ በ8 ክልሎች የሚገኙ ከ41 ሺህ በላይ ዜጎችን ማጥቃቱን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡ ከፍተኛ ረሃብ እና በሽታ የብዙ ኢትጵያዊያንን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል፡፡የትግራይ፣ አማራ፣ አፋር፣ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች በኢትዮጵያ በተከሰተዉ ጦርነት ምክንያት ከባድ ቀዉስን ያስተናገዱ ናቸዉ፡፡ በእነዚህ ክልሎችም የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እና መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ አልያም በከፊል መዉደማቸዉንም ነዉ ድርጅቱ የገለጸዉ፡፡በኢትዮጵያ 20ኛወሩን ያስቆጠረዉ የኮሌራ ወረርሺኝ 41ሺህ ዜጎችን ያጠቃ እና በ8ወረዳዎች የተከሰተ መሆኑንም ድርጅቱ አስታዉቋል፡፡ የአሁኑ የኮሌራ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛዉ መሆኑን ነዉ ዶ/ር ቴዎድሮስ የተናገሩት፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በወባ ወረርሺኝ 1.1 ሚሊየን ዜጎች መያዛቸዉን አንስተዉ ፤ ባለፈዉ ዓመት ከተመዘገበዉ 4 ሚሊየን ቁጥር አሁን ላይ መቀነሱን ነዉ ያስታወቁት፡፡ በዚህኛዉ ዓመት ብቻ ከ1መቶ በላይ በሚሆኑ አከባቢዎች ከ15ሺህ በላይ ሰዎች በኩፍኝ ወረርሺኝ መያዛቸዉንም አንስተዋል፡፡እነዚህ ችግሮች እየተከሰቱ ያሉት ሚሊየኖች መሰረታዊ የሆነ የህክምና አገልግሎት በሚፈልጉባቸዉ ቦታዎች መሆኑንም ነዉ የገለጹት፡፡ @Addis_News
Show all...
👍 9🤔 1🕊 1
ዘንድሮም የሠራተኞች ቀን በአደባባይ አይከበርም ተባለ  በየዓመቱ ሚያዚያ 23 ቀን ሠራተኞች ጥያቄዎቻቸውን እና ብሶታቸውን በአደባባይ የሚያሰሙበትና የሚያከብሩት ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን (ሜይዴይ) ለሁለተኛ ጊዜ በአደባባይ እንደማይከበር የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ። የዘንድሮ አከባበርን በተመለከተ ኢሠማኮ ከኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውም ታውቋል። በዚህም በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በዓለም ደረጃ ደግሞ ለ135ኛ ጊዜ የፊታችን ሚያዝያ 23 ቀን 2016 የሚከበረው በዓል "የአገሪቱን አጠቃላይ ሁኔታ በማገናዘብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ያሉ ከባቢዎችንም ከግምት በመክተት እንደ ባሕር ዳር፣ ኮምቦልቻና ፊንፊኔ ዙሪያ ካሉት ውጪ" በአዳራሽ ውስጥ ለማክበር ተወስኗል ተብሏል። ባለፈው ዓመትይ 48ኛው የሠራተኞች ቀን በዓልን ኢሠማኮ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንዲሁም በክልሎች በሰላማዊ ሰልፍ ለማክበር ቢያቅድም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ቢሮ መከልከሉ አይዘነጋም። ዘንድሮ በአዳራሽ ይከበራል በተባለው ዝግጅት በሠራተኛው በኩል ምላሽ ለሚነሱ ጥያቄዎች የመንግሥት ተወካዮች ምላሽ እንደሚሰጡ ኮንፌዴሬሽኑ ገልጿል። እንዲሁም የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ የኢሰማኮ ጠቅላይ ምክር ቤት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመገናኘት የሚጠይቅ ደብዳቤ መጻፉንና ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑ ተጠቁመዋል። በአንጻሩ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አመራሮች ነሐሴ 24 ቀን 2015 ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ጋር ባደረጉት ውይይት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል፣ የደመወዝ ግብር ቅነሳ እንዲሁም ለዓመታት የተቋረጠው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ሥራ እንዲጀምር ተጠይቀው ነበር። Via:አዲስ ማለዳ @Addis_News
Show all...
👍 14🤔 5
#UPDATE ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ፡፡ የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ አቅርቧል። በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል፡፡ ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል። @Addis_News
Show all...
👍 30🤔 3
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት፣ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት ጥያቄ አቅርቤያለሁ ማለቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ምክር ቤቱ፣ ዐቢይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቅሶ፣ ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋር ጭምር እንዲወያዩ ጥያቄ እንዳቀረበ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። ምክር ቤቱ ይህንኑ ጥያቄውን ከሦስት ሳምንት በፊት ለጠቅላይ ሚንስቴር ጽሕፈት ቤት ማስገባቱንና እስካኹን ምላሽ እየተጠባበቀ እንደኾነ ተናግሯል ተብሏል። ምክር ቤቱ ለውይይት ካነሳቸው አጀንዳዎች መካከል፣ የጋዜጠኞች እሥርና እንግልትና የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የገጠሟቸው ችግሮች እንደሚገኙበት መጥቀሱንም ዜና ምንጩ አመልክቷል። ዐቢይ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች ጋር ተወያይተው አያውቁም። @Addis_News
Show all...
👍 14